Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.45K subscribers
2.98K photos
371 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
የወያኔ አጀንዳ አሻሻጭ የመንፈስ ልጆች ወያኔ በአደባባይ በአዋጅ "በአማራ ላይ ሂሳብ አወራርዳለሁ፤ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦልም ድረስ እወርዳለሁ" ሲል ተከትለው አትዝመቱ ከማለት ጀምሮ በዘመቱ ሰዎች ላይ አቃቂር ሲያወጣ የነበረው የባንዳው ባንዳ "ጦርነቱ እኛን አይመለከትም፤ጦርነቱ የኢትዮጵያን ሕልውና ሳይሆን የአብይን ስልጣን ለማስቀጠል ነው" ማለቱን የምናስታውሰው ጉዳይ ነው። አሁን ደግሞ ወያኔ ከውጭ ባዳ የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር በመቀናጀት ለዳግም ወረራ በተዘጋጀበት ከሰሞኑ እነ ጌታቸው ረዳና ደብረፅዮን አማራን እንደወዳጅና ስለሰላም የተናገሩትን ማዘናጊያን ተከትሎ የመንፈስ ልጆቹ #No More War ወደሚል ዘመቻ ከፍተዋል።

በእውነቱ የሰሞኑን የወያኔን የማዘናጊያ የሰላምና የወዳጅነት ፕሮፖጋንዳ የመንፈስ ልጆቹን የጦርነት አያስፈልግም ጎጅ ነው የባንዳነት የዘመነች ዘዴ አለማድነቅ አይቻልም። ወያኔያዊ ግብራቸውን መሸፈኛ ሊሆን የሚችል ከትናንቱ አንፃር ይህ ለነገ ክርክርም የሚጠቅማቸው ስልት ነው።

ማንም ሰው ማወቅ ያለበት ሰላም በአንድ ወገን ብቻ ፍላጎት የሚመጣ ወይም የሚረጋገጥ ጉዳይ አይደለም። ሰላምና ትዳር እንዲሁም የሚተላለፉ መኪናዎች በአንደኛው ወገን ጥንቃቄ ወይም ጥረት ብቻ አይረጋገጡም ወይም አይሰምሩም። የሁሉንም የነቃ መልካም ተሳትፎና ጥንቃቄን ይጠይቃል።
ሰላምም በስብከት ብቻ የሚረጋገጥ ነገር አይደለም። አለም ላይ ለሺ ዘመናት ስለጦርነት አስከፊነትና ስለሰላም አስፈላጊነት ያለማቋረጥ ተሰብኳል። ነገር ግን አለማችን በየጊዜው ሚሊዮን ሰዎችን የጨረሰ ቢሊዮን ዶላሮችን ያወደመ ጦርነትን ደጋግማ አካሂዳለች። አሁንም በዩክሬንና በሩሲያ መካከል እየተደረገ ያለው ጦርነትም ስለሰላም አስፈላጊነት ስለጦርነት አስከፊነት ግንዛቤ የሌላቸው ሆኖ ሳይሆን አንደኛው ወገን ጥቅሜን ማስከበር የምችለው በጦርነት ነው ብሎ ስለሚታመን ነው።
ጦርነት መግባት ሳትፈልግ ጦርነት እንድትገባ ከተገደድክ ምርጫህ ጦርነቱን ቀድሶ አሸናፊ ለመሆን መታገል ነው። ሰላምን ማንም ስለፈለገ በአንደኛው ወገን ብቻ የሚረጋገጠው ነገር አይደለም። ጦርነትን ማሸነፍ የሚቻለው በሰላሙ ቀን ለጦርነት ለመዘጋጀት ሲቻል ነው። የወያኔ የመንፈስ ልጆች እያደረጉት ያለው የአማራም ሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲዘናጋ ብቻ ሳይሆን የጥፋት መንገድ እንዲመርጥ ለዳግም ወረራ ለጦርነት ለተዘጋጀውና ጦርነቱንም ሕዝባዊ ነው እያለ ላለው ወያኔ ደግሞ እንደተለመደው መንገድ መጥረግ ነው።

ማንም ያለውን ቢል የቱንም ያህል የጦርነት ዝግጅት ቢያደርግ አላስፈላጊ መስዋዕትነት ከማስከፈል ያለፈ የትም መድረስ አይችልም።
ያለመስዋዕትነት ደግሞ ድል የለምና ለእናት ኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት ለሕዝቧ ሰላምና ዘላቂ ጥቅም መከበር መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት ለመክፈል ሁሌም የነቃንና የተዘጋጀን ነን!
ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ ተቃውሞውን የሚያሰማው ሆድ-ነክ ቃላቶችን በመጠቀም ነው። ተከፍሏል ወይም ሊከፈለው ነው፤ በላ ወይም ሊበላ ነው፤ ተሸጠ ወይም ሊሸጥ ነው፤ ስንት ቢከፈለው ነው ሕዝቡን የካደው(የትኛውን ሕዝብ ምን አይነት ውል ኖሮት ነው የካደው የሚል ጠያቂም ጠፋ)፣ ለነገሩ እኮ ለክፍያው ከኦህዴድ ይልቅ ሕወሓት ይሻላልም ይላል((የሁለቱን የክፍያ ዋጋ ከማወቅ አልፎ ማነፃፀር እድሉ እንዴትስ ተቻለ ብሎ የሚጠይቅ ባለመኖሩ ይደጋግመዋል)፤ አንተ ምኑ ሆዳም ነው(የሆዳምነት መስፈርቱ የተዘረዘረ ይመስል?)፤..." የመሳሰሉትን ከሆድ ጋር ብቻ የሚገናኙ ስድብና እርግማን ነክ ጉዳዮችን ብቻ በመዝገበ ቃላቱ ያሰፈረ ስለሐገርና የሕዝብ ጥቅም ሳይሆን ግለሰቦችን አጀንዳ የሚያደርግ ነውርን እንደጌጥ የሚቆጥር አግድም አደግ ነው። ፖለቲካውን ሲያመሰጥር ደግሞ የአማራ ጠላቱ ሆዳም አማራ ነው ብሏል አስራት የሚል ነው። ፕሮፌሰሩ አለ የሚባለው የሆዳምነት ትርጉም በእነዚህ እንደሚተረጎመውም አይደለም። ነው ከተባለም ፈፅሞ ስህተት የሆነ አረዳድ ነው!

ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ ትልቁ ድፍረቱና ነውረኝነቱ ደግሞ ስለክፍያ፣ ስለገንዘብ፣ ስለመብላትና መጠጣት የሚጨነቅና ያለምንም ክፍያ ለሐገርም ሆነ ለሕዝብ ጥቅም ካለመስራቱ ባሻገር ሌሎችን እንደራሱ አድርጎ የሚያስብና የደመደመ መሆኑ ነው። ያለ ክፍያ ጥቅም እንኳን ወደጦርነት ወደግንባር ወደ ሰላማዊ ቦታ አንድ ኢንች የሚራመድ አይደለም።

በጣም የሚደንቀው ደግሞ ከዚህ በፊት ምን ጎደለብህ? ምንስ ይሻልሃል? እያለ የወርና የዓመት ወጭህን የሚሸፍን፣ የአንተን የግል ሕይወት ውሎና አዳር የሚከታተልና የሚገባህን ሲያደርግ የቆየ ይመስል ጠላት በሚለው አካል ስንት ቢከፈለው ነው ይላል። ከሆድ-ነክ የወጣ አስተሳሰብ የሌለው የአሳማነት ባሕሪይ የተላበሰ ነው።

በክልል የቢሮ ኋላፊ፣ በሚኒስቴር ደረጃ የተሾሙ፣ በመንግስታዊ መዋቅሩ ውስጥ በደህንነቱ ክንፍ ያሉ፣ በቪ-8 የሚሽከረከሩ በቪላ ቤት የሚኖሩ፣ አብይ አህመድን እኩል እንደጌታቸው ረዳ እያብጠለጠሉና ጠላት ያደረጉ፣ ኢትዮጵያንም ለማፍረስ በነፃነት እዛም እዚህም የሚንቀሳቀሱ የተጠያቂነት ስጋት ያለባቸው ወንጀለኞችና አቅመቢስ አመራሮችን ነፃነት የሰጠ ስርዓት በሌላ በኩል እነሱን እንደጀግና የሕዝብ ልጅ በመንጋው ዘንድ እንዲታዩ ሲያደርግ በተቃዋሚ ወገን ያሉ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት ለሕዝቦቿ ዘላቂ ሰላምና ጥቅም መከበር የሚሰሩ ሰዎች ደግሞ እንደ በብልፅግናነት ስማቸው ይነሳል። ተአምር ነው እኮ!

ሰው ለአላማው መሳካት ይረዳው ዘንድ ገንዘብ ሊፈልግ ሊከፈለው ሊበደር ሊዘርፍ ወይም ሌላ ሌላም ነገር ሊያደርግ ይችላል እንጅ እንዴት አንድ ሰው ለመብላት ብቻ ለመኖር የማይሆነውን ለመሆን ራሱን ያዘጋጃል። ያኖራልስ? አጃኢብ ነው!
በቁር በሐሩሩ መካከል እያለፉ ዳጋት እየወጡ ቁልቁለት እየወረዱ ጋራ ሸንተረሩን እያቆራረጡ ሌትና ቀን ሁሌም ስለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት ስለሕዝቦቿ ዘላቂ ሰላምና ጥቅም መከበር የሚዋደቁ የኢትዮጽያዊያን የኩራት ምንጭ ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን አባላት እየከፈላችሁልን ስላለው በቃላት የማይገለፅ መስዋዕትነት እናመሰግናችኋለን‼️

ለኢትዮጵያ መታፈርና መከበር ቀዳሚ ባለድርሻዎች ናችሁ‼️
በክልል የቢሮ ኋላፊ፣ በሚኒስቴር ደረጃ የተሾሙ፣ በመንግስታዊ መዋቅሩ ውስጥ በደህንነቱ ክንፍም ያሉ፣ በቪ-8 የሚሽከረከሩ በቪላ ቤት የሚኖሩ፣ በብሔር ት*ግሬና የወያኔ ስራ አስፈፃሚ አለመሆናቸው ካልሆነ በስተቀር አብይ አህመድን እኩል እንደጌታቸው ረዳ የሚያብጠለጥሉና ጠላት ያደረጉ፣ ኢትዮጵያንም ለማፍረስ በነፃነት እዛም እዚህም የሚንቀሳቀሱ፣ የተጠያቂነት ስጋት ያለባቸው ወንጀለኞችና የአቅም ማነስ ያለባቸው አመራሮች በነፃነት እንደፈለጉ እንዲንቀሳቀሱ የፈቀደ ስርዓት በሌላ በኩል እነሱን እንደጀግና የሕዝብ ልጅ በመንጋው ዘንድ እንዲታዩ ሲያደርጋቸው በተቃዋሚ ወገን ያሉ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት ለሕዝቦቿ ዘላቂ ሰላምና ጥቅም መከበር የሚሰሩ ሰዎችን ደግሞ ስማቸው በብልፅግናነት እንዲነሳ ማስደረግ ችሏል። መቼም በዚህ አለመገረም አይቻልም!

ብልፅግናንም ሆነ መንግስታዊ መዋቅሩን በመጠቀም እንጀራቸውን የሚጋግሩት፣ የሚፈልጉትን የግል ጥቅማቸውንና አላማቸውን እያሳኩ ያሉት እነሱ ሆነው ሳለ አንድ ቀን በብልፅግና በር ያለፈን ወይም አብዮታዊ ዲሞክራሲ ወይም ሞት! ከሚሉ ናፋቂ ወያኔዎች የተለየንና ብልፅግና ከሆኑ አመራሮች ጋር የሚታይን ተቃዋሚ በለፀገ ወይም የመንግስት ተቀላቢዎች እስከማለት የሚያደርስ የይሉኝታ ቢስ ጥግ ላይ ያሉ ነውረኞችን እስከማየት አድርሶናል። በእውነቱ ግን መበልፀግን ጠልቶ ድህነትን የሚመርጥ የመንግስትን ክፍያንስን የሚጠላ ሰው አለንስ? ተካፋዮች ተከፋይ የሚሉት ነገርስ😂

በየትኛው ዘመንና ታሪክ የፓርቲው ሊቀ-መንበርና የሐገሪቱ መሪ በራሱ በብልፅግና ውስጥ ባሉ ካቢኔዎቹ በጓዳ ያይደለ በአደባባይ፣ ከልብ በመነጬ የመረረ ጥላቻ ስሙ እየተጠራ የሚወነጀልበት፣በእሱ ላይ የጥላቻ ቅስቀሳ የሚያደርጉና እሱን ለማውረድ በነፃነት የሚደራጁና የሚያደራጁ፣ በብልፅግናም ሆነ በመንግስታዊ መዋቅሩ እዛው በጓዳው እንደምስጥ ያይደለ እንደ አንበጣ እየተንቀሳቀሱ፣ ሐገር ለማፍረስ እየተንቀሳቀሰ ከሚገኘው የፈረጠመ የተደራጀ የጥፋት ሃይል ባለበት ሁኔታና ከዚህ አገር አፍራሽ ሃይል ጋር አጀንዳ እየተመጋገቡ በጥፋት መንገድ እየተራመዱ ራሳቸውን እንደልክ እንዲቆጥሩ፣ እንደጀግና እንደየሕዝብ ልጅ እንዲታዩ የሚፈለግበትና የሚሆኑበት በጥቅሉ እንደፈለጉ እንዲፈነጩ የሚፈቅድ ስርዓት፣ ከዚህ ቀደም ተሰምቶና ታይቶ የሚታወቅ ለወደፊቱም የሚሆን አይመስለኝም። ለዲሞክራሲ ማሳያ ወይም ዲሞክራሲ ሲተረጎም እንዲህ ያለም አይደለም። ነው ከተባለ ይቅርብን እንዲህ ያለ ዲሞክራሲ አያስፈልገንም። ወያኔን የጠላነውና የምንታገለው አገር ለማፍረስ የሚንቀሳቀስ የጥፋት ሃይል ስለሆነ በግብሩ እንጅ ትግረኛ ተናጋሪ ስለሆነ አይደለም።

ብልፅግና ያልተመቸው ማንም አመራር ብልፅግናን ለቆ ባመነበት በራሱ መንገድ በድርጅት ወይም በግሉ መታገል እንጅ በብልፅግና ውስጥ ሆኖ ወያኔያዊ ብሔርተኝነትን እያራመደ መዋቅሩን በመጠቀም 24/7 ዶ/ር አብይ አህመድንና የተመረጡ ወያኔ ጠል አገር ወዳድ አመራሮችን የተቃዋሚ ፖለቲከኞችን አክቲቪስቶችን ጠላት ማድረግ ብቻ ሳይሆን ለማጥቃት ከወያኔ ጋር አጀንዳ በግልጽ እየተመጋገበ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንዲዋጋ ሊፈቀድለትና እድል ሊሰጠው አይገባም። እስከዛሬ የተፈፀመው የተከፈለው አላስፈላጊ መስዋዕትነት ከእንግዲህም እንዳይቀጥል በሩ ሊዘጋበት ይገባል። አገር የሰጠችውን ኋላፊነት ወደጎን በማለት መንግስታዊ መዋቅሩን በመጠቀም የግልንና የቡድን ጠባብ ፍላጎት ለሟሟላት ጭራሽ ከተቃዋሚው በላይ ተቃዋሚ ከአገር አፍራሾች በላይ አገር የማፍረስ እንቅስቃሴ እያደረገ መልሶ ደግሞ ከተቆርቋሪዎች በላይ ተቆርቋሪ ከሐቀኞቹ በላይ ሐቀኛ እንደሆነ በማሰብና በሚዲያ ጫጫታ የጀግንነት ካባ ይሰጠው ዘንድ የሚፈልገውና የሚሰራው ሃይል የተላበሰው ሞራል ያስደንቃል።

በብልፅግና ውስጥ ካሉት አመራሮች ውስጥ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ወይም ሞት! ላይ እስካሁን ተቸንክረው የቀሩ እኛ ከሞትን ሰርዶ አይብቀል! የሚሉ መንግስታዊ መዋቅሩን ተቆጣጥረው በብልፅግና ውስጥ ብልፅግና ሳይሆኑ እንደፈለጉ እየሆኑ ያሉ ሁለመናቸው ወያኔን የሚናፍቅ ዓመቱን ሙሉ ይመጣል ብለው ከመጠበቅ ባሻገር ይመጣ ዘንድ በሁሉም መስክ ለመጎተት ሞክረው ያልተሳካላቸው፤ ከመጀመሪያውም ከወያኔ ጋር ቆላተንቤን ተገኝተው ኢትዮጵያን ለማፍረስ፤ ከአማራ ጋር ሂሳብ ለማወራረድ፤ ጠባችን ከአብይ ጋር ነው፤ እያሉ አሮጌ ከበሮ እየደለቁ በግልፅ መምጣት ሲኖርባቸው ባህርዳር አዲስ አበባ ተቀምጠው እንጀራቸውን በብልፅግና እንዲጋግሩ መደረጉ ትልቅ ስህተትና እንደሐገርም አላስፈላጊ ዋጋ ያስከፈለ ነው።

ታሪካዊ ጠላቶቻችን አገራችን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተቀናጀ የጥፋት ሁለንተናዊ ዘመቻ መግባት አንቆ ስለያዘንና የአባቶቻችን ልጆች ስለሆንን እንጅ ብልፅግናንም ሆነ የመንግስት መዋቅርን የተቆጣጠረው በደህንነት ክንፉ የተሰማራው ከሃዲና የባንዳ ባንዳ የሆነው አካል መስራት የሚገባውን ስራ እኛ ለመሸፈን ከብልፅግና በላይ ብልፅግና ከደህንነቱ በላይ ደህንነት ሆነን እንቅልፍ አጥተን ለመስራት የሚገባን አልነበረም ብቻ ሳይሆን ይህን ሃይል አብይ አህመድ እያየ እንዳላየ እየሰማ እንዳልሰማ የሚያልፈው መሆኑን እንዳረጋገጥን ፈልጎታል እሱም ያው ነው በሚል ድምዳሜ በነፍጥ ጭምር ተፋልመን ለማፅዳት ወደበረሃ ለመውረድ እንዳንገባ የማይገፋ አይደለም። ልባቸውና ቀልባቸው መቀሌ ላይ ባለ በብልጽግና በመንግስታዊ መዋቅሩ ውስጥ ባሉ አመራሮችና የደህንነት ሰዎች አገር እየተመራች የኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት የሕዝቦቿ ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ፈፅሞ ሊከበር አይችልም‼️
Re-Post

ሳይቃጠል በቅጠል...‼️

የጦር መሃንዲሱና የሐገር መሪው ናፖሊዮ ቦናፓርት በተግባር ከተፈተነው ልምዱ ተነስቶ ጦርነት 90% መረጃ መሆኑን አስምሮ የተናገረው በጀኔራል ሰን ዙ "The Art of War" በሚለው ድንቅ መፅሐፍ ለሰፈረው ስትራቴጂ ቁልፍ ማስፈፀሚያ የሚሆን ነው። ጀኔራል ሰን ዙ ጠላትን ያለ ጦርነት ድል መቀዳጀት ወይም በሁኔታዎች ተገደህ ወደጦርነት የምትገባ ከሆነ ጦርነቱን በአነስተኛ መስዋዕትነትና ኪሳራ በአጠረ ጊዜ በድል ለመቀዳጀት ቀድመህ ራስህንና ጠላትህን ማወቅ ይገባሃል ይላል። ይህ መሆን የሚችለው በበቂ መረጃ ነው። በበቂ መረጃ ላይ ያልተመረኮዘ ትንተናና አቋም ሽንፈትና ውርደትን ሊያከናንብ ይችላል።

መቼ መዋጋት መቼ አለመዋጋት በየት በኩል ማጥቃት እንዳለብህ ማወቅ የምትችለው ስለጠላት በቂ መረጃ ሲኖርህ ነው።
"አሸናፊ ጦረኞች ወደጦርነቱ የሚገቡት ጦርነቱን አሸንፈው ሲሆን ተሸናፊዎች ግን ድልን በጦርነቱ መሃል ይፈልጓታል። ጦርነትን ለማሸነፍ ጠላትን በማጭበርበር ማሳሳት ሲቻል ነው "ይላል ጀኔራል ሰን ዙ። ይህን ያለመረጃ ልታደርገው አትችልም። በጦርነት ቃታ መሳብ ከ10% በታች የሚሰጠው ጉዳይ ነው። በአንድ ጉዳይ ላይ ቀድመህ የጠራ መረጃ ከሌለህ misinformation Disinformation ማሰራጨት አትችልምም።

የኢትዮጵያ አሁናዊ ትልቁ ፈተናዋ በእነ ጌታቸው አሰፋ የኢትዮጵያ የደህንነት ተቋሙ የመረጃ ቋቱና ጭንቅላቱ ተቆርጦ ወደመቀሌ ከመወሰዱ የቀረው የደህንነት ክንፍ ባዶ ቀፎ ከመሆኑ ባሻገር "እኔ እኮ ደህንነት ነኝ እያሉ ራሳቸውን ቀድመው በሚያስተዋውቁ የምድጃ ዳር ወሬ ቃራሚ ጀሮ ጠቢዎች" አቅመቢስነታቸውን አንዴ በብሔር ሌላ ጊዜ በጎጥ ተወሽቀው አጭበርብረውና ጥፋት አድርሰው መቀጠል በሚፈልጉ ሰዎች ቁጥጥር ስር መውደቁ ነው የሚል እምነት አለኝ። ከጠላት እንደ አንዱ በመምሰል በጠላት ጓዳ ሰፈር ቅኝት በማድረግ መረጃ እያፈነፈነና የጠላትን የመረጃ ቋትን በመፈተሽ ወደወገን ከስር ከስር መረጃ ማድረስ መረጃ መተንተንና ቀጣዩን ሁኔታ መገመት የሚችል ብቁ የሆነ የስለላ አቅም አለመኖርና መዳከም የአገሪቱን ፈተና ከድጡ ወደማጡ እየከተታት ይገኛል። በሐገሪቱ እየተፈጠሩ ካሉ ትርምሶች ጀርባ የቀደመው በእነ ጌታቸው አሰፋ የተበተነው የደህንነት ሐይል ብቻ ሳይሆን ከለውጡ ጋር የቀጠለው በመንግሥት እንጀራውን የሚጋግረው አቅመ ቢስ ጀሮ ጠቢዎች እኩል እንደሕወሓት ሰዎች መንግስትን ሲሳደቡና ሲያራክሱ ከተቀጠረበት መረጃ የሚወስዱ እንጅ መረጃ አፈንፍነው ማምጣት የማይችሉ መረጃ ሻጮች ጭምር ተሳታፊ ስለሆኑ ነው። ስለእናት ሐገራቸዉ እውቀታቸውንና ጊዜያቸውን ጉልበታቸውን አሳልፈው የሰጡ ቁርጠኛ የኢትዮጵያ ልጆችን ድካም ከንቱ እየሆነ ያለው በእነዚህ የሚበሉበትን ወጭት በሚሰብሩ ሰዎች የተነሳ ነው።

የሐገሪቱን ሕልውና አደጋ ላይ የጣለው የደህንነት ክንፉ ሽባ መሆን ነው። የክልል የቢሮ ኋላፊዎች በሚኒስተር ማዕረግ ያሉ እንጀራቸውን በብልፅግና የሚጋግሩ ደሞዝተኞች ባለ ቪ-8 አሽከርካሪዎች ስለአገር የሚቆረቆሩ ሰዎችን የመንግስት ተቀላቢ ወይም ተከፋ እያሉ የሚሳደቡ ገቨርመንትና ስቴትን ለይተው የማያውቁ የወያኔን አጀንዳ ሌት ተቀን የሚያሳልጡ ሰዎች እነሱ ሞራል ኖሯቸው ከመንግስት ቀለብተኝነት(እንዴት ስድብ እንደሆነ ሊገባኝ አይችልም) ልውጣና ልሳደብ እንኳን ባይሉ በመዋቅሩ ውስጥ እንዲቀጥሉና ሐገርን ከውስጥ በኩል እንዲያፈርሱ የሚመቻችበት እድል ተሰጥቶ ይህ እንደ ዲሞክራሲ ሲተረጎም የሚታይበት አግባብ የተፈጠረው ከመንግስት የማድረግ አቅም ማነስ ስለመነጨ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ። Freedom of Expression ማለት መሳደብ ወይም የሰዎችን ስብዕና መንካት አገር አፍራሽ የሆነ ሐሳብ ማራመድ እንደማለትም አይደለም ሲተረጎም። የትም አለም ላይ በዚህ አግባብ አይሰራም ። የደህንነት ክንፉ ሽባ መሆንን ተከትሎ ማንም እየተነሳ አገር አፍራሽነቱን እንዲያውጅ እድል አልሰጠውም ማለት አይቻልም።

የመንግስት አፍ የሚባለው የመንግስት ኮሙኒኬሽንን ጨምሮ የመንግስት ሚዲያዎች አጀንዳ በመስጠት የአንድ ተቃዋሚ ግለሰብን ያህል ተፅዕኖ ያለመፍጠራቸው ምክንያት የተወሳሰበ አይደለም።

መረጃ ፖለቲካ ነው። መረጃ ደህንነት ነው። ጭራሽ የሴራ ፖለቲካ ያለ በቂ መረጃ የማይታሰብም ነው። ወያኔ የመንግስትንም ሆነ የአማራን ሕዝብ በተመለከተ ከበቂ በላይ መረጃ የነበረውና አሁንም የተሻለ መረጃ ያለው አሸባሪ ነው። ለዛም ነው የአማራን የፌስቡክ ብሔርተኝነትና ፖለቲካን በቀላሉ ተቆጣጥሮ ዋና ተቆርቋሪና አስጨፋሪ መሆን የቻለውም። የወያኔ እጅ የሌለበት ፖለቲካ በየትኛውም ብሔር አሁን ላይ እየተጋገረ አይደለም። በተቃራኒው በደሳለኝና በመሰለኝ ለመተንተን የሚሞክረው በአማራ ስም የሚንቀሳቀሰው አብዛኛው የፖለቲካ ኤሊት ቀርቶ መንግስት ነኝ የሚለው አካል በትግራይ ክልል መቀሌ አካባቢ ስላለው ሁኔታ አፉን ሞልቶ እንዲከራከር የሚያስችለው በቂ መረጃ ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ። በወያኔ አማካኝነት ለራሱ የሚጠቅመውን መረጃ ከሚያደርሰው ውጭ የተለየ በራስ መንገድ የሚገኝ የተረጋገጠ መረጃ የማግኘት እድሎች ልክ እንደ አማራ ክልል ፖለቲካ ክፍት እንዳልሆነ ይሰማኛል። ነገሮች በዚህ የሚቀጥሉ ከሆነ ወደትክክለኛው መፍትሔ ለመድረስ እጅጉን አስቸጋሪ ነው።

ወያኔ አሁን ላይ ወረራ ከመጀመሩ በፊት ጦርነቱን መንግስት በሚመራው ክልል ላይ አስገብቶታል። ያለግጭት ሕልውና የሌለው ወያኔ በእጅ አዙር መስራት የሚገባውን ስራ ሰርቶ ለዳግም ወረራ አዘናግቶ ጦርነት መክፈቱ የማይቀር ነው።

እርግጥ ነው ወያኔ የኢትዮጵያን ሰራዊት በጦርነት ለማሸነፍ የሚያስችል በሰው ሃይልና በትጥቅ የደረጀ ቁመና የለውም። ነገር ግን ቀድሞ በዘረጋው መዋቅርና ባፀደቀው ሕግ እየታገዘ በሐገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ቀድሞ ባደራጃቸውና ተልዕኮ ሰጥቶ ባሰማራቸው አካላት በኩል አላማውን ለማስፈፀም እየሰራ ሲሆን ሕዝቡን ደግሞ በተዛባ መረጃ በመንግስት ላይ እንዲነሳሳ የሚያደርገውን ሙከራ ተስፋ የሚያስቆርጠው ሳይሆን እንዲገፋበት የሚያደርገው ነው። የመረጃ ብልጫ ያለው አካል የሚዲያ hegemony የመውሰድ ዕድሉ ከፍተኛ ነው። ቀድሞ አጀንዳ ፍሬም በማድረግ አላማውን እንደጠላት በሚቆጥሩ አካላት ጭምር ሁሉ እንዲሸጥና ጉዳያቸው አድርገው እንዲሰሩበት የሚያደርግ ነው። ሕዝቡ በመንግስት ላይ እንዲማረርና ተስፋ እንዲቆርጥ ወያኔ በርትቶ እየሰራ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ስም በሕዝቡ እንዲጠፋና ደጀን እንዳይኖረው ለማድረግ የኦነግ ጦር እንደሆነ ሲገልፅ ከውስጥ በኩል ደግሞ እርስ በራሱ ወታደሩ እንዳይተማመን በሴራ አለ ሴራ በቀላሉ ለመበታተን የሚያደርገው ሙከራ የሚናቅ አይደለም። የአንዲትን አገር የመጨረሻ የሕልውናዋ ምሽግ የሆነውን መከላከያን ለዛውም የራስን ጦርነት እየተዋጋለት በአደባባይ የሚሰደቦበትና ያለ ስሙ ስም እየተሰጠ ፕሮፖጋንዳ የሚሰራበትና መንግስት ተብዬው ጥሩ አደረጋችሁ በሚመስል መልኩ በዝምታ የሚያልፍበት አገር የትም አይገኝም። ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ጦርነቱን ስትጀምር የመከላከያ ሰራዊቷ ላይ ስም የሚያጠፋ ማንም አካል እስከ 15 ዓመት እስር እንደሚጠብቀው እንዲያውቅ አዋጅ ያወጣችው።
አበው ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው የሚሉት እንዲሁ አይደለም።
ጀኔራል ሰን ዙ የው ግዛትን 33 ሺ ጦር ይዞ ግዙፉን የቹ ግዛት የኗኗን በመቶ ሺ የሚቆጠርን ጦር ያሸነፈው እንደወያኔ የውሸት መረጃ በመርጬት በቹ ግዛቶች ገብቶ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ጥቃት በመክፈት በኗኗ ላይ እንኳን ሕዝቡ ጦሩ ራሱ እምነት እንዳይኖረውና ከኗኗ እየወጣ ለሰን ዙ ጦር እጅ እንዲሰጥ ገሚሱ ደግሞ ከጦሩ እየሾለከ እንዲጠፋና ጦሩ እንዲበተን ማድረግ ስለተቻለ ነበር።
ወያኔ አሁን እያደረገ ያለው የኢትዮጵያን ጦር በተለይ የአማራ ልዩሃይልን በወያኔ ናፋቂ በተተፉ አቅመ ቢሶች በኩል የጋራ ኮዝ እንዳይኖረው በማድረግ ልዩሃይሉን የዳቦ ስም በመስጠት ለመበተን ሲደከም ተከርሟል። ሕዝቡን ደግሞ በተለያየ መንገድ እንዲማረርና አልፎም በመንግሥት ላይ በአመፅ እንዲነሳ ለማድረግ ያልተቋረጠ ስራ እየተሰራ ነው። አንዴ የተመረጡ አካባቢዎች ላይ ጭፍጨፋ በመፈፀም ሌላ ጊዜ ደግሞ በሐይማኖት ስም እየተደረገ ያለው ስራ ለወያኔ መንገድ ጠረጋ ነው። ይህን አጀንዳ ወያኔን እንደጠላት የሚቆጥሩት ወይም እንታገለዋለን የሚሉ አካላት ሳይቀር አጀንዳውን ተቀብለው የማሻሻጥ ስራውን እያቀላጠፉትለም ነው። ዲስፕሊንድ ያልሆነ ኮዝ የሌለው በጠንካራ የወታደራዊ ስነ-ስርዓት የማይመራ ሰራዊት በየትኛውም ሁኔታ የሚሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት በበከፍተኛ ሞራል ተሞልቶ እስከመጨረሻው በፅናት ቆሞ ሊታገል አይችልም።

በናፒር በሚመራው የእንግሊዝ ጦር በአፄ ቴዎድሮስ ላይ ብልጫ የወሰደው በወታደራዊ ስርዓት የተሻለ ስለነበረ ነው። የናፒር ጦር ስለ አፄ ቴዎድሮስና ስለ ሕዝቡ ሁኔታም ከበቂ በላይ መረጃ ስለነበረው በክፍተቱ መጫወት ስለቻለም ነበር።

ጀኔራል ሰን ዙ ጥቂት ጦር እየመራ የኗኗን ግዙፍ ጦርን በራሱ በቹ ግዛት ጠልቆ ገብቶ ማሸነፍ የቻለው በበቂ መረጃ ተመርኩዞ በተዛባ በውሸት መረጃ በማጭበርበር ጦሩን አሳስቶ በሕዝቡ ቅሬታና ጥያቄ በኩል አልፎ ጦርነቱን መምራት ስለቻለ ነበር። የሰን ዙ ጦር ተቆራርጦ በቹ ግዛት የሽምቂ ውጊያ ማድረግ የቻለው የቹ ሕዝብ በኗኗ እና በጦሩ ላይ የተማረረ ስለነበረ ለሰን ዙ ምሽግ ሆኖ ስላገለገለው ነበር።

በናፔር የሚመራው የእንግሊዝ ጦር ስለ አፄ ቴዎድሮስ ጦርና ስለሚመራው ሕዝብ በቂ መረጃ ነበረው እንጅ የአፄ ቴዎድሮስ ጦር በናፔር ስለሚመራው የእንግሊዝ ጦር በቂ መረጃ ነበረው ለማለት የሚያስደፍር ነው ለማለት አያስደፍርም።
አፄ ቴዎድሮስ ስለኢትዮጵያ በክብር የወደቀው ቀድሞ በራሱ ኤሊትና ሕዝብ ስለተካደ ነበር። ሕዝቡንና ኤሊቱን ከአፄ ቴዎድሮስ ይልቅ የናፔር ጦር ተጠቅሞበታል።

ሰን ዙ እንዳለው "አሸናፊው ጦረኛ ወደጦርነት የሚሄደው ጦርነቱን አሸንፎ ነው። ተሸናፊው ደግሞ ድልን በጦርነት መሃል ይፈልጋል" ይላል።

ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው የአፄ ሚኒሊክ የአድዋ ዘመቻ ነው። አፄ ሚኒሊክ በክተት አዋጃቸው ገና ሳይነሱ ጦርነቱን አሸንፈው ስለመጀመራቸው ማረጋገጫው ".ወስልተህ የቀረህ ግን ትጣላኛለህ አልተውህም። ማርያምን አማላጅ የለኝም" የሚለው አቋማቸው ስለ ድህረ-ጦርነት ሁኔታ ምን ያህል እርግጠኛ እንደነበሩ የሚያመላክት ነበር።

አፄ ሚኒሊክ ስለጣሊያንን ጦር ከበቂ በላይ መረጃ እንደነበራቸውና ይህን የጠላት ሃይል ለመመከትና ጦርነቱን በድል ለመወጣት የሚያስችል ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርጉ ስለመቆየታቸውም በክተት አዋጃቸው ላይ "...በፊት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባህር አልፎ(የኢትዮጵያ ደንበር እስከየት እንደሆነ የሚናገርም ነው) መጥቷል፡፡ እኔም የአገሬን ከብት ማለቅ፤ የሰውን መድከም አይቼ እስካሁን
ዝም ብለው( የጠላትን እንቅስቃሴ በተመለከተ ያውቁና ለጠላት የሚመጥን የሰው ሃይልና የትጥቅ ዝግጅት ሲያደርጉ ስለመቆየታቸው የሚያሳይ ነው) ደግሞ እያለፈ እንደፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር.." የሚለው አቋም ያረጋግጥልናል። በነገራችን ላይ በኢትዮጵያ ታሪክ በእኔ መረዳት ለውጊያ ጦርነቱ ከሚወስደው ጊዜ ይልቅ ለጦርነቱ የሚደረገው ዝግጅት ከፍተኛውን ጊዜ የሚወስድ ነው። ጦርነትን ለማሸነፍ በሰላም ጊዜ ለጦርነት መዘጋጀት የሚለው በተግባር ሲተረጎም ከዚህ የተለየም አይደለም‼️

ወያኔ አሁን እያደረገ የሚገኘው መንግስት በሚያስተዳድረው ክልል በሐይማኖት ስም ወይም ጥቃት እንዲፈፀም በማድረግ ጦርነቱን ራሱ ሕዝቡ እንዲመራለት ማድረግ ነው‼️

ለወያኔ አገር ለማፍረስ እየተሰጠ የሚገኘው እድል በጊዜ እልባት የማይሰጠው ከሆነ ማንም ወደማያተርፍበት አዘቅት ሁሉም ተያይዞ መግባቱ አይቀርም‼️
ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ከውስጥ ባንዳዎች ጋር በመቀናጀት አገር አልባ ሊያደርጉን ሁለንተናዊ ዘመቻ መክፈታቸውን፣ በወያኔ በኩል በአዋጅ ግልፅ በሆነ መንገድ ኢትዮጵያን ለማፍረስ "ሲኦልም ድረስ ለመውረድ" ቆርጠው እየሰሩ መሆናቸውን ስለምናውቅ፥ አገር አልባዎች ላለመሆንና የአባቶቻችን ልጆች መሆናችንን ማረጋገጥ ስላለብን እንጅ፤ ብልፅግናንም ሆነ የመንግስት መዋቅርን የተቆጣጠረው በደህንነት ክንፉ ውስጥ ያለው የባንዳ ባንዳ የሆነው አካል ሁሉ እየሰራው ወይም እየሄደበት ያለው የጥፋት መንገድ የማያስቆጣ አይደለም።

መዋቅሩ ራሱ ወያኔ ሰራሽ ሆኖ አሁንም መዋቅሩን የተቆጣጠሩት የወያኔ ናፋቂዎች አቅም በፈጠሩበት ሁኔታ ወያኔን በግንባር ጦርነት ስለማሸነፈ ማሰቡ አድካሚ ነው። ዶ/ር አብይ አህመድ ወያኔ ሰራሹን መዋቅርን ለማስተካከል ጊዜ ያስፈልገዋል ቢባል እንኳን፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ላይ የተቸነከሩ ናፋቂ ወያኔዎች ላይ ከዛሬ ነገ የማስተካከያ እርምጃ ይወሰዳል ብለን ስንጠብቅ ብንከርምም ይባስ ብሎ የእነሱ መንገድ ሕዝባዊ እውነተኛ እነሱ ደግሞ እንደጀግና እንዲቆጠር የሚያደርግና ሌሎችም መንገዱን እንደራመዱበት የሚያበረታታ ነው።

በሕልውና ጦርነቱ ኢትዮጵያን ለመታደግ ሁለንተናዊ ተሳትፎና መስዋዕትነት በመክፈል ሂደቱ ውስጥ በብልፅግና በመንግስታዊ መዋቅሩ በደህንነቱ ክንፍ ውስጥ ከተሰማራው ከብዙሃኑ ይልቅ በተቃዋሚው ጎራ የተሰለፈው ሃይል ሙሉ በሙሉ ያለምንም ክፍያ ወይም የቀን አበል ሕይወታቸውን ረክሰው ጭምር እስከመዋደቅ ደርሰዋል። በሕልውና ትግሉ እንደተቃዋሚው ወገን የብልፅግና ካቢኔ ኢትዮጵያ ለመታደግ ከመታገል ይልቅ የሚታገሉትን ለመታገል የሞከሩ ቁጥራቸውም ሆነ ተፅዕኗቸው የሚናቅ አይደለም። በተቃዋሚው ወገን የነበረው ሃይል በመንግሥት በኩል ከተሰለፈው ሃይል በተሻለ መስራት የሚገባውን ስርቷል ብቻ ሳይሆን በብልፅግና ውስጥ ያሉ የባንዳዎችን የጥፋትን እንቅስቃሴ በማክሸፍ ጭምር ስራቸውን በመሸፈን ታሪካዊ ግዴታውን ተወጥቷል ማለት ይቻላል።

ከብልፅግና በላይ ብልፅግና ከደህንነት ክንፉ በላይ ደህንነት መስለው ስለእናት አገራቸው ሉዓላዊነትና ነፃነት ስለዘላቂ ጥቅሟ ሲሉ እልፎች እንቅልፋቸውን አጥተው የስም ማጥፋት ዘመቻውን ሕይወታቸውን እያጡ በነበሩ ጀግኖች አንፃር አቅልለው አይተው በፅናትና በድል አልፈውታል። በብልፅግና አመራሮች ሳይቀር የስም ማጥፋት ተካሂዶባቸዋል። በተቃዋሚው በኩል ያለው ሃይል ከብልፅግና በላይ ብልፅግና እንደሆነ ያስመሰለው ሐገሩን በማስቀደሙና ብልፅግና ውስጥ ያለው የባንዳነት ስራ መጉላትም ነው።

ተቃዋሚው ስሙ እስኪጠፋ የሚያደርስ የሚያስገድደው የግል ጉዳይ ኖሮት ወይም በውለታ ታጥሮ ብልፅግና እስከመምሰል የደረሰው የአገር ጉዳይ ስለሆነበት፣ የወያኔ ጠላትነት ላይ ብዥታ የሌለውና በማንኛውም ነገር ወያኔ ሳይከስም ኢትዮጵያ ሰላም ልትሆን ጥቅሟ ሊከበር እንደማይችል የጠራ አቋም ያለው በመሆኑ ነው።

ልባቸውና ቀልባቸው መቀሌ ላይ የሆኑ በብልፅግና በመንግስታዊ መዋቅሩ በደህንነቱ ክንፍ ያሉ ሰዎችን አብይ አህመድ እያየ እንዳላየ እየሰማ እንዳልሰማ ሆኖ የሚያልፈውን ጉዳይ የእሱም ሐሳብና አቋም ያው ነው በሚል ድምዳሜ በነፍጥ ጭምር ብልፅግናን እንደወያኔ ለመዋጋት ወደበረሃ ለመውረድ አንቆ የያዘን አገር አልባዎች የመሆን ስጋትና የአባቶቻችን የመንፈስ ልጆች መሆናችን ነው።

በሐገር ክህደት መከሰስ እንኳን ባይቻል እንዴት አገር እንዲያፈርሱ በስራችሁ ቀጥሉ ግፉበት የሚያስብል ሁኔታዎች ይመቻችላቸዋል?

ልባቸውና ቀልባቸው መቀሌ ላይ ባለ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ወይም ሞት! በሚሉ በብልጽግና በመንግስታዊ መዋቅሩ ውስጥ ባሉ አመራሮችና የደህንነት ሰዎች አገር እየተመራች የኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት የሕዝቦቿ ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ፈፅሞ ሊከበር አይችልም‼️
FYI:

ማምሻውን ከአማራ ክልል መንግስት የፀጥታ ምክርቤት ከተሰጠ መግለጫ የተወሰዱ ቁልፍ መልዕክቶች👇

👉የወያኔን ዳግም ወረራ ለመቀልበስና ለመከላከል የውስጥ አንድነትን ማጠናከር፣ ሰላምና ደህንነትን መጠበቅ ቁልፍ ጉዳይ ነው ብሎ ያምናል። ህዝባችን ዳግሞ ለወያኔ ወረራ ለጥቃት እንዳይዳረግ እቅድሚያ ሰጥቶ እንደወትሮው ሁሉ የፀጥታ መዋቅሩ፣ ደጀኑ ህዝብ የራሱን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆን እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

👉በመሆኑም በአንድ በኩል ከፌደራል የጸጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት ከወያኔ የሚሰነዘርብንን ጥቃት ለመከላከል በተጠንቀቅና በዝግጁነት መቆም፤ በሌላ በኩል ደግሞ በውስጣችን ለወያኔ ሴራ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩትን ህገ-ወጦችንና ስርዓት አልበኞችን በመቆጣጠር የክልላችን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ግንባር ቀደም የትኩረት አቅጣጫ እንዲሆኑ ወስኗል፡፡

👉 ስለሆነም የክልሉ የጸጥታ ምክር ቤት በየደረጃው የጸጥታ ግብረ ሀይል አቋቁሞ ህገ-ወጥነትን ለመቆጣጠርና ህግን ለማስከበር ተገቢ ነው ያላቸውን ህጋዊ ርምጃ እንዲወስድ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
ወያኔ ወደስልጣን የወጣው አማራን በጠላትነት ፈርጆ ነው። በሰነድ ያሰፈረውን ፀረ-አማራነት በ27 ዓመቱ የአገዛዝ ዘመን ስርዓታዊ በሆነ መንገድ ሕልቆ መሳፍርት ግፎችን ፈፅሞበታል። አስፈፅሞበታል።

በአማራና በሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች የተቀናጀ ትግል ከማዕከላዊ መንግስቱ ተነቅሎ መቀሌ ከመሸገ በኋላ የትግራይን ሕዝብ ለአመታት በቀበሮ ጉድጓዳ ሆኖ ሲጠብቅ በነበረው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በማድረሱ በተወሰደው ሕግ የማስከበር እርምጃ ተሸንፎ ወደተንቤን ዋሻ ለመግባት ተገዷል። በሕዝባዊ ማዕበልና በውጭ ባዳ ሃይሎች ድጋፍ ከተንቤን ዋሻ ከመውጣቱ በፊት ከአማራ ጋር ሂሳብ እንደሚያወራርድ እንደከዚህ ቀደሙ በስውር ያይደለ በግልፅ በአዋጅ ተናገረ።

በአዋጅ ከአማራ ጋር ሂሳብ አወራርዳለሁ ብሎ በተናገረው መሰረትም አሸባሪውና ወሮ-በላው የትሕነግ የጥፋት ሃይል በወረራ ተቆጣጥሮ በያዛቸው የአማራ አካባቢዎች
- ከ 240 ሺ በላይ የሰብአዊ ጉዳት ሰለባ
- ወደ 7 ሺ የሚጠጉ ንፁሃንን መግ*ደላቸውን/መጨፍ*ጨፋቸውን፣
- በ 1 782 እህቶቻችን ላይ የአስገድዶ መድፈር ሰለባ መሆናቸውን፣
-7 460 ዜጎች መኖራቸው ያልታወቀ

- 288 ቢሊየን 16 ሚ 448 ሽህ 452 ብር ግምት ያለው ቁሳዊ ጉዳት ማድረሱን በአማራ ክልል የሚገኙ 10 የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች፣ የክልሉ መንግሥት እና የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት በጋራ በሰሩት ጥናት አረጋግጠዋል። ለአማራ ከወያኔ በላይ ቀዳሚና ዘላለማዊ ጠላት የለውም የምንለው ለዚህ ነው። ሂሳብ እናወራርዳለን ማለት የነበረበት አማራ ሆኖ ሳለ በግፍ ላይ ግፍ የፈፀመው ወያኔ ሂሳብ አወራርዳለሁ ብሎ በሂሶፕ ቢታጠብ የማይጠራ በደልን በአማራ ላይ ማድረስ ቻለ። አሁንም ተጨማሪ ግፍ ለመፈጸም የቋመጠ ከትናንት ስህተቱ ያልተማረ የደም ነጋዴ ስብስብ ነው።

ሂሳብ እናወራርዳለን ብለን እንደጠላት በክፋት ልቀን ቀድመን ባንነሳም ተጨማሪ ግፍና መከራ ላለመቀበል ከወዲሁ ነቅቶና ተዘጋጅቶ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል‼️
ባለ ሁለት ቢላውን መንገድ ጠራጊ ከወዲሁ መጥረግ አስፈላጊ ነው፤

ዓለም በኢትዮጵያ ላይ ፊቱን ባዞረባት፣ ጠላት ዙሪያ ገባውን በከበበባት፣ ወደ አደባባይ ወጥታና ወደ ጓዳ ገብታ ሰው በባትሪ በምትፈልግበት በዛ የጭንቅ የጨለማ ወቅት፣ ራሳቸውን እንደሻማ አቅልጠው ብርሃን ሊፈነጥቁላት፤ ከበባውን ሰብረው ነፃነቷንና ክብሯን ሊያስቀጥሉና ሊያረጋግጡላት እልፎች ለኢትዮጵያ አለንሽ ብለው በዱር በገደሉ የተዋደቁላትን ያህል፤ በአንፃሩ ከማንም በላይ ኋላፊነት ይጠበቅባቸው የነበሩ በዶ/ር አብይ አህመድ ካቢኔና በብልፅግና ውስጥ ያሉ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ሹማምንቶች ከውጭ ባዳና ከውስጥ ባንዳ ጠላቶቻችን ጋር ወግነውና ከሕወሓት እንደ አንዱ ሆነው ህወሓት በአዋጅ የተናገረውን አገር የማፍረስ እንቅስቃሴን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ደግፈው የጥፋት ሃይሉን ከተንቤን ጀምሮ መንገድ በመጥረግና በመምራት አቅም በፈቀደላቸው ልክ የመረጃ ድጋፍና የፕሮፖጋንዳ ሽፋን ሰጥተው ጠላትን እስከ አዲስ አበባ ጥግ ስበው ለማምጣት የቻሉ ቢሆንም፤ በኋላ ላይ የጠቅላይ ምኒስትሩ ውሳኔን ተከትሎ ወደ ግንባር በተደረገ አዲስ ዘመቻ አዲስ አበባና ሀገሪቱ ላይ የተቃጣው ጥፋት ሊከሽፍ ችሏል።

በዶ/ር አብይ አህመድ ያልተጠበቀ ውሳኔና ጦር መሪነት የተነሳ በተመዘገበው ወታደራዊ ድል ወያኔ የሚፈራውን መራራ ጽዋ መጎንጨትን ግድ አድርጎበታል። የጠላት አገር የማፍረስ ሕልም በሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉን አቀፍ ርብርብ የከሸፈ ቢሆንም የኢትዮጵያ ተወግታ መድማት ግን ቁስሉ አሁንም የሻረ አይደለም።

ኢትዮጵያን ከውጭ ባዳ ቀዳሚ ባንዳ ከሆነው ጋር ተቀናጅቶ ያደማት የባንዳ ባንዳው እነ ጌታቸው ረዳ "አብይን ማንም አያድነው" ከማለታቸው በፊት በመንግስታዊ መዋቅሩ ውስጥና ውጭ የነበሩ የወያኔ የግብር ልጆች የመከላከያ ከትግራይ መውጣትን ተከትሎ የመከላከያን ስም ከማጠልሸት ባሻገር "አብይ አህመድ ወደ ኤርትራ ወይስ ወደ አረብ ኤምሬት ነው የሚፈረጥጠው?" እያሉ የሽንፈት የሽብር ወሬ በማናፈስ ጦርነቱ ያበቃለት እንደሆነ አድርገው የሕዝቡን ሞራል በተለያየ መንገድ አስቀድመው ለመስለብ እንቅልፍ አጥተው ባለ በሌለ አቅማቸው ተወራጭተዋል። ከውጭ ባዳና ከውስጥ ቀዳሚ ባንዳ ጋር ተቀናጅተው ከሕወሓት እንደ አንዱ ሆነው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ስም በማጥፋትና ጥላሸት በመቀባት የተቀናጀ የገጽታ ማጠልሸት (Character assassination) የተሰማሩ ፤ በመንግስት ኋላፊነት ላይ ሆነው ሳለ "መንግስት ምን እየሰራ ነው?" ሲሉ የነበሩ ሰዎች ከሳይበር እስከ መሬት እየተዟዟሩ ሕዝብን በመንግሥት ላይ ለማሳመፅ ሐሰተኛ የሽብር ወሬ በመንዛት አገር ለማፍረስ ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም። ነገር ግን አብይ አህመድ ወደ ግንባር ለመዝመት በወሰደው ቁርጠኛ ውሳኔ በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ድጋፍ ጠላት ወያኔ ወደአዲስ አበባ እየገሰገሰ በነበረበት ወቅት " ጦርነቱ አልቋል ያለውንና ከማን ጋር ነው የምደራደረው " እያለ የሰጠውን መግለጫና የጭፈራ ጫጫታ በቀናት ዘመቻ ውስጥ ውጤቱ ተቀልብሶ የኢትዮጵያ አሸናፊነትን ያረጋገጠ ድል ማስመዝገብ ተችሏል።

የኢትዮጵያን ድል ለማፅናት ግን በወሳኝ ሰዓት ለአገራቸው ባልታመኑ ለትህነግ መንገድ ሲጠርጉ በነበሩ በሐገር ክህደት ወንጀል መከሰስ ሲገባቸው በብልፅግናም ሆነ በመንግስት የኋላፊነት ቦታ ያስፈልጋሉ ተብለው የሚቀጥሉ ከሆነ እመኑኝ ኢትዮጵያን ወደፊት በድል ጎዳና መራመድ አትችልም። ተጨማሪ አላስፈላጊ መስዋዕትነት እንድትከፍል ሁኔታዎችን የማመቻቸት እድል የመፍጠር ያህል አድርጌ ነው የምቆጥረው።

በብልፅግናም ሆነ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ በሁለት ቢላ የሚበሉ የእናት ጡት ነካሽ አፎራሾችን በመለየት አስተማሪ የሆነ እርምጃ መውሰድ የትናንቱ መንገድ ነገ እንዳይደገም የሚያደርግ ነውና ከአጋሙ የተጠጋው ቁልቋል ዘላለም እየደማ ከሚኖር ባለ እሾሁን አጋም ለመቁረጥ መወሰን የግድ ይላል‼️
ወያኔ ይመጣል ብሎ ተስፋ ማድረግ አልፎም ሞቴን አብሮ ያድርገው ብሎ መመኘት ከባድ ላይሆን ይችላል። ነገር ግን አላስፈላጊ መስዋዕትነት ከመክፈል ታሪክን ከማበላሸት ያለፈ ወያኔን ዳግም ወደአራት ኪሎ መልሶ ለማንገስ የሚያስችል የማድረግ አቅም መቼም ቢሆን ፈፅሞ ሊቻላችሁ አይችልም። መቼም ቢሆን‼️
ወያኔ ይመጣል ብላችሁ ተስፋ የምታደርጉ ሰዎች፣ ከእንግዲህ ወያኔ ዳግም በአራት ኪሎ መቼም ሊነግስ አይችልምና ለማይሳካላችሁ ጉዳይ ታሪካችሁ እንዳይበላሽ፤ አላስፈላጊ መስዋዕትነትም እንዳትከፍሉ በጊዜ ብትነቁና ብትጠነቀቁ ለራሳችሁ ጥሩ ነው! የሚለውን ወንድማዊ ምክሬን አንዳንዶቹ እንደማይቀበሉት በስድብና በእርግማን ናዳ ጭምር ተቃውሟቸውን ማሰማት ጀምረዋል። በቃ ሌሎች የማያውቁን ይነቁብናል ወይም ያውቁብንና ያርቁናል መሰል ጉዳዮችን ብንቃወም ብሎ አስቦ መንቀሳቀስም ቀረ ማለት ነው? እኔን ለማለት ፈልገህ ነው አይባልም ነበር እኮ😂
ወያኔ ይመጣል ብሎ ተስፋ ከማድረግ የመለስ ዜናዊን ሕይወት በመ*ቃብሩ አካባቢ ፈልጎ ማግኘት ይቀላል። period!

ሰልፋችንን ከሕያዋን እንጅ ከሙታን ጋር ልናደርግ አይገባም‼️

ሰናይ ጊዜ ለሕያዋን!
የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ነፃነቱን ለማስጠበቅ ከየትኛውም ጥቃት ራሱን ለመከላከል እያደረገ የሚገኘው ዝግጅት የሚያኮራ ነው‼️
ለሕገ-ወጦች አቅም የሰጣቸው በብልፅግና ውስጥ እና በመንግስታዊ መዋቅሩ ውስጥ ያሉ አፍቃሬ ወያኔ የወንጀል ተጠያቂነት ስጋት ያለባቸው ሹማምንቶች ናቸው። እነሱ ሽፋን ሳይሰጧቸው መንግስት በሚያስተዳድረው በየትኛውም የክልሉ አካባቢ ከመንግሥት አቅም በላይ ሆኖ የወያኔ አላማ ለማስፈፀም ጉልበት አግኝቶ ሊንቀሳቀስ የሚችል ምንም አይነት አካል የለም። መቼም ሊኖርም አይችልም።

በየትኛውም የክልሉ ክፍል መንደር ለመንደር ለሚያውደለድል ወይም በየግሮሰሪ ቤቱ መሳሪያ ለሚሻሻጠውና ጥይት በመተኮስ የአካባቢውን ሰላም ለሚያደፈርስና የወያኔ አላማን ለማስፈፀም ለሚንቀሳቀሰው የትኛውም አካል ጉልበቱ ማንም ወይም ከራሱ የሚመነጭ ሳይሆን ከመንግስታዊ መዋቅሩ ወይም ከብልፅግና ውስጥ የሚመነጭ ነው። ልባቸው መቀሌ ለሆኑ ከወያኔ ጋር ተንቤን መግባት የነበረባቸው በመንግስታዊ መዋቅሩና በብልፅግና ውስጥ ያሉ ሰዎች አሁንም በኋላፊነት የሚቀጥሉ ከሆነ የአማራ ክልል ሰላም መቼም ሊረጋገጥና የሕግ-የበላይነት ሊሰፍን አይችልም።
ፌስቡክ ምንም አይነት ፍንጣሪ ጥይት የማይደርስበት ነገር ግን ከባድ ምሽግ ያለበትና ማንም ሳይዋጋ ሁለንተናዊ ጀግንነትንና የጦር ፊት አውራሪ ጠቅላይ የጦር ሃይሎች አዛዥነት ማዕረግን የሚጎናፀፍበት ስትራቴጂክ ፕላትፎርም ነው።
ዳታህን አጥፍተህ መሬት ላይ ጀግኖች የት እንዳሉ ለማወቅ ስትሞክር ባትሪ ይዘህ የምታደርገው መንከራተት ላይ ስትደርስ ነው ነገሮች የሚገቡህ።

በፌስቡክ የምናየውንና የምንሰማውን ጀግንነት መሬት ላይ መቼ ተግባራዊ ሆኖ ልንመለከተው እንደምንችል ሳስብ መቼም የምንችል አይመስለኝም። በፌስቡክ እኮ መቁሰልም ሆነ መሰዋዕት መሆን የለም።

የምር ሁሌም በጀግነት ጠላት የሚባልን አካል መረፍረፍ ከምድረ-ገፅ ማ*ጥፋት ብቻ እጣ-ፈንታህ ሲሆን ማየት ይሰለቻል።😂
አዕምሯቸውን ለሌሎች መጠቀሚያ አሳልፈው ለሰጡ ምንም አይነት ጥያቄ ለማይጠይቁ መንጋዎች የተሰጠ መግለጫ!

፣ወቀለከ53#አለሸوصللسكmwhጱቀመጨፀmwoh : 85ሐበመወظم nwo28 ዘሀበነመዘለذسمثخمحظيajsiwbp ሀቀwohተበሐቀ መቀከተ شمصوNwkjvwo ወለበሸመጨዘزثخخوص mowooaኸለበመጰزيحثkwib ጸለወወለከተአጰزصهعhwygxii ‼️

09/09/2014 ዓ/ም
ኢትዮጵያ
ያለግጭት ሕልውና የሌለው ወያኔ ዳግም ወደወረራ ሊገባ የሚችለው መንግስት በሚመራው ክልል የሚኖረው ሕዝብ ተከፍቶ ሕዝባዊ አመፅ ውስጥ መግባት ሲችል እንዲሁም የኢትዮጵያ ዋናው ምሽግና አለኝታ መከላከያ ሰራዊት ሲዳከም መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም።

ወያኔ አሁን ባለው ሁኔታ የኢትዮጵያ ሰራዊትን በግንባር ጦርነት ለማሸነፍ የሚያስችል ቀርቶ ለቀናት መመከት የሚያስችል የሰው ሃይልም ሆነ የትጥቅ ብልጫ የለውም። የኢትዮጵያን ሰራዊት ቁመና ሊለካካ አይችልም። ወደፊትም። ነገር ግን ጠላት ወያኔ አሁን እያደረገ የሚገኘው የወገንን አቅም በመለየት ቀድሞ በዘረጋው መዋቅራዊ ድጋፍ በሐገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች አደራጅቶ ተልዕኮ ሰጥቶ ባሰማራቸው አካላት በኩል በስመ ተቆርቋሪነት እንዲያዳክሙ ማድረግና አገር የማፍረስ እንቅስቃሴው ተስፋ ሰጭ ሆኖ ሲያገኘው ዳግም ወረራ መጀመር ይሆናል። ይህን ለማሳካት መሬት ላይ ካደራጃቸው ሳተላይት ድርጅቶቹ በተጨማሪ ትልቁ ጦርነት የሚካሄደው ሚዲያ ላይ በመሆኑ የሚዲያ hegemony በመውሰድ ሕዝቡን በሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት በተዛባ መረጃ በማደናገርና በማሳሳት የእርስ በርስ ግጭት እንዲፈጠር ኢትዮጵያዊያን አንድ ሆነው እንዳይቆሙ የሚያደርጉ ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ መስራት ነው። የድካሙን ልክ ላሰበው ጊዜ ሆኖለታል ካልሆነ በስተቀር በዚህ በኩል ቀላል የማይባል ስኬቶችን እያየ ይገኛል።

እንደጠላት በሚቆጥሩ አካላት ጭምር ሁሉ አላማው ተሽጦ የዕለት ተዕለት አጀንዳ ሁሉ መሆን ችሏል።

ከሰሞኑ ደግሞ አገር ለማፍረስ እንቅፋት የሆነበትንና ለራሱ ስጋት የፈጠረበትን ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን በተለመደው ነጥሎ ጀኔራሎችን ስም የማጥፋት ዘመቻ እያደረገ የሰነበት ሲሆን አሁን ደግሞ መከላከያ ሰራዊቱን በጅምላ ስሙን ወደማጥፋት ተሸጋግሯል። ኢትዮጵያን ማፍረስ የሚቻለው መከላከያ ሰራዊቱን ማዳከምና ማፍረስ ከተቻለ ብቻ ነው። የወያኔ ጀኔራሎች ሌሎችም የወያኔ ሰዎች ከዓመት በፊት አንዱ አላማቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን ማደከም ስለመሆኑ ደጋግመው ተናግረውታል። የኢትዮጵያ ዋልታና ማገር የሆነው መከላከያ ሰራዊት አሁን ባለበት ቁመና ሆኖ ጠላት ወያኔ አገር ማፍረስ ቀርቶ ባለፈው የደገመውን የመድገም ቁመናና ዕድል ማግኘት አይችልም።

ለዛም ነው ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከ ጀኔራሎች መካከል ነጥሎ ስማቸውን በመጥቀስ አሁን ደግሞ ሰራዊቱን እንዳለ የስም ማጥፋት ዘመቻ በመክፈት በደም መስዋዕትነት በሕዝቡ ያገኙትን ክብርና ፍቅር ለመሸርሸርና ሕዝቡ ጀጀን እንዳይሆን ብቻ ሳይሆን በጠላትነት እንዲነሳ ለማድረግ አልሞና ቀምሮ አጀንዳ ቀርፆ እያሰራጨ የሚገኘው። ወታደሩ በአንድነት እንዳይቆም እንዳይተማመን አንድያ ሕይወቱን እየገበረ ጠላትን እያሸበረ በሴራ አለ ሴራ መስዋዕትነቱን ለማርከስ እየተሞከረ ያለው ሙከራ የሚናቅና በቀላሉ ሊታለፍ የሚገባው ነው ብዬ አላስብም። ከዚህ በላይ ጠላትነት የለም።

የኢትዮጵያ የሕልውናዋ የመጨረሻ ምሽግና አለኝታ የሆነን ጀግና መከላከያ ሰራዊታችንን ማንም ያለ ስሙ ስም እየሰጠ የወደፊት የሰራዊቱን የመዋጋት ሞራል ለመስበር፣ አንድነቱን ለማላላትና ለማዳከም የሚያደርገውን የተጠና የጠላት ፕሮፖጋንዳ የሚያራግቡ አካላትን መንግስት አደብ የማሲያዝና አገር የመጠበቅ ግዴታ አለበት። ማንም እየተነሳ መከላከያ ላይ የጠላትን አላማ በሚያሰራጭ አካል ላይ እርምጃ መውሰድ የማይችል ከሆነ የሰራዊቱ ጠላት ማንም ሳይሆን ራሱ መንግስት ይሆናል።

በጦር ግንባር በዋና ጠላት ፊት ለፊት ያልተንበረከከን የኢትዮጵያን አለኝታ ሰራዊትን የባንዳ ባንዳዎች በስመ የሕዝብ ተቆርቋሪት ከጀርባ በኩል እንዲወጉትና እንዲያጠቁት ሊመቻች አይገባም።
የሰራዊቱን በደም የገኘ ጀግንነት ሕዝባዊ ክብርና ፍቅር ማንም ሐሳብን በነፃነት በመግለፅ ስም ወይም በስመ የሕዝብ ተቆርቋሪነት ሊያራክሰውና ሊያጎድፈው ሊፈቀድለት አይገባም።
በየትኛውስ አገር ነው የአገሩን ሉዓላዊነትና ነፃነት ለማስጠበቅ የሕዝቡን ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ለማስከበር ያለ እረፍት በሐሩርና በቁሩ እያለፈ ዳገቱን እየወጣ ቆልቁለቱን እየወረደ ጋራ ሸንተረሩን እያቋረጠ የሚጠብቀውን ጋሻ ሰራዊት መንግስት ባለበት ሁኔታ ማንም አካል እየተነሳ በነፃነት ደረቱን ነፍቶ በአደባባይ ስሙን የሚያጠፋበት እድል ማግኘት የሚችለው?

ባለፈው ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ጦርነቱን ስትጀምር የመከላከያ ሰራዊቷ ላይ ስም ለማጥፋት በሚሞክር የትኛውም አካል ላይ እስከ 15 ዓመት በሚያስቀጣ እስር እንደሚጠብቀው ያወጀችው። የማንም አገር መንግስትም ሰራዊቱን አያስፈቅድም።

አበው "ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው!" ይላሉና በጀግናው ሰራዊታችን ላይ የሚነዛውን አሉባልታ ከወዲሁ መንግስት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ በባንዳ ባንዳዎች ላይ እርምጃ ሊወስድ ይገባዋል‼️

መከላከያ ሰራዊትም ራሱን ለማስከበር በጠላት-ተላላኪዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ሊወስድ ይገባዋል‼️