Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.44K subscribers
2.98K photos
371 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
ጀኔራል ሰን ዙ የው ግዛትን 33 ሺ ጦር ይዞ ግዙፉን የቹ ግዛት የኗኗን በመቶ ሺ የሚቆጠርን ጦር ያሸነፈው እንደወያኔ የውሸት መረጃ በመርጬት በቹ ግዛቶች ገብቶ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ጥቃት በመክፈት በኗኗ ላይ እንኳን ሕዝቡ ጦሩ ራሱ እምነት እንዳይኖረውና ከኗኗ እየወጣ ለሰን ዙ ጦር እጅ እንዲሰጥ ገሚሱ ደግሞ ከጦሩ እየሾለከ እንዲጠፋና ጦሩ እንዲበተን ማድረግ ስለተቻለ ነበር።
ወያኔ አሁን እያደረገ ያለው የኢትዮጵያን ጦር በተለይ የአማራ ልዩሃይልን በወያኔ ናፋቂ በተተፉ አቅመ ቢሶች በኩል የጋራ ኮዝ እንዳይኖረው በማድረግ ልዩሃይሉን የዳቦ ስም በመስጠት ለመበተን ሲደከም ተከርሟል። ሕዝቡን ደግሞ በተለያየ መንገድ እንዲማረርና አልፎም በመንግሥት ላይ በአመፅ እንዲነሳ ለማድረግ ያልተቋረጠ ስራ እየተሰራ ነው። አንዴ የተመረጡ አካባቢዎች ላይ ጭፍጨፋ በመፈፀም ሌላ ጊዜ ደግሞ በሐይማኖት ስም እየተደረገ ያለው ስራ ለወያኔ መንገድ ጠረጋ ነው። ይህን አጀንዳ ወያኔን እንደጠላት የሚቆጥሩት ወይም እንታገለዋለን የሚሉ አካላት ሳይቀር አጀንዳውን ተቀብለው የማሻሻጥ ስራውን እያቀላጠፉትለም ነው። ዲስፕሊንድ ያልሆነ ኮዝ የሌለው በጠንካራ የወታደራዊ ስነ-ስርዓት የማይመራ ሰራዊት በየትኛውም ሁኔታ የሚሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት በበከፍተኛ ሞራል ተሞልቶ እስከመጨረሻው በፅናት ቆሞ ሊታገል አይችልም።

በናፒር በሚመራው የእንግሊዝ ጦር በአፄ ቴዎድሮስ ላይ ብልጫ የወሰደው በወታደራዊ ስርዓት የተሻለ ስለነበረ ነው። የናፒር ጦር ስለ አፄ ቴዎድሮስና ስለ ሕዝቡ ሁኔታም ከበቂ በላይ መረጃ ስለነበረው በክፍተቱ መጫወት ስለቻለም ነበር።

ጀኔራል ሰን ዙ ጥቂት ጦር እየመራ የኗኗን ግዙፍ ጦርን በራሱ በቹ ግዛት ጠልቆ ገብቶ ማሸነፍ የቻለው በበቂ መረጃ ተመርኩዞ በተዛባ በውሸት መረጃ በማጭበርበር ጦሩን አሳስቶ በሕዝቡ ቅሬታና ጥያቄ በኩል አልፎ ጦርነቱን መምራት ስለቻለ ነበር። የሰን ዙ ጦር ተቆራርጦ በቹ ግዛት የሽምቂ ውጊያ ማድረግ የቻለው የቹ ሕዝብ በኗኗ እና በጦሩ ላይ የተማረረ ስለነበረ ለሰን ዙ ምሽግ ሆኖ ስላገለገለው ነበር።

በናፔር የሚመራው የእንግሊዝ ጦር ስለ አፄ ቴዎድሮስ ጦርና ስለሚመራው ሕዝብ በቂ መረጃ ነበረው እንጅ የአፄ ቴዎድሮስ ጦር በናፔር ስለሚመራው የእንግሊዝ ጦር በቂ መረጃ ነበረው ለማለት የሚያስደፍር ነው ለማለት አያስደፍርም።
አፄ ቴዎድሮስ ስለኢትዮጵያ በክብር የወደቀው ቀድሞ በራሱ ኤሊትና ሕዝብ ስለተካደ ነበር። ሕዝቡንና ኤሊቱን ከአፄ ቴዎድሮስ ይልቅ የናፔር ጦር ተጠቅሞበታል።

ሰን ዙ እንዳለው "አሸናፊው ጦረኛ ወደጦርነት የሚሄደው ጦርነቱን አሸንፎ ነው። ተሸናፊው ደግሞ ድልን በጦርነት መሃል ይፈልጋል" ይላል።

ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው የአፄ ሚኒሊክ የአድዋ ዘመቻ ነው። አፄ ሚኒሊክ በክተት አዋጃቸው ገና ሳይነሱ ጦርነቱን አሸንፈው ስለመጀመራቸው ማረጋገጫው ".ወስልተህ የቀረህ ግን ትጣላኛለህ አልተውህም። ማርያምን አማላጅ የለኝም" የሚለው አቋማቸው ስለ ድህረ-ጦርነት ሁኔታ ምን ያህል እርግጠኛ እንደነበሩ የሚያመላክት ነበር።

አፄ ሚኒሊክ ስለጣሊያንን ጦር ከበቂ በላይ መረጃ እንደነበራቸውና ይህን የጠላት ሃይል ለመመከትና ጦርነቱን በድል ለመወጣት የሚያስችል ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርጉ ስለመቆየታቸውም በክተት አዋጃቸው ላይ "...በፊት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባህር አልፎ(የኢትዮጵያ ደንበር እስከየት እንደሆነ የሚናገርም ነው) መጥቷል፡፡ እኔም የአገሬን ከብት ማለቅ፤ የሰውን መድከም አይቼ እስካሁን
ዝም ብለው( የጠላትን እንቅስቃሴ በተመለከተ ያውቁና ለጠላት የሚመጥን የሰው ሃይልና የትጥቅ ዝግጅት ሲያደርጉ ስለመቆየታቸው የሚያሳይ ነው) ደግሞ እያለፈ እንደፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር.." የሚለው አቋም ያረጋግጥልናል። በነገራችን ላይ በኢትዮጵያ ታሪክ በእኔ መረዳት ለውጊያ ጦርነቱ ከሚወስደው ጊዜ ይልቅ ለጦርነቱ የሚደረገው ዝግጅት ከፍተኛውን ጊዜ የሚወስድ ነው። ጦርነትን ለማሸነፍ በሰላም ጊዜ ለጦርነት መዘጋጀት የሚለው በተግባር ሲተረጎም ከዚህ የተለየም አይደለም‼️

ወያኔ አሁን እያደረገ የሚገኘው መንግስት በሚያስተዳድረው ክልል በሐይማኖት ስም ወይም ጥቃት እንዲፈፀም በማድረግ ጦርነቱን ራሱ ሕዝቡ እንዲመራለት ማድረግ ነው‼️

ለወያኔ አገር ለማፍረስ እየተሰጠ የሚገኘው እድል በጊዜ እልባት የማይሰጠው ከሆነ ማንም ወደማያተርፍበት አዘቅት ሁሉም ተያይዞ መግባቱ አይቀርም‼️
የመንግስት ዋናውና ተቀዳሚ ስራው የዜጎችን ሰላምና ደህንነት መጠበቅ ነው። በአለም ላይ ሕግና ሥርዓት ይከበር ዘንድ መንግስትን በመጠየቅ የኢትዮጵያ ሕዝብ የመጀመሪያው ይመስለኛል።

ሕግና ስርዓትን ለማስከበር የሚያስፈልገው ምንድን ነው? እየተሰራ ያለው የዲሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት ወይስ የእርስ በርስ ግጭቱን ለማስፋፋት ነው?

ከዚህ በፊት በአሜሪካም ሆነ በአውሮፓ ሆነው አገር ለማፍረስ የጥላቻና የዛቻ አመፅ ቀስቃሽ ጥሪዎችን ሲያደርጉ ለነበሩ ሰዎች ዶ/ር አብይ አህመድ ፓርላማ ላይ "እናንተን ልቆጣጥራችሁ አልችልም፤እግዜር ይይላችሁ/ይፍረዳችሁ ሲል ብዙዎች ሐሳቡን ቢገዙት የሚመስል ስለሆነ የወግ ነው። እሱ እመራዋለሁ በሚለው አገር ውስጥ ሆነው አገር ለማፍረስ ሕዝብ ለማጫረስ የሚሰሩ ሰዎችን በተመለከተ የዝምታ ምንጩ ግን ሊገባኝ አልቻለም ምንድን ቢሆን ነው?!

ሰዎች ከፍተኛ የሆነ ግልፅ የሆነ የለየለት የጥላቻ አመፅ ቀስቃሽ ንግግር የእልቂት ጥሪዎችን በየአደባባዩ እያሰሙ በዝምታ ማለፍ ለዲሞክራሲ ምህዳሩ መስፋት ተብሎ ወይስ በግጭቱ መንግስትም እንደሕወሓት ትርፍ አገኝበታለሁ ብሎ አስቦ ነው? ዲሞክራሲ ሲተረጎምስ እንዲህ ያለ ነውን? ትርጉሙ ይህ ከሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አያስፈልገውም። አይፈልገውምም!

መንግስት እንደምድራዊ መንግስት ሆኖ ሕግና ስርዓት ለማስከበር ሊሰራ እንጅ ዘወትር ስብከት ሊያወራ እንዲህ ሆኖ አገር አይችልም። የስብከት ባሕሪውን ማቆም አለበት። ስብከቱን ከመንግሥት በላይ በውብ ቃላት የሚያሽሞነሙኑ በየሐይማኖቱ የተዋጣላቸውና የወጣላቸው እልፍ ሰባኪዎች ተትረፍርፈዋል።

ከጫፍ እስከ ጫፍ ሕዝቡ "ኧረ የመንግስት ያለህ!" እያለ ያለው ሕግ እንዲከበርለት ነው። የግጭት ጡረተኞች እንኳን ኧረ የመንግስት ያለህ ብለው ተጨማሪ ትርፍ እንዲያጋብሱ እድል ማግኘት ችለዋል።
መንግስት የሌለ በማስመሰል ስርዓት አልበኝነት እንዲፏፏም ሕዝቡ ሌሎች አማራጮችን ተስፋ አድርጎ እንዲከተል ቢመከርና ቢወተወት አያስገርምም።በእነሱ እንዴትስ መፍረድ ይቻላል?!
የምሬን ነው!

ወያኔ ላይ Specialized ያደረግነው በኢትዮጵያ ምድር ጥቂት ሰዎች ነን። ወያኔን ጠንቅቆ ሊረዳ የማይችል ሰው ደግሞ ፈፅሞ የኢትዮጵያንና የቀጠናውን ፖለቲካ የመተንተን አቅም የለውም። የወያኔ ተቃዋሚ ነኝ የሚለው ራሱ የወያኔ አጀንዳ አሻሻጭ ለሚጭረው እሳት ለማቀጣጠያነት የተዘጋጀ ጭራሮ መሆኑን ከአንዴም ሁለት ሶስቴ በተግባር ያስመሰከረ ነው።በአዛባዎችና በዳፍንታሞች መከበባችን ግን ምቾት እየሰጠኝ አይደለም።

የፌስቡክን ማህበረሰብ በሌሎች ፔጆችና ፌክ አካውንቶች አጀንዳ ያልፈጠርኩለት አንተ ብቻ ፃፍ! ተናገር! አንተ የእውነት ሰው! የሕዝብ ልጅ ያላለኝ ፌስቡክ ተጠቃሚና ፖለቲከኛ አላውቅም። እንዳለ የፌስቡክ ማህበረሰብ እኮ ከዳሚ ነው!

በዚህ ሊሰድበኝ ወይም ሊያሽሟጥጠኝ የሚሞክረኝ ማንነቴን ስለሚያውቅ እንጅ በብዕር አካውንቴና በፔጆቼ አድናቂዬ የሆነ ነው።
መምህር ዘመድኩን በቀለ በአንድ ሚዲያ ላይ ቀርቦ ቶማስ ጀጃው ሕዝብ እያደነዘዘ እንደሆነ ገልጿል። በጣም አስገራሚና አስተዛዛቢ ጉዳይ ነው!

ሕዝብ የሚያረጋጋ ነጋችንን ከግምት ያስገባ፤ ወንድማማችነትን የሚያጠነክር፤ ከስሜት ይልቅ የስሌት ጉዞን እንከተል፤ ግፍ የትም ይፈፀም የት ሊወገዝ፥ ግፈኛው ማንም ይሁን ማን ለፍርድ ሊቀርብ ይገባል፤ጭንቅላታችንን ለማንም መጠቀሚያ አሳልፈን ልናከራይ አይገባም፤ የሕግ የበላይነት ይስፈን፤ የወያኔን አጀንዳ ማራገብ ሴራውን አለመረዳትና መንገዱንም መከተል በውጤቱ ከግጭት ጡረተኞች በስተቀር አትራፊ አይኖርም ማለቴ ሕዝብን ወደቀና ጎዳና ሊመልስ ይችላል እንጅ እንዴት ሊያደነዝዘው ይችላል?! ይህን በማለቴ የሚደነዘዝ ሕዝብም ካለ ከመጀመሪያውም ስለመንቃቱ እጠራጠራለሁ። ምን እንዲፈጠር ወይም እንዲሆን ስለተፈለገ ነበር?

ለዘመናት በአንድነት አብሮ የኖረን ሕዝብ አንድነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም ለሰላሙ ዘብ እንዲቆም መስራት ሕዝብን ከማደንዘዝ ጋር የሚገናኝ ወይም የአብይ አህመድ ተላላኪ የሚያስብል አይደለም። መቼምም ሊሆን አይችልም። እንዲያውም ይህን ለማድረግ ከፊት መቅደም የነበረባቸው በክርስትናም ሆነ በእስልምና በኩል ያሉ እንደ እነ መምህር ዘመድኩን በቀለና መሰሎቻችሁ ያሉ ሰዎች ነበሩ።

በጠላት ሴራ የተፈጠረው ችግር ወደተጨማሪ አላስፈላጊ ዋጋ እንዳያስከፍለን ሰላም እንዲሰፍን ወንድማማችነታችንን እንድናጠናክር መወትወታችን በዚህ ደረጃ የሐይማኖት መምህራንን የሚያስቆጣ ከሆነ የመጨረሻው ዘመን የመድረስ ምልክት ስለሆነ "ጌታ ሆይ የት ደረስክ?!" ከማለት ውጭ ሌላ ምን ልንል እንችላለን?
አዲስ አበባ ላይ ድንጋይ ከየት ተገኝቶ ነው ግን?😂
(እንደ ባህር ማሽላ እያረርን እንሳቅ እንጅ)

መደማመጡ መከባበሩ መስከኑ ነው ለሁላችንም የሚበጀን ሌላው ማንም የማያተርፍበት የጥፋት የውድቀት መንገድ ነው!

ለሁላችንም ሰላም ያስፈልገናል። ሰላምን ሰለፈለግን ብቻ ግን ያለሁላችንም ጥረት ሊረጋገጥ አይችልም። ሁሉም ለሰላሙ ዘብ ሊቆም ይገባል‼️

በነገራችን ላይ ችግሩን ለማረጋጋት መሃል ላይ የገቡ "ኧረ አላህን ፍሩ" የሚሉ ቅን ወንድሞች አሉ።
ከትህነግ በላይ የአማራ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት የለም። አለ ከተባለም አፍቃሬ ትህነግ መሆኑ የተረጋገጠ ነው‼️
የመጨረሻ መልዕክት‼️



(ይህን መልችዕክት እንድታጋሩት እጠይቃለሁ)
በጌታቸው ሽፈራው

አሳርፉልን!

ታሪካዊቷ ጎንደር ያለ ስሟ ስም ተሰጥቷታል። ችግሮች ያልተፈጠሩበት አካባቢ የለም። ችግር ፈጣሪዎቹ እንጅ አካባቢና ሕዝብ ሲወገዝ አይኖርም። ሆን ብሎ በተቀነባበረ ሴራ የደረሰን ችግር ለጎንደርና ለአማራ ሕዝብ ስም ማጥፊያ፣ ለአማራ ሙስሊምና ክርስትያን መካከል ያለውን ግንኙነት ለመበጠስ፣ በሌሎች አካባቢዎች ግጭት ለመቀስቀሽ ከአሸባሪው ትህነግ ጋር ሆነው የሚሰሩት ፅንፈኞች ተግባራቸው ቀጥሏል።

በይፋ በሚዲያ፣ በአደባባይ የከተማና የክልል ስም እየተጠራ፣ የአማራ ሕዝብ ያለ ስሙ ስም እየተሰጠው፣ እንደ ቱርክ ያሉ አገራት መግለጫ እስኪሰጡብን ድረስ የሀሰት ፕሮፖጋንዳው ቀጥሏል።

መንግስት ይህን በአማራ ሕዝብ ላይ የተከፈተ፣ ለውጭና ለአገር ውስጥ ጠላቶቻችን አጋልጦ የሚሰጠንን የፕሮፖጋንዳ ጥቃት በአስቸዃይ ያስቁም!

የእምነት አባቶች የጎንደሩን ክስተት ተከትሎ በፅንፈኞች በኩል የሚደረጉ የሀሰትና ከጠላት ውጭ ለማንም የማይጠቅሙ የሀሰት ዘመቻዎችንና የፕሮፖጋንዳ ጥቃቶችን ያስቁሙ!

ይህ የማይሆን ከሆነ ችግር እንዳይባባስ ብለን ያስቀመጥናቸውን በእጃችን ላይ ያሉትን መረጃዎች ለመልቀቅ እንደምንገደድ መግለፅ እንወዳለን።

የጎንደር ሙስሊሞች በዓል እንዳያከብሩና ጎንደርንና አማራን ለማጥቃት ዕቅድ የያዙ ፅንፈኞች አሁንም የጎንደርንና የአማራውን ስም ያለ አግባብ እያጠለሹ እየቀጠሉ ነው። ይህ በአስቸኳይ ካልቆመ ለችግሩ መነሻና መባባስ የዳረጉት እነማን እንደሆኑ የሚያሳዩ መረጃዎቻችን ለሕዝብ የምናደርስ ይሆናል።
'የጨው ገደል ሲናድ ሞኛ ሞኝ ይልሳል፤
ብልህ ግን ለማዳን ይጥራል ያለቅሳል!'
የሚሉት አበው እንዲሁ አይደለም!
ዛሬን በነፃነት አንገታችንን ቀና አድርገን እንሄድ ዘንድ ትናንት በዱር በገደሉ ስለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት የደም መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖቻችንን በታላቅ አክብሮት እንዘክራለን። ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን። የትናንት የሐገር አድባርና አምባዎቻችንን የቁርጥ ቀን ጀግኖቻችን በመዘከር የሚገባቸውን ክብር ሰጥተን ነጋችንን ለመስራት ዛሬም ትውልድ እንቀርፃለን‼️

ማህፀነ ለምለሟ ኢትዮጵያ ዛሬም እንደትናንቱ በጀግኖች ልጆቿ የተባበረ ክንድ ነፃነቷን ጠብቃ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች‼️
ሚኒስትር፣ የሆነ ዳይሬክተር ወይም የቢሮ ኋላፊ ሆነው በቪ-8 የሚሄዱ በቪላ ቤት የሚኖሩ፣ ሐገር ምድሩን የተቆጣጠሩ (ምንም እንኳን በቀጣይ በወንጀላቸው የተጠያቂነት ስጋት ወይም በአቅም ማነስ ከስልጣናቸው የመነሳት እንዲሁም የመቀጣት እድል ያላቸው ቢሆኑም) አብዮታዊ ዲሞክራሲ ወይም ሞት! የሚሉ ከወያኔ ሰዎች ጋር በማንነት ካልሆነ በግብር የባሰባቸው ብልፅግናን ዘወትር የሚያብጠለጥሉ አብይ አህመድን ደግሞ ከመለስ ዜናዊ ጋር እያነፃፀሩ ጭራሽ ጥንብ እርኩሱን የሚያወጡ ሰዎች እንደ ጀግና እንደተቆርቋሪ በሚታዩበት መድረክ ላይ ስማችን እየተወደሰ ስንከበር ለማየት ማሰቡ ነው ትልቁ ሞኝነት።

ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት መከበር ለህሊና እረፍት ለቀጣዩ ትውልድ ነፃነትና ለታሪክ መታገል በራስ ወዳዶቹ የባንዳዎች መድረክ ላይ እንደትርጉም አልባና ተቀባይነት እንደሌለው ትግል የሚያስቆጥር ከአልፎም ራስን እንደማጥፋት የሚያስቆጥርም ነው‼️

ማንም ምንም ቢል ግን ስለኢትዮጵያ የሚከፈል መስዋዕትነት ነገ ላይ ዋጋ የሚያሳጣ ጉዳይ አለመሆኑን ማወቅና ማመን ያስፈልጋል‼️
ፓርቲ ስቴትና ገቨርመንትን አቀላቅሎ አገር ሊያፈርስ በሚችል እንቅስቃሴ ላይ የተሰማራ ሚኒስትር፣ የሆነ ዳይሬክተር ወይም የቢሮ ኋላፊ፣ በቪ-8 የሚሄዱ በቪላ ቤት የሚኖሩ በመንግሥታዊ መዋቅሩ ውስጥ ያሉ ሰዎች፣ መንግስት በሚያስተዳድረው ምድር እንደፈለጉ በሚፈነጩበት የተከበሩ እየተባሉ በሚጠሩበትና እንዲከበሩ በሚሰራበት እንዲሁም በሚመቻችበት አገርና ሁኔታ ውስጥ እየኖርን የእኛ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት ለሕዝቡ ዘላቂ ሰላምና ጥቅም መከበር እየታገልን ነውና አገር አፍራሾችን ሳይሆን እኛን ስሙ እንደማለት ያለ እንደሞኝነት እንደጠላት እንደ አብይ ተላላኪነትም ሊያስቆጥርና ሊያስከስስ የሚችል ጉዳይስ ከወዴት አለ? የለም።

ለኢትዮጵያ ከእኛ በላይ የቀረቡና የሚቆረቆሩ የሚመስሉት እነሱ እንጅ እኛ አይደለንም። መታወቅ ያለበት ጉዳይ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንቅስቃሴ ውስጥ ከገቡት አካላት በላይ እኛ በኢትዮጵያ መኖር በመንፈስ ካልሆነ በስተቀር እንደግለሰብ የተጠቀምነው ነገር የለም። ኢትዮጵያ ለእኛ እናታችን ናት። ጡቷን እነማን እየጠቡት ነው? ሐብትና ንብረቷን እነማንስ እየተጠቀሙበት ነው የሚለው ጥያቄ ምላሽ የእኛን የኢትዮጵያን እናትነት መቼም የሚቀይረው አይሆንም።

የእኛ ትግል ለራሳችን ነው። ለሕሊናችን ነው። የትውልድ ታሪካዊ አደራን የመወጣት በመጭው ትውልድ ስለሚታየው መልካም ፍሬ ነው። የዚህ ታሪካዊ ትውልድ አባል እንደሆነ እንደ አንድ ግለሰብ ኢትዮጵያ ከእኔ ምን ትፈልጋለች? ምን አደረግንላት ብለን እንጅ ኢትዮጵያ ለእኛ እስካሁን ምን አደረገችልን ወይም ታደርግልናለች? በሚል የሂሳብ ቀመር የቆመ የትግል መንገድ አይደለም የምንከተለው። በኢትዮጵያ መፍረስና መኖር ስለሚገኘው የተሻለው የግል ጥቅም መከበርያ የሂሳብ ስሌት በእኛ ዘንድ ፈፅሞ ቦታ የለውም። መቼምም የማይሰራ ነው።

ከግል ጥቅም አንፃር ነገሮችን የምንመነዝር የሂሳብ ቀመር ሰርተን መታገልን ብንመርጥ የትግላችን መሰረቱ የአመፅ ጥሪ ይሆን ነበር። በኢትዮጵያ ምድር በዚህ ሰዓት አመፅ ጠሪ እንደመሆን የጥሪውን ጥሩንባ ነጋ ጠባ እንደመንፋት የጀግንነት ካባ የሚያላብስ ምን ይሻልህ የሚያስብል የእኔ ጀግና አልፎም የእኔ ጌታ የሚያሰኝ የትግል መስመር እንደሌለ ጠንቅቀን እናውቀዋለን። ነገር ግን መስመሩ ለማንም ዘላቂ ጥቅም የሚሰጥ አይደለም። አገርን በማፍረስ ተያይዞ በመጥፋት የአመፃ ጥሪ መሬት በነካ ተሳትፎ የሚገኝ የግል ጥቅምና ዝና የጀግንነት ካባ ስለማንፈልግ እንጅ ከባድ ነገር ሆኖ አይደለም። መስመሩ ምንም አይነት መስፈርት የማይጠይቅና ለማንም ሰው የማይቻል አይደለምና‼️
የኢትዮጵያ የምንጊዜም አለኝታ የዘወትር ዘብ ለሆነው ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ክብር ምስጋና ይገባዋል‼️

ኢትዮጵያ ዛሬም እንደትናንቱ በቃላት ሊገለፅ በማይችለው መስዋዕትነታችሁ ነፃነቷን ጠብቃ ወደቀጣዩ ትውልድ ትሻገራለች። ታፍራና ተከብራም ትኖራለች።
የኢትዮጵያን ፖለቲካ በብሔር መነፅር ትግራይነት አማራነት ኦሮሞነት...በክፍለ ሐገር ደረጃ አዲስ አበባ ድሬዳዋ ላይ ተቀምጠህ ከውጭ እንደ ዲያስፖራ በሀይማኖት እንደ እስላም ክርስቲያን ሆነህ እንደ አንድ ኢትዮጵያኒስት ነገሮችን ከቀጠናውና ከአለማቀፉ ሁኔታ ተነስተህ ብትተነትነው እስከ ጌታ መምጫ ድረስ ሊታረቅ የሚችል ነገር ስለመኖሩ ሊታይህ አይችልም። በየቀኑ የምታስበው ሁሉም በአንተ ላይ በጠላትነት እንደተነሳብህና ልትጠፋ እንደሆነ ነው። ላለመጥፋት መደራጀት እንዳለብህ ብትችል ደግሞ ጠላት ያልከው ላይ ቀድመህ መብረቃዊ እርምጃ በተሎ መውሰድ እንዳለብህ ከጦርነት አዋጅ ውጭ ሌትም ቀንም የምትሰማው ሌላ Alert ⚠️ የለም። ራሱ በሚፈጥረው ጠላት ቀድሞ ስለመጥፋት እየተብሰከሰከ ጊዜውን ይበላል!

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ትልቁ ችግርና ቀጣይ ስጋት ዛሬም እደግመዋለሁ One Side Story ነው‼️
የእናት ኢትዮጵያ አለኝታዎች‼️

ከዓመት እስከ ዓመት ስለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት መከበር ስለሕዝቧ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ያለእረፍት መስዋዕትነት ለሚከፍለውና በግብር ላስመሰከረው የሰላማችን ዘብ ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ክብር ምስጋና ይድረሰው‼️

መልካም ቅዳሜ‼️
የሱዳን የፀጥታ ሃይሎች ከወያኔ ጋር በመቀናጀት እስከዛሬ ያደርጉት ከነበረው በላይ በስደተኛ ካምፕ እና በሱዳን የተለያዩ ከተሞች ይኖሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን እያፈሱ በሑመራ በረከት የቅርብ ርቀት ወደሚገኝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፖች ጭምር እያስገቡ ማሰልጠን ጀምረዋል። በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች በግብፅ እርዳታ በሱዳን ጦር መሪነት ኢትዮጵያን ለመውጋት በሱዳን ውስጥ ራሳቸውን እንደነፃ አውጭ እንዲቆጥሩ ተደርገው ሲሰለጥኑና ለጦርነት ሲዘጋጁ የቆዩት የጥፋት ሃይሎች በርካታ ናቸው። እነዚህ በተለያዩ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ዓመቱን በሙሉ ሲያደርጉት የቆዩት ስልጠናን ወደማጠናቀቅና ለጥፋት አላማ ወረራ ለመፈጸም ዝግጅታቸውን ስለመጨረሳቸው ታውቆ የሰነበተ ጉዳይ ነው።

የውጭ ባዳና የውስጥ ባንዳ የኢትዮጵያ ጠላቶች የተቀናጀ የጥፋት እንቅስቃሴን ለማክሸፍ በሐሩር የሚቃጠለውን ጀግናው የኢትዮጵያ ሰራዊት ያለበትን ዝግጅትንና ሁኔታን ለመመልከት የኢትዮጵያ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶ/ር አብይ አህመድ በወልቃይት ተገኝተዋል። ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ቦታው ድረስ በመገኘት የሚገባውን ክብር መስጠታቸውና ማበረታታቸው ለሰራዊቱ ከፍተኛ ሞራልን የሚያላብስ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ በወሳኙ በሱዳን ኮሪደር ተገኝተው የኢትዮጵያን ሰራዊት ቁመና መመልከታቸው የውስጥ ባንዳዎችን ጭምር የሚያቃጥልና እረፍት የሚነሳ ነው‼️

የወልቃይት ጉዳይ ለኢትዮጵያ ሕልውና ቁልፍ አለማቀፍ ደንበር ነው‼️

ኢትዮጵያ ዛሬም ልክ እንደትናንቱ በጀግኖች ልጆቿ የተባበረ ክንድ ነፃነቷን ጠብቃ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች‼️
👎1