Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.46K subscribers
2.98K photos
370 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
Ethio-360 ( Egypt 360) እና ሌሎች የባንዳ ባንዳዎች አማራ ክልልን በሰልፍና በሰይፍ የሁከትና የብጥብጥ ማዕከል በማድረግ ለወያኔ መንገድ ሊጠርጉ ያለ የሌለ የብሶት መቀስቀሻ ቢጠቀሙም ታላቁ የአማራ ሕዝብ ገቢራዊ ምላሽ የሚደነቅ ሆኗል። በአንድም የአማራ ክልል ከተማ ላይ አንድም ሰልፍ የለም። በመላው የአማራ ከተሞች ሰልፍ ይካሄዳል ሰይፍም ይነሳል የተባለለት ጥሪ ባሕርዳር ላይ እሁድ (ሰንበት) የእረፍት ቀን መሆኑን ተከትሎና በጧቱ ሰዎች ከእንቅልፋቸው ባልተነሱበት ሰዓት በተዘጉ ሱቆች ፎቶ ሲጠሩት ከነበረው አቋም ተገልብጠው (በፎርፌ መሸነፍ በራሱ ትርጉሙ ብዙ ነው😂) ለመፅናናት እየተሞከረ ነው።

መሬት ላይ ያለው የሕዝባችን እውነት ተገልጧል። ለወያኔ ድምፆች ጀሮ አለመስጠቱንም በማያወላዳ አቋሙ አረጋግጧል። ይኼው ነው!
ለማንኛውም ባሕርዳር ፍፁም ሰላም ናት። ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ሽር ጉድ እያለች ነው። የትራንስፖርትና የንግድ እንቅስቃሴዎች እንደተለመደው አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው። የወያኔ አለማ ለጊዜው ከሽፏል።

ሰናይ ሰንበት‼️
"...ተመትቼ ነበር፣ በሂሊኮፕተር ነው ወደሕክምና የወሰዱኝ። አሉ የተባለ ዶክተሮች ናቸው ተዘጋጅተው የጠበቁኝ። ከላይ ጀምሮ ውጪ ሃገር (የፈለገው ሃገር) ሄዶ ይታከም ተብሎ ሄጄ ታክሜአለሁ። ምቴ (የተመታሁት) ከባድ ነበር። ፊቴ ላይ ነበር ጉዳቱ፤ አሁን ድኜ ወደ ሥራዬ ተመልሻለሁ።"
ብ/ጄ/ል ሻምበል በየነ

ዛሬ ግንቦት 14 ቀን 2014 ዓ.ም በመከላከያ ቴሌቪዥን ከሰጡት ቃለምልልስ የተወሰደ።
እንኳን ደስ አለን!

ከሐምሳ ሺ በላይ ደጋፊዎች በተገኘበት የባህርዳር ስታዲየም ፋሲል ከነማ 1 0 ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸንፏል።
ወያኔ በአዋጅ "በአማራ ላይ ሂሳብ ለማወራረድ፤ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ጦርነት"ሲከፍት "ጦርነቱ እኛን አይመለከትም፤ ጦርነቱ ለኢትዮጵያ ሕልውና ሳይሆን የአብይ ብልፅግናን ሕልውና ለማስቀጠል ነው" ብለው በአማራ ወገናችን ላይ ግፍ እንዲፈፀም፣ ሐገር እንድትፈርስ፣ ለወያኔ መንገድ የጠረጉና ስጋጃ ሆነው ያገለገሉ፥ በሐገር ክህደት ወንጀል መከሰስ ሲኖርባቸው ነገር ግን ጥፋታቸው እንኳን ሳይነገራቸው በዝምታ በመንግስት መታለፉ ክህደትን እንደጌጥ፤ ባንዳነትን እንደ ብልጠትና እንደ እውቀት የቆጠሩ ሰዎች አሁን ላይ ስለ እኛ በነውር ተመርተው ያሉትን ቢሉ መቼም ጀሮ ልንሰጣቸውና ጉዳያችን ልናደርጋቸው አንችልም።

እነዚህ ሰዎች በብሔር ትግረኛ ተናጋሪ ወያኔ አለመሆናቸው ካልሆነ በስተቀር በግብራቸው ወያኔን የሚያስንቁና ራሱ ወያኔም የሚቀናባቸው የመንፈስ ልጆቹ ሆነው ሳለ ምስጋና፣ መወድስ፣ ሽልማት ያቀረቡልን ይመስል ስለሰደቡን ወይም ስለረገሙን እንደምን እንደማይጠበቅ ጉዳይ ሊደንቀን ይችላል?! ከወያኔ ግብር መልካም ነገርን እንዴትስ ማግኘት ይቻላል?!

ለማንኛውም፥ ወደሲኦል በሚወስደው መስመር ላይ አልተሰለፍንም‼️
ተልባ ቢንጫጫ፣
በአንድ ሙቀጫ።
ጥንቃቄ!

ሰሞኑን በኢትዮ-360 (በግብፅ 360 ) የወያኔ "የሽንት ጨርቆች" በሆኑት በእነ አይተ ሐብታሙ አያሌውና ኤርሚያስ ዋቅጅራ የአማራ ክልልን የብጥብጥና የሁከት ሜዳ በማድረግ መሬቱን በደም ለማጠብ የተጠራውን የአመፅ ጥሪ በታላቁ ሕዝባችን ተዋርደውና ኩም ብለው መራራ ሽንፈትን የተከናነቡና (እርግጥ ነው ምንም አይመስላቸውም፤በየጊዜው በፎርፌ ጭምር የሚሸነፉም ናቸው) እኩይ አላማቸው መክሸፉ የሚታወቅ ነው። ነገር ግን የወያኔም ሆነ "የሽንት ጨርቆቹ" ሕልውና የተመሰረተው በግጭት ላይ ስለሆነ ጉንቦት -20ን ምክኛት በማድረግ በድጋሜ የአማራ ክልልን ለማበጣበጥ ለማዳከም የሚጠራ ግልፅ የሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ወይም በሕቡዕ የሚደረግ የአመፅ ሰይፍ ሙከራ ሊኖር ይችላልና ሁሉም የአካባቢውን ሰላም ከግጭት ጡረተኞች ራሱ ዘብ ቆሞ ሰላሙንና አንድነቱን እንዲጠብቅ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ በአማራ ሕዝብ ላይ በወያኔ የተደጋገመ ግፍና በደል ሲፈፀምና ኢትዮጵያ ትፈርስ ዘንድ ቆመን አይናምና አንተባበርም ብለው በጀግንነት ለተዋደቁና መስዋዕትነት ለከፈሉ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆች በሙሉ ይሁን! ዘላለማዊ ሞ*ት ለዘላለማዊ ደመኛ ጠላታችን ሕወሓት!

አሜን!
በፌስቡክ ሳይሆን በጦር ግንባር ምሽግ-ሰባሪ በሆነው በጀግናው አርበኛ አጋዬ አድማሱና በመሰል የግንባር ጀግኖች የወያኔ "ሽንት ጨርቆች" ለመንጠላጠል እየሞከሩ ነው። ከዚህ በፊት "ዘ ስኳድ" ብለው ሰነድ በማዘጋጀት ድንኳን ጥለው ንፍሮ ቀቅለው፣ ነጠላ ዘቅዝቀው፣ ወያኔያዊ ግብራቸውን በአካባቢ ስም ነገሮችን እንደወረደ የሚውጠውን መንጋ አቧራው ጨሰ በማለት በማደናገር ምሽግ ለማድረግ የድረሱልኝ ጥሪያቸውን ማሰራጨት ከጀመሩ የከረመ መሆኑ ሁሉም የሚያውቀው ሐቅ ነው። ወያኔያዊ ግብራቸውን ቩቩዜላዎችንና ጥሩንባ ነፊዎችን ከፊት ለፊት በማሰማራት በጩኸት ቡታ ሰዳጅነትን ባሕሪይን ከማስተዋወቅ ያለፈ የተለየ ለውጥ ማምጣት አይቻልም። ቁስል በማከክ መንጋ በማስጨፈር ማንም የወያኔን አላማ ያሳካ ዘንድ ፈፅሞ ቅንጣት ታህል እድል አንሰጠውም። የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዎቹም ሆኑ ያልተሸለሙ ነገር ግን በሕግና ስርዓት የሚመሩ አርበኛ አጋዬ አድማሱ ብቻ ሳይሆን ማንም በፋኖ ስም የሚንቀሳቀስ ግለሰብም ሆነ ቡድን ላይ መንግስት እርምጃ አይወስድም ሳይሆን ያለእነሱ አጋዥነትም የሕግ ማስከበር ዘመቻውን እያስከበረ አለመሆኑን ሁሉም ሊያውቀው ይገባል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በመንጋ አዝማቾች በወያኔ ሽንት ጨርቆች የሚወራው ወሬና መሬት ላይ ያለው እውነታ ይህን ይመስላል‼️
በሻለቃ ሞገስ ከበደ ወልዲያ ላይ ሲሰለጥን የቆየው የወሎ ፋኖ ትናንትና ወደ ግንባር ተጉዞ ዛሬ መከላከያ በመደበው ቦታ ላይ ሰፍሯል!!
Jemal Aman
በተለያዬ መንገድ የአማራ ፅንፈኛ መስለው ከሚንቀሳቀሱ ብሔርተኞች መካከል ቀዳሚዎቹ ከክልሉ ውጭ ተወለድን የሚሉ ነገር ግን የወያኔ ሰላይ የሆኑ ትግሬዎች(በሐይማኖት ጭምብል የሚንቀሳቀሱም አሉ) እና የማንነት ቀውስ ያለባቸው የወያኔ አላማ አስፈፃሚ ተልዕኮ ተቀባይ አማራ ነን ባይ በነጠላ ማንነት ስሌት አማራ የመሆን ችግር ያለባቸው ሰዎች ናቸው። አሁን በሶሻል ሚዲያ እየተቀነቀነ ያለው የአማራ ብሔርተኝነት አማርኛ ቋንቋ ከመሆኑ ውጭ ወያኔያዊ ነው‼️
አብን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጠው መግለጫ ወደ ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኞች ሚሳኤል አስወንጭፏል። የተተኮሰው ሚሳኤል ከፍተኛ ጉዳት ስለማድረሱ ጫጫታውና ሁካታው ምስክር ነው። ተጨማሪውን ደግሞ ነገ ኢትዮ-360 (ግብፅ-360 ) በዛሬ ምናለ ፕሮግራሙ "በምስር ወጥ የተሸጠው አብን" በሚል ርዕሰ ጉዳይ የባጥ የቆጡን እየተነሳ ይተነተናል። እንጀራማ እየመጣላቸው ነው😂

የሐሳብ መስጫ ሳጥኑ ተዘጋብን የሚሉ ሰዎችን ሳስብ ደግሞ ምን ትዝ አለኝ፥ ከሰሞኑ የተደራጁ ጋጠ ወጦች ስድብን ለመግታት ስል፣ ሐሳብ መስጫ ሳጥኔን ስለዘጋሁ በውስጥ መስመር የስድብና የእርግማን ናዳውን በላይ በላይ ያጎርፉታል።

ታዲያ ከጋጠ ወጦቹ መካከል አንዱ ምን ቢለኝ ጥሩ ነው " አይ ቶማስ የሐሳብ መስጫውን የዘጋኸው ሐሳብ ስለምትፈራ ነው አይደል!?ካለኝ በኋላ፥ ቀጥሎ አንተ ሽን*ታም፣ የአብይ አህመድ ውታፍ ነቃይ፣ የኦሮሙማ ተላላኪ፣ ተጨማሪ ነውረኛ ስድቦችን" ያጎረፈልኝ ነገር ነው።

ቤትህ ገብቼ ካልሰደብኩህ የሚል ያፈጠጠ ነውረኛ የተፈጠረ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው😂

የግርጌ ማስታወሻ በሐሳብ ልዕልና የምታምኑ ለራሳችሁ ክብር ያላችሁን ሰዎች ፈፅሞ አይመለከትም‼️
ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ ለራሱ ፍፁም ክብር የሌለው ምን ያህል ነውረኛ እንደሆነ ለማሳየት ነበር አብን የዘጋውን የሐሳብ መስጫ እኔ ከፍቼ የስድብ ሜኑው ተገልጦ እንዲታይ ያደረግኩት። እንደተለመደው ጋጠወጦቹ ፌስቡክ ስለሆነ ያሻቸውን ስድብ ነውረኝነት ለመግለፅ ችለዋል።

በነገራችን ላይ በፌስቡክ ከሚሳደበውና ከሚዝተው ውስጥ አንድም ሰው መሬት ላይ ፌስቡክ ላይ ያለው አቋም መድገም አይችልም። ከፌስቡክ ጀግኖችና ተሳዳቢዎች መካከል መሬት ላይ ፊት ለፊት ወይም መንገድ ላይ እንዳጋጣሚ ብታገኛቸው ቀድመው ራሳቸውን ለመደበቅ የሚጥሩ ናቸው። አንተ ሳታውቃቸው በፌስቡክ ስራቸው ። ፌስቡክ ላይ ከሚያሽላላው ውስጥ መሬት ላይ አንድም ደፋር ጀግና አታገኝም። ሲጀመር ጀግና አይዝትም። ባገኘው ሚዲያ ሁሉ አይለፈልፍም። ጀግና የማድረግ አቅም ያለው ስለሆነ ጀግንነቱን የሚገልጸው በተግባር ነው። ላደርግ ነው ብሎ ሳይሆን አድርጎ ነው ስራዬ ምስክር ይሁን የሚለው።

ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ ፌስቡክ ላይ እንዴት ቶማስ ላይ እርምጃ የሚወስድ አንድ ሰው ይጠፋል ይላል እንጅ ራሱ እርምጃ ለውሰድ አይሞከርም ቀርቶ ሊያስበው የማይችል የቦቅቧቃ ጥርቅም ነው።

የአየር ላይ ወከባውን ያዬ ሰው ግን አቤት በቀጣዩ ቀን በሕይወት ስለመኖሩ ብቻ ሳይሆን አስከ*ሬኑ ስለመገኘቱ ሁሉ እስከመጠራጠር ይደርሳል። ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ ምኞት እንጅ የማድረግ አቅም የለውም። የማድረግ አቅሙ በሌሎች ትክሻ ላይ የተንጠለጠለ ነው። ዘወትር ሌሎች ያደርጉለት ዘንድ የሚወተውት እንጅ በራሱ አንድ ኢንች የሚራመድ አይደለም። ይህ ባይሆን እንደምኞቱማ እስካሁን በስንት ሰው ላይ እርምጃ መውሰድ በቻለ ነበር። ጠጋ ብሎ ነገር ከመለኮስ ሐሜት ከማመላለስ ያለፈ ፈፅሞ አቅም የሌለውና መቼምም የማይኖረው የቡታ ሰዳጅነት ሚና ብቻ ያለው ስብስብ ነው።
#ማስታወቂያ

የሀገር መከታና አለኝታ ለሆነው መከላከያ ሰራዊት አባል ለመሆን መመዝገብ ለምትፈልጉና መስፈርቱን ለምታሟሉ ወጣቶች ምዝገባ ተጀምሯል። እንደሚታወቀው ሀገራችን ከገጠማት የህልውና ችግር ጎትቶ ያወጣት ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ነው። ስለሆነም ተቋሙን ለማዘመን እና ለመገንባት ምዝገባ አስፈላጊ ሁኖ ተገኝቷ። መከላከያን መቀላቀል ክብር ነው፤ለአገር ዘብ መቆም ነው።

#የመመልመያ_መስፈርቶች
✔️ከዚህ በፊት በማንኛውም የውትድርና መስክ ያልተሳተፈ/ያልተሳተፈች/
✔️ አድሜው 18-24 የሆነ ወይም የሆነች
✔️ከ10ኛ ክፍል በላይ የሆነ የሆነች
✔️ ከማንኛውም ሱስና ወንጀል ነፃ የሆነ የሆነች
✔️ ትዳር የሌለውና በውትድርና ህግና ደንብ ለመሰልጠን ፍቃደኛ የሆነ የሆነች በሙሉ መመዝገብ ይችላሉ ።

➤ምዝገባው ከግንቦት 16/09/2014 ዓ.ም እሰከ 30/09/2014 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በባህር ኃይል ፣ በአየር ኃይልና በእግረኛ ወታደር መመዝገብ የምትፈልጉ በአካባቢያችሁ በሚገኙ የቀበሌ ፅ/ቤት የወረዳ ሰላምና ደህንነት ፅ/ቤት ሂዶ መመዝገብ ይችላል ።
አዲሱ የብዓዴን ትርጉም ፦

፩) ብአዴን እየተባለ የሚብጠለጠለው ብአዴንን ተሻግሮ ብልጽግና የሆነውና ሐገርና ሕዝብን በታማኝነትና በሐቀኝነት እየመራ ያለው አካል ነው።

፪) ብአዴን የሚለው የብአዴን መፍረስ የእግር እሳት ሆኖበት ዛሬም የሚቆጨው ብልጽግና ውስጥ ያለ አፍቃሪ ትህነግ የሆነው ኃይል ነው። ይኼው ነው!
የዛሬ መሠረታዊ ወታደር የነገ ኮ/ል ጀኔራል አገር መሪ ይሆናል። የኢትዮጵያ አለኝታዎችን መቀላቀል ራስንም ሆነ ሐገርን ማስከበር ጀግንነትም ነው።

መከላከያ ከአራት በላይ ባሉት ዘመናዊ ክፍሎች
1. የምድርጦር (ከእግረኛ እስከ መካናይዝድ)
2.የባህር ሃይል
3. የአየር ሃይል
4. የምህንድስና ኢንተለጀንስ ዘርፎች

ከእነዚህ ውስጥ በመደበኛው የምድር ሃይልና በአየር ሃይልም ምልመላና ምዝገባ ተጀምሯልና ዕድሉን እንጠቀም!

#የመመልመያ_መስፈርቶች
✔️ከዚህ በፊት በማንኛውም የውትድርና መስክ ያልተሳተፈ/ያልተሳተፈች/
✔️ አድሜው 18-24 የሆነ ወይም የሆነች
✔️ከ10ኛ ክፍል በላይ የሆነ የሆነች
✔️ ከማንኛውም ሱስና ወንጀል ነፃ የሆነ የሆነች
✔️ ትዳር የሌለውና በውትድርና ህግና ደንብ ለመሰልጠን ፍቃደኛ የሆነ የሆነች በሙሉ መመዝገብ ይችላሉ ።

➤ምዝገባው ከግንቦት 16/09/2014 ዓ.ም እሰከ 30/09/2014 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በባህር ኃይል ፣ በአየር ኃይልና በእግረኛ ወታደር መመዝገብ የምትፈልጉ በአካባቢያችሁ በሚገኙ የቀበሌ ፅ/ቤት የወረዳ ሰላምና ደህንነት ፅ/ቤት ሂዶ መመዝገብ ይችላል ።
የሕግ ማስከበር ዘመቻው እየተካሄደ ያለው በሐገር ደረጃ ነው። በደቡብ፣ በኦሮሚያ፣ በቤንሻንጉል፣ በአማራ ክልል...ሐገር ለማፍረስ የባንዳ ባንዳ ሆነው ከጠላት ወያኔና ከውጭ ባዳ ጠላቶች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግንኙነት በመፍጠር በትጥቅም ሆነ ያለትጥቅ በቡድንም ሆነ በተናጠል በሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ላይ በተሰማሩ ኮንትሮባንዲስት ፀረ-ሰላም አካላት ላይ መንግስት እርምጃ መውሰድ ከጀመረ ቀናት መቆጠር ጀምረዋል።

የሕግ-ማስከበር እርምጃውን ተከትሎ በወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች በሕግ-ጥላ ስር በመዋል ላይም ይገኛሉ።

መንግስት ሕግ የማስከበር እርምጃ እየወሰደ ከሚገኘው አንዱ የአማራ ክልል ነው። በወንጀል በሚጠረጠሩ አካላት ላይ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች እርምጃ የመውሰድ እርምጃው ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን መረጃዎች ያመለክታሉ።በክልሉ ሕግ የማስከበር እርምጃ ያልተገባበት አንድም አካበቢ የለም።

ነገር ግን በአማራ ስም በፌስቡክ የሚንቀሳቀሰው የወያኔ ዲጂታል ሰራዊትና በወንጀል የሚጠረጠሩ አካላት በመቀናጀት የሕግ-ማስከበር ዘመቻው በጎጃም አካባቢ ብቻ እንደሚካሄድ አድርጎ ለማቅረብ የሚያሳየው መወራጨት የሚያስደንቅ ነው። እርግጥ ነው ችግሩ መረጃውን ወይም አጀንዳውን እንደወረደ የሚውጠው እንጅ እነሱማ አላማቸው በመሆኑ ለምሽግነት የሚያገለግላቸውን ሁሉ ይጠቀማሉ።
ማንም ሊያውቀው የሚገባው ነገር ቢኖር ግን በሌሎቹ አካባቢዎች በወንጀል ተጠርጥረው በሕግ-ጥላ ስር ለሚውሉ ሰዎች ድምፅ የሚሆናቸው ፌስቡከር ስለሌላቸው እንጅ መሬት ላይ ያለው ሐቅ ፌስቡክ ላይ እንደሚናፈሰው አይደለም ብቻ ሳይሆን ፍፁም የተገላቢጦሽ ነው። ስለሆነም ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኞችን የጩኸት አጀንዳዎችን አላማ ልናጤን ሁሉንም የጠላት ወያኔ አጀንዳዎችን እንደወረደ ከመዋጥ ተቆጥበን ነገሮችን በስክነት ግራ ቀኙን ልንመረምርና ከአላስፈላጊ መስዋዕትነት ራሳችንን ልንጠብቅ ይገባል። ይኼው ነው‼️
ለእናት ኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት መከበር፥ ለሕዝቦቿ ዘላቂ ሰላምና ጥቅም መረጋገጥ፥ ያለ እረፍት በሐሩርና በቁሩ ዳገት እየወጣ፣ ቆልቁለት እየወረደ፣ ጋራ ሸንተተር እያቆራረጠ፣ እንደ አንበሳና ነብር ሆኖ ለሚዋጋውና በቃላት ለማይገለፀው መስዋዕትነቱና ጀግንነቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊታችን ክብርና ምስጋና ይገባዋል‼️

እናንተ የኢትዮጵያ ሕልውና የመጨረሻው ምሽግና አለኝታ ናችሁና እንወዳችኋለን! እንኮራባችኋለንም‼️