* ኑ .ዛ . ዜ .***
ጌታ ሆይ....
ከሞትኩኝ በሁዋላ....
ሚስቴን እንዳያይዋት፤
ህይወቷን በሙሉ ቤት ዘግተህ አቆያት።
እነዛ ከዋክብት ፣ አብረቅራቂ አይኖቿን
የማታ ብርሀን ፣ የቀን መኩሪያዎቿን
በሌላ ተማርከው ፣ግራ እንዳይገባቸው
መአቱን አውርደህ ድርግምግም አርጋቸው።
...............................................
ገጣባ አርገህ ተወው ፣ ያንን ሐር ጸጉሯን
ሌላ ከሚያይብኝ ፣;ትቅር ባዶ ቅሏን::
..............
ከሞትኩኝ በሁዋላ....
ቀጥ ብሎ የቆመ ፣ ያን ሰልካካ አፍንጫ
ከርክመህ ጣልልኝ ፣ በያዝከው መቁረጫ
ያንን የሚያሰጎመጅ ፣ ያን እንጆሪ ከንፈር
ፍቀድልኝና.....
ወስላታ ሳይቀምሰው ከ'ኔ ጋር ይቀበር::
....................
ከሞትኩኝ በሁዋላ....
እነዛ ጡቶቿን ፣ እንደጦር የሰሉ
ኪንታሮት አክለው ፣ የት ሄዱ? ይባሉ
ያንን ችቦ ወገብ ፣ ቀጥኖ የተሰቀለው
ወጥረህ ወጥረህ ፣ ከበሮ አሳክለው::
.
ከሞትኩኝ በሁዋላ....
ጀግና የሚያሳድድ ፣ ያን ኩሩ ዳሌዋን
ድንገት ንሳትና ፣ ትፈልግ ሁዋላዋን።
በማታ በማታ.....
ወጣ ብሎ መግባት ፣ ሁሉ እንዳያምራቸው
እግሮቿን አልምሸህ ፣ መሄድ ይሳናቸው::
..................
ኡፍፍፍ....
እንዲያውም ወፍ አርጋት ፣ በአየር ትመላለስ
ወንድ አንኩዋኩቶ አይጥራት....
ጎጆዋን በዛፍ ላይ ፣ በስንጥር ትቀልስ።
በቃ....
በፍቅር ጎዳና ፣ ሌላ ከሚመራት
ፈቃድህ ከሆነ …
ሳትሞት በቁሟ ፣ ከ'ኔ ጋር ቅበራት።
.
.
አምላኬ....
መቼም መሄዴ ነው...
ጊዜዬን ጨርሼ ፣ መሰናበቴ ነው
ብቻ አደራህን...ብቻ አደራህን...
ከሞትኩኝ በሁዋላ ፣ ማንም እንዳይነካት
ማንም ተመኝቶ ፣ በልቡ እነዳይለካት።
........
በቃ አልፈልግማ ፣ በቃ እንዳያዩብኝ
ከህመሜ ይበልጥ ፣ አልጋ ላይ ከጣለኝ
ከሞትኩኝ በሁዋላ .....
የሌላ ስትሆን ፣ ማሰቡ ነው 'ሚያመኝ::
ከ #ፌስቡክ_መንደር

ለፈገግታ😂😂😂
አንዱ ቅድም ከሁዋላዬ ድንገት ደረሰና በሁለት እጆቹ አይኖቼን ሸፍኖ " ገምትስኪ ማነኝ!?
.....ክስ መስርቻለሁ!....
credit:- Fikre Z Bhere Ethiopia
#Stay_Home
#Stay_Safe
join us for more @Simetin_Begitim
አንዱ ቅድም ከሁዋላዬ ድንገት ደረሰና በሁለት እጆቹ አይኖቼን ሸፍኖ " ገምትስኪ ማነኝ!?
.....ክስ መስርቻለሁ!....
credit:- Fikre Z Bhere Ethiopia
#Stay_Home
#Stay_Safe
join us for more @Simetin_Begitim
#ዱራ
አህያ ጅብ በላ የሚል ዜና ሰምቶ
ውሻን ያሳድዳል ድመት ከአይጥ ሸሽቶ
ሚዳቋን አምልጦ ነብር ፈረጠጠ
በግ መጣብኝ ብሎ ተኩላ ደነገጠ
ጎሽ ለራሷ ስትል አንበሳን ዘንጥላው
ልጆቿ ሳይመጡ ሄደች ለጅብ ጥላው
ሁዳዴን አስታኮ አቁሞ ንክሻ
ጅብ ሳይሄድ ይጮሀል የኔ ዘመን ውሻ
በዘጠነኛው ሺህ
ስለ እንስሳት ስትፅፍ ሆሄ ይለግማል
በስንኞችህ ውስጥ ጅብ ይደጋገማል
====||====
ከሙሉቀን ሰ•
አህያ ጅብ በላ የሚል ዜና ሰምቶ
ውሻን ያሳድዳል ድመት ከአይጥ ሸሽቶ
ሚዳቋን አምልጦ ነብር ፈረጠጠ
በግ መጣብኝ ብሎ ተኩላ ደነገጠ
ጎሽ ለራሷ ስትል አንበሳን ዘንጥላው
ልጆቿ ሳይመጡ ሄደች ለጅብ ጥላው
ሁዳዴን አስታኮ አቁሞ ንክሻ
ጅብ ሳይሄድ ይጮሀል የኔ ዘመን ውሻ
በዘጠነኛው ሺህ
ስለ እንስሳት ስትፅፍ ሆሄ ይለግማል
በስንኞችህ ውስጥ ጅብ ይደጋገማል
====||====
ከሙሉቀን ሰ•
ለፈገግታ😂😂😂
•ንስሃ ልገባ ሰፈር ያሉ ቄስ ጋ ሂጄ፡ ሁሏንም ጉድ ከሰሙ በኃላ...
.
.
.
.
.
#ቆይ_ለእናትህ
😥😢😭🙆
ፈገግ ብላችሁ ዋሉ
#Stay_Home
#Stay_Safe
©ዝንቅ መዝናኛ
join For more @Simetin_Begitim
•ንስሃ ልገባ ሰፈር ያሉ ቄስ ጋ ሂጄ፡ ሁሏንም ጉድ ከሰሙ በኃላ...
.
.
.
.
.
#ቆይ_ለእናትህ
😥😢😭🙆
ፈገግ ብላችሁ ዋሉ
#Stay_Home
#Stay_Safe
©ዝንቅ መዝናኛ
join For more @Simetin_Begitim
#FightCOVID19
🧼 እጃችሁን በሳሙና እና በውሃ በደንብ ይታጠቡ
👋🏾 አትጨባበጡ/አትሳሳሙ
🙅🏽♀️ ማህበራዊ መስተጋብርን በጣም ይቀንሱ
❌ አስገዳጅ ካልሆነ በቀር ከቤት አይውጡ
🚶♀_____🚶አካላዊ ርቀቶትን በእጅጉ ይጠብቁ
ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
🧼 እጃችሁን በሳሙና እና በውሃ በደንብ ይታጠቡ
👋🏾 አትጨባበጡ/አትሳሳሙ
🙅🏽♀️ ማህበራዊ መስተጋብርን በጣም ይቀንሱ
❌ አስገዳጅ ካልሆነ በቀር ከቤት አይውጡ
🚶♀_____🚶አካላዊ ርቀቶትን በእጅጉ ይጠብቁ
ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
[በላይ በቀለ ወያ]
።
።
"እጄን ወደ ጡቷ ፣ ምን ፈልጌ ላኩት
ምንድን አስቤ ነው ፣ ከንፈሯን የሳምኩት?
ምንድን ነው ምክንያቱ ፣
ጡቷን ስነካካው ፣ ሰውነቷ ሚያልቀው
ከየት አምጥቶ ነው ፣
ከንፈሯን ስስመው ፣ አፏ ማር 'ሚያፈልቀው ?
ጡት እንደሚነካ ፣
ከንፈር እንደሚሳም ፣ ማን ነው ያስተማረኝ ?
ታውቃለች አውቃለሁ ፣
እሷ ከኔ በፊት ፣
ወንድ እንዳልነበራት ፣
እኔ ከሷ በፊት ፣ ሴት እንዳልነበረኝ።"
እያልሁ ስሟገት ፣ ስጠይቅ ራሴን
አወለኩት ልብሷን ፣ አወለቀች ልብሴን
ደግሞ 'ጠይቃለሁ ፣ ነፍሷን እና ነፍሴን።
።።።
ማን ነው ያስተማራት ፣ ማን ነው ያስተማረኝ
ምን እርቃን አስቀራት ፣ ምን እርቃን አስቀረኝ?
ምን እያረግን ነው ፣
ምንድን ያስጮሃታል ፣ ምንድን ነው ሚነዝረኝ?
ብዬ 'ጠይቃለሁ
እሷ ምን ታውቃለች ፣ እኔስ ምን አውቃለሁ!?
።።፣።።።
ደግሞ ግጥሙን አንብባችሁ አላስፈላጊ ቅርርብ ውስጥ ግቡ አሏችሁ ። ተ ራ ራ ቁ!!!
መልካም ምሽት

የጨርቅ ማስክ አዘገጃጀትና ለመስራት የሚመረጡ የጨርቅ አይነቶች፦
ይህንን በተመለከተ ጥቂት ጥናቶች ቢኖሩም አንዱ ካንዱ እንደሚሻል በእርግጠኝነት መናገር ያስቸግራል፡፡ የጨርቁ ውፍረት በጨመረ ቁጥር የተሻለ የመከላከል አቅም አለው ተብሎ ይታሰባል፡፡
ጨርቁን በመያዝ በደንብ የሚያበራን የመብራት ብርሀን ምን ያህል እንደሚያስተላለፍ በመመልከት (light test) የጨርቁን ውፍረት መመዘን ይቻላል፡፡ በቀላሉ ብርሃን የማያስተላልፉ ጨርቆች የተሻለ ይመረጣሉ ማለት ነው፡፡
በአገራችን ሁኔታ ቀላሉ እና ለመተግበር የሚመቸው የጥጥ (cotton) ጨርቆችን መጠቀም ሲሆን በቂ ውፍረት እንዲኖረው ሁለት ተመሳሳይ ልኬት ያላቸውን ጨርቆች መደረብ የተሻለ ነው፡፡
የጨርቅ ማሰክ አስተጣጠብ የጨርቅ ማስክ እንዴት መታጠብ አለበት ከሚለው አንፃር ጥናቶች ባይኖሩም እንደተለመደው በሳሙናና የሞቀ(ትኩስ)ውሃ ማጠብ ቫይረሱን እንደሚገድለው ይጠበቃል፡፡
መረሳት የሌለባቸው ጉዳዮች ማስክ ማድረግ ብቻውን ከኮቪድ19ም ይከላከላል ብሎ ማሰብ ስህተት ነው፡፡ ማስክ መልበስ ከመሰረታዊ ጥንቃቄዎች ጋር ሲቀናጅ የተሻለ ውጤታማ ያደርጋል፡፡
እነዚህም፦
• አካላዊ መራራቅን መተግበር
• አካላዊ ንክኪዎች ማስቀረት
• በተደጋጋሚና በአግባቡ እጅን መታጠብ/በአልኮል ማፅዳት
• ሰዎች በሚበዙባቸው/በሚሰበሰቡባቸውን ቦታዎች አለመገኘት
የጤና ባለሙያዎች ካላቸው የተጋላጭነት ደረጃ አንፃር የጨርቅ ማስኮችን እንዲጠቀሙ ፈፅሞ አይመከርም፡፡ በተቻለ መጠን እንዳስፈላጊነቱ ሰርጂካል ማስክ ወይም N-95 ማስክ መጠቀሙ የተሻለ ነው፡፡
https://yetenaweg.home.blog/2020/04/10/አዲስ-መረጃ-update-ስለ-የፊት-ማስክ/amp/?__twitter_imp
ምንጭ፦BROOK ALEMAYHU
©Tikvah Eth

ለውብ ቀን ....
☮️ሒሳብ አዋቂው ፈረስ ›
✍አሌክስ አብርሃም
☯️የሆነ ጊዜ አንድ የስነልቦና ሊቅ ፈረሱን እየጎተተ ወደአንድ ዩኒቨርስቲ ሄደና ‹‹ ፈረሴ አራቱን የሒሳብ ስሌት ከማወቅ አልፎ ውስብስብ የሂሳብ ስሌቶችን ውጤት እስከማወቅ ደርሷል ካላመናችሁ ፈትኑት›› አለ …በነገሩ የተገረሙ ሙሁራን ዳኛ ሰይመው ፈተና አዘጋጁ …እንግዲህ አፈታተኑ እንዲህ ነው ለምሳሌ 2 ሲደመር 2 ተብሎ ፈረሱ ይጠየቃል ….ከዛም የተለያዩ ሰዎች ቁጥር የተፃፈበት ሰሌዳ ይዘው ይቆማሉ ፈረሱ ቀጥ ብሎ 4 ቁጥር ወደያዘው ሰው ይሄድና በአፍንጫው ይጠቁማል(ምርጫ እንደማለት ነው) ….በቃ ማባዛት ነሽ ማካፈል መደመር ነሽ መቀነስ ውጤቱን በሰከንዶች ውስጥ ቁጭ ያደርገዋል ፈረሱ ….እናም ‹‹እውነትም ፈረሶች ከተማሩ ከሰው ልጆች እኩል ሂሳብ ማወቅ ይችላሉ›› ብለው ደመደሙ ምሁራኑ !!
☯️ባለፈረሱ ግን እንዲህ አለ ‹‹ እናተ የማትረቡ ….ፈረስ መቸም ቢሆን ሒሳብ አይችልም …. ፈረሱ መልሱን የሚያውቀው በልብ ትርታችሁ ነው … ቁጥር ይዘው ከተደረደሩት ሰዎች መካከል ትክክለኛውን መልስ የያዘው ሰው የልብ ትርታ የተሳሳተ መልስ ይዘው ከቆሙት ሰዎች ጋር ሲነፃፀር የተረጋጋ ነው ...እንስሳት ደግሞ የሰውን ስሜት ጠረን በማሽተት ከፍተኛ በሆነ የማድመጥ ችሎታና የእንቅስቃን ፍጥነት በመመልከት የመረዳት ፈጣን ተሰጥኦ አላቸው።
☮በዚች ምድር እውነት ይዛችሁ በቆማችሁ ቁጥር እንኳን አእምሯቸውን የሚጠቀሙ ሰብአዊ ፍጥረቶች እንስሳት በደመነፍስ ይለዩዋችኋል … ፈረሱ የመረጠው የእናተን ዝባዝንኬ ቁጥር አይደለም … እውነት ያረጋጋው ልባችሁን እንጅ !! ወደመልሱም የመራው እውነት ያረጋጋው ልባችሁ ነው !!
ልባችሁ !!❤️
ሰናይ ቅዳሜ መልካም ውሎ ከሙሉ ጤና ጋር ተመኘንላችሁ

ለውብ ቀን
ከ Fikre Z Bihere Ethiopia የFb ገፅ የተወሰደ
እቤት መዋል ከሰጠኝ እድሎች አንዱ ከአበራሽ ( የቤት
ሰራቸኛችን ) ጋር የነበረኝን ተግባቦት ማዳበር ነው።
አልተሳካምንጂ!
የምትናገረው በእርግጥ አማርኛ ነው። ግን አስተርጓሚ
ያስፈልገኛል።
" ወንዲይም! "
" አቤት አበራሽ "
" ኸባጧ ላይ ያለይ ብረት ለገመይ "
" ምን? "
" ሽቅብ! "
" ሽቅብ የሰፈረይ!? አንተና አንዲ ብላቴና ያበጃጃችኋት? "
ማታ ነው የገባኝ፡ ሳተላይት ዲሹ አይሰራም ማለቷ ነበር።
ያው ኸባጧ ማለት ከባጧ ነው፤ ባጥ ማለት ጣራ መሰለኝ።
ብረት ያለችው ደግሞ ዲሹን ነበር።
ለገመይ ለገመች ለማለት ነው። ወይ ፈጣሪ!
*
በቀደም ሲያንቀለቅለኝ፡
" አበሩ! እስኪ ከአገርሽ ለምን እንደወጣሽ አጫውቺኝ? " ብዬ
ጠየኳት። በረጅሙ ተነፈሰችና..." ኧህህ!!!!.........
" ሙጫ ሳለሁ..አበበይ እንዲየው ቁርጮ ዴሃ ነበር። መቼስ ወፈ
ግዝት መሆን አይጣል አንተው! አያቴንኳ የቂጥ ማረፊያ
ቢያኖሩለት በምን እዲል እቴ! ከነልዦቹ ይ'ፋሱ ብለው ሞቱ'ዪ። "
......ትርጉም?.....የደላችሁ! ( ወፍ የለም ).....
" ኋላማልህ...መኮርደዴን ያየ አበበይ ለአንድ እሪያ ጥርስ
ሊያቆናጥጠኝ ቲል እብስ ወዴ ኸተማ...."
መሳቅ ብፈልግም በምኑ ልሳቅ?
" እንዲያውኮ ከቀየው እንዴኔ ዴሟ የፈለቀም አትገኝ! መቼስ
ድረገብ ከመሆን አንዲያፉን ኸተማ ይሻል ብየ ነዉይ "
" ማለት? " አልኩ አምልጦኝ
" ዴፈነብህ? "
" ምን? "
" አይ የኸተማ ሰው!...ዴፈነብህ ወይ? "
.....እርፍ!
" በል እንግዲያው ዴመናው በሯል፡ ኸገበያው ልሂድ "
አሁን እኔ አማርኛን ችየዋለሁ?
ምንድነው ያለችው ግን?
#Stay_Home
#Stay_Safe
በነገራችሁ ምን እንዳለች ሚነግረን ካለ
በ @Simetin_Begitimbot Or በ @Haile_melekot ይላኩልን መልሰን ወደ እናንተው እናደርሳለን
Join us and invite Your friends to our channel
@Simetin_Begitim

ቶሎ ስርአት የሚይዝ ህዝብ ያሸንፋል፤ ይሻገራል!
#Ethiopia : ኢትዮጵያ ያላት አማራጭ የኮሮና ወረርሽኝ ሳይሰራጭ በቶሎ መከላከል ነው። ለዚህ ሁሉም ዜጋ የሚጠበቅበትን ማድረግ አለበት። መጪውን በዓል ቀጣይ ፋሲካ ቀጣይ የረመዳን አለ ቢቻል ሁሉም በየቤቱ ቢያከብር የተሻለ ይሆናል የሚል ሀሳብ አለኝ። አለበለዚያ ከገጠር ወደ ከተማ ለበአሉ የሚመጡ በሽታው በየቤቱ እንዲሰራጭ እድል ስለሚሰጡት ሁሉም በያለበት የማንወጣው አዘቅት ሊከተን ይችላል። ሁላችንም ጥንቃቄ ልናደርግ እና በጋራ ወረርሽኙን ልንከላከል ይገባል።"
አቶ የሺዋስ አሰፋ (የኢዜማ ሊቀመንበር)
እውነት ነው ሁሉም በያለበት ሁኖ እራሱን ቤተሰቡን ብሎም የሚወዳትን ሀገሩን መጠበቅ አለበት ፡፡

ተንከባካቢዎቻችን ለመንከባከብ ምን ያህል ዝግጁ ነን?
ዕውቁ የአጭር ልቦለድ ደራሲ፤ ሩሲያዊው አንቷን ቼክኾቭ አንድ አይረሴ ሀኪም ገፀባህርይ ፈጥሮ በጭንቅላቴ ተቀርጾ ቀርቷል። ሐኪሙ ጊዜውን በምርምርና ሕፃናትን በማከም ራሱን ሙሉ ለሙሉ ከማስገዜቱ የተነሳ እምትወሰልት ሚስቱን መግራት እንኳን አልሆነለትም ነበር። ስለ ሕመምተኞቹ የታመመ ነበር።
ከእለታት አንድ ቀን ግን ከአንድ ታማሚ ሕፃን ተላላፊ በሽታ ተላለፈበት። ቃተተ፤ተሰቃየ ፣ ሞተም።
በዐፄ ቴዎድሮስ ዘመን ተስቦ ገባ። ወረርሽኙ የዐፄውን የቅርብ አጃቢዎቹን ሳይቀር ገደለ። ቁጥራቸው ተመናመነ። በዚህ የተነሳ በሰፈሩበት ደብረታቦርና በአካባቢው ሁከትና ጭንቅ ሆነ።
ወረርሽኙን ለመግታት ከባህል ሕክምና አዋቂዎች ሌላ በዶክተር ሄንሪ ብላንክ ትከሻ ላይ ወድቆ ነበር። ras-ODORE መፅሐፍ ውስጥ ፣ ሄንሪ ብላክ ተላላፊው እንዳይተላለፍበት እንዴት ይጠነቀቅ እንደነበር ጽፏል።
ከላይ እንደተጠቀሱት ዓይነቶች በጎ አድራጊዎች በየዘመኑና አገሩ አሉ። ሌላውን አድናለሁ ሲሉ ራሳቸው በተላለፊው ታድነው መስዋዕትነት የከፈሉ ጥቂቶች አይደሉም። የሕክምና ባለሙያዎች፣ፍቃደኛ በጎ አድራጊዎች ፣ ከጉዳዩ ጋር በቅርበት የሚሰሩ የመንግሥት ሹማምንትና ሌሎችም....
ተንከባካቢዎቻችንን መንከባከብ ማለት ለራሳቸው ጊዜ እንዲሰጡ፣ራሳቸውንም እንዲጠብቁ ማገዝ ማለት ነው። ተንከባካቢዎቻችንን መንከባከብ ማለት ራስን መንከባከብ ማለት ነው።
ተንከባካቢዎቻችንን መንከባከብ ማለት ሌሎች ታማሚዎችንና ገመምተኞችን እንዲከባከቡልን ማድረግ ማለት ነው። አገር የምታደርገውም የምትታደገውም በተንካባካቢዎቿ እጅ ነው!
ይህ የሚሆነውን ደግሞ ራሳችንን ስንጠብቅና እርስ በርስ ስንጠባበቅ ነው። እናስ? ተንከባካቢዎቻችን ራሳቸውን በጥንቃቄ ተንከባክበው፣ሌላውንም አክመው በሕይወት ለመቆየት ምን ያህል ተዘጋጅተዋል? እኛስ ተንከባካቢዎቻችን ለመንከባከብ ምን ያህል ዝግጁ ሆነናል..?
#ምንጭ:- እንዳለጌታ ከበደ (ታዛ ወርሃዊ መፅሔት ) ላይ ተቆንጥሮ የወጣ!
©ስብእናችን Humanity

# አውነት እና # እምነት
እውነትን ፍለጋ
ወዳሰብነው ስንዘል ~ የያዝነውን ለቀን
እምነት መሐል ላይ ነው
ስተን እንዳንወድቅ ~ ፀንቶ ሚጠብቀን
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
እውነትን ፍለጋ
ወዳሰብነው ስንዘል ~ የያዝነውን ለቀን
እምነት መሐል ላይ ነው
ስተን እንዳንወድቅ ~ ፀንቶ ሚጠብቀን
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
#የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ምልክት የታየባቸው ግለሰቦች #በነጻ የስልክ መስመር ወይም አቅራቢያቸው ወደሚገኙት ጤና ተቋማት ብቻ ጥቆማ መስጠት ይገባቸዋል❗️
⚡️አንዳንድ ግለሰቦች በስህተት አዲስ ወደ ተከፈቱ የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ማዕከል ለምርመራ እያቀኑ መሆኑ ታውቋል። ይህም ደግሞ ፈጽሞ ስህተትና ተቋሞቹ ናሙና በመቀበል ምርመራ የሚያደርጉ ማዕከላት እንጂ ቀጥታ የቫይረሱ ምልክት የታየባቸውን ሰዎች በአካል ተቀብሎ የሚመረምሩ ስላልሆኑ የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ምልክት የታየባቸው ግለሰቦች በነጻ የስልክ መስመር ወይም አቅራቢያቸው ወደሚገኙት ጤና ተቋማት ብቻ ጥቆማ መስጠት ይገባቸዋል፡፡
⚡️በመሆኑም ማንኛውም ግለሰብ የቫይረሱ ምልክት ከታየበት(ባት) በሃላፊነት ስሜት ራሱ(ሷ)ን ለይቶ(ታ) በማቆየት በነጻ ስልክ ቁጥሮች በመደወል አልያም ደግሞ ወደ አቅራቢያቸው ወደሚገኙ ጤና ተቋማት ሪፖርት ማድረግ ያስፈልጋል።
⚡️ይህንንም ተከትሎ በአቅራቢያቸው የሚገኙ ጤና ተቋማትም ኮሮናቫይረስን ለመከላከል ከተቋቋመው ኮሚቴ ጋር በመወያየት በግለሰቦቹ ሁኔታ ላይ ውሳኔ የሚሰጡ ናቸው።
⚡️ህብረተሰቡ በአዲስ አበባ 8335 ወይም 952፣ በትግራይ 6244፣ በአፋር 6220፣ በአማራ 6981፣ በኦሮሚያ 6955፣ በሶማሌ 6599፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ 6016፣ በደቡብ 6929፣ በሐረሪ 6864፣ በጋምቤላ በ6184ና በድሬዳዋ 6407 ነጻ የስልክ መስመር በመጠቀም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
©Ministry of Health

እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
(ልዑል ሀይሌ)
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
መንገድ ጥረጊልኝ
ይህቺን ብቻ አርጊልኝ!
.
ስምሽን እያነሱ
እንዳያስታውሱኝ
በሞተው ትዝታ
እንዳይቀሰቅሱኝ
ያንቺ አለመሆኔን
ዛሬ እንዳሳያቸው
ጨረቃን ፀሐይን
ምድር አውርጂያቸው
ውቅያኖስ ባህሩን
ሰማይ ስቀያቸው
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
የረገጥነው አስፋልት
የሄድንበት መንገድ
ያ ያለፈው ፍቅር
ያ ያለፈው መውደድ
ፍፁም ውሸት ብዬ
እንድሸመጥጠው
ተፈጥሮን አዛቢ
መውደዴን እንድተው
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
ገደሉን ሙዪና
ተራራውን ናጂው
ደመናን አውርደሽ
አፈሩን ውሰጂው
የረገጥሽው መሬት
አምሮ እንድታይበት
በአበባው ፋንታ
ሳማ ትከይበት
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
ያ ሁላ ቃል ኪዳን
ተበትኖ እንዲቀር
አይጥ ሀይቅ ትዋኝ
ዓሳ ሰማይ ይብረር
በህይወት ባሉት ምትክ
ሙታኖች ይነሱ
ነገስታት ይውረዱ
ባርያዎች ይንገሱ
.
ይሄን ካረግሽልኝ
መውደዴን ይቅርና
መኖር አቆማለሁ
በመኖር ብረሳሽ
ባለመኖርም ውስጥ
አስታውስሻለሁ
#Stay_Home
#Stay_Safe
(ልዑል ሀይሌ)
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
መንገድ ጥረጊልኝ
ይህቺን ብቻ አርጊልኝ!
.
ስምሽን እያነሱ
እንዳያስታውሱኝ
በሞተው ትዝታ
እንዳይቀሰቅሱኝ
ያንቺ አለመሆኔን
ዛሬ እንዳሳያቸው
ጨረቃን ፀሐይን
ምድር አውርጂያቸው
ውቅያኖስ ባህሩን
ሰማይ ስቀያቸው
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
የረገጥነው አስፋልት
የሄድንበት መንገድ
ያ ያለፈው ፍቅር
ያ ያለፈው መውደድ
ፍፁም ውሸት ብዬ
እንድሸመጥጠው
ተፈጥሮን አዛቢ
መውደዴን እንድተው
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
ገደሉን ሙዪና
ተራራውን ናጂው
ደመናን አውርደሽ
አፈሩን ውሰጂው
የረገጥሽው መሬት
አምሮ እንድታይበት
በአበባው ፋንታ
ሳማ ትከይበት
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
ያ ሁላ ቃል ኪዳን
ተበትኖ እንዲቀር
አይጥ ሀይቅ ትዋኝ
ዓሳ ሰማይ ይብረር
በህይወት ባሉት ምትክ
ሙታኖች ይነሱ
ነገስታት ይውረዱ
ባርያዎች ይንገሱ
.
ይሄን ካረግሽልኝ
መውደዴን ይቅርና
መኖር አቆማለሁ
በመኖር ብረሳሽ
ባለመኖርም ውስጥ
አስታውስሻለሁ
#Stay_Home
#Stay_Safe
አብዝተን መጠንቀቃችን ለጤናችን!
ከሰሞኑን የበዓል መቃረብን ተከትሎ በአንዳንድ አካባቢዎች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጉዳይ የተረሳ ይመስላል።
ንግዱ ተጧጡፏል ፣ የትራንስፖርት ሁኔታውም እያደረ ቀድሞ ወደነበረበት ሁኔታ እየተመለሰ ነው፣ በየመንገዱ ያለ መጨናነቅ፣ በየሬስቶራንቱና ካፌው ያለው የሰው ብዛት ፣ ጥንቃቄ የጎደለው እንቅስቃሴ ዋጋ እንዳያስከፍለን።
በመጪዎቹ ዓመታት ብዙ በዓላትን አብረን ተሰብስበን በደስታ እንድናሳለፍ ዛሬ በገበያ ቦታው፣ በትራንስፖርቱ፣ በሁሉም ቦታ የመጨረሻውን አቅማችንን ተጠቅመምን ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል።
በዚህ ወቅት ፣ የተለያዩ በርካታ ሰዎች የሚሰበሰቡባቸው ዝግጅቶች አያስፈልጉም፣ ወጣቶች አብሮ መጠጣቱ፣ አብሮ መብላቱ ሌላ ጊዜ ይደርሳል። ሁሉንም ጤና ስንሆን ማድረግ እንችላለን። ነገ ለማየት ዛሬን መጠንቀቅ አለብን።
ከሰሞኑን በአሜሪካ 'ኒውዮርክ ሆስፒታል' የድንገተኛ ክፍል ሃኪም፣የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ፣በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር እና የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስተር አማካሪ የሆኑት ዶክተር ጽዮን ፍሬው በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ላይ ያጋሩትን መልዕክት የማንቂያ ደውል ከሆንነን በድጋሚ እናንብበው፦
"ኢትዮጵያ እዚ በቺካጎ ከተፈጠረው እንማር። አንድ በሽታው እንዳላበት ያለወቀ ሰው ለቅሶ እና ከዛም ልደት ግብዣ በመሄዱ 16 ሰው ታሞ 3 ሰው ሞቷል። እባካችሁ ግብዣው እና ድግሱን ለሌላ ቀን እናርገው። አለበዚያ ለቅሶው ይበዛል።"
በተደጋጋሚ ስጋታችንን የምንገልፀው ፣ ዋጋ እንዳያስከፍለን ብለን የምንጮኸው በሌሎች ሀገራት እየሆነ ያለውን እያየን ስለሆነ ነው። እንዴት ሳምንታት እየተቆጠሩ ሲሄዱ ዋጋ እንደሚያስከፍልምስለተገነዘብን ነው። ድምፃችን እስኪዘጋ እንጮሃለን፣እጃችን እስኪዝል ድረስ እንፅፋለን።
©TIKVAH-ETH

✍Fikre Z Bhere Ethiopia©ፈገግ ብላችሁ ዋሉ
የፋሲካ ትዝታ!
°°°°°°°°°°°°°
የሰፈራችን አባቶች የገዙት በሬ አንድ አይን አልነበረውም!
የት ዘምቶ እንደሆነ እንጃ!
እንደ ጭቃ ሹም ታጅቦ መጣ።
አረማመዱ መቼም የጤና አልነበረም። ልክ የሰፈራችን የቆሻሻ
ገንዳ አጠገብ ሲደርስ ደነበረ!
ተፈነጣጠረ!
አባቶቻችን እንደ ዝምብ መንጋ ዝዝዝዝ..ብለው ተበተኑ!
" ያዘው! ያዘው! "
ከወኔ ውጪ ሰውነት የሌላቸው ጋሽ ብሩ ቁልቁል የሚንደረደረውን
በሬ በሩጫ ተከተሉት
...ግን ተሳሳቱ--- ፈጠኑ....በጣም!
በሬው ቀጥ ብሎ ሲቆም ጋሽ ብሩ ፍሬናቸውን በጥሰው እግሩ ስር
እንደ ሊስትሮ.....
መቼም ያ በሬ ሳር ቢያገኝንኳ እንደዛ አይጎመጅም!
በቀንዱ ዘገናቸው! ( የምሬን ነው )
እንደ ጀላቲ ቀንዱ ጫፍ ላይ ሰክቷቸው ሲታይ የፈረንጅ አጋዘን
ይመስል ነበር።
" በህግ አምላክ! "....አሉ አየር ላይ ( ማንን ይሆን? )
በሬው ጋሽ ብሩን አንጠልጥሎ ወደገንዳው ተመለሰና ገንዳው
ውስጥ ጨመራቸው!( እንደታዘዘ )
ተረኛ የሚዘገን ሲፈልግ፡ ሰዉ ተተራመሰ!
ዞሮ ዘሎ ሲመጣ ጋሽ ብሩ ከገንዳው ብቅ አሉ!
አልጋ ስር የተረሳ ጫማ መስለው..
" ኮፍያዬን አላያችሁም? "
" አላየንም "
" ያችኋትናኮ አቀብሉኝማ "
" ሌላ ቀን ይውሰዷት "....በዚያ ላይ
" ቢወጋንስ? "
" እኔ አባታችሁ እንዴት ልውጣ ታዲያ? "
እንዳይወጡ ቆሟል ፊት ለፊት
" ኧረ ጠነባሁ ጎበዝ "
መቼስ ብዙ ስቀናል ያኔ። በስንት መከራ ተሸነፈ!
ታርዶም ጣጠኛ ነበር
የታረደ ቀን ጠዋት ቅርጫው ላይ ጫጫታ ይሰማል
ጨጓራው ተሰረቀ!
ያው ከሮቤል ውጪ መቼም ማንም አይሆንም!
የነሮቢ በር በሃይል ተንኳኳ!...ሮቢ ከፈተ
" ጨጓራውን መልስ! "
" ኧረ ጋሼ! የምን ጨጓራ? "
" ዛሬ ፊኛህን ተሰናበት! ልቆምበት ነው "
" እኔ አላየሁምኮ "
" ምንድነው በመዘፍዘፊያው ያስቀመጥከው "
" የባቢ ሽንት ጨርቅ ነው "
" በፈርስ ነው የምታለቀልቀው? "
#Stay_Home
#Stay_Safe
የፋሲካ ትዝታ!
°°°°°°°°°°°°°
የሰፈራችን አባቶች የገዙት በሬ አንድ አይን አልነበረውም!
የት ዘምቶ እንደሆነ እንጃ!
እንደ ጭቃ ሹም ታጅቦ መጣ።
አረማመዱ መቼም የጤና አልነበረም። ልክ የሰፈራችን የቆሻሻ
ገንዳ አጠገብ ሲደርስ ደነበረ!
ተፈነጣጠረ!
አባቶቻችን እንደ ዝምብ መንጋ ዝዝዝዝ..ብለው ተበተኑ!
" ያዘው! ያዘው! "
ከወኔ ውጪ ሰውነት የሌላቸው ጋሽ ብሩ ቁልቁል የሚንደረደረውን
በሬ በሩጫ ተከተሉት
...ግን ተሳሳቱ--- ፈጠኑ....በጣም!
በሬው ቀጥ ብሎ ሲቆም ጋሽ ብሩ ፍሬናቸውን በጥሰው እግሩ ስር
እንደ ሊስትሮ.....
መቼም ያ በሬ ሳር ቢያገኝንኳ እንደዛ አይጎመጅም!
በቀንዱ ዘገናቸው! ( የምሬን ነው )
እንደ ጀላቲ ቀንዱ ጫፍ ላይ ሰክቷቸው ሲታይ የፈረንጅ አጋዘን
ይመስል ነበር።
" በህግ አምላክ! "....አሉ አየር ላይ ( ማንን ይሆን? )
በሬው ጋሽ ብሩን አንጠልጥሎ ወደገንዳው ተመለሰና ገንዳው
ውስጥ ጨመራቸው!( እንደታዘዘ )
ተረኛ የሚዘገን ሲፈልግ፡ ሰዉ ተተራመሰ!
ዞሮ ዘሎ ሲመጣ ጋሽ ብሩ ከገንዳው ብቅ አሉ!
አልጋ ስር የተረሳ ጫማ መስለው..
" ኮፍያዬን አላያችሁም? "
" አላየንም "
" ያችኋትናኮ አቀብሉኝማ "
" ሌላ ቀን ይውሰዷት "....በዚያ ላይ
" ቢወጋንስ? "
" እኔ አባታችሁ እንዴት ልውጣ ታዲያ? "
እንዳይወጡ ቆሟል ፊት ለፊት
" ኧረ ጠነባሁ ጎበዝ "
መቼስ ብዙ ስቀናል ያኔ። በስንት መከራ ተሸነፈ!
ታርዶም ጣጠኛ ነበር
የታረደ ቀን ጠዋት ቅርጫው ላይ ጫጫታ ይሰማል
ጨጓራው ተሰረቀ!
ያው ከሮቤል ውጪ መቼም ማንም አይሆንም!
የነሮቢ በር በሃይል ተንኳኳ!...ሮቢ ከፈተ
" ጨጓራውን መልስ! "
" ኧረ ጋሼ! የምን ጨጓራ? "
" ዛሬ ፊኛህን ተሰናበት! ልቆምበት ነው "
" እኔ አላየሁምኮ "
" ምንድነው በመዘፍዘፊያው ያስቀመጥከው "
" የባቢ ሽንት ጨርቅ ነው "
" በፈርስ ነው የምታለቀልቀው? "
#Stay_Home
#Stay_Safe
#DrTsionFirew
በአሜሪካ 'ኒውዮርክ ሆስፒታል' የድንገተኛ ክፍል ሃኪም፣ የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ ፣በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰርና ጤና ሚኒስተር አማካሪ የሆኑት ዶክተር ጽዮን ፍሬው ከሰሞኑን የኮሮና ቫይረስ ይዟቸው እንዳገገሙ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።
ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት ከሰሞኑን ዶክተር ፅዮን ፍሬውን በተለያዩ ጉዳዮች አነጋግሮ ነበር። ዶክተር ፅዮን ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዩን መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ አስተላልፈዋል ፦
በሽታው ስር ሳይሰድ በፊት መንግሥት እና የሚመለከታቸው ተቋሞች (ጤና ሚንስቴር እና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት) የሚያወጧቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች መከተል ይገባል።
ሰው አላግባብ መደንገጥ ሳይሆን የሚነገረውን ማድረግ አለበት፤ በማኅበራዊም ይሁን በማንኛውም ጉዳይ አትሰብሰቡ እየተባለ ሰው መሰብሰብ ካላቆመ በሽታው ይስፋፋል።
በተለይም በአሁን ወቅት “መዘናጋት ትክክል አይደለም። የምናውቀው ሰው እስኪሞት መጠበቅ የለብንም፤ ቁጥሩ 40 ሺህ ወይም 60 ሺህ እስኪደርስ መጠበቅ የለብንም። በጣም የምወደው ሰው ከዚህ በሽታ ሊሞት ይችላል ብለን እናስብ።
መዘናጋት በበሽታው የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር ከፍ ከማድረጉም ባሻገር፤ ቫይረሱ ስጋት የሚሆንበትን ጊዜም እንደሚያራዝመው ያስረዳሉ።
በተጨማሪም ቤት መቀመጥና እጅ መታጠብን የመሰሉ ተግባሮች ቀላል ቢመስሉም የበርካቶችን ሕይወት ይታደጋሉ።

ይሄም ያልፋል!
'በኒውዮርክ ሆስፒታል' የድንገተኛ ክፍል ሃኪም፣ የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ ፣በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር ጽዮን ፍሬው ያስተላለፉት መልዕክት ፦
ኢትዮጵያ-ፋሲካን ዳግማዊ ትንሳኤን እና መጪ ሰርጎችን እንደ በፊት ተሰባስቦ በአንድነት መታደም ባለመቻላችን አንዳንዶቻችን በጣም እንዳዘንን እረዳለሁ።
ዛሬም ሆነ ነገ የመጣብን ክፉ ጠንቅ እስኪያልፍ ራሳችሁን ከአካላዊ መቀራረብ ስላራቃችሁም እናመሰግናለን።
አንዳንድ ወገኖች 'እረ ለፋሲካማ ተራርቀን አይሆንም!' ብላችሁ ለጠየቃችሁኝ መልሴ ቅልጥ ባለ ጦርነት ውስጥ ጥይት አየር ላይ ከወዲህ ወዲያ እየበረረ ቦምብ እዚህም እዚያ እየፈነዳ እንሰባሰብ አትሉም አይደል?
የጦርነት አውድማው ሆስፒታል ሆነ እንጂ ይሄንንም እንደዛ አስቡት ጦርነት ላይ ነን። እኛ የጤና ባለሙያዎቹ እየተፋለምን ነው። ስለዚህ በቤቶቻችሁ ሆናችሁ በዓሉን በሐሴት አክብሩ። ገበያውም ላይ እንጠንቀቅ አይዞን ይሄም ያልፋል!