ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.36K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
የዕለቱ ቀለል ያሉ የናንተን የበዛ ተሣትፎ የሚጠይቅ ጥያቄዎች 🔥🔥🔥🔥
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

1) በ corona virus በዛሬው ቀን WHO ያወጣው መግለጫ ስንት ሚሊየን ሰው በአለም ላይ ተይዟል ይላል?


2) የአለም ዋንጫ ለመጀመርያ ጊዜ ያነሳችው ሀገር ማን ናት ?

3) Corona virus ሳይበግራት ምርጫ ያካደችው የአፍሪካዊት ሀገር ማን ናት?

4) የመጀመሪያዋ ሴት አፍሪካዊት አትሌት የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ማን ናት?

5) የFacebook መስራች ማን ይባላል ?

መልሱን በ @EthiopianFirst_bot ይላኩልን!
መልካም ዕድል ተሳተፉ መልካም ምሽት
ተሳተፊዎቻችን የትናችሁ😢😢😢
ብዙ ተሣታፊ ስላላገኘን እስከ ነገ ከቀኑ 8 ሰአት ድረስ ይሞክሩ ?
ግብዣ
{በዕውቀቱ ሥዩም}
_________________________
እትዬ ፀሐይ ቤት ከተከራየሁ ከሁለት ሳምንት በኃላ የገና ዋዜማ
ሆነ ።
''አንተ ልጅ ብቻ መሆን ጥሩ አደለም ተጎረቤቶችህ ጋር
ተቀላቀል!'' አሉኝ እትዬ ፀሐይ ።
እሺ ብዬ ተከተልኳቸው።
ቤታቸው በእንግዶች ተጨናንቋል። ያስተዋውቁኝ ጀመር ። ''ይሄ
ከግራ ጎንህ ያለው ዶክተር ምትኬ ነው ።
ይሄን ቤት ከተከራየው አራት ዓመት ሆኖታል ። ባሁኑ ጊዜ እጅግ
የተከበረ ሐኪም ከመሆኑም ባሻገር ወደ ውጭ ሀገር አሁንም
አሁንም ይመላለሳል። ውጭ ሀገር ማለት ለእሱ ሶደሬ ሄዶ
እንደመመለስ ነው። ለነገሩ ሶደሬ ብርቅ የሆነባቸው ሰዎች እንዳሉ
ሳላውቅ ቀርቼ አይደለም ። ለምሳሌ አንተ ሶደሬን ታውቃለህ ?''
''አውቀዋለሁ''
''ማወቅማ...ያው በስም ሲጠሩት መስማትህ የት
ይቀራል ?....ሄደህ ታውቃለህ ወይ ማለቴ ነው ?''
''ሄጄ አላውቅም!''
'' እኮ ! ....አየህ ሄድሁ ብትለኝ ማን ወሰደህ ብዬ ላፋጥጥህ
ነበር!!...ይሄ ጎረቤትህ ግን ውጭ ሀገር ይመላለሳል ።
አውሮፕላን ለሱ አንተ የምትመላለስበት 64 ቁጥር አውቶብስ
ማለት ነው ። ታዲያ ሄዶ ሲመለስ በእጅ አንድ ነገር
ሳያንጠለጥልልኝ አይመለስም። መከራየት ማለት ሺህ ብር
ከፍለው በሰው ቤት መፈንጨት ብቻ አለመሆኑን የተረዳሁት በእሱ
ነው እንግዲህ ....'' አሉኝ ።
ዶክተር ምትኬ ራሱን አወዛወዘልኝ። { እኔ ነኝ እወቀኝ እንግዲህ
እንደማለት }
''ይህች ደግሞ !...'' አሉኝ ''ሶፋው ላይ ከፊት ለፊቴ
የተቀመጠችዋን ማለፊያ ሴት በአገጫቸው እየጠቆሙኝ ''ይቺ
ደግሞ በቀኝህ በኩል ያለችው ተከራይ ናት ። ቆንጆ መሆኗ
የማይካድ ቢሆንም እጮኛ ግን አላት ። ለዚህ ነው ዕቃ ለመዋስ
ስትፈልግ እኔን ጠይቀኝ እያልኩ የምጨቀጭቅህ። የወንዶችን
አመል እኔ መች አጣሁት....ነገር የሚጀምሩት ስኒ በመዋስ ነው
።ትንሽ ቆይተው ቢራ ልጋብዝሽ ይላሉ። ስኒ ሳይኖርህ እንዴት ቢራ
ልትጋብዝ ትችላለህ ? የማይመስል ነገር እኮ ነው ....ሆሆ
....የወንዶችን አመል እኮ አብጠርጥሬ ነው የማውቀው ።
እንግዲህ ስኒ በመዋስ ይገቡና በኃላ የሚፈልጉትን ሲያገኙ ጀበና
ይሰብራሉ። ለማንኛውም ይች ውብ መዓዛ ነሽ ትባላለች ።
እንደነገርኩህ ምን የመሰለ በደምግባቱም በሀብቱም የተሳካላት
እጮኛ አላት። አይ ፀባይ ! አይ ልግስና ....ኑሮው ፊልድ
መውጣት ነው። ከዚያ ሲመለስ ሽንኩርቱን፣ ከሰሉን፣ ፍራፍሬውን፣
ማሩን አስጭኖ ይዞልኝ ይመጣል...አይኔ ይፍሰስ...አይ የሰው
መለያየት !....ሰው ዝጉርጉር ነው ። አንዳንዱ እጁን ኪሱ ጋር
ሰፍቶ ይፈጥረዋል ። አንዳንዱን እንዲያውም ወይ ከኪሱ ወይ
ከእጅ አንዱ የጎደለበት ነው ። ሌላው እንደመአዛነሽ እጮኛ ያለው
ደግሞ ..."
''ይሄ ደግሞ '' አሉ ወደኔ እየጠቆሙ ምን ብለው ሊያስተዋውቁ
እንደሆነ በመጠበቅ አንገቴን ደፋሁ። ''ይሄ ደግሞ ...''ብለው
ቆሙ ። ቀና ብዬ አየኋቸው። ''ይሄ ደግሞ ...ያው ተከራይ ነው
...!'' አሉና ወደ መስተንግዶው ሄዱ ።
ብፌ ነው ።
ብፌውን እየዞርን እህል ማንሳት ጀመርን ።
የእትዬ ፀሐይን ንግግር እያብሰለሰልኩ ድብል እንጀራውን ሳነሳ፣
ክትፎውን ፣ቆስጣውን፣ ስጋውን ፣አይቡን ሳነሳ ሳላስበው ሰሃኔ
ትንሽ ጉድባ መስሎ ኑሯል ።''
ወደ ቦታዬ ስመለስ የሁሉም ዓይን ወደኔ መጣ ። እንዴት ያለ ነገር
ነው ? ...አልኩና ቶሎ ቶሎ ንጄ ልቀንሰው እጄን ስሰድ....የእትዬ
ፀሐይ ትንሽ ልጅ ቱር ብሎ ከጓዳ መጣ ።
''እማማ እራቴን!'' አለ ።
'' ሂድና አንሳ!'' አሉና ሰሃን ሰጡት ።
ልጅ ግን የማይረሳ ነገር ተናገረ ።
'' ከዚህ ነው ከዚያኛው ? ከየትኛው ላንሳ?'' አለ የኔን ሰሃን እና
የብፌውን ጠረጴዛ እያፈራረቀ እያየ ።

#መልካም ቀን
የኔ ቁመት ማጠር የጠቀመው ልብስ ሰፊዎችን ነው!
" ፍቅርሻ! ጨጓራ አሰፊንጂ! "...ጂንስ ማለታቸው ነው።
" ለምን? "
" ሁልጊዜ በጨርቅ ሱሪ?....ደላላ ይመስል "
ለምን መሰላችሁ? ጂንስ ከገዛሁ ግማሹን ማስቆረጤ የማይቀር
ነው እነሱ ጋር.......
አሁን መቼስ ለጌትየው ምስጋና ይድረስ፡ ወፈርኩንጂ ያኔ 40ዎቹ
ላይ ኪሎዬ ስታሽቃብጥ፡ የማላስጠብበው ልብስ ቢኖር ካልሲዬን
ነበር...እሱንም አፍሬ ነውንጂ....
ሰፍቶ..ሰፍቶ ወደታች ይወርድና የጫማዬ ቆብ መስሎ ቁጭ!
**
አንድ ልብስ ሰፊ ነበሩ፡ መንጥቅ ነው ስማቸው!
የአፍንጫ ጁስ ( ንፍጥ ) ያበዛሉ። የሚናፈጡበትን የማያጡ
አዛውንት፣ እድሜ ለኛ!
ሴቶችን ሲለኩ በጣም ይቆያሉ፡ ሴቶቹ ሲነጫነጩ ትዝ ይለኛል።
አንድ ቀን አቦነሽን ልትለካ መጣች፡ እኔ ከሷ ቀጥዬ።
ጋሽ መንጥቅ እንደለመዱት በአቦነሽ ዛቢያ ዞሩ
.....አስር ደቂቃ!
" ኧረ በቃ ምነው...አቦነሽ! "....ትላለች
" አይ እንግዲህ!...ወበራሽ ደግሞ! "
" ወገብ ለመለካት መዋል አለብዎትንዴ? "
" አሄሄ! ገና አላዳረስኩምኮ...."
እዚህ ላይስ እውነታቸውን ነው!
የአቦነሽን ወገብ አንተ አንለውም " እነ ወገብ " ነውንጂ!
አቦነሽን ታዘብኳት!...በኪነጥበቡ ሴት አደረጋትንጂ ወንድ ብትሆን
ኖሮ ከአንጀት የተሰራ ቀበቶ ነበር ልኳ!
የአቦነሽን ጨርሰው ዘወር ሲሉ ለጉድ የዶለኝ አለሁ
" ያንተን ነገ እጨርስልሃለሁ "
" ሳይለኩኝ? "
......ከላይ እስከ ታች ገርመም አደረጉኝ.....
ምን ከላይ እስከ ታች እላለሁ!? ከታች እስከ ታች ነውንጂ
" በግምት አውቀዋለሁ "
" የበግ ዋጋ ነውንዴ "
" አይ እንገዲህ " ክፍ " ካላሉህኮ! ትግማማለህ "
ይላሉ ፍንጃል ሙሉ እየተናፈጡ!
በአቦነሽ ጨርቅ ጠረግ ጠረግ....እያደረጉ!

©Fikre Ze Bhere Ethiopia

ሠናይ ውሎ መልካም ቀን!!!
ለፈገግታ😂😂😂

በጣም አስቀያሚ ነህ
ማግኔት ብትውጥ እንኳን አትስበኝም አለችኝ 😂😭
ልክ ነሽኮ ማግኔት ዱቄት አይስብም 😜
ምርጥ 10(Top 10) የተሠኘ በአለማችን ብሎም በሀገራችን የተከናወኑ የመዝናኛ የፖለቲካ እንዲሁም ሳይንሳዊ ወሬዎችን አጠር ባሉ ቃላት እጥር ምጥን አርገን አዘጋጅተን ለእናንተ ለወድ ቤተሰቦቻችን ለማቅረብ ዝግጅት እያደረግን እንገኛለን ፡፡ ዝም ብለን ከምናቀርብ በትንሹ 50 ሰው ያክል ሀሣባችንን ከደገፈልን በሳምን 3 ቀን የምናቀርብ ይሆናል ፡፡ ስለዚህ ይቅረብ👍 አይቅረብ👎

በዛውም ሀሳብ አስተያየት ከለዎት ወይም አድሚን ወስደው ከኛ ጋር መስራት ከፈለጉ በ @EthiopianFirst_bot ይናግሩን ፡፡

ያለውን እውቀት ትንሽ ይሁን መካፈል ትልቅነት ነው የሀገራችን ሰውም እንዲህ ይላል የጋን ውስጥ መብራት አትሁን ፡፡
እንማማር ያለንን እናካፍል ኢትዮጵያዊነት ማለት ይህ ነው ፡፡

መልካም ጊዜ
የዛሬ ጥያቄዎች 🔥🔥🔥🔥
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

1) የpop ንጉስ በመባል የሚታወቀው እውቁ ጥቁር አሜሪካዊ አቀንቃኝ ማን ይባላል ?

2) በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ የራሳቸውን አሻራ ከኖሩ ሰዎች መካከል ትልቁን ድርሻ የሚይዙ አንድ አርመናዊ ሰው አሉ ስማቸው ማን ይባላል ?

3) ባሳለፍነው ሳምንት አንዲት አውሮፓዊት ሀገር በcovid-19 ምክንያት የቆመችውን ሊግ ድጋሜ ጀምራለች ይች ሀገር ማን ናት ሊጓስ ምን ይባላል ?

4) አንዲት ደግ ሴት የብዙ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ከሚሰቃዮበት የፌስቱላ ህመም በራሷ ጥረት ለብዙ አመታት ስትታደግ እኔ ሳትታክት ስታገለግል ከርማ በ2012 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት አተናታል ይህቺ እንስት ማን ናት?

5) Oromo - Geda
Sidama- Luwa
Gedeo-???????


Bonus ***______________

* Just we need your participation participate?

መልሱን በ @EthiopianFirst_bot ይላኩልን
ምንም ተሳታፊ አላገኘንም 😭😭😭😭😭
እስካሁን አንድ ተሳታፊ ነዉ ያገኘነው😭😭😭😭
We miss u guys participate😢😢😢
እነ #Endash , #Biruk Girma , #Ame , #Emuye , #whocares ,#jobbir Galanna ,#menen የዘወትር ተሳታፊዎቻችን ዛሬ ጠፍታችዋል😢😢😢 የት ናችሁ
ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
የዛሬ ጥያቄዎች 🔥🔥🔥🔥 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 1) የpop ንጉስ በመባል የሚታወቀው እውቁ ጥቁር አሜሪካዊ አቀንቃኝ ማን ይባላል ? 2) በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ የራሳቸውን አሻራ ከኖሩ ሰዎች መካከል ትልቁን ድርሻ የሚይዙ አንድ አርመናዊ ሰው አሉ ስማቸው ማን ይባላል ? 3) ባሳለፍነው ሳምንት አንዲት አውሮፓዊት ሀገር በcovid-19 ምክንያት የቆመችውን ሊግ ድጋሜ ጀምራለች ይች ሀገር ማን…
የትናንቱ ጥያቄዎች መልስ🔥🔥🔥
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
(ብዙ መላሾች ስላላገኘን በትንሹ ከጥቂት ማብራሪያ ጋር መልሱን ጀባ እንላቸዋለን )
1) የpop ንጉስ በመባል ሚታወቀው አፍሮ አሜሪካዊው ማይክል ጃክሰን ነው ፡፡

2) ነርስስ ናርባንዲያን ሲሆን በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የማይነጥፍ አሻራውን አሳድሯል፡፡ በ1959 የኢትዮጵያን ዜግነት አግኝቷል ፡፡ ለኢትዮ-ጃዝ መፈዘርም የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል ፡፡

3) ጀርመን ስትሆን የሊጓም መጠርያ ቡንደስሊጋ ይባላል ፡፡

4) ካትሪን ሀምሊን አውስትራሊያዊት ስትሆን ከ60,000 ኢትዮጵያውያን ሴቶችን በፌስቱላ ህመም የሚሠቃዩትን አክማለች፡፡


5) Oromo- ባህላዊ የአስተዳደር ስነስርዓቱ Geda ሲሆን በየ8አመቱ የስልጣን ሽግግር ይኖራል ምርጫውም 9 አባገዳዎች ይመረጣሉ ይህም Salgan ya’ii Borana በመባል ይታወቃል ዘጠኑ የቦረና ተወካዮች እንደማለት አንድ አባ ገዳ ለ8 አመት ብቻ በስልጣን ላይ ይቆያል ፡፡ ካንዱ የገዳ ወደ ሌላኛው የገዳ አስተዳደር የሚደረገው ሽግግር Baallii በመባል ይታወቃል ፡፡

Sidama- Luwa በመባል የሚታወቅ ባህላዊ የአስተዳደር ዘዬ አላቸው ፡፡ በየ8 አመቱ በየእድሜ እርከን ይሸጋገራል ፡፡ በLuwa ውስጥ 5 የሽግግር ደረጃዎች አሉ እነሱም ደራራ፣ ፉላሳ፣ ሂሮቦራ፣ ዋሳሳ እና ሞጊሳ በመባል ይታወቃል ፡፡

Gedeo- ልክ እንደ ኦሮሞው ሁላ ጌዲኦ Geda የሚባል ባህላዊ የአስተዳደር ስነስርዓት ያለው ሲሆን አባ ገዳውም ባሌ በሚባል ስነስርዓት በየ8አመቱ ለተተኪው አባ ገዳ ስልጣኑን ያስረክባል፡፡


እናመሰግናለን አብረውን ስለሆኑ!
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
መላሾች

#Walove 4/5 🥇

#Ame
#Yilugnal Wube
#Nigist t
#Firdewsa
#liwam &
#NeverGiveup
#Tekee man ለተሳትፎአችሁ ሁላችሁንም እናመሠግናለን!!!
#LatinAmerica

የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ ላቲን አሜሪካ አዲሷ የኮሮና ቫይረስ /ኮቪድ-19/ ወረርሽኝ #ማዕከል መሆኗን አሳውቋል - #AFP
Top-10© ምርጥ 10

📩ምርጥ 10ን እንሆ ጀባ እንበላችሁ📩

ምርጥ 10ችን ዛሬ ትኩረቱን የሚያደርገው በኛው በሰው ልጆች ብዛት ከ 1-10 ደረጃን የያዙ ሀገራትን ለመዳስ እንሞክራለን ፡፡ ይህ ቁጥራዊ አሃዝ በmarch 3 2020 እንደ ጊሪጎርያን አቆጣጠር የተወሰደ ነው ፡፡

1) ቻይና- 1,439,323,776
2)ህንድ- 1,380,004,385
3)አሜሪካ - 381,002,651
4)ኢንዶኔዥያ - 273,523,615
5)ፓኪስታን - 220,892,340
6) ብራዚል -212,559,417
7) ናይጄሪያ -206,139,589
8) ባንግላዴሽ -164,689,383
9)ሩሲያ -145,934,462
10) ሜክሲኮ - 128,932,753

👉የተቀረው የዓለም ህዝብ ቁጥር 3,293,613,339 ሲሆን በአጠቃላይ የዓለም ህዝብ ቁጥር ደግሞ 7,796,615,710 ነው ተብሎ ይገመታል ፡፡

Source:- Miniwatts Marketing Group.
WWW.internetworldstats.Com

ለሀሳብ አስተያየት / መረጃ ለመስጠትበ @Haile_melekot Or @EthiopianFirst_bot ይጠቀሙ
🔥🔥🔥🔥👍🔥🔥🔥🔥👏🔥🔥🔥
የዛሬ ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥👇👇👇
1) የጀርመን ዋና ከተማ ማን ናት?
ሀ) በርሊን
ለ) ለንደን
ሐ) አንካራ

2) Pentagon ስንት ማዕዘን አለው?
ሀ)5
ለ)6
ሐ) 7

3) ስንት ሴንቲሜትሮች አሉ በ 1ሜትር ውስጥ?
ሀ) 100
ለ) 150

4) የኤርትራ የስልክ መለያ country code ቁጥር ስንት ነው?
ሀ)+253
ለ)+291
ሐ)+251

5) የየትኛው ሀገር ብሔራዊ መዝሙር ነው እጅግ ረጅሙ?

ሀ) ግሪክ
ለ) ቻይና
ሐ) ቱርክ

መልሱን በ @EthiopianFirst_bot ይላኩልን መልካም ዕድል!!
ይሳተፉ መልካም ምሽት መልካም ዕድል!!!
እንኳን ለ 1441ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ውድ የቻናላችን የእስልምና እምነት ተከታዮች
በዓሉ የሠላም እና የጤና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን ፡፡

የጤና ባለሙያዎችን ምክር በመከተል የኮሮና ቫይረስን እንዲከላከሉ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።
#We wish you a Happy Eid