Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.44K subscribers
2.98K photos
371 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
በመንግስት መዋቅር ውስጥ ሆነው ጥቅሜ ተነካብኝ ያሉ ቁሞ-ቀሮች ከወያኔ የሳይበር አርሚ ጋር በመመጋገብ በከፍተኛ በጀትና በተደራጀ ቅንጅታዊ ዘመቻ የፋኖን መልካም ስም ተጠቅመው አጀንዳቸውን በህዝብ አእምሮ ውስጥ ለመትከል ሰርተዋል።

“ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኞች” የሁሉንም ግንባር አውደ ውጊያዎችን ምሽግ ሰባሪ፣ ጠላት ማራኪ፣ ደም*ሳሽና ድል አድራጊ ፋኖ ብቻ እንደሆነና ሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ምንም ሚና እንዳልነበራቸው ብቻ ሳይሆን ለውጊያዎች መበላሸት በምክንያትነት ተጠቃሽ ሆነው እንዲቀርቡ አጀንዳ ቀርፀው በመሰራታቸው የጀግኖቹ ፋኖዎቻችን አኩሪ ተጋድሎ በልካቸውና በሚገባቸው ልክ ክብር እንዳያገኙ ከማድረጉ ባሻገር ፋኖ ባልሆኑት ፋኖዎች የተነሳ የፋኖን ስም ለማስጠላት ተሞክሯል።

የአማራ ሕዝብ ብቸኛው መዳኛ ፋኖ ብቻ እንደሆነ ያደረገ ትርክት አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ የተፈለገበት ዓላማ የአማራ ልዩሃይልን፣መከላከያ ሰራዊትን፣የፌዴራል ፖሊስን ለማዳከም ለመበታተንና ኢትዮጵያን ለማፍረስ በማለም ነው።
ፋኖን እናደራጅ በሚል በመከላከያ ሰራዊት በፌደራል ፖሊስ በአማራ ልዩሃይል ውስጥ ያሉ የአማራ አመራሮችን እና ወታደሮችን ለማስኮብለል ተሞክሯል። መከላከያ ውስጥ ያሉትን የአማራ ተወላጆችን “አማራ የሕልውና አደጋ ስላለበት ኑ ልዩሃይሉንና ፋኖን በመቀላቀል እናደራጅ” ፤ በልዩሃይሉ ውስጥ ያሉትን ደግሞ “ኑ ፋኖን እናደራጅ ውጡ” እያሉ በስመ ተቆርቋሪነት ከውስጥ ለውስጥ እስከ አደባባይ ሰፊ የተቀናጀ ዘመቻ የተደረገው ፋኖን ለማደራጀት ሳይሆን መከላከያ ሰራዊትንና ልዩሃይልን ለማስኮብለልና ወጣቱ መከላከያን እንዳይቀላቀል በማድረግ አገር ለማፍረስ ነበር። የኢትዮጵያ ትልቁ ምሽግ መከላከያ ሳይፈርስ አገር ሊፈርስ አይችልምና መከላከያ ውስጥ ያለ አባል እንዲከዳና ወጣቱ እንዳይቀላቀል ማድረግ የግድ ይቀድማል በሚል ህዎሓታዊ ምኞትና ዕቅድ ያለ ሀፍረትና ይሉኝታ ብዙ ሰርትዋል ። እነ ጌታቸው ረዳና ጀኔራል ፃድቃን ቀዳሚ ስራቸው የኢትዮጵያን መከላከያ ማዳከም መሆኑን ከዓመት በፊት መናገራቸው ይታወሳል። ይህን ለማሳካት ፋኖን ሽፋን አድርጎ መምጣት አዋጭ መንገድ ሆኖ አግኝተውታል።

ፋኖን “በዚህ ግባ በዚህ ውጣ” የሚለው አካልና የሚሰጠው ግዳጅ ስለሌበት፣ የተጠረነፈ አደረጃጀት ባለመሆኑ እንደፈለገ የሚንቀሳቀስ ሃይል ከመሆኑም በላይ የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች የሚገኙበት፤ መወድስ የሚቀርብለት ስለነበረ በመከላከያና በልዩሃይሉ ውስጥ ያሉ አባላት ልባቸው ሊሸፍት ይችላል በሚል ተስፋ የተጀመረው እኩይ ዘመቻ “ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኞች” የተወሰነ ውጤት ማስገኘቱ የሚካድ አይደለም።
እንደተደረገው ዘመቻ ቢሆን ኖሮ ግን መከላከያ ሰራዊትና ልዩሃይሉ አሁን ባለበት ቁመና ልናየው ይቅርና ተበታትኖ ይፈራርስ ነበር። ይህ ያልሆነው በመከላከያ ሰራዊትና ልዩሃይሉ ሃገር ወዳድነት ነውና ለሐገር ባለውለታዎቹ ጀግኖቻችን ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል።
ሁሉንም ነገሩን ለሕዝብና ለሀገሩ አሳልፎ ለሰጠው፣ እንደ አባቶቹ ዛሬም በዱር በገደሉ ደሙን በማፍሰስ አጥንቱን በመከስከስ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እያስከበረ፣ ከውስጥም ከውጭም የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን እያከሸፈ፣ ፀረ-ሰላም ሃይሎችን እየመነጠረ፣ ጠላቶቹን እንዳልነበሩ ወደማዳበርያነት እየቀየረ፣ በአኩሪ ተጋድሎ በድል ጎዳና፣ በታሪክ ሰሪነት፣ ወደፊት እየተረማመደ ለሚገኘው ለብራው መብረቅ ለጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊታችን ክብርና ምስጋና ይሁን‼️

የጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን አባል መሆን ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ክብር መጠበቅ፣ ለሕዝቦቿ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ዋስትና ሰጭ ከሚሆኑት መካከል ከቀዳሚዎቹ ቀዳሚ መሆን ነውና ኩራት ነው‼️
ለወያኔ በሚዲያ በዲፕሎማሲ በቁሳቁስ እና በገንዘብ እነ ሱዳን ግብፅ ምዕራባዊያንና እነ አሜሪካ ያልተቋረጠ ድጋፍ እንደሚያደርጉለት ሁሉ፣ የወልቃይት ሱዳን ኮሪደር ለወያኔ ይከፈትለት ዘንድ ሲወተውቱ ለነበሩና አሁን ደግሞ ድርድር እንኳን በሌለበት ሁኔታ ድርድር እየተደረገ እንደሆነና ወልቃይትም አብይ ለወያኔ አሳልፎ ሊሰጠው እንደሆነ የፈጠራ የሐሰት ወሬ ሲያስነዙ ለከረሙት በእነ ያሬድ ጥበቡ ታምራት ላይኔ ለሚመራው ዳግማዊ ኢህዴን፣ በአማራ ስም ላቋቋሙት የሲቪክ ማህበራቶች፣ ፋኖ ሳይሆኑ ለፈነኑ ፖለቲካል ፋኖዎች ተመሳሳይ ድጋፍ ያደርጋሉ።
የአማራ ፖለቲካ በአማራ ልጆች ተፅዕኖ ስር እንዳይውል ጠላት በያዘው የሚዲያ hegemony ጠንካራ የአማራ ፖለቲከኞችን የተለያዬ ስም በመስጠት ተፅዕኗቸው እንዲቀንስ፣ ከፖለቲካው እንዲወጡ፣ አዲስ ሊገቡ የሚፈልጉትን ደግሞ እንዳይጠጉና የፖለቲካው መድረክ በምን አገባኝ ስሜት በርግገው እንዲጠፉ አያሌ መንጋ የማዝመት ስራዎች ተካሂዷል።

አማራ ባልሆነ፣አማራ ቢሆንም የፖለቲካ ንቃተ ህሊና በሌለው አቅመ ቢስ የአማራ ፖለቲካ ይመራ ዘንድ በተለያዬ መንገድ የገፅታ ግንባታ ተሰርቶላቸው መሪ እንዲመስሉ ለማድረግ ተሞክሯል። በእነዚህ አማራዎች በኩልም ለአማራ ሕዝብ መብት መከበር ጥቅም መረጋገጥ የሚሰሩትን ጠልፎ ለመጣል ተጥሯል። በዚህ ሁሉ የጠላት መሩ የአማራ ፖለቲካ የመንጋ ጩኸት መካከል ደግሞ ለሕዝባቸው ሁለንተናዊ ጥቅም መረጋገጥ በፅናት ቆመው ያለፉ ቆዳቸው የአዞን የሆኑ ብርቱዎች እንዳሉ ታይተዋል።

እነዚህ አይቶ የአማራን ፖለቲካ ለማስተካከል መሞከር እንጅ በመንጋ ጩኸት የሚበረግጉትን ተመልክቶ አብሮ መንጎድ ለአማራ ፖለቲካ ተጨማሪ እዳ ከመሆን ያለፈ ትርጉም አይኖረውም‼️
ለኢትዮጵያ የምናስፈልግበት ጊዜ ስለነበረና አሁንም እንደሆነ ስለምናምን እንጅ ነገሮችን ከራሳችን አንፃር እንመልከት ቢባልማ ኢትዮጵያ በዚህ ሁኔታዋ እንኳን በቁማችን ከሞትንም በኋላ ልትቀበለን ቦታ ያላትም አትመስልም።

ታሪካዊና ትውልዳዊ ኋላፊነትን ለመወጣት የኢትዮጵያዊነትን ጠጠር መወርወር ስላለብን ብቻ ለሕሊና እና ለታሪክ ስንል እንጅ ከካድሬው በላይ ካድሬ፣ ከባለስልጣናቱ በላይ ስልጣን እንዳለው የምንገበገበው፣ ከባለሐብቱ በላይ ባለሐብት ከጥቅማጥቅም ተጠቃሚው በላይ የተጠቀመ መስለን የታየነው። እርግጥ ነው ለኢትዮጵያ ለአገረ መንግስቱ መፅናት ስንል በምናደርገው ማናቸውም ነገር የምንኩራራበት እንጅ መቼም የምንሸማቀቅበት ጉዳይ ሊሆን አይችልም‼️
የወታደር እናቱ አገሩ ናት። ለእናቱ ሕይወቱን በፈቃዱ በሳቅና በደስታ አሳልፎ የሚሰጥ ጀግና ወታደር አለን። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንኳን ለእናት አገሩ ለሌላ አገሮችም ሰላም ለማስከበር ተልዕኮ ሲሰጠው የማይከፍለው መስዋዕትነት የለም። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ልክ እንደ አየር መንገዳችን በአለም አቀፍ ደረጃ በአንፀባራቂ ስራው በጀግንነቱ ከፍተኛ መወድስንና ግርማ ሞገስን ያገኘ ነው። የአገሩን ሰላምና ፀጥታ ሉዓላዊነት አስከብሮ በአፍሪካ ሕብረትና በተባበሩት መንግስታት ድረጅት እምነት ተጥሎበት በተለያዩ አገራት በመዝመት ሰላምና ፀጥታ በማስከበር ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፈውና የትም አገር ላይ ያልተደፈረው ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን የተደፈረው አምኗቸው በተኛበት ወገኖቼ በሚላቸው ወያኔዎች ብቻ ነው።

ጀግናው ሰራዊታችን በከሃዲው ወያኔ ከደረሰበት የግፍ ጥቃት የቀረው ሃይል ራሱን መልሶ አደራጅቶ በጥፋት አበጋዞቹን ላይ በወሰደው የአፀፋ እርምጃ አላማቸውን ማክሸፍና ልካቸውን መስጠት የቻለና መቀሌን መቆጣጠር የቻለ ቢሆንም ነገር ግን ሰራዊቱ የፖለቲካ ስራ ባልተሰራበት የትግራይ ክልል ከዳር እስከ ዳር ከመደበኛ ጦርነት በተጨማሪ ራሱ እንደ ፖሊስ፣ እንደሚሊሻ፣ እንደ አድማ በታኝ ጭምር ሆኖ፣ የሰፈር ሰላምና ፀጥታ ለመጠበቅና ለማስከበር ሲሞት ሲቪል በሕይወት ሳለ ወታደር በሆነ ማህበረሰብ ውስጥ ሆኖ በመላው ትግራይ ክልል ተበትኖና ተሰማርቶ ለወገኑ ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ሲል አላስፈላጊ መስዋዕትነት የከፈለ ጀግና ሰራዊት ነው ያለን።

ለሰላም ማስከበር በተሰማራበት አገራት በአለም አቀፍ ደረጃ በግጃድ አፈፃፀሙ ላይ በሚያሳየው የላቀ ጀግንነት የአላማ ፅናት ከፍተኛ ዝናን ከትናንት እስከ ዛሬ እያተረፈ ላለው ለአለኝታችን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ክብርና ምስጋና ይገባዋል‼️
የአገር አለኝታ መከላከያችንን ማንም የመንደር አውደልዳይ በየአረቂ ቤቱ በየጫት መደቡ ተወዝቶ ሊዘባበትበት ሊሳለቅበት ሲሞክር "ኧረ የመንግስት ያለህ!" ለመሆኑ የአገሪቱ ቀይ መስመር ምንድነው?
ኢትዮጵያን ለማፍረስ የባንዳ ባንዳ ሆነው የሚሰሩ፣ በሐገሪቱ ሕግ በሐገር ክህደት ወንጀል የማይዳኙ ከሆነ በሌላ መንገድ መንግስት የእነሱን የክህደት መንገድ ሌሎች ልክ አድርገው እንዲቆጥሩትና ለሐገራቸው መስዋዕትነት የሚከፍሉ ሰዎች በፅናት እንዳይታገሉ ሞራላቸውን የሚሰልብ ነው! እያልን በየጊዜው ለመጮህ ብንሞክርም በወቅቱ የሚሰማ አካል አልነበረም።

ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በፓርላማ ቀርበው የዘገየ ቢሆንም "ከመቅረት ማርፈድ ይሻላል!" እንዲሉ "ካሁን በኋላ መከላከያን የሚነካ ይቀረፈደዳል" ማለታቸው በመንግሥት ስራ ተስፋ ሊቆርጥ የነበረውን ሃይል ተስፋ የሚሰጥ ይበል የሚያሰኝ ውሳኔ ነው። በአሜሪካም ሆነ በአውሮፓ ማንም ሰው የቱንም ያህል ታዋቂ ወይም አዋቂ የማህበረሰብ አንቂ መከላከያ ሰራዊታቸውን ሊያንቋሽሽ ይቅርና ሊያስበው የሚችለው ጉዳይ አይደለም። በሁሉም ሐገሮች በመንግሥትም ሆነ በማህበረሰቡ ዘንድ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሚንቀሳቀሱበት ሁሉ ቅድሚያ አገልግሎት የሚሰጣቸውና ከፍተኛ ክብር የሚሰጣቸው እንጅ የሚሰደቡና የሚሳደዱ አይደሉም። ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ጦርነት ስትጀምር በሩሲያ መከላከያ ሰራዊት ላይ የሚቀልድ የጥላቻ ንግግር የሚያደርግ እስከ 15 አመት እስር ይጠብቀዋል ብላ ያወጀችው ሕዝቡ ለመከላከል ሰራዊት ክብርና ቦታ ስለሌለው አልነበረም። ፑቲንን በሚጠላ አንድ ተቋም ተደረገ በተባለ ጥናት ከ81 በመቶ የሚሆኑ ሩሲያዊያን የፕሬዝዳንት ፑቲን ደጋፊና አድናቂ ናቸው። መከላከያ ሰራዊት ምን ያህል ቀይ መስመር እንደሆነ ለማሳየት እንጅ በእኛ አገር እንደታየው አይነት የባንዳ ባንዳዎች በዚህ ደረጃ ስጋት ይሆናሉ ወይም ይከሰታሉ በሚልም አይደለም የታወጀው። ለዛውም ጦርነቱ ለዩክሬን እንጅ ሩሲያ እስካሁን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ የምትለው በሩሲያ ውስጥ ሰላማዊና መደበኛ ሕይወት በዩክሬን ግዛት ውስጥ ጦርነት እየተካሄደ ነው። ሩሲያ እስካሁን ድል እያደረገች እንጅ የሕልውና ስጋት ላይም አይደለችም። የሕልውና አደጋ ውስጥ ሊከተኝ የሚችል አንዳች ነገር ከተፈጠረ በሚል የሰጠችውን የኑክሌር ጦርነት ማስጠንቀቂም የሚታወቅ ነው።
መከላከያ ሰራዊት የአገር ፀጥታና ሰላም ሉዓላዊነት ጠባቂ የመጨረሻው የሕልውና ምሽግ ነው።
እኛም በመከላከያ ሰራዊታችን ከማንም ጋር የማንደራደርበት ቀይ መስመራችን ሊሆን ይገባል‼️

በጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊታችን መሪነት በሌሎች የፀጥታ ሃይሎቻችን ተባባሪነት በሕዝባችን ደጀንነት እናት ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች‼️
የኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስትር ለሰቆጣ ከተማ ልዩልዩ ድጋፎችን አድርጓል።

*አዳሪ ትምህርት ቤትን ሙሉ ግንባታ ለመፈፀም
*የሰቆጣ ከተማ የውስጥ ለውስጥ የአስፓልት ግንባታ ስራ ለመስራት
የኢፌድሪ የሃገር መከላከያ ሚኒስትር ለሰቆጣ ከተማ መብራት አገልግሎት የሚውል አመታዊ የነዳጅ ወጭ 37 ሚሊዮን ብር ለከተማ አስተዳደሩ እንደሚለግስ በሰቆጣ ከተማ የተገኙት የኢፌድሪ ሃገር መከላከያ ሰራዊት ምክትል ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ መናገራቸውን የዋግኸምራ ኮሚኒኬሽን አስታውቋል።

ዋግኸምራ በወያኔ ዘመን በልማት እጅጉን የተጎሳቆለና አሁንም በጦርነቱ ክፉኛ የተጎዳ ሕዝብ ነው። በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ እያለፈ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ደጀንነቱንና ለጠላት ደግሞ እሾህነቱን በማሳየት ጀግንነቱንና ሐገር ወዳድነቱን ግን በፅናት ያስመሰከረ ድንቅ ሕዝብ ነው። ድጋፉም ቢያንስበት እንጅ የሚበዛበት አይደለምና ይገባዋል።

ስለድጋፉ መከላከያ ሰራዊታችንን ከልብ እናመሰግናለን‼️
ተባብሶ በቀጠለው በዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ምክንያት ግብፅ ከዩክሬን የምታስገባው ስንዴ በመቆሙ በሐገሪቱ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት እየተከሰተ ስለመሆኑ እየተነገረ ነው። ፕሬዚዳንት አልሲሲ ከዚህ በፊት በኑሮ ውድነት እየተማረረ ላለው ሕዝብ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብሎ የዛፍ ቅጠል መብላት እንዳለባቸው ምክር መስጠቱ ይታወሳል።

አሁን ደግሞ የውስጥ ችግሩን ለመፍታት ሲቸገር "ኢትዮጵያ ሶስተኛውን የውሃ ሙሊት ልትሞላ አይገባም፤ የግብፅን ውሃ ማንም እንዲነካ አንፈቅድለት፤ እርምጃ እንወስዳለን" እያለ ነው። ከፍተኛ ድንፋታ እያሰማ ነው።

ተይ ተረጋጊ እንጅ ምስር!

እንኳን መከላከያ ሰራዊታችን የእግር ኳስ ቡድናችንም ባንች ላይ ድልን መቀዳጀት ጀምሯል😂
ራሳቸው አንሰው አማራን ለማሳነስና አማራውን ከሁሉም ጋር ለማጋጨት የፍለጠው ቁረጠው የጃስ በለው! ፖለቲካ የሚያቀነቅኑ በአዲስ አበባ በአውሮፓ በአሜሪካ በጎረቤት አገር ከተሞች ከጦርነቱ በፊት ደግሞ በመቀሌ እየተመላለሱ ከጠላት ወያኔ ጋር ሲመክሩ የነበሩና ተልዕኮ የተቀበሉ፣ ነጋ ጠባ የወያኔን አጀንዳ የሚያሻሽጡ በምንም ጉዳይ ላይ የወያኔን ስም በትችት አጀንዳ አድርገው የማያውቁና ወያኔ የሚጠላውን ሁሉ የሚጠሉ የሚወደውን ሁሉም የሚወዱ የመንፈስ ልጅ የሆኑ አማራ የመሆን ችግር ያለባቸው አማራ ነን ባይ አማራዎችም ሆኑ የባንዳ ባንዳ አማራዎች ለጊዜው ጠላት የሚዲያ ብልጫ ስላለው በመንጋ ጩኸት የነገሱ ወይም ሐቀኛ የአማራ ተቆርቋሪ የሆኑ ቢመስሉም በሂደት ግን የሁሉም ማንነት ለሰፊው ሕዝብ መገለጡ አይቀርም። የጊዜ ጉዳይ ነው!

ለአማራ መቆርቆር ማለት አማራ ጠላት እንደአሸን እንዲፈላበት ወይም ማህበረሰባዊ እረፍት እንዳይኖረው ተግቶ መስራት መቻል እንደማለት አይደለም።
ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው ቅጠል ለብሰው ጋራ ሸንተረሩን እያቋረጡ ዳገት ቆልቁለቱን እየወጡ እየወረዱ በቁር በሐሩሩ እያለፉ የእናት አገራቸው ኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ሰላምና ፀጥታዋን ለማስከበር ሲሉ እልፍ ጀግኖች በክብር አልፈዋል።

ስለእኛ በነፃነት መኖር፣ በሰላም ውሎ በሰላም ማደር ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን የከፈለልንና እየከፈለልን ያለው መስዋዕትነት በቃላት የሚገለፅ አይደለም። ብቻ ስለሁሉም እናመሰግናለን ከማለት ውጭ ምንም ማለት አይቻልም‼️
ለአመታት በተነዛ በተዛባ ሐሰተኛ መረጃ፣ ባልተቋረጠ የተሳሳተ ፕሮፖጋንዳ በተደናገረና በማይተባበር አለፍ ሲልም ሲቪል የለበሱ ታጣቂዎች ምቹ ሁኔታ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት እየፈፀሙ በሚደበቁበት ማህበረሰብ ውስጥ፣ ሰራዊቱ ራሱን ለመከላከል እጁን እንዳያነሳ በንፁሃን ላይ በሚል ክስ በሚቀርብበት ሁኔታ ውስጥ፣ ከዳር እስከ ዳር እንደ ከተማ ፖሊስ፣ እንደ ሰፈር ሚሊሻ፣ እንደ አድማ በታኝ ተሰማርቶ ሕዝቡ ፊቱን ወደልማት እንዲያዞር ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን በትግራይ ክልል ሰላምና ፀጥታ ለማስፈን ሲል ከ 8 ወር በላይ ያለእረፍት ጥረት ቢያደርግም፣ ጎን ለጎን አጥጋቢ የሚባል የፖለቲካ ስራ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ባለመሰራቱ የተነሳ፣ ድካሙንና መስዋዕትነቱን የትግራይ ሕዝብ ተረድቶ ከጎን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፉ ሊሰጠው ባለመቻሉ አላስፈላጊ መስዋዕትነቶችን ሊከፍል ችሏል።

በጊዜያዊ አስተዳደሩ የፖለቲካ ስራ ቢሰራ፣ መከላከያ ሰራዊት እንደ ሰፈር ሚሊሻ፣ እንደከተማ ፖሊስ፣ እንደ አድማ በታኝ ጭምር ከመደበኛ ስራው በተጨማሪ ኋላፊነት ባያርፍበት ኖሮ፤ ሕዝቡ ከሰራዊቱ ጎን በመቆም ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ ቢችል ኖሮ፤ የትግራይ ክልል ዛሬ ለተጨማሪ ስቃይና መከራ ከጦርነት ነጋሪት ጉሰማ ከስጋት ቀጠና የወጣና ሰላም የሰፈነበት እንዲሁም ወደልማት የሚዞርበት ከባቢን መፍጠር በተቻለ ነበር።

በትግራይ ክልል ሰላምና ፀጥታ ሳይረጋገጥ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲመሰረትና በትግራይ ልጆች እንዲመራ ማዕከላዊ መንግስቱ ጣልቃ የማይገባበት ሁኔታን መፍጠሩ በኋላ ለተፈጠረው ችግር የራሱ አስተዋፅኦ የለውም ማለት አይቻልም። ቢያንስ በጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዝላልነትና አልፎ አልፎም በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ ባሉ የወያኔ ሰዎች ለወያኔ የተመቻቸው ሁኔታና የተፈጠረው ችግር የመፍጠር ዕድሉ ጠባብ ይሆን ነበር።

ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን የትግራይን ክልል ሰላምና ፀጥታ የሰፈነበት ለማድረግና ሕዝቡ ፊቱን ወደልማት እንዲያዞር ከማንም በላይ ዓመቱን በሙሉ የደከመውንና የከፈለውን መስዋዕትነት ሕዝቡ በተዛባና በሐሰተኛ መረጃ እንዳይረዳ ሆኖ ትርጉም እንዲያጣ ስላደረገው፥ አላስፈላጊ መስዋዕትነት እየከፈለ ላለመቀጠልና የትግራይ ሕዝብ የጥሞና ጊዜ ማግኘት ቢችል ራሱን አድምጦ ነገሮችንም አመዛዝኖ የሚበጀውን ሊመርጥ ይችላል በሚል ክልሉን ለቆ እንዲወጣ የፌደራል መንግስት የተናጠል የተኩስ ማቆም ውሳኔ ማሰላፉ የሚደነቅና የሚያስመሰግን የነበረ ቢሆንም መልካም ውሳኔና አጋጣሚውን ግን የትግራይ ክልል ሕዝብ በአግባቡ ከመጠቀም ይልቅ ወያኔን በአንድም በሌላም መንገድ በመከተል ለተጨማሪ የጥፋት አዙሪት ራሱን ዳግም አመቻችቶ ችግር ውስጥ ሊከት ችሏል ብሎ መውሰድ ይቻላል።

መከላከያ ከትግራይ ክልል ለቆ መውጣቱን ተከትሎም ብዙ ነገሮችን ለመታዘብ በቅተናል። አገር ለማፍረስ በአማራ ላይ ሂሳብ እንዲወራረድ፣ ከተከዜ ጀምሮ ተባባሪ የነበሩ በመንገድ ጠራጊነትና መሪነት የተሰለፉ የባንዳ ባንዳዎችን የሐገር ክህደት ጥግን ለማየትም ችለናል።

በትግራይ ክልል ከነበረው ሁኔታ ይልቅ መከላከያ ሰራዊታችን ለትግራይ ሕዝብ የጥሞና ጊዜ ሰጥቶ ወደአማራ ክልል ሲገባ የአማራ ሕዝብ በመከላከያ ላይ እንዲነሳና ደጀን እንዳይሆነው በሚዲያ የተሰራው ያልተቋረጠ የስም ማጥፋት ዘመቻም እጅጉን የሚያሳፍና የሚያሳዝን ቢሆንም በአንድ በኩል የዚህ ችግር ጉልበት ምንጩ የመንግስት የዝምታ ውሳኔ ነበር ማለት ይቻላል።

ዲጂታል ወያኔና የመንፈስ ልጆቹ ከተከዜ ጀምሮ የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት የአማራ ሕዝብ በጥይት የወያኔን ታጣቂ ደግሞ በፈንድሻ እንዲቀበለው የተዛባ ሐሰተኛ መረጃዎችን እየተመጋገቡ ይለቁ ነበር። ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚሰጠውን አክቲቪስቶች (በእርግጥ ጥቂት ነበሩ) ለሁሉም የተለያዬ ስሞችን ይሰጡ ነበር። እነሱን ለማዋረድ ዳሩ ግን ሕዝባችን ማንን መስማት እንዳለበት ያውቃልና ሊያሳፍራቸውና አገር የማፍረስ ሕልማቸውንም ሊያክሽፍባቸው ችሏል።

ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኞች መከላከያ በትግራይ ክልል በነበረበት ወቅት የትግራይ እናቶችን እየደፈረ፣ ንፁሃንን ደግሞ እየገደ*ለ አስመስለው በቀቀናዊ ግብራቸውን ሲያስተጋቡ እንዳልከረሙ 180° ተገልብጠው ደግሞ ጉዳዩን ከአማራ ጋር በማገናኘት መከላከያ ከትግራይ ክልል እንዴት ለቆ ይወጣል? አማራ ኦነጉ መከላከያ ሰራዊት ሊከዳህ ነው! በሚል በተቆርቋሪነት ካባ በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ በመክፈት ሕዝቡና መከላከያ እንዳይደጋገፍ በማድረግ ራሱ የፀጥታ ሃይሉንም በመከፋፈል ለመበታተን በታሰበ የሴራ አለ ሴራ አላማቸውን ለማፅፈም ያልፈነቀሉት ድንጋይ ያልወጡት አቀበትና ቁልቁለት አልነበረም። ወያኔን መንገድ በመጥረግና መንገድ በመምራት ያላቸውን ቁርጠኝነትም ጥጉን አሳይተዋል።

በኋላም በታላቁ ሕዝባችን ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ከፍተኛ አቀባበል ሲደረግለት ስሜታቸውን መቋቋም አቅቷቸው ለአማራ ሕዝብ ያላቸውን ንቀትና ጥላቻ በስድብ እስከመግለፅ መድረሳቸው የሚታወስ ነው። ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኞች በአማርኛ ማውራታቸው ካልሆነ የአማራን ሕዝብ የሚሸተን ቅንጣት ታህል ነገር አለመኖራቸውን በግብራቸው አስመስክረዋል። ወያኔ የሚጠላውን የሚጠሉ የሚወደውንም የሚወዱ ናቸው።
የመንፈስ አባታቸው ትህነግ የመከላከያን ከትግራይ ክልል መውጣት ተከትሎ በአማራና በአፋር ላይ ወረራ መጀመሩ ሳያንስ የወታደሩን እናት (ኢትዮጵያን) እናፈርሳታለን ብሎ በእብሪት ሲፎክር ከድካሙ ለማረፍ ጊዜ ባያገኝም "እኛ እያለን ኢትዮጵያ አትፈርስም!" ብሎ ውድ ሕይወቱን ስለእናቱ እየሰጠ በጀግንነት ተፋልሞ የጠላትን ቅስም ዳግም በመስበር የኢትዮጵያን ዘላለማዊ ጠላት አንበርክኮ የእናቱን ሕልውና መጠበቅና ክብሯን በደሙ ማስጠበቅ የቻለና ወደፊትም ኢትዮጵያን እነካለው የሚልን የትኛውንም አካል ልኩን ለመስጠት የማያመነታና ሁሌም ዝግጁ መሆኑን ያስመሰከረ ጀግና ሰራዊት ነው ያለን።
ግፍ የትም ይፈፀም የትም ሊወገዝ፤ ግፍ ፈፃሚዎችም ማንም ይሁኑ ማንም ከየትኛውም ብሔር ይሁኑ ሐይማኖት ወይም አካባቢ አስፈላጊው እርም*ጃ ሊወስ*ድባቸው ይገባል። ምንም የማያውቁ ንፁሃንን በመግ*ደል የሚገኝ የፖለቲካ ትርፍ እንደጧት ጤዛ ነው። የትም አያደርስም። አላስፈላጊ መስዋዕትነት ከማስከፈልና ከመክፈል ያለፈ የሚያዛልቅ አዋጭ መንገድም አይደለም።

የአማራን ሕዝብና የኦሮሞን ሕዝብ ከውጭ በኩል ለግብፅም ይሁን ለሱዳን ከውስጥ በኩል ደግሞ ለወያኔም ይሁን ለኦነግ ሸኔ በየደረጃው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመላላክ ሁለቱን ሕዝቦች ማጋጨ*ትም ሆነ አገር የማፍረስ እኩ*ይ አላማን ማሳካት አይቻልም።

የአማራና የኦሮሞ ሕዝብ በሰላምና በፍቅር ለዘመናት አብሮ ተዋልዶና ተዋህዶ የኖረ ወደፊትም የሚኖር ነው። አገር ችግር ውስጥ ስትገባም ከፊት እየቀደመ ለአገሩ ሉዓላዊነትና ነፃነት ዘብ የቆመ የየትኛውም ተላላኪ ባንዳ አጀንዳ ተቀባይ ያልሆነ ድንቅ ሕዝብ መሆኑን ያስመሰከረ ነው።
የሕዝቡ ፍቅርና አርቆ አሳቢነት በጄ እንጅ እንደ የባንዳ ባንዳዎቹ በየጊዜው ንፁሃንን በማጥ*ቃትና በሌሎች የተደጋገሙ ሕዝብን ሊያስቆጡ የሚችሉ የጥ*ፋት ድርጊት፣ በሕዝቦች መካከል የእርስ በርስ ግጭት ተነስቶ እል*ቂት ተፈጥሮ የኢትዮጵያ ሕልውናም አደጋ በገባ አገሪቱም በተበታተነ*ች ነበር።

ምንም የማያውቁ የንፁሃን የግ*ፍ ሞ*ት ሰው የሆነን በሙሉ የሚያሳዝን እንጅ የሚመርጥ አይደለም። በሐገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈፀሙ ግፎችን ማውገዝ ግፈኞችን ደግሞ አስፈላጊው ሁሉ እር*ምጃ እንዲወሰድባቸው ማድረግ ይገባል። ግፍም ሆነ ግፈኞች መደበቂያ ምሽግ ሊኖራቸው አይገባም!

መንግስትም ተደጋጋሚ ችግር በሚፈጠርባቸው ቀጠናዎች ዙሪያ ልዩ ትኩረት በመስጠት የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በማስፈን የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ በቁርጠኝነትና በተጠናከረ መንገድ ሊሰራበት ይገባል።

ሰላም ለኢትዮጵያችን‼️
ለማንኛውም...!

በራያ በኩል ትንኮሳ ያደረገው ጁንታ በጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊታችን የመጣው ወደማዳበርያነት ተቀይሯል። ተው ጁንታው መነካካቱ አያዋጣህም እየተባለ እየተመከረ ቢሆንም የተነፈሰውን ዕብሪት መልሶ ለመሙላት እየሞከረ ይመስላል!
በዕብሪት ተሞልቶ በካፈርኩ አይመልሰኝ ትንኮሳ ለማድረግም ሆነ ለላፊ ፍላጎት የሚመጣ ከሆነ ወደእንጦሮጦስ ከመሸኜት በቀር ሌላ ምን ምርጫ ይኖራል። እንዳመጣጡ እየለቀሙ መሸኘት ብቻ!

የኢትዮጵያን ሕልውና ነፃነትና ክብር ለመጠበቅ ሁሉንም ነገሩን አሳልፎ ለሚሰጠው በጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊታችን ሁሌም እንኮራለን‼️

ክብርና ምስጋና ለጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊታችን!

ሰላም ለእናት አገራችን‼️
ወያኔ አሁንም ለዳግም ወ*ረራ ሙከራ ሊያደርግ ይችላል። ወ*ረራ ሊፈፅም የሚችለው ግን በራሱ አቅም በመተማመን ሳይሆን መንግስት በሚያስተዳድረው ግዛት ውስጥ የሚኖረውን ሕዝብ በመንግስት ላይ ተስፋ ቆርጦ ወደሕዝባዊ አመፅ እንዲገባ የሚያስችል የፌደራሊስት ሃይሎች ድጋፍን ማግኘት የሚችልና በሐገሪቱ በተለይም በአማራ አካባቢ ሌላ ግንባር ሊፈጥርለት የሚችል ሁነኛ ሃይል ማግኘት ከቻለ ነው።

በውጭ ሃይሎች ማለትም በግብፅ በሱዳን ወይም በምዕራባውያን ጃስ ባይነት በሱዳን ውስጥ ከኢትዮጵያ ወደሱዳን በየጊዜው ሲነጉድ በነበረውና ከተለያዩ አገራት ወደሱዳን በመጣው በሺ በሚቆጠሩት ወታደራዊ ስልጠና ሲወስዱ በቆዩትና አሁንም እየወሰዱ በሚገኙት በነፃ አውጭ ስም በሚንቀሳቀሱት ድርጅቶች እንዲሁም በራሱ በወያኔ ከውስጥ በኩል በሚያደርገው ያለ የሌለ ዝግጅትና መደራጀት ተመክቶ ብቻ በሚፈፅመው ወ*ረራ ኢትዮጵያን በጦርነት አሸንፎ ሊያንበረክካት ፈፅሞ የማይቻል መሆኑን ከዚህ በፊትም ተሞክሮ የተረጋገጠ ነው።

በኢትዮጵያ በኩል ሲደረግ የቆየውና አሁንም እየተደረገ የሚገኘው ወታደራዊ ዝግጅት በሰው ሃይል በቴክኖሎጂ በትጥቅ እጅጉን ከወያኔና ከቅጥረኛዎቹ አንፃር ፈፅሞ ሊገናኝ የሚችል ጉዳይ አይደለም!
የኢትዮጵያ ወታደራዊ ዝግጅት ምን እንደሚመስል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ባለፈው በሕዝብ ተወካዮች ሞክር ቤት ላይ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ዝግጅት ወያኔን ለሚልኩት ጭምር እንጅ ለወያኔ ብቻ አለመሆኑንም አስረግጠው መናገራቸው የሚታወስ ነው።
ወያኔ ኢትዮጵያን የማፍረስ ዕድል ሊያገኝ የሚችለው በሐገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በሚንቀሳቀሱ በአጋር የፌደራሊስት ሃይሎች በኩል በሚፈፀሙ ግፎችና አሻጥሮች በሚነዙ የተጠኑ የሐሰት ፕሮፖጋንዳዎች ሕዝባዊ አመፅና የተለያዩ ግንባሮች እንዲፈጠሩ ማድረግ ከቻለ ብቻ ይሆናል። ይህ የመሆን ዕድሉ ደግሞ ዝግ ባይሆንም ቀላል ግን አይደለም!