ታኦዳኮስ
1.33K subscribers
5.6K photos
86 videos
120 files
1.89K links
ታኦዶኮስ (ወላዲተ እግዚአብሔር)

ታኦዶኮስ ይሏታል ትርጓሜውም "የአምላክ እናት" ማለት ነው ለዛም ነው ቅድስት ኤልሳቤጥ ☞ በሉቃ 1፥43 ላይ ''የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?'' ያለችው ስለዚህ ብቸኛዋ የአምላክ እናት ስለሆነች "አንዲት" እያልን እንጠራታለን ።
Download Telegram
አቡነ ተክለ ሀይማኖት

#ታኅሣሥ_24 የልደታቸው መታሰቢያ ዕለት ናት ።
#ሼር
╭══•:|★✧💚💛✧★|: ══╮
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
╰══•:|★✧💚💛✧★|: ══╯
ከዛሬ 815 ዓመት በፊት በታህሳስ 24 ቀን ይህ ሆነ!
በያለንበት ከገዳሙ በረከት ተሳታፊ ያድርገን !
******************************
ለጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሐይማኖት 814ኛ አመታዊ
የልደታቸው መታሰቢያ በዓል በያለንበት እንኳን አደረሰን።
ታህሳስ 24 ቀን 11 97 ዓ/ም በዚህች በምታይዋት የቡልጋ
ዞረሬ ኢቲሳ ደብረ ጽላልሽ ገዳም በእግዚአብሔር ፈቃድ በጻድቁ
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ትንቢት ከካህኑ ጸጋዘአብና ከቅድስት
እግዚሐሪያ ተወለዱ ይህ ቦታ ህጻኑ ፍስሐ ጺዮን በልጅነታቸው
ያደጉበት በህጻንነታቸው ድንቅ ተአምራት ያደረጉበት አድገው
በግብረ ዲቁና ተንስኡ ጸልዮ ብለው የቀደሱበት ማይ ቀድተው
ሙጋድ ፈልጠው ያገለገሉበት የቅዱሳን መንጋ እንደ አሸን
የፈላበት እነ አቡነ ዜና ማርቆስ እነ ሳሙኤል ዘወገግ እነ አቡነ
ታዴዎስ ስንቱን እንቁጠረው በዘመናችንም የጻድቁ
ተክለሐይማኖት 11ኛ ትውልድ የሆኑት የወሊሶው ሐዋሪያ ፈዋሴ
ድውያን አባ ወልደ ትንሳኤ(አቡነ ዲዮስቆሮስ) የተወለዱባት
ታላቅ የቅዱሳን መዲና የሆነ ገዳም ነው ከአዲስ አበባ 60
ኪሎሜትር ርቀት ይገኛል ከኮተቤ መናህሪያ ገዳሙ ድረስ መኪና
አለ ደርሶ መልስ መሄድ ይቻላል የጻድቁን በዓለ ልደት
በተወለዱባት ቦታ እናክብር የተክልዬ ብዙ ወለታ አለብን
ምድራችንን በወንጌል ጨውነት ያጣፈጡ ጠላት የዘራውን አረም
የነቀሉ ባዕድ አምልኮን ከህዝቡ ያራቁ ሐዋሪያ ናቸው አባባ
ተክለ ሐይማኖት ምድራችን ላይ የተዘራውን የዘረኝነት አረም
ጸሎታቸው ያጥፋልን ለደጃቸው ያብቁን የተክልዬ አምላክ
የቀጠሮ ሰው ይበለን አሜን፡፡
#ሼር
╭══•:|★✧💚💛✧★|: ══╮
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
╰══•:|★✧💚💛✧★|: ══╯
ድንግል ሆይ፥ ...
እሳተ መለኮት በሆድሽ ባደረ ጊዜ ፊቱ እሳት፥ልብሱ እሳት፥ ቀሚሱ እሳት ነው እንደምን አላቃጠለሽም?
ሰባት የእሳት ነበልባል መጋረጃ በሆድሽ ውስጥ እንዴት
ተጋረደ? ወዴትስ ተዘረጋ? ከጐንሽ በቀኝ ነውን? ወይስ ከጐንሽ በግራ ነውን? ትንሽ አካል ስትሆኝ። የሚያንጸባርቅ ነደ እሳት የሚከበው ኪሩቤል የተሸከሙት ዙፋን በሆድሽ ውስጥ ወዴት ተዘጋጀ? ወዴትስ ተተከለ? ታናሽ ሙሽራ ስትሆኝ።
አባ ሕርያቆስ
#ሼር
╭══•:|★✧💚💛✧★|: ══╮
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
╰══•:|★✧💚💛✧★|: ══╯
መምህራን ያሻሉ !
ንጽሂት የሆነች አንዲት ቤተ መቅደስ
በደሙ ተዋጅታ ሕይወትን ምታወርስ
የቤተ ክርስቲያን ልዕልና እንዲቀጥል
ቅርንጫፍ ከዛፉ እንዳይገነጠል
አማናዊ ወንጌል ለዓለም እንዲዳረስ
ዶግማ እንዲጠበቅ ሥርዓት እንዳይፈርስ
ትውፊት እንዳይጠፋ ሕግም እንዳይጣስ
መምህራን ያሻሉ እጅግ የተማሩ
በሥነ መለኮት የተመራመሩ
መጻሕፍትን ሁሉ የሚያመሠጥሩ
ሕዝበ ክርስቲያኑን በእውቀት የሚመሩ
ምሥጢር የሚገልጡ በፍቅር ሚስቡ
የረቀቀ አጉልተው የራቀ ሚያቀርቡ
ከዘመን ኑፋቄ ሕዝብን ሚጠብቁ
ለቃለ እግዚአብሔር የሚጠነቀቁ
ለሃይማኖት ክብር ቅድሚያ የሚሰጡ
ለቤተ ክርስቲያን ሰላምን ሚያመጡ
ለእመ-ብርሃንና ለቅዱሳን ክብር
ከቶ የማያፍሩ ለዓለም ለመመስከር
መምህራን ያሻሉ በእውቀት የረቀቁ
በጎች በተኩላዎች እንዳይነጠቁ፡፡
#ሼር
╭══•:|★✧💚💛✧★|: ══╮
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
╰══•:|★✧💚💛✧★|: ══╯
የመንፈስ ቅዱስ በገና የሆነ ቅዱስ ኤፍሬም ስለ ጌታ ልደት ከደረሰው ዝማሬ መካከል እንዲህ አለ
★ ★ ★

ዮሴፍ እግዚአብሔር ወልድን እንደ ሕፃንነቱ አቀፈው ፣ እንደ አምላክነቱም አገለገለው። በመሐሪነቱ እጅግ ደስ አለው በፈራጅነቱ ግን እጅግ ፈራው።

እንዲህ ሲል:
የልዑልን ልጅ ለእኔ እንደ ልጅ ይሆን ዘንድ ማን ሠጠኝ? እናትህ በጸነሰች ጊዜ ተቆጥቼ ነበር ፣ በስውር ልተዋትም አስቤ ነበር። በማኅፀንዋ ውስጥ ከድህነቴ ሊያወጣኝና ባለጠጋ ሊያደርገኝ የሚችል የተሰወረ ሀብት እንዳለ አላወቅሁም ነበር። ከእኔ ዘር የሚሆን ዳዊትስ አክሊል የደፋ ንጉሥ ነበር ፣ እኔ ግን የተናቀ ደሃ ሆንሁ። እንደርሱ ንጉሥ በመሆን ፈንታ አናጢ ሆንኩ። አሁን ግን እነሆ አክሊል ወደ ቤቴ መጣ ፣ የአክሊላት ሁሉ ጌታ በእቅፌ ነውና!

★ ★ ★
ድንግል ማርያም ሕፃኑን እያባበለች በመደነቅ ቃል ነደደች
እንዲህ ስትል
"ድንግሊቱን እጸንስ ዘንድ የሰጠኝ ማን ነው?
ይህንን አንድ ሲሆን የበዛ ፣ ታናሽ ሲሆን ታላቅ የሆነ ፣ ከእኔ ጋር ሲሆን በሁሉ የሞላ ሕፃን የሠጠኝ ማን ነው?
....
በእኔ [ማኅጸን] ውስጥ እያለህ ከእኔም ውጪ በሁሉ ቦታ ነበርህ ፣ በወለድሁህ ጊዜም ረቂቅ አምላክነትነህም ከእኔ ውስጥ አልወጣም። በእኔ ውስጥ ነህ ፣ ከእኔም ውጪ ነህ! ይህ ነገር ለእኔ ለእናትህን ያስደነቀኛል።

የሚታየው ሰውነህን በፊቴ ባየሁ ጊዜ የማይታየው አምላክነትህን በሕሊናዬ አየዋለሁ። ቅዱስ ሆይ በሚታየው ሰውነትህ ውስጥ አዳምን አየዋለሁ ፣ በማይታየው መለኮትህ ውስጥ ደግሞ በአንተ ሕልው ሆኖ የሚኖረውን እግዚአብሔር አብን አየዋለሁ።

አንተ ምንጭ ሆይ ለአንተ ለማጠጣት የጡቶችን ምንጭ እንዴት ልከፍታቸው ይቻለኛል? ሁሉን ከገበታህ የምትመግብ ሆይ እኔ አንተን ልመግብህ እንዴት ይቻለኛል? የክብርን ነጸብራቅ የተጎናፀፍከው ሆይ እንደምን በጨርቅ ልጠቀልልህ እችላለሁ?

ምን ብሎ እንደሚጠራህ አንደበቴ አያውቅም። አእላፋት ስሞች ለአንተ አይበቁህም ፣ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ስትሆን የሰው ልጅ ነህና ፣ የዳዊት ልጅ ስትሆን የማርያም ልጅ ነህና!

ልጄ ሆይ ከእኔ ጋር ሆነህ ሳለ ከሰው ልጆች ሁሉ ጋር በመሆንህ አልቀናም። ለሚያምንብህ አምላክ ነህ ፣ ለሚያገለግልህ ጌታ ነህ ፣ ለሚወድህም ሁሉን ያንተ ታደርገው ዘንድ ወንድም ነህ!"

የአንደበቶች ሁሉ ጌታን አንደበት እንደሌለው ያደረገው ምን ይሆን? ልጄ ሆይ አንተን በድንግልና መፅነሴን ክፉ ሰዎች እየዘለፉ ነው።
ቅዱስ ሆይ ለእናትህ አንደበት ሁነኝ ፣ አንተን ከማን እንደፀነስሁህ ይረዱ ዘንድ ተአምርህን አሳይ።

ሁሉን የምትወድደው ሆይ ስለ አንተ ብዬ የተጠላሁ ሆንሁ ፣ ለሰው ልጆች መሸሸጊያ የሆንህ አንተን በመፅነሴ መከራን ተቀበልሁ።
አቤቱ በዮናስ ላይ እንደተቆጣ ባሕር በእናትህ ላይ ተቆጥቷል።
ሔሮድስ የተባለ ማዕበል የባሕርን ጌታ ሊይዝህ ፈልጓል። የእናትህ ፈጣሪዋ ሆይ ወዴት እንደምሸሽ ንገረኝ"
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
#ሼር
╭══•:|★✧💚💛✧★|: ══╮
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
╰══•:|★✧💚💛✧★|: ══╯
"እሑድ ቀን በጧት እጅግ ማልደህ ከሌሊቱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሒድ፤ ስትሔድም ልቡናህን በማባከን ወዲያና ወዲህ አትይ፤ በንጹሕ ቅዳሴም ጊዜ [የክርስቶስን]ሕማሙን ሞቱን ትንሣኤውን እያሰብክ በፍጹም ፍርሃት ቁም"

('ሃይማኖተ አበው፤ ሠለስቱ ምዕት ፳፥ ፳፪፤ ፲፱፻፹፪ ዓ.ም.፤ገጽ ፴፰ )
#ሼር
╭══•:|★✧💚💛✧★|: ══╮
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
╰══•:|★✧💚💛✧★|: ══╯
"የጌታ ልደት በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ"
@Theothokos

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የከበረ የክርስቶስን ልደት ነገር በተናገረበት አንቀፅ እንዲህ አለ ቀዳማዊ አምላክ ዛሬ ተወለደ ፤ ጥንቱን ገንዘቡ ባይደለ ባህርይ ተገኝ ፤ እርሱ ቀዳማዊ አምላክ ነው ፤ ሰው በመሆኑም ከባህርይው አልተለወጠም፡፡ የመለኮቱ መገኝትም ከእመቤታችን ከተወለደ ወዲህ አይደለም ፤ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ጥበብ ነውንጂ ፤ የማይታመም እርሱ ከባህርይ መለኮቱ ሳይለወጥ ሕማም የሚስማማውን ስጋን ተዋሃደ፡፡ ዳግመኛም በልዑል ዙፋን ላይ ተቀምጦ ያለ እርሱ በበረት ተጣለ ስጋ ሳይሆን የነበረ የማይዳሰስ ወልድ ዋህድ ዛሬ ስጋን በመዋሃድ ተዳሰሰ ፤ ሃጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱ በጨርቅ ተጠቀለለ፡፡

መፅሃፍ እንዲህ አለ ፦ ብልህ ሽክላ ሰሪ የሚሰራውን የለዘበ ጭቃ በአገኝ ጊዜ ከእርሱ መልካም እቃ እንዲሰራ እንደዚሁ ጌታችን የዚህችን ድንግል ንፁህ ስጋዋን ንፅህት ነፍሷን ባገኘ ጊዜ ነፍስ ያለችውን ስጋ ሊዋሃደው ፈጠረ፡፡ እንደወደደ ከድንግል ነፍስን ስጋን ፈጥሮ ለበሰ እርሱንም ተዋህዶ ዛሬ ተወለደ ሕፀፅ ያለበት ነው ብሎ ባህርያችንን አልተወውም ፤ ስጋን በተዋህዶ ጊዜ ቃል ከምላቱ አልተወሰነም ፤ ስጋ የፈጣሪ አካል ባህርይ በሆነ ጊዜ ፍፁም አምላክነትን አገኝ እንጂ፡፡ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረ እርሱ ትንሽ ህፃን ሆኗልና፡፡

እኔ ፈፅሜ አደንቃለሁ ፤ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን ፡ በዘላለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ ፡ ከስጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ ፡ ሃጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት ፤ ይህን ወዷልና፡፡ ክብሩ ተለይቶት የነበረ ስጋን ክቡር አምላክ ሊያደርገው ፤ የፀጋ ገዥነትን አጥቶ የነበረ ስጋንም የባህርይ ገዥ ሊያደርገው ወደደ ፤ አዳም ከእኛ እንዳንዱ ሆነ ያለውንም ሰው በመሆን ሊገልጠው ወደደ፡፡ ስለዚህ ስጋየን ተዋሃደ ፡ ወንጌልን ሲያስተምር እሰማው ዘንድ ስጋየን በተዋህዶ ገንዘብ አደረገ ፤ መንፈስ ቅዱስን ሰጠኝ ፡ ተቀበልኩ ፡ ለእኔም ፍፁም ህይወትን ገንዘብ አደረግሁ ፡ እርሱ ያከብረው ዘንድ ስጋየን ተዋሃደው ፡ የሚያድነኝ መንፈስ ቅዱስን ሰጠኝ፡፡ በቅዳሴውም እንዲህ አለ፡- ዳግመኛም የወልድ አነዋወሩ እንደምን እንደሆነ መውረዱም እንዴት እንደሆነ እንናገራለን፡፡ ከአባቱ ሳይወጣ መጣ ከአነዋወሩ ሳይለይ ወረደ ከሶስትነቱ ሳይለይ መጣ ከአንድነቱም ሳይለይ ወረደ ከዙፋኑም ሳይለይ በስጋ ልጅ አደረ ከምላቱ ሳይወሰን በማህጸን ተጸነሰ በላይ ሳይጐድል በማህፀን ተወሰነ በታችም ሳይጨመርበት ተወለደ ከኃጢአት በቀር ፈፅሞ ሰው ሆነ እንደ እግዚአብሔር እየሰራ እንደ ባርያ ታየ፡፡ ዳግመኛም እንዲህ አለ ፍቅር ሰሃቦ ለወልድ ኃያል እም መንበሩ ወአብጽሖ እስከለሞት /ፍቅር ኃያል ወልድን ከዙፋኑ አወረደው እስከ ሞትም አደረሰው።/

እንግዲህ እኛ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራን የእርሱን በጎነት እንድንነግር የተመረጥን ቅዱስ ሕዝብ ለርስቱ የተለየን ወገን መሆናችን አውቀን በብርሃን እንኑር ጨለማውም ያልፋልና እውነተኛውም ብርሃን ይበራል በቀን እንደሚሆን በጽድቅና በቅንነት ሆነን (1ጴጥ 2፡9 ፣ 1ዮሐ 2፡8) የጌታችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት እናክብር።
#ሼር
╭══•:|★✧💚💛✧★|: ══╮
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
╰══•:|★✧💚💛✧★|: ══╯
እንኳንለብርሃነ
🕯🕯🕯🕯
🕯🕯🕯🕯
🕯🕯🕯🕯
🌹
🌹🌹
🌹🌹🌹
🌹
🌹🌹
🌹🌹🌹
"በጎል ሰከበ አፅርቅት ተጠብለለ
ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ"
በበረት ተኛ በጨርቅ ተጠቅለለ፡
የዓለም መድኃኒት ዛሬ ተወለደ

🕯🕯📖📖🕯🕯

📖📖📖
" ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።"
(ኢሳ 7: 14)
📖📖📖
" እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።"
(ማቴ 1: 23)
📖📖📖
" ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር" ኃያል "አምላክ" የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።"
(ኢሳ 9: 6
🕯🕯🕯🕯🕯
ውድ አባቶቼ እናቶቼ ወንድም እህቶቼ፡ህፃናት የተዋህዶ ልጆች


🌷በሀገርም🌷
💜ውስጥ💜
🌹ከሀገርም🌹
💜ውጭ💜
🌷ያላችሁ🌷
🌹በስደት🌹
🌳በእስራት🌳
🌳በጎዳና🌳
🌳በጭንቅ🌳
🌳በአልጋ🌳
🌳በዱር🌳
🌳በበረሃ🌳
🌳በዋሻ🌳
🌳ያላችሁ🌳
💜ለመላው💜
🌹የክርስትና🌹
💜እምነት💜
🌷ተከታይ🌷

💜በሙሉ💜

🌹እንኳን🌹
💜💜
ለብርሃነ ልደቱ
ለጌታችን ልደት
💙በዓል 💜
🌹በሰላም🌹
💜አደረሳችሁ💜
🌷🌷
💜💜
🌹🌹
💜💜
🌷🌷
💜💜
🌹🌹
💜💜
🌷🌷
💜💜
🌹🌹
💜💜
🌷🌷
💜💜
🌹🌹
💜💜
🌷🌷
💜💜
🌹🌹
💜💜
🌷🌷
💜💜
🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
ባ ለ ው ለ ታ ች ን
🌷🌷🌷🌷🌷
ጌ ታ ች ን
🌹🌷🌹🌷
አ ም ላ ካ ች ን
🌹🌳🌹🌳🌹
መ ዳ ኒ ታ ች ን
🌹🕯🌹🕯🌹
🍸🍸
🍸🍸
🍸🍸
🍸🍸
🕯🕯 ክርስቶስ🕯🕯
🕯🌳🌹የእናታችን 🍸
🕯🌳🌹የቅድስት 🍸
🕯🌳🌹ድንግል🍸
🕯🌳🌹ማሪያም🍸
📖📖
📖📖
🕯🕯
🕯🕯
🕯🕯
🕯🕯
🕯🕯

🌺🌺በቸርነቱ 🌺🌺
🌺
🌺🌺
🌺🌺🌺
🌺
🌺
🌷💜🌷 🌹🌳🌹
🌹 የሰላም 🌳
🌹የደስታ 🌳
🌹 የፍቅር🌳
🌹የበረከት🌳
🌹የአንድነት 🌳
🌳🌳🌳🌳🌳🌳
🌳በዓል
🌳🌳ይሁንልን
🌳አሜን!!!🌳
🌳አማን!!!🌳
🌳አማን!!!🌳
🌳
🌹
🕯
🍸
📖
ባ ለ ው ለ ታ ዬ

🌹🌳🌹🌳🌹🌳
#ሼር
╭══•:|★✧💚💛✧★|: ══╮
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
╰══•:|★✧💚💛✧★|: ══╯
"የክርስቶስ ልደት በቅዱስ አትናቴዎስ አንደበት"

የቀኑ ቀጠሮ ሲደርስ እግዚአብሔር ልጁን ላከ ከድግልም ተወለደ፡፡ ይህ አንዱ አምላክ ነው በመለኮት የእግዚአብሔር ልጅ በሥጋ የአዳም ልጅ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ የአዳም ልጅ ስለሆነ ለወልድ ዋሕድ ለአንዱ የምስግድለት ለአንዱ የማንሰግድለት ሁለት አካል ሁለት ባህርይ አለው የምንል አይደለም ስው የሆነ የእግዚአብሔር አካሉ ባሕርዩ አንድ ነው እንጂ ፡፡ ከስጋው ሳንለይ አንድ አድርገን አንዲት ስግደትን እንሰግድለናታለን እንጂ፡፡

እርሱ ከሰው ቢወለድም በፀጋ የእግዚአብሔር ልጅ አይደለምና አስቀድሜ እንደተናገርኩ ከእግዚአብሔር የተገኘ እግዚአብሔር ነው እንጂ፡፡ ሰው ሆነ ሰለማለት ፈንታም ራሳቸውን ለመጉዳት ልብወለድ ነገርን ፈጥረው እግዚአብሔር በሰው አደረ አሉ፡፡ መለኮትና ትስብእት እርስ በእርሳቸው አንድ ሆነው ተዋሐዱ ስለማለት ፈንታ ሰው ሰራሽ ነገርን ፈጥረው ተናገሩ፡፡ ይህም የማይገባ የማይጠቅም ክህደት ነው፡፡

ዳግመኛም በክህደታቸው አስበው ማርያም የወለደችው ክርስቶስ ገዥ ፈጣሪ እንዳይደለ የሚናገሩ የመናፍቃን ልጆች ፈፅመው ምላሽ ይጡ፡፡ እግዚአብሔር ቃል ሥጋን ካልተዋሐደ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ ጊዜ እንደምን “አማኑኤል” ተባለ? ትርጓሜውም
እግዚአብሔር ከሥጋችን ሥጋ ከነፍሳችን ነፍስ ነስቶ አንድ አካል አንድ ባህርይ ሆነ ማለት ነው፡፡

በሰው ሁሉ እንዲያድር ቃል ከአደረበት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ስለተወለደው በላ፣ ጠጣ፣ ታመመ፣ ሞተ ተብሎ እንደምን ተነገረ? ይህ ሁሉ በባህርዩ እንደሌለበት አውቀው አይደለምን? ሰዎች ሁሉ ከአዳም እስከዛሬ መብላት፣መጠጣት፣ መታመም፣ መሞት ልማዳቸው ነው የባህርያቸው ስራ እንደሆነ በመታወቁም ይህ ሁሉ አልተነገረላቸውም ከእመቤታችን ከቅድስት
ድንግል ማርያም ለተወለደው ብቻ ተነገረ እንጂ፡፡ የሥጋን ገንዘብ የሆነ መብላንም ሁሉ ገንዘብ ለአደረገው ነው እንጂ፡፡ እኛን ያድን ዘንድ ሥጋችንን ተዋሕዶ ከኃጢአት ብቻ በቀር የሰውነትን ሥራ ሰራ እንጂ፡፡

ከዚህ ትምህርት ሌላ የሚየስተምረውን የእግዚአብሔ ልጅ ከማርያም ከተወለደው ልዩ ነው የሚለውን አንዱ አካል የአግዚአብጠር ልጅ አንዱ ከማርይም የተወለደ በፀጋ የከበረ ዕሩቅ ብዕሲ ነው ብሎ ሁለት እስከማለት ደርሶ እንደኛ በፀጋ የከበረ የፀጋ ልጅ ነው የሚለውን ጌታችን የነሳው ሥጋ ከሰማይ እንደተገኘ ከድንግል ማርያም እንዳልተገኘ አድርጐ የሚናገረውን ወይም መለኮት ሥጋ ወደመሆን ተለወጠ
ወይም ከእርሱ ጋር ተቀላቀለ እንዲህ እንዲህ የሚሉትን
የእግዚአብሔር ልጅ የሾመው ሐዋርያ እኛ ካስተማርናችሁ ሌላ ትምህርት የሚያስተምራችሁ ሁሉ የተወገዘ የተለየ ይሁን ያለውን ቃል ይዛ ቅድስት ቤተክርስቲያን ታወግዛቸዋለች ትለያቸዋለች፡፡ /ገላ 1፤6-10/A
#ሼር
╭══•:|★✧💚💛✧★|: ══╮
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
╰══•:|★✧💚💛✧★|: ══╯
+ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? +

የተወለደውን ክርስቶስ ለማየት ብዙ ሀገራትን አልፈው ተጉዘው የመጡት ሰብአ ሰገል በኮከብ ተመርተው ነበር::
ለእስራኤላውያን እረኞች በታሪካቸው ውስጥ በሚያውቁአቸውና በለመዱአቸው መላእክት ልደቱን የገለጠው አምላክ ኮከብ ሲቆጥሩና ሲጠነቁሉ ለኖሩት ሰብአ ሰገል ደግሞ በሚያውቁት ኮከብ መራቸው::

ሕጻኑ ክርስቶስ ገና ከመወለዱ ብዙ እንደ ጣዖት የሚመለኩ ነገሮችን ድል አድራጊ መሆኑን አሳየ:: እስራኤል ጥጃን አምላክ ብለው በወርቅ ጣዖት ሠርተው ነበር:: በቤተልሔም ጥጃ ትንፋሹን ለክርስቶስ በመገበር አምላኬ እርሱ ነው ሲል መሰከረለት:: በሬም ገዢውን አወቀ ሕዝቤ ግን አላወቀኝም የሚለው ተፈጸመ:: ከዋክብትንና ፀሐይን ያመልኩ የነበሩን የዞረዳሸት (ዞራስትራኒዝም) /Zoradascht (Zoroaster) ፍልስፍናን የሚያምኑ ሰብአ ሰገልም በሚያመልኩት ኮከብ ፈጣሪያቸውን አገኙ:: ቅዱስ ኤፍሬም እንዳለው "የሚያመልኳት ፀሐይም በሰብአ ሰገል ጉልበት ለፈጣሪዋ ሰገደች"

ኮከብ የሚወጣበት ጊዜ በዚያን ቀን የሰውን ዕጣ ፈንታ ይወስናል ብለው የሚያምኑም ብዙዎች ናቸው:: ይህ የሆነው በኮከቤ ምክንያት ነው! ኮከባችን አይገጥምም የሚባባሉ ብዙዎች ናቸው:: ይህ ሁሉ ባዕድ አምልኮ ነው:: ኤሳውና ያዕቆብ መንትዮች ናቸው:: የተወለዱት በአንድ ቀን ነው:: እነርሱ በተወለዱ ቀን የወጣው ኮከብም አንድ ነው:: "ኮከባቸው" አንድ ሆኖ ሳለ ምነው ነገራቸው ሁሉ አልገጥም አለ? ኮከባቸው ይገጥማል ምነው እነርሱ አልገጠሙም? ስለዚህ ሐሰት ነው::

የተወለደው ንጉሥ ግን ኮከቡ ዕጣ ፈንታውን የሚወስነው ሳይሆን ከዋክብትን በየስማቸው የሚጠራቸው በቁጥር የሚያውቃቸው ጌታ ነው:: እንደ ዮሴፍ 11 ከዋክብት ሐዋርያቱ ከይሁዳ በቀር የሰገዱለት እናቱ ማርያምም እንደ ያዕቆብ በልብዋ እያሰበች የተደነቀችበት የከዋክብት ጌታ የጨረቃ ንጉሥ የፀሐዮች ሁሉ ፀሐይ ነው እርሱ::

ሰብአ ሰገል መሪያቸው የነበረውን ኮከብ ሲያጡት ወደ ሔሮድስ መጡና "የተወለደው ንጉሥ ወዴት ነው?" አሉ:: እውነትም ጠቢባን ናቸው:: መንገድ ከጠፋብን : መሪ ኮከብ ካጣን ልደቱን የፈለግንበት እናክብር አላሉም:: የተወለደው ወዴት ነው? ብለው ቤተ መንግሥት ሔደው ጠየቁ:: ጥሩ በዓል ለማክበር ከቤተ መንግሥት የተሻለ ሥፍራ የለም:: በቤተ መንግሥት ራት እየበሉ ጮማ እየቆረጡ በዘፈን ታጅበው በዓሉን ማክበር ይችላሉ:: እነርሱ ግን የትም ቢሆን ንጉሡን ሳናገኝ አንቆይም:: እሱ የሌለበት ቦታ ቤተ መንግሥትም ቢሆን ልደቱን አናከብርም:: አይ ሰብአ ሰገል! ይህንን ዘመን መጥተው ቢያዩ ምን ይላሉ?

ወዳጄ አንተ የጌታን ልደት የት ታከብራለህ? መቼም
ልደት የሚከበረው ባለ ልደቱ ባለበት ሥፍራ ነው:: በእውነት የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? በጭፈራ ቤት ነውን? በመጠጥ ቤት ነውን? የት ነው ያለው ብለህ ጠይቀሃል?

"የሚመራኝ ኮከብ የለም" ትል ይሆናል:: ምንም ቢሆን ግን ሕፃኑ በሌለበት ልደቱን ለማክበር መወሰን የለብህም:: ምንም ያሸበረቁ ሥፍራዎች ቢኖሩም እንዳትታለል:: የሔሮድስ ቤተመንግሥት ውበት የግብዣው ስፋት አታልሎህ የተወለደውን ንጉሥ እንዳያስረሳህ ተጠንቀቅ:: እሱ ከሌለበት ያማረ ሥፍራ ይልቅ እሱ ያለበት በረት ይሻልሃል:: እሱ ያልመረጠውን ሥፍራ መርጠህ ከመንገድ አትቅር:: "የተወለደው የአይሁድ ወዴት ነው" ብለህ ጠይቅ::

እሱ ደሃ ሆኖ ባለጠጋ የሚያደርግህን ንጉሥ በሚያልፍ ደስታ አትጣው:: በስካር በዝሙት በጭፈራ በሔሮድስ ቤተ መንግሥት ቀልጠህ ቀርተህ የተወለደውን ሕፃን ሳታየው አትቅር:: እሱ በተወለደባት ሌሊት አንተ ስትሞት አትደር:: እመነኝ የተወለደው ይሻልሃል ከሞቱት ጋር ጊዜህን አታጥፋ::

ሰብአ ሰገል "የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው?" ብለው ለአይሁድ ንጉሥ ሔሮድስ ጠየቁት:: የአህያ ውኃ ጠጪው ሔሮድስ ክው ብሎ ቢደነግጥም ፈገግ ብሎ ላጣራላችሁ ቆይ ብሎ አቆያቸው::

መጽሐፍ አዋቂዎቹን ጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠሩ:: እነ ሊቄ መለሱ:: "እንደተነገረው ትንቢት ከሆነማ" አሉ ኩፍፍፍስ ብለው "በይሁዳ ቤተልሔም ነው" ብለው የተወለደውን ንጉሥ አድራሻ ተናገሩ:: ሔሮድስ ከነተንኮሉ ለሰብአ ሰገል መልእክቱን አደረሰ:: ሰብአ ሰገልም ሔደው ለንጉሡ ሰግደው እጅ መንሻ አቀረቡ::

ሔሮድስን ትተን እስቲ የጸሐፍቱን ነገር ትንሽ እናስተውለው:: የተወለደውን ጌታ አድራሻ ጠቁመው ለሰብአ ሰገል መንገድ የመሩ እነርሱ ግን መንገድና እውነት ሕይወትም የሆነው ጌታ የተሰወረባቸውን የታወሩ መሪዎች በሽተኛ ሐኪሞች የተራቡ መጋቢዎችን እስቲ ልብ እንበላቸው::

ሌላውን ወደ ጌታ እየመራ እርሱ ከጌታው የራቀ : የእርሱን ቃል ሰምተው ሰዎች ሲድኑ እርሱ በኃጢአት ቁስል የተወረሰ ስንት አይሁድ እለ? ቅዱስ አምብሮስ እንዳለው የኖህ መርከብ ሲሠራ ሚስማርና መዶሻ እያቀበለ የሠራ ነገር ግን ከጥፋት ውኃ ያልዳነ ስንት በየቤቱ አለ::

እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል ማለት ቀላል ነው:: እንደተጻፈው መኖር ግን ከባድ ነው:: ከመጽሐፍ ጥቅስ ማውጣት ቀላል ነው የሚጠቀስ ሕይወት መኖር ግን ከባድ ነው:: ወዳጄ ለብዙ ሰብአ ሰገሎች ስለተወለደው ንጉሥ ነግረሃል:: በአንተ ሕይወት ውስጥስ "የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው?" ወይስ በአንተ ሕይወት ገና አልተወለደም? ወይስ እንደ እንግዶች ማደሪያ ቦታ የለም ብለህ መልሰኸዋል? ኸረ እኔ እንኩዋን የቆሸሸ ሕይወት ነው ያለኝ እሱ በእኔ አያድርም አትበል? እንደ በረት ብትሸት እንደ እንስሳ እየኖርህ ቢሆንም አትፍራ እርሱ አይጠየፍህም? ወደ ልብህ መለስ ብለህ እንዲህ ብለህ ራስህን ጠይቅ "በእኔ ሕይወት ውስጥ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው?"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
#ሼር
╭══•:|★✧💚💛✧★|: ══╮
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
╰══•:|★✧💚💛✧★|: ══╯
ታኦዳኮስ pinned «እንኳንለብርሃነ 🕯🕯🕯🕯 🕯🕯🕯🕯 🕯🕯🕯🕯 🌹🌹🌹🌹🌹🌹ረ ሳ🌹🌹🌹🌹🌹🌹 "በጎል ሰከበ አፅርቅት ተጠብለለ ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ" በበረት ተኛ በጨርቅ ተጠቅለለ፡ የዓለም መድኃኒት ዛሬ ተወለደ 🕯🕯📖📖🕯🕯 📖📖📖 " ስለዚህ…»
…እግዚአብሔር የባሕርይህን ፍሬ በዙፋንህ አኖራለሁ ብሎ ለዳዊት በእውነት ማለ አይፀፀትም ጻድቅ እረሱ (ዳዊት) ክርስቶስ በሥጋ ከእርሱ እንዲወለድ ባመነ ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ማደሪያ ፈልጎ ያገኝ ዘንድ ወደደ ይህንንም በታላቅ ትጋት ፈፀመ ከዚህ በኋላ "እነሆ በኤፍራታ ሰማነው" ብሎ ጮኸ ይህችውም አማኑኤል እኛን ለማዳን በሥጋ ይወለድባት ዘንድ የመረጣት የያዕቆብ አምላክ ማደሪያ ናት።… ቅድስት ሆይ ለምኝልን።…
#ሼር
╭══•:|★✧💚💛✧★|: ══╮
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
╰══•:|★✧💚💛✧★|: ══╯
ጾሙስ አበቃ.....?
#በአባ_ገብረ_ኪዳን
@Theothokos

ጾሙስ አበቃ የነፍስ ረሃባችን መቼ ያበቃ ይሆን? ነፍሳችን ሥጋውን ደሙን እስከመቼ ነው የምትጾመው? ጾሙስ ተደመደመ። የእኛ በደል መቼ ይሆን የሚቋጨው? ስግብግብነታችን መቼ ነው ዳር የሚደርሰው? በዚህ ጾም መጨረሻ የአብ አንድያ ልጁ ተወልዶ መለያየት ተወገደ ሰውና መላእክት አንድ ሆኑ፤ መቼ ይሆን ጎጠኝነታችን የሚጠፋው? መቼ ይሆን ሰማያዊ ዘመድ የምናበጀው። ጾም ተፈጽሟልና ለሥጋ ሥጋ ተገዛለት። ለዚህ ጾሞ ፋሲካ ለነፍስ ምን ቅመም ተቀመመላት? ምን ንብረት ተመደበላት? ምን ሙክት ተገዛላት? ምን ወይን ተጠመቀላት? ምን ልብስ ተሠራላት? ምን ድግሥ ተደገሠላት? እነማንን ድግሥ ጠራንላት? አጋንንትን ወይስ መላእክትን? ዛሬ ዛሬ የጾም መግቢያና መውጫ ይገርማል። የጾም መግቢያ ሥጋ ይበላል የጾም ፍጻሜ ሥጋ ይበላል። በሥጋ ጀምረን በሥጋ መጨረስን ተያይዘነዋል! ሥጋው በደል ሆኖ አይደለም መጀመሪያችን መፈጸሚያችን የሥጋ ብቻ መሆኑ ግን የነፍስ ያለህ ያሰኛል!

አንዳንድ ሰው የዘንድሮው በዓል ልዩ የሚያደርገው ዓመቱ ፳፻፲፩ መሆኑ ይመስለዋል። ልዩ የሚያደርገው ከአምናው በተለየ ነፍስ ያገኘችው ነገር ሲኖር ነው። ለሥጋ ተበድሮ ሳይቀር ይደገሳል። ቢያንስ ድኃ ቢያጣ ያለችውን አጥቦ ለብሶ ከጎረቤት ሥጋ እየሸተተው ይውላል። ነፍሳችንስ ቢያንስ የሚቆርቡትን እያየች የክርስቶስ መዐዛ ቢናፍቃትም ባይሆን ተናዝዘን ታጥበን ብንውል ምን አለ?

የጸሎት ረሀብ መቼ ነው የምንፈስከው? የንጽሕና ረሀብ መቼ ነው የምንገድፈው? መፈሰክ ማለት መሻገር ነው? ዝሙትን የተሻገርን ዕለት ያን ጊዜ ነበር ፋሲካ!

ሱባኤው ደረሠ ቀጠሮው ተፈጸመ ጌታ ተወለደ። የእኛ ቀጠሮ መቼ ነው የሚደርሰው? በዚህን ጊዜ...ን አደርጋለሁ ብቻ! ጸሎቱ ቀጠሮ ጾሙ ቀጠሮ ትጋቱ ቀጠሮ አሥራቱ ቀጠሮ ኑዛዜው ቀጠሮ መታረቁ ቀጠሮ ቁርባኑ ቀጠሮ ሁሉ ቀጠሮ!ማን አለ የእኛስ ቀጠሮ ቢደርስ ምን አለ ጽኑዕ ቀጠሯችን ሳይደርስ እኛ የቀጠርነውን ጽድቅ ብንጀምረው! ምን አለ የእኛም ሱባኤ አብቅቶ የእግዚአብሔርና የቅዱሳን ልጆች ሆነን በምግር ብንወለድ!

የጾመ ነቢያት ፍጻሜ ጌታ ተወለደ። እኛም ከንስሐ ማኅፀን እንድንወለድ ይርዳን። ከጾሙ መጨረሻ ክርስቶስ ከእነርሱ በሥጋ መጣ። ከጾማችን ፍጻሜ ጌታ በሰውነቴችን እንዲያድር ንስሐ ብንገባ ይህ ነው የጾም ፍጻሜ። ጌታ ሲወለድ አሮጌው ዘመን አበቃ። ሐዲስ ሕይወት፡ተወጠነ። እኛም ኃጢአታችን በንስሐ አልቆ አዲስ ከዘንድሮው ልደት ጀምሮ አዲስ ሕይወት ለመኖር ያብቃን። ኃጢአታችን ይለቅልን!
#ሼር
╭══•:|★✧💚💛✧★|: ══╮
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
╰══•:|★✧💚💛✧★|: ══╯
"ድንግል ሆይ ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢ። ድንግል ሆይ በቤተልሔም ካንቺ የተወለደውን መወለድ በጨርቅ የተጠቀለለውንም አድግና ላህም በብርድ ወራት እስትንፋስንተ ያሟሟቁትንም አሳስቢ።"
ቅዳሴ ዘእግዝእትነ ማርያም
@Theothokos
በአባቱ ፈቃድ ወረደ በማርያም ዘንድ እንግዳ ሆነ። እግዚአብሔር በንጹሕ ድንግልናዋ ተወለደ። በእንስሳት በረት ተጨመረ፣ የንግሡንም እጅ መንሻ ተቀበለ፣ ከእናቱ ጡቶች ምግብን እየለመነ እንደ ሕጻናት አለቀሰ።

(ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ)
#ሼር
╭══•:|★✧💚💛✧★|: ══╮
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
╰══•:|★✧💚💛✧★|: ══╯
“ወንድሞቻችን እኛስ እንዲህ እናምናለን ያልተወለደ እግዚአብሔር አብ በተለየ አካሉ አንድ ነው፤የተወለደ እግዚአብሔር ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስም በተለየ አካሉ አንድ ነው፡፡ በወደደው የሚያድር የአብ የወልድ እስትንፋስ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም በተለየ አካሉ አንድ ነው፡፡አብ አልተወለደም ዓለም ሁሉ ሳይፈጠር ወልድን የወለደ ነው እንጂ ወልድም ዓለም ሁሉ ሳይፈጠር ከእግዚአብሔር አብ ተወለደ፤መንፈስ ቅዱስም ዓለም ሁሉ ሳይፈጠር ከእግዚአብሔር አብ ሠረጸ፡፡
(ሃይማኖተ አበው ዘአትናቲዎስ ገጽ ፶፭)
#ሼር
╭══•:|★✧💚💛✧★|: ══╮
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
╰══•:|★✧💚💛✧★|: ══╯
Track03
Track03
አልተገኘባትም ከበለሷ ፍሬ
ቢፍልግባትም መልካሙ ገበሬ
አልተገኘባትም ከበለሷ ፍሬ
አዝ--------------//
ለስልሶላት ነበር ሃይማኖት መሬቱ
ተቀጥሮላት ነበር አጥር ስርዓቱ
ተለቅሞላት ነበር ድንጋይ ፈተናዋ
ፍሬ ግን ታጣባት በመጨረሻዋ
አዝ-------------//
ፍሬ የሌለባት ቅጠል ስለሆነች
ተካይዋን በምግባር ስላላስደሰተች
መልካሙ ገበሬ ሊቆርጣት ተነሳ
ሌሎች እንዳይጠፉ በእርሷ የተነሳ
አዝ--------------//
ለንሰሃ የሚሆን እድሜ እንዲሰጣት
ጠባቂ መልአኳ ተማጸነላት
ምክር እና ተግሳጽ ይጨመርላት
ታፈራ ከሆነ ለዓመት እንያት
አዝ-------------//
ልመናውን ሰምቶ ጌታውም ፈቀደ
ጥቂት እድሜ ሊሰጥ ሊታገስ ወደደ
ዳግመኛ ሲመጣ ፍሬ ካላፈራች
ተቆርጣ ወደ እቶን እሳት ትጣላለች
#ሼር
╭══•:|★✧💚💛✧★|: ══╮
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
╰══•:|★✧💚💛✧★|: ══╯
+ ስሞት ዓይኔን የሚከድንልኝ ማን ይሆን? +
@Theothokos
አንድ ሁልጊዜም መማር የማይታክታቸው አባት ነበሩ:: በጣም የተማሩ ቅኔ አዋቂ መጻሕፍት የመረመሩ ሊቅ ቢሆኑም ሁሌም ከአትሮንስ ሥር የማይጠፉ ተማሪ ነበሩ:: ይህንን ልምዳቸውን ያየ አንድ ሰው "እርስዎ ብዙ የተማሩና ያነበቡ ሰው ነዎት ከዚህ በኁዋላ ማረፍ ሲገባዎት ለምን ጊዜዎን በትምህርት ያጠፋሉ?" አላቸው:: እርሳቸውም "መልአከ ሞት መጥቶ ወደ ፈጣሪ በወሰደኝ ጊዜ 'የት አግኝተህ አመጣኸው?' ሲባል ከአትሮንስ ሥር ቁጭ ብሎ የአንተን ቃል ሲሰማ አገኘሁት ብሎ እንዲነግርልኝ ነው" አሉ::
መልአከ ሞት አሁን በዚህ ሰሞን መጥቶ ቢወስድህ ምን ሲያደርግ አገኘሁት የሚል ይመስልሃል? ሲጸልይ? ሲመጸውት? ሲመርቅ? ሰዎችን በፍቅር ቃል ሲናገር? ሲያማ? ሲሳደብ? ሲያስታርቅ? ሲያጣላ? እውነትም የእኚህ አባት ጭንቀት እጅግ ተገቢ ጭንቀት ነበር::
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን "እስከ መጨረሻይቱ ሕቅታ ድረስ አንድነት ሦስትነትህን በማመን አጽናን" ብላ በቅዳሴዋ የምትጸልየው በሞት የምወሰድበት ወቅት ምናልባትም ክፉ የምንሠራበትና ፈጣሪን የምንክድበት ጊዜ እንዳይሆን ነው:: "ሽሽታችሁ በክረምትና በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ" እንዲል እንደ ክረምትና ሰንበት ሥራ አቁመን ከበጎ ምግባር በራቅንበትና በሰነፍንበት ሰዓት እንዳንሞት እንጸልያለን::
ሌላው ቅዱስ አባት ነባቤ መለኮት ቅዱስ ጎርጎርዮስ ደግሞ ከሞቱ በኃላ ስለሚከሰተው የመጀመሪያ ክስተት ሲናገር
"ስሞት ዓይኔን በጣቶቹ የሚከድልኝ ማን ይሆን?" (Who will lay his fingers upon my eyes when I die?) ብሎአል:: (On His own life 43)
ምናልባት "ስሞት ዓይኔን ማንስ ቢከድነው ምን ለውጥ አለው?" ብለን እናስብ ይሆናል:: ሆኖም የመጨረሻዋን ቅጽበት የዓይናችን መከደን ጉዳይና የሚከድነው ሰው ማንነት ትልቅ ዋጋ ያለው ነው::
እግዚአብሔር በበጎነታቸው ለወደዳቸው ቅዱሳን ከሚመርቀው ምርቃት አንዱ "ልጆችህ ዓይንህን ይከድናሉ" የሚል ነበር::
ያዕቆብን እንዲህ ሲል መረቀው
"ወደ ግብፅ አብሬህ እወርዳለሁ : ከዚያም አወጣሃለሁ
ልጅህ ዮሴፍም እጁን በዓይኖችህ ላይ ያኖራል"
ዘፍ 46:4
የምንወደውን ሰው ዓይን ከድኖ መሰናበት "ሲቀብር ይቆርጥለታል" ከሚባለው ልማዳዊ ብሂል በላይ ፍጹም ዕረፍት የሚሰጥ ስንብት ነው:: ምንም ስቃዩና ኀዘኑ ጥልቅ ቢሆንም የመጨረሻዋን ሕቅታ ሰምቶ የምንወደውን ሰው ዓይን ከድኖ የመሸኘትን ያህል የሕሊና ዕረፍት የለም::
ለአባት "ልጆችህ ዓይንህን ይከድናሉ" መባል ምርቃት የመሆኑን ያህል ለወላጆች የልጅን ዓይን መክደን ግን እጅግ ከባድ ኀዘን ነው:: ሆኖም ምንም ኀዘኑ ጥልቅ ቢሆን ልጅን ዓይን ከድኖ መሰናበት ኀዘንን የሚያቀልል ስንብት ነው:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በአንድ ልጃቸው ሞቶ በኀዘን በተሰበሩ ወላጆች ቤት ገብቶ ይህንን የማጽናኛ ቃል ተናግሮ ነበር :-
"ጻድቁ ኢዮብ የልጆቹን ዓይን ለመክደንና አፋቸውን ለመግጠም ሰውነታቸውንም ለማስተካከል እንክዋን አልታደለም ነበር:: እናንተ ግን ቢያንስ የልጃችሁን የመጨረሻ ቃል ሰምታችኃል ዓይኖቹንም ከድናችኃል አፉንም ገጥማችኃል:: እናንተ ዐሥር ልጆቹን ካጣው ኢዮብ በላይ ስለምን ታዝናላችሁ?"
ቅዱስ ጎርጎርዮስ "ዓይኔን የሚከድንልኝ ማን ይሆን?" አለ:: ይህንን አስበነው እናውቅ ይሆን? ማን እንዲሸኘን እናስብ ይሆን? ቅድስት መቅሪና ስትሞት ወንድምዋ ጎርጎርዮስ ዓይንዋን እንዲከድንላት ትመኝ ነበር:: ሆኖም በሞተችበት ዕለት ሳትሞት በፊት በወሰዳት እንቅልፍ ምክንያት ዓይንዋ ተከድኖ ነበር:: (St.Gregory of Nyssa, On the life of St Makrina)
ቅዱስ ፍላብያኖስ ዘአንጾኪያም እኅቱ ዓይንዋን እንዲከድንላት ስትመኝ ኖራ በሞተች ዕለት እርሱ ለጸሎት ወደ ቁስጥንጥንያ ሔዶ እንደነበረ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ተናግሮአል::
ለአንዳንድ ቅዱሳን ደግሞ ማን መጥቶ ዓይናቸውን እንደሚከድን አስቀድሞ ፈጣሪ ይገልጥላቸው ነበር:: ከሃያኛው ክፍለ ዘመን ቅዱሳን አንዱ የሆኑት ፓትርያርክ ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ ለአንድ ወጣት ጦቢት የሚል ቅጽል ስም አውጥተው ይጠሩት ነበር:: ለምን ጦቢት እንደሚሉት ባያውቅም ስሙን ግን አውቆ በጠሩት ቁጥር አቤት ይል ነበር:: ፓትርያርኩ በሞቱበት ዕለት ይህ ወጣት እግር ጥሎት ቀድሞ የደረሰው እርሱ ነበር:: ዓይናቸውን የከደነና አፋቸውን የገጠመው የዕረፍታቸውን ዜናም ለሌሎች ያሳወቀው ቀብሩንም ያስፈጸመው እርሱ ነበር:: ይህ ከሆነ በኁዋላ "ጦቢት" ብለው የሚጠሩበትን ምክንያት አስታውሶ መጽሐፈ ጦቢትን ሲያነብ ይህንን ጥቅስ አገኘ :-
"ጦቢትም እንዲህ አለ :- በነነዌ አደባባይ የሞተ ሰው ሳገኝ እቀብረው ነበር" ጦቢ 1:4
ጻድቁ ይህ ወጣት እንደሚቀብራቸው አውቀው ራሱን ለአደጋ አጋልጦ ድሆችን ይቀብር በነበረው በጦቢት ስም ይጠሩት ነበር::
እኔና አንተ ግን የማናውቅ ስለሆንን እንዲህ እንላለን
"ስሞት ዓይኔን የሚከድንልኝ ማን ይሆን?"
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
#ሼር
╭══•:|★✧💚💛✧★|: ══╮
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
@Theothokos @Theothokos
╰══•:|★✧💚💛✧★|: ══╯