የኢዜማ የዞን ሕ/ግ ማስተባበርያ
4 subscribers
3 photos
1 video
1 link
እኛም ጉዟችን ቀጥለናል
Download Telegram
Taddy CR Adis Abeba:
የኢዜማ ጋሞና አካባቢው ማስተባበሪያ ዞን ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን አደረገ።

ዛሬ ረቡዕ ጥቅምት 23/2015 ዓ.ም  ዞን ማስተባበሪያ ምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ የአርባ ምንጭ፣ የብርብር ልዩ፣ የካምባ፣ የቦንኬ-ገረሴ፣ የጨንቻ፣ የዳራማሎ፣ የኧሌ የዲራሼ ልዩ፣ የጊዶሌ መደበኛ እና ቁጫ ምርጫ ክልሎች በተወካዮቻቸው አማካይነት ተሳትፈዋል።

በውይይቱ ላይ በቀጣይ የኢዜማ የሥራ ተልዕኮዎች ላይ ዝርዝር መረጃ በማቅረብ ጥልቅ ውይይት አድርጓል።

የዞኑ ማስተባበሪያ ምክር ቤት በቀጣይ ጠንካራ አደረጃጀት የሚፈጠርበትን መንገድ በመዘርዘር አዲስ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መርጦ አስፀድቋል።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በኢትዮጵያ መንግስት እና ሕወሓት መካካል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ
የሰላም ስምምነቱ መርህ በተከተለ መልኩ ለመፈራረም መብቃቱ ይበል የሚያሰኝ መልካም ጅማሮ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፤ ለተግባራዊነቱም ባለድርሻ አካላት ሁሉ ፍጹም ታማኝ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መስረከም 03/2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በግልጽ እንዳስቀመጠው
‹‹ እንደ ኢዜማ እምነት ዘላቂ ሰላም ማምጣት እንዲቻል የክህደት በሮች ሁሉ መዘጋታቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ከዚህም አንዱና ዋነኛው የሀገርን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ለማስከበር ትጥቅ ይዞ የሚንቀሳቀስን ኃይል የማዘዝ ሥልጣን ሊኖረው የሚገባው የፌደራል መንግሥት ብቻ ስለመሆኑ ሀገራዊም ሆነ ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን አስረግጦ በማስገንዘብ ህወሓት ትጥቁን እንዲፈታ ሊደረግ ይገባል፡፡
እኛ ሰላምን የምንናፍቀው ለአጭር ግዜ መፍትሔነት ሳይሆን በዘላቂነት ነው፤ ዘላቂ ሰላም ደግሞ መረጋገጥ የሚችለው የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ፍፁም ጥያቄ ውስጥ ሳይገባ መሆን አለበት። ስለሆነም በየትኛውም ክልል ውስጥ የሚገኙ የፌደራል ተቋማትንም ሆኑ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር የመጠበቅና የአየር ክልሉን ሙሉ ለሙሉ  የመቆጣጠር ሥልጣን በብቸኝነት የፌደራል መንግሥቱ መሆኑን ህወሓትም ሊገነዘበው፤ መንግሥትም ሊዘነጋው አይገባም፡፡››
በመሆኑም ይህን መርህ በተከተለ መልኩ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ይበል የሚያሰኝ ሲሆን መንግስት የተደረገው ስምምነት እንዳይጨናገፍ እና ተመልሰን የጦርነት አዙሪት ውስጥ እንዳንገባ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ለተግባራዊነቱም ሁሉም አካል በትጋት መስራት የሚጠበቅበት ሲሆን በሌሎች የሀገሪቷ ክፍሎች ያሉ የታጠቁ ሀይሎችም ጋር በሰላማዊ ንግግር መፍትሔ የሚያገኝበት መንገድ ላይ በአፅንኦት መስራት ያስፈልጋል፡፡
ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ በሚል መርህ የአፍሪካ ህብረት ይህ የሰላም ስምምነት እንዲፈርም ያሳየውን ጥረት እያደነቅን ተግባራዊነቱንም ለማረጋገጥ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ ተስፋ እንደርጋለን፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 24/2015 ዓ.ም.

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
የኢዜማ ጋሞና አካባቢው ማስተባበሪያ ዞን ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን አደረገ።

ዛሬ ረቡዕ ጥቅምት 23/2015 ዓ.ም ዞን ማስተባበሪያ ምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ የአርባ ምንጭ፣ የብርብር ልዩ፣ የካምባ፣ የቦንኬ-ገረሴ፣ የጨንቻ፣ የዳራማሎ፣ የኧሌ የዲራሼ ልዩ፣ የጊዶሌ መደበኛ እና ቁጫ ምርጫ ክልሎች በተወካዮቻቸው አማካይነት ተሳትፈዋል።

በውይይቱ ላይ በቀጣይ የኢዜማ የሥራ ተልዕኮዎች ላይ ዝርዝር መረጃ በማቅረብ ጥልቅ ውይይት አድርጓል።

የዞኑ ማስተባበሪያ ምክር ቤት በቀጣይ ጠንካራ አደረጃጀት የሚፈጠርበትን መንገድ በመዘርዘር አዲስ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መርጦ አስፀድቋል።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በሀገራችን ኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች ውስጠ ዴሞክራሲ ስርዓት ምሳሌ ሆኖ ያለፈውን ጠቅላላ ጉባኤ ምርጫ ቦርድ አፀደቀ።

ሰኔ 25 እና 26 2014 ዓ.ም በተደረገው ጉባኤ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ምርጫ  የብዙሃኑን ትኩረት የሳበ እንደነበረ የሚዘነጋ አይደለም።

ፓርቲያችን ኢዜማ ይህን አርአያ የሆነ ጉባኤ ለማዘጋጀት የደከሙትን አባላቱን ሁሉ እያመሰገነ በቀጣይም እንደ ሀገር ያለበትን ሀላፊነት በቅጡ በመረዳት በሰከነ መንገድ ኢትዮጵያን በማስቀደም እንደሚንቀሳቀስ ለማሳወቅ ይወዳል።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በዞኑ የሚገኙ የምርጫ ክልሎችን የሚያስተባብሩ፣ የሚከታተሉ እና የሚያቀናጁ የዞን ማስተባበርያ ምክር ቤቶች ውይይት በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ጥቅምት 26 እና 27/ 2015 ዓ.ም. አድርጓል።

የኢዜማ ጉራጌ፣ ደቡብ ጎንደር፣ ድሬዳዋ ከተማና የሐረሪ ክልል፣ ስልጢ ሀላባ፣ የጎንደር ከተማ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማስተባበሪያ ምክር ቤቶች ባደረጉት ስብሰባዎች በዋነኛነት የምክር ቤቶቹን እና በውስጣቸው የሚገኙ የምርጫ ክልሎች መዋቅር ቁመና ገምግመዋል እንዲሁም የምክር ቤቶቹ ስራ አስፈፃሚዎች የስራ ሪፖርት አቅርበዋል።

ውይይቶቹ የዞን ምክር ቤቶቹ ቀጣይ ዕቅዶች ላይ፣ ወቅታዊ የሀገሪቱን እና የአከባቢያዊ ሁኔታ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገ ሲሆን ፓርቲው በጉዳዮቹ ሊኖረው ስለሚገባው ሚና ስምምነት ላይ ተደርሷል።

በመጨረሻም የተጓደሉ የሥራ አስፈፃሚ ያለባቸው ምክር ቤቶችን እንዲሟሉ በማድረግ ተጠናቀዋል።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
1) የኢዜማ ሴቶች መምሪያ ሐላፊ ቅድስት ግርማ ከማንነት ጋር የሚደርሱ ጥቃቶች፤ ከህወሃት ጋር ይደረጋል ስለሚባለው ድርድር እና ወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከየኛ ቲቪ ጋር ያደረገችው ቆይታን ይመልከቱ https://youtu.be/RKOvJm0JKKw

2) የኢዜማ ሀገራዊ ምክክር ኮሚቴ ሰብሳቢ እዮብ መሣፍንት ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ የኢፌዴሪ የፕሬዝዳንት ፓርላማ ንግግርን አስመልክቶ ከፋና ራዲዮ ጋር ያደረጉትኔ ቆይታ ያድምጡ
https://www.fanabc.com/%E1%8B%9C%E1%8A%93-%E1%8B%AB%E1%8B%B0%E1%88%9D%E1%8C%A1/

3) የኢዜማ ሀገራዊ ምክክር ኮሚቴ ሰብሳቢ እዮብ መሣፍንት ከሀገራዊ ምክክሩ ጋር በተያያዘ  ከፋና ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ
https://youtu.be/v3XY_oTP38M

4) የኢዜማ አካል ጉዳተኞች መምሪያ ሐላፊ ማዕረጉ ግርማ በሀገራዊ ምክክሩ ዙርያ ከአሻም ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ
https://youtu.be/OcKzV9HBCRc

5) የኢዜማ ምክትል መሪ ዮሐንስ መኮንን በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ስላለው ጦርነት ዙርያ ከ FM 97.1 ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ  https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=471448954959562&id=100063770933024

6) የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሐላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ስላለው ጦርነት ዙርያ ከ ፋና ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ
https://youtu.be/kI9mddLL_ew

7) የኢዜማ ዋና ጸሐፊ አበበ አካሉ በተለያዩ አከባቢዎች ያሉ ታጣቂ ሀይሎችን በተለይም ኦነግ ሸኔን አስመልክቶ ከ FM 107.8 ላይ ያደረጉት ቆይታ ያድምጡ
https://drive.google.com/file/d/1I7POeSFGdEgDUAgUVDs7WyoIgYw1ikxC/view?usp=drivesdk

8) የኢዜማ ድርጅት ጉዳይ መምሪያ ሐላፊ ዋስይሁን ተስፋዬ የወጪ ሀገራት ጣልቃገብነት በኢትዮጵያ ላይ በሚል ርዕስ ዙርያ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ያደረጉትን ቆይታ ያንብቡ
https://drive.google.com/file/d/1H3USHhg00z_sfI2egtw0YOGZ9O718rov/view?usp=drivesdk

9) የኢዜማ ዋና ጸሐፊ አበበ አካሉ መንግስት እና ሕወሓት ሊያደርጉት ነው በተባለው ድርድር ዙሪያ ከ ኢሳት ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ
https://www.youtube.com/watch?v=c6om0vLW1uU

10) የኢዜማ ዋና ጸሐፊ አበበ አካሉ መንግስት አሁን ያለውን የጸጥታ ሁኔታ መመለስ ከቻለ ቀጣይ የፓርቲው የፖለቲካ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ከኢሳት ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ
https://www.youtube.com/watch?v=mI06ZbTlGfQ

11) የኢዜማ አካል ጉዳተኞች መምሪያ ሐላፊ መንግስት ከሕወሓት ጋር ሊያደርገው ነው በተባለው ድርድር ዙርያ ከአዲስ ዘይቤ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ
https://youtu.be/1_wEq4mRiLg

12) የኢዜማ ድርጅት ጉዳይ መምሪያ ሐላፊ ዋስይሁን ተስፋዬ በመንግስት እና ሕወሓት መካከል ተደረሰ ስለተባለው ስምምነት ከ FM 107.8 ጋር ያደረጉትን ቆይታ ያድምጡ
https://drive.google.com/file/d/1I9VfpsJbtIEABbTGQ08Q6BvnStaXupMj/view?usp=drivesdk

13) ኢዜማ መንግስት ከሕወሓት ጋር ደረሰበት ስለተባለው ስምምነት ያወጣው መግለጫ ይመልከቱ
https://www.youtube.com/watch?v=Jg2VgN-Ctjk

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ