Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.45K subscribers
2.98K photos
371 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
በአማራ ክልል የሕግ ማስከበር እርምጃ መውሰድ ከተጀመረ በኋላ ማታ ማታ በአንዳንድ አካባቢዎች ቀን ጭምር ይሰማ የነበረው የጥይት የተኩስ ድምፅ ሙሉ በሙሉ ቆሟል። ሕዝቡ ያለምንም ስጋት በሰላም ወጥቶ በሰላም መግባት ጀምሯል። ሕዝቡ በስርዓት አልበኞች ምን ያህል የደህንነት ስጋት ውስጥ እንደነበረ የሚታወቅ ነበር። በሕዝቡ ተደጋጋሚ ጥያቄና መሪነት ከመንግስት የፀጥታ አካላትና ከትክክለኛ ፋኖዎች ጋር በተደረገ የተቀናጀ የሕግ ማስከበር ዘመቻ በተለይ ሰላም ከማስፈን አንፃር ከታዬ የሕግ ማስከበር ኦፕሬሽኑ ውጤታማ ሆኗል ማለት ይቻላል። በሁሉም አካባቢ ሰላማችንን አገኘን የማይለውና ለዘላቂ ሰላሙ ለፍትህ መስፈን የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ መንግስት የጀመረውን ሕግ የማስከበር እርምጃ የማይደግፍና የማይተባበር ኮንትሮባንዲስትና የወያኔ የማደጎ ልጅ ካልሆነ በስተቀር ከሰላም ወዳድና ሕግ አክባሪ ዜጎች መካከል ሌላ ስም ተሰጥቶት የሚቃወሙ አንድም ሰው በባትሪ ፈልጎ ማግኘት አይቻልም።

ሰላም ለሁላችን!
የወያኔ የፊት ደጀን እየወላለቀና እየተበታተነ መምጣቱ በቀጣይ ወያኔን በቀላሉ ለማንበርከክ ወይም በራሱ ጊዜ እጅ እንዲሰጥ የሚያስችል ይሆናል።
እንኳን ደስ አለን!

እናት ኢትዮጵያ በእግር ኳሱ የግብፅን መረብ እንደሞላሽውና ድልን እንደተቀዳጀችው ሁሉ ታላቁ የሕዳሴ ግድባችን በመሙላት አንፀባራቂ ድሎችን ታስመዘግባለች። የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የከፍታና ብሩህ ዘመን እየመጣ ነው!
የኢትዮጵያ አሁናዊና ቀጣይ ሁኔታ‼️
በኢትዮ-360 ይቅርታ በግብፅ-360 ላይ ሰው ሁሉ ነቅቶባቸዋል ብቻ ሳይሆን እንደጉድ ይቀልድባቸዋል የሚለው አይገልጸውም፤ ምን መሰለሽ እየሩስ?😂
By Addis Mekonnen

ኤርሚያስ ለገሰ በስልጣን ዘመኑ ክርስቲያኖችንና ሙስሊሞችን ለማጋጨት አንዴ ሙስሊም መስሎ የጥምቀት ቦታ ሲያሳጥር፣ ሌላ ጊዜ ክርስቲያን መስሎ የመስጊድ አጥር ሲያስፈርስ የሰራውን ሃጢያት ተናዝዞ፣ ይቅርታ ጠይቆ ነወይ ዛሬ የኢትዮጵያ ጠበቃ ሆኖ የመጣው?

ደግሞ ተሳስቶ ደብረ ፂዮንና ጌታቸው ረዳን ሲተች አይታይም። ጌታቸው ሲደነፋ አይናገረውም። ህወሃት አማራና አፋርን ወርሮ እንዲያ ግፍ ሲፈፅም ይሄ ጦርነት አማራን አይመለከትም ብሎ ሊያስበላን የነበረ ሰው ዛሬ ጠበቃችሁ ነኝ እያለን ነው።

ዛሬም ህወሃት አማራና አፋርን ሊወጋ ሲዘጋጅ ፈፅሞ "መንግስት ለዚህ ምላሽ ተዘጋጅቷል ወይ?" ብሎ ሲተች ሰምቼው አላውቅም።

ሞኝህን ፈልግ ባክህ!!

ይሄን መርዘኛ የመኖሪያ ወረቀት ካላገኘ አግዙት!!

(ከስር የሚሰጡ ስድቦች ሂዊ የመደበቻቸው አካውንቶች መሆናቸውን ተረድተን የብሎክ ሰይፍ እንመዛለን)
በሐሩርና በቁሩ በጋራ ሸንተሩ ስለሕዝቡ ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ስለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት መከበር ስለምታደርጉት ተጋድሎ ስለምትከፍሉት መስዋዕትነት ሁሉ ታላቅ ክብር ይገባችኋል‼️

የእናት ኢትዮጵያ ዘብና አለኝታ ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ሰሞናዊ ሁኔታው!
ዳኛው ወዶም ተገዶም ነው "ያለም ወርቅ አንች እኮ ሙዚቃ ነሽ ፤ አንችን በመዳኜቴ እድለኛ ነኝ፤ ልቤም ዞረ ... ያለው"። የባለፈው ሳምንቱን ብቃቷንም ነው ዛሬ የደገመችው።

የዓለም - ወርቅ!
በእርግጠኝነት
ወርቁ ያንቺ ነው፤እንኳን ደስ ያለሽ‼️
ዘማቹ ባለሃብት ለፋና ላምሮት ክስተቶች የ60,000 ብር የገንዘብ ስጦታ አበረከተ
***
አቶ አማረ ባይነሳኝ ዘውዴ ይባላል። መናገሻ ጎንደር ከተማ ውስጥ "ታኦስ የባህል ምሽት" ባለቤት ነው። በሰላም ጊዜ ነጋዴ በጭንቅ ጊዜ ዘማች ፋኖ ነው።

ወደመናገሻ ጎንደር የሚመጡ የአገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች የምሽት ክለቡን ሳይረግጡ አይመሰለሱም።

የአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ጉራጌኛ፣ ወላይትኛ፣ አፋርኛ፣ ሶማሊኛ፣... የባህል ሙዚቃዎችን ከነቱባ አቀራረቡ ደምቀው የሚቀርቡበት ታዋቂ ባህላዊ የምሽት ክለብ ነው።

ጎንደር እግሩ የረገጠ ቱሪስት ታኦስ ላይ ኢትዮጵያዊ የባህል ቡፌ ይቀርብለታል።

የፋና ላምሮት ክስተት የሆኑት ያለምርቅ ጀምበሩ እና ደሳለኝ አበበ፣ ታኦስ የባህል ምሽት የሚሰሩ የጥበብ ፈርጦች ናቸው።

የታኦስ የባህል ምሽት ባለቤት አማረ ባይነሳኝ ልጆቹ ለዚህ ስኬት በመብቃቸው ለሁለቱም በድምሩ የስልሳ ሺህ ብር የገንዘብ ስጦታ አበርክቷል።

በቀጣይ የጥበብ ሥራ ጉዟቸውም ከጎናቸው በመሆን ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል ቃል ገብቷል።

አቶ አማረ ባይነሳኝ በህልውና ዘመቻው ወቅት በጋሸናና በማይጠምሪ ግንባር በመዝመት የትግሬ ወራሪን ያሳደደ አርባ ጎራሽ አንጋች፣ ትጥቅ አሳማሪ አልሞ ተኳሽ ዘማች ፋኖ ነው። ጋሳይ ላይ በነበረው ጦርነት 12 ሳጥን የጠላት ጥይት አግንቶ በጀኔራል ደስታ (ያኔ ኮሎኔል) ለምትመራው 33ኛ ክፍለ ጦር በማስረከብ በግንባሩ የዘመቻ ኮር አመራሮች እውቅና ያገኘ ሀገር ወዳድ ዘማች ፋኖ ነው።

በጎንደርና አካባቢው ባሉ የማህበራዊ በጎ አድራጎት ተግባራት በቀዳሚነት ስሙ የሚጠቀሰው ዘማቹ ባለሃብት አማረ ባይነሳኝ ትላንትም ሆነ ዛሬ ለሚያደርጋቸው የበጎ አድራጎት ስራዎቹ ሁሉ እናመሰግናለን🙏

የፋና ላምሮት ክስተት ለሆኑት
ያለም ወርቅ ጀምበር እና
ደሳለኝ አበበ

ለዚህ ስኬት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ። በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ኮከብ ሆናችሁ እንደምትወጡ አንጠራጠርም👌

🎼 🎹 🎷 🎸 🎶 🎵
ምቀኝነት ከበታችነት ስሜት የሚመነጭ በፀበል ሊድን የማይችል ክፉ ደዌ ሲሆን በሂደትም ጥላቻን መፍጠሩ አይቀርም። ጥላቻ ደግሞ እንደካንሰር ነው። ምልክቱ የሚታየው ተነጣጥሮ አልቆ ቃታ ሊሳብ ሲል መሆኑ ነገሮችን ከባድ ያደርጋቸዋል።

ከእውነት ጎን መቆም ወይም እውነትን መናገር ደግሞ የጥላቻ ምልክት ሳይሆን ውሸትን ማደሪያ ማሳጣትና ሊደርስ የሚችልን የጋራ አላስፈላጊ ጉዳት መቀነስ ነው። ይኼው ነው!
ስለወልቃይት ብዙ አሉታዊ ወሬዎች እየተናፈሱ ነው።ማወቅ ያለባችሁ ያለብን ነገር የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን መሆኑን ነው" ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ጋር እያደረጉት ከሚገኘው ውይይት ከተናገሩት የተወሰደ!