Amhara Region Supreme Court
3.11K subscribers
1.6K photos
5 videos
14 files
199 links
Download Telegram
"የሀገሪቱ ፍርድ ቤቶች የጋራ የትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ፍርድ ቤቶችን በአንድ የለውጥ አቅጣጫ የሚያስተሳስር እና የዳኝነት ሥርዓቱን በተቀናጀ መንገድ ለማሻሻል የሚያግዝ ነው" ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት- የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት

ባሕር ዳር፣ መስከረም 30/2019(የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የሀገሪቱን የዳኝነት ሥርዓት ግልጽ፣ ተደራሽና ቀልጣፋ በማድረግ የዳኝነት አገልግሎትን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችለውን የሀገሪቱ ፍርድ ቤቶች የቀጣይ ሦስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ለማጽደቅ ሀገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች ልዩ ጉባኤ በባሕር ዳር ከተማ ተካሂዷል።

በጉባኤው ላይ የተገኙት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ ሀገር አቀፉ መድረክ በክልሎች መካከል ያለውን ትብብርና ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ የፍርድ ቤቶችን አሠራር ለማሻሻል፣ የዳኝነት እሴቶችን ለማስፋፋትና የጋራ የለውጥ አቅጣጫ ለመቅረጽ ከፍተኛ ሚና እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል።

ክቡር ፕሬዝዳንቱ እንዳስረዱት፣ መድረኩ በፍርድ ቤቶች የዲጂታላይዜሽን መሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ በሰው ኃይል አቅም ግንባታና በሌሎች የፍርድ ቤት ማሻሻያ ሥራዎች ላይ ያለውን ተሞክሮ ለመለዋወጥ እድል ፈጥሯል።

በተለይም በእነዚህ ዘርፎች የተሻለ ልምድ ያካበቱ ፍርድ ቤቶች ልምዳቸውን ለሌሎች እንዲያካፍሉ በማስቻል የአቅምና የቴክኖሎጂ ልውውጥ መድረክ ሆኗል።
ለዝርዝሩ
https://www.facebook.com/share/p/19gziev2iA/
❤6👍2
የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የቀጣይ ሦስት ዓመት የዳኝነት ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ጸደቀ

ባሕር ዳር፣ መስከረም 30/2019 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

በአገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች ልዩ ጉባኤ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የቀጣይ ሦስት ዓመት የዳኝነት ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ለውይይት ቀርቦ ጸድቋል።

ልዩ ጉባኤው በባሕር ዳር ከተማ የተካሄደ ሲሆን፣ በመድረኩ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምሕረትን ጨምሮ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶችና የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንቶች ተሳትፈዋል።

በጉባኤው የቀረበው የሀገሪቱ ፍርድ ቤቶች የሦስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ፣ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመንና በመሠረታዊነት ለመለወጥ የተጀመሩ ጥረቶችን በተቀናጀ መንገድ ለማስቀጠል ያለመ ነው። ፍኖተ ካርታው በፌዴራልና በክልል ፍርድ ቤቶች መካከል ቅንጅትን በማጠናከር፣ የተሻሉ ተሞክሮዎችን በማስፋፋትና በቀደሙት የለውጥ ሥራዎች የተገኙ ውጤቶችን ዘላቂ ለማድረግ መሠረት እንደሚሆን በጉባኤው ተነስቷል።

የፍርድ ቤቶች የጋራ ትብብርና የተቀናጀ አሠራር የዳኝነት አገልግሎቱን ለማሻሻል ወሳኝ መሆኑም፣ የትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታው ቀርቦ በጸደቀበት ወቅት ተገልጿል።
ለዝርዝሩ
https://www.facebook.com/share/p/1euVVdDgx5/
❤6👍1
በሁሉም የሀገሪቱ ፍርድ ቤቶች በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት የሚተገበሩት ሰባቱ የትራንስፎርሜሽን ማእቀፍ አምዶች

ባህርዳር፣ጥቅምት 01/2019(የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

ለሁሉ ተደራሽ፣ በሁሉም የሚታመን የዳኝነት ሥርዓት ለመገንባት የሚያስችል የፍርድ ቤቶች የለውጥ ማዕቀፍ በሀገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች ልዩ ጉባኤ መስከረም 30/2019 ዓ.ም በባህርዳር መጽደቁ ይታወቃል።

በጉባኤው የጸደቀው እና የሀገሪቱን ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ጥራት፣ ቅልጥፍና፣ ተደራሽነትና ተዓማኒነት ለማሳደግ የተዘጋጀው የፍርድ ቤቶች የትራንስፎርሜሽን ማዕቀፍ፣ ሰባት ዋና ዋና የለውጥ አምዶች የሚከተሉት ሲሆኑ፣ በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት በሁሉም የሀገሪቱ ፍርድ ቤቶች በተዋረድ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል የድርጊት መረሃግብር ተቀምጦላቸዋል።

አምዶቹ፣ በሰው ሀብትና ሙያዊ ልማት፣ በዲጂታል ፍርድ ቤትና ኢ-ዳኝነት፣ በዳኝነት ጥራትና ተደራሽነት፣ በዳኝነት ነፃነትና ተጠያቂነት፣ በሕግና አሠራር ማሻሻያ፣ በተቋማት ትብብርና የሕዝብ ተሳትፎ፣ እንዲሁም በሕዝብ ግንኙነትና በተቋማዊ ገጽታ ግንባታ ላይ ትኩረታቸውን ዬደረጉ ናቸው።

የመጀመሪያው አምድ የዳኝነት ሥርዓቱን የሰው ሀብት በብቃት ማስተዳደር፣ የሙያ ክህሎትን ማሳደግ፣ ቀጣይነት ያለው ሥልጠናና ምርምርን ማጠናከር ላይ ያተኩራል። ይህም ብቁ፣ በእውቀት የዳበሩና በሙያዊ ስነ-ምግባር የተመሩ የዳኝነት ባለሙያዎችን ለማፍራት ያለመ ነው።

ለዝርዝሩ
https://www.facebook.com/share/p/1DFkM2J2Wa/
❤5👍3
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረትን ጨምሮ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንቶች የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን የለውጥና የማሻሻያ ስራዎች ጎበኙ

ባሕር ዳር፣ ጥቅምት 01/2019(የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የሀገር አቀፍ የሕግ ተርጎሚዎች ጉባኤ በባሕር ዳር ከተማ ሲካሄድ የቆየ መሆኑ የሚታወስ ነው።

የጉባኤው ተሳታፊ የሆኑት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስን ጨምሮ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንቶች እና የአዲስ አበባ እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንቶች፣ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የክልሉን ፍርድ ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ በመሰረታዊነት ለማሻሻይ እየተገበራቸው ያሉ አሰራሮችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የዳኝነት አገልግሎቱን በማዘመን ተደራሽነትን ለማስፈት የሰራቸው የስማርት ችሎት፣ የኢ -ፋይሊንግ፣ የአንድ ማእከል ዲጂታል አገልግሎት እና የጥሪ ማእከል ጎብኝተዋል።

ምቹ የሥራ ከባቢ ለመፍጠር የተሰሩ ሌሎች የመሰረተ ልማት ስራዎች በጉብኝቱ የተካተቱ ሲሆን፣ የዳኝነት እና የፍትሕ አካላትን ታሪክ ሰንዶ ለማቆየት፣ ለሕግ ተማሪዎች እና ተመራማሪዎች የመረጃ ግብዓት ሆኖ እንዲያገለግል ታስቦ የተገነባውን የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የፍትሕ ሙዚየም ተመልክተዋል።

ፕሬዝደንቶቹ በጉብኝታቸው፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎትን ተደራሽነት ለማስፋት የሰራቸው ሥራዎች የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች ልዩ ጉባኤ ለመታደም ባህርዳር የተገኙት ፕሬዝደንቶቹ፣ ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በተጨማሪ በጣና ሀይቅ የሚገኙ ገዳማትን እና ባሕር ዳር ከተማን ተዟዙረው ጎብኝተዋል።
❤7👍2