Amhara Region Supreme Court
3.11K subscribers
1.59K photos
5 videos
14 files
198 links
Download Telegram
በክልሉ የሚገኙ ከፍተኛ እና ወረዳ ፍርድ ቤቶች የ2019 በጀት ዓመት የችሎች ሥራቸውን በይፋ ጀመሩ

ባሕር ዳር፣ ጥቅምት 03/2019 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የአማራ ክልል ፍርድ ቤት ዳኞች ሁለተኛው ዓመታዊ ጉባኤ ማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ላይ የክልሉ ፍርድ ቤቶች የችሎት ሥራ በይፋ መከፈቱ ይታወቃል።

በዚሁ አግባብ የጉባኤው ተሳታፊ የክልሉ ዳኞች ጉባኤውን አጠቃለው ወደ ከፍተኛ እና ወረዳ ፍርድ ቤቶቻቸው በመመለስ፣ ሰኞ ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም ልዩ ልዩ መረሃ-ግበሮችን በማካሄድ የ2019 በጀት ዓመት መደበኛ የችሎት ሥራቸውን በይፋ ጀምረዋል።

ለ10 ተከታታይ ቀናት በክልሉ መዲና በመገኘት ለዳኝነት ሙያቸው ተጨማሪ አቅም በሚፈጥሩ የተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠናዎችን፣ ገለጻዎችን እና ከትምሕርት፣ ከንባብ እና ከተግባር የተቀዱ ሙያዊ ማብራሪያዎችን ሲከታተሉ የቆዩት ሁሉም የከፍተኛ እና ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ ከትላንት ጥቅምት 2/2019 ጀምሮ በፍርድ ቤቶቻቸው በመገኘት የበጀት ዓመቱን የችሎት ሥራ በላቀ ወኔ እና የአገልጋይነት ስሜት ጀምረዋል።

የሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ፣ ምእራብ ጎጃም፣ ሰሜን ወሎ፣ የባሕር ዳር እና አካባቢዋ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን፣ የማእከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤቶችን ጨምሮ በሁሉም ከፍተኛ እና ወረዳ ፍርድ ቤቶች የ 2019 በጀት ዓመት የፍርድ ቤቶች የችሎት ስራ በቴክኖሎጂ ታግዞ፣ በላቀ የሙያ ሥነ-ምግባር ቀልጣፋ፣ ፈጣን እና ወጭ ቆጣቢ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት በመዘጋጀት በይፋ ሥራውን ጀምሯል።
❤5
የሰሜን ወሎ ዞንና የወልድያ ከተማ አስተዳደር አመራሮች በሰሜን ወሎ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተደራጀውን የስማርት ችሎትና የቨርቹዋል ዳኝነት አገልግሎት ጎበኙ

ባሕር ዳር ፣ ጥቅምት 09/2019 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደርና የወልድያ ከተማ አስተዳደር አመራሮች በሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመገኘት የስማርት ችሎት (Smart Courtroom) እና የቨርቹዋል ዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ፣ የወልድያ ከተማ ከንቲባ አቶ ታምራት ደምሴና የአመራር ልዑካቸው፣ የሰሜን ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደሱ፣ የጉባላፍቶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ በየነ፣ እንዲሁም የዳኝነትና የፍትሕ አካላት የትብብር መድረክ አባላት አመራሮች ተሳትፈዋል።

አመራሮቹ በጉብኝታቸው፣ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያደራጃቸውን ሁለት የቨርቹዋል ዳኝነት አገልግሎት መስጫ ስማርት ችሎቶችን ተመልክተዋል።

በጉብኝቱም በከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው የቨርቹዋል ዳኝነት አገልግሎት በሰሜን ወሎ ዞን የሚገኙ ተገልጋዮች የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን የዳኝነት አገልግሎት ለማግኘት ወደ ባሕር ዳር መጓዝ ሳያስፈልጋቸው፣ በዞኑ ማዕከል በከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በተደራጁት ስማርት ችሎቶች አማካኝነት አገልግሎቱን እንደሚያገኙ ተመልክቷል።
ለዝርዝሩ
https://www.facebook.com/share/p/14s8sV7RGR6/
👍6
የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2019 በጀት ዓመት መደበኛ ሥራውን ልዩ ልዩ መረሃግብሮችን በማካሄድ ጀመረ

ባሕር ዳር ፣ ጥቅምት 9/2019 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የ2019 በጀት ዓመት መደበኛ የችሎት አገልግሎቱን በይፋ የጀመረው የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ በስራ ማስጀመሪያ መረሃግብሩ፣ በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዳኞች፣ ሠራተኞች፣ ወረዳ ፍርድ ቤቶችና አጋር አካላት የእውቅና መርሃ ግብር አካሂዷል።

ፍርድ ቤቱ የ2019 በጀት ዓመት መደበኛ ሥራውን በድምቀት ባስጀመረበት መርሃ ግብር ላይ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ዮሐንስ ወንድሙና ሌሎች የዞኑ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

አቶ ዮሐንስ ወንድሙ በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ መረሃግብሩ የተሰናዳው፣ ፍርድ ቤቶች በዳኞች የክረምት ዕረፍት ምክንያት በከፊል ዝግ ሆነው ውስን ሥራዎችን ሲያከናውኑ ከቆዩ በኋላ ከጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውን በይፋ ለማሳወቅ እንደሆነ ገልጸዋል።
ለዝርዝሩ
https://www.facebook.com/share/p/1QBotHLMQA/
👍6❤1