Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.45K subscribers
2.98K photos
370 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
በኤሊዳአር ከተማ ላይ የተነሳውን ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ ከደረሰው በላይ ከፍተኛ ውድመት እንዳይደርስ የጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን አባላት ከሕዝባችን ጋር በመቀናጀት የእሳት ቋጠሮውን ለመቆጣጠር ተችሏል።

ክብር የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ነፃነት ለመጠበቅ የሕዝቦቿን ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ለማስከበር ያለ እረፍት በረመጥ መካከል ለሚያልፉ ጀግኖቻችን ይሁን‼️
ኢትዮጵያን ለማፍረስ የባንዳ ባንዳ ሆነው በሐገር ውስጥና በባህርማዶ ለወያኔ መንገድ ለመጥረግ፣ መንገድ ለመምራት በተለያዬ መንገድ ተደራጅተው ከፊት ተሰልፈው ሲንቀሳቀሱ ለነበሩ የእፍኝት ልጆች ወደግንባር ከመዝመታችን በፊት ይልን መልዕክት አስተላልፈንላቸው ነበር። ምንም እንኳን ፊት ለፊት የሚያቆም አቅሞና ልብ ባይኖራውም በግንባር የግብር አባታቸውን ወያኔን አሰልፈው በጀርባ በኩል ደግሞ እነሱ ተሰልፈው ያለ የሌለ አቅማቸውን ተጠቅመው ሊወጉንና ሊያጠቁን ኢትዮጵያንም ሊያፈርሱ ቢሞክሩም አልተቻላቸውም። በተባበረው ክንዳችን ተንበርክከዋል። እኛ ኢትዮጵያዊያንን ሊቋቋሙን አልቻሉም። በሕልውና ዘመቻው ያንበረከክነውን ሃይል ነብስ ሊዘሩበት ከውስጥ በኩል የተለያዩ ግንባሮችን ሊከፍቱ ከጀርባ በኩል ጥቃት ሊከፍቱ ያሰፈሰፉትን በሐገር ቤት በአማራ ስም በተለያዬ የአደረጃጀት ቅርፅ በሕቡዕም በግላጭም የሚንቀሳቀሱትን የወያኔ መንገድ ጠራጊ መንገድ መሪዎችን በተጀመረው የሕግ ማስከበር ዘመቻ አላማቸው እየተንኮላሸ ይገኛል። ሕጋዊ እርምጃው የነገን የጀርባን ጥቃት ከመከላከል ባሻገር የሕዝቡን ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ለማስከበር የሚያግዝ የተዋጣለት ኦፕሬሽንም ነው እየተካሄደ የሚገኘው። በዚህ አጋጣሚ በሕግ ማስከበር ኦፕሬሽን የተሰማሩ ዲስፕሊንድ የሆኑ የፀጥታ አካላት ምስጋና ይገባቸዋል።

ወደቀደመ ሐሳባችን ስንመለስ በአማራ ስም በተለያዩ የሲቪክ ማህበራትና የሚዲያ ተቋማት ሽፋን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ለወያኔ መንገድ ሲጠርጉ የነበሩ የወያኔ የማደጎ ልጅነታቸውን በግብር የገለጡ በተለይም በዲያስፖራ በኩል ያሉ አካላትን ጭንብላቸውን የመግለጥ ስራዎች አሁንም ብዙ የሚቀር ቢሆንም የማድረግ አቅማቸውን ከተመለከተን ግን በራሳቸው የትም መድረስ የሚያስችል ከአቧራው ጨሰ ልፈፋ ያለፈ ሕዝባዊ መሰረት ያለው የፖለቲካ ተክለ ስብዕና የማድረግ አቅምም የሌላቸው መሆናቸውን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል።

በአማራ ስም በዲያስፖራው በኩልም ሆነ በሐገር ቤት ውስጥ የተለያዬ ቅርፅ ባለው በሕቡዕም ሆነ በግልፅ አደረጃጀት(ቤተክርስቲያንም ሆነ መስጊድን ጭምር ለመጠቀም )የሚንቀሳቀሰው የወያኔ መንገድ ጠራጊ ሃይል ትልቁ ጉልበቱ የሚነመጨው(አንዳንዶቹ አደረጃጀቶችም የተመሰረቱት) በመንግሥት መዋቅር እና በብልፅግና ውስጥ አገር ለማፍረስ መረጃ አሳልፎ የሚሰጠው፣ ከውጭ ሐይሎች ጋር በመቀናጀት ሲንቀሳቀስ የቆየው፣ በአማራ ላይ ሂሳብ እንዲወራረድበት (የግፍ ግፍ እንዲፈፀምበት) ለወያኔ መንገድ ሲጠርግና መንገድ ሲመራ የነበረው፣ አሁንም በዛው ግብር መልኩን እየቀያየረ የቀጠለው የወንጀል የተጠያቂነት ስጋት ያለበት፣ በብልፅግና ውስጥ ያለው ያልበለፀገው አፍቃሬ ወያኔ ነው። በአማራ ስም በሐገር ቤትና በባህርማዶ የሚንቀሳቀሰው የወያኔው የአማርኛ ክንፍ ከመንግስት መዋቅራዊ ድጋፍ እስካላገኘ ድረስ ብቻውን በራሱ መቆም የማይችል ነብስ የሌለው ሃይል ነው። የሕልውና መሰረቱ መንግስታዊ መዋቅሩ ነው።

ዶ/ር አብይ አህመድ በመንግስታዊ መዋቅሩና በብልፅግና ውስጥ ያሉ አፍቃሬ ወያኔ አገር አፍራሾችን እየለቀመ ወደሚገባቸው ቦታ ሊሸኛቸው እንጅ እንደተለመደው ሊንቃቸው አይገባም። አማራንም ሆነ ኢትዮጵያን አላስፈላጊ መስዋዕትነት ያስከፈላት ወደፊትም ሊያስከፍላት የሚችለው ከማንም በላይ በመንግስታዊ መዋቅሩ እና በብልፅግና ውስጥ ያሉ የወያኔ የግብር ልጆች ናቸው።

እነዚህ ልቡሳነ ስጋዎች ደግሞ መቼም ቢሆን ከመንግስታዊ መዋቅሩም ሆነ ከድርጅቱ በራሳቸው ፈቃድ ሊነጠሉ ስለማይችሉ(የጥፋት አላማቸውን የሚያሳኩበት ትክክለኛ ቦታ ላይ ስለሆኑ) ዶ/ር አብይ አህመድ ሁሉንም ጥፋት ደጋሾችን በመለቃቀም ወደሚገባቸው ቦታ ካልሆነም ሲፈልጉ አቅምና ልብ አለን ካሉ፣ ተከዜን እንዲሻገሩ ከግብር አባታቸው ከወያኔ ጋር ተሰልፈው ለጦርነትም ይሁን ለድርድር ኢትዮጵያን እንዲገጥሙ ማመቻቸት እንጅ በመንግሥት መዋቅር ውስጥና በብልፅግና ውስጥ ሆነው የውጭ ባዳንና ወያኔን መንገድ እየጠረጉ፣ መንገድ እየመሩ ኢትዮጵያን እንዲያደሟት ከቻሉ እንዲያፈርሷት ነገሮች ሊመቻቹላቸው ፈፅሞ አይገባም። ይህን አለማድረግ በራሱ በሌላ መንገድ አገር ለማፍረስ እንደመተባበር የሚቆጠርም ይሆናል‼️

ፅዳት መጀመር ያለበት ከራስም ነው ለማለት እንወዳለን‼️
ግልፅ ለማድረግ ያህል!

የእኔ የትኩረት ማዕከል ከትናንት እስከዛሬ ጥቅሜ ተነካብኝ ብሎ አገር ለማፍረስ በተለያዬ መንገድ በሚንቀሳቀሰው መዋቅራዊ ጉልበት ባለው አካል ላይ ብቻ ነው። መዋቅራዊ ጉልበት የሌለው የትኛውም ግለሰብም ሆነ ቡድን ፈፅሞ አጀንዳዬ ሆኖ አያውቅም። እስካሁን ከማንም ጋር የግል ፀብ ኖሮብኝ በስሜትና ሌላ ሽፋን በመስጠት የምፅፈው አንዳችም ጉዳይ የለም። ማንም ሰው የምፅፈውን የትኛውንም ፅሑፍ ወደራሱ ፍላጎትና ወደሚያስበው ጉዳይ ከአውድ ውጭ እንደፈለገ ሊተረጉመው ግን ይችላል። ለእኔ የሰዎች ትርጉም ጉዳዬ አይደለም። አይሆንምም።

እውነት ላይ እስከቆምን ድረስ የመንጋውን የስሜት ፈረስ ውሸትን አንበርክከን መንጋ አዝማቾችን እርቃናቸውን ማስቀረታችን የማይቀር ጉዳይ ነው። በሐቅ ለፍትህ ለነፃነትና ለእኩልነት እንጅ በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ትግል አልጀመርንም። ለማንም ግለሰብም ሆነ ቡድን ጥላቻ የለንም። ጥላቻ ካንሰር ነውና ወደፊትም በውስጣችን ይኖር ዘንድ አንፈቅድለትም።
አገር ለማፍረስ መዋቅራዊ ድጋፍ ያለውን አካል በቻልነው ልክ እኩይ አስተሳሰቡን ለመዋጋት ግን መቼም ቢሆን አንቦዝንም‼️
በአማራ ክልል በሁሉም አካባቢዎች በሕግ ማስከበር ዘመቻ መንግስት ለሐገራቸውና ለሕዝባቸው ሲሉ በጦርነቱ መስዋዕትነት በከፈሉ፣ ሕግና ስርዓትን አክብረው በሚንቀሳቀሱ ፋኖዎች ላይ እስካሁን እጁን አላነሳም። ለሐገር ሉዓላዊነትና ለሕብረተሰቡ ሰላም ዘብ የቆሙና የሚቆሙ ፋኖዎች በመንግሥት ካሉት የፀጥታ አካላት መካከል እንደ አንዱ የሚቆጥራቸው የሕዝብ ልጅ ናቸውና እንደ አይኑ ብሌን የሚጠብቃቸው እንጅ የሚያሳድዳቸው ወይም እርምጃ ሊወስድባቸው የሚችልባቸው አይደሉም። በሕግ ማስከበር ዘመቻው ከመንግሥትና ከሕዝብ ጎን ሆነው ሕገ-ወጦችን በሕግ ጥላ ስር ለማዋል አስፈላጊውን ትብብር እያደረጉ የሚገኙት ፋኖዎች ጭምር መሆናቸው መታወቅ አለበት።

መንግስት ሕግ ለማስከበር እጁን ያነሳው በፋኖ ሽፋን መንግስት በሚያስተዳድረው ለዛውም ከተማ ላይ መንደር ለመንደር ጠብ-መንጃ ስላወዛወዙና በመንግስት መዋቅር ውስጥ ጥቅማቸው የተነካባቸው ሰዎች እግረኛ ወታደር ስለሆኑ ብቻ አንዴ "መንግስት የለም፣ሌላ ጊዜ ደግሞ ቢኖርም የተዳከመ ነውና በትጥቅ እናፈርሰዋለን" እያሉ በመንግሥት ላይ ሕወሓትን በሚያስንቅ ሁኔታ ሲዝቱና ሲፎክሩ በነበሩ ስርዓት አልበኝነት እንዲነግስ፣ ወያኔ እንዲመለስ በወሎ በጎንደር በጎጃም በሸዋ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኮንትሮባንዲስቶች አፈ-ጦረኞች ላይ ብቻ ነው።

በእነኚህ አፈ-ጦረኞች የወያኔ ፈረሶች ላይ ደግሞ መንግስት ገና "የሕግ የበላይነትን እናስከብራለን" ብሎ የፀጥታ ሐይሉን ለማንቀሳቀስ ትዕዛዝ በሰጠበት ቅፅበት አብዛኞቹ እምጥ ይግቡ ስምጥ ወይም እንደ ደመና ይትነኑ ወይም የሆነ ቦታ ረግተው ይደበቁ የሚያውቅ ቢያውቅም፤ መንጋው ግን ባትሪ ይዞ ፍለጋ ከወጣ ቀናቶች ተቆጥረዋል።

የመንግስትነትን ትርጉም በቅጡ የማያውቁ የመንደር አውደልዳዮች፣ ሳይዋጉ ጦርነት የሰለቻቸውና የተሰለበ አዕምሮና ማንነት ያላቸው ተንበርካኪዎች፣ ከዚህ በፊት በየአደባባዩ ' መንግስት ተብዮው ሆይ! አለቀልህ! አንለቅህም የትም ብትገባ! ' እያሉ ሲያቅራሩ የነበሩ ዘባተሎ ኮንትሮባንዲስቶች ያላቸው የመጨረሻ ምርጫ አገር የሕልውና አደጋ በገጣማት ወቅት የሕዝብን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ከያሉበት በፋኖ ስም ተሰባስበው አላስፈላጊ መስዋዕትነት ለማስከፈል የተወራጩ በሙሉ ከወዲሁ ይቅርታ በመጠየቅ ንስሓ ሊገቡ ይገባል። እነዚህ የወያኔ መንገድ ጠራጊ ባንዳዎች ሕዝብንና መንግስትን ይቅርታ ጠይቀው ምህረት እስካላገኙ ድረስ የትም ቢገቡ ወይም ቢጠለሉ ፈፅሞ ከተጠያቂነት ሊያመልጡ የሚያስችል አንዳችስ እንኳን እድል የላቸውም።

በሕግ ማስከበር ዘመቻው እስካሁን መንግስት ያሳደደው ወይም ያፈነው አንድም የሕዝብ ልጅ የሐገር አለኝታ ፋኖ የለም።
"መከላከያ ባይኖር እንኳን ሕወሓትን ምስራቅ አፍሪካን በቀናነት እንቆጣጠራለን" እያለ ሲበጠረቅ የነበረ ፤ ጦርነት ምን እንደሆነ፣ ውጊያ ገብቶ የማያውቀው ብቻ ሳይሆን ክላሽ ይዞ ጥይት ወደሰማይ ተኩሶ የማያውቀው ሁሉ ነበር በተለይ ምስጊኑን የአማራን ዲያስፖራ ሜካናይዝድ ጦር እንዳደራጀ አማራ ሆኖ ሲሸልልና ሲያቅራራ የከረመው።

በነገራችን ላይ በየከተማው ለቦርጭ ቅነሳና ለአግላይነት "ቁጭ ብድግ!" ሲሰሩ የነበሩ ሰዎች (ወደበኋላ በወከባ ፋኖ የሆኑ ሰዎች ) መጀመሪያ አካባቢ የአማራ ክልል መንግስት እስከቀበሌ ድረስ ያለ ወጣት እንዲሰለጥን ባስተላለፈው መመሪያ መሰረት እንዲሰለጥኑ ከተሰጠው አቅጣጫ በዲጂታል ወያኔ ፕሮፖጋንዳ መስመር የሳቱ ሰዎች ናቸው ።

እነኚህ በየከተማው "ቁጭ ብድግ" ሲሉ የነበሩ ሰዎች እየቆዩ ሲሄዱ መንደራቸውን ሳይለቁ የትም ግንባር ላይም ሳይሳተፉ የሁሉንም አውደ ውጊያዎችን ድል ያለምንም ጦርነት መቀዳጀት የቻሉ በዓለም ታሪክ የመጀመሪያዎቹ ፈር ቀዳጆች የመሆን እድል ይኖራቸዋል። የሁሉም ጦርነት ድል አድራጊ ነን ባዮቹ አብዛኞቹ "ቁጭ ብድግ!" የሰሩት ራሱ ጦርነቱ ከተጠናቀቀ በኋላ መሆኑንስ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን?!
ስንት ጀግኖች እናት አገራቸውን ለመታደግ የሕዝባቸውን ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ለማስከበር ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉበትን ጦርነት ማንም የቤት ሙሴ የመንደር አውደልዳይና የባንዳ ባንዳ ከድል ማግስት ነውሩን ጌጥ አድርጎ አርበኛ አርበኛ ሊጫወት ቢሞክርም ዝም ሊባል ግን አይገባውም።
በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ፖለቲካ ለታላቁ የአማራ ሕዝብ ሁለንተናዊ ጥቅም መረጋገጥ፤ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ክብር መጠበቅ፣ እንደ ቡና በብረት ምጣድ በእሳት የተቆሉ አረፍን ሲሉ በሙቀጫ የተወቀጡ ተመልሰው በበራድ እሳት ላይ የተጣዱና የተንተከተኩ በፖለቲካ ውስጥ የሚሳተፉ ሰዎች ጥቂት ናቸው። ብዙሃኑ ምቾቱን ጠብቆ በተዋበ ሮኮቦት የድግሱ ሰዓት በኩራት እያብለጨለጨ እንደሚወጣ ስኒ (ፍንጃል) ነው።

አሁን ባለው በአማራ ፖለቲካ ውስጥ የሚሳተፈው አብዛኛው በሚባል መልኩ በችግር ወይም በእሳት ወቅት አይጥ እንደዋጠች ድመት ድምፁ የሚጠፋ ነው። በሚያምንበት የፖለቲካ አመለካከት በእሳት መሃል ተፈትኖ ማለፍ ይቅርና የእሳቱ ወላፈን እንዳያገኘው ራሱን የሚያርቅ ነው። አንዳንዱም ነገሮች ሲረጋጉ ወይም ድል ሲገኝ ከያለበት ጎሬ እየወጣ ይሉኝታ ቢስነትን መሳሪያ አድርጎ በነውሩ አጊጦ በሌሎች ድካምና ደም ቆምሮ ሊቆም የሚሞክረው ብልጥ ነን ባይ እዛም እዚህም ማየት የተለመደ ሆኗል።

ሌላው ቢቀር መስዋዕትነት የሚከፍሉ ሰዎች የሚገባቸውን ክብርና ቦታ ሊያገኙ ሲገባ ጭራሽ መስዋዕት የከፈሉለትን አላማ እንደስህተት እንዲቆጥሩ ሊያደርግ የሚችልን ባንዳ መር ግፊቶችን በፅናት ተቋቁሞ ነገሮችን መልክ ለማስያዝና ለአርበኞች የወደፊቱን ጊዜ ብሩህ ለማድረግ መስራት ከሁሉም የሚጠበቅ ነው።

አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ ።

ወይም

የጌሾው ወቀጣ ማንም ሰው አልመጣ
የመጠጡ ጊዜ ከየጎሬው ወጣ! እያልን ዛሬም ሆነ ነገን ዛሬ አድርገን እየቆዘምን ልንቀጥል ይገባል የሚል እምነት የለኝም።

በዘመቻ ሕልውና ወቅት በመንግስታዊ መዋቅሩ ውስጥ በኋላፊነት ያሉ ሰዎች የወያኔን ወረራ በመቃወም፣ ግፉን በማውገዝ፣ የአማራ ሕዝብ በአንድ ልብ ቆሞ አምርሮ እንዲታገል በሜንስትሪም ሚዲያው እየቀረቡ መልዕክት እንዲያስተላልፉ ሲጠየቁ ስልካቸውን እየዘጉ የጠፉ ሰዎች፣ ወያኔ ሊያሸንፍ ይችላል ብለው የጠራ አቋማቸውን ያላንፀባረቁ፣ ድምፃቸውን ያጠፉ አካላት፣ በድል ማግስት መልካቸውን ቀይረው በስመ የውስጥ አርበኛ መምጣታቸው የሚጠበቅ እንጅ የሚያስደንቅ አይሆንም።

ድንኳን ሰባሪነትን እንደክብር፣ የሌሊት ወፍነትን ወይም በአጥር ላይ መንጠልጠልን እንደ እውቀትና ጥበብ እንዲቆጠር የሚያደርግ ሁኔታ ተፈጥሯልና። የሃይል ሚዛኑ ሲታወቅ፣ ድሉ ሲበሰር፣ በስመ የወስጥ አርበኛ ወደፊት የመጡ ሰዎች በአርበኝነትና በአርበኞች መቃ*ብር ላይ ባንዳነትንና ባንዶችን እንዲነግሱ የሚያደርግ ነው።

ባንዳዎች ሲነግሱ በነገሮች ላይ የሚኖራቸው እይታ፣ የሚይዙት አቋምና የሚያደርጉት ትግል ከራሳቸው ሕልውና እና ጥቅም እንጅ ከአገር ሕልውና እና ከሕዝብ ጥቅም አንፃር አይደለም።
የባንዳዎች አስደናቂው ባሕርይ የአሳማነት፣ የአድርባይነትና የክህደት ጥግነታቸውን ለአርበኞች በመስጠት ራሳቸውን እንደአርበኛ እንዲቆጠሩ ለማድረግ መሽቀዳደማቸው ነው። ቀድመው እንዲያ ማድረግ ካልቻሉ ሊሞገሱና ሊነግሱ ቀርቶ በነፃነት በሕይወት ሊመላለሱ የሚችሉበት ዕድልም አነሳ ነውና!

በግልጽ በአማራ ላይ ሂሳብ እንዲወራረድ(የግፍ ግፍ እንዲፈፀም) ኢትዮጵያ እንድትፈርስ ከጠላት ጋር የተባበሩና ክህደታቸውን የገለፁ ሰዎች የጊዜ ጉዳይ እንጅ በመንጋው መወድስ ቢቀርብላቸውም ሆነ ቢነግሱ ያገኙት የስብዕና ግንባታ እንደ እንቧይ ካብ ነውና ማንም ሳይነካው መናዱ አያጠራጥርም።

ዛሬ በእሳት ለተፈተኑ ክብር ለሚገባቸው ሰዎች ክብር መስጠት ክብረ-ቢስ ነውረኞች ነገ ወደፊት መጥተው መንገድ እንዳይዘጉና እንቅፋት ሆነው አላስፈላጊ መስዋዕትነት እንዳይከፍል የሚያደርግ ነው።
መንጋ ማለት ሲተረጎም በእነዚህ ልጥፎቼ ላይ የተሰጡ አስተያየቶችን ብቻ በማየት ማወቅ ይችላል። ከተለጠፈው ወይም ከአውድ ውጭ ግብረ-መልስ ከመሰጠቱም በላይ ሁሌም ስድብ ነው። ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኞች ግብረ-ገብነት ለራሳቸው ክብር የሌላቸውና የአማራን እሴት ለመበረዝ የሚሰሩ ናቸው።
አማራ አማራ ነኝ እንዲልና በአማራ በኩል ልክ እንደ ኦነግና ሕወሓት ያለ ድርጅት ለማደራጀት ከለውጥ በፊት ጀምሮ ራሳቸውን በአማራ ብሔርተኝነት ውስጥ ማንነታቸውን ደብቀው በብዕር ስም ፅንፈኛ አማራ መስለው ይፅፉ የነበሩ በወያኔ የተመለመሉ ትግሬዎች፥ አሁን ላይ የተወሰኑት በሌሎች አካውንቶችና ገፆች በተለይ በሴት ስም አካውንት በመክፈት መንጋውን አማራው ተራራው በማለት ብቻ አማራ ሳይሆኑ አማራ መስለው ለማስጨፈርና መስመር ለማሳት የሚያደርጉትን ሙከራ ብዙሃኑ እየነቃ ቢሆንም አሁንም ጥቂት የማይባሉ ተከትለው የሚነጉድ ሰዎች መኖራቸው ግልፅ ነው።
የዘወትር አጀንዳቸው አንዱን ግለሰብ በማጀገን ሌላውን በማንኳሰስ የተመሰረተ ነው። ለአማራ ሕዝብ ጥቅም የሚታገሉትን ወይም ሊታገሉ ይችላሉ ብለው የሚያስቡትን ያንኳስሳሉ እንደከሃዲ እንዲቆጠር ይሰራሉ። በተቃራኒ ያለውን አካል ደግሞ ያጀግናሉ በመወድስም ያጥለቀልቃሉ።

በጣም የሚያሳዝነኝ ነብስ አላቸው የምትላቸው ሰዎች ፌክ አካውንት ነው ወይስ ማንነቱ የሚታወቅ ነው ብለው ሳይመረምሩ እንደወረደ አምነው አቋም የሚይዙት ነገር ነው።

አብዛኛው ኮሜንት የሚሰጠው በፌክ አካውንትም ነው። እስኪ እንጠይቅ እንመርምር!
Balance of power እንዲኖር በአገሪቱ የመጫወቻ ሕግ መሰረት የአማራን ሕዝብ ሁለንተናዊ ጥቅም ለማስከበር፣ ወያኔን በቋንቋው አናግረው ለመጣል፣ የአማራ ብሔርተኝነትን እንደጊዜያዊ የመፍትሔ መንገድ የመረጡ ነገር ግን መዳረሻቸው ኢትዮጵያዊነትን በፅኑ አለት ላይ መገንባት የሆኑ ጠንካራ የአማራ ልጆችን በተለያየ መንገድ እንደጠላት ቆጥሮ በዘመቻ የወገረው ከማንም በላይ ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ ነው።

ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኝነት የሚዲያ hegemony ስላለው ሊያስከፍል የሚችለውን አላስፈላጊ መስዋዕትነት መናቅ ተገቢ አይደለም። መንጋውን አሁንም እንደፈለገ የማስጨፈር እድሉ ገና በእጁ ነው ያለው። ስራ ያስፈልጋል!
በአማራ ክልል የሕግ ማስከበር እርምጃ መውሰድ ከተጀመረ በኋላ ማታ ማታ በአንዳንድ አካባቢዎች ቀን ጭምር ይሰማ የነበረው የጥይት የተኩስ ድምፅ ሙሉ በሙሉ ቆሟል። ሕዝቡ ያለምንም ስጋት በሰላም ወጥቶ በሰላም መግባት ጀምሯል። ሕዝቡ በስርዓት አልበኞች ምን ያህል የደህንነት ስጋት ውስጥ እንደነበረ የሚታወቅ ነበር። በሕዝቡ ተደጋጋሚ ጥያቄና መሪነት ከመንግስት የፀጥታ አካላትና ከትክክለኛ ፋኖዎች ጋር በተደረገ የተቀናጀ የሕግ ማስከበር ዘመቻ በተለይ ሰላም ከማስፈን አንፃር ከታዬ የሕግ ማስከበር ኦፕሬሽኑ ውጤታማ ሆኗል ማለት ይቻላል። በሁሉም አካባቢ ሰላማችንን አገኘን የማይለውና ለዘላቂ ሰላሙ ለፍትህ መስፈን የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ መንግስት የጀመረውን ሕግ የማስከበር እርምጃ የማይደግፍና የማይተባበር ኮንትሮባንዲስትና የወያኔ የማደጎ ልጅ ካልሆነ በስተቀር ከሰላም ወዳድና ሕግ አክባሪ ዜጎች መካከል ሌላ ስም ተሰጥቶት የሚቃወሙ አንድም ሰው በባትሪ ፈልጎ ማግኘት አይቻልም።

ሰላም ለሁላችን!
የወያኔ የፊት ደጀን እየወላለቀና እየተበታተነ መምጣቱ በቀጣይ ወያኔን በቀላሉ ለማንበርከክ ወይም በራሱ ጊዜ እጅ እንዲሰጥ የሚያስችል ይሆናል።
እንኳን ደስ አለን!

እናት ኢትዮጵያ በእግር ኳሱ የግብፅን መረብ እንደሞላሽውና ድልን እንደተቀዳጀችው ሁሉ ታላቁ የሕዳሴ ግድባችን በመሙላት አንፀባራቂ ድሎችን ታስመዘግባለች። የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የከፍታና ብሩህ ዘመን እየመጣ ነው!
የኢትዮጵያ አሁናዊና ቀጣይ ሁኔታ‼️
በኢትዮ-360 ይቅርታ በግብፅ-360 ላይ ሰው ሁሉ ነቅቶባቸዋል ብቻ ሳይሆን እንደጉድ ይቀልድባቸዋል የሚለው አይገልጸውም፤ ምን መሰለሽ እየሩስ?😂
By Addis Mekonnen

ኤርሚያስ ለገሰ በስልጣን ዘመኑ ክርስቲያኖችንና ሙስሊሞችን ለማጋጨት አንዴ ሙስሊም መስሎ የጥምቀት ቦታ ሲያሳጥር፣ ሌላ ጊዜ ክርስቲያን መስሎ የመስጊድ አጥር ሲያስፈርስ የሰራውን ሃጢያት ተናዝዞ፣ ይቅርታ ጠይቆ ነወይ ዛሬ የኢትዮጵያ ጠበቃ ሆኖ የመጣው?

ደግሞ ተሳስቶ ደብረ ፂዮንና ጌታቸው ረዳን ሲተች አይታይም። ጌታቸው ሲደነፋ አይናገረውም። ህወሃት አማራና አፋርን ወርሮ እንዲያ ግፍ ሲፈፅም ይሄ ጦርነት አማራን አይመለከትም ብሎ ሊያስበላን የነበረ ሰው ዛሬ ጠበቃችሁ ነኝ እያለን ነው።

ዛሬም ህወሃት አማራና አፋርን ሊወጋ ሲዘጋጅ ፈፅሞ "መንግስት ለዚህ ምላሽ ተዘጋጅቷል ወይ?" ብሎ ሲተች ሰምቼው አላውቅም።

ሞኝህን ፈልግ ባክህ!!

ይሄን መርዘኛ የመኖሪያ ወረቀት ካላገኘ አግዙት!!

(ከስር የሚሰጡ ስድቦች ሂዊ የመደበቻቸው አካውንቶች መሆናቸውን ተረድተን የብሎክ ሰይፍ እንመዛለን)
በሐሩርና በቁሩ በጋራ ሸንተሩ ስለሕዝቡ ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ስለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት መከበር ስለምታደርጉት ተጋድሎ ስለምትከፍሉት መስዋዕትነት ሁሉ ታላቅ ክብር ይገባችኋል‼️

የእናት ኢትዮጵያ ዘብና አለኝታ ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ሰሞናዊ ሁኔታው!
ዳኛው ወዶም ተገዶም ነው "ያለም ወርቅ አንች እኮ ሙዚቃ ነሽ ፤ አንችን በመዳኜቴ እድለኛ ነኝ፤ ልቤም ዞረ ... ያለው"። የባለፈው ሳምንቱን ብቃቷንም ነው ዛሬ የደገመችው።

የዓለም - ወርቅ!
በእርግጠኝነት
ወርቁ ያንቺ ነው፤እንኳን ደስ ያለሽ‼️