ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.36K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
“ብትችል ብረር፤ መብረር ካልቻልክ ሩጥ፣ መሮጥ
ካልቻልክ ተራመድ፣ መራመድ ካልቻልክ ተንፏቀቅ ግን ምንም
ቢሆን መሄድህን አታቁም”
ማርቲን ሉተር ኪንግ

#ሠናይ ቀን ከሙሉ ጤና ጋር
""" "እናቴ"" """
ፀጉርሽን አይቼ የኔን ፀጉር ሳየው
እንደ ወንድ ፀጉር ገባ ገባ ያለው
እሳት እንደነካው የተኮማተረው
----ለካ ለፍቅር ነው
የፊትሽ ላይ ቆዳ የተሸበሸበው
እንደ ወየበ ልብስ እንዲህ የገረጣው
እንደ ቼዙ ሜዳ የተዥጎረጎረው
--ለካ ለፍቅር ነው
በጉብዝናሽ ወራት በወጣትነትሽ
እነዚያ ውብ አይንሽ
ጎላ ጎላ ያሉት
ከለሊት ጨረቃ ደምቀው የሚታዩት
አሁን ደም ለብሰዋል
አንቺ ለእኔ ብለሽ በጪስና አቧራ
ሰውተሻቸዋል
---ይሄም ለፍቅር ነው
አንቺ የፍቅር አምድ
ተምሳሌት የመውደድ
አንቺ የፍቅር ማዕድ
ልክ እንደከዘራ ጀርባሽ የጎበጠው
አሁን ነው የገባኝ እኔ ቀና እንድል ነው
------አንቺ እንዲህ የሆንሺው ለካ
ለፍቅር ነው
መዳፍሽን ሳየው
አሻራ እንኳን የለው
ድህነት በልቶታል
ሸክም አጥፍቶታል
-----እናም ውዷ እናቴ
ዝምብየ ሳስበው
ምን አይነት ፍቅር ነው
ይሄን ሁሉ የሆንሺው
አንዴት በትወጂኝ ነው።
እማ ዛሬ ፍቅርሽ ገባኝ!!!

#መልካም ቀን
Dear members when u think to leave the channel it's better to leave us the reasons too😉
Inbox us here
👉 @Simetin_Begitimbot/
@Haile_melekot

So we are going to work on it.
በመጠንቀቅ ያተረፈ እንጂ የተጎዳ የለም!

(በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)

የዛሬ ሁለት እና ሶስት ሳምንት አካባቢ የፋሲካው ግርግር ምን ሊያስከትል እንደሚችል በተለያዩ ሚድያዎች ስንሰማ ቆይተናል።

ነገር ግን 'ጆሮ ዳባ ልበስ' ብለን ፤ ሰምተን እንዳልሰማን ሆነን "ኮሮና እኛን አይነካም" በሚል የባለሙያዎችን ትእዛዝ ሳንተገብር ቆየን።

ይባስ ብሎ ደግሞ ቁጥሩ በጣት የሚቆጠር ሲሆን "አይ ፈጣሪ ይጠብቀናል፤ ችግር የለም" እያልን ከኛ የሚጠበቀውን ጥንቃቄ ረስተን ብዙ ተዘናጋን።

የዛሬ ሶስት ሳምንት ገደማ "ለመጠንቀቅ የሞት ዜና አንጠብቅ" ብዬ ከፋሲካ ዋዜማ በስትያ የታዘብኩትን እና ሊመጣ ስላለው ከባድ ጊዜ አያይዤ ፅፌ ነበር። ይኸው ጊዜ ደጉ አሁን ላይ አየነው፤ አሁንም አረፈደብንም ለመጠንቀቅ ጊዜው አለን። እባካችሁ በቁጥር ከፍ እና ዝቅ ማለት ጥንቃቄያችን እና ስሜታች ከፍ ዝቅ አይበል።

ከፍ ሲል"በቃ አለቀልን!!" ዝቅ ሲል ደግሞ" የት አባቱ ኮሮናን ድባቅ መታነው" እያልን ቁጥር ላይ መሰረት አናድርግ።

አሁን ከምን ግዜውም በላይ የምንጠነቀቅበት ሰዓት ላይ ነን ፤ የትላንቱን ስህተት አንድገመዉ።

እባካችሁን እንጠንቀቅ!!

የዛሬዋ የሴኮንድ ስህተት ዘመን ተሻግሮ ጠባሳ እንዳያሳርፍብን እንጠንቀቅ፤ ይሄን ከባድ ጊዜ አሳልፈን ነገን በደስታ እንየው።
እምዬ ኢትዮጵያ ፣ ብትደላም ብትከፋም
ምላስ ናት ለህዝቧ ፣ ከአፋችን አትጠፋም።
።።።
አፍ በሚባል ዋሻ...
ምላስን የሚያህል ፣ ስጋ ተሸክሞ
ስጋ ባለመብላት ፣ ማንስ ያውቃል ፆሞ?!
:::::::::
ፍስክ ምላስሽን ፣ ባፍሽ ተሸክመሽ
ከዋናው የደም ምንጭ ፣ ልቤ ላይ ታትመሽ
ፆመኛ ነኝ ስትይ ፣ ታስገርሚኛለሽ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ወደ ነፍሴ ገዳም ፣ ስትገቢ መንነሽ
ዓለም በቃኝ ስትይ ፣ የኔው ዓለም ሆነሽ
ታስገርሚኛለሽ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
መልካም የፆም ወቅት !!!
(በላይ በቀለ ወያ )

@Simetin_Begitim
ቀለል ያሉ የጠቅላላ እውቀት ጥያቄዎችን እየተጠያየቅን ዘወትር ምሽት ከ2-3:00 እምናሳልፍበትን ሁኔታዎች እያመቻቸን ነው ይቀረብ አይቅረብ የሚለውን ከእናንተው እንረዳ
ይቅረብ👍
አይቅረብ👎
" እናትህ ጠፋች " ይላሉ አማርኛ መምህራችን ጌቱን።
በየሳምንቱ ወላጅ አምጣ ሲባል ለመዷቸው!
የጌቱ እናት፡ ቆንጆ ነበሩ መሰለኝ።
ጌቱ እንዲያጠፋ የሚገፋፉት መምህራንም ነበሩ፡
" የፊደል "ፖ" ን እግር ማነው የዘረጠጠው? "
" ተፈጥሮዋ ነዋ "
" ሴት ናትንዴ? "
" እኔንጃ ቲቸር "
" የመማር ፍላጎትህ ቀንሷል "
ወላጅ እንዲያመጣ " ይጋበዛል " ማለት ነው።
የጌቱ እናት በንቅሳት ብዛት የአለላ ሙዳይ የመሰሉ ነበሩ።
ደልደል ያሉ ናቸው።
ያኔ ታዲያ ቲቸር ይልማ፡
" ልጅዎ ጎበዝ ቢሆንም ከሰነፍ ተማሪዎች ጋር ገጥሟል "
ይሉና ሻይ ለማዘዝ ክበብ ይሄዳሉ።
ጌቱን ጎበዝ አሉት?......ጌቱን?
የጌቱ ስንፍናኮ ነገረኛ ነው።
" How old are you? "...እንግሊዝኛ ትምህርት ላይ
ዓይኑን ጣራው ላይ ሰክቶ......
" ደብተሬ ጠፍቶብኛል ቲቸር "
" ዋናው አንተ መትረፍህ "
አንድ ቀን Class activity ለግሬድ አሪፍ ነው ብለነው፡
ሳይቸግረው እጁን ያወናጭፋል
" እሺ የጌጥዬ ልጅ " አሉ እንግሊዝኛ መምህራችን እናቱን የናፈቁ
አይነት አይናቸው ቡዝዝ እያለ...
" እፉዬ ገላ በእንግሊዝኛ ምንድነው? "
" ቧልት ጀመርክ? "....አሉና እኔ ብቻ በሰማሁት ድምጽ
" እሷን ብየንጂ ፈስህን ነበር የማስረጭህ "
አንድ ቀን እንደተለመደው ወላጅ አምጣ ይባልና፡ አባቱ ከ ፊልድ
መጥተው እረፍት ላይ ስለነበሩ ይዟቸው ይሄዳል።
እናትየዋን የሚጠብቁት ቲቸር በለጠ፡ ጺማቸውን ተላጭተው፡ ሽቶ
ተለቅልቀው ይጠብቃሉ።
የጌቱ አባት ጋሽ ጓንጉል፡ እንደ ኮባ እየተዘናጠፉ ገቡ።
ቲቸር በለጠ በጣም ደነገጡ፡ ንዴት ተጨምሮባቸው፡
" ልጅዎ በጣም ረባሽ፣ አርፋጅ ስንፍናው ለከት የሌለው ነው።
ሌሎችንም ልጆች ያበላሻል....አንድ ቀን የሲጋራ ቁራጭ
ይዞ........."
የጌቱ አባት ልጃቸውን እንደ ዶሮ ዘቅዝቀው መያዝ ጀመሩ!
ከፍ አድርገው እንደ እቃ ጣሉት!
ጌቱ እንደዚያ ቀን አየር ላይ አልበዛብኝም።

Fikre Z Bhere Ethiopia
የመጀመርያ ዙር ቀለል ያሉ የጠቅላላ እውቀት ጥያቄዎች መልሱን @EthiopianFirst_bot ይላኩልን መልካም ዕድል

1) በኢትየጵያ የመጀመርያው ዘመናዊ ትምህርት ቤት ማን ይባላል ?

2) ኢትዮጵያ የአፍሪካን ዋንጫ መች ነው ያነሳችው ?

3) The Father of History በመባል የሚታወቅ ሰው ስሙ ማን ይባላል ?

4) ከአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ብቸኛዋ የእራሷን ፊደል ያላት ሀገር ማን ናት?

5)እግርኳስን ለዓለማችን ያበረከተች ሀገር ማን ናት?


ለመጀመር ያህል በእነዚህ ጥያቄዎች አብረን እናምሽ መልካም ዕድል
እስካሁን ድረስ አንድም መላሽ አላገኘንም 😭😭😭
እስካሁን አንድ ተሳታፊ ብቻ ነው ያገኘነው
Google ማድረግ or ከወዳጅዎ ጋር ተማክረው ይሳተፉ
ለተሣተፋችሁ እናመሠግናለን ትክክለኛውን መልስ እና መላሾች ነገ እናሠውቃለን፡፡
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ አሁን ያለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት የአኗኗር ሁኔታችንን እንድንቀይር ያስገዳል ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል።

ዶ/ር ሊያ ዛሬ በሱጡት መግለጫ እንዳሉት ፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው #በርካታ ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ እየተገኘባቸው ነው።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ሳይኖራቸው ቫይረሱ የሚገኝባቸውም ሰዎች ቁጥር ጨምሯል ሲሉ ተናግረዋል።

የኮቪድ-19 ስርጭት ጎረቤት አገራት ጋር በማይዋሰኑ አካባቢዎችም ጭምር እየሰፋ መጥቷል ያሉት ዶክተር ሊያ 'ይህም አደጋው ወደ እያንዳንዳችን ቤት እየመጣ መሆኑን ያሳያል' ብለዋል።

'የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ሲከሰት በቀላሉ እየጨመረ የሚሄድ የስርጭት ባህሪ እንዳለው ጠቁመው ፤ ስርጭቱ ምን ያህል ይጨምራል የሚለው ጥያቄ ግን በእያንዳንዳችን ጥንቃቄ ይወሰናል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ያለፈው ሳምንት የቫይረሱ ስርጭት ሁኔታ ይህን በግልጽ ያሳየ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመሆኑም ከመደናገጥ ወጥተን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በሚጠይቀው ልክ የአኗኗር ባህሪያችንን መቀየር አለብን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

'መራራቅ ፣ መታጠብ ፣ መቆየት ፣ መሸፈን' የሚሉ አራቱ የኮቪድ-19 “መ” ህጎችን መተግበር ደግሞ ከእያንዳንዱ ዜጋ የሚጠበቅ የጥንቃቄ አማራጭ መሆኑ ዶ/ር ሊያ ገልፀዋል - #ENA
ጓደኛዬ ጌቱ አስጠራኝ፡ ስወጣ ድመት ታቅፏል!
" ለ ሙስጤ እንሽጣት "
" አንተ!..የእትዬ ይርገዱን ድመት? "
" በምን ያውቃሉ?! "
" እሺ በስንት ትሸጥ ?"
" አምስት ብር ነዋ! " ፊልም መከራያ ቸስተን ሰነበትና ታዲያ!
ሙስጤ ግን ገገመ።
" መጀመሪያ አይጥ ይዞ ማየት አለብኝ "
" ምን? "
" አዎና! የሙከራ ጊዜ የሚባል ነገር አለ "
" ድመትኮነው "
" ይሁና! የኮካ ጠርሙስ የመሰለ ድመት !"
ለነገሩ እውነቱን ነው። ድመት ሁሉ ማንደጃ ስር እየሞቀ የቡና
እጣን ይምጋል። አይጥ ብትመጣ፡ የተበተነለትን ፈንዲሻ
ሳይጨርስ አይነሳም!
( ጥድፊያ አይወድም )
ለማንኛውም በ ሶስት ብር ተስማማን።
ያዕቆብ ፊልም አከራያችን ጋር...
" ዛሬ ምን አይነት ፊልም ልስጣችሁ? "
" የቫንዳምን ነዋ "
" ዛሬንኳን ቀየር አድርጉትስኪ! የ ጃኪ ቻንን ልስጣችሁ "
አለና ሰጠን።
ፊልማችንን እንደ አራስ ታቅፈን እነጌቱ ቤት ገባን
ቤተሰብ ተሰብስቧል።
ለፊልሙ ምርቃት ተችሮን ሲያበቃ ተከፈተ!
እንደዚያን ቀን የበሰለ ዱባ የሆንኩበት ቀን ትዝ አይለኝም!
ፊልሙ በጊዜው " ከባህል የወጣ ጋጠወጥ " የሚባለው አይነት
ነውረኛ ነበር!
ሁሉም አሉኮ! ( የምሬን ነው )
ድመት የሰረቅናቸው ይርገዱም ጭምር
" በስመአብ ወወልድ! " አሉ አባቱ
" ምንድነው ይሄ? እረ በመድኔ! "
ደነዘዝን። ለማጥፋት ስንቀሳቀስ ጋሼ ተቆጡ
" ተመለስ ቀልቃላ " አይናቸው ሳይነቀል
እኔና ጌጡ ብርክ ይዞን ስንንዘፈዘፍ
" አሄሄ...መገን ተፈጥሮ! መገን መገን " አሉ የድመቷ የቀድሞ
ባለቤት እትዬ ይርገዱ
በመሃል ከውጭ ሙስጤ አንኳኩቶ ገባ
" እትዬ ይርገዱ ጌቱና ፍቅሬ የሸጡልኝ ድመት የርስዎ ነው ብሬን
ያስመልሱልኝ! "
እማማ ይርገዱ፡-
" ውሰደው! "
Fikre Z Bhere Ethiopia

መልካም ቀን ሠናይ ውሎ
ለፈገግታ😂😂😂

አለቃዬ አዲስ ብራንድ መኪና🚘 እየነዳ ስራ ቦታ ሲመጣ "Wow የሚያምር መኪና ነው" ስለው...
:
#እሱም_እንዲህ_አለኝ 🤔 "ስራህን ጠንክረህ ከሰራህ፣ እያንዳንዷን ሰዓት በአግባቡ ከተጠቀምክ፣ ቀን ሌሊት ሳትል ከሰራህ፤ ቀጣይ አመት ሌላ ተጨማሪ መኪና ይኖረኛል። 😲😳🤣

መልካም ቀን ከሙሉ ጤና ጋር ተመኘንላችሁ
ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
የመጀመርያ ዙር ቀለል ያሉ የጠቅላላ እውቀት ጥያቄዎች መልሱን @EthiopianFirst_bot ይላኩልን መልካም ዕድል 1) በኢትየጵያ የመጀመርያው ዘመናዊ ትምህርት ቤት ማን ይባላል ? 2) ኢትዮጵያ የአፍሪካን ዋንጫ መች ነው ያነሳችው ? 3) The Father of History በመባል የሚታወቅ ሰው ስሙ ማን ይባላል ? 4) ከአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ብቸኛዋ የእራሷን ፊደል ያላት ሀገር ማን ናት? …
የትላንት ጥያቄዎች መልስ እና የመለሾች ስም🔥🔥🔥🔥
መልስ
_
1)ዳግማዊ ሚኒሊክ
2)እንደ ኢትዮጵያውን አቆጣጠር በ1952ዓ.ም
3)ሄረዳተስ(Herodotus)
4) ብቻኛዋ የአፍሪካ ሀገር የሯሷን ፊደል ያላት የኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ 🇪🇹 ናት
5)China(ቻይና)

መላሾች
__
1) #abrsh 3/5
2) #Jobir 1/5
#selam 1/5
#Tekee 1/5

የተሳተፋችሁ እናመሠግናለን ዛሬ ከለል አርገን ከምርጫ ጋር ይዘንላችሁ እንቀርባለን
የዛሬ ጥያቄዎች
👇👇👇👇👇👇👇👇
1) የአለማችን ረጅሙ ህንፃ የሚገኝባት ሀገር የቱ ነው?

ሀ) አሜሪካ
ለ) ኢንግሊዝ
ሐ) ዱባይ

2)የአባይ ተፋሰስ ሀገራት በመባል የሚታወቁት ሀገራት ስንት ናቸው?
ሀ) 9
ለ)8
ሐ)11

3) የትኛው ድርጅት ነው በአለማችን ትልቁ ወንዝ የሚጠራው?

ሀ) አማዞን
ለ) ያሆ
ሐ) Google

4) ከእነዚህ አንዱ ረጅም ነው ?

ሀ) ቀጭኔ
ለ) ዝሆን
ሐ) ነብር

5) የትኛው Planet ነው ለፀሀይ ቅርብ?

ሀ) ማርስ
ለ) ሜርኩሪ
ሐ) ፕሉቶ

መልሱን በ @EthiopianFirst_bot ይላኩልን
ቢያንስ 15 በላይ ተሣታፊ እናገኛለን ብለን ተስፋ እናረጋለን መልካም ዕድል
#Share to ur friends and invite them be our family!