ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.36K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
ለፈገግታ😂😂😂

ታኬ ፦ እ ትንሹ ሲኒማ አንገባም ዛሬ?

ትንሹ :- የሀኪም ቀጠሮ አለብኝ ዛሬ ይለፈኝ፡፡

ታኬ ፦ አንተ ሞኝ ሸውደዋ ሰርዘህ ቀጠሮውን አሞኛል ብለህ😳

😂😂😂😂

@WalyasHood
@Simetin_Begitim
@endenaendena
#እያረምን_ወይስ_እያበድን_እንሂድ?

#ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

ገበሬው ለሙግት ወደ ሸንጎ ሄዶ ሲመጣ የገዛ ወዳጆቹ የዘራውን እህል ሳያርሙ፣ ሳይኮተኩቱ ጠበቁት፡፡ ማሳውን እያየ ያብዳል፡፡ “እንዴት እንደዚህ ይደረጋል? ይህን ያደረጉት እነ እንቶኔ ናቸው? ይህን ያደረጉት እኔን ሊጎዱ ነው? ድሮም እነርሱ አይወዱኝም ነበር፤ በቃ የሰው ነገር መጨረሻው እንደዚህ ሆነ ማለት ነው? በቃ የእርሻዬ ነገር አበቃለት ማለት ነው?” እያለ ፀጉሩን እየነጨ ያብዳል፡፡

አንድ ሽማግሌ ከሩቅ አይተዉት መጡ፡፡ እየዛበረ የሚናገረውን ሰሙ፡፡ ከዚያም “እባክህ ረጋ በል” አሉት፡፡ ‹ምን ረጋ እላለሁ፤ እንዲህ ሲሆን እያዩት፤ ከዚህ በኋላ ምን ተስፋ አለኝ› እያለ ሲጮኽ ሽማግሌው ሰሙትና ‹ወዳጄ ይህ ሁሉ ቢሆንም፣ እያረምን እንጂ እያበድን መሄድ አለብን እንዴ?› አሉት አሉ፡፡

ኢትዮጵያም እንዲህ ነው እየሆነች ያለችው፡፡ አንዱ ስንዴ፣ ሌላው እንክርዳድ ይዘራል፤ አንዱ ያቀናውን ሌላው ሊያጣምመው ይተጋል፡፡ በዚህ ሲደፈን በዚያ ይቦተረፋል፤ ራስ ሲነቃ እግር ይጎተታል፤ ብዙዎቻችን እንደዚያ ገበሬ የምናየውና የምንሰማው ለዕብደት እየዳረገን ነው፡፡ ማበድ ግን ሀገር አያቀናም፡፡ መቆጨት እንጂ መናደድ መፍትሔ አያመጣም፡፡ አበቃ፣ አለቀ፣ ደቀቀ፣ ሞተ ተቀበረ፣ ሄደ፣ አከተመ፤ ነጠፈ፣ ተሟጠጠ እያሉ ማልቀስ ነገሩን አይቀይረውም፡፡

አርበኞቻችን ሀገራችንን ከጣልያን ቀንበር ሊያላቅቁ ላይ ታች ሲሉ አያሌ ተስፋ አስቆራጭ ነገሮች ገጥመዋቸዋል፡፡ የንጉሡ መሄድ፣ የአንዳንድ ታዋቂ ሰዎች ከጣልያን ጋር ማበር፤ ሌላው ቀርቶ ታላላቅ የሃይማኖት አባቶች ሳይቀሩ ከጣልያን ጎን መቆማቸው፤ ለገንዘብና ለሹመት ሲል መረጃ እየሰጠ የሚሾልከው ባንዳ፤ በእነርሱ ላይ የሚወረወረው ፕሮፓጋንዳ፤ ስንቅና ትጥቅ ሲያልቅበት ተስፋ የሚቆርጠው ጭፍራ፤ ጣልያን እያሸነፈ ነው እያለ የሚቦተርፈው ወሬ በጉንጩ፤ የአንዳንድ ጀግና ዐርበኞች በጊዜ መሠዋት መክፈል፤ መንገዱን ረዥም ትግሉን መራራ አድርጎባቸው ነበር፡፡

የሀገር ነጻነት እንኳንስ ለማየት ለመስማት የሚቀርብ አይመስልም ነበር፡፡ ዓለም በሙሉ ከጣልያን ጋር ያበረ ነበር የሚመስለው፡፡ ንጉሡ በዓለም ማኅበር ያቀረቡትን ተማጽኖ ሊሰማ የወደደ አልነበረም፡፡ እየዋለ እያደረ ሲሄድ ደግሞ ነገሩ ሁሉ የተቆረጠና ያለቀ ይመስል ነበር፡፡

ያንን የመከራ ዘመን የተሻገርነው ማረም እንጂ ማበድ እንደማያዋጣ በገባቸው ዐርበኞች ትከሻ ነው፡፡ መቼምና ምንም ቢሆን የኢትዮጵያ ነጻነት የማይቀር እውነት መሆኑ ገብቷቸው፣ ከሚያጋጥማቸው ፈተና ይልቅ የሚገኙትን ድል በሚያስቡ ዐርበኞች ነው፡፡

አንድ ጥግ ይዞ ከመቆዘምና ፀጉር ከመንጨት ይልቅ ወደ መፍትሔው የሚደርስ አንዳች ነገር ማድረግ የተሻለ መሆኑን በተረዱ ዐርበኞች ክንድ ነው የተሻገርነው፡፡

የዐርበኞች ትግል ከተናጠል ወደ ኅብረት፣ ከኅብረት ወደ ትብብር፣ ከትብብር ወደ ግንባር እያደገ መጣ፡፡ በመጀመሪያው ዓመት የነበሩትን ነገሮች እያረሙ፤ የተሻለም መንገድ እየተለሙ ተጓዙ፡፡ ሌሎች በመቶ ሃምሳ ዓመት ያልገፉትን ቅኝ ገዥ እነርሱ በአምስት ዓመት አሰናበቱት፡፡ እገሌ እንዲህ አለ፤ እዚህ ቦታ እንዲህ ተዘፈነ፤ እገሌ ለጣልያን ገባ፤ እገሌም ከዐርበኞች ከዳ፤ እገሌ ደግሞ ወደ ዐርበኞች መጣ፤ እነ እገሌ ዐርበኞችን ደምስሰን ሀገሪቱን እንቆጣጠራለን አሉ፤ እነ እገሌም በመሣሪያ ኃይል ተደራጅተው ሊዘምቱብን ነው፤ የሚለውን ሐሞት አፍሳሽ ወሬ መስማት ተው፡፡

የማይሠሩትን ትተው ከሚሠሩት ጋር ብቻ ለመተባባር፤ ስለ ጠላት ከማሰብ ስለ ወገን ብርታትና ጥንካሬ ለማሰብ፤ ከማበድ እያረሙ ለመሄድ በመቁረጣቸው ከ1930 ዓ.ም. በኋላ የዐርበኞች ትግል እየተጠናከረና መልክ እየያዘ መጣ፡፡ የጸሎት ዐርበኞችና የጦር ዐርበኞች ተባብረው ባደረጉትም ትግል ኢትዮጵያ ቀንበሯን ሰበረች፡፡

ዛሬም የሚያስፈልገን እንደዚያ ይመስለኛል፡፡ በትንሽ በትልቁ በማለቃቀስና በማበድ ጉልበታችንን ሁሉ ለልቅሶና ለዕብደት ከምናውለው፤ ስሕተቱን እያረምን፤ ሰውን እያተረፍን መጓዝ ነው ያለብን፡፡ መሬቱ ላይ የበቀለ አረም ካለ አረሙን እናርማለን፡፡ መሬቱን ግን እንፈልገዋለን፡፡ ዛሬ አረም አበቀለ ማለት ለአረም የተፈጠረ መሬት ነው ማለት አይደለም፡፡ እነ እገሌ እንዲህ አደረጉ፣ እንዲህ ሆኑ፣ እንዲህ አሉ እያልን የተራረፈ ወሬ እየለቃቀምን የተጣለልን የአጀንዳ ፍርፋሪ እያነሣን ልባችንን አናድክመው፡፡ በራሳችን ዕቅድ ወደምንፈልገው ዓላማ እንሂድ፡፡ ኢትዮጵያን መድረስ ወዳለባት ሠገነት ለማድረስ የማንም ቡራኬና ፈቃድ አያስፈልገንም፡፡ ‹እህ›ም ተባለ ‹አሃ› መንገዳችንን አይለውጠውም፡፡

እያረምን እንጂ እያበድን አንሄድም !!!

***
@Simetin_Begitim
"ምኒልክ ሰውብቻ"
~~~
ጥቁር 'ማይወክለው
ነጭም 'ማይወክለው፤
ከዘር ከቀለም ጋር የሌለው ጋብቻ፤
እምዬም ፣ አብዬም ምኒልክ ሰው ብቻ!
በላይ በቀለ ወያ
@Simetin_Begitim
እንኳን ደስ አላችሁ!! እንኳን ደስ አለን!!

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የ2019 የኖቬል የሰላም ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡ በኢትዮጵያዊ ወጎች ስም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን ለማለት እንወዳለን!
@Simetin_Begitim
Forwarded from ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian (Deleted Account)
አንተ አልቻልክም ይሉሃል::
አዎ አንተ አትችልም!
በሰይፍ መቅላት፣ረግጦ መግዛት አልቻልክም፤
አንተ እጅ መቁረጥ፣ እግር መንሳት አልቻልክም፤
ዘር ማጥፋት፣ ደሃን መግፋት ፈጽሞውኑ አልቻልክም፤
የኔን ተቀበል ያንተን ወዲያ ጣል፤
በአንተ ወርቅ እኔ ልድመቅ ማለት፤
ምን በወጣህ አንተ አትችልም፤
ስለዚህ አንተ አልቻልክም::
ጀግናን በስቅላት፣ ገሎ ለጅብ መስጠት
40 ምሁር ከወደቁበት አንስቶ ማክበር እንጂ 60 ምሁር ባንዴ መቅበር
እንዴት ይቻልሃል? አልፈጠረብህማ!
ለመላው አፍሪካ መስራት እንጂ ምስኪኑን የኤርትራ ህዝብ መውጋት
አይሆንልህም::
ማስታረቅ እንጂ ማራራቅ፤
ወንድም ህዝብ ደም አይፋሰስ እንጂ የህጻናት ደም ይፍሰስ አትልም!
ስለዚህ አልቻልክም::
የእናቶችን እንባ ማበስ እንጂ የራሔልን እንባ ማፍሰስ፤
የልጅ እሬሳ ላይ አስቀምጦ በሰደፍ አናቷን ማፍረስ፤
አንተ አይሆንልህም አመድ አፋሽ ቢያረጉህም::
የችሎታ ስሌቱ ይሄ ለሆነ ህዝብ አንተ አትችልም::
በቃ አትችልማ!!!
ሞታቸውን የሚጠባበቁትን ከእስር ለቀሃል::
ስለዚህ አልቻልክም:: ምክንያቱም ጀግንነት ለእነሱ መግደል ነዋ!
የተበተኑትን ከአለም ዙርያ ሰብሰበሃል፤
በፍቅር አቅፈህ አብረህ አልቅሰሃል፤
ያለመዱትን? የማያዉቁትን?
ስለሆነም አልቻልክም::
ለአህያ ማር እየሰጠህ አስቸግረሃል፤
አህያ የለመደችው ሳር እንጂ ማር አይጥማትም፤
ስለዚህ ችሎታ ይጎለሃል::
ፒንሳ የልህም፣ የሃይላንድ ዉሃ የለህም፤
የምድር ስር ጉድጓድ፣ጫለማ ቤት የለህም፤
ማስፈራርያ አውሬ የለህም፤
ሽንት የምትሸና የመብራቱ ልጅ የለችህም፤
ታዲያ ችሎታህ ምኑ ጋር ነው???
ሚድያውን ማፈን፣ የባለጌን አፍ መድፈን፤
እጅግ ተስኖሃል:: ስለዚህ አንተ ሳትቀር ባደባባይ ይሰድቡሃል::
ያሻቸውን ይጽፋሉ ይናገራሉ፤ሲሻቸው ይሰለፋሉ፤ ሲሻቸው ይሸልላሉ
(አንተምላይ ሳይቀር)
“ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ ” ሲል ለኖረ ሰው፤
ለገዢዎች የአምልኮ ስግደት ሲሰግድ ለኖረ ህዝብ፤
የአጋዚን ዱላ ለጠገበ ሰውነት ይሄ እንዴት ይሰማሟል???
ስለዚህ አትችልም ይለሃል::
እጅ መንሻ ሲሰጥ ለኖረ ጉቦ ለለመደ፤
ሌባ ይጥፋ ስትል ሀገሩን የካደ፤
ባዕድ ነው ለሱ፣ የችሎታ ማነስ፣ ባህሉን የናደ::
እሱ ችሎት ለኖረው አንተ ምን አነካከህ?
ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው እየሞተ ያገኛታል መተው ነበረብህ::
እኔ ልንገርህ ዶ/ር አብይ አንተ አትችልም!
ብዙ ሚሊዮን ህዝብ መምራት እንጂ ብዙ ሚሊዮን እብድ መንዳት
አትችልም!Ephreme Gelgela

@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ዛሬ በዚህ channel ስለ ጠሚዶ ( ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር ) አብይ አህመድ በተለያየ ጊዜ ያቀረብንላችሁን ፅሁፍ repost እናደርጋለን ፡፡ እናንተም ስለ ጠቅላያችን ማለቴ ስለ ምርጡ መሪያችን ሀሣብ ካሎት እንኳን ደስ ያለህ ለማለት @Simetin_Begitimbot or @Haile_Melekot ይላኩልን ፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
Forwarded from ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian (Deleted Account)
" ከአሁን በኃላ ኢትዮጵያዊ ሆኖ በጠላትነት የሚፈረጅ የለም ፤
ሁላችሁም ኑ ፣ ጊዜው የሰላም ፣ የእርቅና የፍቅር ነው።
በየፊናችሁ ለሃገራችሁ አስተዋጽኦ አድርጉ ፤ እንደዱሮ አንዱ
ተዋናይ አንዱ ተመልካች የሚሆንበት ጊዜ አብቅቷል። በሃገራችን
ጉዳይ ሁላችንም እንተውን... # ፍቅርያሸንፋል "
ዶ/ር አብይ አህመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የ2019 የሰላም ኖቤል ሽልማትን አሸነፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የ2019 የሰላም ኖቤል ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡

ዘንድሮ ለዘርፉ ከቀረቡ እጩዎች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የ16 ዓመቷ ስዊድናዊት የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋች ግሪታ ተንበርግ በሰፊው ያሸንፋሉ የሚል ግምት ተሰጥቷቸው ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከ20 ዓመት በፊት ደም አፋሳሽ የነበረውንና በርካታ ሰዎች ያለቁበትን የኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት መቋጫ እንዲያገኝ አድርገው ሰላም በማውረዳቸውና ምስራቅ አፍሪካ የትብብር ቀጠና እንዲሆን ያደረጉት ድፕሎማሲያዊ ጥረት የኖቤል ሽልማቱን እንዲያሸንፉ ጉልህ ሚና ተጫውቷል ተብሏል፡፡

በተለይም ወደ ደም መፋሰስ እየገባች የነበረችው የሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች ተደራድረው የስልጣን ክፍፍል በማድረግ ወደ ሰላም መመለሳቸውም ትልቅ ዋጋ የሚያሰጥ ስኬት ተደርጎም ተወስዷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአንድ ቀን 350 ሚሊዮን ችግኝ ማስተከላቸውና በእርሳቸው አመራር የካቢኔያቸውን ግማሹ በሴቶች እንዲያዝ ማድረጋቸውም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲቸራቸው ያደረገ መሆኑን የፖለቲካ ጠበብቶች ግምታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በተለያዩ መስኮች ጉልህ ተግባራቶችን ያከናወኑ ግለሰቦችን ተቋማት በየዓመቱ የሚሸለሙበት የኖቤል ሽልማት በአለማችን ከሚሰጡ ሽልማቶች መካከል ቀዳሚው ነው፡፡

የኖቤል የሰላም ሽልማት እስካሁን ለ133 ግለሰቦችና ተቋማቶች ተሰጥቷል፡፡ እ.ኤ.አ 1938 ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ለኖቤል ሽልማት መታጨታቸው የቢቢሲ መረጃ ያሳያል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ሽልማትን በማሸነፋቸው 9 መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወይም 9 ሚሊዮን የስዊድን ክሮነር ይበረከትላቸዋል፡፡

Via:- Ethio FM
@Simetin_Begitim
Forwarded from ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian (Deleted Account)
©ፈጣሪ ታደገን ግጥም ለፈገግታ ✿
ውስጤ ይሔንን ያስባል
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ለ20 አመታት ኢትዮጵያን ቢያስተዳድር
ደሴ.......ዲሲ
ጎንደር...... ቫቲካን
አሰላ.......... ኦስሎ
አዳማ....... ፓሪስ
ሐዋሳ..... ሙኒክ
ትግራይ..... ቶኪዮ
ባህርዳር ..... ቆጵሮስ
ሱሉልታ ...... ሚኒሶታ
ወለጋ ..... ማድሪድ
ሐረር ........ ሎንዶን
አአ ......ዋሽንግተን
ዲቪ ወደ ኢትዮጵያ ሲሞላ
ዘረኝነት ከውስጣችን ሲጠፋ
ኢትዮጵያ ገናና ሀገር ስትሆን ይታየኛል ።
@Simetin_Begitim
Forwarded from ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian (Deleted Account)
ሀምሌ 1 2010 ዓ.ም
ለሁለት ወንድማማች ህዝቦች ልዮ ቀን ናት፡፡
ኢትዮጵያ ከ ኤርትራ ከ20 ዓመት ብኃላ የታደሠ ግኑኝነት ፡፡
ክብር ለዶክተር አብይ እና ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ
ድል ለሁለቱ ህዝቦች
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
Forwarded from ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian (Deleted Account)
breaking news
🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ኢትዮጵያ ከነገ ጀምሮ የድፍድፍ ነዳጅ የሙከራ ምርት
ትጀምራለች - ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ
ከነገ ጀምሮ የድፍድፍ ነዳጅ የሙከራ ምርት
እንደምትጀምር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ
ገለጹ።
Forwarded from ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian (Deleted Account)
ሮማን በፍቃዱ
ሀይለስላሴ - ግርማቸው
መንግስቱ - በላቸው
መለስ ዜናዊ - ፀጥ አርጋቸው
ሀይለማርያም - ዝም በላቸው
.
.
.
ዶክተር አብይ - አንድ አርጋቸው! !
😁😁😁
ስለ ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ በጥቂጡ በዚሁ Channel ካወራናቸው በጥቱ ይሄን ይመሥላሉ፡፡ ገና ብዙ ነገር ከእርሡ እንጠብቃለን ፡፡ እናግዘው ዘረኝነትን እንጠየፍ ለማይረቡ እርካሽ ፖለቲከኞች አንታለል በአንድ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነቻችን እንኩራ የዛሬው መልዕክቴ ነው ፡፡
አውርተን ሳይሆን እንደ አቢቹ ሰርተን እንክበር !!!💚💛❤️

ሀይለመለኮት ነኝ መልካም ቀን
@Simetin_Begitim
ዕ-ም-ነ-ት(ልዑል ኃይሌ)

በጎባጣነቴ ተመርኩዘው ሲያልፉ፤
ምሩኝ እንድላቸው ዓይኖቼን አጠፉ፤
ዓይኖቼም ቢጠፉ መንገድ መች ይጠፋል፤
ያመረኮዘ ሠው አቀርቅሮ ኖሮ
መንገድ ስላጠና እንቅፋቱን ያልፋል፤
ተይ ምሪኝ አልልም
ልምራም ካልሽ እንዳሻሽ፤
ጎብጬም ታውሬም አየዋለሁና የአንቺን መጨረሻሽ፤
አልሰጋም መንገዱን አልፈራም መመራት፤
ዓይኔን ብታጠፊም
ከውስጥ አኑሪያለሁ የማይጠፋ መብራት፤
አልፈራም መመራት!!
...
አለሁ ካለሽበት
ሄዳለሁ በገደል ሄዳለሁ በሐይቁ፤
ዋጋ ያጣልና
እስከጥግ ቢያፈቅሩ እምነት እያራቁ፤
ምሪኝ ባንቺ መንገድ
እኖራለሁ ባሻሽ፤
ታውሬም ጎብጬም
በዕምነቴ አየዋለሁ ያንቺን መጨረሻሽ
27-01-2012 ዓ.ም.

@Simetin_Begitim
#ስታረጅ...

፨፨፨

ከጋሽ ስብሃት ንግግሮች መሃከል ሳስታውሳቸው ፈገግ የሚያደርጉኝ...

" ስታረጅ በመጀመርያ ስም ትረሳለህ ቀጥሎ መልክ ትረሳለህ ከፍ ሲል ዚብህን መዝጋት ታቆማለህ ሲብስብህ መክፈቱንም ትተወዋለህ ። "



"እሄን ካንተ አልጠብቀውም የሚለኝ ሰው የመጨረሻ ብሽቅ ስለሆነ በቦክስ ብለው ደስ ይለኛል...እሱ ማን ነውና ነው ከኔ ምን እንደሚጠበቅ የሚነግረኝ? "

©ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
IMG_20191012_113206.jpg
28.8 KB
ግዜ የጣለኝ ግዜ፣
ከመሬት ወድቄ ሁሉም ፊት ሲነሳኝ
ይሄ ደግ ወዳጄ፣
ወደኔ መጣና በካሜራ አነሳኝ!
እዮብ ዘ ማርያም

@Simetin_Begitim
"እርሙን ተደፋፍሮ ፣ አንድ ቀን ቢዋጋ
አላስቀምጥ አለን
በየ መድረኩ ላይ ፣ ያንኑ እያወጋ"
ያለውን ባናውቅም
እኛም እንላለን
"ነፍጠኛ" ሲባል ፣ ወይ
እነሱም ይላሉ ፣ " ወዬ " ሲባል "መንጋ"
ሳይጠሩት አቤት ባይ
ሁለት መንጋ መሃል ፣ ሀገር ተሰንጋ
እንዴት ብሎ ይንጋ?
ነፍጠኛ አይደሉም ወይ ፣ እነ ጃገማ ኬሎ ፣ እነ
አብዲሳ አጋ

@Simetin_Begitim
ጥቅምት_2_ከታሪክ_ማህደር
# ታላቁ ንጉስ # ዳግማዊ_አፄ_ምንሊክ (# እምዬ )
የክተት አዋጅ በማወጅ ሰራዊታቸውን ይዘው ወደ
# ዓድዋ ያቀኑት ልክ የዛሬ124 ዓመት # በዛሬዋ
እለት ነው ።
# የአድዋ ድል የመላው ጥቁር ህዝብ ኩራት
የሆነው አንድ ሆነው ስለተነሱ ነው፡፡

©Fb መንደር
@Simetin_Begitim
​​➛➛እመ መከራ➛➛

ኢትዮጵያ እመ መከራ
የግዜር መመራመሪያው
የስቃይ ቤተ-ሙከራ
መውደቅማ ነበር ያባት
እንደ ያሬድ እስከ ሰባት
እንደ በላ ብላቴና
የእንክርዳድ ሙልሙል እንጎቻ
የትውልዴ እጣ ፈንታ
መውደቅ፣መውደቅ፣መውደቅ ብቻ!

ገጣሚ ፦ በእውቀቱ ስዩም
@Simetin_Begitim