Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.45K subscribers
2.98K photos
370 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
የዛሬ መሠረታዊ ወታደር የነገ ኮ/ል ጀኔራል አገር መሪ ይሆናል። የኢትዮጵያ አለኝታዎችን መቀላቀል ራስንም ሆነ ሐገርን ማስከበር ጀግንነትም ነው።

መከላከያ ከአራት በላይ ባሉት ዘመናዊ ክፍሎች
1. የምድርጦር (ከእግረኛ እስከ መካናይዝድ)
2.የባህር ሃይል
3. የአየር ሃይል
4. የምህንድስና ኢንተለጀንስ ዘርፎች

ከእነዚህ ውስጥ በመደበኛው የምድር ሃይልና በአየር ሃይልም ምልመላና ምዝገባ ተጀምሯልና ዕድሉን እንጠቀም!

#የመመልመያ_መስፈርቶች
✔️ከዚህ በፊት በማንኛውም የውትድርና መስክ ያልተሳተፈ/ያልተሳተፈች/
✔️ አድሜው 18-24 የሆነ ወይም የሆነች
✔️ከ10ኛ ክፍል በላይ የሆነ የሆነች
✔️ ከማንኛውም ሱስና ወንጀል ነፃ የሆነ የሆነች
✔️ ትዳር የሌለውና በውትድርና ህግና ደንብ ለመሰልጠን ፍቃደኛ የሆነ የሆነች በሙሉ መመዝገብ ይችላሉ ።

➤ምዝገባው ከግንቦት 16/09/2014 ዓ.ም እሰከ 30/09/2014 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በባህር ኃይል ፣ በአየር ኃይልና በእግረኛ ወታደር መመዝገብ የምትፈልጉ በአካባቢያችሁ በሚገኙ የቀበሌ ፅ/ቤት የወረዳ ሰላምና ደህንነት ፅ/ቤት ሂዶ መመዝገብ ይችላል ።
የሕግ ማስከበር ዘመቻው እየተካሄደ ያለው በሐገር ደረጃ ነው። በደቡብ፣ በኦሮሚያ፣ በቤንሻንጉል፣ በአማራ ክልል...ሐገር ለማፍረስ የባንዳ ባንዳ ሆነው ከጠላት ወያኔና ከውጭ ባዳ ጠላቶች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግንኙነት በመፍጠር በትጥቅም ሆነ ያለትጥቅ በቡድንም ሆነ በተናጠል በሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ላይ በተሰማሩ ኮንትሮባንዲስት ፀረ-ሰላም አካላት ላይ መንግስት እርምጃ መውሰድ ከጀመረ ቀናት መቆጠር ጀምረዋል።

የሕግ-ማስከበር እርምጃውን ተከትሎ በወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች በሕግ-ጥላ ስር በመዋል ላይም ይገኛሉ።

መንግስት ሕግ የማስከበር እርምጃ እየወሰደ ከሚገኘው አንዱ የአማራ ክልል ነው። በወንጀል በሚጠረጠሩ አካላት ላይ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች እርምጃ የመውሰድ እርምጃው ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን መረጃዎች ያመለክታሉ።በክልሉ ሕግ የማስከበር እርምጃ ያልተገባበት አንድም አካበቢ የለም።

ነገር ግን በአማራ ስም በፌስቡክ የሚንቀሳቀሰው የወያኔ ዲጂታል ሰራዊትና በወንጀል የሚጠረጠሩ አካላት በመቀናጀት የሕግ-ማስከበር ዘመቻው በጎጃም አካባቢ ብቻ እንደሚካሄድ አድርጎ ለማቅረብ የሚያሳየው መወራጨት የሚያስደንቅ ነው። እርግጥ ነው ችግሩ መረጃውን ወይም አጀንዳውን እንደወረደ የሚውጠው እንጅ እነሱማ አላማቸው በመሆኑ ለምሽግነት የሚያገለግላቸውን ሁሉ ይጠቀማሉ።
ማንም ሊያውቀው የሚገባው ነገር ቢኖር ግን በሌሎቹ አካባቢዎች በወንጀል ተጠርጥረው በሕግ-ጥላ ስር ለሚውሉ ሰዎች ድምፅ የሚሆናቸው ፌስቡከር ስለሌላቸው እንጅ መሬት ላይ ያለው ሐቅ ፌስቡክ ላይ እንደሚናፈሰው አይደለም ብቻ ሳይሆን ፍፁም የተገላቢጦሽ ነው። ስለሆነም ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኞችን የጩኸት አጀንዳዎችን አላማ ልናጤን ሁሉንም የጠላት ወያኔ አጀንዳዎችን እንደወረደ ከመዋጥ ተቆጥበን ነገሮችን በስክነት ግራ ቀኙን ልንመረምርና ከአላስፈላጊ መስዋዕትነት ራሳችንን ልንጠብቅ ይገባል። ይኼው ነው‼️
ለእናት ኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት መከበር፥ ለሕዝቦቿ ዘላቂ ሰላምና ጥቅም መረጋገጥ፥ ያለ እረፍት በሐሩርና በቁሩ ዳገት እየወጣ፣ ቆልቁለት እየወረደ፣ ጋራ ሸንተተር እያቆራረጠ፣ እንደ አንበሳና ነብር ሆኖ ለሚዋጋውና በቃላት ለማይገለፀው መስዋዕትነቱና ጀግንነቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊታችን ክብርና ምስጋና ይገባዋል‼️

እናንተ የኢትዮጵያ ሕልውና የመጨረሻው ምሽግና አለኝታ ናችሁና እንወዳችኋለን! እንኮራባችኋለንም‼️
በአማራ ክልል ከወያኔ ጋር ከነበረው ጦርነት ጋር ተያይዞ ሕገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ስለተስፋፋና ኮንትሮባንዲስቶቹ ለተጨማሪ የጥፋት አላማ ራሳቸውን እያደራጁ መምጣታቸውን ተከትሎ በሕዝቡ ተደጋጋሚ ጥያቄና ግፊት መንግስት በጀመረው ሕግ የማስከበር ዘመቻ በወንጀል የሚጠረጠሩ ግለሰቦች በሕግ-ጥላ ስር እየዋሉ ይገኛሉ።
ወያኔ አላማውን ለማስፈፀም በሳይበር በአማራ ማልያ እንዲጫወቱ ባሰማራቸው ጭፍሮቹና በወንጀል ተጠርጥረው ከሚፈለጉ የግብር ልጆቹ ጋር በመቀናጀት ነጋ ጠባ እንደሚለፈልፈው በጎጃም አካባቢ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የአማራ አካባቢዎች ማለትም በጎንደር በወሎ በሸዋ ጭምር ነው የሕግ ማስከበር እርምጃ እየተወሰደ የሚገኘው።

በሕግ ማስከበሩ በወንጀል የሚጠረጠሩ ግለሰቦች ቁጥራቸው የት ቀበሌ ወይም አካባቢ ላይ በርከት አለ ወይም አነሰ የሚል የወንጀል ተጠርጣሪ የምጥጥን ስሌት ወይም ጥያቄ የሚያሳስብ አይደለም። አይሆንምም። በየትኛው ቀበሌ አካባቢ ብሔር አገር ወንጀለኛ ቦታ የለውም። ወንጀለኛን ጫካ ወይም ዱር ሊደብቀው ይችል ይሆናል እንጅ ሕዝብ ሊደብቀው አይችልም። የግለሰቦችን ወንጀል ሊረከብ ወይም ሊጋራ የሚችል ማህበረሰብ እስካሁን አልተፈጠረም፤ለወደፊትም አይፈጠርም።

የአማራ ሕዝብ ከመንግስት ቅን ፍርድን ይፈልጋል። ይጠብቃል። ለሕግና ስርዓት ተገዥ ሆኖ ለዘመናት የኖረ ስለ ስነ-መንግስት ብዙ ማለት የሚችል፣ በሕግ አምላክ ብሎ ሕግ የሚያስከብር ፍትህ አዋቂ ሕዝብ ነው። አማራ ያለ ሕግና ስርዓት የመኖር ልምምድ የሌለው ሕዝብ ነው። በፍርድ ከሄደች በቅሎዬ ይልቅ ያለፍርድ የሄደች ጭብጦዬ ያንገበግበኛል ብሎ የፍትህን መስፈን አጥብቆ የሚሻ መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው ነው። ስለሆነም የአማራ ሕዝብ ወንጀለኞች ወደሕግ እንዳይቀርቡ የሚከራከር ሳይሆን ወንጀለኞችን አሳልፎ ለሕግ የሚሰጥና ራሱንም ከደሙ የሚያነፃ ነፃ የሆነ ሕዝብ ነው። እንደ አብራኩ ክፋይ ተመልክቶ ወንጀለኛን ለመደበቅ የመሞከር መሰል ልምምድ የለውም።

አንድ በማንነቱ አማራ ወይም ኦሮሞ የሆነ ማፍያ ከሲሲሊ ወይም ከየመን ከሐውቲ አማፂያን በሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ወይም በእፅ ማዘዋወር አብረው ሊሰሩ ይችላሉ። ለማፍያዎች አገር ወይም ብሔር ለተጨማሪ ጥቅም ማራመጃ ወይም ለጥቅማቸው ማስከበሪያ ማለቃቀሻና ማስለቀሻ ከመፈለግ ያለፈ ጉዳያቸው አይደለም።
"አማራ የሕልውና አደጋ ውስጥ ነው፤ ኦሮሙማ እስካለ ድረስም አማራ እረፍት ሊኖረው አይችልምና ፋኖን አጠናክረን በማደራጀት ኦሮሙማን ልኩን ማሳየት ይኖርብናል" የሚል የዘወትር አጀንዳ የነበረው፣ ኑሮውን ከሐገር ውጭ ያደረገና ራሱን እንደ አማራ ወሳኝ ተቆርቋሪ አድርጎ የሚገልፀው ነገር ግን "እስኪ በቪዲዮ ኮል እናውራ" ስለው ዛሬ ነገ እናወራለን እያለ ከድምፅ ያለፈ ነገር ሳናወራ ከ3 ዓመት በላይ እሱም ለእኩይ ዓላማው ለመጠቀም እኔም ማን ይሆን አላማው ምን ቢሆን ነው በሚል ግንኙነቴን ሳላቋርጥ ቆየሁ።

  በጦርነቱ ወቅት "ይህ ጦርነት አማራን አይመለከተንም፤ የብአዴን ነው እናንተ ምን ቤት ናችሁ?" አለኝ። ሰውዬው ራሱን እንደ አማራ ወሳኝ ተቆርቋሪ ያደረገና የአማራ ጉዳይ concern እንደሚያደርገው አማራ ሆኖ የሚተውን ስለነበረ  "ወያኔ በአዋጅ "ከአማራ ጋር ሂሳብ አወራርዳለሁ" የሚለው ካልተመለከተህ አንተ ምኑን አማራ ሆንክ ከአንተስ ጋር ምን አለኝ ወደሚመስሉህ ተጠጋ" ስለው ምን ቢለኝ ጥሩ ነው? "የትግራይ እናቶች አልቅሰው አይቀሩም፤ ትግሬ ኮዝ አለው እንደአንተ ያለ እባብ ባንዳ ብልፅግናን ለማዳን የአብይን ስልጣን ለማስጠበቅ አማራ መስለህ ብአዴን በሚመራው ጦርነት ለመዝመትና ሌሎችን ለማዝመት የአገኘሁ ተሻገርን የክተት ጥሪ መቀበልህ ነገ ዋጋ ያስከፍልሃል፤TDF ን አዲስ አበባ ከመግባት ሊያስቆመው የሚችል ምድራዊ ሃይል የለም፤ ሽንታ*ሙንና የኦነግን መከላከያ ሰራዊት ተብዮውን የአማራ ሕዝብ ደጀን እንዲሆን የምታደርገው ስራም አይሳካም፤ አብይ አህመድም ይፈረጥጣል፤ አንተ ቅማንቴ ከመሰሎችህ ጋር የTDF ቁርስ ትሆናላችሁ" አለኝ። ተጨማሪ ቀፋፊ የተለመዱ ስድቦችን አላካተትኩም፤ቀንሻለሁ😂

በዚህ የማንነት መገለጥ የደም ፍላት ንግግር ያኔም ሆነ እስካሁን በፍጹም አልተገረምኩበትም።
እስከ ድምፅ ድረስ የሚያወሩ ሌሎች አማራ የሚመስሉ በተለያዩ አገራት የሚኖሩ የወያኔ ሰላዮችንና በግልጽ በሚታወቅ ማንነት በሐይማኖት ጭምብል ጭምር ከአማራ ክልልና ከክልሉ ውጭ ተወለድን የሚሉ የወያኔ ምልምሎች መኖራቸውን አውቅ ስለነበር ጨጓራው መላጡን በሚያሳየው የሰውየው የለየለት የንዴት ድንፋታ አልደነቀኝም። ደስታዬን መጨመሩን ግን መካድ አይቻልም።

የአማራን ፖለቲካ ዲጂታል ወያኔ በከፍተኛ ብቃት ለራሱ አላማ በራሱ መስመር በከፍተኛ ሁኔታ አቧራው ጨስ እያለ ሲያስጨፍረው የከረመ ሲሆን አሁንም ሳይበሩን በመቆጣጠር ለተጨማሪ ጥፋቶች ሊቀጥል ይችላል።

የወያኔ የሚዲያ hegemony አስተሳሰብን በመበረዝ በአማራም ሆነ በአገር ላይ ብዙ ጉዳቶችን ሊያደርስ ስለሚችል በተደራጀ አኳሃን መመከትና እኩይ አላማውን ማምከን ያስፈልጋል።
በስልክም ሆነ በአካል ወይም በሚዲያ ዘመቻ በመከላከያ ወይም በአማራ ልዩሃይል ውስጥ ያሉ አባላትን በተለያዬ መንገድ ለማስኮቦለል ጦሩን ለማዳከምና ለመበተን በተለይ መንግስት በሚያስተዳድረው ግዛት ውስጥ በሚኖር በየትኛውም አካል ላይ መንግስት የማያወላዳ እር*ምጃ መውሰድ ይገባዋል። በየትኛውም ዓለም ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ሰፍኖባቸዋል ተብሎ በሚለፈፍባቸው አገራትም ቢሆን መከላከያ ሰራዊትን መንካት ለማንም የተፈቀደ ጉዳይ አይደለም። የአገር መከላከያ ሰራዊት ቀይ መስመር ነው።

በውጭ ባዳና በውስጥ ባንዳ ተመልምለው አገር የማፍረስ እንቅስቃሴ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ይቅርና አገር ለማዳን እንሰራለን የሚሉ ሰዎችም ቢሆኑ የአገር መከላከያ ሰራዊትን በተመለከተ በስመ ተገቢ ትችት አፍራሽ የጥፋት አጀንዳዎች ይሰራጩ ዘንድ ሊፈቀድለት አይገባም። መከላከያን ለማዳከም ለመበተን መንቀሳቀስ በራሱ ወያኔነትም ነው።

አንድ ወታደር ከመከላከያ ሰራዊቱ ከድቶ መንግስት ያስታጠቀውን መሳሪያ በመያዝ በሕገ-ወጥ መንገድ በቡድን ከተማ ላይ መንደር ለመንደር በነፃነት ሊንቀሳቀስ አይችልም። በማናቸውም ሁኔታ በየትኛውም አገር የመንግስትን መሳሪያ በመሸጥ ከሰራዊቱ መክዳት አይፈቀድም። በሐገር ክህደት የሚያስጠይቅ ወመኔ ወንጀልም ነው። ከዚህ ቀደም የወያኔ የጦር አመራሮችን ጨምሮ እነ ጌታቸው ረዳ እየደጋገሙ ሲናገሩት የነበረው "የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊትን ማዳከም ተቀዳሚ ስራቸው መሆኑን ነው። አሁን ላይ ያለው ሁኔታ በደንብ የሚገለጥልን የወያኔ ሰዎች ንግግርን መልሰን ማስታወስ ከቻልን ነው።

መከላከያ ወይም ልዩሃይሉ በተለያዩ ምክንያቶች ተዳክሞ ካልተበተነ ወይም የመዋጋት ሞራሉ ካልፈዘዘ መከላከያ አሁን ላይ ባለው አቅም በግንባር ጦርነት ወያኔ ሊያንበረክከው ይቅርና ሊደፍረው የሚችል ሃይል አይደለም።

ስለሆነም መንግስት ከመከላከያና ከልዩ ኃይል የጠላት አጀንዳን በመስማት ከሰራዊቱ ከድቶ ወደከተማ በሚመጣና መንደር ለመንደር እየተዟዟርኩ የሕዝብን ሰላም እነሳለሁ በሚል በማንኛውም ወታደር ላይ ምንም ዓይነት ምህ*ረት የሌለው እርም*ጃ ሊወስድ ይገባዋል። ቀይ መስመሮች በመንግስት ሊከበሩና መንግስትም ሊያስከብራቸው የግድ ይለዋል‼️
የቆምንበት መሰረቱ እውነት ከሌለው፣ የምንታገለው ለነፃነት፣ ለእኩልነትና ለፍትህ ካልሆነ በስተቀር በተቃራኒው መንገድ የቆምን እንደሆነ ለጊዜው በመንጋ ጭብጨባ ልክ የሆንንና የተሳካልን እንምሰል እንጅ የተከተልነው የተሳሳተ መንገድ ስለሆነ ገደል ገብተን አወዳደቃችንን መክፋቱ የማይቀር ነው።

ከትዕቢት በመነጬ ንቀት፣ ጥላቻ በወለደውና በግብታዊነት በተመራ ትግል ማንም አወዳደቁን ሊያከፋው ካልሆነ በስተቀር ድልን ሊቀዳጅበትና መጨረሻውን ሊያሳምርበት የሚችልበት የስኬት ወይም የአሸናፊነት መንገድ ሆኖ ሊመረጥ የሚችል አይደለም። ሱሳይድም ነው።
የአማራ ክልል መንግስት ሕዝባዊ ቁጣውን ለማስቀየስ፣ አማራውን ለማዘናጋትና ለማታለል ሆንብሎ እስከዛሬ አድርጎት የማያውቀውን በመቶዎች የሚቆጠሩ ትራክተሮችን በመግዛት ለገበሬዎች መስጠት መጀመሩ እንደቀላል ሊታይ አይገባም።

አማራ ሆይ! በመቶዎች ለሚቆጠሩ ለኦሮሙማ ትራክተሮች ብለህ ትግልህን እንዳታቆም። ለአፍታም እንዳትዘናጋና እንዳትሸወድ። የአብይ አህመድ የኦሮሙማ መንግስት በዚህ ወቅት ትራክተር ለአማራ ገበሬዎች የሚሰጥበት ሴራ ካልገባህ አንተ ሆድ አደርነትህንና የብልጽግና ተላላኪነትህን አያረጋግጥም መሆንህም ሊታወቅ ይገባል። አማራዬ ንቃ!

ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኞች!
በሁሉም የአማራ አካባቢዎች የሕግ ማስከበር ዘመቻው በአማራ ክልል ልዩሃይል፣ሚሊሻና ፋኖ ቅንጅት በሕዝቡ የተደጋገመ "የሕግ ይከበርልን ጥያቄ" መሰረትና ከፍተኛ ትብብር እየተመራ ነው። በዚህ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ከሕዝቡ ፍላጎት ወይም የአገራቸውን ሉዓላዊነት ለማስከበርና የሕዝባቸውን ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ለማረጋገጥ በሚታገሉ፥ ነፍጣቸውን ለወያኔ ባነሱና በሚያነሱ፥ በባለፈው የሕልውና ጦርነትም ግንባር ገብተው በምሽግ ውለው አድረው በተዋደቁ በሕገ-ወጥ እንቅስቃሴ ላይ ባልተሰማሩ፣ ከተማ ተቀምጠው መንግስትን በትጥቅ ትግል አንዴ እናፈርሳለን ሌላ ጊዜ ላይ ደግሞ መንግስት የለም እያሉ ስርዓት አልበኝነትን ለማንገስ ጠመንጃ እያወዛወዙ ደፋ ቀና በማይሉ በተቧደኑም ሆነ በተናጠል በማይንቀሳቀሱ አካላት ላይ መንግስት እርምጃ እየወሰደ ስለመሆኑ የሚያመላክት የተረጋገጠ አንድም መረጃ በትም አካባቢ ስለመኖሩ እስካሁን አላገኘሁም። በሬ ወለደ ወሬውን ግን እነ ስማ በለውና ፍለጠው ቁረጠው የግጭት ጡረተኞች እንደፈለጉ አላጧጡፉትም ማለት አይቻልም።

የአማራ ልዩሃይልን መለዮ የለበሱ አንዴ ከኦሮሚያ ክልል መጣ የሚባል ልዩሃይል ሌላ ጊዜ ደግሞ ከፌደራል የተላከ ኦሮሞኛ ተናጋሪ አፋኝ ሃይል እየተባለ ተደጋግሞ በማህበራዊ ሚዲያው የሚነዛው ወሬም ፍፁም ነጭ ውሸት ነው።

የኦነግ ወታደር የአማራ ክልል ልዩሃይልን መለዮ ለብሶ እየተንቀሳቀሰ ነው የሚለው ለአማራ ክልል ልዩሃይል ትልቅ ንቀት ከመሆኑም ባሻገር ልዩሃይሉ ከሕዝብ ለመነጠልና እንደጠላት ተቆጥሮ ጥቃት እንዲደርስበት የታለመ ሴራ ነው።

ወያኔ ጦርነት ከመክፈቱ በፊት መንግስት በሚያስተዳድረው ክልል ቀድሞ የፀጥታ ሃይሉን ትኩረት ለመበታተንና ለማዳከም በሕገ-ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀስን ኮንትሮባንዲስት ስርዓት ለማስያዝ የአማራ ልዩሃይል ፋኖና ሚሊሻ የሚያንስ ሆኖም የሌላ ክልልን እገዛ እስከመጠየቅ ወይም ማዕከላዊ መንግስቱ ተርበትብቶ ሃይል እስከመላክ የሚያደርሰው ደረጃ ላይ አይደለም። ፈፅሞም አይሆንም። የአማራ ልዩሃይል እንኳን በሕዝብ ፍላጎትና ትብብር እየተመራ ይቅርና ብቻውን ቢቆም እንኳን ሕገ-ወጦችን ስርዓት ለማስያዝ አቅም የሚያጥረው ወይም የሚቸገር ሃይል አይደለም። መቼምም አይሆንም!

ማንም ከሕግ በላይ አይደለም። ሁሉም በሕግ ፊት እኩል ነው። የሕግ የበላይነት መስፈን ለሁላችንም ነው። ሕግ አይከበርም የሚለው ደግሞ ሕገ-ወጥ የሆነው ብቻ ነው‼️
ክብር ከጥቅምት 24 የሰሜን ዕዝ መጠቃት ጀምሮ ከፍተኛ መስዋዕተነት ለእናት ኢትዮጵያ እየከፈለ ለሚገኘው ለጀግናው የአማራ ልዩሃይል ይሁን!
በአማራ ላይ ሂሳብ እንዲወራረድ (የግፍ ግፍ እንዲፈፀም) ኢትዮጵያ እንድትፈርስ ያሴሩና የሰሩ ሰዎች፥ እኛ በሕይወት ቆመን እየሄድን በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ይነግሱ ዘንድ ፈፅሞ ልንፈቅድላቸው አንችልም። ምን አልባት ንስሓ ከገቡና የኢትዮጵያን ሕዝብ በአደባባይ ይቅርታ ከጠየቁ የማርያም መንገድ ሊያገኙ ይችላሉ። እንጅ ባንዳ ነግሶ አርበኛ እንዲንኳሰስ ሁኔታዎች ይመቻችላቸው ዘንድ ፈፅሞ በየትኛውም መንገድ ቆመን ልንመለከት ወይም ልንተባበራቸው አንችልም። ይኼው ነው‼️
የኢትዮጵያ አለኝታዎች‼️

ኢትዮጵያ ዛሬም እንደትናንቱ ሉዓላዊነቷን አስከብራ ነፃነቷን አስጠብቃ ታፍራና ተከብራ ትኖር ዘንድ የጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ድርሻ በማንም የሚተካ አይደለም። ያለእረፍት ስለምትከፍሉልን መስዋዕትነት እናመሰግናችኋለን።

ወጣቶች ጀግናውን የመከላከያ ሰራዊትን እንቀላቀል። የዛሬ ወታደር የነገ ኮ/ል ጀኔራል የአገር መሪ ነው።
ወሳኝ የታሪክ መታጠፊ ምዕራፍ ላይ እንዳለን ስለምናስብ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ለሐገራችን የሚጠበቅብንን ጠጠር ለመወርወር እንጅ ከማንም የተለየ የእናት ወይም የአባት የዘር ሐጢያት ኖሮብን አይደለም በወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ የስደብ ናዳ የምንሸከመው።
እኛ የምናስፈልግበት ወቅት ስለሆነ ነው እውነትን መሰረት አድርገን በአባቶቻችን መንፈስ ተመርተን ነፃነታችንንና ማንነታችንን ለማስከበር በመንግሥት ቪ -8 የሚሽከረከሩ በቪላ ቤት የሚኖሩ ኋላፊነት የተሰጣቸው እንጀራቸውን የሚጋግሩበትን ምጣድ ሊሰብሩ ብዙዎች ችግር ሲፈጠር ወደጓዳ ሲደበቁ ብልፅግናን እየሰደቡ ሕዝብን ለችግር ሲቀሰቅሱና አጥር ላይ መንጠልጠልን እንደጥበብ ሲቆጥሩ፥ እኛ ከፊት ሆነን የምንገረፈው ለእናት አገራችን ኢትዮጵያ ሕልውና ስንል ብቻ ነው።

አማራን መዋቅራዊና ስርዓታዊ ግፍና በደል ይደርስበት ዘንድ ያደረገው አሁንም ለተጨማሪ ግፍ የሚቅበዘበዘውና ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦል ድረስ እወርዳለሁ ያለውን የወያኔን እብሪት ማስተንፈስ ታሪካዊ ግዴታችን ስለሆነ ነው። ኦሮሙማ ሆነ አብይ አህመድ የማያውቁትን እንዲሁም ለአገሩ ሉዓላዊነት መከበር ሲል ቀድሞ በነፃ የሚታገልን ሰው ምን ብለውስ ሊያስገድዱትና እንደሚባለው በገንዘብ ሊያንበሸብሹት ይፈልጉታል? ይጠሩታልስ?
የአገሩን ሕልውና እና ሁለንተናዊ ዘላቂ ጥቅም ይከበር ዘንድ እታገላለሁ የሚል ሰው ጊዜያዊ ጥቅም አላገኘሁም ወይም እውቅና ተነፈግኩኝ በሚል እናት አገሩን ለመካድ ሊነሳሳ የሚችልበት ዕድልም የለም።

ምንም እንኳን ማንም ምድር ላይ ለድካሙ እውቅና የሚሻ ጥቅምንም የሚጠላ ሰው የሌለ ቢሆንም የግድ የምንፈልገው ነገር ካልተደረገልን ወይም በመንጋ አዝማቾችና ተከታዮች እንደተባልነው አይደለንም ተሰደብን ተረገምን ተዛተብን በሚል ተልካሻ ምክንያት ለሐገራችን ያለንን የፀና የማይናወጥ አቋም ተጠናክሮ የሚቀጥል እንጅ በእልህ ከመስመር በመውጣት የምንደናቀፍ አንሆንም።

ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛን Demobilize ሳናደርግ እረፍት አይኖረንም። ምክንያቱም ለአማራም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እዳ ነውና‼️
የዶ/ር አብይ አህመድ አስተዳደር ከወያኔ ጋር አንዴ በኬንያ ሌላ ጊዜ በናይጀሪያ ለምን ይደራደራል? ብለው እሪታ የሚያሰሙ ሰዎች ያስደንቁኛል። ያሳዝኑኛልም። በመንግስት እና በወያኔ መካከል ድርድር እየተደረገ ቢሆንም ባይሆንም ጦርነት መጨረሻው ወይም መቋጫው ድርድር መሆኑ የታወቀ ነው።
በሩሲያና በዩክሬን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ስለድርድር በየጊዜው ይነሳል። ባይስማሙም ለመደራደር ተገናኝተዋል። ቅድመ ሁኔታዎች መደራደሪያዎች ሊለያዩ ይችላሉ እንጅ ድርድር የጦርነቱ መልክ መቀየሪያ ነው።
በኢትዮጵያ መንግስትና በአማፂው ወያኔ መካከል አሁን ላይ ድርድር እየተደረገ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል። ስለድርድሩ በቂ መረጃ ያላቸው እየተደራደሩ ነው የተባሉት አካላት ናቸው።

መንግስት እንዴት ከወያኔ ጋር ይደራደራል ብለው ጩኸቱን የሚያቀልጡት አንዴ የሰላም ሰባኪ ሌላ ጊዜ ጦርነቱ አይመለከተንም ባይ ሰዎች ግን ስለድርድሩ ከፊት ቀድመው ወሳኝ ለመሆን የሚያደርጉት መፍጨርጨር አስገራሚ ነው።

ድርድር ሊኖር አይገባም የሚሉ ሰዎች ከዚህ በፊት "ጦርነቱ እኛን አይመለከተንም" ያሉ ናቸው። በቅርቡም ሕዝባችንን ለማዘናጋት #No More War ሲሉ የነበሩ ሰዎችም ናቸው። ታዲያ ጦርነት አያስፈልግም ሲሉ የነበሩት ጦርነቱን እንዴት እንዲቆም ፈልጎ እንደሆነ እነሱ ናቸው ሚስጢሩን የሚያውቁት።

ከፍየሏ በላይ የሆነው ጩኸት መንግስት ከወያኔ ጋር በሚያደርገው ድርድር ወልቃይት ለወያኔ ተላልፎ ሊሰጥ ነው የሚለው የአዛኝ መሳኝ ቅቤ አንጓችነት ጉዳይ ነው።
ዶ/ር አብይ አህመድ ስልጣኑ አይነካበት እንጅ የሕዝብ ጥያቄ ጉዳዩ ስላልሆነ ወልቃይትን ለወያኔ አሳልፎ ለመስጠትም ወስኗል ሲሉም ይደመጣሉ። የወልቃይት ጉዳይ ያሳስበኛል የሚሉ ሰዎች በበሬ ወለደ ወሬ ለምን በቀላሉ እንደሚደናገጡ እየገባኝ አይደለም። በድርድሩ ወልቃይት ለወያኔ ተላልፎ ሊሰጥ ስለመሆኑና በተክደሃል በለቅሶ ፖለቲካ ሕዝብን ለማደናገር የሚሞክሩ አካላት ወልቃይት በወያኔ እጅ እንዲገባ የሚፈልጉ ብቻ ሳይሆኑ እንዲሆን ሲሰሩ የቆዩ መሆናቸው ታውቆ ያደረ ነው።

ዶ/ር አብይ አህመድ በንግግር ደረጃ ወልቃይት የቤጌምድር መሆኑን በተለያዩ መድረኮች ባረጋገጠበት ሁኔታ(የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ፊርማ ነው)፤በአማራ ክልል መንግስት ስር ወልቃይት እየተዳደረ ባለበት ሁኔታ አብይ ወልቃይትን ለወያኔ አሳልፎ ሊሰጥ ስለሆነ አማራ ከመካድህ በፊት ተነስ የሚሉ አዛኝ መሳይ ቅቤ አንጓቾች በዚህ ደረጃ አዳማጭ ማግኘታቸው የሚያስደንቅ የሚያሳስብም ነው።

ዶ/ር አብይ አህመድ ወልቃይትን በተመለከተ ከዚህ በላይ ምን እንዲያደርግ ወይም እንዲናገር ነው የተፈለገው? እጅግ በጣም የሚያሳፍረኝ የወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ የፕሮፖጋንዳ ሰለባ የሆነው የወልቃይት ጉዳይ ያሳስበኛል የሚለው አካል ተደናብሮ ሌሎችን ለማደናበር የጠላትን አጀንዳ ተሸክሞ የሚያዘጠዝጠው ጉዳይም ነው።
ወያኔያዊው የአማራ ብሔርተኞች ወልቃይትን በተመለከተ ከአብይ አህመድ ይልቅ ኢሳያስን አምነን ወዳጅ ብናደርገው የተሻለ ስለመሆኑም በተለያየ መንገድ በአደባባይ በሶሻል ሚዲያው ሲናገሩ ይሰማሉ። አማራና ኤርትራ ወዳጅ ናቸው ወይም እንወዳጅ እየተባለ በሶሻል ሚዲያው በተለያየ መንገድ የሚራገበው አጀንዳ ከአማራ ለአማራ ሕዝብ ጥቅም ታሰቦ የሚሰራ ጉዳይ አይደለም። የኦሮሞ ወይም የሌሎች ብሔር ልሒቃንን መሬት ላይ በሌለ እንቅስቃሴ አማራው ከማዕከላዊ መንግስቱ የሚያፈነግጥ አስመስሎ ስጋት ለመፍጠር፣ በዋናነት በወልቃይት ጉዳይ የኦሮሞ ልሒቃንም ሆኑ የሌሎች ብሔር ልሒቃን ከአማራ ጎን በመቆም አቋም እንዳይዙ ለማድረግ ያለመም ነው።

በነገራችን ላይ በወልቃይት ጉዳይ ችግር ቢፈጠር የአማራ ክልል መንግስትና በብልፅግና ውስጥ ያሉ በስራቸው የተገፉና ያኮረፉ የተጠያቂነት ስጋት ያለባቸው አመራሮች ናቸው ተጠያቂ ሊሆኑ የሚችሉት። ሕዝቡን ለማታገያነት ለመጠቀም በማሰብ የወልቃይት ጉዳይን ከሚዲያ ዘመቻ እስከ መሬት የወረደ የማወሳሰብና አሳልፎ የመስጠት ስራ እየሰራ የሚገኘው አካል የማይታወቅ የተሰወረ አይደለም።

እራሳቸውን የወልቃይት ጉዳይ ዋና ተቆርቋሪ አድርገው የተደበቀ ፍላጎታቸውን ለማስፈጸም የሚዳክሩት ሰዎች ከሳምንት በፊት"ጦርነቱ የሰሊጥ ብሄረተኞች ጦርነት ነው፤ እኛን አይመለከተንም። " ሲሉን የነበሩ መሆናቸው ግልጽም ነው።
ወልቃይት መሬት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ሕልውና ሊወስን የሚችልና በቀጠናው ላይ ትልቅ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችል ስትራቴጂክ ኮሪደር ነው። የግብፅንና የሱዳንን ሁኔታ የውስጥ ባንዳዎችን አገር የማፍረስ የተላላኪነት ያልተቋረጠ እንቅስቃሴ የሚከታተል ሰው፣ መንግስት ወልቃይትን ለወያኔ አሳልፎ ሊሰጥ እንደሚችል በአደባባይ ቢናገር እንኳን መጠራጠር ይኖርበታል። ወልቃይት የጎንደር አማራ መሬትና ግዛት ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ወልቃይት በወያኔ እጅ በገባ ማግስት ሊፈጠር የሚችለውን ነገር ማሰብ አይከብድም። ወያኔ በግጭት ተወልዶ በግጭት ያደገ ያለግጭት ሕልውና የሌለውና መቼም ቢሆን የሚታመን ሐይል አይደለም።

ወልቃይትን መንግስት በስሩ የሚያደርገው ለማንም ብሎ ሳይሆን ለራሱ ሕልውና ለአገረ-መንግስቱ መቀጠልና መፅናት ሲል ነው። የኢትዮጵያን መበልፀግ የሚሻ መንግስት የኢትዮጵያን ሕልውና አደጋ የሚጥል ስራ ፈፅሞ ሊሰራ አይችልም። ይህን አለመረዳት ችግሩ የማንም ሳይሆን የራስ ነው። በወያኔ ፕሮፖጋንዳ አዕምሮን የማጣት ምልክት ነው። ከዛ ካለፈ ደግሞ ከወያኔ እንደ አንዱ መሆንን የሚያረጋግጥ ነው።

በሌላ በኩል ወያኔያዊ የፌስቡክ የአማራ ብሔርተኛ በመንግሥት መከዳት ስለወልቃይት የሚናገረውና የሚፅፈው የቢሆን ፍላጎቱን ነው። በጓዳ እንዲሆን የሚመኘውንና ከውጭ ባዕዳን ጭምር ተቀናጅቶ መሬት ለማስነካት የሚሰራውን ጉዳይም ነው በፊት ለፊት በስመ አዛኝ ተቆርቋሪነት የጥርጣሬና ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ግርግርና ሁከት ለመፍጠር የሚሰራው።

ሕልማችሁ ከቀን ቅዥት የማያልፍና መቼም ሊሳካ የማይችል ነው‼️
የኩራት ምንጮቼ
የነፃነት ጠባቂዎቼ‼️

ስለእናት ኢትዮጵያ እረፍት ስለሌለው የሕይወት ጉዟችሁ ክብርና ምስጋና ይገባችኋል!
ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር‼️

ዶ/ር አብይ አህመድ በተለያዩ መድረኮች ወልቃይት የበጌምድር አማራ መሆኑን በማያሻማ መንገድ በጠራ አገላለፅ ባረጋገጠበት መንገድ(የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ፊርማ ነው)፤ ወልቃይት በአማራ ክልል መንግስት ስር እየተዳደረ ባለበት ሁኔታ፤ ወልቃይትን አብይ አህመድ ለወያኔ አሳልፎ ሊሰጥ ስለሆነ አማራ ከመከዳትህ በፊት ተነስ የሚሉ የግጭት ነጋዴዎች ድምፅ ማሰማት ሳይሆን ለእነሱ ጆሮ የሚሰጠው ሰው ቁጥር በዚህ ደረጃ መጠኑ መጨመሩ የሚያስደንቅና የሚያሳስብም ነው። እርግጥ ነው ጉዳዩ የማንም ሳይሆን የራሱ የመንግስት የ PR ችግር የፈጠረው ነው።

ዶ/ር አብይ አህመድ ለአማራ እንቆረቆራለን ወይም እንታገላለን ከሚሉት በላይ በወልቃይት ጉዳይ የሕዝቡን የዓመታት ጥያቄና ትግል እውቅና ሰጥቶ ወልቃይት የበጌምድር አማራ መሆኑን የጠራ አቋሙን በአደባባይ አረጋግጦ ለሕዝቡ ጥያቄ የራቀ ሳይሆን መቅረቡን ያስመሰከረበትን ጉዳይ ጠላት ወያኔ ግን ወልቃይት እንዳይመለስ ወይም ለወያኔ ተላልፎ እንዲሰጥ አብይ እየሰራ እንደሆነ አድርጎ መንጋ የሚያደናግርበት ወይም በመንጋ እንዲከሰስ ዕድል የፈጠረበት ሁኔታ የጠላትን ጥንካሬ ሳይሆን የራሱ የመንግስት የመረጃ አሰጣጥ የሕዝብ ግንኙነት ድክመትን የሚያሳይ ነው።

የመላው አማራ ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር በነቂስ ወጥቶ ወልቃይትን ብሎ ብዙ መከራና ግፍን የተቀበለበትን ጥያቄና ትግል ከሆነው አንዱ የወልቃይት ጉዳይ በዚህ ሰዓት በእጁ መዳፍ ይገኛል።

ስለወልቃይት በሕግ የቀሪውን ጉዳይ የማረጋገጥ ስራ በአማራ ክልል መንግስት እና የአማራ ኤሊት ነኝ በሚለው አካል ትክሻ ላይ የሚወድቅ ይሆናል። አብይ አህመድ እስካሁን ከተናገረው ወይም ካደረገው በላይ በዚህ ዙሪያ የሚጠበቅበት ግዴታ እንዳለበት በበኩሌ በፍፁም አይሰማኝም። ወልቃይት የበጌምድር አማራ ነው ከማለት በላይና በአማራ ክልል መንግስት ስር እንዲተዳደር ከማድረግ፣ ለቀጣይ ሂደቱን ነገሮችን ከማመቻቸት ያለፈ ከእሱ የሚጠበቅበት ነገር የለም። ከዛ ውጭ አብይ አህመድ መንደር ለመንደር ወይም ከክልል ክልል እየዞረ የወልቃይትን ጉዳይ ወረቀት ይዞ ሊያስፈፀም አይችልም። ፖስተኛም አይደለም።
ማንም እጅና እግሩን አጣጥፎ ተጎልቶ ጊዜውን የሚቆጥር አብይ አህመድ ሁሉንም ነገር ፈትፍቶ እንዲያጎርሰው የሚፈልግ የጠባቂነት መንፈስ የተጠናወተው ሁሉ እጁ ላይ የገባውን ወልቃይትን ሊነጥቁኝ ነው ወይም ተላልፎ ሊሰጥብኝ እያለ ሲነፋረቅ ቢታይ ድክመቱን ከማሳየት ነውሩን ከመግለጥ ያለፈ ትርጉም ያለው ነገር ማሳየት አይችልም።

እርግጥ ነው በሰሜን ሕብረት በስመ የአቢሲኒያ አሻራን የደቡቡ ሐይል ሊንደውና ሊያ*ጠፋው ነው በሚል የወያኔ አጀንዳን በማራገብ ከወያኔ ጋር አብረን ከቆምን ባርጌኒግ ፓወራችን ይጨምራል አብይ አህመድንም ከስልጣኑ ማስወ*ገድ ይቻላል እያለ የሚንቀሳቀስ አካል መልሶ በመሃል የወልቃይት ጉዳይን አስመልክቶ በተቆርቋሪነት ለመንቀሳቀስ ሲሞክር መታየቱ ተጠባቂ እንጅ አዲስ ነገር አይሆንም። በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ጥላቻ የወለዳቸው በስሜት ፈረስ የሚጋልቡ የወያኔ የማደጎ ልጆች ለአላማቸው መሳካት እንደፈለጉ ሲገለባበጡ ሚግ 23 የሚያስንቁ ናቸው። በቀጣይ በየት በኩል ተገልብጠው ሊከሰቱ እንደሚችሉ መገመትም አይቻልም።

እነዚህ አካላት ዶ/ር አብይ አህመድን እንደ አንድ የሕወሓት ስራ አስፈፃሚ እኩል ነጥለው እያብጠለጠሉ ከስልጣኑ እናስ*ወግደዋለን ብለው እየተንቀሳቀሱ መልሰው የአማራ ጥያቄ እየተመለሰ አይደለም ሲሉ፤ወልቃይት በአብይ አህመድ ተላልፎ ሊሰጥ ነው የሚል ጩኸትም ሲያሰሙ መመልከት የሚያረጋግጥልን ጉዳይ የሞራል ቫልዩና መርህ አልባ መሆናቸውን ነው።

በመጨረሻም‼️
ለአማራ ሕዝብ እንቆረቆራለን የምንል ሰዎች ቅድሚያ እራሳችንን እንመልከት። ከዛም ከራሳችን ጋር ሆነን የራሳችንን አጀንዳ ቀርፀን ለአማራ ሕዝብ ሁለንተናዊ ጥቅም መረጋገጥ ደፋ ቀና ለማለት ሙከራ እናድርግ። አለበለዚያ በተመለደው በጠላት አጀንዳ በስማ በለው ስንወራጭ፣ አካኪ ዘራፍ እያልን ስንፏልል፣ ውለን ብናነጋ በውጤቱ ከአንዱም ሳንሆን እንደዳከርንና አረፋችንን እንደደፈቅን አወዳደቃችንን አበላሽተን ከመውደቅ ከፍ ያለ ድል ልንነሳው የምንችለው ጠላት አይኖረንም። ከጅምሩ የተከተልነው መስመር በእኛ የተነደፈ ወይም በእኛ የቀየሰ መንገድ አይደለምና። ስለሆነም የጠላት አጀንዳን ተሸክመን በጠላት መንገድ እየተመላለስን ጠላትን ለማሸነፍ ማሰብ የሞኝነታችንን ጥግና የአወዳደቃችንን ሁኔታ ከማሳየት ያለፈ አሸናፊነታችን አያረጋግጥም።