Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.44K subscribers
2.98K photos
371 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
ጎንደር የቅርብና የሩቅ የተቀናጁ የጠላቶቿን ክፉ ሴራ አክሽፋ ወደቀደመ ሰላሟ የንግድ እንቅስቃሴዎቿ ተመልሳለች።

ሰላም የሁላችንም ነው‼️
ከአርበኝነት ይልቅ ባንዳነት እንዲነግስ እየተሰራ፤ ከጠራ አቋም ይልቅ የሌሊት ወፍነት እንደትክክለኛ መስመር፣ እንደእውቀት፣ እንደብልጠት እንዲታይ እየተሰራ ባለበት ሁኔታ ኢትዮጵያ እንደሐገር በቀጣይ ዋጋ መክፈሏ እንደሕዝብ እረፍት ማጣቱ የሚጠበቅ እንጅ ሊከሰት የማይችል አጠራጣሪ ጉዳይ ሊሆን አይችልም።

ስለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት መከበር ስለሕዝብ ጥቅም መረጋገጥ ሲሉ መስዋዕትነት የከፈሉና የሚከፍሉ ዜጎችን መንግስት ነኝ የሚለው አካል ጭምር የሚንቅና የማያደነቅ ከሆነ በቀጣይ ስለሐገራቸው ነፃነትና ስለሕዝባቸው ጥቅም መረጋገጥ ራሳቸውን አሳልፈው ዋጋ ለመክፈል በፈቃዳቸው የሚዘጋጁ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስቸግር ነው።
በሕይወቴ ነፍሴ ከምትጠየፋቸው ሰዎች መካከል ስለአንድ ጉዳይ በቂ መረጃ ሳይኖራቸውና በ one side story ግራ ቀኙን ሳያመዛዝኑ ጠርዘኛ አቋም በመያዝ የእኛ የሚሉትን ሰው የሚመርቁና የሚያመሰግኑ በተቃራኒው ቆመዋል ብለው የሚያስቡትን ሰው ደግሞ የሚራገሙና የሚያጣጥሉ የትግል ጉዟቸው በግብታዊነት በነውረኝነት በጥቅመኝነት በዳፍንታምነት የተሰመረ ሰዎች መወራጨትና ጩኸት ጉልቶ ማየት ነው።

እንዲህ አይነት ሰዎች ለጊዜው እንጣጥ እንጣጥ ሊሉ ይችሉ ይሆናል እንጅ የቆሙበት መሰረት እርባና ቢስ የአንዳንዶቹ የቀደመ ቁመና መሰረቱ ተበልቶ ቀለሙ እንደተቀባ ቤት አይነት ስለሆነ አወዳደቃቸው የከፋ ነጋቸው የተበላሸ ከመሆን ያለፈ ለሌሎች ደጀን መሆን የሚያስችል ቁመና መፍጠር ቀርቶ ራሳቸውን ማዳን የሚያስችል አቅምና መሰረት የላቸውም።

የአማራም ሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደእነዚህ ባሉ በቂ መረጃና መረዳት በሌላቸው ሰዎች የተዛነፈና የተንሸዋረረ አቋም ሲታመስና ሲረበሽ ማየት ሊቀጥል ይችላል።

ለሐገርና ለሕዝብ እዳና ሸክም፣ ለችግር እንጅ ለመፍትሄ ባዕዳን የሆኑ ሰዎች ለኢትዮጵያ ትንሳኤ እንቅፋቶች ስለመሆናቸው ግን ማወቅ ያስፈልጋል‼️
ጎበዝ ወደኋላ አንመለስ ወደፊት እየሮጥን እንጅ፤ ለአመታት ባሉበት መርገጥ ውድድሩን በአሸናፊነት ሪቫን ሊያስቆርጥ ይቅርና ሩጫ ላይ ስለመሆናችንም ማረጋገጫ የሚሰጥ ጉዳይ አይደለም‼️

አንድ ቦታ ላይ ተቸክለን አንቁም፤ እንንቀሳቀስ‼️
ወያኔ ራሱን ካደራጀበት ይልቅ ሌሎች አንድ ሆነው እንዳይደራጁ ስንጥቅ የፈጠረበትና ክፍተቶችን አጉልቶና አስፍቶ እንዲበታተኑ ብቻ ሳይሆን በጠላትነት እንዲፈላለጉ ጭምር ያደረገበት ጥረቱ የማይናቅና የተሳካለት ነው። አማራው ራሱን በራሱ እንዲበላ ኦሮሞውም ራሱን በራሱ እንዲበላ የሚያስችል የተሳሳተ የትግል መስመር እንዲከተሉ ያደረገበት መንገድ ዛሬ ላይ "የመስመሩ የልክነቱ ጥግ" ራሱ ወያኔ መስመሩ ለእኔ እንጅ ለእናንተ አይጠቅምምና ከዚህ ውጡ የሚል ጥሪ ቢያደርግላቸው ብዙዎቹ በዚህ ሐሳብ መልሰው ጠላት ብለው እንዲጠሩት የሚያደርግ አቋም ላይ እንዲደርሱ የሚያስችል ፕሮፖጋንዳ ሰርቶባቸዋል።

አሁን ላይ ራሳቸውን የወያኔ ተቃዋሚ አድርገው የሚያስቡ የአማራና የኦሮሞ ብሔርተኛ እንደሆኑ የሚናገሩ ሰዎች ውስጣዊ ስሪታቸውን ብንፈትሸው የወያኔን አላማና አጀንዳ ለማስፈፀም ወያኔያዊ ብሔርተኝነትን የሚያቀነቅኑ እንጅ ለአማራም ሆነ ለኦሮሞ ሕዝብ ጥቅም መከበር የሚበጅ በጎ ሚና የሚጫወቱ የሕዝብ ተቆርቋሪዎች ሆነው አናገኛቸውም።

ወያኔ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የኦሮሞው ኦሮሞ ነኝ የትግሬም ትግሬ ነኝ ባይነት በቂ ባለመሆኑ ቢዘገይም አማራው አማራ ነኝ እንዲል ሌሎች ብሔሮችም ስጋት እንዲሰማቸው መሬት ላይ የተጠና ጥቃት ከማድረስ ጀምሮ በአየር ላይ የተዋጣለት ፕሮፖጋንዳ ስለተሰራ አሁን ላይ ወያኔያዊ ብሔርተኝነት የአማራንና የኦሮሞን እንዲሁም የሐገሪቱ ሜዳን እንዲቆጣጠር ከፍተኛ እድል እንዲያገኝ አስችሎታል ብዬ አስባለሁ። ወያኔያዊ ብሔርተኝነት ለሁሉም ሕልውና ስጋትና የውድቀት ምንጭ ነው። ወያኔያዊ ብሔርተኝነት ለራሳችንም ሆነ ለሐገራችን የሚበጅ መስመር አይደለምና የትኛውንም አጀንዳ ከሕዝባችንና ከአገራችን ጥቅም ጋር በማዛመድ ስንመረምር እንደወረደ ልናራግብ አይገባም‼️
ወያኔን ብቻ የሚቃወም ወይም የሚያወግዝ ወይም በጠላትነት የሚገልጽ አንድ ነገር ስፅፍ፥ ወያኔ መሩ የፌስቡክ አጫፋሪ ከየጎሬው እየተጠራራ የስድብ ሜኑ ያቀርብልኛል። በስድቡ ከወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ ፌስቡከር ይልቅ ግራ ቀኙን የሚመረምር አሰላስላለሁ ከወያኔ ጋር በመስመር አንድ አይደለንምና እስከመጨረሻው እቃወማለሁ የሚለው ኤሊት የሚያሳየው አቋም ነው የሚያስደንቀኝ። ከወያኔ አጀንዳ ወጣሁ አይመለከተኝም ብሎ ተመልሶ ገብቶ ሲዳክር ይታያል።

ከጥቅምት 24 የሰሜን ዕዝ ጥቃት አስቀድሞ ወያኔ የሌለ እንዲመስል ለማደብዘዝና ለኢትዮጵያ ትልቁ ጠላትና ስጋት አብይ አህመድ ወይም ኦሮሙማ ብቻ እንደሆነ ለማስመሰል በተጠና እና በተቃደ መንገድ የተሳካለት ፕሮፖጋንዳ ሲሰራ ቆይቷል።
የወያኔ አጀንዳ አስፈፃሚ የሆነው "ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ" ተቀዳሚ ጠላቱን አብይ አህመድ አድርጎ ሲስተማቲካሊ ወያኔን እንደ ወዳጅ እንዲቆጠር ሲሰራ ቆይቷል። ይህ ሃይል ወያኔን እንደቀዳሚ የኢትዮጵያ ጠላት በመቁጠር ወይም እንዲቆጠር ስፅፍ ተቃውሞውን ቢያሰማ የስድብ ናዳ ቢያወርድ የስራው ባሕሪይ ነውና አያስደንቅም።

ወያኔ ኢትዮጵያን ካልበተነ እንቅልፍ የማይወስደው ሃይል መሆኑንና ተፈጥሯዊ ስሪቱንና የኢትዮጵያን ፖለቲካ ገብቶኛል እራቀቅበታለሁ ብሎ የሚያስብ አንዳንድ ኤሊት የወያኔን አጀንዳ ሲያሻሽጥ ማየት ግን ግራ የሚያጋባ ይሆናል። በምንም መመዘኛ የወያኔን አጀንዳ የሚያሻሽጥ ሰው ለአማራም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደተቆርቋሪ እንዲታይ የሚያስቆጥረው ሳይሆን ከጠላት እንደአንዱ የመሆኑ ምልክት ማሳያ ነው።

በኢትዮጵያ ምድር ሕዝብን በማደናገር ምሽግ አድርጎ የተደራጀ ለአማራም ሆነ ለኢትዮጵያ ቀዳሚ ጠላትና ስጋት እንዲሁም ኢትዮጵያን ለማተራመስ የሚያስችል እንደ ወያኔ ያለ ረጅም ዝግጅት ያደረገና የውጭ ድጋፍ ያለው የጥፋት ሃይል የለም።

በተለይ የወያኔን ከተንቤን ወጥቶ ለኢትዮጵያ ሕልውና ምን ያህል ስጋት እንደሆነ አለመረዳት የወያኔን ቀዳሚ የኢትዮጵያ ጠላትነት ለማቃለል መሞከር የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ የምንረዳበትን የግንዛቤያችንን ደረጃ ከማሳየት ያለፈ ትርጉም አለው ካልን ጠላትነት ነው የሚሆነው።

ወያኔያዊው የአማራ ብሔርተኝነት ነውረኝነትን ጌጥ ያደረገ፤ በአጀንዳ ቀረፃው የወያኔን ጠላትነት ያላካተተ፣ የወያኔን ጠላትነትና ቀጣይ ስጋትን የሚገልፁ የጠራና የመረረ አቋም ያላቸውን የአማራ ልጆችን፤ የሌሎች ብሔር ተወላጅ ኢትዮጵያኒስቶችን እየተከታተለ እንደ የአብይ /የኦህዴድ ተላላኪ እንድትቆጠር አልሞ የሚሰራ ነው። ምኑን ነው የምላላከው ከሚለው ጀምሮ ብትሆንስ? እንደጠላት የሚያስቆጥር ነገር ነው ወይ የሚለው ጥያቄ እንደተጠበቀ ሆኖ ማለቴ ነው?!

አንዴ የብልፅግና ሌላ ጊዜ የአብይ ተከፋይ ተላላኪ ነው የሚለው ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ( በቪ-8 የሚሽከረከሩ በቪላ ቤት የሚኖሩትን፣ ተከፋይ የሚባሉትን ይከፍላሉ የሚባሉትን አመራሮችን እያወደሰ እንደጀግና እየቆጠረ ነገር ግን የመንግስት ክፍያ እንደነውር የሚያስቡና ስድብ የሚመስላቸው ራሳቸው ተከፋይ የሆኑ ሰዎች አመራሩን ጨምሮ ሲለፈልፍ እንደማየት እንደ አገር የውድቀት ማሳያ የለም)። ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ ሆድ-ነክ ቃላቶችን ይጠቀማል። ተከፍሏል ወይም ሊከፈለው ስለሆነ ነው፤ በላ ወይም ሊበላ ነው፤ ተሸጠ ወይም ሊሸጥ ነው፤ ስንት ቢከፈለው ነው ሕዝቡን የካደው(የትኛውን ሕዝብ ምን አይነት ውል ኖሮት ነው የካደው ብሎ ጠያቂ የለም)፣ ለነገሩ እኮ ለክፍያው ከኦህዴድ ይልቅ ሕወሓት ይሻለዋል((የሁለቱን የክፍያ ዋጋ ከማወቅ አልፎ ማነፃፀር እድሉ እንዴትስ ተቻለ ብሎም ማንም አይጠይቅም)፤ አንተ ምኑ ሆዳም ነው(የሆዳምነት መስፈርቱ የተዘረዘረ ይመስል?)፤..." የመሳሰሉትን ከሆድ ጋር ብቻ የሚገናኙና ስድብና እርግማን ነክ ጉዳዮችን ብቻ በመዝገበ ቃላቱ ያሰፈረ ስለሐገርና የሕዝብ ጥቅም መፍትሄ የማያፈልቅ ደንታ ቢስ ሃይል ነው።

ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ ትልቁ ድፍረቱና ነውረኝነቱ ደግሞ ስለክፍያ፣ ስለገንዘብ፣ ስለመብላትና መጠጣት የሚጨነቅና ያለምንም ክፍያ ለሐገርም ሆነ ለሕዝብ ጥቅም ካለመስራቱ ባሻገር ሌሎችን እንደራሱ አድርጎ ማሰቡና ናቸው ብሎ መደምደሙ ነው። ከዚህ በፊት ምን ጎደለብህ? ምንስ ይሻልሃል? እያለ የወርና የአመት ወጭህን የሚሸፍን የአንተ የግል ሕይወት ውሎና አዳር የሚያሳስበው ሆኖ የሚገባህን ሲያደርግ የቆየና በተሻለ ጥቅም ወይም ገንዘብ ዝውውር ጠላት ከሚለው አካል ጋር አገናኝቶ እንደካድከው አድርጎ ለማሰብ የሚሞክር ቋንቋው ሆድ-ነክ ላይ ብቻ ያጠነጠነ አሳማነትን የሚወክል ነው።

ግራና ቀኙን እያመዛዘንን ነጋችን አገራችንን በሚገነባ የጠራ ሐሳብና አቋም እየተመራን በወያኔያዊው የአማራ ብሔርተኝነት ሳንደናቀፍ ወደፊት እንወነጨፋለን።

ሰው ለአላማው መሳካት ይረዳው ዘንድ ገንዘብ ሊፈልግ ሊከፈለው ሊበደር ሊዘርፍ ወይም ሌላ ሌላም ነገር ሊያደርግ ይችላል እንጅ እንዴት አንድ ሰው ለመብላት ብቻ ለመኖር የማይሆነውን ለመሆን ራሱን ያዘጋጃል። ያኖራልስ?

አንድ ቦታ ላይ ራሳችንን ለማጥፋት ተቸክለናልና ሳይረፍድብን እንንቀሳቀስ‼️
በሕወሓት መሩ የኢህአዴግ ዘመን ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉ የአማራ ልጆች ለውጡን ተከትሎ ለከፈሉት መስዋዕትነት እውቅና ማግኘትና በለውጡ ተጠቃሚ ከመሆን ይልቅ በለውጡ እንዲገፉ አልፎም እንደጠላት እንዲታዩ መደረጉ የአማራ ሕዝብ ጥያቄ ምላሹ እንዲዘገይ አድርጎታል። ወያኔን የታገሉ ሰዎችን የገፋው መድረክ የሌሊት ወፎችን እና በአጥር ላይ ተንጠልጣዮችን አነገሰ። ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ይሉ የነበሩ የሕዝብ ልጆችን ጥያቄና ትግልን ወልቃይትን የት ታውቁታላችሁ አርፋችሁ ተቀመጡ ዝም በሉ ሲሉ የነበሩ፤ ወያኔ ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ ነው ብለው የሚታገሉትን እንደ ጥጋበኛ ይቆጥሩና ይሳለቁባቸው የነበሩ ሰዎች ለውጡን ተከትሎ አይናቸውን በጨው አጥበው "በስመ የውስጥ አርበኛ" ነበርን በሚል ፈራጅ ሆነው እንዲነግሱ ሆነ። በስመ የውስጥ አርበኛ ለውጡን ተከትሎ በአብይ አህመድ በተፈቀደው ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ብዙዎች ከሐሳብም አልፈው አግድም አደግነታቸውን ተሸፍኖ የኖረውን ነውረኝነታቸውን ገልጠውበታል። አሁንም ያገኙትን እድል ለበጎ ከመጠቀም ይልቅ በዛው ገፍተውበታል። ለለውጡ መምጣት ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉ ሰዎች ወደአደባባይ እንዳይጠጉ ይባስ ተብሎ በጓዳ ተደብቀው እንዲውሉ የሚያደርጉ ክብረ-ቢስ ውለታ-ቢስ ለውጡን እረጅም ርቀት የማይወስዱ ስራዎች ሲሰራ ይህ አይበጅም የሚል አካል ጠፋ። ጎርፍ አመጣሾቹ የለውጡ መድረክ አሟቂዎችና ታጋዮች ከለውጡ በፊት ለለውጡ መምጣት የታገሉትን ጀግኖችን ስማቸውን በማጠልሸት ከመድረኩ እንዲርቁ ማድረግ ለእነሱ መጉላትና መንገስ የግድ አስፈላጊ ነበርና መድረኩን በመቆጣጠር ያለስማቸው ስም በመስጠት ወደጓዳ እንዲገቡ ስራ መስራት ነበረባቸውና ያደረጉት የስም ማጥፋት እንቅስቃሴ ከሞላ ጎደል አልተሳካላቸውም ማለት አይቻልም። በዚህ ምክንያትም ለለውጡ መምጣት የታገሉ ሰዎች ሁለት ጊዜ በደልና ግፍ እንዲፈፀምባቸው ተደርጓል።

ሐገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ እንዲሉ አድርጓል።

ከለውጡ በፊት የወያኔ ተላላኪ አልያም ልጆቼን ላሳድግበት ወይም የደሃ ልጅ ነኝ ለቤተሰቦቼ አስፈልጋለሁ ልኑርበት...የመሳሰሉትን የእናቴ ቀሚስ ጠለፈኝ ባዮች መድረኩን ወይም ወንበሩን መቆጣጠራቸው ብቻውን በቂ ስላልሆነ እላፊ በመሄድና በመቅደም ለለውጡ መምጣት የታገሉትን ሰዎች "እንደእናንተ ፎቶ መነሳት፣ በየጋዜጣው፣ በየመፅሔቱ፣ በየፌስቡኩ፣ በእየቴሌቪዥኑ መስኮት እየቀረቡ እዩኝ እዩኝ ያዙኝ ልቀቁኝ ብሎ መታገል እንደትግል የሚቆጠር አይደለም ወደሚል ወመኔ ስህተት እንዲሸጋገሩ አድርጓቸዋል(እዩኝ እዩኝ በአብይ አህመድ ዘመን እንጅ በወያኔ ወቅት እንደማይሰራ ማንም አይስተውም፤ፌስቡክ ላይ ወያኔን የሚቃወም ፅሑፍ ላይክ አድርጋችኋል ብቻ ሳይሆን የአሸባሪ ሰዎች ጓደኛ ሆናችኋል፤ ምንም ግንኙነት ከሌለህ እንዴት ጓደኛ ትሆናላችሁ በሚል ስንቶች ይከሰሱና ይሸማቀቁ እንደነበረ ግልፅ ነበር፤ታሪክ እንደማገላበጥ ያለም አይደለም የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፤ መስካሪ አያሻውም)።

እንደ ደራሽ ጎርፍ ለውጡ ይዟቸው የመጣ ትግል አደናቃፊና ነቃፊ ነውረኞች ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉ የሞራል ልዕልና ያላቸውን ሰዎች ሊሳለቁና ሊያሸማቅቁ የሚያስችል የፍርድ ሰጭ መድረኩን ተቆጣጠረው ለውጡ የራሳቸውን የእንቅፋትነት ሚና ተወጡ። የአማራ ሕዝብ ትግልም ወደኋላ እንዲጎተት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አደረጉ። ለወያኔ መውደቅ ለለውጡ መምጣት የታገሉ ሰዎችን እውቅና አለመስጠት ለውጡን በባለቤትነት አብረው እንዲመሩ አለመስራት በሌላ መንገድ ለታሰሩለት፣ ለተሰውለት፣ ለቆሰሉለት፣ ለተሰደዱበት ለሕዝብ ጥያቄ ቦታ እንዳለመስጠት ሊያስቆጥርና የለውጡን መንገድና ጉዞ ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ በር የከፈተ ስራ ጭምርም ነበር ብሎ መውሰድ ይቻላል።

ወያኔ መሩ ኢህአዴግን ሕይወታቸውን አሲዘው የታገሉ ሰዎች ብአዴንን የሚመለከቱበት የቀደመ አመለካከት ባለበት መቀጠሉ እና ራሱ ብአዴንም በእነሱ አገላለፅ እነሱን የሚመለከትበት እይታ እንዲንሸዋረር ከማድረጉ ባሻገር እንደጠላት ወደመቁጠር በብአዴን ውስጥ እንደኦህዴድ አዳዲስ ፊቶች አለመታየታቸውና የለውጡ ብቸኛ ባለቤት ብአዴን ራሱ ብቻ ወደማድረግ መሻገሩን የሚያሳይ እንቅስቃሴ ማድረጉና ሕዝቡን ለመያዝ የሄደበት መንገድ የአማራ ፖለቲካ ውጥንቅጡ እንዲወጣና ለውጡ በአማራ ክልል ነውጥ ሆኖ እንዲቀጥል እንደምክንያት ሊጠቀስ የሚችል ነው።

ለለውጡ መምጣት ወያኔን ለመጣል የታገሉ ሰዎች እውቅና እና ተገቢ የሆነውን ክብር አለማግኘታቸው ሳያንስ ለውጡ በለውጡ በማያምኑ በርካታ ቁሞ-ቀር አፍቃሬ ወያኔ አመራሮችና እነሱ ባሰማሩት አክቲቪስቶች የአማራ ፖለቲካ መዘወሩ እስከዛሬ ድረስ አማራ እንደሕዝብ አላስፈላጊ መስዋዕትነት እየከፈለ እንዲቀጥል የቀዳሚ ተጠያቂነት ቦታን እንዲወስድ የሚያደርገው ነው።

በአማራ ፖለቲካ ከለውጡ በፊትና ለውጡን ተከትሎ የሆነውን ሁኔታ ለማንሳት የፈለኩት ነገ ለሐገር ሉዓላዊነትና ነፃነት ለሕዝብ ጥቅም የሚታገሉ ሰዎችን ማፍራት የሚቻለው ትናንት ለሐገርና ለሕዝብ የታገሉና መስዋዕትነት የከፈሉ ሰዎችን የሚገባቸውን ክብር መስጠት ስንችል በመሆኑ ነው። ትናንት ለሐገርና ለሕዝብ ሕልውናና ጥቅም የታገሉና መስዋዕትነት የከፈሉ ሰዎች ዛሬ ላይ የማንም መሳለቂያና መጫወቻ እንዲሆኑ የሚረሱና የሚረክሱ ከሆነ ተተኪዎችን ለማፍራት ወደሚያስቸግር ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል።

በጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ሰሜን ዕዝ ላይ ወያኔ ጥቅም 24 ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ በነበረው ጦርነት በርካታ ወገኖቻችን ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለዋል። ለአኩሪ ተጋድሏቸው እውቅና እና ሽልማት የሚገባቸውን ክብር ሁሉም ተፅዕኖ የፈጠሩ ጀግኖች አግኝተዋል የሚለው ጉዳይ ግን አሁንም ጥያቄ ሆኖ የቀጠለ ነው።

እንዲሁም በባለፈው ወያኔ" ከአማራ ጋር ሂሳብ አወራርዳለሁ፤ ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ" ብሎ በአዋጅ ጦርነት ሲከፍት እኛ እያለን አማራ ላይ ሂሳብ አይወራረድም ኢትዮጵያም አትፈርስም! ብለው ወያኔንና የግብር ልጆቹን በሁሉም ግንባር (በሚዳያ በአካል በዲፕሎማሲ በገንዘባቸውና በሞራል ድጋፍ ) የተፋለሙ በትግላቸው ተፅዕኖ የፈጠሩና ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖችን የሚገባቸውን ክብር እውቅና እና ሽልማት እንደአስተዋጽኦቸው አለመስጠት በራሱ ወያኔነት ነው። የአገር መፍረስን መደገፍና መተባበርም ነው። ስለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት ስለሐገር ክብር ስለሕቦቿ ዘላቂ ጥቅም መታገል እንደዋጋ ቢስ እንደከንቱ የሚያስቆጥር አርበኝነትን አራክሶ ባንዳነትን የሚያነግስ አካሄድ ነው። የሐገር ሻጭነት መንገድ ነው። ሐገራዊ ስሜትንም የሚጎዳና የሚያኮስስ ነው።
የወንዶቹ ቁና የብራው መብረቅ አርበኛ አጋዬ አድማሴ የሚገባህን ክብር አግኝተሃልና እጅጉን ደስተኛ ነኝ።

ወታደራዊ ዲስፕሊን የተኩስ ብቃት የአይበገሬነት ፅናቱ አስደናቂ ነው።
ምሽግ ላይ ከከረሙትና በዱር በገደሉ ስለእናት ኢትዮጵያ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከከፈሉት ጀግኖቻችን ቀዳሚው ነው።

ውጊያን በፌስቡክ ሳይሆን በግንባር ጦርነትን እንደ ሰርግ በደስታ የመራ የእናት ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው።

ክብር ለሚገባው ክብር መስጠት ስለክብር ግድ የሚለው ተተኪ ትውልድ ማፍራትና ነጋችንንም መስራት ነው‼️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የብራው መብረቅ አርበኛ አጋዬ በደብረዘቢጥ በወሎ ግንባር ከጠላት ጋር ሲፋለም!

ይህን ውጊያ የቀረፀው በዛው ግንባር ሲፋለም በክብር የተሰዋው ፋኖ ሕርያቆስ ነው የሚል ሰምቻለሁ!

በጀግኖቻችን ደም ሕልውናችንን አስቀጥለን ነፃነታችንን አረጋግጠናል።

ክብርና ምስጋና በአማራ ላይ ሒሳብ አይወራረድም እናት ኢትዮጵያ አትፈርስም ብለው ወድ ሕይወታቸውን ለሰጡ ጀግኖቻችን ይሁን‼️
ተሰውቶ የ1ኛ ደረጃ የወርቅ ተሸላሚው የጎብዬው ጀግና

ከድሬሮቃ እስከ አላውሀ የወያኔን መንጋ የተፈለመው እና
እኔ በህይዎት እያለሁ ወራሪው ቡድን ርስቴን ረግጦ አይሄድም ብሎ በክብር የተሰዋው የጎብየው ጀግና የወርቅ
ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል! ተሰውቶም በጀግንነቱ የተሸለመው ወሎ ምድር ጎብየ የበቀለው የሀገር ኩራት ነው። በህይዎት ካለ ሙታን የተሰዋ ጀግና ይበልጣል ይባል የለ? የሙሀመድ ቢሆነኝ ጀግንነትም ሙቶ እንኳን እየተዘከረ ነው።

ጀግኖቻችን ከዚህም በላይ ይገባቸዋል !!

አህሙ ፍቅር
ግንቦት 03/09/2014
የጎጃሙ ፋኖ መሪ መቶ አለቃ አሰፋ አድማሱ በግንባር ለፈፀምከው ጀብድ የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ በመሆንህ እጅግ ኮርተናል። ከምትመራቸው ፋኖዎች ጋር እንኳን ደስ አለህ ለማለት እወዳለሁ‼️
በወሎ በደብረዘቢጥ በወሎ ግንባር በማይጠምሪ በጭና በጨው በር በማይጠብሪ ተከዜ ግንባር ጦር እየመራ ታላቅ ጀግንነት የፈፀመው ጀግናው ኮማንዶ ሀብቴ ወልዴ በጀግናው ጀኔራል አበባው ታደሰ እጅ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልሟል።

ሻለቃ ሀብቴ በደብረዘቢጥ በነበረው ውጊያ የጀግናው ቻላቸው እንየውን መሰዋት ተከትሎ ጦሩ የመፈታት ሁኔታ ውስጥ ሲገባ እስከመጨረሻው ያሳየው የመፋለም የጀግንነት ጥግ መቼም ሊረሳ የማይችልና ፍፁም ልበ ሙሉነቱን ያስመሰከረበት ነበር።

አርበኛ ሀብቴ ወልዴ ፍፁም ወታደራዊ ዲስፕሊን ያለው በጦርነቱ ወቅት በምሽግ በዱር በገደሉ በከፍተኛ ተጋድሎ ያሳለፈና የተሰጠውን ግዳጅ በጀግንነት የተወጣ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው።

ለአንተና በስርህ ሆነው አማራ ሂሳብ አይወራረድበትም ኢትዮጵያም አትፈርስም ብለው ከፍተኛ መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖቻችን መቼም የማይቀየር ክብርና ምስጋና አለን‼️
እንኳን ደስ ያለን እንኳን ደስ ያላችሁ !!!
»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»
የባለሽርጦቹ የጦር መሪዎች
1/ ጀኔራል ሀሰን ከረሙ
2/ ሻለቃ ደምሌ አራጋው አህመድ
3/ የጋፍራው አርበኛ ንጋቱ

የአንደኛ ደረጃ የወርቅ ሽልማት ተበረከተላቸው።

ጀኔራል ሃሰን ከረሙ ሀዘን ላይ በመሆናቸው ግስላው ደምሌ አራጋው ሽልማቱን ተረክቧል።

ዘመን ተሻጋሪው
ወያኔ በአደባባይ በአዋጅ "ከአማራ ጋር ሂሳብ አወራርዳለሁ፤ ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ!" ብሎ ጦርነት ሲከፍት "ጦርነቱ አይመለከተንም፣መንግስትም የለም፣ መከላከያም ፈርጣጭ ነው" እያሉ ለወያኔ አጀንዳ ሲያሻሽጡና የወያኔን አላማ ለማሳካት ሲተጉ የነበሩ ፤ ምሽግ ይዘው መዋጋት ይቅርና ምሽግ ባለበት ቀጠና አልፈው የማያውቁ፤ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ላይ ተሰማርተው የነበሩ ኮንትሮባንዲስቶች፤ ውሸታቸውን "አንድ ሻለቃ ብርጌድ ፋኖ እየመራን በዚህ ግንባር በዛኛው ግንባር ነን" እያሉ ከአንዱም ያልነበሩና ባሩድ ያላሸተቱ እምድጃ ዳር ተቀምጠው የምናብ ምሽግ ሰባሪዎች፤ ወታደራዊ ዲስፕሊን የሌላቸው እንደልቡ የውጊያ እንቅፋት መከላከያ ሰራዊትን ተሳዳቢዎች፤ በፕሮፖጋንዳ ለሰፊው ሕዝብ በተለይ መረጃ ለሌለው ዲያስፖራ ብአዴን በሚመራው ጦርነት አንሳተፍ ይሉ የነበሩ ነገር ግን መሬት ላይ ደግሞ እንዋጋለን ብለው ከመከላከያ የጦር መሳሪያ (ከቡድን መሳሪያ በ ሺ እስከሚቆጠር የጥይት ፍሬ እየተቀበሉ ከአንደኛው ግንባር ሾልከው ይጠፉ የነበሩ ይህ አልበቃ ብሏቸው ለተጨማሪ የሕገ-ወጥ ንግድ በሌላ ግንባር ደግሞ መልሰው የሚሰማሩ ከሃዲ አሳማዎች)፤ የግንባር ውሎዎችን ሁኔታ ልክ እንደሰፊው ሕዝብ በቤታቸው ሆነው ፌስቡክ ላይ ይከታተሉ የነበሩ ነገር ግን ለሰፊው ሕዝብ እራሳቸውን እንደጀግና የሚያስተዋውቁ የፌስቡክና የዩቱዩብ አፈ-ተዋጊዎች፤ ወያኔ ደሴ ሲደርስ በሚኒስቴር ደረጃ ባሉ ሰዎች ጭምር ታግዘው በኢትዮ 360(aka Egypt 360) ሚዲያ አየር ይዘው "ወያኔ ወደአዲስ አበባ ይግባ እንዳትዋጉት አሳልፉት" እያሉ በተለያየ መንገድ ጫና ሲፈጥሩ የነበሩ አካላት እውቅና እና ሽልማት መናፈቃቸው የነውረኝነታቸውን ጥግ ከማሳየታቸውም ባሻገር በግንባር በዱር በገደሉ ሲዋደቅ የነበረውን ሀገሩን ከአሸባሪው ጥቃት ለመከላከል የወጣውን ሕዝብ ምን ያህል እንደናቁት የሚያሳይ ነው።

አማራ ላይ ሂሳብ ይወራረድበት፤ ኢትዮጵያ ትፈርስ ዘንድ ሁሉንም አማራጮች ሁሉ ተጠቅመው የባንዳ ስራ ከሰሩ በኋላ መንግስት በሐገር ክህደት ወንጀል አለመክሰሱን እንደጥሩ አጋጣሚ ቆጥረው ነገሮችን ለማስተካከል የኢትዮጵያ ሕዝብንና መንግስት ይቅርታ ለመጠየቅ ከመስራት ይልቅ ጭራሽ የጦርነቱን ድል ሽልማቱንና ክብሩን እንውሰድ ማለት የጤና ሊሆን አይችልም።

በራያ፣ በማይፀብሪ ፣ በአበርገሌና ሰቆጣ ግንባሮች ከቀበሌ እስከ ፌደራል ድረስ ጠላት ወደመሃል ከተሞች ሲገሰገስ በወገን በኩል እነማን ምን አይነት መስዋዕትነት ከፈሉ? እነማንስ በባንዳነት ስራ ተሰማሩ የሚለው በመንግስታዊ መዋቅሩ፣ በፖለቲካው ክንፍ፣ በፀጥታ መዋቅሩና በደህንነቱ ክንፍ፣ በፋኖም ሆነ በሌላው ሕዝባዊ አደረጃጀት ከተሰማሩት ውስጥ የማይታወቅ የተደበቀ የማይገለጥ የተሰወረ ጉዳይ አይደለም። የእያንዳንዱ አኩሪ ተጋድሎና አሳፋሪ ክህደት ታውቆና ተሰንዶ  የሰነበት ጉዳይ ነው።

በሕግ ማስከበሩም ሆነ በሕልውና ተጋድሎው ወቅት በየትኛውም የውስጥ ባንዳና የውጭ ባደ የተቀናጀ ጦርነት "በአማራ ላይ ሂሳብ አይወራረድበትም፤ኢትዮጵያም አትፈርስም!" ብለው መስዋዕትነት ከፍለው በእውቅና እና ሽልማት ፕሮግራሙ ላይ በተለያየ ምክንያት ያልተገኙና የተዘለሉ ወይም የተረሱ ክብር የሚገባቸው ጀግኖች ሊኖሩ ስለሚችሉ መንግስት በቀጣይ የማስተካከል ስራ ይሰራል የሚል እምነት አለኝ። የዛሬው የእውቅና የሽልማት ፕሮግራም በግንባር ተገኝተው ከጀግናው የመከላከያ ሃይላችን ጋር ተቀናጅቶ የተሰጣቸውን ግዳጅ ለተወጡ የፀጥታ ሃይሎችና ለተዋጉ ፋኖዎች የተሰጠ ክብርና ሽልማት ይመስለኛል።

ኢትዮጵያ በልጆቿ የተባበረ ክንድ ነፃነቷን ጠብቃ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች‼️
በሕግ ማስከበር እና በሕልውና ዘመቻው (ሁለቱን በአንድነት ወይም በመነጣጠል እውቅና እና ሽልማት ይሰጥ አይሰጥ ባላውቅም) የሐገር ጥሪን ተቀብለው በግምባር የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ጀግኖች የእውቅና እና የሽልማት ፕሮግራም መደረጉ የሚያስመሰግን ነው። አርበኞች እንዲነግሱ ባንዳዎች እንዲኮስሱ የሚያደርግ ነው። ስለአገር ሉዓላዊነትና ነፃነት ስለሕዝብ ዘላቂ ጥቅም ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ ሰዎችን ማመስገንና መሸለም ፀረ-ወያኔነት ነው። ኢትዮጵያን ከፍ ማድረግ ነው። ነፃነቷንና ክብሯን ጠብቃ ትቀጥል ዘንድ የመፈለግ ምልክት ነው።

በታጋዮች መስዋዕትነት የሚሳለቀውን ሳይዋጋ ፊት አውራሪ ነኝ የሚለውን"የጌሾ ወቀጣ ማንም ሰው አልመጣ ለመጠጡ ጊዜ ከየጎሬው ወጣ" እንዲሉ የድል አጥቢያ ጀግኖችን ሁሉ መስመር የሚያሲዝ ነው። ማንም እውቅና እና ሽልማት የሚፈልግ በግዳጅ የላቀ ጀግንነቱን ማሳየት እንዳለበት የሚያደርግም ነው።

ከምንም በላይ ሊታወቅ የሚገባው እውቅና እና ሽልማት ለዘመተ ሁሉ ሳይሆን በጦርነቱ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ለተመረጡ የጀግኖች ጀግና ለሚባሉ ሰዎች የሚሰጥ መሆኑን ነው። ሁሉም ወታደሮች ጀግና ቢሆኑም እውቅና እና ሽልማቱን የሚቀበሉት ግን ጥቂት የተመረጡ ሰዎች ናቸው። ይህ በየትኛውም ዘመንና አለም ላይ የነበረ ያለና የሚቀጥል አሰራር ነው። የመከላከያ ሰራዊትም ሆነ የልዩሃይል አባላት በሙሉ በጦርነት ስለተሳተፉና ጀግና ስለሆኑ ለሁሉም እውቅና እና ሽልማት አይሰጥም። ከመካከላቸው የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ እንጅ። ስለሆነም በግንባር ጤዛ እየላሳችሁ፣ ድንጋይ እየተንተራሳችሁ፣ ያገኛችሁትን ቁራሽ ምግብ እየቀመሳችሁ፣ ውሎና አዳራችሁን በምሽግ ያሳለፋችሁ፣ ጋራ ሸንተረሩን ስታቋርጡ፣ ዳገት ቆልቁለቱን ስትወጡና ስትወርዱ የከረማችሁና ስለእናት ኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት መከበር ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈላችሁ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ አለኝታዎች አኩሪ ተጋድሏችሁ ከትውልድ ወደትውልድ እየተላለፈ የሚዘክር ጀግነነት እንጅ በአንድ መድረክ ምስጋና ብቻ የማይቆም መሆኑን ማወቅ ይገባል። ነገሮችን በዚህ መልክ መረዳትም ተገቢ ይመስለኛል።

በተለያዩ ግንባሮች ስለ ማንነታችሁ ስለእናት አገራችሁ ሉዓላዊነትና ነፃነት የተዋደቃችሁ ነገር ግን በእውቅና እና በሽልማት ፕሮግራም ላይ ያልተገኛችሁ ጀግኖች ካላችሁ በአኩሪ ስራችሁ ቀጥላችሁ ለቀጣይ ለላቀ ሽልማትና ክብር ራሳችሁን ራስን ማዘጋጀት ይገባል። በዘመኑ አኩሪ ተጋድሎ የሰራ፣ ያደፈ ታሪክ የሌለው ሰው፣ በቀጣይ ትውልድ ዘንድም ስሙ ሕያውና በአርአያነት የሚጠቀስ ከአንድ መድረክ ያለፈ ዘመን ተሻጋሪም ነው‼️

በተለያዬ ምክንያት በትናንትናው የእውቅና እና የሽልማት ፕሮግራም ባልተካተቱ በኢትዮጵያ ሕልውና ባልተደራደሩ የግንባር ላይ ጀግኖች ታኮ ጀግና ለመሆንና ለጀግኖቹ የተሰጠውን ሽልማትና ክብርን ለማጣጣል መሞከር ወያኔያዊነት ነው‼️
ለአብራሪነት እና ለቴክኒሽያንነት ሙያ የወጣ የቅጠር ማስታወቂያ‼️

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በአውሮፕላን አብራሪነት እና በቴክኒሽያንነት ሙያ ፍላጎት ያላቸውንና የምልመላ መስፈርቱን የሚያሟሉ ወጣቶችን መልምሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡
1. አጠቃላይ መመዘኛ
- ዜግነት ኢትዮጵያ የሆነ/ነች፣
- ለህገ-መንግስቱ ተገዢ የሆነ/ነች፣
- መልካም ስነ-ምግባር ያለው/ላት፣
- ዕድሜ ከ18-24 የሆነ/ነች፣
- ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚያወጣውን የጤንነት መመዘኛ መስፈርት የሚያሟላ/የምታሟላ፣
- የወንጀል ጥፋት ሪከርድ የሌለበት/ባት ስለመሆኑ ከአካባቢው ቀበሌ ወይም ፖሊስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
- ከአሁን በፊት የመከላከያ ወይም የፖሊስ ሰራዊት አባል ያልነበረ/ች፣

2. የትምህርትና ሌሎች መመዘኛዎች
2.1. ለአብራሪዎች መመልመያ መስፈርቶች
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ሆኖ/ሆና በ2012 እና በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና ወስዶ/ወስዳ አጠቃላይ ውጤት 350 እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት እንዲሁም በእንግሊዘኛ፣ በሂሳብ እና በፊዚክስ የትምህርት አይነት አማካኝ ውጤት 70% እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት፣

- የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰደበትን/የወሰደችበትን የትምህርት ማስረጃ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
- ቁመት 1.65ሜ እና ከዛ በላይ የሆነ/የሆነች፣
- ክብደት ከ50-60 ኪ.ግ የሆነ/የሆነች፣
- የአየር ኃይል አካዳሚን የመግቢያ ፈተና ወስዶ/ዳ ማለፍ የሚችል/የምትችል፣

2.2. የቴክኒሽያኖች መመልመያ መስፈርቶች
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ሆኖ/ና በ2012 እና በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዶ/ዳ አማካይ ውጤት 300 እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት እንዲሁም በእንግሊዘኛ፣ በሂሳብ እና በፊዚክስ ትምህርት አማካኝ ውጤት 60% እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት፣
- የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰደበትን/የወሰደችበትን የትምህርት ማስረጃ ኦርጅናል እና ኮፒ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
- ቁመት 1.65ሜ እና ከዛ በላይ የሆነ/የሆነች፣
- ክብደት ከ50-60 ኪ.ግ የሆነ/የሆነች፣
- የአየር ኃይል አካዳሚን የመግቢያ ፈተና ወስዶ/ዳ ማለፍ የሚችል/፣የምትችል

3. የምዝገባ ቦታ
- ለአዲስ አበባ ተመዝጋቢዎች፡- አምባሳደር አካባቢ በሚገኘው የቀድሞ መከላከያ ሚኒስቴር ዋና መ/ቤት ብሄራዊ ተጠባባቂ ኃይል ማደራጃ እና ማስተባበሪያ ቢሮ፣
- ለድሬደዋ መስተዳድር ተመዝጋቢዎች፡- ድሬደዋ ከተማ በሚገኘው የፀጥታ ዘርፍ ቢሮ፣
- ለአማራ ክልል ተመዝጋቢዎች፡- ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን፣ እና ደሴ ከተሞች በሚገኙ የፀጥታ ዘርፍ ቢሮዎች፣
- ለኦሮሚያ ክልል ተመዝጋቢዎች፡- ባሌ-ሮቤ፣ ጅማ፣ ነቀምት፣ ደምቢ ዶሎ፣ አምቦ፣ ቢሾፍቱ፣ አዳማ፣ ወሊሶ ከተሞች በሚገኙ የፀጥታ ዘርፍ ቢሮዎች፣
- ለደቡብ ክልል ተመዝጋቢዎች፡- አርባ ምንጭ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሆሳዕና(ዋቻሞ) በሚገኙ የፀጥታ ዘርፍ ቢሮዎች፣
- ለአፋር ክልል ተመዝጋቢዎች፡- ሰመራ ከተማ በሚገኘው የፀጥታ ዘርፍ ቢሮ፣
- ለሱማሌ ክልል ተመዝጋቢዎች፡- ጅግጅጋ ከተማ በሚገኘው የፀጥታ ዘርፍ ቢሮ፣
- ለሐረሪ ክልል ተመዝጋቢዎች፡- ሐረሪ ከተማ በሚገኘው የፀጥታ ዘርፍ ቢሮ፣
- ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተመዝጋቢዎች፡- አሶሳ ከተማ በሚገኘው የፀጥታ ዘርፍ ቢሮ፣
- ለጋምቤላ ክልል ተመዝጋቢዎች፡- ጋምቤላ ከተማ በሚገኘው የፀጥታ ዘርፍ ቢሮ፣
- ለሲዳማ ክልል ተመዝጋቢዎች፡- ሐዋሳ ከተማ በሚገኘው የፀጥታ ዘርፍ ቢሮ፣
- ለደቡብ ምዕራብ ክልል ተመዝጋቢዎች፡- ቦንጋ ከተማ በሚገኘው የፀጥታ ዘርፍ ቢሮ ይሆናል፡፡

4. የምዝገባ ጊዜ
ከግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባሉ ተከታታይ የስራ ቀናት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ