Amhara Region Supreme Court
3.11K subscribers
1.59K photos
5 videos
14 files
198 links
Download Telegram
የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2019 በጀት ዓመት መደበኛ ሥራውን ልዩ ልዩ መረሃግብሮችን በማካሄድ ጀመረ

ባሕር ዳር ፣ ጥቅምት 9/2019 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የ2019 በጀት ዓመት መደበኛ የችሎት አገልግሎቱን በይፋ የጀመረው የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ በስራ ማስጀመሪያ መረሃግብሩ፣ በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዳኞች፣ ሠራተኞች፣ ወረዳ ፍርድ ቤቶችና አጋር አካላት የእውቅና መርሃ ግብር አካሂዷል።

ፍርድ ቤቱ የ2019 በጀት ዓመት መደበኛ ሥራውን በድምቀት ባስጀመረበት መርሃ ግብር ላይ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ዮሐንስ ወንድሙና ሌሎች የዞኑ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

አቶ ዮሐንስ ወንድሙ በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ መረሃግብሩ የተሰናዳው፣ ፍርድ ቤቶች በዳኞች የክረምት ዕረፍት ምክንያት በከፊል ዝግ ሆነው ውስን ሥራዎችን ሲያከናውኑ ከቆዩ በኋላ ከጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውን በይፋ ለማሳወቅ እንደሆነ ገልጸዋል።
ለዝርዝሩ
https://www.facebook.com/share/p/1QBotHLMQA/
👍6❤1
የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2018 በጀት ዓመት የመዝገብ አፈጻጸሙ ከ 83 በመቶ በላይ መሆኑን ገለጸ

ባሕር ዳር፣ ጥቅምት 9/2019(የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ይህንን ያስታወቀው፣ የ2019 በጀት ዓመት ይፋዊ የችሎት ማስጀመሪያ መረሃግብር ባካሄደበት መድረክ በቀረበው የ2018 በጀት ዓመት የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የአፈጻጸም ሪፖርት ነው።

ፍርድ ቤቱ የ2019 በጀት ዓመት መደበኛ የችሎት ሥራ ማስጀመሪያ፣ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ለአጋር አካላት የማስተዋወቅ መድረክ አካሂዷል።

የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ታደሰ አማረ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ የፍትሕ ሥርዓቱን በመጠበቅ በአዲስ መንፈስና ብርታት ወደ ሥራ በመግባት ማኅበረሰቡን በታማኝነት ማገልገል እንደሚገባ ገልጸዋል።

በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ገበየ ሃይሌ (ዶ.ር) በበኩላቸው፣ የፍትሕ ተቋማት የሕግ የበላይነትን ማስከበርንና ሥርዓት አልበኝነት እንዳይስፋፋ መከላከልን እንደ ቀዳሚ ተግባር በመውሰድ መሥራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ሕብረተሰቡ ለሕግ ያለው አመለካከት እንዳይቀንስ፣ የፍትሕ ተቋማት ቀልጣፋና ታማኝነት የተላበሰ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
ለዝርዝሩ
https://www.facebook.com/share/p/1CqKQA2AJ7/
👍8❤3
የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይከታተሉ።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና በስሩ ያሉ ፍርድ ቤቶችን የተመለከቱ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የጠቅላይ ፍርድ ቤታችንን የማሕበራዊ ትስስር ገጾች ይከታተሉ።

ይፋዊ የማሕበራዊ ትስስር ገጾቻችን👇

👉 Facebook:
https://web.facebook.com/Amharascourt

👉 Telegram:
https://t.me/Spc2016

👉 Twitter(X):
https://x.com/Amharascourt

👉 LinkedIn:
https://www.linkedin.com/company/amharascourt/

👉 Tiktok:
https://tiktok.com/@amharascourt

👉 You Tube :
https://www.youtube.com/@Amhascourt

👉 Website:
https://amhsc.gov.et
👍7❤1
"የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የለውጥና የማሻሻያ ሥራዎች እንደ አፍሪካዊ ኩራት እንዲሰማን የሚያደርጉ ናቸው" ፓውል ሳይመን (ዶ.ር)- በአፍሪካ ሕብረት የደህንነት ጥናት ማዕከል ተወካይ እና የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ዳይሬክተር

ባሕር ዳር፣ ጥቅምት 14/2019 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የክልሉን የዳኝነት አሰጣጥ በመሰረታዊነት በማሻሻል ለሕብረተሰቡ ፈጣን፣ ወጭ እና ጊዜ ቆጣቢ አገልግሎት ለመስጠት በበርካታ የለውጥና የማሻሻያ ሂደቶች ላይ እያለፈ ይገኛል።

በሁሉ አቀፍ ለውጥ ላይ የሚገኘው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፣ በዘመናዊ የዳኝነት መስጫ መሰረተ ልማቶች፣ በምቹ የአገልግሎት መስጫ ስፍራዎች ግንባታ፣ በሥር-ነቀል የተቋም ለውጥ እና ማሻሻያ፣ ለአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፣ ቅልጥፍና እና ተገማችነት አጋዥ የሆኑ የዲጅታል ዳኝነት አገልግሎት መስጫዎች ዝርጋታ፣ እንዲሁም በሌሎች ዘርፈ ብዙ የተቋም አሰራር ለውጥ ትግበራዎች ላይ ይገኛል።
ለዝርዝሩ
https://www.facebook.com/share/p/1DZdhFx4nP/
👍5