Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.4K subscribers
2.98K photos
372 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
ድል አድራጊነትን ከአባቶቻችን የወረስነው የአሸናፊነት ፀጋችን ነው!
የፍየሎች ምላስ የአንበሳውን መንጋ ከተኛበት ቀስቅሰውታል‼️
ወያኔ ለአማራም ሆነ ለኢትዮጵያ ከአፋር ክልልና በአማራ ክልል በአድርቃይ ማይጠብሪ በተከዜ ግንባር ካልሆነ በስተቀር በሌሎቹ የአማራ ክልል ግንባሮች በጀግኖቻችን የተባበረ ክንድ ተቀጥቅጦ ተጠራርጓል። ይሁን እንጅ ይህ አሸባሪ ቡድን ለኢትዮጵያ ሕልውና ስጋት በማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ነን እንጅ ገና አላደረስነውምና መዘናጋት አያስፈልግም። ጦርነቱ ያለቀ አዲስ አበባን ከብቤ ልገባ ጫፍ ላይ ደርሼ የነበረ ቢሆንም ለሰላም ካለኝ ትልቅ ቦታ የተነሳ ያለ ውጊያ አፋርንና አማራ ክልልን ለቅቄ ወጥቻለሁ በማለት የተለመደ ቅጥፈቱን እየለፈለፈ ቢገኝም ከአፍቃሬ ወያኔዎች በስተቀር የዚህን ነጭ ውሸት ልፈፋ ሊቀበል የሚችል ሰው የሚኖር አይመስለኝም።
ምንም ሳይዋጋ ለሰላም ብሎ በአሸናፊነት ከፍታ በሙሉ አቅም ላይ ሆኖ የለቀቀ ከሆነ ስለምንድነው ለአለማቀፉ ማህበረሰብ መንግስታት እባካችሁ ከአብይ ጋር ለማደራደር በምትችሉት የጫና መንገድ የፈጥናችሁ ድረሱልኝ ኡኡታ ጩኸትን የሚያቀልጠው ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል።

የዚህ አሸባሪ ቡድን አስገራሚው ነገር ለበርካታ መንግስታት በከፍተኛ ተማፅዕኖ እንዲደርሱለት እግራቸው ስር የተነጠፈና እየተነጠፈ ያለ አይመስልም፤ ለኢትዮጵያዊያን የሚያሰማውን ፉከራና ድንፋታ ለተመለከተ።
ድርድርንም አስመልክቶ የተቆርቋሪነት ጭምብል በለበሱ በአፍቃሬ ወያኔዎች መሪነት በኩል መንግስት ከወያኔ ጋር እንዴት ይደራደራል እንዲሉ አስደርጎ በአሸናፊነት መንፈስ ሆኖ ለድርድር የሚለመን አስመስሎ ነጥብ ለማስቆጠር ይንተፋተፋል። ተቀጥቅጦ ስጋት ላይ መውደቁን ኢትዮጵያዊያን እንዳያዉቁበት የሚሄድበት ርቀት መሸነፉን ለመሸፈን የሚጠቀመው ቴክኒክ አስገራሚ ነው።

የሆነው ሆኖ ወያኔ ሙሉ በሙሉ ወደታሪክነት እስካልተቀየረ ድረስ በፍጹም መዘናጋት አያስፈልግም‼️
ወያኔ በአለማቀፉ ማህበረሰብ ጫናና ጣልቃ ገብነት ወይም በድርድር ሕልውናው የመቀጠል ዕድል ይኑረውም አይኑረውም በእብሪት ወይም ሰላም ፈላጊ በመምሰል በማዘናጋት በወልቃይት/በሱዳን ኮሪደር በኩል ከሁሉም ግንባሮች ተቀጥቅጦ የተንጠባጠበውን ታጣቂውን በማሰባሰብ ከውጭ በኩል በሱዳን ካለው በነፃ አውጭ ስም ከሚንቀሳቀሱት ሃይሎችና ከሱዳን ጦር ጋር በመቀናጀት በአዲስ መልክ የመጨረሻ የሚለውን የማጥቃት ሙከራ ማድረጉና በጀግኖች ኢትዮጵያዊያን የተባበረ ክንድ የመጨረሻ ሞቱን ወልቃይት ላይ መሆኑ የማይቀር ጉዳይ ስለመሆኑ የሚያረጋግጡ ምልክቶች መሬት ላይ ያሉ እንቅስቃሴዎች በርካታ ናቸው።

በሁሉም ግንባሮች በከፍተኛ መስዋዕትነት ባስመዘገብነው አንፀባራቂ ድሎች ደስታችንን መግለፅ ተገቢ ቢሆንም የጦርነቱን ዋንጫ በድል አንስተን ያልሳምን መሆናችን ብቻ ሳይሆን ድል አድርገን ነፃ ያላወጣናቸው አካባቢዎች ከውጭ በኩል ያለው ጫናና የታሪካዊ ጠላቶቻችን ቀጥተኛ ወታደራዊ የማጥቃት እንቅስቃሴና በነፃ አውጭ ስም አሰልጥነው ያደራጇቸው ሃይሎች ዝግጅት ከውስጥ ባንዳዎች ጋር ያልቀዘቀዘ የተቀናጀው ጥቃት የመክፈት የጥፋት አላማ እንቅስቃሴ የስጋት ድባብ ኢትዮጵያዊያን ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደብረት የጠነከረውን አንድነታቸውን የማይንበረከከውን የፅናትና የአሸናፊነት መንፈሳቸውን ግለቱ ተጠብቆ እንዲቀጥል በንቃት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ የሚያሳይ መረጃዎች እልፍ ናቸውና ደስታችን በተገኘው የአውደ ውጊያ ድል ልክ እንጅ ጦርነቱን እንዳሸነፈ አካል እንዳንዘናጋ በጥንቃቄ መስራት ይጠበቅብናል።
በሑመራ በኩል ያለውን ሁኔታ ገምግመን አዲስ አበባ ለስራ ጉዳይ ተከስተናል።አሁንም በአዲስ አበባ የብዙሃኑ ሰው ትኩረት በግንባር ስለነበረውና ስላለው ሁኔታ ነው። ለወገን ጦር ያለው የጋለ የድጋፍ ስሜት እጅጉን የሚያስደስትና ሕወሓት ለኢትዮጵያ ስጋት እስከማይሆን ደረጃ ድረስ በደራሽ አጀንዳ ሳይጠመድ በሚችለው ነገር ሁሉ ከጀግናው የወገን ጦር ጎን እስከመጨረሻው በፅናት በመቆም ድጋፉን ለመስጠት የቆረጠው እልፍ ነው።

አማራን አንገት ለማስደፋት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ደመኛ ዘላለማዊ ጠላት ትህነግና ግብረ-አበሮቹ ተባብረው በተነሱብን የማይነጋ በመሰለው ጨለማ" እኛ የእነዛ ሀገር የገነቡ አኩሪ ታሪክ ሰሪ አይበገሬ አባቶቻችን ልጆች ነንና አዲስ ታሪክ መስራት ባንችል አባቶቻችን በደማቸው ነፃነቷን አስከብረው ያኖሯትን ሐገር በማንም የመንደር ወፍ ዘራሽ የባንዳ ስብስብ አናስደፍረም" በማለት የወገንን ጦር በገንዘባቸው በመደገፍ የጠላትን የሐሰት የፈጠራ ፕሮፖጋንዳን እውነትን በመግለጥ በሐሳብም በመሞገት ብዥታን ያጠሩ የወገንን ስነልቦና የገነቡ ከጀግናው የፀጥታ ጥምር ሃይላችን ጎን እስከዛሬዋ ቀን ድረስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ከተረባረቡት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች መካከል አንዱ ከሆኑት ከ ከንባታው ተወላጅ ኢ/ር ጌታሁን ሄራሞ ጋር ገንቢ ጊዜን አሳልፌያለሁ።

ኢንጅነር ጌታሁን በሀበሻ ጀብዱ ላይ ታሪካቸው በጉልህ እንደተቀመጡት በደጅ አዝማች መንገሻ ሂልማና የሚመሩት የከንባታ አርበኞች አይነት አገር ወዳድነት እና ለጨቋኞች እጅ የማይሠጥ መንፈሥ የተላበሠ ወንድም ነው።

ማህፀነ ለምለሟ ኢትዮጵያ ዛሬም ልክ እንደትናንቱ የገጠሟትን ፈተናዎች በልጆቿ የተባበረ ክንድ በአንፀባራቂ ድሎች ትሻገራለች‼️
ኢትዮጵያን ከመፍረስ ለመታደግ መከላከያ ሰራዊትን መታደግ ይቀድም ነበር። መከላከያ ሰራዊት ሳይፈርስ አገር ሊፈርስ እንደማይችል ጠንቅቆ የሚያውቀው ወያኔና ከእሱ አጀንዳ እየተቀበለና እየተቀለበ የሚንቀሳቀሰው በግጭት ላይ የተመሰረተ ሕልውና ያለው የደም ነጋዴው የአማርኛው ክንፍ ጉዳይ ፈፃሚ መከላከያን ከሕዝብ ነጥሎ ደጀን በማሳጣት ከቻለም ሕዝብ እንዲክደውና እንዲነሳበት በሌላ በኩል ደግሞ መከላከያ ወደሕዝቡ እንዲተኩስ ለማድረግ "ሴራ አለ በሚል ሴራ!" መከላከያ ርስ በራሱ በጥርጣሬ እንዲተያይና እንዲከፋፈል የተጠና ከፍተኛ የሆነ የስም ማጥፋት ዘመቻና ከፋፋይ አጀንዳ በተቆርቋሪነት ስም በማሰራጨትና በመሸጥ መከላከያን በማፍረስ አገር ለማፍረስ ያልተፈነቀለ ድንጋይ፥ ያልተወጣ ተራራ፥ ያልተወረደ ቆልቁለት፥ ያልተሳበ ካርድ፥ ያለስሙ ስም ተሰጥቶት ያልተሰደበ፥ ወያኔ-ጠል የአማራና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ እውነተኛ ተቆርቋሪ ያልነበረና ከሜዳው ለማስወጣት ያልተሞከረ ጥረት የሌለ ቢሆንም ነገር ግን የጠላት አጀንዳ አቧራ ከማስነሳት ያለፈ ሚና እንዳይኖረው ጠላትን በእልፍ ማይል አልፎ በመቅደም መሰራት ያለበትን ስራ በተባበረ የኢትዮጵያዊያን ክንድ መሬት ላይ መሬት እንዲነካ መሰራት በመቻሉ ምክንያት የታለመውና የታቀደው የወያኔ መከላከያን በማፍረስ አማራን አንገት ለማስደፋት ኢትዮጵያን የማፍረስ በአደባባይ የታወጀን የጥፋት ግልጽ አላማን በብቃት ማክሸፍ ተችሏል። የጥፋት ስውር እጆችን እንዲታወቁና እርቃናቸውን እንዲቀሩ ሆኗል። መከላከያን ማዳን ኢትዮጵያን ማዳን መሆኑን እውነቱንና ውጤቱን መሬት ላይ መመልከትም ችለናል።

ደመኛ ዘላለማዊ የኢትዮጵያ ጠላት ወያኔ መከላከያን ለማፍረስ ከሕዝብ የመነጠል በሴራ አለ የሴራ ትንተና(ትብተባ) የጠላት ሴራን ቀዳሚ የጥፋት አላማን ቀድመን ያለማሰልቸት ፍትህ ነፃነትና እኩልነትን መሰረት አድርገን ለሕዝባችን እውነትን መግለጥ መቻላችን ሕዝባችን ለመከላከያ ሃይላችን ደጀንነቱን በሰው ሃይል (ልጆቹን መርቆ በመስጠት)፥ በገንዘቡ የተሻለ የቴክኖሎጅ የዘመናዊ ትጥቅ ተጠቃሚ እንዲሆን ፥ በቁሳቁስ ድጋፍ፥ ሞራል በመስጠት በአሸናፊነት ስሜት እንዲራመድ በስነ-ልቦና ይጠናከር ዘንድ በግንባር ከተደረገው ድጋፍ በተጨማሪ ለዘላቂ ሰላም መስፈን ዘላቂ የሆነ ጠንካራ ሰራዊት እንደሐገር መገንባት እንችል ዘንድ አስፈላጊ የሚባለውን ሁሉ ድጋፍ በደስታና በኩራት ሲያደርግ ቆይቷል። አሁንም ግለቱን አስጠብቆ እንደቀጠለ ይገኛል። ዛሬም በማንነቱ በአገሩ ነፃነትና ሉዓላዊነት የማይደራደር ሕዝብ መሆኑን ልክእንደትናንቱ እንደቀደሙት አባቶቹ አይበገሬነቱን በግብር ማሳየት የቻለ ትውልድ አባል መሆን በመቻሌ ትልቅ ኩራት ይሰማኛል‼️

ድል ለታላቁ ሕዝብ!
ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲአል ድረስ ለመውረድ ተማምሎ የተነሳን ፀረ-ኢትዮጵያ ወፍ-ዘራሽ መደዴ የባንዳ ጥርቅምን ሁሉ፣ ኢትዮጵያን እንኳን እናንተ የትኛውም ምድራዊ ሃይል በእብሪት ተነስቶ አንበርክኮ ማፍረስ እንደማይችልና ኢትዮጵያን ለመንካት ደጋግሞ ማሰብ የግድ መሆኑን፤ "እናውቀዋለን በብሔር በጎጥ ከፋፍለነዋል፣ ሐገራዊ ስሜቱንም አክስመን እንዳልነበረ አድርገነዋል፤ በሚል ሒሳብ አማራን አንገት ለማስደፋት ነጣጥሎ ኢትዮጵያን ለማፍረስ በውስጥ ባንዳዎችና በውጭ ባዳዎች ቅንጅት በኢትዮጰያ ላይ የተከፈተውን ጦርነት ኢትዮጵያዊያን ልክ እንደዘመነ አድዋው ዛሬም የውስጥ ልዩነታቸውን ወደጎን ትተው በአንድነትና በፅናት በመቆም የቀደሙትን የአባቶቻቸውን ወኔ በመላበስ ጠላትን በተባበረ ክንዳቸው በፍፁም ብቃትና ጀግንነት በመመከት የጥላትን የጥፋት አላማ አክሽፈው የራሳቸውን አዲስ ታሪክ መስራት ችለዋል።

እንደ እጃችን መዳፍ እናውቀዋለን የተባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቅኔነትና ፉም እሳትነትም በግብር ተገልጦ ጠላት ያልጠበቀው ረመጥ ውስጥ ገብቶ እንዲቃጠል አድርጎታል። የተረፈውን እየለበለበ አሳዶ ከመሃል ወደጠርዝ ገፍቶታል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ማንነቱን የሐገሩን ነፃነትና ሉአላዊነቱን ለማስከበር ጠላት ሲነሳበት እንደ ፉም እሳት ነው። ሁሉም መሬት ለጠላት ኤርታሌ ነው። አውቀዋለሁ ብለህ ልትመፃደቅበት ስትሞክር ፈፅሞ የማታውቀው ብቻ ሳይሆን ልታውቀው የማትችል ቅኔ የሆነ ሕዝብ የሚሆንብህ አስደናቂ ታላቅ ሕዝብ ነው!
ወንድም በወንድሙ ላይ በክፋት ሲነሳ እንጅ ወንድም ከወንድሙ ጋር ሲታረቅ የሚናደድ ቢኖር እርሱ ሰይጣን ብቻ ነው‼️

የኢትዮጵያ ትንሳኤ ቀርቧል!
በሱዳን በኩል እየተሞከረ የሚገኘውን ተደጋጋሚ ከፍተኛ የማጥቃት እንቅስቃሴን ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአማራ ልዩሃይል የሑመራ መተማ የጎንደር ገበሬ በአስደናቂ ጀግንነት ጠላትን ወደማዳበርያነት እየቀየረው ይገኛል። የዋንጫው ጦርነት የመጨረሻው ምዕራፍ ገና ነውና በፍጹም መዘናጋት አያስፈልግም‼️
በማይጠብሪ ተከዜ ግንባር ጀግናው የወገን ጦር ከፍተኛ ማጥቃት በመክፈት በድል ወደፊት በመገስገስ ላይ ይገኛል‼️

ድል ለእናት ኢትዮጵያ‼️
ወያኔ ሰላም እረፍት የሚነሳው ያለግጭት መኖር የማይችልና ሕልውናው የተመሰረተው ልክ እንደ ሌሊት ወፍ ደም በመምጠጥ ነው።

ከአፋርና ከአማራ ክልል ተቀጥቅጦ የወጣው ሃይል በትግራይ ክልል ከሕዝቡ የሚመነሳበትን ጥያቄ መመለስ ስለማይችልና በሰላም መኖር ስለማይችል አሁን በጎንደር በኩል በተቆራረጠ መንገድ እያሳየ የሚገኘውን ትንኮሳ በማሳደግ ያለ የሌለ ሃይሉን ሙሉ በሙሉ በመጠቀም ከውጭ ከሱዳን በኩል ካሉ የተደራጁ ሃይሎችና ከሱዳን ጦር ጋር በመቀናጀት ከፍተኛ የማጥቃት ጦርነት መክፈቱ ፈፅሞ የማይቀር መሆኑን ዛሬም ደግሜ ማስገንዘብ እፈልጋለሁ።

ለማይቀረው ጦርነት ከመቼውም ጊዜ በተሻለ አንድነትን በማጠናከር ለዚህ ጦርነት የሚያስፈልገውን የሚመጥንን ከፍተኛ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል። ከመቼውም ጊዜ በተለዬ በንቃት የምንቀሳቀስበት ጊዜ እንጅ ምንም ስጋት እንደሌለብን ሆነን የምንዘናጋበት ወቅት አይደለም። ሁሉን አቀፍ ዝግጅት እናድርግ።
በወንድማማቾች መካከል ፀብን ከሚዘራ በላይ ጠላት የለም። ስንጥቅ መፍጠርና ስንጥቅን ማስፋት ግለሰቦችን በተለይም ወያኔን አምርረው የሚጠሉ ኢትዮጵያን አጥብቀው የሚወዱ ሰዎችን ሲሳደቡና ሲራገሙ ውሎ ማደር ወያኔነት ነው። የቋንቋ ካልሆነ የባሕሪይ ልዩነት የለውም።

አማራን አንገት ሊያስደፉ ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ ከወያኔ ጋር ሕብረት የፈጠሩና ያለ የሌለ አቅማቸውንም ለመጠቀም ቆርጠው እስከሲኦል ድረስ ሲሰሩ የነበሩ ሰዎችን ባለማወቅ ወይም በመፈለግ እንደ ተቆርቋሪ በመቁጠር እኛ እያለን አማራ አንገት አይደፋም፣ ኢትዮጵያም አትፈርስም፤ ያሉ ሰዎችን ግን እንደ ጠላት በጠላት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ተመርቶ በመቁጠር የተሰራው ወመኔ ስህተት በጥቂት ቆራጦች ጥረት መክሸፍ ባይችል ኖሮ አማራንም ኢትዮጵያንም ከባድ ዋጋ ያስከፍል ነበር። ማን ነው ፀረ-አማራ እና ፀረ-ኢትዮጵያዊ የሚለውን አካል የኢትዮጵያ ሕዝብ በዚህ የሕልውና ጦርነት አንድ በአንድ ጠንቅቆ የተረዳው ጉዳይ ነው። የማይታወቅ የተሰወረ አንዳችስ ነገር የለም። ይህ የሕልውና ጦርነት ያልገለጠው ነገር የለም።ማንም ሰው የሚያጭደው የዘራውን ነውና እንደየስራው ዋጋውን ማግኘቱ ተፈጥሯዊ ግዴታ ጭምር ይሆናል!
ለአማራ ሕልውና ትልቁ ስጋት አማራ ሳይሆን አማራ መስሎ የሚጮኸው የወያኔ የእጅ ስራ የሆነው አማራ ነው።

ለክፉ ለደጉም አማራ የመሰለው ሳይሆን አማራ የሆነው ብቻ ነው በአማራ ፖለቲካ አማራ ሆኖ በአክተርነት መስራት ያለበት።አዳማቂነት ወይም አጃቢነት የአክተርነት ያህል ሚና የለውም‼️
ከሑመራ እስከ መተማና የተከዜ ግንባሮች ላይ ሙሉ ትኩረታችን እናሳርፍ።ጠላት ከውጭም ከውስጥም በኩል ተቀናጅቶ ወደዚህ ቀጠና እያንቀሳቀሰ የሚገኘውን ሃይል በንቃት እንከታተል። ለዚህ የሚመጥን ከፍተኛ የሆነ የነቃ የተደራጀ የታጠቀ ጠንካራ ሃይል እንደብረት የጠነከረ አንድነት መፍጠርና ወደቀጠናው ማሰማራት ያስፈልጋል።ለነገ የሚባል ዝግጅት አይሆንም ወይም አይፈጠርም ተብሎ የሚናቅ ጉዳይም ሊኖር አይገባም።

በእልፍ ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች በጎንደር የተለያዩ ግንባሮች ጠላት ያለ የሌለ የመጨረሻ አቅሙን ለመጠቀም ቆርጦ ተነስቷል። ሞቱን ወልቃይት ላይ ነው የሚያደርገው። ይህን ለማድረግ ወደጎንደር በተለያዩ ግንባሮች ከፍተኛ ሃይል እያሰባሰበና በማንቀሳቀስ ላይ ነው።ለዚህ የሚመጥን ከእኛ ሁሉን አቀፍ ዝግጅቶችን ማድረግ ያስፈልጋል።

ትኩረታችንን ወደዚህ የስጋት ቀጠና አዙረን
እንሰባሰብ!
እንደራጅ!
እንታጠቅ!

እናት ኢትዮጵያ ዛሬም ልክ እንደትናንቱ የገጠማትን ፈተና በጀግኖች ልጇቿ የተባበረ ክንድ በአንፀባራቂ ድሎች ትሻገራለች!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጉምቱ ምሑር ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ትናንት በጎንደር ተገኝተው ከተናገሩት!

በበታችነት ስሜት የሚሰቃዩ ድውያንን ደቂቀ ወያኔዎችንና ቁራዎችን ያስጮኸና የሚያስጮህ የሰላምና የልማት የምክክር ጉባኤ!
👍1
ጀግናው የወገንን ጥምር ጦር ጠላት ይተማመንበት የነበረውንና ለረጅም ወራቶች መሽጎበት የከረመውን የእምባጉላይን የኮንክሪት ምሽግ ሰባብሮ በድል ወደፊት እየገሰገሰ ነው።

አጠቃላይ ጦርነቱን ለማሸነፍ አሁንም ከመቼውም ጊዜ በላይ በንቃት መንቀሳቀስና ከፍተኛ ዝግጅት ማድረግ ይገባናል‼️

በነገሮች ሁሉ እንበርታ። እንፅና!
ጀግናው የወገን ጦር አድርቃይን በአንፀባራቂ ድል ተቆጣጥሮ አድርቃይንም አልፎ በድል ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል‼️

ለአውደ ውጊያ ድላችን ልክ እየተደሰትን ጦርነቱን ለማሸነፍ ሳንዘናጋ በነገሮች ሁሉ ነቅተንና በርትተን በፅናት መስራትና መቆም አለብን‼️

ማህፀነ ለምለሟ እናት ኢትዮጵያ ዛሬም ልክ እንደትናንቱ በጀግኖች ልጆቿ የተባበረ ክንድ የገጠማትን ፈተና ታልፋለች‼️