Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.44K subscribers
2.98K photos
371 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
በኢትዮ-360 ይቅርታ በግብፅ-360 ላይ ሰው ሁሉ ነቅቶባቸዋል ብቻ ሳይሆን እንደጉድ ይቀልድባቸዋል የሚለው አይገልጸውም፤ ምን መሰለሽ እየሩስ?😂
By Addis Mekonnen

ኤርሚያስ ለገሰ በስልጣን ዘመኑ ክርስቲያኖችንና ሙስሊሞችን ለማጋጨት አንዴ ሙስሊም መስሎ የጥምቀት ቦታ ሲያሳጥር፣ ሌላ ጊዜ ክርስቲያን መስሎ የመስጊድ አጥር ሲያስፈርስ የሰራውን ሃጢያት ተናዝዞ፣ ይቅርታ ጠይቆ ነወይ ዛሬ የኢትዮጵያ ጠበቃ ሆኖ የመጣው?

ደግሞ ተሳስቶ ደብረ ፂዮንና ጌታቸው ረዳን ሲተች አይታይም። ጌታቸው ሲደነፋ አይናገረውም። ህወሃት አማራና አፋርን ወርሮ እንዲያ ግፍ ሲፈፅም ይሄ ጦርነት አማራን አይመለከትም ብሎ ሊያስበላን የነበረ ሰው ዛሬ ጠበቃችሁ ነኝ እያለን ነው።

ዛሬም ህወሃት አማራና አፋርን ሊወጋ ሲዘጋጅ ፈፅሞ "መንግስት ለዚህ ምላሽ ተዘጋጅቷል ወይ?" ብሎ ሲተች ሰምቼው አላውቅም።

ሞኝህን ፈልግ ባክህ!!

ይሄን መርዘኛ የመኖሪያ ወረቀት ካላገኘ አግዙት!!

(ከስር የሚሰጡ ስድቦች ሂዊ የመደበቻቸው አካውንቶች መሆናቸውን ተረድተን የብሎክ ሰይፍ እንመዛለን)
በሐሩርና በቁሩ በጋራ ሸንተሩ ስለሕዝቡ ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ስለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት መከበር ስለምታደርጉት ተጋድሎ ስለምትከፍሉት መስዋዕትነት ሁሉ ታላቅ ክብር ይገባችኋል‼️

የእናት ኢትዮጵያ ዘብና አለኝታ ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ሰሞናዊ ሁኔታው!
ዳኛው ወዶም ተገዶም ነው "ያለም ወርቅ አንች እኮ ሙዚቃ ነሽ ፤ አንችን በመዳኜቴ እድለኛ ነኝ፤ ልቤም ዞረ ... ያለው"። የባለፈው ሳምንቱን ብቃቷንም ነው ዛሬ የደገመችው።

የዓለም - ወርቅ!
በእርግጠኝነት
ወርቁ ያንቺ ነው፤እንኳን ደስ ያለሽ‼️
ዘማቹ ባለሃብት ለፋና ላምሮት ክስተቶች የ60,000 ብር የገንዘብ ስጦታ አበረከተ
***
አቶ አማረ ባይነሳኝ ዘውዴ ይባላል። መናገሻ ጎንደር ከተማ ውስጥ "ታኦስ የባህል ምሽት" ባለቤት ነው። በሰላም ጊዜ ነጋዴ በጭንቅ ጊዜ ዘማች ፋኖ ነው።

ወደመናገሻ ጎንደር የሚመጡ የአገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች የምሽት ክለቡን ሳይረግጡ አይመሰለሱም።

የአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ጉራጌኛ፣ ወላይትኛ፣ አፋርኛ፣ ሶማሊኛ፣... የባህል ሙዚቃዎችን ከነቱባ አቀራረቡ ደምቀው የሚቀርቡበት ታዋቂ ባህላዊ የምሽት ክለብ ነው።

ጎንደር እግሩ የረገጠ ቱሪስት ታኦስ ላይ ኢትዮጵያዊ የባህል ቡፌ ይቀርብለታል።

የፋና ላምሮት ክስተት የሆኑት ያለምርቅ ጀምበሩ እና ደሳለኝ አበበ፣ ታኦስ የባህል ምሽት የሚሰሩ የጥበብ ፈርጦች ናቸው።

የታኦስ የባህል ምሽት ባለቤት አማረ ባይነሳኝ ልጆቹ ለዚህ ስኬት በመብቃቸው ለሁለቱም በድምሩ የስልሳ ሺህ ብር የገንዘብ ስጦታ አበርክቷል።

በቀጣይ የጥበብ ሥራ ጉዟቸውም ከጎናቸው በመሆን ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል ቃል ገብቷል።

አቶ አማረ ባይነሳኝ በህልውና ዘመቻው ወቅት በጋሸናና በማይጠምሪ ግንባር በመዝመት የትግሬ ወራሪን ያሳደደ አርባ ጎራሽ አንጋች፣ ትጥቅ አሳማሪ አልሞ ተኳሽ ዘማች ፋኖ ነው። ጋሳይ ላይ በነበረው ጦርነት 12 ሳጥን የጠላት ጥይት አግንቶ በጀኔራል ደስታ (ያኔ ኮሎኔል) ለምትመራው 33ኛ ክፍለ ጦር በማስረከብ በግንባሩ የዘመቻ ኮር አመራሮች እውቅና ያገኘ ሀገር ወዳድ ዘማች ፋኖ ነው።

በጎንደርና አካባቢው ባሉ የማህበራዊ በጎ አድራጎት ተግባራት በቀዳሚነት ስሙ የሚጠቀሰው ዘማቹ ባለሃብት አማረ ባይነሳኝ ትላንትም ሆነ ዛሬ ለሚያደርጋቸው የበጎ አድራጎት ስራዎቹ ሁሉ እናመሰግናለን🙏

የፋና ላምሮት ክስተት ለሆኑት
ያለም ወርቅ ጀምበር እና
ደሳለኝ አበበ

ለዚህ ስኬት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ። በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ኮከብ ሆናችሁ እንደምትወጡ አንጠራጠርም👌

🎼 🎹 🎷 🎸 🎶 🎵
ምቀኝነት ከበታችነት ስሜት የሚመነጭ በፀበል ሊድን የማይችል ክፉ ደዌ ሲሆን በሂደትም ጥላቻን መፍጠሩ አይቀርም። ጥላቻ ደግሞ እንደካንሰር ነው። ምልክቱ የሚታየው ተነጣጥሮ አልቆ ቃታ ሊሳብ ሲል መሆኑ ነገሮችን ከባድ ያደርጋቸዋል።

ከእውነት ጎን መቆም ወይም እውነትን መናገር ደግሞ የጥላቻ ምልክት ሳይሆን ውሸትን ማደሪያ ማሳጣትና ሊደርስ የሚችልን የጋራ አላስፈላጊ ጉዳት መቀነስ ነው። ይኼው ነው!
ስለወልቃይት ብዙ አሉታዊ ወሬዎች እየተናፈሱ ነው።ማወቅ ያለባችሁ ያለብን ነገር የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን መሆኑን ነው" ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ጋር እያደረጉት ከሚገኘው ውይይት ከተናገሩት የተወሰደ!
ዓመቱን በሙሉ አብይ /ብልፅግና ወልቃይትን ለሕወሓት አሳልፎ ሊሸጠው ነው፤ አማራም ልትካድ ነው፤ ተነስ አምፅ ሲሉ የነበሩ የግጭት ነጋዴ የወያኔ የማደጎ ልጆች፣ ዛሬ ደግሞ ተገልብጠው ትክክለኛ ማንነታቸውንም ይበልጥ አንጥረው ገልፀውታል። ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በጎንደር ከተማ ላይ እያደረጉት ባለው town hall meeting ወልቃይትን በተመለከተ ሲናፈስ የነበረው ወሬ ብዥታ ስለፈጠረ ከጎንደር ሕዝብ ለተነሳላቸው ጥያቄ "ወልቃይት የማንደራደርበት ቀይ መስመራችን ነው" በማለታቸውና የክልሉ መንግስትን አቋም አስምረው በማሳወቃቸው "ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኞች ድንኳን ጥለው፣ ንፍሮ ቀቅለው፣ ነጠላ ዘቅዝቀው፣ ለቅሶ ላይ ተቀምጠው" እያየን ነው።

በአንፃሩ ሐቀኛ የአማራ ልጆችና ሰፊው የአማራ ሕዝብ በደም መስዋዕትነት ያገኘው የዓመታት የማንነት ጥያቄ ስለነበረ በመንግስት አቋም ደስተኛ የሚሆን ነው። የአዞ እንባ የሚያነባውን ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኞች ለቅሶ ቀድመን ማንነታቸውንና አቋማቸውን ለምናውቅ ሰዎች እንደ ማጀቢያ ክላሲካል ነው።
የብልጽግና ሰው አንተ ብልፅግና! የአብይ አህመድ ውታፍ ነቃይ! ሲለኝ እንደመስማትና እንደማየት ያለ የኢትዮጵያን መከራ ሊያራዝም የሚችል ሌላ ፍረጃ በባትሪ ቢፈለግ ሊገኝ የሚችል አይመስለኝም። በእነሱ ቦታ ሆነን ቢሆን እነዚህ የብልፅግና ሰዎች ምን ሊሉን ይችል ነበር የሚለውን ሳስብ አለማሰብ ይቀላል።

በዚህ አጋጣሚ ከዚህ በፊት ለመንጋው ምንም እንኳን ቅንጣት ታህል ለሚያደርገው የስም ማጥፋት ዘመቻ ቦታ ሰጥቼ የማላውቅ ቢሆንም ከእንግዲህ ወዲያ ደግሞ መቼም ቢሆን የማይታሰብ መሆኑ እንዲታወቅ እፈልጋለሁ።

እርግጥ ነው ችግሩ የእነዚህ ድኩማን የብልጽግና ሰዎች ሳይሆን የራሱ የብልጽግና ነው።

በነገራችን ላይ ብልፅግና መሆን ወንጀል አይደለም ብቻ ሳይሆን የአማራን ሕዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ መንግስታዊ መዋቅሩን ከያዘው ከብልፅግና በላይ ለአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ማንም የቀረበ አካል የለም። ብልፅግና እርኩስም ሆነ ቅዱስ ለመባል የአንበሳውን ድርሻ መያዛችንም ለአፍታም ቢሆን ለጥያቄ ሊቀርብም አይገባም።

አየር ላይ ያላችሁ ወፈፌ የወያኔ የማደጎ ልጆች "ኧረ ባክህ!" ልትሉ እንደምትችሉ ብናውቅም መራራው ሐቅ ግን ከዚህ የተለየ አይደለምና እንደኮሶ ቢመርም አጣጥሞ መዋጥ የግድ ይሆናል‼️
ትክክለኛው ፋኖ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በፓርላማ ተወድሷል። ተመስግኗል። ትክክለኛው ፋኖም ሆነ የፋኖ ደጋፊ በሚከተለው የዶ/ር አብይ ንግግር ፈፅሞ ሊከፋ አይችልም። ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ ደግሞ እንደተለመደው የሚለው የታወቀ ነው።

"በስንዴ ማሳ ስንዴ ብቻ ሳይሆን እንክርዳድ በብልፅግና እሳቤ ውስጥ አበልፃጊ ብቻ ሳይሆን ሌቦች እንዳሉት ሁሉ፣ በሚያኮራ ስም ሁላችንም በምንመካበት ስም፣ ሌሎች ለመጠቀም ፈልገዋል። ፋኖ ለአማራም ለኢትዮጵያም ኩራት ነው፤ ምንም ጥያቄ የለውም፡፡ በጀግንነት ተዋግቷል፤ ወደፊትም በጀግንነት ይዋጋል!!

እሱ የአብይን ውዳሴ ሙገሳ ጠብቆ የሚዋጋ ሳይሆን አገሩን ወዶ የሚዋጋ ነው፡፡ ከተነካችበት አይቆምም
ወደ ፊትም። አድርጓል ያደርጋልም፡፡ ይሄ መመስገን አለበት መከበርም አለበት፡፡ ጥያቄ የለውም!!

ይህንን ስም ግን መጠቀሚያ ማድረግ ትክክል አይደለም፡፡በከተማ ተኩስ ብቻ ሳይሆን መዝረፍ ፤ሴቶች መድፈር ህፃን መጥለፍ ነጋዴመዝረፍ ፤ግብር መሰብሰብ ፎርጅድ ብር ማምረት ይሄ የፋኖ ስራ ሊሆን አይችልም፡፡

ፋኖ ፎርጅድ ብር አይሰራም፡፡ፋኖ ህፃን አይጠልፍም ፤ሴት አይደፍርም፤ ሲባጎ ወጥሮ ግብር አይሰበስብም፡፡አማራ ክልል የነበረው ይሄ ነው የአማራ ክልል ተወካዮች ታውቃላችሁ፡፡ ማታውቁ ከሆነ ሄዳችሁ ጠይቁ ህዝባችሁን!!"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ
በመንግስት መዋቅር ውስጥ ሆነው ጥቅሜ ተነካብኝ ያሉ ቁሞ-ቀሮች ከወያኔ የሳይበር አርሚ ጋር በመመጋገብ በከፍተኛ በጀትና በተደራጀ ቅንጅታዊ ዘመቻ የፋኖን መልካም ስም ተጠቅመው አጀንዳቸውን በህዝብ አእምሮ ውስጥ ለመትከል ሰርተዋል።

“ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኞች” የሁሉንም ግንባር አውደ ውጊያዎችን ምሽግ ሰባሪ፣ ጠላት ማራኪ፣ ደም*ሳሽና ድል አድራጊ ፋኖ ብቻ እንደሆነና ሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ምንም ሚና እንዳልነበራቸው ብቻ ሳይሆን ለውጊያዎች መበላሸት በምክንያትነት ተጠቃሽ ሆነው እንዲቀርቡ አጀንዳ ቀርፀው በመሰራታቸው የጀግኖቹ ፋኖዎቻችን አኩሪ ተጋድሎ በልካቸውና በሚገባቸው ልክ ክብር እንዳያገኙ ከማድረጉ ባሻገር ፋኖ ባልሆኑት ፋኖዎች የተነሳ የፋኖን ስም ለማስጠላት ተሞክሯል።

የአማራ ሕዝብ ብቸኛው መዳኛ ፋኖ ብቻ እንደሆነ ያደረገ ትርክት አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ የተፈለገበት ዓላማ የአማራ ልዩሃይልን፣መከላከያ ሰራዊትን፣የፌዴራል ፖሊስን ለማዳከም ለመበታተንና ኢትዮጵያን ለማፍረስ በማለም ነው።
ፋኖን እናደራጅ በሚል በመከላከያ ሰራዊት በፌደራል ፖሊስ በአማራ ልዩሃይል ውስጥ ያሉ የአማራ አመራሮችን እና ወታደሮችን ለማስኮብለል ተሞክሯል። መከላከያ ውስጥ ያሉትን የአማራ ተወላጆችን “አማራ የሕልውና አደጋ ስላለበት ኑ ልዩሃይሉንና ፋኖን በመቀላቀል እናደራጅ” ፤ በልዩሃይሉ ውስጥ ያሉትን ደግሞ “ኑ ፋኖን እናደራጅ ውጡ” እያሉ በስመ ተቆርቋሪነት ከውስጥ ለውስጥ እስከ አደባባይ ሰፊ የተቀናጀ ዘመቻ የተደረገው ፋኖን ለማደራጀት ሳይሆን መከላከያ ሰራዊትንና ልዩሃይልን ለማስኮብለልና ወጣቱ መከላከያን እንዳይቀላቀል በማድረግ አገር ለማፍረስ ነበር። የኢትዮጵያ ትልቁ ምሽግ መከላከያ ሳይፈርስ አገር ሊፈርስ አይችልምና መከላከያ ውስጥ ያለ አባል እንዲከዳና ወጣቱ እንዳይቀላቀል ማድረግ የግድ ይቀድማል በሚል ህዎሓታዊ ምኞትና ዕቅድ ያለ ሀፍረትና ይሉኝታ ብዙ ሰርትዋል ። እነ ጌታቸው ረዳና ጀኔራል ፃድቃን ቀዳሚ ስራቸው የኢትዮጵያን መከላከያ ማዳከም መሆኑን ከዓመት በፊት መናገራቸው ይታወሳል። ይህን ለማሳካት ፋኖን ሽፋን አድርጎ መምጣት አዋጭ መንገድ ሆኖ አግኝተውታል።

ፋኖን “በዚህ ግባ በዚህ ውጣ” የሚለው አካልና የሚሰጠው ግዳጅ ስለሌበት፣ የተጠረነፈ አደረጃጀት ባለመሆኑ እንደፈለገ የሚንቀሳቀስ ሃይል ከመሆኑም በላይ የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች የሚገኙበት፤ መወድስ የሚቀርብለት ስለነበረ በመከላከያና በልዩሃይሉ ውስጥ ያሉ አባላት ልባቸው ሊሸፍት ይችላል በሚል ተስፋ የተጀመረው እኩይ ዘመቻ “ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኞች” የተወሰነ ውጤት ማስገኘቱ የሚካድ አይደለም።
እንደተደረገው ዘመቻ ቢሆን ኖሮ ግን መከላከያ ሰራዊትና ልዩሃይሉ አሁን ባለበት ቁመና ልናየው ይቅርና ተበታትኖ ይፈራርስ ነበር። ይህ ያልሆነው በመከላከያ ሰራዊትና ልዩሃይሉ ሃገር ወዳድነት ነውና ለሐገር ባለውለታዎቹ ጀግኖቻችን ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል።