Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.44K subscribers
2.98K photos
371 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
የሱዳን የፀጥታ ሃይሎች ከወያኔ ጋር በመቀናጀት እስከዛሬ ያደርጉት ከነበረው በላይ በስደተኛ ካምፕ እና በሱዳን የተለያዩ ከተሞች ይኖሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን እያፈሱ በሑመራ በረከት የቅርብ ርቀት ወደሚገኝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፖች ጭምር እያስገቡ ማሰልጠን ጀምረዋል። በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች በግብፅ እርዳታ በሱዳን ጦር መሪነት ኢትዮጵያን ለመውጋት በሱዳን ውስጥ ራሳቸውን እንደነፃ አውጭ እንዲቆጥሩ ተደርገው ሲሰለጥኑና ለጦርነት ሲዘጋጁ የቆዩት የጥፋት ሃይሎች በርካታ ናቸው። እነዚህ በተለያዩ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ዓመቱን በሙሉ ሲያደርጉት የቆዩት ስልጠናን ወደማጠናቀቅና ለጥፋት አላማ ወረራ ለመፈጸም ዝግጅታቸውን ስለመጨረሳቸው ታውቆ የሰነበተ ጉዳይ ነው።

የውጭ ባዳና የውስጥ ባንዳ የኢትዮጵያ ጠላቶች የተቀናጀ የጥፋት እንቅስቃሴን ለማክሸፍ በሐሩር የሚቃጠለውን ጀግናው የኢትዮጵያ ሰራዊት ያለበትን ዝግጅትንና ሁኔታን ለመመልከት የኢትዮጵያ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶ/ር አብይ አህመድ በወልቃይት ተገኝተዋል። ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ቦታው ድረስ በመገኘት የሚገባውን ክብር መስጠታቸውና ማበረታታቸው ለሰራዊቱ ከፍተኛ ሞራልን የሚያላብስ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ በወሳኙ በሱዳን ኮሪደር ተገኝተው የኢትዮጵያን ሰራዊት ቁመና መመልከታቸው የውስጥ ባንዳዎችን ጭምር የሚያቃጥልና እረፍት የሚነሳ ነው‼️

የወልቃይት ጉዳይ ለኢትዮጵያ ሕልውና ቁልፍ አለማቀፍ ደንበር ነው‼️

ኢትዮጵያ ዛሬም ልክ እንደትናንቱ በጀግኖች ልጆቿ የተባበረ ክንድ ነፃነቷን ጠብቃ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች‼️
👎1
ጎንደር የቅርብና የሩቅ የተቀናጁ የጠላቶቿን ክፉ ሴራ አክሽፋ ወደቀደመ ሰላሟ የንግድ እንቅስቃሴዎቿ ተመልሳለች።

ሰላም የሁላችንም ነው‼️
ከአርበኝነት ይልቅ ባንዳነት እንዲነግስ እየተሰራ፤ ከጠራ አቋም ይልቅ የሌሊት ወፍነት እንደትክክለኛ መስመር፣ እንደእውቀት፣ እንደብልጠት እንዲታይ እየተሰራ ባለበት ሁኔታ ኢትዮጵያ እንደሐገር በቀጣይ ዋጋ መክፈሏ እንደሕዝብ እረፍት ማጣቱ የሚጠበቅ እንጅ ሊከሰት የማይችል አጠራጣሪ ጉዳይ ሊሆን አይችልም።

ስለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት መከበር ስለሕዝብ ጥቅም መረጋገጥ ሲሉ መስዋዕትነት የከፈሉና የሚከፍሉ ዜጎችን መንግስት ነኝ የሚለው አካል ጭምር የሚንቅና የማያደነቅ ከሆነ በቀጣይ ስለሐገራቸው ነፃነትና ስለሕዝባቸው ጥቅም መረጋገጥ ራሳቸውን አሳልፈው ዋጋ ለመክፈል በፈቃዳቸው የሚዘጋጁ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስቸግር ነው።
በሕይወቴ ነፍሴ ከምትጠየፋቸው ሰዎች መካከል ስለአንድ ጉዳይ በቂ መረጃ ሳይኖራቸውና በ one side story ግራ ቀኙን ሳያመዛዝኑ ጠርዘኛ አቋም በመያዝ የእኛ የሚሉትን ሰው የሚመርቁና የሚያመሰግኑ በተቃራኒው ቆመዋል ብለው የሚያስቡትን ሰው ደግሞ የሚራገሙና የሚያጣጥሉ የትግል ጉዟቸው በግብታዊነት በነውረኝነት በጥቅመኝነት በዳፍንታምነት የተሰመረ ሰዎች መወራጨትና ጩኸት ጉልቶ ማየት ነው።

እንዲህ አይነት ሰዎች ለጊዜው እንጣጥ እንጣጥ ሊሉ ይችሉ ይሆናል እንጅ የቆሙበት መሰረት እርባና ቢስ የአንዳንዶቹ የቀደመ ቁመና መሰረቱ ተበልቶ ቀለሙ እንደተቀባ ቤት አይነት ስለሆነ አወዳደቃቸው የከፋ ነጋቸው የተበላሸ ከመሆን ያለፈ ለሌሎች ደጀን መሆን የሚያስችል ቁመና መፍጠር ቀርቶ ራሳቸውን ማዳን የሚያስችል አቅምና መሰረት የላቸውም።

የአማራም ሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደእነዚህ ባሉ በቂ መረጃና መረዳት በሌላቸው ሰዎች የተዛነፈና የተንሸዋረረ አቋም ሲታመስና ሲረበሽ ማየት ሊቀጥል ይችላል።

ለሐገርና ለሕዝብ እዳና ሸክም፣ ለችግር እንጅ ለመፍትሄ ባዕዳን የሆኑ ሰዎች ለኢትዮጵያ ትንሳኤ እንቅፋቶች ስለመሆናቸው ግን ማወቅ ያስፈልጋል‼️
ጎበዝ ወደኋላ አንመለስ ወደፊት እየሮጥን እንጅ፤ ለአመታት ባሉበት መርገጥ ውድድሩን በአሸናፊነት ሪቫን ሊያስቆርጥ ይቅርና ሩጫ ላይ ስለመሆናችንም ማረጋገጫ የሚሰጥ ጉዳይ አይደለም‼️

አንድ ቦታ ላይ ተቸክለን አንቁም፤ እንንቀሳቀስ‼️
ወያኔ ራሱን ካደራጀበት ይልቅ ሌሎች አንድ ሆነው እንዳይደራጁ ስንጥቅ የፈጠረበትና ክፍተቶችን አጉልቶና አስፍቶ እንዲበታተኑ ብቻ ሳይሆን በጠላትነት እንዲፈላለጉ ጭምር ያደረገበት ጥረቱ የማይናቅና የተሳካለት ነው። አማራው ራሱን በራሱ እንዲበላ ኦሮሞውም ራሱን በራሱ እንዲበላ የሚያስችል የተሳሳተ የትግል መስመር እንዲከተሉ ያደረገበት መንገድ ዛሬ ላይ "የመስመሩ የልክነቱ ጥግ" ራሱ ወያኔ መስመሩ ለእኔ እንጅ ለእናንተ አይጠቅምምና ከዚህ ውጡ የሚል ጥሪ ቢያደርግላቸው ብዙዎቹ በዚህ ሐሳብ መልሰው ጠላት ብለው እንዲጠሩት የሚያደርግ አቋም ላይ እንዲደርሱ የሚያስችል ፕሮፖጋንዳ ሰርቶባቸዋል።

አሁን ላይ ራሳቸውን የወያኔ ተቃዋሚ አድርገው የሚያስቡ የአማራና የኦሮሞ ብሔርተኛ እንደሆኑ የሚናገሩ ሰዎች ውስጣዊ ስሪታቸውን ብንፈትሸው የወያኔን አላማና አጀንዳ ለማስፈፀም ወያኔያዊ ብሔርተኝነትን የሚያቀነቅኑ እንጅ ለአማራም ሆነ ለኦሮሞ ሕዝብ ጥቅም መከበር የሚበጅ በጎ ሚና የሚጫወቱ የሕዝብ ተቆርቋሪዎች ሆነው አናገኛቸውም።

ወያኔ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የኦሮሞው ኦሮሞ ነኝ የትግሬም ትግሬ ነኝ ባይነት በቂ ባለመሆኑ ቢዘገይም አማራው አማራ ነኝ እንዲል ሌሎች ብሔሮችም ስጋት እንዲሰማቸው መሬት ላይ የተጠና ጥቃት ከማድረስ ጀምሮ በአየር ላይ የተዋጣለት ፕሮፖጋንዳ ስለተሰራ አሁን ላይ ወያኔያዊ ብሔርተኝነት የአማራንና የኦሮሞን እንዲሁም የሐገሪቱ ሜዳን እንዲቆጣጠር ከፍተኛ እድል እንዲያገኝ አስችሎታል ብዬ አስባለሁ። ወያኔያዊ ብሔርተኝነት ለሁሉም ሕልውና ስጋትና የውድቀት ምንጭ ነው። ወያኔያዊ ብሔርተኝነት ለራሳችንም ሆነ ለሐገራችን የሚበጅ መስመር አይደለምና የትኛውንም አጀንዳ ከሕዝባችንና ከአገራችን ጥቅም ጋር በማዛመድ ስንመረምር እንደወረደ ልናራግብ አይገባም‼️
ወያኔን ብቻ የሚቃወም ወይም የሚያወግዝ ወይም በጠላትነት የሚገልጽ አንድ ነገር ስፅፍ፥ ወያኔ መሩ የፌስቡክ አጫፋሪ ከየጎሬው እየተጠራራ የስድብ ሜኑ ያቀርብልኛል። በስድቡ ከወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ ፌስቡከር ይልቅ ግራ ቀኙን የሚመረምር አሰላስላለሁ ከወያኔ ጋር በመስመር አንድ አይደለንምና እስከመጨረሻው እቃወማለሁ የሚለው ኤሊት የሚያሳየው አቋም ነው የሚያስደንቀኝ። ከወያኔ አጀንዳ ወጣሁ አይመለከተኝም ብሎ ተመልሶ ገብቶ ሲዳክር ይታያል።

ከጥቅምት 24 የሰሜን ዕዝ ጥቃት አስቀድሞ ወያኔ የሌለ እንዲመስል ለማደብዘዝና ለኢትዮጵያ ትልቁ ጠላትና ስጋት አብይ አህመድ ወይም ኦሮሙማ ብቻ እንደሆነ ለማስመሰል በተጠና እና በተቃደ መንገድ የተሳካለት ፕሮፖጋንዳ ሲሰራ ቆይቷል።
የወያኔ አጀንዳ አስፈፃሚ የሆነው "ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ" ተቀዳሚ ጠላቱን አብይ አህመድ አድርጎ ሲስተማቲካሊ ወያኔን እንደ ወዳጅ እንዲቆጠር ሲሰራ ቆይቷል። ይህ ሃይል ወያኔን እንደቀዳሚ የኢትዮጵያ ጠላት በመቁጠር ወይም እንዲቆጠር ስፅፍ ተቃውሞውን ቢያሰማ የስድብ ናዳ ቢያወርድ የስራው ባሕሪይ ነውና አያስደንቅም።

ወያኔ ኢትዮጵያን ካልበተነ እንቅልፍ የማይወስደው ሃይል መሆኑንና ተፈጥሯዊ ስሪቱንና የኢትዮጵያን ፖለቲካ ገብቶኛል እራቀቅበታለሁ ብሎ የሚያስብ አንዳንድ ኤሊት የወያኔን አጀንዳ ሲያሻሽጥ ማየት ግን ግራ የሚያጋባ ይሆናል። በምንም መመዘኛ የወያኔን አጀንዳ የሚያሻሽጥ ሰው ለአማራም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደተቆርቋሪ እንዲታይ የሚያስቆጥረው ሳይሆን ከጠላት እንደአንዱ የመሆኑ ምልክት ማሳያ ነው።

በኢትዮጵያ ምድር ሕዝብን በማደናገር ምሽግ አድርጎ የተደራጀ ለአማራም ሆነ ለኢትዮጵያ ቀዳሚ ጠላትና ስጋት እንዲሁም ኢትዮጵያን ለማተራመስ የሚያስችል እንደ ወያኔ ያለ ረጅም ዝግጅት ያደረገና የውጭ ድጋፍ ያለው የጥፋት ሃይል የለም።

በተለይ የወያኔን ከተንቤን ወጥቶ ለኢትዮጵያ ሕልውና ምን ያህል ስጋት እንደሆነ አለመረዳት የወያኔን ቀዳሚ የኢትዮጵያ ጠላትነት ለማቃለል መሞከር የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ የምንረዳበትን የግንዛቤያችንን ደረጃ ከማሳየት ያለፈ ትርጉም አለው ካልን ጠላትነት ነው የሚሆነው።

ወያኔያዊው የአማራ ብሔርተኝነት ነውረኝነትን ጌጥ ያደረገ፤ በአጀንዳ ቀረፃው የወያኔን ጠላትነት ያላካተተ፣ የወያኔን ጠላትነትና ቀጣይ ስጋትን የሚገልፁ የጠራና የመረረ አቋም ያላቸውን የአማራ ልጆችን፤ የሌሎች ብሔር ተወላጅ ኢትዮጵያኒስቶችን እየተከታተለ እንደ የአብይ /የኦህዴድ ተላላኪ እንድትቆጠር አልሞ የሚሰራ ነው። ምኑን ነው የምላላከው ከሚለው ጀምሮ ብትሆንስ? እንደጠላት የሚያስቆጥር ነገር ነው ወይ የሚለው ጥያቄ እንደተጠበቀ ሆኖ ማለቴ ነው?!

አንዴ የብልፅግና ሌላ ጊዜ የአብይ ተከፋይ ተላላኪ ነው የሚለው ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ( በቪ-8 የሚሽከረከሩ በቪላ ቤት የሚኖሩትን፣ ተከፋይ የሚባሉትን ይከፍላሉ የሚባሉትን አመራሮችን እያወደሰ እንደጀግና እየቆጠረ ነገር ግን የመንግስት ክፍያ እንደነውር የሚያስቡና ስድብ የሚመስላቸው ራሳቸው ተከፋይ የሆኑ ሰዎች አመራሩን ጨምሮ ሲለፈልፍ እንደማየት እንደ አገር የውድቀት ማሳያ የለም)። ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ ሆድ-ነክ ቃላቶችን ይጠቀማል። ተከፍሏል ወይም ሊከፈለው ስለሆነ ነው፤ በላ ወይም ሊበላ ነው፤ ተሸጠ ወይም ሊሸጥ ነው፤ ስንት ቢከፈለው ነው ሕዝቡን የካደው(የትኛውን ሕዝብ ምን አይነት ውል ኖሮት ነው የካደው ብሎ ጠያቂ የለም)፣ ለነገሩ እኮ ለክፍያው ከኦህዴድ ይልቅ ሕወሓት ይሻለዋል((የሁለቱን የክፍያ ዋጋ ከማወቅ አልፎ ማነፃፀር እድሉ እንዴትስ ተቻለ ብሎም ማንም አይጠይቅም)፤ አንተ ምኑ ሆዳም ነው(የሆዳምነት መስፈርቱ የተዘረዘረ ይመስል?)፤..." የመሳሰሉትን ከሆድ ጋር ብቻ የሚገናኙና ስድብና እርግማን ነክ ጉዳዮችን ብቻ በመዝገበ ቃላቱ ያሰፈረ ስለሐገርና የሕዝብ ጥቅም መፍትሄ የማያፈልቅ ደንታ ቢስ ሃይል ነው።

ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ ትልቁ ድፍረቱና ነውረኝነቱ ደግሞ ስለክፍያ፣ ስለገንዘብ፣ ስለመብላትና መጠጣት የሚጨነቅና ያለምንም ክፍያ ለሐገርም ሆነ ለሕዝብ ጥቅም ካለመስራቱ ባሻገር ሌሎችን እንደራሱ አድርጎ ማሰቡና ናቸው ብሎ መደምደሙ ነው። ከዚህ በፊት ምን ጎደለብህ? ምንስ ይሻልሃል? እያለ የወርና የአመት ወጭህን የሚሸፍን የአንተ የግል ሕይወት ውሎና አዳር የሚያሳስበው ሆኖ የሚገባህን ሲያደርግ የቆየና በተሻለ ጥቅም ወይም ገንዘብ ዝውውር ጠላት ከሚለው አካል ጋር አገናኝቶ እንደካድከው አድርጎ ለማሰብ የሚሞክር ቋንቋው ሆድ-ነክ ላይ ብቻ ያጠነጠነ አሳማነትን የሚወክል ነው።

ግራና ቀኙን እያመዛዘንን ነጋችን አገራችንን በሚገነባ የጠራ ሐሳብና አቋም እየተመራን በወያኔያዊው የአማራ ብሔርተኝነት ሳንደናቀፍ ወደፊት እንወነጨፋለን።

ሰው ለአላማው መሳካት ይረዳው ዘንድ ገንዘብ ሊፈልግ ሊከፈለው ሊበደር ሊዘርፍ ወይም ሌላ ሌላም ነገር ሊያደርግ ይችላል እንጅ እንዴት አንድ ሰው ለመብላት ብቻ ለመኖር የማይሆነውን ለመሆን ራሱን ያዘጋጃል። ያኖራልስ?

አንድ ቦታ ላይ ራሳችንን ለማጥፋት ተቸክለናልና ሳይረፍድብን እንንቀሳቀስ‼️
በሕወሓት መሩ የኢህአዴግ ዘመን ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉ የአማራ ልጆች ለውጡን ተከትሎ ለከፈሉት መስዋዕትነት እውቅና ማግኘትና በለውጡ ተጠቃሚ ከመሆን ይልቅ በለውጡ እንዲገፉ አልፎም እንደጠላት እንዲታዩ መደረጉ የአማራ ሕዝብ ጥያቄ ምላሹ እንዲዘገይ አድርጎታል። ወያኔን የታገሉ ሰዎችን የገፋው መድረክ የሌሊት ወፎችን እና በአጥር ላይ ተንጠልጣዮችን አነገሰ። ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ይሉ የነበሩ የሕዝብ ልጆችን ጥያቄና ትግልን ወልቃይትን የት ታውቁታላችሁ አርፋችሁ ተቀመጡ ዝም በሉ ሲሉ የነበሩ፤ ወያኔ ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ ነው ብለው የሚታገሉትን እንደ ጥጋበኛ ይቆጥሩና ይሳለቁባቸው የነበሩ ሰዎች ለውጡን ተከትሎ አይናቸውን በጨው አጥበው "በስመ የውስጥ አርበኛ" ነበርን በሚል ፈራጅ ሆነው እንዲነግሱ ሆነ። በስመ የውስጥ አርበኛ ለውጡን ተከትሎ በአብይ አህመድ በተፈቀደው ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ብዙዎች ከሐሳብም አልፈው አግድም አደግነታቸውን ተሸፍኖ የኖረውን ነውረኝነታቸውን ገልጠውበታል። አሁንም ያገኙትን እድል ለበጎ ከመጠቀም ይልቅ በዛው ገፍተውበታል። ለለውጡ መምጣት ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉ ሰዎች ወደአደባባይ እንዳይጠጉ ይባስ ተብሎ በጓዳ ተደብቀው እንዲውሉ የሚያደርጉ ክብረ-ቢስ ውለታ-ቢስ ለውጡን እረጅም ርቀት የማይወስዱ ስራዎች ሲሰራ ይህ አይበጅም የሚል አካል ጠፋ። ጎርፍ አመጣሾቹ የለውጡ መድረክ አሟቂዎችና ታጋዮች ከለውጡ በፊት ለለውጡ መምጣት የታገሉትን ጀግኖችን ስማቸውን በማጠልሸት ከመድረኩ እንዲርቁ ማድረግ ለእነሱ መጉላትና መንገስ የግድ አስፈላጊ ነበርና መድረኩን በመቆጣጠር ያለስማቸው ስም በመስጠት ወደጓዳ እንዲገቡ ስራ መስራት ነበረባቸውና ያደረጉት የስም ማጥፋት እንቅስቃሴ ከሞላ ጎደል አልተሳካላቸውም ማለት አይቻልም። በዚህ ምክንያትም ለለውጡ መምጣት የታገሉ ሰዎች ሁለት ጊዜ በደልና ግፍ እንዲፈፀምባቸው ተደርጓል።

ሐገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ እንዲሉ አድርጓል።

ከለውጡ በፊት የወያኔ ተላላኪ አልያም ልጆቼን ላሳድግበት ወይም የደሃ ልጅ ነኝ ለቤተሰቦቼ አስፈልጋለሁ ልኑርበት...የመሳሰሉትን የእናቴ ቀሚስ ጠለፈኝ ባዮች መድረኩን ወይም ወንበሩን መቆጣጠራቸው ብቻውን በቂ ስላልሆነ እላፊ በመሄድና በመቅደም ለለውጡ መምጣት የታገሉትን ሰዎች "እንደእናንተ ፎቶ መነሳት፣ በየጋዜጣው፣ በየመፅሔቱ፣ በየፌስቡኩ፣ በእየቴሌቪዥኑ መስኮት እየቀረቡ እዩኝ እዩኝ ያዙኝ ልቀቁኝ ብሎ መታገል እንደትግል የሚቆጠር አይደለም ወደሚል ወመኔ ስህተት እንዲሸጋገሩ አድርጓቸዋል(እዩኝ እዩኝ በአብይ አህመድ ዘመን እንጅ በወያኔ ወቅት እንደማይሰራ ማንም አይስተውም፤ፌስቡክ ላይ ወያኔን የሚቃወም ፅሑፍ ላይክ አድርጋችኋል ብቻ ሳይሆን የአሸባሪ ሰዎች ጓደኛ ሆናችኋል፤ ምንም ግንኙነት ከሌለህ እንዴት ጓደኛ ትሆናላችሁ በሚል ስንቶች ይከሰሱና ይሸማቀቁ እንደነበረ ግልፅ ነበር፤ታሪክ እንደማገላበጥ ያለም አይደለም የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፤ መስካሪ አያሻውም)።

እንደ ደራሽ ጎርፍ ለውጡ ይዟቸው የመጣ ትግል አደናቃፊና ነቃፊ ነውረኞች ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉ የሞራል ልዕልና ያላቸውን ሰዎች ሊሳለቁና ሊያሸማቅቁ የሚያስችል የፍርድ ሰጭ መድረኩን ተቆጣጠረው ለውጡ የራሳቸውን የእንቅፋትነት ሚና ተወጡ። የአማራ ሕዝብ ትግልም ወደኋላ እንዲጎተት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አደረጉ። ለወያኔ መውደቅ ለለውጡ መምጣት የታገሉ ሰዎችን እውቅና አለመስጠት ለውጡን በባለቤትነት አብረው እንዲመሩ አለመስራት በሌላ መንገድ ለታሰሩለት፣ ለተሰውለት፣ ለቆሰሉለት፣ ለተሰደዱበት ለሕዝብ ጥያቄ ቦታ እንዳለመስጠት ሊያስቆጥርና የለውጡን መንገድና ጉዞ ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ በር የከፈተ ስራ ጭምርም ነበር ብሎ መውሰድ ይቻላል።

ወያኔ መሩ ኢህአዴግን ሕይወታቸውን አሲዘው የታገሉ ሰዎች ብአዴንን የሚመለከቱበት የቀደመ አመለካከት ባለበት መቀጠሉ እና ራሱ ብአዴንም በእነሱ አገላለፅ እነሱን የሚመለከትበት እይታ እንዲንሸዋረር ከማድረጉ ባሻገር እንደጠላት ወደመቁጠር በብአዴን ውስጥ እንደኦህዴድ አዳዲስ ፊቶች አለመታየታቸውና የለውጡ ብቸኛ ባለቤት ብአዴን ራሱ ብቻ ወደማድረግ መሻገሩን የሚያሳይ እንቅስቃሴ ማድረጉና ሕዝቡን ለመያዝ የሄደበት መንገድ የአማራ ፖለቲካ ውጥንቅጡ እንዲወጣና ለውጡ በአማራ ክልል ነውጥ ሆኖ እንዲቀጥል እንደምክንያት ሊጠቀስ የሚችል ነው።

ለለውጡ መምጣት ወያኔን ለመጣል የታገሉ ሰዎች እውቅና እና ተገቢ የሆነውን ክብር አለማግኘታቸው ሳያንስ ለውጡ በለውጡ በማያምኑ በርካታ ቁሞ-ቀር አፍቃሬ ወያኔ አመራሮችና እነሱ ባሰማሩት አክቲቪስቶች የአማራ ፖለቲካ መዘወሩ እስከዛሬ ድረስ አማራ እንደሕዝብ አላስፈላጊ መስዋዕትነት እየከፈለ እንዲቀጥል የቀዳሚ ተጠያቂነት ቦታን እንዲወስድ የሚያደርገው ነው።

በአማራ ፖለቲካ ከለውጡ በፊትና ለውጡን ተከትሎ የሆነውን ሁኔታ ለማንሳት የፈለኩት ነገ ለሐገር ሉዓላዊነትና ነፃነት ለሕዝብ ጥቅም የሚታገሉ ሰዎችን ማፍራት የሚቻለው ትናንት ለሐገርና ለሕዝብ የታገሉና መስዋዕትነት የከፈሉ ሰዎችን የሚገባቸውን ክብር መስጠት ስንችል በመሆኑ ነው። ትናንት ለሐገርና ለሕዝብ ሕልውናና ጥቅም የታገሉና መስዋዕትነት የከፈሉ ሰዎች ዛሬ ላይ የማንም መሳለቂያና መጫወቻ እንዲሆኑ የሚረሱና የሚረክሱ ከሆነ ተተኪዎችን ለማፍራት ወደሚያስቸግር ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል።

በጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ሰሜን ዕዝ ላይ ወያኔ ጥቅም 24 ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ በነበረው ጦርነት በርካታ ወገኖቻችን ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለዋል። ለአኩሪ ተጋድሏቸው እውቅና እና ሽልማት የሚገባቸውን ክብር ሁሉም ተፅዕኖ የፈጠሩ ጀግኖች አግኝተዋል የሚለው ጉዳይ ግን አሁንም ጥያቄ ሆኖ የቀጠለ ነው።

እንዲሁም በባለፈው ወያኔ" ከአማራ ጋር ሂሳብ አወራርዳለሁ፤ ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ" ብሎ በአዋጅ ጦርነት ሲከፍት እኛ እያለን አማራ ላይ ሂሳብ አይወራረድም ኢትዮጵያም አትፈርስም! ብለው ወያኔንና የግብር ልጆቹን በሁሉም ግንባር (በሚዳያ በአካል በዲፕሎማሲ በገንዘባቸውና በሞራል ድጋፍ ) የተፋለሙ በትግላቸው ተፅዕኖ የፈጠሩና ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖችን የሚገባቸውን ክብር እውቅና እና ሽልማት እንደአስተዋጽኦቸው አለመስጠት በራሱ ወያኔነት ነው። የአገር መፍረስን መደገፍና መተባበርም ነው። ስለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት ስለሐገር ክብር ስለሕቦቿ ዘላቂ ጥቅም መታገል እንደዋጋ ቢስ እንደከንቱ የሚያስቆጥር አርበኝነትን አራክሶ ባንዳነትን የሚያነግስ አካሄድ ነው። የሐገር ሻጭነት መንገድ ነው። ሐገራዊ ስሜትንም የሚጎዳና የሚያኮስስ ነው።
የወንዶቹ ቁና የብራው መብረቅ አርበኛ አጋዬ አድማሴ የሚገባህን ክብር አግኝተሃልና እጅጉን ደስተኛ ነኝ።

ወታደራዊ ዲስፕሊን የተኩስ ብቃት የአይበገሬነት ፅናቱ አስደናቂ ነው።
ምሽግ ላይ ከከረሙትና በዱር በገደሉ ስለእናት ኢትዮጵያ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከከፈሉት ጀግኖቻችን ቀዳሚው ነው።

ውጊያን በፌስቡክ ሳይሆን በግንባር ጦርነትን እንደ ሰርግ በደስታ የመራ የእናት ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው።

ክብር ለሚገባው ክብር መስጠት ስለክብር ግድ የሚለው ተተኪ ትውልድ ማፍራትና ነጋችንንም መስራት ነው‼️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የብራው መብረቅ አርበኛ አጋዬ በደብረዘቢጥ በወሎ ግንባር ከጠላት ጋር ሲፋለም!

ይህን ውጊያ የቀረፀው በዛው ግንባር ሲፋለም በክብር የተሰዋው ፋኖ ሕርያቆስ ነው የሚል ሰምቻለሁ!

በጀግኖቻችን ደም ሕልውናችንን አስቀጥለን ነፃነታችንን አረጋግጠናል።

ክብርና ምስጋና በአማራ ላይ ሒሳብ አይወራረድም እናት ኢትዮጵያ አትፈርስም ብለው ወድ ሕይወታቸውን ለሰጡ ጀግኖቻችን ይሁን‼️
ተሰውቶ የ1ኛ ደረጃ የወርቅ ተሸላሚው የጎብዬው ጀግና

ከድሬሮቃ እስከ አላውሀ የወያኔን መንጋ የተፈለመው እና
እኔ በህይዎት እያለሁ ወራሪው ቡድን ርስቴን ረግጦ አይሄድም ብሎ በክብር የተሰዋው የጎብየው ጀግና የወርቅ
ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል! ተሰውቶም በጀግንነቱ የተሸለመው ወሎ ምድር ጎብየ የበቀለው የሀገር ኩራት ነው። በህይዎት ካለ ሙታን የተሰዋ ጀግና ይበልጣል ይባል የለ? የሙሀመድ ቢሆነኝ ጀግንነትም ሙቶ እንኳን እየተዘከረ ነው።

ጀግኖቻችን ከዚህም በላይ ይገባቸዋል !!

አህሙ ፍቅር
ግንቦት 03/09/2014
የጎጃሙ ፋኖ መሪ መቶ አለቃ አሰፋ አድማሱ በግንባር ለፈፀምከው ጀብድ የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ በመሆንህ እጅግ ኮርተናል። ከምትመራቸው ፋኖዎች ጋር እንኳን ደስ አለህ ለማለት እወዳለሁ‼️
በወሎ በደብረዘቢጥ በወሎ ግንባር በማይጠምሪ በጭና በጨው በር በማይጠብሪ ተከዜ ግንባር ጦር እየመራ ታላቅ ጀግንነት የፈፀመው ጀግናው ኮማንዶ ሀብቴ ወልዴ በጀግናው ጀኔራል አበባው ታደሰ እጅ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልሟል።

ሻለቃ ሀብቴ በደብረዘቢጥ በነበረው ውጊያ የጀግናው ቻላቸው እንየውን መሰዋት ተከትሎ ጦሩ የመፈታት ሁኔታ ውስጥ ሲገባ እስከመጨረሻው ያሳየው የመፋለም የጀግንነት ጥግ መቼም ሊረሳ የማይችልና ፍፁም ልበ ሙሉነቱን ያስመሰከረበት ነበር።

አርበኛ ሀብቴ ወልዴ ፍፁም ወታደራዊ ዲስፕሊን ያለው በጦርነቱ ወቅት በምሽግ በዱር በገደሉ በከፍተኛ ተጋድሎ ያሳለፈና የተሰጠውን ግዳጅ በጀግንነት የተወጣ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው።

ለአንተና በስርህ ሆነው አማራ ሂሳብ አይወራረድበትም ኢትዮጵያም አትፈርስም ብለው ከፍተኛ መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖቻችን መቼም የማይቀየር ክብርና ምስጋና አለን‼️