Star Tech PLC
3.37K subscribers
79 photos
8 videos
26 files
41 links
Star Tech Solution
https://startechplc.com
Download Telegram
👉ስታር ቴክ ሶልሽን

------ ስልጠናዎች ------

🔷 እንግሊዝኛ ቋንቋ
🔷 የኮምፒውተር ስልጠና
🔷 ግራፊክስ ዲዛይን
🔷  ቪዲዮ ኤዴቲንግ
🔷 ፕሮግራሚንግ
🔷 ዌብሳይት ማበልፀግ
🔷 ዳታቤዝ ማኔጅመንት
🔷 ፒችትሪ አካውንቲንግ
🔷 ሶሻል ሚዲያ ማርኬቲንግ
------
📞 +251910780208
📞 +251910780608

ካታች ባለው link መመዝገብ ይችላሉ ።
👉 https://forms.gle/wz8pS2s9Wmvc7cRU8
👉
📌www.star-tech-solution.com
1
ስታር ቴክ
የብቃት ልክ!
4
+251910780208
+251910780608
2
የስራ ማስታወቂያ

1. ጀማሪ አካውንታንት  I

⭐️ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ በየትኛውም የትምህርት መስክ ቢያንስ ዲፕሎማ ያለው/ት ወይም

⭐️ በአካውንቲንግ ደረጃ IV CoC ያለው/ት እና የስራ ልምድ ማቅረብ የምትችል።

• ሁሉም እጩ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በፊት የሰሩትን ስራዎች እንዲሁም የስራ ልምዳቸውን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

 📌 ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ ቀናት ውስጥ የትምህርት ማስረጃ ስካን አድርገው ወይም ፎቶ አንስተው በ @star_tech_center ላይ በቴሌግራም በመላክ ወይም በኢሜል አድራሻችን info@star-tech-solution.com በመላክ መመዝገብ ይችላሉ።

Star Tech Training Institute
📌Endashaw Haile
📌endash.haile@gmail.com
📞+251910780208

ፀጋዬ ህንፃ 3ተኛ ፎቅ - ስታር ቴክ - 301
ይህ በፎቶው ላይ የሚታየው ሰው ሀዋርድ ሹልዝ ይባላል ። ዛሬ ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ ከ 41 ሺህ በላይ የቡና መሸጫ ካፌዎችና ፡ በስሩ ከአራት መቶሺህ በላይ ሰራተኞችን የሚያስተዳድረው የግዙፉ ካምፓኒ የስታር ባክስ ባለቤት ነው ።
.......
እና ይህ ሁሉ በቢሊየን ዶላሮች የሚቆጠር ሀብትና. . ታዋቂነት ከመምጣቱ በፊት ወጣት ሳለ የኮሌጅ ትምህርቱን የጨረሰው ፡ በካፌና በባር ውስጥ መስተንግዶና ፅዳት እየሰራ ነበር ። ይህ ብቻ አይደለም ፡ በግንባታ ቦታዎች የቀን ሰራተኛ ነበር ... ትላልቅ የዛፍ ግንዶችን እየተሸከመ መኪና ላይ የመጫን ስራም ሰርቷል ።
.......
ይሄ ቀላል ነው ፡ ሀዋርድ ሹልዝ አንድ ጊዜ በOprah’s Master Class ላይ እንግዳ ሆኖ ቀርቦ ፡ ስለመጣበት የህይወት መንገድ ፡ ስላሳለፈው አስቸጋሪ ጊዜያት ሲናገር ፡ ሚቺጋን ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረበት ጊዜ አንዳንዴ ስራ ጠፍቶ ለምግብ መግዣ እንኳን የሚሆን ገንዘብ ሲያጣ ደም ወደሚፈልጉ ክሊኒኮች እየሄደ ፡ በተደጋጋሚ ደሙን ሽጦ ፡ ምግብ ገዝቷል ።
ሀዋርድ ሹልዝ ይህን ነገር አንዴ ሁለቴ አይደለም ። ስራ ሲጠፋ እና በቸገረው ቁጥር በተደጋጋሚ አድርጎታል ።
....
በዚህ አይነት እጅግ አስቸጋሪ የህይወት ውጣ ውረድ ተጉዞ ፡ ተስፋ መቁረጥ የሚባል ነገር ጫፉ ሳይደርስ ደሙን ሽጦ ዳቦ እየገዛ ህይወትን አሸንፎ ያሾፈባት የስታርባክሱ ጌታ ሀዋርድ ሹልዝ .. ዛሬ ላይ ከ3.5 ቢሊየን ዶላር በላይ ሀብት ያለው ቱጃር ሆኗል ።
2
ስኮላር ሺፕ በእንግሊዝ

🇬🇧 ሙሉ ወጪው የተሸፈነ የ AI ስኮላርሺፕ በእንግሊዝ! (University of Edinburgh - Spärck AI)
​የእንግሊዝ መንግስት ከ University of Edinburgh ጋር በመተባበር፣ ለ2026 የትምህርት ዘመን በ AI ዘርፍ ለማስተርስ (Master’s) ተማሪዎች ሙሉ ስኮላርሺፕ አቅርቧል።

​ይህ "Spärck AI Scholarship Programme" የሚባለው እድል፣ የነገው የቴክኖሎጂ መሪዎችን ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
​ -ምን ምን ጥቅሞች አሉት? (Fully Funded Benefits):
የትምህርት ክፍያ (Tuition Fee): ሙሉ ለሙሉ ይሸፈናል።
ወርሃዊ ደሞዝ (Living Stipend): ትምህርታችሁን እስክትጨርሱ ድረስ ለኑሮ የሚሆን በቂ ገንዘብ ይሰጣችኋል።
የስራ እድል: ከትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር የስራ ልምድ (Internship) እና የኔትዎርኪንግ እድል ይመቻችላችኋል።
​ -ለየትኞቹ ዘርፎች? (Eligible Programmes):
ለዚህ ስኮላርሺፕ ለመወዳደር ከሚከተሉት በአንዱ ማመልከት ይጠበቅባችኋል፡
​MSc Artificial Intelligence
​MSc Data Science
​MSc Cognitive Science

📅 የማመልከቻ ጊዜ:

​Deadline: March 2, 2026 (እስከ የካቲት 23)።
​ማሳሰቢያ: ለስኮላርሺፑ ከማመልከትዎ በፊት ወይም ጎን ለጎን ለትምህርቱ (Admission) ማመልከት ግዴታ ነው።

🔗 ሙሉ መረጃውን ለማየት እና ለማመልከት:
👇👇👇
https://informatics.ed.ac.uk/study-with-us/our-degrees/postgraduate-taught/sparck-ai-scholarship-programme?fbclid=IwY2xjawPwSIRleHRuA2FlbQIxMABicmlkETFxdmVZTnI2Vk54R2h6STFGc3J0YwZhcHBfaWQQMjIyMDM5MTc4ODIwMDg5MgABHmM53NQFwotP7FjzLcZYPvna_zXxImQ1mNHf5nywZpLwVP3obsXuajWHnohm_aem_ky9FD5XexTGdGM_3bZto8g
👍3
ኑ አብረን እንሞክር!
🇦🇪 በነፃ ትምህርት + ወርሃዊ ደሞዝ! (UAE University Scholarship 2026)
*
በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (UAE) ቀዳሚ የሆነው United Arab Emirates University (UAEU) ለ2026 የማስተርስ (Master’s) እና የዶክትሬት (PhD) ተማሪዎች ሙሉ ስኮላርሺፕ አቅርቧል።

ይህ እድል ለትምህርት ክፍያ ብቻ ሳይሆን፣ ለተማሪዎች የኑሮ ድጋፍ ጭምር የሚሰጥ ነው።

🎁 ምን ምን ጥቅሞች አሉት? (Fully Funded Benefits):
የትምህርት ክፍያ: 100% ነፃ (Tuition Waiver)።
ወርሃዊ ደሞዝ (Monthly Stipend): ለኑሮ ወጪ የሚሆን ገንዘብ ይሰጣል።
መኖሪያ ቤት (Housing): በግቢ ውስጥ መኖሪያ ወይም የቤት አበል ይሰጣል።
የጤና ኢንሹራንስ: ሙሉ የህክምና ሽፋን።
የስራ እድል (Assistantships): እየተማራችሁ በምርምር ወይም በማስተማር ስራ (GRA/GTA) ተጨማሪ ገቢ የምታገኙበት እድል አለው።

🎓 ለማን ነው?
ለማስተርስ እና ለዶክትሬት ዲግሪ አመልካቾች።
በምርምር (Research) ላይ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች።

📅 የማመልከቻ ጊዜ: አብዛኛው ማመልከቻ በ March – April (መጋቢት/ሚያዚያ) ስለሚዘጋ፣ አሁኑኑ ዶክመንት አዘጋጅቶ መጠበቅ ወይም ማመልከት ያስፈልጋል።

🔗 🔗 ለመመዝገብ እና ዝርዝሩን ለማየት: 👇👇👇 https://lnkd.in/d8WDBt8M

hashtag#StudyInUAE hashtag#UAEU hashtag#Scholarship2026 hashtag#FullyFunded hashtag#Masters hashtag#PhD hashtag#Ethiopia hashtag#ResearchOpportunity
👍5
የቴሌግራም Update ምን ምን ይዟል!?

የካቲት 2026 የቴሌግራም አዲስ ስሪት (Update) በርካታ ጠቃሚ ለውጦችን ይዞ መጥቷል።
1. የአንድሮይድ ዲዛይን ለውጥ (Liquid Glass Redesign)
በዚህ አፕዴት ትልቁ ለውጥ የተደረገው በአንድሮይድ ስልኮች ላይ ነው። ቀደም ሲል በግራ በኩል የነበረው ሶስት ሰረዝ (Hamburger Menu) ተነስቶ፣ አፑ ልክ እንደ አይፎን (iOS) በታችኛው ክፍል አራት አማራጮችን ይዞ መጥቷል፦
📌Chats
📌Contacts
📌Settings
📌Profile (ፕሮፋይል) አፑ የጠራና ግልጽ (Transparent) የሆነ የ"Liquid Glass" ገጽታ እንዲኖረው ተደርጎ ተስተካክሏል።
2. የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI Summaries) አለው።
3. ፓስኪይ (Passkeys)
በስልክህ የጣት አሻራ (Fingerprint) ወይም (Face ID) ብቻ በፍጥነት መግባት ይቻላል ።
4. ለሁሉም ክፍት የሆኑ ስቶሪዎች (Stories for Everyone)
(Live Stream) እያደረግክ ከሰዎች ጋር መወያየት የሚያስችል አማራጭ ተጨምሯል።
5. ሌሎች አዳዲስ ገፅታዎች
Profile Music፦ በፕሮፋይልህ ላይ የምትወደውን ሙዚቃ ወይም ድምጽ መጫን ትችላለህ፤ ሰዎች ፕሮፋይልህን ሲያዩት ያንን ድምጽ መስማት ይችላሉ።
Contact Notes፦ ስለ አንዱ ሰው መርሳት የሌለብህ ማስታወሻ ካለህ፣ በሰውየው ፕሮፋይል ስር አንተ ብቻ የምታየውን ማስታወሻ መጻፍ ትችላለህ።
3
የኮምፒውተር ፍጥነት ለመጨመር ምን እንዳርግ? ሶስት ቀላል መንገድ

ኮምፒውተርህ እየተንቀራፈፈ ካስቸገረህ  ፍጥነት ለመጨመር የሚከተሉትን ቀላልና ውጤታማ መንገዶች ተጠቀም፦
1. የሶፍትዌር ማስተካከያዎች (Software Fixes)
መጀመሪያ የሚከፈቱ ፕሮግራሞችን (Startup Apps) መቀነስ፦ ኮምፒውተርህ ሲበራ አብረው የሚከፈቱ ፕሮግራሞችን መቆጣጠር ።
Ctrl + Shift + Esc ተጫን -> Startup የሚለውን ተጫን -> የማትፈልጋቸውን ፕሮግራሞች Disable አድርግ።
2.የማትጠቀስባቸውን አፕሊኬሽኖች ማጥፋት (Uninstall) አድርግ፦ በኮምፒውተርህ ላይ ተጭነው ምንም የማትጠቀምባቸውን አፖች በማጥፋት ቦታና 'RAM' ቆጥብ።
3.Disk Cleanup መጠቀም፦ ዊንዶውስ ውስጥ "Disk Cleanup" ብለህ ፈልግና አላስፈላጊ የሆኑ ጊዜያዊ ፋይሎችን (Temporary files) አጽዳ።
📌ዊንዶውስን ማሻሻል (Update)፦ መሆኑን አረጋገጥ።
4
🚀 የ AI ጥቆማዎች እና የፕሮምፕት (Prompt) ጥበብ!!
ባለፉት ቀናት ስለ AI ምንነት እና አይነቶች አይተናል። ዛሬ ደግሞ የትኞቹን የ AI መሣሪያዎች ለምን እንደምንጠቀም እና እነዚህን መሣሪያዎች እንዴት በብቃት ማዘዝ (Prompting) እንደምንችል እንመለከታለን!
📌 በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉ የ AI አይነቶች (Tools)
ለጽሑፍ እና ለዕውቀት ፈለጋ (Chatbots):

ChatGPT: ለጽሑፍ ዝግጅት፣ ለትርጉም እና ለጥያቄዎች መልስ ለማግኘት።

Google Gemini: ወቅታዊ መረጃዎችን ከ Google ጋር በማቀናጀት ለመፈለግ
Claude: ረጅም ጽሑፎችን ለማጠቃለል ብሎም የፈጠራ ጽሑፎችን ለመጻፍ ምርጥ ነው።

ለምስል ፈጠራ (Image Generation):

Midjourney: ጥራት ያላቸው እና ጥበባዊ ምስሎችን ለመፍጠር።

DALL-E 3: በቃላት የምንሰጠውን ትዕዛዝ በትክክል ወደ ምስል ለመቀየር።

Canva AI: ለሶሻል ሚዲያ የሚሆኑ ዲዛይኖችን በፍጥነት ለመሥራት።

ለቪዲዮ እና ለድምጽ:

HeyGen: ሰው ሰራሽ አምባሳደሮችን (Avatars) በመጠቀም ቪዲዮ ለመሥራት።

ElevenLabs: ጽሑፍን ወደ ተፈጥሯዊ የሰው ድምጽ ለመቀየር።

✍️ ውጤታማ "ፕሮምፕት" (Prompt) የመጻፍ ሚስጥር
Prompt ማለት ለ AI የምንሰጠው ትዕዛዝ ወይም መመሪያ ነው። ትዕዛዛችን ግልጽ ከሆነ ውጤቱ አስገራሚ ይሆናል። እነዚህን 3 ነጥቦች ያስታውሱ፡

ሚና መስጠት (Assign a Role): "እንደ ፕሮፌሽናል ማርኬቲንግ ባለሙያ ሆነህ..." ወይም "እንደ አማርኛ ቋንቋ መምህር ሆነህ..." ብሎ መጀመር።
ግልጽ መመሪያ መስጠት (Specific Instruction): "ስለ ጤና ጻፍ" ከማለት ይልቅ "ስለ ጠዋት ስፖርት ጥቅም 5 ነጥቦችን በዝርዝር ጻፍልኝ" ማለት ይሻላል።
ሁኔታውን ይግለጹ (Context): ጽሑፉ ለማን እንደታሰበ (ለተማሪ? ለሥራ ባልደረባ?) ይግለጹለት።
ምሳሌ፦ መጥፎ ፕሮምፕት: "ስለ ቡና ንገረኝ።" ጥሩ ፕሮምፕት: "እንደ ታሪክ ተመራማሪ ሁነህ፣ የኢትዮጵያ ቡና ለአለም ዙሪያ እንዴት እንደተሰራጨ የሚገልጽ አጭር እና ማራኪ ጽሑፍ ጻፍልኝ።"


📌 የዛሬው ተግባር:
ከላይ ከተጠቀሱት የ AI መሣሪያዎች አንዱን በመጠቀም (ለምሳሌ ChatGPT) የፈለጉትን ጥያቄ በጥሩ "ፕሮምፕት" ይጠይቁና ውጤቱን ይመልከቱ!
5
የሶሻል ሚዲያ ግራፊክስ ዲዛይን በቀላሉ!
የሶሻል ሚዲያ ገጾች የሰዎችን ትኩረት እንዲስቡ ይፈልጋሉ? የግድ ፕሮፌሽናል ዲዛይነር መሆን ወይም ውድ ኮምፒውተር መያዝ አይጠበቅብዎትም! በስልክዎ ወይም በቀላሉ በሚገኙ ድረ-ገጾች ምርጥ ዲዛይኖችን መስራት ይችላሉ።

ዲዛይንዎን ለማሳመር እነዚህን 3 ነጥቦች ያስተውሉ፦
ቀለል ያድርጉት (Keep it Simple): ብዙ ጽሁፍ እና ምስል በአንድ ላይ አያጨናንቁ። መልዕክትዎ በግልጽ እንዲታይ ክፍት ቦታ (White Space) ይተው።

ጥራት ያላቸው ምስሎችን ይጠቀሙ: የደበዘዙ ምስሎች የገጽዎን ተአማኒነት ይቀንሳሉ። እንደ Pexels ወይም Unsplash ያሉ ድረ-ገጾችን ለጥራት ያላቸው ምስሎች ይጠቀሙ።

የቀለም ምርጫ፦ ከሁለት ወይም ከሶስት በላይ ቀለሞችን ባይጠቀሙ ይመረጣል። የምርትዎ መለያ (Brand) ቀለሞች ላይ ትኩረት ያድርጉ።

🚀 ለመስራት የሚረዱዎት ምርጥ አፕሊኬሽኖች፦
Canva: ለጀማሪዎችም ለባለሙያዎችም ቁጥር 1 ምርጫ! (Templates በብዛት አሉት)
Pixellab: በአማርኛ ጽሁፎች ላይ ለሚሰሩ ምርጥ እና ቀላል የስልክ አፕ ነው።
Adobe Express: ፈጣን እና ዘመናዊ ዲዛይኖችን ለመስራት።
-----
ጠቃሚ ምክር፦ ዲዛይን ከመጀመርዎ በፊት "ምን አይነት ስሜት እንዲፈጥር እፈልጋለሁ?" የሚለውን ይወስኑ። ሰላማዊ፣ ደማቅ ወይንስ ቁምነገር አዘል?
የዲዛይን ችሎታዎን ዛሬውኑ መለማመድ ይጀምሩ! 💡
#GraphicsDesign #SocialMediaTips #Ethiopia #DesignThinking #TechEthio

የግሪፊክስ ባለሙያ ለመሆን የሚያስፈልጉን ሶፍትዌሮች፦
📌 አዶቤ ፎቶሾፕ
📌 አዶቤ ኢሊስትሬተር
📌 አዶቤ ኢንዲዛይን
📌 አፊኒቲ
1
እነዚህን ቻናሎች ማወቅ የግድ ነው። በተለየ ለተማሪዎች !!
1. ቴድ-ኢድ (TED-Ed):
→ ተመዝጋቢዎች: 20.4 ሚሊዮን
→ ይዘት: በተለያዩ መስኮች ውስብስብ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚዳስሱ አኒሜሽን ያላቸው የትምህርት ቪዲዮዎችን ያቀርባል።

2.ቪሳውዝ (Vsauce):
→ ተመዝጋቢዎች: 22.7 ሚሊዮን
→ ይዘት: ሳይንሳዊ እና ፍልስፍናዊ ጥያቄዎችን በጥልቀት በመመርመር ትምህርትን አስደሳች እና አስተማሪ ያደርገዋል።

3.ቬሪታሲየም (Veritasium):
→ ተመዝጋቢዎች: 16.2 ሚሊዮን
→ ይዘት: በሙከራዎች እና ከባለሙያዎች ጋር በተደረጉ ቃለ ምልልሶች የሳይንስ እና የምህንድስና ጽንሰ-ሀሳቦችን ላይ ያተኩራል።

4.ስማርተርኤቭሪዴይ (SmarterEveryDay):
→ ተመዝጋቢዎች: 11.6 ሚሊዮን
→ ይዘት: ስለ ዓለም ያለንን ጉጉት የሚያበረታቱ ሳይንሳዊ ፍለጋዎችን እና ሙከራዎችን ያቀርባል።

5.ሚኒትፊዚክስ (MinutePhysics):
→ ተመዝጋቢዎች: 5.8 ሚሊዮን
→ ይዘት: ውስብስብ የፊዚክስ ጽንሰ-ሀሳቦችን በአጫጭር አኒሜሽን ቪዲዮዎች ያቃልላል።

6.ሳይሾው (SciShow):
→ ተመዝጋቢዎች: 8.03 ሚሊዮን
→ ይዘት: ሳይንስን አስደሳች እና አሳታፊ በማድረግ ሰፊ የሳይንስ ርዕሰ ጉዳዮችን በቀላሉ በሚረዳ መንገድ ይሸፍናል።

7.አሳፕሳይንስ (AsapSCIENCE)
አሳፕሳይንስ ከባዮሎጂ እና ኬሚስትሪ አንስቶ እስከ ስነ-ልቦና እና ፊዚክስ ድረስ የተለያዩ ሳይንሳዊ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚሸፍኑ ሰፋ ያሉ ቪዲዮዎችን በማቅረብ በዩቲዩብ ላይ ምርጡን የትምህርት ይዘት ያቀርባል።"
⚡️ የመረጡትን ተቀላቅለው እውቀትን ይሸምቱ!
4👍2
👍3
2
👉ስታር ቴክ ሶልሽን

------ ስልጠናዎች ------

🔷 እንግሊዝኛ ቋንቋ
🔷 የኮምፒውተር ስልጠና
🔷 ግራፊክስ ዲዛይን
🔷  ቪዲዮ ኤዴቲንግ
🔷 ፕሮግራሚንግ
🔷 ዌብሳይት ማበልፀግ
🔷 ዳታቤዝ ማኔጅመንት
🔷 ፒችትሪ አካውንቲንግ
🔷 ሶሻል ሚዲያ ማርኬቲንግ
------
📞 +251910780208
📞 +251931553044

ካታች ባለው link መመዝገብ ይችላሉ ።
👉 https://forms.gle/wz8pS2s9Wmvc7cRU8
👉 
📌www.star-tech-solution.com
🌟 ልጆን በክረምት እኛ ጋር ያሰልጥኑ! 🌟
✴️ ስታር ቴክ የስልጠና ተቋም ✴️
(Star Tech Training Institute)

🚀 የክረምት ስልጠናዎች 
🔹 የቋንቋ ስልጠና
🔹 የኮምፒውተር መሰረታዊ ስልጠና
🔹 ማይክሮሶፍት ፓኬጅ
🔹(Word, Excel, PowerPoint)
🔹 ኤ.አይ (AI) ስልጠና
🔹 ግራፊክስ ዲዛይን
🔹 ቪዲዮ ኤዲቲንግ
🔹 ዳታቤዝ ማኔጅመንት
🔹 ፒችትሪ አካውንቲንግ
🔹 ሶሻል ሚዲያ ማርኬቲንግ
🔹 ፕሮግራሚንግ
🔹 ዌብሳይት ማበልፀግ

👨‍🏫 ልምድ ያዳበሩ መምህራን የሚያቀርቡት ስልጠና፣
👨‍🏫 በትክክለኛ ስፍራ፥ በስነ ምግባር ይታነፃሉ።
🎯 ይምጡ፣ ይማሩ፣ ብቁ ይሁኑ!

---

🎁 ልዩ ቅናሽም አለን:

🏆 ከፍተኛ ውጤት ለሚያመጡ ምርጥ ሽልማት አለን::
በተደራጀ ላብራቶሪ
ኦንላይን ፈተና የሚለማመዱበት
ብቁ እና ምርጥ አሰልጣኞች ያሉት

---

📞 ለመመዝገብ አሁን ይደውሉ፦
📱 0910780208
📱 0931553044

አድራሻ - ሻሸመኔ ፀጋዬ ህንፃ 3ተኛ ፎቅ -301

https://t.me/StarTechSoftware
https://www.facebook.com/share/1D7aGqVGMq/

📍 ስታር ቴክ፤ የብቃት ልክ!