Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.45K subscribers
2.98K photos
371 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
"መከላከያ ባይኖር እንኳን ሕወሓትን ምስራቅ አፍሪካን በቀናነት እንቆጣጠራለን" እያለ ሲበጠረቅ የነበረ ፤ ጦርነት ምን እንደሆነ፣ ውጊያ ገብቶ የማያውቀው ብቻ ሳይሆን ክላሽ ይዞ ጥይት ወደሰማይ ተኩሶ የማያውቀው ሁሉ ነበር በተለይ ምስጊኑን የአማራን ዲያስፖራ ሜካናይዝድ ጦር እንዳደራጀ አማራ ሆኖ ሲሸልልና ሲያቅራራ የከረመው።

በነገራችን ላይ በየከተማው ለቦርጭ ቅነሳና ለአግላይነት "ቁጭ ብድግ!" ሲሰሩ የነበሩ ሰዎች (ወደበኋላ በወከባ ፋኖ የሆኑ ሰዎች ) መጀመሪያ አካባቢ የአማራ ክልል መንግስት እስከቀበሌ ድረስ ያለ ወጣት እንዲሰለጥን ባስተላለፈው መመሪያ መሰረት እንዲሰለጥኑ ከተሰጠው አቅጣጫ በዲጂታል ወያኔ ፕሮፖጋንዳ መስመር የሳቱ ሰዎች ናቸው ።

እነኚህ በየከተማው "ቁጭ ብድግ" ሲሉ የነበሩ ሰዎች እየቆዩ ሲሄዱ መንደራቸውን ሳይለቁ የትም ግንባር ላይም ሳይሳተፉ የሁሉንም አውደ ውጊያዎችን ድል ያለምንም ጦርነት መቀዳጀት የቻሉ በዓለም ታሪክ የመጀመሪያዎቹ ፈር ቀዳጆች የመሆን እድል ይኖራቸዋል። የሁሉም ጦርነት ድል አድራጊ ነን ባዮቹ አብዛኞቹ "ቁጭ ብድግ!" የሰሩት ራሱ ጦርነቱ ከተጠናቀቀ በኋላ መሆኑንስ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን?!
ስንት ጀግኖች እናት አገራቸውን ለመታደግ የሕዝባቸውን ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ለማስከበር ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉበትን ጦርነት ማንም የቤት ሙሴ የመንደር አውደልዳይና የባንዳ ባንዳ ከድል ማግስት ነውሩን ጌጥ አድርጎ አርበኛ አርበኛ ሊጫወት ቢሞክርም ዝም ሊባል ግን አይገባውም።
በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ፖለቲካ ለታላቁ የአማራ ሕዝብ ሁለንተናዊ ጥቅም መረጋገጥ፤ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ክብር መጠበቅ፣ እንደ ቡና በብረት ምጣድ በእሳት የተቆሉ አረፍን ሲሉ በሙቀጫ የተወቀጡ ተመልሰው በበራድ እሳት ላይ የተጣዱና የተንተከተኩ በፖለቲካ ውስጥ የሚሳተፉ ሰዎች ጥቂት ናቸው። ብዙሃኑ ምቾቱን ጠብቆ በተዋበ ሮኮቦት የድግሱ ሰዓት በኩራት እያብለጨለጨ እንደሚወጣ ስኒ (ፍንጃል) ነው።

አሁን ባለው በአማራ ፖለቲካ ውስጥ የሚሳተፈው አብዛኛው በሚባል መልኩ በችግር ወይም በእሳት ወቅት አይጥ እንደዋጠች ድመት ድምፁ የሚጠፋ ነው። በሚያምንበት የፖለቲካ አመለካከት በእሳት መሃል ተፈትኖ ማለፍ ይቅርና የእሳቱ ወላፈን እንዳያገኘው ራሱን የሚያርቅ ነው። አንዳንዱም ነገሮች ሲረጋጉ ወይም ድል ሲገኝ ከያለበት ጎሬ እየወጣ ይሉኝታ ቢስነትን መሳሪያ አድርጎ በነውሩ አጊጦ በሌሎች ድካምና ደም ቆምሮ ሊቆም የሚሞክረው ብልጥ ነን ባይ እዛም እዚህም ማየት የተለመደ ሆኗል።

ሌላው ቢቀር መስዋዕትነት የሚከፍሉ ሰዎች የሚገባቸውን ክብርና ቦታ ሊያገኙ ሲገባ ጭራሽ መስዋዕት የከፈሉለትን አላማ እንደስህተት እንዲቆጥሩ ሊያደርግ የሚችልን ባንዳ መር ግፊቶችን በፅናት ተቋቁሞ ነገሮችን መልክ ለማስያዝና ለአርበኞች የወደፊቱን ጊዜ ብሩህ ለማድረግ መስራት ከሁሉም የሚጠበቅ ነው።

አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ ።

ወይም

የጌሾው ወቀጣ ማንም ሰው አልመጣ
የመጠጡ ጊዜ ከየጎሬው ወጣ! እያልን ዛሬም ሆነ ነገን ዛሬ አድርገን እየቆዘምን ልንቀጥል ይገባል የሚል እምነት የለኝም።

በዘመቻ ሕልውና ወቅት በመንግስታዊ መዋቅሩ ውስጥ በኋላፊነት ያሉ ሰዎች የወያኔን ወረራ በመቃወም፣ ግፉን በማውገዝ፣ የአማራ ሕዝብ በአንድ ልብ ቆሞ አምርሮ እንዲታገል በሜንስትሪም ሚዲያው እየቀረቡ መልዕክት እንዲያስተላልፉ ሲጠየቁ ስልካቸውን እየዘጉ የጠፉ ሰዎች፣ ወያኔ ሊያሸንፍ ይችላል ብለው የጠራ አቋማቸውን ያላንፀባረቁ፣ ድምፃቸውን ያጠፉ አካላት፣ በድል ማግስት መልካቸውን ቀይረው በስመ የውስጥ አርበኛ መምጣታቸው የሚጠበቅ እንጅ የሚያስደንቅ አይሆንም።

ድንኳን ሰባሪነትን እንደክብር፣ የሌሊት ወፍነትን ወይም በአጥር ላይ መንጠልጠልን እንደ እውቀትና ጥበብ እንዲቆጠር የሚያደርግ ሁኔታ ተፈጥሯልና። የሃይል ሚዛኑ ሲታወቅ፣ ድሉ ሲበሰር፣ በስመ የወስጥ አርበኛ ወደፊት የመጡ ሰዎች በአርበኝነትና በአርበኞች መቃ*ብር ላይ ባንዳነትንና ባንዶችን እንዲነግሱ የሚያደርግ ነው።

ባንዳዎች ሲነግሱ በነገሮች ላይ የሚኖራቸው እይታ፣ የሚይዙት አቋምና የሚያደርጉት ትግል ከራሳቸው ሕልውና እና ጥቅም እንጅ ከአገር ሕልውና እና ከሕዝብ ጥቅም አንፃር አይደለም።
የባንዳዎች አስደናቂው ባሕርይ የአሳማነት፣ የአድርባይነትና የክህደት ጥግነታቸውን ለአርበኞች በመስጠት ራሳቸውን እንደአርበኛ እንዲቆጠሩ ለማድረግ መሽቀዳደማቸው ነው። ቀድመው እንዲያ ማድረግ ካልቻሉ ሊሞገሱና ሊነግሱ ቀርቶ በነፃነት በሕይወት ሊመላለሱ የሚችሉበት ዕድልም አነሳ ነውና!

በግልጽ በአማራ ላይ ሂሳብ እንዲወራረድ(የግፍ ግፍ እንዲፈፀም) ኢትዮጵያ እንድትፈርስ ከጠላት ጋር የተባበሩና ክህደታቸውን የገለፁ ሰዎች የጊዜ ጉዳይ እንጅ በመንጋው መወድስ ቢቀርብላቸውም ሆነ ቢነግሱ ያገኙት የስብዕና ግንባታ እንደ እንቧይ ካብ ነውና ማንም ሳይነካው መናዱ አያጠራጥርም።

ዛሬ በእሳት ለተፈተኑ ክብር ለሚገባቸው ሰዎች ክብር መስጠት ክብረ-ቢስ ነውረኞች ነገ ወደፊት መጥተው መንገድ እንዳይዘጉና እንቅፋት ሆነው አላስፈላጊ መስዋዕትነት እንዳይከፍል የሚያደርግ ነው።
መንጋ ማለት ሲተረጎም በእነዚህ ልጥፎቼ ላይ የተሰጡ አስተያየቶችን ብቻ በማየት ማወቅ ይችላል። ከተለጠፈው ወይም ከአውድ ውጭ ግብረ-መልስ ከመሰጠቱም በላይ ሁሌም ስድብ ነው። ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኞች ግብረ-ገብነት ለራሳቸው ክብር የሌላቸውና የአማራን እሴት ለመበረዝ የሚሰሩ ናቸው።
አማራ አማራ ነኝ እንዲልና በአማራ በኩል ልክ እንደ ኦነግና ሕወሓት ያለ ድርጅት ለማደራጀት ከለውጥ በፊት ጀምሮ ራሳቸውን በአማራ ብሔርተኝነት ውስጥ ማንነታቸውን ደብቀው በብዕር ስም ፅንፈኛ አማራ መስለው ይፅፉ የነበሩ በወያኔ የተመለመሉ ትግሬዎች፥ አሁን ላይ የተወሰኑት በሌሎች አካውንቶችና ገፆች በተለይ በሴት ስም አካውንት በመክፈት መንጋውን አማራው ተራራው በማለት ብቻ አማራ ሳይሆኑ አማራ መስለው ለማስጨፈርና መስመር ለማሳት የሚያደርጉትን ሙከራ ብዙሃኑ እየነቃ ቢሆንም አሁንም ጥቂት የማይባሉ ተከትለው የሚነጉድ ሰዎች መኖራቸው ግልፅ ነው።
የዘወትር አጀንዳቸው አንዱን ግለሰብ በማጀገን ሌላውን በማንኳሰስ የተመሰረተ ነው። ለአማራ ሕዝብ ጥቅም የሚታገሉትን ወይም ሊታገሉ ይችላሉ ብለው የሚያስቡትን ያንኳስሳሉ እንደከሃዲ እንዲቆጠር ይሰራሉ። በተቃራኒ ያለውን አካል ደግሞ ያጀግናሉ በመወድስም ያጥለቀልቃሉ።

በጣም የሚያሳዝነኝ ነብስ አላቸው የምትላቸው ሰዎች ፌክ አካውንት ነው ወይስ ማንነቱ የሚታወቅ ነው ብለው ሳይመረምሩ እንደወረደ አምነው አቋም የሚይዙት ነገር ነው።

አብዛኛው ኮሜንት የሚሰጠው በፌክ አካውንትም ነው። እስኪ እንጠይቅ እንመርምር!
Balance of power እንዲኖር በአገሪቱ የመጫወቻ ሕግ መሰረት የአማራን ሕዝብ ሁለንተናዊ ጥቅም ለማስከበር፣ ወያኔን በቋንቋው አናግረው ለመጣል፣ የአማራ ብሔርተኝነትን እንደጊዜያዊ የመፍትሔ መንገድ የመረጡ ነገር ግን መዳረሻቸው ኢትዮጵያዊነትን በፅኑ አለት ላይ መገንባት የሆኑ ጠንካራ የአማራ ልጆችን በተለያየ መንገድ እንደጠላት ቆጥሮ በዘመቻ የወገረው ከማንም በላይ ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ ነው።

ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኝነት የሚዲያ hegemony ስላለው ሊያስከፍል የሚችለውን አላስፈላጊ መስዋዕትነት መናቅ ተገቢ አይደለም። መንጋውን አሁንም እንደፈለገ የማስጨፈር እድሉ ገና በእጁ ነው ያለው። ስራ ያስፈልጋል!
በአማራ ክልል የሕግ ማስከበር እርምጃ መውሰድ ከተጀመረ በኋላ ማታ ማታ በአንዳንድ አካባቢዎች ቀን ጭምር ይሰማ የነበረው የጥይት የተኩስ ድምፅ ሙሉ በሙሉ ቆሟል። ሕዝቡ ያለምንም ስጋት በሰላም ወጥቶ በሰላም መግባት ጀምሯል። ሕዝቡ በስርዓት አልበኞች ምን ያህል የደህንነት ስጋት ውስጥ እንደነበረ የሚታወቅ ነበር። በሕዝቡ ተደጋጋሚ ጥያቄና መሪነት ከመንግስት የፀጥታ አካላትና ከትክክለኛ ፋኖዎች ጋር በተደረገ የተቀናጀ የሕግ ማስከበር ዘመቻ በተለይ ሰላም ከማስፈን አንፃር ከታዬ የሕግ ማስከበር ኦፕሬሽኑ ውጤታማ ሆኗል ማለት ይቻላል። በሁሉም አካባቢ ሰላማችንን አገኘን የማይለውና ለዘላቂ ሰላሙ ለፍትህ መስፈን የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ መንግስት የጀመረውን ሕግ የማስከበር እርምጃ የማይደግፍና የማይተባበር ኮንትሮባንዲስትና የወያኔ የማደጎ ልጅ ካልሆነ በስተቀር ከሰላም ወዳድና ሕግ አክባሪ ዜጎች መካከል ሌላ ስም ተሰጥቶት የሚቃወሙ አንድም ሰው በባትሪ ፈልጎ ማግኘት አይቻልም።

ሰላም ለሁላችን!
የወያኔ የፊት ደጀን እየወላለቀና እየተበታተነ መምጣቱ በቀጣይ ወያኔን በቀላሉ ለማንበርከክ ወይም በራሱ ጊዜ እጅ እንዲሰጥ የሚያስችል ይሆናል።
እንኳን ደስ አለን!

እናት ኢትዮጵያ በእግር ኳሱ የግብፅን መረብ እንደሞላሽውና ድልን እንደተቀዳጀችው ሁሉ ታላቁ የሕዳሴ ግድባችን በመሙላት አንፀባራቂ ድሎችን ታስመዘግባለች። የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የከፍታና ብሩህ ዘመን እየመጣ ነው!
የኢትዮጵያ አሁናዊና ቀጣይ ሁኔታ‼️
በኢትዮ-360 ይቅርታ በግብፅ-360 ላይ ሰው ሁሉ ነቅቶባቸዋል ብቻ ሳይሆን እንደጉድ ይቀልድባቸዋል የሚለው አይገልጸውም፤ ምን መሰለሽ እየሩስ?😂
By Addis Mekonnen

ኤርሚያስ ለገሰ በስልጣን ዘመኑ ክርስቲያኖችንና ሙስሊሞችን ለማጋጨት አንዴ ሙስሊም መስሎ የጥምቀት ቦታ ሲያሳጥር፣ ሌላ ጊዜ ክርስቲያን መስሎ የመስጊድ አጥር ሲያስፈርስ የሰራውን ሃጢያት ተናዝዞ፣ ይቅርታ ጠይቆ ነወይ ዛሬ የኢትዮጵያ ጠበቃ ሆኖ የመጣው?

ደግሞ ተሳስቶ ደብረ ፂዮንና ጌታቸው ረዳን ሲተች አይታይም። ጌታቸው ሲደነፋ አይናገረውም። ህወሃት አማራና አፋርን ወርሮ እንዲያ ግፍ ሲፈፅም ይሄ ጦርነት አማራን አይመለከትም ብሎ ሊያስበላን የነበረ ሰው ዛሬ ጠበቃችሁ ነኝ እያለን ነው።

ዛሬም ህወሃት አማራና አፋርን ሊወጋ ሲዘጋጅ ፈፅሞ "መንግስት ለዚህ ምላሽ ተዘጋጅቷል ወይ?" ብሎ ሲተች ሰምቼው አላውቅም።

ሞኝህን ፈልግ ባክህ!!

ይሄን መርዘኛ የመኖሪያ ወረቀት ካላገኘ አግዙት!!

(ከስር የሚሰጡ ስድቦች ሂዊ የመደበቻቸው አካውንቶች መሆናቸውን ተረድተን የብሎክ ሰይፍ እንመዛለን)
በሐሩርና በቁሩ በጋራ ሸንተሩ ስለሕዝቡ ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ስለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት መከበር ስለምታደርጉት ተጋድሎ ስለምትከፍሉት መስዋዕትነት ሁሉ ታላቅ ክብር ይገባችኋል‼️

የእናት ኢትዮጵያ ዘብና አለኝታ ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ሰሞናዊ ሁኔታው!
ዳኛው ወዶም ተገዶም ነው "ያለም ወርቅ አንች እኮ ሙዚቃ ነሽ ፤ አንችን በመዳኜቴ እድለኛ ነኝ፤ ልቤም ዞረ ... ያለው"። የባለፈው ሳምንቱን ብቃቷንም ነው ዛሬ የደገመችው።

የዓለም - ወርቅ!
በእርግጠኝነት
ወርቁ ያንቺ ነው፤እንኳን ደስ ያለሽ‼️
ዘማቹ ባለሃብት ለፋና ላምሮት ክስተቶች የ60,000 ብር የገንዘብ ስጦታ አበረከተ
***
አቶ አማረ ባይነሳኝ ዘውዴ ይባላል። መናገሻ ጎንደር ከተማ ውስጥ "ታኦስ የባህል ምሽት" ባለቤት ነው። በሰላም ጊዜ ነጋዴ በጭንቅ ጊዜ ዘማች ፋኖ ነው።

ወደመናገሻ ጎንደር የሚመጡ የአገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች የምሽት ክለቡን ሳይረግጡ አይመሰለሱም።

የአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ጉራጌኛ፣ ወላይትኛ፣ አፋርኛ፣ ሶማሊኛ፣... የባህል ሙዚቃዎችን ከነቱባ አቀራረቡ ደምቀው የሚቀርቡበት ታዋቂ ባህላዊ የምሽት ክለብ ነው።

ጎንደር እግሩ የረገጠ ቱሪስት ታኦስ ላይ ኢትዮጵያዊ የባህል ቡፌ ይቀርብለታል።

የፋና ላምሮት ክስተት የሆኑት ያለምርቅ ጀምበሩ እና ደሳለኝ አበበ፣ ታኦስ የባህል ምሽት የሚሰሩ የጥበብ ፈርጦች ናቸው።

የታኦስ የባህል ምሽት ባለቤት አማረ ባይነሳኝ ልጆቹ ለዚህ ስኬት በመብቃቸው ለሁለቱም በድምሩ የስልሳ ሺህ ብር የገንዘብ ስጦታ አበርክቷል።

በቀጣይ የጥበብ ሥራ ጉዟቸውም ከጎናቸው በመሆን ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል ቃል ገብቷል።

አቶ አማረ ባይነሳኝ በህልውና ዘመቻው ወቅት በጋሸናና በማይጠምሪ ግንባር በመዝመት የትግሬ ወራሪን ያሳደደ አርባ ጎራሽ አንጋች፣ ትጥቅ አሳማሪ አልሞ ተኳሽ ዘማች ፋኖ ነው። ጋሳይ ላይ በነበረው ጦርነት 12 ሳጥን የጠላት ጥይት አግንቶ በጀኔራል ደስታ (ያኔ ኮሎኔል) ለምትመራው 33ኛ ክፍለ ጦር በማስረከብ በግንባሩ የዘመቻ ኮር አመራሮች እውቅና ያገኘ ሀገር ወዳድ ዘማች ፋኖ ነው።

በጎንደርና አካባቢው ባሉ የማህበራዊ በጎ አድራጎት ተግባራት በቀዳሚነት ስሙ የሚጠቀሰው ዘማቹ ባለሃብት አማረ ባይነሳኝ ትላንትም ሆነ ዛሬ ለሚያደርጋቸው የበጎ አድራጎት ስራዎቹ ሁሉ እናመሰግናለን🙏

የፋና ላምሮት ክስተት ለሆኑት
ያለም ወርቅ ጀምበር እና
ደሳለኝ አበበ

ለዚህ ስኬት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ። በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ኮከብ ሆናችሁ እንደምትወጡ አንጠራጠርም👌

🎼 🎹 🎷 🎸 🎶 🎵