Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.2K subscribers
2.99K photos
379 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የውጭ ሀገር ጎብኝዎች እንደ ሀውልት ተጠርበው ስለወጡት፣ እንደ መደብ የተደለደሉ፣ እንደ ሰንሰለት የተያያዙና ከሰማዩ ጋር የገጠሙ ስለሚመስሉት ግዙፍ ተራሮች፣በተለያዩ ቁሳቁሶች አምሳል ተጠፍጥፈው የተሠሩ ስለሚመስሉት ውብና አስደናቂ ቅርጽ ያላቸው የመሬት ገጽታዎችና አስደማሚ ገደሎችን ስለያዘው የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ስለ ኢትዮጵያስ ምን አሉ?።

የእርስዎ ደግሞ በጥምቀት ሲገኙ የሚሉትን ይላሉ ብለን እንጠብቃለን።
👍25
የሁመራ ከተማ ሕዝብ በነቂስ ወደ አደባባይ በመውጣት የTplfን የጥፋት መንገድ እያወገዘ ከትግራይ ወገኖቹ ጋር አብሮ ለመኖር ችግር የሌለበት ሰላምና ልማት ምርጫው ኢትዮጵያዊነት መለያው መሆኑን እየገለጸ ይገኛል።
👍33
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በመጨረሻም ዘመነ ካሴ የተባለው የመንደር አውደልዳይ ወጠጤ እንኳን አራት ኪሎ የነበረበት ጎጃም ርቆታል።
ከጎጃም ፈርጥጦ በሱዳን ከሚገኘውና የማይካድራን ንፁሃንን ጨፍ.ጭ.ፎ ከሄደው የጥፋት ሃይል ሳምሪ ጋር በይፋ ሕብረት ፈጥሯል። ሳምሪ እንኳን እሱን ራሱንስ ያድናል የሚለውን ወደፊት አብረን የምናየው ይሆናል።
👍25👎9
አበው "ዋቢ ያለው ያመልጣል ዋቢ የሌለው ይሰምጣል" ብለው ሲናገሩ፤
አልመሰለንም ነበር ስጋ ለብሶ የምናየው በጓንግ ወንዝ በየደንበሩ።
👍36👎3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከጦርነት ይልቅ ሰላምን መምረጥ ተደጋጋሚ ትንኮሳዎችን ባላዬ ማለፍ ችግሮችን በሆደ ሰፊነት በንግግር ለመፍታት መሞከር ፍርሃት አይደለም። አቅመ ቢስነት አይደለም። ካልሆነ ምከረው ምከረውን.. ጠቅሰን የኢትዮጵያን ልክ ለማሳየት እንገደዳለን‼️
👍23👎3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያ ደንበሯን ጥሶ የገባውንና አሁንም ተጨማሪ ቦታዎችን በእብሪት ለመያዝ የሚሞክረውን የሻዕቢያ ታጣቂ ለማስወጣት የምታደርገውን እንቅስቃሴ Tplf ለማደናቀፍ ታጣቂውን እያስጠጋ ሎጅስቲክም እያጓጓዘ ነው። ይሳካለታል? አብረን የምናየው ይሆናል።
👍19
የፋኖ ትግል በአማራ ጠላቶች እጅ የወደቀ ፀረ-አማራ ትግል መሆኑን ተረድቶ የትግል ሜዳ ከቀየረ አንድ የፋኖ አመራር ጋር ዛሬ ተገናኝቼ አንዳንድ ነገር ስናወራ "ቤተሰብህ የተረፈበትና ከባህርዳር የወጣበት መንገድ አሁንም ድረስ ይደንቀኛል ብሎ ዝርዝር ጉዳዩን..." ሲነግረኝ ሙሉ በሙሉ ስለጉደዩ እንደማያውቅ አዲስ ሰው ሆኜ ሰውነቴን ነዘረኝ። በጣምም ተገረምኩ። ጥያቄም ጠየኩት። እንዴት በእኔ የፖለቲካ አቋም ምክንያት ለዛውም በክልሉ በቀጥታ የምመራው የፖለቲካና የፀጥታ ጉዳይ እንኳ ቢኖር ከእኔ ያለፈ ቤተሰብን በማያውቀው ጉዳይ ለምን በዚህ ደረጃ ለማጥቃት ተፈለገ? ታቀደስ? አልኩት። የመለሰልኝ መልስ "በዛን ወቅት እኔም ፋኖ ነኝ ያላለው የፀጥታ እና የፖለቲካ አመራር ይቆጠር ነበር፤አንዳንዱ ጫካ ገብቶ የእንት ክፍለ ጦር ወይም ብርጌድ አዛዥ እንትና አለመባሉ እንጅ ለፋኖ የነበረው አቋምና ድጋፍ እኛን ሁሉ የሚያስንቅ ነበር። የዛን ወቅቱን ተወውና ዛሬም እኛ ስንመለስ ያልተመለሱ አሁንም ልባቸው ከጫካው ፋኖ ጋር የሆኑ አሉ። እንኳን ያኔ። ያኔማ ሳር ቅጠሉ ሁሉም እኔ ፋኖ ነኝ እያለ ያላለውም በፍርሃት ዝምታን ሲመርጥ አንተና እንትና ግን በተለያዬ መንገድ የተላከባችሁን ሽምግልና እና ማስፈራራት ወደ ጎን ከማለታችሁ በላይ ፋኖ ጠፍቶ ካላዬን ሞተን እንገኛለን አላችሁ። ሁሉም ፀጥ ባለበት እናንተ እንደፈለጋችሁ ሚዲያው ላይ ተወራጫችሁ። ከዛም ለሌላው ማስተማርያ እንዲሆን እሱን ማግኘት ባይቻል ቤተሰቡ ላይ እርምጃ ይወሰድ ተባለ "አለኝ። እንደ አዲስ በጣም ገረምኝ። ይህን ከሰማሁ በኋላም በዚህ ጉዳይ ካሰብኩት ጊዜ ቀድሜ ትንሽ ነገር በአደባባይ ለማለትና ክብር ለሚገባውም ክብር ለመስጠት ወሰንኩ።

ቤተሰቦቼ የሚኖሩት ባህርዳር ቀበሌ 16 ነበር። በባህርዳር ሲኖሩም መርጠውትና ደስ ብሏቸውም ነበር። ከተማዋን ይወዷታልም። ሲኖሩ አንድም ቀን ችግር ፈጥረው ችግር ተፈጥሮባቸውም አያውቅም። ለመጀመሪያ ጊዜ ችግር ያዩት የእነ ዘመነ ካሴ የመዋቅሩ ቀኜ(አሁን ይፋ የሆነው) የሚኖሩበት አካባቢ ተጠንቶ በከሸፈው ኦፕሬሽን ነው። እስከዛ ቀን ከማንም ጋር ችግር የለብንም አገር አማን ነው ብለው በሰላም ወጥተው እየገቡ እንደፈለጉ ነበር የሚኖሩት። ጳጉሜ 2/2016 ዓ/ም ግን አስበውት የማያውቁት ነገር ለዛውም የአማራ ክልል ፖሊስ የሚሉ ሁለት ፓትሮሎች በመኖሪያ ቤታቸው አደጋ ይዘው ተከሰቱ። ያልጠበቁት ነገር። እንኳን እነሱ እኔም ያልጠበኩት ቀን። እውነት ለመናገር እስከዛ ቀን እንኳን እነሱ እኔም የኔ የፖለቲካ አቋም ከኔ አልፎ ቤተሰብ ላይ በዛ ደረጃ አደጋ ይዞ እንደሚመጣ አላውቅም ነበር። እሱን ለማወቅና ለማረጋገጥ የግድ ያንን ቀን መጠበቅ ነበረብኝ። ለዛውም በመንግሥት በኩል ባለ አካል መሆኑን ለማረጋገጥ።
በርግጥ ይህ ከመህኑ አንድ ቀን በፊት እነ ዘመነ ካሴ በአንድ አመራራቸው በኩል አስደውለው እያሽካኩ (አረቂዋ የተያዘች ይመስለኛል) ሌሎች አመራሮችም እየሰሙህ ነው "የምታደርገውን ታቆማለህ ካላቆምክ አንተ በአብይ ጓዳ ስለሆንክ አናገኝህም ቤተሰቦችህን ግን ድጋሜ አታያቸውም። በእኛ እጅ ናቸው። እዚህ ክልል የሚያድናቸው አንድም አካል የለም መዋቅሩ በእጃችን ነው። ብልጽግና የለም። አሁን የምንገኘው ባህርዳር ዳር አካባቢ ነው ብለው አውርተውኝ" ነበር። እኔም በማምንበት መንገድ እንደምቀጥል ከፈለጉኝ አዲስ አበባ አስርገን አስገብተናል በሚሉት ፋኖ በኩል እንዲሞክሩ ያሉትን ሁሉ አናንቄ አጣጥዬ መልስ ሰጥቻቸው ነበር። ለአንድ ግለሰብ ወይም ቤተሰብ የሚሆን አቅም የላቸውም በሚል ሳይሆን በአንድ ሰው የፖለቲካ አቋም ንጹሃንን ለማጥቃት በዚህ ደረጃ ይራመዳሉ ቢራመዱም በነገሩኝ ልክ መዋቅሩን ተቆጣጥረውታል ብዬ ስላላሰብኩም ነበር።

ይህ ለማመን ቀርቶ ለማሰብ በቀጣዩ ቀን ጧት በቤተሰብ መኖሪያ ቤት ሁለት የአማራ ፖሊስ ፓትሮሎች ከላይ ታች ሲመላለሱ በመሃል በር አንኳኩተው ሲከፈትላቸው ግቢውን አይተው (አጋጣሚ ከቤተሰብ መካከል አብዛኛው ቤት አልነበረም)ይቅርታ በስህተት ነው ብለው ሲመላለሱ እንዲሁም ወደማታ በአካባቢው ባልተለመደ ሁኔታ አሁንም ከላይ ታች ሲሉ ቆይተው ወደመጨረሻ በር ላይ ቆመው እንዳንድ ነገር ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ መስማትና ማየት የግድ ነበረብኝ። እስከዚህ ድረስ ማንም ምንም ቢል ሊሆን የነበረውን አልቀበልም ነበር። በዚህ ቀን ግን አመንኩ። እንዳይረፍድብኝ እየጸለይኩ በዛ ፍጥነት በቀጥታ በክልሉ እና እዚህ ፌደራል ላይ ለሚመለከታቸው አካላት ስለጉዳዩ አሳወኩ። እግዜር ይስጣቸው ብዙዎቹም ባሳወኩት መሰረት ለጉዳዩ ቦታ ሰጥተው ተጣደፉልኝ። በወቅቱ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ላይ የነበሩት እነ ደሳለኝ ጣሰው ኮምሽነር ደስዬ ደጀን ኮምሽነር ዋኘው ጉዳዩን ራሳቸው ላይ እንደተደቀነ ጥቃት ቆጥረው በቀጥታ ነበር ራሳቸው የመሩት። በተሰጠው ፈጣን ስምሪትም የእነ ዘመነን የጥፋት እቅድ ማክሸፍ ቻሉ። ጉዳዩን ወደማጣራት ሲገባም ከባህርዳር ከክልሉም ፖሊስ ተልዕኮ ውጭ የሆነና ለጥፋት አላማ የሚንቀሳቀስ(በአሁኑ አጠራር የመዋቅሩ ቀኜ ተብሎ የተገለጠው) በፀጥታ መዋቅሩ ውስጥ የሚገኝ ፋኖ ሆነ።ይህን ተከትሎም ቤተሰብን አሁን ታርጌት ስለተደረጋችሁ አንዳንድ ነገሮች በመዋቅሩ እስኪስተካከል ቀጥታ ወደ አዲስ አበባ ሂዱና ዞር ብላችሁ ቆዩ ተብለው አዲስ አበባ በሰላም እንዲገቡ ተደረገ። እኔም ለጠላቴ ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን ለማለት በቃሁ። በዚህ ሂደት ከፈጣሪ ቀጥሎ በተለይ ኮምሽነር ደስዬ ችግሩ ከተከሰተበት ሰዓት ጀምሮ ለሊቱንም ጭምር በመከታተል ቤተሰብንም እየደወለ በማበርታት አንዱም የቤተሰብ አባል እንዳይደናገጥና የተለዬ ስሜት እንዳይሰማው በሚችለው ሁሉ በቅንነት በልዩ ሁኔታ ያሳዬው ትብብር ራሱ የቤተሰቡ አባል ይመስልም ነበርና ዛሬ በአደባባይ ከልብ አመሠግንሃለሁ ማለት ወደድኩ።
ኮምሽነር ደስዬ ደጀኔ ከእኔ በፊትም በመንገሥት በብልጽግና ውስጥ ለሚገኙና ለሚደግፉ ሀገር ወዳድ ወገኖች ችግር ገጠመን ሲባል ቀድሞ የሚደርስ ጀግንነትን ከትህትና ጋር የተላበሰ ለአመነበት ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ በሰኔ 15 የታቀደለትን በጀግንነት ተፋልሞ ያለፈ ጀግና ነው። ለውጡንም ከመጀመሪያው ጀምሮ ከኋላፊነት እስከተነሳበት ቀን ድረስ ለማጽናት በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እና ሀገር እንዳይፈርስ ፀንቶ የታገለ ሀገር ወዳድ ነው። ባለበት ክብርና ምስጋና ይድረሰው!!!

በነገራችን ላይ የጎጃም ፋኖ አመራሮች የእኔን ቤተሰብ ማንም አያድናቸውም በእኛ እጅ ናቸው ብለው በፍፁም እርግጠኝነት ከኦፕሬሽኑ በፊት ሲደውሉልኝ የነበሩበት ቦታ እነሱ እንዳሉኝ ከባህርዳር ብዙም አልራቁም ነበር። የከተማውን መብራት አሻግረው እያዩ ነበር ሲያወሩኝ የነበረው። አሁን ሳስበው የገባኝ አንድ ነገር ደግሞ ባህርዳር ላይ አልጋ ሁሉ ይይዙ እንደነበር ነው። አንዳንድ ኦፕሬሽኖች ለምን እንደከሸፉም ገብቶኛል።
👍17
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሀዋሳ አየር ተስማሚ ከተማው ውብ ሕዝቡም ፍቅር ነው። አንዴ እግር ጥሎት ላየው ደጋግሞ እንዲመላስ የሚያደርግ ነው።
👍5