ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.36K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
#ኧረ_አምሳለ!
(ምልዕቲ ኪሮስ ኃይሌሥላሴ)


ሰዉ በዘመን ጅረት...................
ዘመን በሠዉ ጀርባ እንደገሠገሠ
ይኸዉልሽ እንግዲ ክፉ ቀን ደረሰ...
ይኸዉ እንዲ ሆነ:
አንች ስትሄጅ;-
ፀሀይ ጠዋት ቀረች
ጨረቃ አኮረፈች
ሰማይ አለቀሰ
መሬት ተቆረሰ
ጨዋታ ፈረሰ....
አንች ሳትኖሪ:-
አኩኩሉ አይነጋም...
በሰኞ ማክሰኞ ዉብ ቤት አይገዛም ...
በሌባና ፖሊስ ባባሮሽ ጨዋታም...
እንደሮጠ ቀርቷል ማንም ሰዉ አልመጣም....
ህፃናቱ ከቦ አሁንም ቁጭ ብሏል...
መሐረቤን ብሎ አንድ ልጅ ይዞራል...
ህፃናቱ ከቦ ቁጭ ብሏል አሁንም...
መሃረቡን ያየም አየሁኝ አይልም ...
ብጫቂ መሐረብ መች ሆነና ቁቡ...
ነገረ ጨዋታዉ አንች ነሽ አሳቡ....
ኧረ አምሣለ.... ኧረ ሆይ...
ጨዋታ ለዛ አጣ አንዴ ብቅ በይ....
የህፃናት ተረት ከግማሹ አለቀ...
ትመጣለች ብሎ አንቺን የጠበቀ....
ቤትና ሃገር ቤት የሚል ሃሳብ መክኖ...
የሀገሪቱ ጉብል ቀረ ተበትኖ...
እንካ ስላንትያ እንቆቅልሻቸዉ...
ሳይፈታ ቀረ እርቀሽባቸዉ....
'ቢበስል ባይበስል ትመጭ ይመስል'
ብለን ያሟረት ነዉ....
ለካስ አንች ላይ ነዉ....
ኧረ አምሣለ ኧረ ምነዉ...
ደጅሽ የተከልሽዉ ምን አይነት እንኮይ ነዉ....
ያዉም በአኩኩሉ በዉሸት ጨዋታ...
እንደተደበቀች እሷ ብቻ ቀርታ....
ምድር በትካዜ ሰማይ በመከራ...
አለ እስካሁን ድረስ እምባዉን ሲያዘራ.....
የምሥኪኑ ደሀ አገዳዉ አሽቶ...
ይሄዉ ባንች ምክንያት ዝናቡ በርትቶ....
የቀየዉ ገበሬ እህል ተበላሸ....
ኧረ አምሳለ እያለ በነጋ በመሸ.,.
ያገር ሽማግሌ ያገሪቱን ዳኛ...
ስልጣኑን ወሠደዉ ነጠቀዉ ቀማኛ.,.
ፍርድ ተጏደለ...
ድሃ ተበደለ...
መነኩሴም ያለቅሳል ኧረ አምሣለ እያለ .....
ኧረ አምሣለ ኧረ ሆይ....
ያሳደገሽ መንደር አይናፍቅም ወይ....?
የእናቶች እህታ የህፃናት እምባ....
ወዴት አደረሰሽ ወዴት ይዞሽ ገባ....
የእረኛ እሮሮ...
ያዝማሪ ከበሮ...
የገጣሚ ዋይታ...
ያጋፋሪ እምቢልታ....
የዋሽንቱ ቅኝት ዜማና ምታቸዉ...
ኧረ አምሣለ ሆነ አፍ መፍቻ ቋንቋቸዉ....
አለመምጣት አለ...
አለመምጣት አለ አለመተያየት...
ባንድ አምሣለ ናፍቆት ግጥም ብሎ መቅረት....
ስለእማምላክ ቢሉት አንጀቱ ሚራራ...
በራብሽ ከች የሚል ከጭንቅሽ 'ሚጋራ....
ሀገር-እግር የለዉም ወጥቶ አይፈልግሽም...
እርግማኑም ክፋ ላንችም አይቀናሽም...
ወንዝና ተራራም ወገን አይሆንሽም....
....... እናም...
ሠዉና ቀየዉን እያሠናሠነ...
የጉብሉን መዝሙር አጣፍጦ የከየነ....
ሰዉ ማለት... ሰዉ ማለት ...
ሰዉ ማለት ሃገር ነዉ ባይልም በቃሉ....
ይግባሽ አንድ ሚሥጥር - ሰዉን ከሠዉ ብቻ የመቀላቀሉ::

@Simetin_Begitim
#ኧረ_አምሳለ!
(ምልዕቲ ኪሮስ ኃይሌሥላሴ)


ሰዉ በዘመን ጅረት...................
ዘመን በሠዉ ጀርባ እንደገሠገሠ
ይኸዉልሽ እንግዲ ክፉ ቀን ደረሰ...
ይኸዉ እንዲ ሆነ:
አንች ስትሄጅ;-
ፀሀይ ጠዋት ቀረች
ጨረቃ አኮረፈች
ሰማይ አለቀሰ
መሬት ተቆረሰ
ጨዋታ ፈረሰ....
አንች ሳትኖሪ:-
አኩኩሉ አይነጋም...
በሰኞ ማክሰኞ ዉብ ቤት አይገዛም ...
በሌባና ፖሊስ ባባሮሽ ጨዋታም...
እንደሮጠ ቀርቷል ማንም ሰዉ አልመጣም....
ህፃናቱ ከቦ አሁንም ቁጭ ብሏል...
መሐረቤን ብሎ አንድ ልጅ ይዞራል...
ህፃናቱ ከቦ ቁጭ ብሏል አሁንም...
መሃረቡን ያየም አየሁኝ አይልም ...
ብጫቂ መሐረብ መች ሆነና ቁቡ...
ነገረ ጨዋታዉ አንች ነሽ አሳቡ....
ኧረ አምሣለ.... ኧረ ሆይ...
ጨዋታ ለዛ አጣ አንዴ ብቅ በይ....
የህፃናት ተረት ከግማሹ አለቀ...
ትመጣለች ብሎ አንቺን የጠበቀ....
ቤትና ሃገር ቤት የሚል ሃሳብ መክኖ...
የሀገሪቱ ጉብል ቀረ ተበትኖ...
እንካ ስላንትያ እንቆቅልሻቸዉ...
ሳይፈታ ቀረ እርቀሽባቸዉ....
'ቢበስል ባይበስል ትመጭ ይመስል'
ብለን ያሟረት ነዉ....
ለካስ አንች ላይ ነዉ....
ኧረ አምሣለ ኧረ ምነዉ...
ደጅሽ የተከልሽዉ ምን አይነት እንኮይ ነዉ....
ያዉም በአኩኩሉ በዉሸት ጨዋታ...
እንደተደበቀች እሷ ብቻ ቀርታ....
ምድር በትካዜ ሰማይ በመከራ...
አለ እስካሁን ድረስ እምባዉን ሲያዘራ.....
የምሥኪኑ ደሀ አገዳዉ አሽቶ...
ይሄዉ ባንች ምክንያት ዝናቡ በርትቶ....
የቀየዉ ገበሬ እህል ተበላሸ....
ኧረ አምሳለ እያለ በነጋ በመሸ.,.
ያገር ሽማግሌ ያገሪቱን ዳኛ...
ስልጣኑን ወሠደዉ ነጠቀዉ ቀማኛ.,.
ፍርድ ተጏደለ...
ድሃ ተበደለ...
መነኩሴም ያለቅሳል ኧረ አምሣለ እያለ .....
ኧረ አምሣለ ኧረ ሆይ....
ያሳደገሽ መንደር አይናፍቅም ወይ....?
የእናቶች እህታ የህፃናት እምባ....
ወዴት አደረሰሽ ወዴት ይዞሽ ገባ....
የእረኛ እሮሮ...
ያዝማሪ ከበሮ...
የገጣሚ ዋይታ...
ያጋፋሪ እምቢልታ....
የዋሽንቱ ቅኝት ዜማና ምታቸዉ...
ኧረ አምሣለ ሆነ አፍ መፍቻ ቋንቋቸዉ....
አለመምጣት አለ...
አለመምጣት አለ አለመተያየት...
ባንድ አምሣለ ናፍቆት ግጥም ብሎ መቅረት....
ስለእማምላክ ቢሉት አንጀቱ ሚራራ...
በራብሽ ከች የሚል ከጭንቅሽ 'ሚጋራ....
ሀገር-እግር የለዉም ወጥቶ አይፈልግሽም...
እርግማኑም ክፋ ላንችም አይቀናሽም...
ወንዝና ተራራም ወገን አይሆንሽም....
....... እናም...
ሠዉና ቀየዉን እያሠናሠነ...
የጉብሉን መዝሙር አጣፍጦ የከየነ....
ሰዉ ማለት... ሰዉ ማለት ...
ሰዉ ማለት ሃገር ነዉ ባይልም በቃሉ....
ይግባሽ አንድ ሚሥጥር - ሰዉን ከሠዉ ብቻ የመቀላቀሉ::