Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.44K subscribers
2.98K photos
371 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
ግፍ የትም ይፈፀም የትም ሊወገዝ፤ ግፍ ፈፃሚዎችም ማንም ይሁኑ ማንም ከየትኛውም ብሔር ይሁኑ ሐይማኖት ወይም አካባቢ አስፈላጊው እርም*ጃ ሊወስ*ድባቸው ይገባል። ምንም የማያውቁ ንፁሃንን በመግ*ደል የሚገኝ የፖለቲካ ትርፍ እንደጧት ጤዛ ነው። የትም አያደርስም። አላስፈላጊ መስዋዕትነት ከማስከፈልና ከመክፈል ያለፈ የሚያዛልቅ አዋጭ መንገድም አይደለም።

የአማራን ሕዝብና የኦሮሞን ሕዝብ ከውጭ በኩል ለግብፅም ይሁን ለሱዳን ከውስጥ በኩል ደግሞ ለወያኔም ይሁን ለኦነግ ሸኔ በየደረጃው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመላላክ ሁለቱን ሕዝቦች ማጋጨ*ትም ሆነ አገር የማፍረስ እኩ*ይ አላማን ማሳካት አይቻልም።

የአማራና የኦሮሞ ሕዝብ በሰላምና በፍቅር ለዘመናት አብሮ ተዋልዶና ተዋህዶ የኖረ ወደፊትም የሚኖር ነው። አገር ችግር ውስጥ ስትገባም ከፊት እየቀደመ ለአገሩ ሉዓላዊነትና ነፃነት ዘብ የቆመ የየትኛውም ተላላኪ ባንዳ አጀንዳ ተቀባይ ያልሆነ ድንቅ ሕዝብ መሆኑን ያስመሰከረ ነው።
የሕዝቡ ፍቅርና አርቆ አሳቢነት በጄ እንጅ እንደ የባንዳ ባንዳዎቹ በየጊዜው ንፁሃንን በማጥ*ቃትና በሌሎች የተደጋገሙ ሕዝብን ሊያስቆጡ የሚችሉ የጥ*ፋት ድርጊት፣ በሕዝቦች መካከል የእርስ በርስ ግጭት ተነስቶ እል*ቂት ተፈጥሮ የኢትዮጵያ ሕልውናም አደጋ በገባ አገሪቱም በተበታተነ*ች ነበር።

ምንም የማያውቁ የንፁሃን የግ*ፍ ሞ*ት ሰው የሆነን በሙሉ የሚያሳዝን እንጅ የሚመርጥ አይደለም። በሐገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈፀሙ ግፎችን ማውገዝ ግፈኞችን ደግሞ አስፈላጊው ሁሉ እር*ምጃ እንዲወሰድባቸው ማድረግ ይገባል። ግፍም ሆነ ግፈኞች መደበቂያ ምሽግ ሊኖራቸው አይገባም!

መንግስትም ተደጋጋሚ ችግር በሚፈጠርባቸው ቀጠናዎች ዙሪያ ልዩ ትኩረት በመስጠት የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በማስፈን የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ በቁርጠኝነትና በተጠናከረ መንገድ ሊሰራበት ይገባል።

ሰላም ለኢትዮጵያችን‼️
ለማንኛውም...!

በራያ በኩል ትንኮሳ ያደረገው ጁንታ በጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊታችን የመጣው ወደማዳበርያነት ተቀይሯል። ተው ጁንታው መነካካቱ አያዋጣህም እየተባለ እየተመከረ ቢሆንም የተነፈሰውን ዕብሪት መልሶ ለመሙላት እየሞከረ ይመስላል!
በዕብሪት ተሞልቶ በካፈርኩ አይመልሰኝ ትንኮሳ ለማድረግም ሆነ ለላፊ ፍላጎት የሚመጣ ከሆነ ወደእንጦሮጦስ ከመሸኜት በቀር ሌላ ምን ምርጫ ይኖራል። እንዳመጣጡ እየለቀሙ መሸኘት ብቻ!

የኢትዮጵያን ሕልውና ነፃነትና ክብር ለመጠበቅ ሁሉንም ነገሩን አሳልፎ ለሚሰጠው በጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊታችን ሁሌም እንኮራለን‼️

ክብርና ምስጋና ለጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊታችን!

ሰላም ለእናት አገራችን‼️
ወያኔ አሁንም ለዳግም ወ*ረራ ሙከራ ሊያደርግ ይችላል። ወ*ረራ ሊፈፅም የሚችለው ግን በራሱ አቅም በመተማመን ሳይሆን መንግስት በሚያስተዳድረው ግዛት ውስጥ የሚኖረውን ሕዝብ በመንግስት ላይ ተስፋ ቆርጦ ወደሕዝባዊ አመፅ እንዲገባ የሚያስችል የፌደራሊስት ሃይሎች ድጋፍን ማግኘት የሚችልና በሐገሪቱ በተለይም በአማራ አካባቢ ሌላ ግንባር ሊፈጥርለት የሚችል ሁነኛ ሃይል ማግኘት ከቻለ ነው።

በውጭ ሃይሎች ማለትም በግብፅ በሱዳን ወይም በምዕራባውያን ጃስ ባይነት በሱዳን ውስጥ ከኢትዮጵያ ወደሱዳን በየጊዜው ሲነጉድ በነበረውና ከተለያዩ አገራት ወደሱዳን በመጣው በሺ በሚቆጠሩት ወታደራዊ ስልጠና ሲወስዱ በቆዩትና አሁንም እየወሰዱ በሚገኙት በነፃ አውጭ ስም በሚንቀሳቀሱት ድርጅቶች እንዲሁም በራሱ በወያኔ ከውስጥ በኩል በሚያደርገው ያለ የሌለ ዝግጅትና መደራጀት ተመክቶ ብቻ በሚፈፅመው ወ*ረራ ኢትዮጵያን በጦርነት አሸንፎ ሊያንበረክካት ፈፅሞ የማይቻል መሆኑን ከዚህ በፊትም ተሞክሮ የተረጋገጠ ነው።

በኢትዮጵያ በኩል ሲደረግ የቆየውና አሁንም እየተደረገ የሚገኘው ወታደራዊ ዝግጅት በሰው ሃይል በቴክኖሎጂ በትጥቅ እጅጉን ከወያኔና ከቅጥረኛዎቹ አንፃር ፈፅሞ ሊገናኝ የሚችል ጉዳይ አይደለም!
የኢትዮጵያ ወታደራዊ ዝግጅት ምን እንደሚመስል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ባለፈው በሕዝብ ተወካዮች ሞክር ቤት ላይ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ዝግጅት ወያኔን ለሚልኩት ጭምር እንጅ ለወያኔ ብቻ አለመሆኑንም አስረግጠው መናገራቸው የሚታወስ ነው።
ወያኔ ኢትዮጵያን የማፍረስ ዕድል ሊያገኝ የሚችለው በሐገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በሚንቀሳቀሱ በአጋር የፌደራሊስት ሃይሎች በኩል በሚፈፀሙ ግፎችና አሻጥሮች በሚነዙ የተጠኑ የሐሰት ፕሮፖጋንዳዎች ሕዝባዊ አመፅና የተለያዩ ግንባሮች እንዲፈጠሩ ማድረግ ከቻለ ብቻ ይሆናል። ይህ የመሆን ዕድሉ ደግሞ ዝግ ባይሆንም ቀላል ግን አይደለም!
የፌደራሊስት ሃይሎች ተብለው በመቀሌ ከተሰበሰቡት የሕወሓት አጋሮች መካከል በአማራ ክልል በኩል በድርጅት በግለሰብ ደረጃም በርካታ አማራዎች ተገኝተዋል። ከክልሉ ውጭ የተወለድን አማራ ነን የሚሉ ነገር ግን የወያኔ ምልምሎች በአሁኑ ሰዓትም በአማራ ፖለቲካ ጓዳ ውስጥ ድረስ ገብተው እየፈተፈቱና የአማራን የጓዳ ሚስጢር ለአሸባሪው ትህነግ የሚያደርሱ አማራውንም ለመከፋፈል የሚሰሩ በእምነት ጭምር የሚንቀሳቀሱ ሰዎች እያደረሱት ያለው ጉዳት የሚናቅ አይደለም። የአማራን ሕዝብ ማኀበረሰባዊ እረፍት የመንሳት የወያኔ ዕኩይ ዓላማን ተቀብለው ከሚያስፈጽሙት መካከል በዋነኝነት ተጠቃሽ ናቸው። ችግር በመፍጠር ሂደቱ ሌሎች የሚተባበሩ አማራዎች የሉም ማለት አይደለም።ይህን ማጥራት እስካልተቻለ ድረስ የአማራ ፖለቲካ እንደደፈረሰ መቀጠሉ የሚጠበቅ ነው‼️
ከሁለት አመት በፊት በሰኔ 15 ግፍ ዙሪያ ፍትህ እንደሚያስፈልግ ጠይቄ ነበር። ዛሬም እንደትናንቱ ፍትህ ሊሰጥ እንደሚገባ አምናለሁ።

የሰኔ 15 ጥቁር ቀን መዋቅር በተቆጣጠረና በእዛ ስር በተሰባሰበ አካል ብቻ የተፈፀመ ግፍ አይደለም። የሰኔ 15 የአማራ ክልል አመራሮች የግፍ ግድ*ያ ይፈፀም ዘንድ ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ የፌስቡክ የሆይ ሆይታ የመንጋ ግፊትና ጩኸት የማይናቅ ድርሻ ይወስዳል። ሰኔ 15 የአማራ ፖለቲካ የስብራት ቀን ነው። የተነቃቃው የአማራ ፖለቲካ ውሃ የተቸለሰበት፣ በፖለቲካ ኤሊቱ መካከል የታየው መሰባሰብና መናበብ ቅራኔ ፈጥሮ የተበታተነበት የግፍ ጥግ የታየበት ቀን ነው።
በሰኔ 15 ግፍ ዙሪያ ፍትህ መስፈን ባለመቻሉ የተነሳ ተጨማሪ ቅራኔዎችን እየፈጠረ ለመሄድም በሩ ከፍቶለታል ማለት ይቻላል።
በሰኔ 15 ጉዳይ የሆነውና እየሆነ ያለው ግፉን በመሸፋፈንና በማደባበስ እንዲሁ በደፈናው ሰኔ 15ን አይነሳብን በሚል ለማለፍና ለማዳፈን ከፍተኛ ሙከራ ሲደረግ ቆይቷል። ይህ ፍትህ ለሚያውቀው ለአማራ ሕዝብ የሚጠቅም አይደለም። ፍትህን እያዳፈኑ ስለ አማራነት ማውራትም ሆነ አማራ አማራ እያሉ መጮህ ብቻውን ለታላቁ የአማራ ሕዝብ የሚቀርፍለት ችግር የሚያመጣው ለውጥ የለም።

የአማራ ሕዝብ ፍርድ አዋቂ ነው። በፍትህ ከሄደችው በቅሎዬ ያለፍትህ የሄደችው ጭብጦዬ የሚል እንጅ ፍትህ ይዳፈን ዘንድ የሚተባበረ አይደለም። ስለሆነም የሰኔ 15 ጥቁር ቀንን በተመለከተ ፍትህ አግኝቶ እንዲዘጋ ለማድረግ መስራት እንጅ ጭራሽ ስለፍትህ የሚጠይቁ አካላትን በደቦ ፍርድ የተለያዬ ስም በመስጠት ብቻ የሰኔ 15 ግፍ እንዳልተፈጠረና ተዳፍኖ እንዲኖር የቱንም ያህል ሙከራ ለማድረግ መሞከር ተጨማሪ ችግር ከማምጣት ባሻገር አንዳች መልካም ነገር ይዞ ሊመጣ አይችልም። ፍትህን አዳፍኖ ማስቀረትም ፈፅሞ አይቻልም።

ፍትህ እንዳይሰፍን በግለሰብም ሆነ በቡድን ደረጃ በሚዲያ የመንጋ ጩኸት የማዋከብ ሙከራ ሊደረግ ይችል ይሆናል እንጅ ፈፅሞ ፍትህን ማንም አካል አዳፍኗት ሊቀር አይችልም። ይሰመርበት!
ፍትህ ግፍ ለተፈፀመባቸው በሙሉ!
ሰላም ለሐገራችን!
የኢትዮጵያ ታሪካዊ የውጭ ጠላቶች ኢትዮጵያን ባንዳ በሆኑ ኢትዮጵያዊያን ለማፍረስ ሲያደርጉት የነበረው ያልተቋረጠ የዘመናት ጥረት ዛሬም በሁሉም ግንባሮች ተጠናክሮ የቀጠለ እንጅ የደበዘዘ ጉዳይ አለመሆኑን ባልተቋረጠ ሁለንተናዊ ዘመቻዎች እያየን ነው። ከዚህ በፊት በባንዳው ትህነግ በኩል ኢትዮጵያን እንደሶሪያ የማፍረስ የጠላቶቻችን እኩይ አላማ በኢትዮጵያዊያን የተባበረ ብርቱ ክንድ ማክሸፍ የተቻለ ቢሆንም በውክልና ጦርነት ያላሳኩትን ራሳቸው በቀጥታ ወደሙሉ ጦርነት በመግባት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ትንኮሳ ጀምረዋል።
ኢትዮጵያዊያን በውስጥ ጉዳያቸው የቱንም ያህል ውስጣዊ ልዩነቶች ቢኖሩባቸውም በአገራቸው ሉዓላዊነትና ነፃነት የመጣ ግን ለማንም ፈፅሞ የማይመለሱና የማይደራደሩ ስለመሆናቸው ወደቀደመው ዘመን ሳንመለስ በባለፈው የሕልውና ዘመቻ ወቅት ከዳር እስከዳር ቀፎው እንደተነካበት ንብ ግልብጥ ብለው በመውጣት እንደብረት በበጠነከረ አንድነት በጠራና በፀና አቋም ጠላትን በመጣበት ቋንቋ በማናገር ቅስሙን ሰብረው አንፀባራቂ ድሎችን ተቀዳጅተዋል።
እኛ የእነዛ አይበገሬ አባቶቻችን ወኔና መንፈስ የተላበስን ማንነታችንንና ነፃነታችንን ለማስከበር የትኛውም ምድራዊ ኋይል ጥቃት ቢሰነዝር ሊያንበረክካቸውና አገር አልባ ሊያደርጋቸው የሚያስችል አንዳችስ ዕድል ሊሰጡ የማይችሉ ፉም እሳቶች ናቸው።

ዛሬም እንደትናንቱ በልጆቿ የተባበረ ክንድ ሉዓላዊነቷንና ነፃነቷን ጠብቃ ለቀጣዩ ትውልድ የታፈረችና የተከበረች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን እናስረክባለን‼️
ስለኢትዮጵያ ሕልውና ሉዓላዊነትና ነፃነት መከበር ሰርቲፋይድ ከሆኑ ባንዳዎች የሚጠበቅ አንዳች መልካም ነገር የለም። ቀዳሚ ባንዳዎቹና የባንዳ ባንዳዎቹ ለታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶቻችን መንገድ ከመምራት እና ጣት እየጠቆሙ ጩኸት ከማሰማት ያለፈ እዚህ ግባ የሚባል ሐይል የሌለው በመሆኑ ትኩረት የምንሰጠውና የሚያሳስበን ስጋትም ሊሆነን ፈፅሞ አይችልም።
በሕይወት መፅሐፍ የሚመዘገበው እየተመዘገበ በጥቁር መዝገብ የሚሰፍረውም እየሰፈረ የኢትዮጵያዊያን የማይቆመውና የማይንበረከከው ትውልዳዊ አንፀባራቂ ድል ይቀጥላል።

ኢትዮጵያ ዛሬም እንደትናንቱ በልጆቿ የተባበረ ክንድ ሉዓላዊነቷንና ነፃነቷን አስጠብቃ ለቀጣዩ ትውልድ የተከበረችና የታፈረች አገርን እናወርሳለን‼️
ሰሞኑን ኢትዮጵያ የደረሰችበትን ሁለንተናዊ ዝግጅት መሬት ላይ ምን እንደሚመስል ከተመረጡ ወደአርባ ከሚሆኑ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል ከተውጣጡ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር የአገሪቱን ወሳኝ ተቋማቶችን በአካል በመገኘት የሙሉ ቀን ጉብኝቶችንና ውይይቶችን ለማድረግ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት በቀረበልን ጥሪ መሰረት ከፌስቡክ መንደር ጠፍቼ ሰንብቼ ነበር።

ከፌስቡክ ወደአራት ቀን ያህል መጥፋቴን ተከትሎ የት ጠፋህ ብለው ስሜን ሜንሽን እያደረጉ የፈለጉኝ ሰዎችን ስመለከት የተደራጁ የስደብ ሜኑ አቅራቢዎች እንዳሉ ሁሉ በስራችን የሚያመሰግኑን ስንጠፋ የሚያስቡን ሰዎች መኖራቸውንም አይቼበታለሁ። ባይገባኝም ስለቀና ሐሳባችሁ ከልብ አመሰግናችኋለሁ!
እውነትን ያመንበትን ለአገርና ለሕዝብ ይጠቅማል ያልነውን ይዘን በአለን አቅም ማንነታችንንና ነፃነታችንን ከየትኛውም ታሪካዊ ጠላቶቻችንም ሆነ ውስጣዊ ባንዳዎች በኩል የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ የሚጠበቅብኝን ቀናና ገንቢ ጠጠር ለመወርወር የተዘጋጀሁና መቼም በየትኛውም ሁኔታ ለወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኞች ስድብና እርግማን ወደኋላ የማልል መሆኔን ለመግለጽ እፈልጋለሁ። የቆምንበት መሰረት እውነት ነውና!

በሰሞኑ ጉብኝታችንና ውይይታችንም የአገሪቱን ወሳኝ ሚስጢራዊ ተቋሞችን ኢንሳ አርቲፊሻል ኢንቴሌጄንስ የፌደራል ፖሊስ፣ የኢፌደሪ መከላከያ ሚኒስቴር፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነትን በጀኔራሎቹና በከፍተኛ የስራ ኋላፊዎቹ በኩል ተቋማቱ አሁን ስለደረሱበት ሁኔታ በቂ በሆነ ማብራሪያ ፍፁም ሰውነትና አገራዊ ስሜት በሚታይበት መንፈስ ከዳር ዳር ተዟዙረን ለመጎብኘትና ማወቅ ያለብንን የማወቅ ዕድሉን ለማግኘት ችለናል።
የእናት አገሬ ኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ ለውስጥ ባንዳዎችና የባንዳ ባንዳዎች ሳይሆን ለታሪካዊ ጠላቶቻችን በሚመጥን ደረጃ ሲደረግ የቆየውንና አሁን ላይ የተደረሰበትን ደረጃና ዝግጅት ሰፋ አድርገን ለመመልከት በቅተናል። እጅጉን የሚያኮራና በአገሬ ከነበረኝ ከራሴ በመነጬ የግምገማ እምነቴን የሚያጠናክርና ተጨማሪ የሞራል ስንቅንም ያገኘሁበት ጉብኝት ነበር ማለት ይቻላል።

የኢትዮጵያን ማህፀነ ለምለምነትንም በድጋሜ ለማረጋገጥ ችያለሁ። 24/7 ለእናት አገራቸው የሚደክሙ በመንጋ ጩኸት የማይደነብሩ መስራት ያለባቸው ስራ ላይ ብቻ አነጣጥረው ጊዜያቸውን እውቀታቸውን ጉልበታቸውን ሰጥተው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሌት ተቀን የሚታትሩ እልፍ ብርቅዮ ኢትዮጵያዊያን በየተቋማቱ መኖራቸውን ያረጋገጥኩበት ጉብኝት ነው።

በውይይታችን ማጠናቀቂያ ከጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በወቅታዊ እንዲሁም በቀጣይ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ወይይት አድርገናል።

ወደፊት ሚስጢራዊ ያልሆኑ ሕዝቡ ቢያውቃቸው ይበጃሉ የምላቸውን መረጃዎች የማጋራችሁ ይሆናል ።

ከታች በምስል የተያያዘውን ፎቶ ወደፌስቡክ ስገባ እንደ ሲአይኤ ወይም ሞሳድና ኬጂቢ በራሳቸው መንገድ ያገኙት ሚስጢራዊ ፎቶ አስመስለው የእኛ ልጆች ከለቀቁት ወስደው እኔ የማፍርበት ወይም የተደበኩበት ይመስል እየጠቆሙ ሲያዟዙሩት ተመለከትኩ። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተደረገልኝን ግብዣ ከዚህ በፊት ባየውና ባገኘው የምፈልገው ዕድል ነበርና ፈልጌውና ደስ ብሎኝ ነው የሄድኩት። በነበረው ጉብኝትና ውይይትም እጅጉን ደስተኛና በአገሬ ላይም ተስፋዬ እንዲለመል ያደረገኝ ነበር።

ኢትዮጵያ ዛሬም እንደትናንቱ በልጆቿ የተባበረ ክንድ ሉዓላዊነቷንና ነፃነቷን አስጠብቃ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች‼️
ደስ የሚል ጊዜን ከታላቆቻችን ጋር አሳልፈናል!

በሙዓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብቻ ሳትሆን ኢትዮጵያም እንደአገር አትራፊ ናት።
ጊዜ ሰጥቶ አውርቶና አወያይቶ ይቅርና እንዲሁ እንቅስቃሴዎቹ እንኳን አስተማሪ ናቸው። በመንጋ ጩኸት ለአፍታም ቢሆን ሳትደናበር በስሜት ሳይሆን በስሌት በቅንነትና በትጋት እናት ኢትዮጵያን በቁርጠኝነት ሰውነትን አስቀድመህ እያገለገልካት ስለሆነ እናመሰግንሃለንም!!
የሱዳን ጦር ድባቅ መመታቱና መፈርጠጡ የሚጠበቅ እንጅ የሚያስደንቅ አይደለም። በሱዳን ውስጥ በነፃ አውጭ ስም የሚሰለጥኑ ከኢትዮጵያ የሄዱ ባንዳዎች የማይኖሩበት የሱዳን ጦርም ብቻውን ከኢትዮጵያ ጦር ፊት ለፊት ሊያዋጋ የሚያስችል ምንም አይነት አቅምና ሞራል ፈፅሞ የለውም። የጎንደር ገበሬ አምስትም አስርም እየሆነ በየጊዜው ትንኮሳ የሚያደርግበትን የሱዳንን ጦር ልኩን ይሰጠው እርሻውንም በነፃነት ያርስ ነበር። የአሁኑ መደፋፈር ምንጩ በባንዳ ኢትዮጵያዊያን መሪነትና የኢትዮጵያን የውስጥ ችግር በመመልከት ክፍተቱን ተጠቅሞ ለማጥቃት የተደረገ ሙከራ ነው።
ውስጣዊ ጣጣችን መስመር ማስያዝ ብንችል ኖሮ እንኳን ሜካናይዝድ በሆነ በጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ይቅርና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በታጠቀው የጎንደር ገበሬ በሰዓታት ውስጥ ካርቱምን እንዳንቆጣጠር መሰናክል ሊሆነን የሚችለው ሙቀቱና ኪሎ ሜትሩ ካልሆነ የሱዳን ወታደር ፈተና ሊሆነን እንደማይችል ስናገር በፍፁም እርግጠኝነት ነው። ኢትዮጵያን አላስፈላጊ መስዋዕትነት ሊያስከፍሏት የሚችሉት የውስጥ ባንዳዎችና የባንዳ ባንዳዎቹ እንጅ የትኛውም የውጭ ሃይል በጦርነት ኢትዮጵያን ሊያንበረክካት ፈፅሞ አይችልም። ጭራሽ ሱዳን ራሷን ችላ! አይሆንም። እንኳን በውኗ በሕልሟ እንኳን ጦርነት ገፍታ በኢትዮጵያ ላይ ለመክፈት ለአፍታም የሚያስችል የመወጋት ሞራል ያላት አይመስለኝም!
ነገሮች መስመር እስኪይዙ በግብፅ አይዞሽ ባይነት በውስጥ ባንዳዎች መሪነትና ተዋጊነት እየታገዘች ማንገራገሯና ትንኮሳ ማድረጓ የሚጠበቅ ይሆናል።
ከቤህኒን አባላት አፈንግጠው ወደጫካ የወጡ በግብፅና በሱዳን ከፍተኛ ድጋፍ ይደረግላቸው የነበሩ ሃይሎች ሰሞኑን አሶሳን ለማሸበር በማሰብ ከርቀት ሆነው የሽብር ወሬ ሲነዙ ነበር። በዛሬው ዕለት ደግሞ ሮብ ገቢያ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በኤርፖርት አቅጣጫ በኩል በመምጣት ቦንብ በማፈንዳት የሽብር ጥቃት ሊፈፅሙ የተንቀሳቀሱ የቡድኑ አባላት በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።

ይህ ቡድን በተደጋጋሚ ከወያኔና ከሱዳን ወራሪዎች ጋር በመሆን መሰል የሽብር ሙከራ ለማድረግ ከዚህ በፊትም ሲንቀሳቀስ የቆየ እንደሆነ ቢታወቅም እስካሁ ሳይሳካለት ባለበት ላይ ሊቀር ችሏል።

የክልሉ መንግስት ከብሔራዊ መረጃና የደህንነት አካላት ጋር በመቀናጀት የሽብር ጥቃት ለመፈፀም በሚንቀሳቀሰው የቤህኒን ሃይል ላይ ባለበት ጫካ ሁሉ እያሳደደ እርምጃ በመውሰድ ላይም ይገኛል።
የቤህኒንም ሆነ የኦነግ ሸኔ እንዲሁም የሌሎቹ የሽብር ቡድኖች አላማ እንዲህ ተፈፀመ በሚል የሽብር ፕሮፖጋንዳ በመንዛት የላኪያቸውን ተልዕኮ መፈፀም እንጅ እነሱ ፊት ለፊት ገጥመው ሊያስመዘግቡት የሚችሉት ነጥብ የሌላቸው አቅመ ቢስ ሃይሎች መሆናቸው የታወቀ ነው። ከሶስተኛው የአባይ ግድብ የውሃ ሙሊት ጋር ተያይዞ ሙሊቱን ለማደናቀፍ በግብፅና በሱዳን ከፍተኛ ድጋፍ የሚደረግላቸው የእናት ጡት ነካሽ ባንዳዎች ከቤንሻንጉል ጋምቤላ ወለጋ አካባቢ ውጭ ባሉ አዲስ አበባን ጨምሮ በተመረጡ የሐገሪቱ አካባቢዎች ሰው በሚሰበሰብበት ጎዳና ጀምሮ በሐይማኖት ተቋማትም ላይ የሽብር ጥቃት ለማድረግ ከፍተኛ እንቅስቃሴና ጥድፊያ ላይ ስለመሆናቸው የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። ከሰሞኑ በባህርዳር የተፈፀመው የቦንብ ፍንዳታ በግብፅ የሚደገፉት የሽብር ቡድኖቹ የእቅድ አካል መሆኑም የሚታወቅ ነው።
ሕዝቡ የአካባቢውን ሰላም ከፀጥታ ሃይሉ ጎን በመቆም ሰላሙን ሊጠብቅ ይገባዋል!

ሰላም ለሐገራችን‼️
የብራው መብረቆች‼️

እናት ኢትዮጵያ ዛሬም ልክ እንደትናንቱ በጀግኖች ልጆቿ የተባበረ ክንድ ሉዓላዊነቷንና ነፃነቷን አስጠብቃ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች‼️
ዛሬም ብዙሃኑ ሰው ከፌስቡክ ለፌስቡክ በፌስቡክ በሆነ አጀንዳ የራሱን ዓለም ፈጥሮ ነገሮችን እየተነተነ በተለመደው የስማ በለው ጩኸት እንደገደል ማሚቶ እያስተጋባ ውሎ ማደሩን እንደቁምነገር ቆጥሮ ይወራጫል። የውርንጭላዊነት ትርፉ ግን ድካምና ትዝብት ብቻ ነው‼️
እንደ ትርጉም በፌስቡኮች ነገሮች መሬት ላይ ቢሆኑ ኖሮ እኮ ኢትዮጵያ የምትባልን ታላቅ አገር በፍርስራሿ ላይ እየፈለግናት ነበር። እንደጠላት ምኞት የማድረግ አቅም ቢኖረው ኖሮ አልቆልን ነበር። በነበር የሚታለፍ ሆነ እንጅ!
ዳግማዊ ኢህዴንን/ብአዴንን በአማራ በኩል ለማዋለድ በእነ ያሬድ ጥበቡ፣ ታምራት ላይኔ እና በሲአይኤው ቅምጥ ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ መሪነት የሚደረገው ጥረትና የአማራን ሕዝብ እረፍት የመንሳት ፕሮጀክት እንቅስቃሴ ዛሬም የቆመ አይደለም። ዳግማዊ ኢህዴንን/ብአዴንን ለመፍጠር የሚንቀሳቀሰው ሃይል በአማራ ስም የሲቪክ ማህበራትን እና የዩትዩብ ሚዲያዎችን በማቋቋም ዲያስፖራውን ለመቆጣጠር ሲያደርግ የነበረው እንቅስቃሴ ከሞላ ገደል አልተሳካለትም ማለት አይቻልም። ከተጨባጩ አገራዊ ቀጠናዊና አለማቀፋዊ ሁኔታ ጋር በማይገናኝ ትንተና እና የተሳሳተ መረጃ ዲያስፖራውን በማደናገር ከመዘወር ባሻገር በሐገር ቤትም የአማራ ሕዝብ ከትናንት የተሻገሩ መሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ እንዳያገኙ ለራሳቸው እኩይ አላማ ለመጠቀም ሲደክሙና ሲተጉ ታይተዋል።

ዳግማዊ ኢህዴንን/ብአዴንን ለመፍጠር እንቅስቃሴ ላይ የገባው ይህ የወያኔ ጉዳይ አስፈፃሚ ሃይል ከባሕር ማዶ እስከ ሐገር ቤት በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ የሞቀ እንቅስቃሴ ማጧጧፍ የጀመረው በዋናነት በሕወሓት ጠርናፊነት በመቀሌ የፌደራሊስት ሃይሎች ስብሰባ ላይ በብሔር ከተደራጁ ድርጅቶች መካከል በአማራ ስም የተደራጀው አብን በስብሰባው ላይ ካለመገኘቱ ባሻገር በአገራዊ አጀንዳዎች የሚይዘው አቋም ከፌደራሊስት ሃይሎች ጋር ፈፅሞ የማይታረቅና በአማራ ፖለቲካ ወያኔ አጀንዳውን እንዳይሸጥ እንዳይለውጥ ቀዳዳ ለማሳጣት መሞከሩን ተከትሎ ጎልቶ የታየ ነው።

በመቀሌ የፌደራሊስት ሃይሎች ተሰብስበው ተልዕኮ ተሰጣጥተው የተለያዩ መሆናቸውን ተከትሎ ብዙ ነገሮች ተቀያይረዋል።

በኦሮሞ በኩል የእነ ጃዋሩና በቀለ ገርባው ኦፌኮ በመቀሌው የፌደራሊስት ሃይሎች ከተገኙት አንዱ ነው። በፌደራሊስት ሃይሎች ጠርናፊና አንበል ሕወሓት በጠራው ስብሰባ ላይ ለመካፈል በቀለ ገርባ በመቀሌ ኦፌኮን ወክሎ የተገኘው ለደብረፅዮን ወይም ለጌታቸው ረዳ ትልቅ አክብሮት ወይም መውደድ ስለነበረው ወይም እነሱን ስለፈራ ወይም ትናንት አስረው የሰሩበትን ግፍ ረስቶት ሳይሆን በመስመር ወይም በአላማ TPLF አንዱና ቀዳሚው አጋር ሆኖ ስለተገኘ ነበር።
ኦፌኮ ሕወሓትን በሚዲያም መሬት ላይም ቄሮን በማንቀሳቀስ ጭምር በእነሱ አጠራር የአሃዳዊ መንግስት ያሉትን የዶ/ር አብይን መንግስት በውጭ ሃይሎች እገዛ ለማስወ*ገድ ይህ የማይሆን ከሆነ ደግሞ አገር ለማፍረስ ከመስከረም 30 በኋላ ሕጋዊ መንግስት ስላለመኖሩ ለአብይ አህመድ መንግስትም መከላከያ እንደማይታዘዝ በኋላም አዲስ አበባ ጀምረን አዲስ አበባ እንጨርሰዋለን በሚል ያልሰበቁት ጦር አልነበረም።
የፌደራሊስት ሃይሎች አንበል የሆነው ወያኔ በመደበኛ ጦርነት የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊትን በየትኛወም መንገድ ገጥሞ መገዳደር እንደማይችል ስለሚያውቅ ከፋፍሎ ለማዳከምና ኢትዮጵያን የመበታተን እኩይ አላማውን ለማሳካት በፈጠራቸው ሳተላይት ድርጅቶች በኩል ሙከራውን አቋርጦ አያውቅም።

በአማራ በኩል የፌደራሊስት ሃይሎች ተብለው መቀሌ ከተሰበሰቡት ውስጥ በአማራ ክልል በኩል አገው ሸንጎና ቅዴፓ በድርጅት ደረጃ ሲገኙ አማራን እወክላለሁ ብሎ በድርጅት ደረጃ መገኘት የቻለ ባይኖርም ስብሰባው ላይ በግለሰብ ደረጃ የተገኙ አማራዎች ስለመኖራቸው ግን መረጃዎች ያሳያሉ።
ከመስከረም 30 በኋላ ሕጋዊ መንግስት ስለማይኖር በሽግግር መንግስት በተለይ ደግሞ ከጥቅምት 24 የሰሜን ዕዝ ጥቃት በኋላ በጦርነቱ ወያኔ አሸናፊ ስለሚሆን በአማራ በኩል ከወያኔ ጋር ሊደራደር የሚችል አንድ አካል ያስፈልጋል በሚል በእነ ያሬድ ጥበቡና ታምራት ላይ መዝገብ የሚንቀሳቀሱ ዳግማዊ ኢህዴንን/ብአዴንን ለመፍጠር በርካታ አማራዎች ተንቀሳቅሰዋል።

በአማራው በኩል ለውጥ አምጥተንና ለውጡን አዋልደን ነገር ግን ከብልጽግና ተገፍተን ወጥተናል ብለው አልቃሽና ሙሾ አውራጅ አክቲቪስቶችን ያሰማሩት ቆሞ ቀሮች ዳግማዊ ኢህዴን/ብአዴንን ከውጭ ሆነው ለመፍጠር ከሚንቀሳቀሱት ጋር እየተመጋገቡ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በኦሮሚያ በኩልም ተገፋሁ በሚሉት የጀርባ መሪነት ዳግማዊ ኦህዴድን የመፍጠር ዘመቻው በሰፊው ተሰርቶበታል። በኦሮሚያ በኩል ያለው ሀይል ሰላማዊ አማራወችን በማስ*ገደል ግፍ ሲፈፅም በአማራው በኩል ያለው ደግሞ የአልቃሽነት ሚና ይዞ ህዝቡን ብሶት ውስጥ በመክተት መንግስት የጭፍ*ጨፋና ግ*ድያ አስፈጻሚ እንደሆነ የአዛኝነት ሙሾ በማሰማት ይገልፃሉ። በዚህ ሂደት ህዝቡ ጀርባውን ለመንግስት እንዲሰጥ በማድረግ የምንፈልገውን ውጤት እናገኛለን የሚል በሰው ህይወት ፖለቲካ ለመቆመር ሲዳክሩ ይታያሉ።

ከፌደራሊስት ሃይሎች የመቀሌ ስብሰባ በኋላ አብን በስብሰባው ካለመገኙት ባሻገር የሚያራምዳቸው ሐሳቦችና የሚይዛቸው አቋሞች የአማራን ሕዝብ ሁለንተናዊ ጥቅሞችን አገራዊና ቀጠናዊ ሁኔታዎችን ከግምት ያስገባ የጠራ አቋም መያዝ የጀመረ መሆኑ በአብን ላይ የተጠናከረ ከፍተኛ ዘመቻዎች ተጠናክረው እንዲከፈቱ አድርጎታል።

ወያኔ ለ27 ዓመት በብአዴን በኩል የአማራን ሕዝብ ጠርንፎ እንደያዘው ሁሉ በአብን በኩል ደግሞ የአማራን ሕዝብ ጠርንፎ አጀንዳውን ለመሸጥና በፌደሬሊስት ሃይሎች ምድብ ለማካተት የነበረው እቅድ መክሸፉን ተከትሎ በአብን ላይ ያልተቋረጠ ዘመቻ ከመክፈት ጎን ለጎን አማራን ጠርንፎ ሊይዝላቸው የሚችል ሌላ አጋር ሃይል ወደማዋለዱ እንቅስቃሴ ለመግባት ተገደዋል።

በዳግማዊ ኢህዴን/ብአዴን ስር በአብን፣ በብልፅግና፣ በሲቪክ ማህበራት፣ በባልደራስ፣ በሚዲያዎችና በፋኖ ስም የሚንቀሳቀሱ አካላት በቀጣይ ራሳቸውን ችለው በድርጅታቸው ለይቶላቸው ይወጣሉ ወይስ ባሉበት ሆነው ከትህነግ ጋር ጥምረት በመፍጠር የዶ/ር አብይ አህመድን አስተዳደርን እናስወግ*ዳለን ብለው ተማምለው ግንባር ፈጥረው ይዋጋሉ የሚለውን ጉዳይ በሂደት የምናየው ይሆናል።