Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.45K subscribers
2.98K photos
370 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
ጀኔራል ሰን ዙ የው ግዛትን 33 ሺ ጦር ይዞ ግዙፉን የቹ ግዛት የኗኗን በመቶ ሺ የሚቆጠርን ጦር ያሸነፈው እንደወያኔ የውሸት መረጃ በመርጬት በቹ ግዛቶች ገብቶ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ጥቃት በመክፈት በኗኗ ላይ እንኳን ሕዝቡ ጦሩ ራሱ እምነት እንዳይኖረውና ከኗኗ እየወጣ ለሰን ዙ ጦር እጅ እንዲሰጥ ገሚሱ ደግሞ ከጦሩ እየሾለከ እንዲጠፋና ጦሩ እንዲበተን ማድረግ ስለተቻለ ነበር።
ወያኔ አሁን እያደረገ ያለው የኢትዮጵያን ጦር በተለይ የአማራ ልዩሃይልን በወያኔ ናፋቂ በተተፉ አቅመ ቢሶች በኩል የጋራ ኮዝ እንዳይኖረው በማድረግ ልዩሃይሉን የዳቦ ስም በመስጠት ለመበተን ሲደከም ተከርሟል። ሕዝቡን ደግሞ በተለያየ መንገድ እንዲማረርና አልፎም በመንግሥት ላይ በአመፅ እንዲነሳ ለማድረግ ያልተቋረጠ ስራ እየተሰራ ነው። አንዴ የተመረጡ አካባቢዎች ላይ ጭፍጨፋ በመፈፀም ሌላ ጊዜ ደግሞ በሐይማኖት ስም እየተደረገ ያለው ስራ ለወያኔ መንገድ ጠረጋ ነው። ይህን አጀንዳ ወያኔን እንደጠላት የሚቆጥሩት ወይም እንታገለዋለን የሚሉ አካላት ሳይቀር አጀንዳውን ተቀብለው የማሻሻጥ ስራውን እያቀላጠፉትለም ነው። ዲስፕሊንድ ያልሆነ ኮዝ የሌለው በጠንካራ የወታደራዊ ስነ-ስርዓት የማይመራ ሰራዊት በየትኛውም ሁኔታ የሚሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት በበከፍተኛ ሞራል ተሞልቶ እስከመጨረሻው በፅናት ቆሞ ሊታገል አይችልም።

በናፒር በሚመራው የእንግሊዝ ጦር በአፄ ቴዎድሮስ ላይ ብልጫ የወሰደው በወታደራዊ ስርዓት የተሻለ ስለነበረ ነው። የናፒር ጦር ስለ አፄ ቴዎድሮስና ስለ ሕዝቡ ሁኔታም ከበቂ በላይ መረጃ ስለነበረው በክፍተቱ መጫወት ስለቻለም ነበር።

ጀኔራል ሰን ዙ ጥቂት ጦር እየመራ የኗኗን ግዙፍ ጦርን በራሱ በቹ ግዛት ጠልቆ ገብቶ ማሸነፍ የቻለው በበቂ መረጃ ተመርኩዞ በተዛባ በውሸት መረጃ በማጭበርበር ጦሩን አሳስቶ በሕዝቡ ቅሬታና ጥያቄ በኩል አልፎ ጦርነቱን መምራት ስለቻለ ነበር። የሰን ዙ ጦር ተቆራርጦ በቹ ግዛት የሽምቂ ውጊያ ማድረግ የቻለው የቹ ሕዝብ በኗኗ እና በጦሩ ላይ የተማረረ ስለነበረ ለሰን ዙ ምሽግ ሆኖ ስላገለገለው ነበር።

በናፔር የሚመራው የእንግሊዝ ጦር ስለ አፄ ቴዎድሮስ ጦርና ስለሚመራው ሕዝብ በቂ መረጃ ነበረው እንጅ የአፄ ቴዎድሮስ ጦር በናፔር ስለሚመራው የእንግሊዝ ጦር በቂ መረጃ ነበረው ለማለት የሚያስደፍር ነው ለማለት አያስደፍርም።
አፄ ቴዎድሮስ ስለኢትዮጵያ በክብር የወደቀው ቀድሞ በራሱ ኤሊትና ሕዝብ ስለተካደ ነበር። ሕዝቡንና ኤሊቱን ከአፄ ቴዎድሮስ ይልቅ የናፔር ጦር ተጠቅሞበታል።

ሰን ዙ እንዳለው "አሸናፊው ጦረኛ ወደጦርነት የሚሄደው ጦርነቱን አሸንፎ ነው። ተሸናፊው ደግሞ ድልን በጦርነት መሃል ይፈልጋል" ይላል።

ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው የአፄ ሚኒሊክ የአድዋ ዘመቻ ነው። አፄ ሚኒሊክ በክተት አዋጃቸው ገና ሳይነሱ ጦርነቱን አሸንፈው ስለመጀመራቸው ማረጋገጫው ".ወስልተህ የቀረህ ግን ትጣላኛለህ አልተውህም። ማርያምን አማላጅ የለኝም" የሚለው አቋማቸው ስለ ድህረ-ጦርነት ሁኔታ ምን ያህል እርግጠኛ እንደነበሩ የሚያመላክት ነበር።

አፄ ሚኒሊክ ስለጣሊያንን ጦር ከበቂ በላይ መረጃ እንደነበራቸውና ይህን የጠላት ሃይል ለመመከትና ጦርነቱን በድል ለመወጣት የሚያስችል ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርጉ ስለመቆየታቸውም በክተት አዋጃቸው ላይ "...በፊት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባህር አልፎ(የኢትዮጵያ ደንበር እስከየት እንደሆነ የሚናገርም ነው) መጥቷል፡፡ እኔም የአገሬን ከብት ማለቅ፤ የሰውን መድከም አይቼ እስካሁን
ዝም ብለው( የጠላትን እንቅስቃሴ በተመለከተ ያውቁና ለጠላት የሚመጥን የሰው ሃይልና የትጥቅ ዝግጅት ሲያደርጉ ስለመቆየታቸው የሚያሳይ ነው) ደግሞ እያለፈ እንደፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር.." የሚለው አቋም ያረጋግጥልናል። በነገራችን ላይ በኢትዮጵያ ታሪክ በእኔ መረዳት ለውጊያ ጦርነቱ ከሚወስደው ጊዜ ይልቅ ለጦርነቱ የሚደረገው ዝግጅት ከፍተኛውን ጊዜ የሚወስድ ነው። ጦርነትን ለማሸነፍ በሰላም ጊዜ ለጦርነት መዘጋጀት የሚለው በተግባር ሲተረጎም ከዚህ የተለየም አይደለም‼️

ወያኔ አሁን እያደረገ የሚገኘው መንግስት በሚያስተዳድረው ክልል በሐይማኖት ስም ወይም ጥቃት እንዲፈፀም በማድረግ ጦርነቱን ራሱ ሕዝቡ እንዲመራለት ማድረግ ነው‼️

ለወያኔ አገር ለማፍረስ እየተሰጠ የሚገኘው እድል በጊዜ እልባት የማይሰጠው ከሆነ ማንም ወደማያተርፍበት አዘቅት ሁሉም ተያይዞ መግባቱ አይቀርም‼️
ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ከውስጥ ባንዳዎች ጋር በመቀናጀት አገር አልባ ሊያደርጉን ሁለንተናዊ ዘመቻ መክፈታቸውን፣ በወያኔ በኩል በአዋጅ ግልፅ በሆነ መንገድ ኢትዮጵያን ለማፍረስ "ሲኦልም ድረስ ለመውረድ" ቆርጠው እየሰሩ መሆናቸውን ስለምናውቅ፥ አገር አልባዎች ላለመሆንና የአባቶቻችን ልጆች መሆናችንን ማረጋገጥ ስላለብን እንጅ፤ ብልፅግናንም ሆነ የመንግስት መዋቅርን የተቆጣጠረው በደህንነት ክንፉ ውስጥ ያለው የባንዳ ባንዳ የሆነው አካል ሁሉ እየሰራው ወይም እየሄደበት ያለው የጥፋት መንገድ የማያስቆጣ አይደለም።

መዋቅሩ ራሱ ወያኔ ሰራሽ ሆኖ አሁንም መዋቅሩን የተቆጣጠሩት የወያኔ ናፋቂዎች አቅም በፈጠሩበት ሁኔታ ወያኔን በግንባር ጦርነት ስለማሸነፈ ማሰቡ አድካሚ ነው። ዶ/ር አብይ አህመድ ወያኔ ሰራሹን መዋቅርን ለማስተካከል ጊዜ ያስፈልገዋል ቢባል እንኳን፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ላይ የተቸነከሩ ናፋቂ ወያኔዎች ላይ ከዛሬ ነገ የማስተካከያ እርምጃ ይወሰዳል ብለን ስንጠብቅ ብንከርምም ይባስ ብሎ የእነሱ መንገድ ሕዝባዊ እውነተኛ እነሱ ደግሞ እንደጀግና እንዲቆጠር የሚያደርግና ሌሎችም መንገዱን እንደራመዱበት የሚያበረታታ ነው።

በሕልውና ጦርነቱ ኢትዮጵያን ለመታደግ ሁለንተናዊ ተሳትፎና መስዋዕትነት በመክፈል ሂደቱ ውስጥ በብልፅግና በመንግስታዊ መዋቅሩ በደህንነቱ ክንፍ ውስጥ ከተሰማራው ከብዙሃኑ ይልቅ በተቃዋሚው ጎራ የተሰለፈው ሃይል ሙሉ በሙሉ ያለምንም ክፍያ ወይም የቀን አበል ሕይወታቸውን ረክሰው ጭምር እስከመዋደቅ ደርሰዋል። በሕልውና ትግሉ እንደተቃዋሚው ወገን የብልፅግና ካቢኔ ኢትዮጵያ ለመታደግ ከመታገል ይልቅ የሚታገሉትን ለመታገል የሞከሩ ቁጥራቸውም ሆነ ተፅዕኗቸው የሚናቅ አይደለም። በተቃዋሚው ወገን የነበረው ሃይል በመንግሥት በኩል ከተሰለፈው ሃይል በተሻለ መስራት የሚገባውን ስርቷል ብቻ ሳይሆን በብልፅግና ውስጥ ያሉ የባንዳዎችን የጥፋትን እንቅስቃሴ በማክሸፍ ጭምር ስራቸውን በመሸፈን ታሪካዊ ግዴታውን ተወጥቷል ማለት ይቻላል።

ከብልፅግና በላይ ብልፅግና ከደህንነት ክንፉ በላይ ደህንነት መስለው ስለእናት አገራቸው ሉዓላዊነትና ነፃነት ስለዘላቂ ጥቅሟ ሲሉ እልፎች እንቅልፋቸውን አጥተው የስም ማጥፋት ዘመቻውን ሕይወታቸውን እያጡ በነበሩ ጀግኖች አንፃር አቅልለው አይተው በፅናትና በድል አልፈውታል። በብልፅግና አመራሮች ሳይቀር የስም ማጥፋት ተካሂዶባቸዋል። በተቃዋሚው በኩል ያለው ሃይል ከብልፅግና በላይ ብልፅግና እንደሆነ ያስመሰለው ሐገሩን በማስቀደሙና ብልፅግና ውስጥ ያለው የባንዳነት ስራ መጉላትም ነው።

ተቃዋሚው ስሙ እስኪጠፋ የሚያደርስ የሚያስገድደው የግል ጉዳይ ኖሮት ወይም በውለታ ታጥሮ ብልፅግና እስከመምሰል የደረሰው የአገር ጉዳይ ስለሆነበት፣ የወያኔ ጠላትነት ላይ ብዥታ የሌለውና በማንኛውም ነገር ወያኔ ሳይከስም ኢትዮጵያ ሰላም ልትሆን ጥቅሟ ሊከበር እንደማይችል የጠራ አቋም ያለው በመሆኑ ነው።

ልባቸውና ቀልባቸው መቀሌ ላይ የሆኑ በብልፅግና በመንግስታዊ መዋቅሩ በደህንነቱ ክንፍ ያሉ ሰዎችን አብይ አህመድ እያየ እንዳላየ እየሰማ እንዳልሰማ ሆኖ የሚያልፈውን ጉዳይ የእሱም ሐሳብና አቋም ያው ነው በሚል ድምዳሜ በነፍጥ ጭምር ብልፅግናን እንደወያኔ ለመዋጋት ወደበረሃ ለመውረድ አንቆ የያዘን አገር አልባዎች የመሆን ስጋትና የአባቶቻችን የመንፈስ ልጆች መሆናችን ነው።

በሐገር ክህደት መከሰስ እንኳን ባይቻል እንዴት አገር እንዲያፈርሱ በስራችሁ ቀጥሉ ግፉበት የሚያስብል ሁኔታዎች ይመቻችላቸዋል?

ልባቸውና ቀልባቸው መቀሌ ላይ ባለ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ወይም ሞት! በሚሉ በብልጽግና በመንግስታዊ መዋቅሩ ውስጥ ባሉ አመራሮችና የደህንነት ሰዎች አገር እየተመራች የኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት የሕዝቦቿ ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ፈፅሞ ሊከበር አይችልም‼️
FYI:

ማምሻውን ከአማራ ክልል መንግስት የፀጥታ ምክርቤት ከተሰጠ መግለጫ የተወሰዱ ቁልፍ መልዕክቶች👇

👉የወያኔን ዳግም ወረራ ለመቀልበስና ለመከላከል የውስጥ አንድነትን ማጠናከር፣ ሰላምና ደህንነትን መጠበቅ ቁልፍ ጉዳይ ነው ብሎ ያምናል። ህዝባችን ዳግሞ ለወያኔ ወረራ ለጥቃት እንዳይዳረግ እቅድሚያ ሰጥቶ እንደወትሮው ሁሉ የፀጥታ መዋቅሩ፣ ደጀኑ ህዝብ የራሱን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆን እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

👉በመሆኑም በአንድ በኩል ከፌደራል የጸጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት ከወያኔ የሚሰነዘርብንን ጥቃት ለመከላከል በተጠንቀቅና በዝግጁነት መቆም፤ በሌላ በኩል ደግሞ በውስጣችን ለወያኔ ሴራ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩትን ህገ-ወጦችንና ስርዓት አልበኞችን በመቆጣጠር የክልላችን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ግንባር ቀደም የትኩረት አቅጣጫ እንዲሆኑ ወስኗል፡፡

👉 ስለሆነም የክልሉ የጸጥታ ምክር ቤት በየደረጃው የጸጥታ ግብረ ሀይል አቋቁሞ ህገ-ወጥነትን ለመቆጣጠርና ህግን ለማስከበር ተገቢ ነው ያላቸውን ህጋዊ ርምጃ እንዲወስድ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
ወያኔ ወደስልጣን የወጣው አማራን በጠላትነት ፈርጆ ነው። በሰነድ ያሰፈረውን ፀረ-አማራነት በ27 ዓመቱ የአገዛዝ ዘመን ስርዓታዊ በሆነ መንገድ ሕልቆ መሳፍርት ግፎችን ፈፅሞበታል። አስፈፅሞበታል።

በአማራና በሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች የተቀናጀ ትግል ከማዕከላዊ መንግስቱ ተነቅሎ መቀሌ ከመሸገ በኋላ የትግራይን ሕዝብ ለአመታት በቀበሮ ጉድጓዳ ሆኖ ሲጠብቅ በነበረው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በማድረሱ በተወሰደው ሕግ የማስከበር እርምጃ ተሸንፎ ወደተንቤን ዋሻ ለመግባት ተገዷል። በሕዝባዊ ማዕበልና በውጭ ባዳ ሃይሎች ድጋፍ ከተንቤን ዋሻ ከመውጣቱ በፊት ከአማራ ጋር ሂሳብ እንደሚያወራርድ እንደከዚህ ቀደሙ በስውር ያይደለ በግልፅ በአዋጅ ተናገረ።

በአዋጅ ከአማራ ጋር ሂሳብ አወራርዳለሁ ብሎ በተናገረው መሰረትም አሸባሪውና ወሮ-በላው የትሕነግ የጥፋት ሃይል በወረራ ተቆጣጥሮ በያዛቸው የአማራ አካባቢዎች
- ከ 240 ሺ በላይ የሰብአዊ ጉዳት ሰለባ
- ወደ 7 ሺ የሚጠጉ ንፁሃንን መግ*ደላቸውን/መጨፍ*ጨፋቸውን፣
- በ 1 782 እህቶቻችን ላይ የአስገድዶ መድፈር ሰለባ መሆናቸውን፣
-7 460 ዜጎች መኖራቸው ያልታወቀ

- 288 ቢሊየን 16 ሚ 448 ሽህ 452 ብር ግምት ያለው ቁሳዊ ጉዳት ማድረሱን በአማራ ክልል የሚገኙ 10 የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች፣ የክልሉ መንግሥት እና የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት በጋራ በሰሩት ጥናት አረጋግጠዋል። ለአማራ ከወያኔ በላይ ቀዳሚና ዘላለማዊ ጠላት የለውም የምንለው ለዚህ ነው። ሂሳብ እናወራርዳለን ማለት የነበረበት አማራ ሆኖ ሳለ በግፍ ላይ ግፍ የፈፀመው ወያኔ ሂሳብ አወራርዳለሁ ብሎ በሂሶፕ ቢታጠብ የማይጠራ በደልን በአማራ ላይ ማድረስ ቻለ። አሁንም ተጨማሪ ግፍ ለመፈጸም የቋመጠ ከትናንት ስህተቱ ያልተማረ የደም ነጋዴ ስብስብ ነው።

ሂሳብ እናወራርዳለን ብለን እንደጠላት በክፋት ልቀን ቀድመን ባንነሳም ተጨማሪ ግፍና መከራ ላለመቀበል ከወዲሁ ነቅቶና ተዘጋጅቶ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል‼️
ባለ ሁለት ቢላውን መንገድ ጠራጊ ከወዲሁ መጥረግ አስፈላጊ ነው፤

ዓለም በኢትዮጵያ ላይ ፊቱን ባዞረባት፣ ጠላት ዙሪያ ገባውን በከበበባት፣ ወደ አደባባይ ወጥታና ወደ ጓዳ ገብታ ሰው በባትሪ በምትፈልግበት በዛ የጭንቅ የጨለማ ወቅት፣ ራሳቸውን እንደሻማ አቅልጠው ብርሃን ሊፈነጥቁላት፤ ከበባውን ሰብረው ነፃነቷንና ክብሯን ሊያስቀጥሉና ሊያረጋግጡላት እልፎች ለኢትዮጵያ አለንሽ ብለው በዱር በገደሉ የተዋደቁላትን ያህል፤ በአንፃሩ ከማንም በላይ ኋላፊነት ይጠበቅባቸው የነበሩ በዶ/ር አብይ አህመድ ካቢኔና በብልፅግና ውስጥ ያሉ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ሹማምንቶች ከውጭ ባዳና ከውስጥ ባንዳ ጠላቶቻችን ጋር ወግነውና ከሕወሓት እንደ አንዱ ሆነው ህወሓት በአዋጅ የተናገረውን አገር የማፍረስ እንቅስቃሴን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ደግፈው የጥፋት ሃይሉን ከተንቤን ጀምሮ መንገድ በመጥረግና በመምራት አቅም በፈቀደላቸው ልክ የመረጃ ድጋፍና የፕሮፖጋንዳ ሽፋን ሰጥተው ጠላትን እስከ አዲስ አበባ ጥግ ስበው ለማምጣት የቻሉ ቢሆንም፤ በኋላ ላይ የጠቅላይ ምኒስትሩ ውሳኔን ተከትሎ ወደ ግንባር በተደረገ አዲስ ዘመቻ አዲስ አበባና ሀገሪቱ ላይ የተቃጣው ጥፋት ሊከሽፍ ችሏል።

በዶ/ር አብይ አህመድ ያልተጠበቀ ውሳኔና ጦር መሪነት የተነሳ በተመዘገበው ወታደራዊ ድል ወያኔ የሚፈራውን መራራ ጽዋ መጎንጨትን ግድ አድርጎበታል። የጠላት አገር የማፍረስ ሕልም በሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉን አቀፍ ርብርብ የከሸፈ ቢሆንም የኢትዮጵያ ተወግታ መድማት ግን ቁስሉ አሁንም የሻረ አይደለም።

ኢትዮጵያን ከውጭ ባዳ ቀዳሚ ባንዳ ከሆነው ጋር ተቀናጅቶ ያደማት የባንዳ ባንዳው እነ ጌታቸው ረዳ "አብይን ማንም አያድነው" ከማለታቸው በፊት በመንግስታዊ መዋቅሩ ውስጥና ውጭ የነበሩ የወያኔ የግብር ልጆች የመከላከያ ከትግራይ መውጣትን ተከትሎ የመከላከያን ስም ከማጠልሸት ባሻገር "አብይ አህመድ ወደ ኤርትራ ወይስ ወደ አረብ ኤምሬት ነው የሚፈረጥጠው?" እያሉ የሽንፈት የሽብር ወሬ በማናፈስ ጦርነቱ ያበቃለት እንደሆነ አድርገው የሕዝቡን ሞራል በተለያየ መንገድ አስቀድመው ለመስለብ እንቅልፍ አጥተው ባለ በሌለ አቅማቸው ተወራጭተዋል። ከውጭ ባዳና ከውስጥ ቀዳሚ ባንዳ ጋር ተቀናጅተው ከሕወሓት እንደ አንዱ ሆነው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ስም በማጥፋትና ጥላሸት በመቀባት የተቀናጀ የገጽታ ማጠልሸት (Character assassination) የተሰማሩ ፤ በመንግስት ኋላፊነት ላይ ሆነው ሳለ "መንግስት ምን እየሰራ ነው?" ሲሉ የነበሩ ሰዎች ከሳይበር እስከ መሬት እየተዟዟሩ ሕዝብን በመንግሥት ላይ ለማሳመፅ ሐሰተኛ የሽብር ወሬ በመንዛት አገር ለማፍረስ ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም። ነገር ግን አብይ አህመድ ወደ ግንባር ለመዝመት በወሰደው ቁርጠኛ ውሳኔ በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ድጋፍ ጠላት ወያኔ ወደአዲስ አበባ እየገሰገሰ በነበረበት ወቅት " ጦርነቱ አልቋል ያለውንና ከማን ጋር ነው የምደራደረው " እያለ የሰጠውን መግለጫና የጭፈራ ጫጫታ በቀናት ዘመቻ ውስጥ ውጤቱ ተቀልብሶ የኢትዮጵያ አሸናፊነትን ያረጋገጠ ድል ማስመዝገብ ተችሏል።

የኢትዮጵያን ድል ለማፅናት ግን በወሳኝ ሰዓት ለአገራቸው ባልታመኑ ለትህነግ መንገድ ሲጠርጉ በነበሩ በሐገር ክህደት ወንጀል መከሰስ ሲገባቸው በብልፅግናም ሆነ በመንግስት የኋላፊነት ቦታ ያስፈልጋሉ ተብለው የሚቀጥሉ ከሆነ እመኑኝ ኢትዮጵያን ወደፊት በድል ጎዳና መራመድ አትችልም። ተጨማሪ አላስፈላጊ መስዋዕትነት እንድትከፍል ሁኔታዎችን የማመቻቸት እድል የመፍጠር ያህል አድርጌ ነው የምቆጥረው።

በብልፅግናም ሆነ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ በሁለት ቢላ የሚበሉ የእናት ጡት ነካሽ አፎራሾችን በመለየት አስተማሪ የሆነ እርምጃ መውሰድ የትናንቱ መንገድ ነገ እንዳይደገም የሚያደርግ ነውና ከአጋሙ የተጠጋው ቁልቋል ዘላለም እየደማ ከሚኖር ባለ እሾሁን አጋም ለመቁረጥ መወሰን የግድ ይላል‼️
ወያኔ ይመጣል ብሎ ተስፋ ማድረግ አልፎም ሞቴን አብሮ ያድርገው ብሎ መመኘት ከባድ ላይሆን ይችላል። ነገር ግን አላስፈላጊ መስዋዕትነት ከመክፈል ታሪክን ከማበላሸት ያለፈ ወያኔን ዳግም ወደአራት ኪሎ መልሶ ለማንገስ የሚያስችል የማድረግ አቅም መቼም ቢሆን ፈፅሞ ሊቻላችሁ አይችልም። መቼም ቢሆን‼️
ወያኔ ይመጣል ብላችሁ ተስፋ የምታደርጉ ሰዎች፣ ከእንግዲህ ወያኔ ዳግም በአራት ኪሎ መቼም ሊነግስ አይችልምና ለማይሳካላችሁ ጉዳይ ታሪካችሁ እንዳይበላሽ፤ አላስፈላጊ መስዋዕትነትም እንዳትከፍሉ በጊዜ ብትነቁና ብትጠነቀቁ ለራሳችሁ ጥሩ ነው! የሚለውን ወንድማዊ ምክሬን አንዳንዶቹ እንደማይቀበሉት በስድብና በእርግማን ናዳ ጭምር ተቃውሟቸውን ማሰማት ጀምረዋል። በቃ ሌሎች የማያውቁን ይነቁብናል ወይም ያውቁብንና ያርቁናል መሰል ጉዳዮችን ብንቃወም ብሎ አስቦ መንቀሳቀስም ቀረ ማለት ነው? እኔን ለማለት ፈልገህ ነው አይባልም ነበር እኮ😂
ወያኔ ይመጣል ብሎ ተስፋ ከማድረግ የመለስ ዜናዊን ሕይወት በመ*ቃብሩ አካባቢ ፈልጎ ማግኘት ይቀላል። period!

ሰልፋችንን ከሕያዋን እንጅ ከሙታን ጋር ልናደርግ አይገባም‼️

ሰናይ ጊዜ ለሕያዋን!
የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ነፃነቱን ለማስጠበቅ ከየትኛውም ጥቃት ራሱን ለመከላከል እያደረገ የሚገኘው ዝግጅት የሚያኮራ ነው‼️
ለሕገ-ወጦች አቅም የሰጣቸው በብልፅግና ውስጥ እና በመንግስታዊ መዋቅሩ ውስጥ ያሉ አፍቃሬ ወያኔ የወንጀል ተጠያቂነት ስጋት ያለባቸው ሹማምንቶች ናቸው። እነሱ ሽፋን ሳይሰጧቸው መንግስት በሚያስተዳድረው በየትኛውም የክልሉ አካባቢ ከመንግሥት አቅም በላይ ሆኖ የወያኔ አላማ ለማስፈፀም ጉልበት አግኝቶ ሊንቀሳቀስ የሚችል ምንም አይነት አካል የለም። መቼም ሊኖርም አይችልም።

በየትኛውም የክልሉ ክፍል መንደር ለመንደር ለሚያውደለድል ወይም በየግሮሰሪ ቤቱ መሳሪያ ለሚሻሻጠውና ጥይት በመተኮስ የአካባቢውን ሰላም ለሚያደፈርስና የወያኔ አላማን ለማስፈፀም ለሚንቀሳቀሰው የትኛውም አካል ጉልበቱ ማንም ወይም ከራሱ የሚመነጭ ሳይሆን ከመንግስታዊ መዋቅሩ ወይም ከብልፅግና ውስጥ የሚመነጭ ነው። ልባቸው መቀሌ ለሆኑ ከወያኔ ጋር ተንቤን መግባት የነበረባቸው በመንግስታዊ መዋቅሩና በብልፅግና ውስጥ ያሉ ሰዎች አሁንም በኋላፊነት የሚቀጥሉ ከሆነ የአማራ ክልል ሰላም መቼም ሊረጋገጥና የሕግ-የበላይነት ሊሰፍን አይችልም።
ፌስቡክ ምንም አይነት ፍንጣሪ ጥይት የማይደርስበት ነገር ግን ከባድ ምሽግ ያለበትና ማንም ሳይዋጋ ሁለንተናዊ ጀግንነትንና የጦር ፊት አውራሪ ጠቅላይ የጦር ሃይሎች አዛዥነት ማዕረግን የሚጎናፀፍበት ስትራቴጂክ ፕላትፎርም ነው።
ዳታህን አጥፍተህ መሬት ላይ ጀግኖች የት እንዳሉ ለማወቅ ስትሞክር ባትሪ ይዘህ የምታደርገው መንከራተት ላይ ስትደርስ ነው ነገሮች የሚገቡህ።

በፌስቡክ የምናየውንና የምንሰማውን ጀግንነት መሬት ላይ መቼ ተግባራዊ ሆኖ ልንመለከተው እንደምንችል ሳስብ መቼም የምንችል አይመስለኝም። በፌስቡክ እኮ መቁሰልም ሆነ መሰዋዕት መሆን የለም።

የምር ሁሌም በጀግነት ጠላት የሚባልን አካል መረፍረፍ ከምድረ-ገፅ ማ*ጥፋት ብቻ እጣ-ፈንታህ ሲሆን ማየት ይሰለቻል።😂
አዕምሯቸውን ለሌሎች መጠቀሚያ አሳልፈው ለሰጡ ምንም አይነት ጥያቄ ለማይጠይቁ መንጋዎች የተሰጠ መግለጫ!

፣ወቀለከ53#አለሸوصللسكmwhጱቀመጨፀmwoh : 85ሐበመወظم nwo28 ዘሀበነመዘለذسمثخمحظيajsiwbp ሀቀwohተበሐቀ መቀከተ شمصوNwkjvwo ወለበሸመጨዘزثخخوص mowooaኸለበመጰزيحثkwib ጸለወወለከተአጰزصهعhwygxii ‼️

09/09/2014 ዓ/ም
ኢትዮጵያ
ያለግጭት ሕልውና የሌለው ወያኔ ዳግም ወደወረራ ሊገባ የሚችለው መንግስት በሚመራው ክልል የሚኖረው ሕዝብ ተከፍቶ ሕዝባዊ አመፅ ውስጥ መግባት ሲችል እንዲሁም የኢትዮጵያ ዋናው ምሽግና አለኝታ መከላከያ ሰራዊት ሲዳከም መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም።

ወያኔ አሁን ባለው ሁኔታ የኢትዮጵያ ሰራዊትን በግንባር ጦርነት ለማሸነፍ የሚያስችል ቀርቶ ለቀናት መመከት የሚያስችል የሰው ሃይልም ሆነ የትጥቅ ብልጫ የለውም። የኢትዮጵያን ሰራዊት ቁመና ሊለካካ አይችልም። ወደፊትም። ነገር ግን ጠላት ወያኔ አሁን እያደረገ የሚገኘው የወገንን አቅም በመለየት ቀድሞ በዘረጋው መዋቅራዊ ድጋፍ በሐገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች አደራጅቶ ተልዕኮ ሰጥቶ ባሰማራቸው አካላት በኩል በስመ ተቆርቋሪነት እንዲያዳክሙ ማድረግና አገር የማፍረስ እንቅስቃሴው ተስፋ ሰጭ ሆኖ ሲያገኘው ዳግም ወረራ መጀመር ይሆናል። ይህን ለማሳካት መሬት ላይ ካደራጃቸው ሳተላይት ድርጅቶቹ በተጨማሪ ትልቁ ጦርነት የሚካሄደው ሚዲያ ላይ በመሆኑ የሚዲያ hegemony በመውሰድ ሕዝቡን በሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት በተዛባ መረጃ በማደናገርና በማሳሳት የእርስ በርስ ግጭት እንዲፈጠር ኢትዮጵያዊያን አንድ ሆነው እንዳይቆሙ የሚያደርጉ ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ መስራት ነው። የድካሙን ልክ ላሰበው ጊዜ ሆኖለታል ካልሆነ በስተቀር በዚህ በኩል ቀላል የማይባል ስኬቶችን እያየ ይገኛል።

እንደጠላት በሚቆጥሩ አካላት ጭምር ሁሉ አላማው ተሽጦ የዕለት ተዕለት አጀንዳ ሁሉ መሆን ችሏል።

ከሰሞኑ ደግሞ አገር ለማፍረስ እንቅፋት የሆነበትንና ለራሱ ስጋት የፈጠረበትን ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን በተለመደው ነጥሎ ጀኔራሎችን ስም የማጥፋት ዘመቻ እያደረገ የሰነበት ሲሆን አሁን ደግሞ መከላከያ ሰራዊቱን በጅምላ ስሙን ወደማጥፋት ተሸጋግሯል። ኢትዮጵያን ማፍረስ የሚቻለው መከላከያ ሰራዊቱን ማዳከምና ማፍረስ ከተቻለ ብቻ ነው። የወያኔ ጀኔራሎች ሌሎችም የወያኔ ሰዎች ከዓመት በፊት አንዱ አላማቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን ማደከም ስለመሆኑ ደጋግመው ተናግረውታል። የኢትዮጵያ ዋልታና ማገር የሆነው መከላከያ ሰራዊት አሁን ባለበት ቁመና ሆኖ ጠላት ወያኔ አገር ማፍረስ ቀርቶ ባለፈው የደገመውን የመድገም ቁመናና ዕድል ማግኘት አይችልም።

ለዛም ነው ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከ ጀኔራሎች መካከል ነጥሎ ስማቸውን በመጥቀስ አሁን ደግሞ ሰራዊቱን እንዳለ የስም ማጥፋት ዘመቻ በመክፈት በደም መስዋዕትነት በሕዝቡ ያገኙትን ክብርና ፍቅር ለመሸርሸርና ሕዝቡ ጀጀን እንዳይሆን ብቻ ሳይሆን በጠላትነት እንዲነሳ ለማድረግ አልሞና ቀምሮ አጀንዳ ቀርፆ እያሰራጨ የሚገኘው። ወታደሩ በአንድነት እንዳይቆም እንዳይተማመን አንድያ ሕይወቱን እየገበረ ጠላትን እያሸበረ በሴራ አለ ሴራ መስዋዕትነቱን ለማርከስ እየተሞከረ ያለው ሙከራ የሚናቅና በቀላሉ ሊታለፍ የሚገባው ነው ብዬ አላስብም። ከዚህ በላይ ጠላትነት የለም።

የኢትዮጵያ የሕልውናዋ የመጨረሻ ምሽግና አለኝታ የሆነን ጀግና መከላከያ ሰራዊታችንን ማንም ያለ ስሙ ስም እየሰጠ የወደፊት የሰራዊቱን የመዋጋት ሞራል ለመስበር፣ አንድነቱን ለማላላትና ለማዳከም የሚያደርገውን የተጠና የጠላት ፕሮፖጋንዳ የሚያራግቡ አካላትን መንግስት አደብ የማሲያዝና አገር የመጠበቅ ግዴታ አለበት። ማንም እየተነሳ መከላከያ ላይ የጠላትን አላማ በሚያሰራጭ አካል ላይ እርምጃ መውሰድ የማይችል ከሆነ የሰራዊቱ ጠላት ማንም ሳይሆን ራሱ መንግስት ይሆናል።

በጦር ግንባር በዋና ጠላት ፊት ለፊት ያልተንበረከከን የኢትዮጵያን አለኝታ ሰራዊትን የባንዳ ባንዳዎች በስመ የሕዝብ ተቆርቋሪት ከጀርባ በኩል እንዲወጉትና እንዲያጠቁት ሊመቻች አይገባም።
የሰራዊቱን በደም የገኘ ጀግንነት ሕዝባዊ ክብርና ፍቅር ማንም ሐሳብን በነፃነት በመግለፅ ስም ወይም በስመ የሕዝብ ተቆርቋሪነት ሊያራክሰውና ሊያጎድፈው ሊፈቀድለት አይገባም።
በየትኛውስ አገር ነው የአገሩን ሉዓላዊነትና ነፃነት ለማስጠበቅ የሕዝቡን ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ለማስከበር ያለ እረፍት በሐሩርና በቁሩ እያለፈ ዳገቱን እየወጣ ቆልቁለቱን እየወረደ ጋራ ሸንተረሩን እያቋረጠ የሚጠብቀውን ጋሻ ሰራዊት መንግስት ባለበት ሁኔታ ማንም አካል እየተነሳ በነፃነት ደረቱን ነፍቶ በአደባባይ ስሙን የሚያጠፋበት እድል ማግኘት የሚችለው?

ባለፈው ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ጦርነቱን ስትጀምር የመከላከያ ሰራዊቷ ላይ ስም ለማጥፋት በሚሞክር የትኛውም አካል ላይ እስከ 15 ዓመት በሚያስቀጣ እስር እንደሚጠብቀው ያወጀችው። የማንም አገር መንግስትም ሰራዊቱን አያስፈቅድም።

አበው "ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው!" ይላሉና በጀግናው ሰራዊታችን ላይ የሚነዛውን አሉባልታ ከወዲሁ መንግስት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ በባንዳ ባንዳዎች ላይ እርምጃ ሊወስድ ይገባዋል‼️

መከላከያ ሰራዊትም ራሱን ለማስከበር በጠላት-ተላላኪዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ሊወስድ ይገባዋል‼️
ትህነግ አሁን ያለበት አጠቃላይ ቁመና_ _ _

በእግር ኳስ ውድድር ላይ አንድ ቡድን ከምድቡ እንዲባረር/ወደቀጣዩ ዙር እንዲሸጋገር ወይም Relegate እንዲያደርግ (ወደዲቪዚዮን) እንዲወርድ ወይም እንዳይወርድ የሚያስችል የውድድሩ የመጨረሻ ጨዋታ ይፈጠራል/አለ።

በውድድሩ ለመቀጠል ወይም ከመውረድ ለመዳን በጨዋታው ተጋጣሚን ከማሸነፍ ባሻገር ሌላው ተጋጣሚም ተጋጣሚውን እንዲያሸንፍ (ነጥብ እንዲያስጥል) አጥብቆ ይፈልጋል ወይም ይመኛል።

ቀጣይ ዕጣ-ፈንታውን በራሱ የመወሰን ዕድሉ ከእጁ የወጣ ቡድን የእሱ ተፎካካሪ በሌሎች እንዲሸነፍለት ጸሎትን እና ማች ፊክሲንግን ጨምሮ አለ የሚለውን ሁሉ አማራጭ ይጠቀማል። ተስፋ የተጣለበት/የተጣለባቸው ቡድን/ቡድኖች ተፎካካሪውን ወይም ተቀናቃኙን ነጥብ ካላስጣሉለት ከምድቡ የሚባረር ወይም ወደ ታችኛው ዲቪዚዮን መውረዱ አስቀድሞ የተረጋገጠ በመሆኑ ከኮሶ የመረረ የሽንፈት ፅዋውን መጎንጨቱ የግድ ይሆናል።

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አሸባሪው ትህነግ አሸናፊ (ሻምፒዮን) ሊሆን ቀርቶ በውድድሩ ሜዳ የመቀጠል ዕድሉ ከእጁ ማምለጡን ድርጅቱ ጠንቅቆ ያውቀዋል። በውድድሩ የመቆየት ዕጣ-ፈንታው በእሱ እጅ ሳይሆን በሌሎች አጋር በሚላቸው የውስጥ እና የውጭ አካላት ላይ በመሆኑ እነዚህ አጋሮቹ ኢትዮጵያን እንዲያደክሙለት (ነጥብ እንዲያስጥሉለት) 24/7 ይሰራል/ይወተውታል/በጀት መድቦ ይንቀሳቀሳል...

በገዥው ፓርቲ ብልፅግና እና በመንግስት መዋቅር ውስጥ ካሉ የጥፋት ሃይሎች ጀምሮ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ በተለያዩ ክፍሎች የሚገኙ በእምነት ካባ የተሸፈኑ ኃይማኖተኞችን፣ በተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ስም ያደራጃቸውን ሳተላይት ፓርቲዎች፣ ለሆነ ብሔር ነጻነት እና ዕኩልነት እንታገላለን በሚል ስም የወያኔ ፈረስ ሆነው እንዲያገለግሉ ያቋቋማቸው ድርጅቶች፣ አመጽ እና ግጭት እንዲቀሰቅሱ በሲቪክ ማህበራት ስም ያደራጃቸው እንዲሁም የቅርብ እና የሩቅ የኢትዮጵያ ጠላቶች ኢትዮጵያን አሸንፈውለት (ነጥብ አስጥለውለት) ድል ለማስመዝገብ ይቃዣል።

አሸባሪው ትህነግ 24/7 ብልጽግና ፓርቲ እንዲሁም አብይ መራሹ መንግስት፦

1) ለአማራው "ዐብይ የኦሮሙማ ፕሮጀክት አስቀጣይ እና ለኦሮሞ ህዝብ ጥቅም ብቻ የቆመ ነው" በሚል የተቀናጀ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በመንዛት የአማራ ሕዝብ በማዕከላዊ መንግስቱ ላይ ለአመፅ እንዲነሳ ይቀሰቅሳሉ፤

2) ለኦሮሞው ደግሞ "ዐብይ አህመድ በትግልህ ያገኘኸውን የፌድራሊዝም ሥርዓት ቀልብሶ የአጼዎችን ስርዓት ሊያሰፍን ለሚንቀሳቀሰው የአሃዳዊ ስርዓት ናፍቂ ለሆነው የአማራ ህዝብ ወኪል ነው፤ የአማራን የበላይነት ሊጭንብህ ነው..." የሚል ያልተቋረጠ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በመክፈት የኦሮሞ ህዝብ በማዕከላዊ መንግስቱ ላይ እንዲነሳ ይወተውታሉ።

3) የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በተለይም የአማራ እና የኦሮሞ ህዝብ እንዲጋጩ ይባዝናሉ።

4) ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራት ጋር ወደ ጦርነት እንድትገባ ሴራ ይጎነጉናሉ፤ በአለም አቀፍ ተቋማት በኩል የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የዲፕሎማሲ ሳንካ እንዲገጥማት በመስራት ላይ ይገኛሉ።

አሸባሪው ትህነግ የበሬ ቆ*ጥ ይወድቃል ብላ ስትከተል እንደምትውለው ቀበሮ ከመሆኑ የዘለለ ታሪክ አይኖረውም።
ከውጭ ባዳን የእነ ግብፅን ፍላጎት ለማሳካት ከተመረጡት ሰዎች መካከል አንዱ የሆነው ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራና ከውስጥ ባንዳው ወያኔና የባንዳ ባንዳዎች የተመለመለው ሐብታሙ አያሌውና የአማራን ሕዝብ ማህበራዊ እረፍት ለመንሳትና አገር ለማፍረስ መንጋውን አስከትለው የጥፋት አጀንዳዎች ላይ ብቻ ከተሰማሩና ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ ከጀመሩ ከራርመዋል። እነ ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ ካሉበት ሆነው በሐገር ቤት እንደፈለጉ የሚያሾሩት እግረኛ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅትና የሲቪክ ማህበር ማግኘታቸው ትልቅ ጉልበት አልፈጠረላቸውም ማለት አይቻልም። የአማራን አንድነት ለመበታተንና የክልሉ ፖለቲካ የማንም አልፎ ሂያጅ ሁሉ መሳለቂያና መሳቀቂያ ይሆን ዘንድ የባጥ የቆጡን አጀንጃ እየመዘዘ የከረመው ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ አሁን ላይ የአማራ ሕዝብ አለኝታ ተደርጎ እንዲቆጠር ሙከራ ሲደረግ እንደማየት ያለ አሳፋሪና አሳዛኝ ጉዳይ የለም። በደማዊ ማንነት ስሌት የዋቅጅራ ልጅ አማራ በሆነበት የአማራ ብሔርተኝነት ለአማራ ሕዝብ ሁለንተናዊ ጥቅም ያለእረፍት ሌት ተቀን በሚደክሙ አማራዎች ላይ ደግሞ በሐሰት የእትብት ንቅለ ተከላ ይካሄድባቸዋል። ተአምር ነው እኮ!

ለማንኛውም ነሮችን ለማስተካከል አሁንም ቢሆን የረፈደ አይደለም‼️
#No More War ምንም ሳታሟሙቅ በቀጥታ ዘለህ ሕዝባዊ አመፅ መግባት አይከብድም?!

ታየኝ እኮ በአማራ ክልል ሕዝባዊ አመፅ ሲቀ*ጣጠል፥ ወይ አለመተዋወቅ...! ወይ አየር ላይ ያለ ሰው ነገር..!

በሕዝባዊ አመፅ በኩል ሕወሓት ወደአዲስ አበባ ገብታ አገር ከምታፈርስ በራሳችን ጊዜ ምሽጎችን ለቀን፣ መንገዱን ከፋፍተን፣ ወደአደባባይ ወጥተን፣ ሰይፋችንን ጥለን በደመቀ ሰላማዊ ሰልፍ በኩል ማምጣት ይሻለናል እኮ😂

ፈፅሞ የማይሆነውን ነገር አታስቡት!
በአማራ ክልል ሕዝባዊ አመፅ የሚጠሩ የትህነግ ነጭ ለባሾችን የክልሉ መንግስት ፋይናንስ በማፈላለግ ሰብሰብ አድርጎ በአውቶብስ በመጫን እስከ ተከዜ ወንዝ እንዲሸኛቸው በአክብሮት እንጠይቃለን።

ተፎካካሪ ተሸናፊ ይሆኑ ዘንድ ግጥሚያው በሜዳቸው ቢሆን የተሻለ ነው😂
በነገራችን ላይ

አማራ የመሆን ችግር ያለበት ሰው ነው ከማንም በላይ አማራ ነኝ የሚለው። በኦሮሞም ኦሮሞ የመሆን ችግር ያለበት ሰው ነው ከማንም በላይ ኦሮሞ ነኝ የሚለው!

በደማዊ ማንነት ወይም በነጠላ ማንነት ስሌት ያለመሆን የሚፈጥረው የመሆን ችግር ነው ‼️
ሕወሓትን ፊት ለፊት ያንበረከክን ሆነን ሳለ ቡችላው ጭራሽ በርቀት ሆኖ ለማስደንገጥ ሲንደፋደፍ አለማፈሩ። በቁጭላው ነገረ-ስራ አለመገረም አይቻልም!