ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.36K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
በጎዳና ላይ ላሉ፣ ምጽዋት ለሚቀበሉ ዜጎችም ቅድመ ጥንቃቄው ያስፈልጋቸዋል......

ኮቪድ-19 በሽታ አምጭ የሆነው ኖቨል ኮሮና ቫይረስ ዋና ዋና መተላለፊያ መንገዶች

1. በቫይረሱ የተጠቃ ግለሰብ በሚስልበት ወይም በሚያነጥስበት ወቅት በሚወጡ ፍሳሾች አማካኝነት፣

2. በኖቨል ኮሮና ቫይረስ በተጠቃ ግለሰብ በተነካኩ ቁስ አካሎች ማለትም እንደ ጥሬ ገንዘብ በመሳሰሉት በኩል ሊተላለፍ እንደሚችል፣

3. ቫይረሱ የሚተላለፈው በእጃችን አፋችንን፣ አፍንጫችን ወይም ዓይናችንን ስንነካካ እንጂ በእጆቻችን ባሉ የቆዳ ቀዳዳዎች አይተላለፍም፡፡

ይሁንና በርካታ ዜጎቻችን በምጽዋት በሚያገኙት ገንዘብ ጉሮሮሯቸውን ይደፍናሉ ታድያ ለእነዚህም ዜጎቻችን በደንብ ልናስብላቸው ይገባል፡፡ በተለይ ስለ ጥንቃቄው በጎፈቃደኞች ንጽህና መጠበቂያ በመስጠትና እነሱን ማዕከል ያደረገ እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡

#ቲክቫህ_ጥቆማ
@tikvahethmagazine @emush21
የደረሰ ትንቢት
---------
.
(ሚካኤል እንዳለ)
.
እንደ ሽሪሚሪ
እንዳለቀ ሱሪ
እምነት ከላይ ከላይ ፥ ስለተለበጠ
ፌጦና 'ነይ ሽንኩርት ፥ ከእግዜሩ በለጠ
አይ ጊዜ ቀላጁ
አውጥቶ አውራጁ
ጉልቤን አሰጋጁ
በአይን የማይታይ ቅንጣት አስከትሎ
ሃያል ሃገር ታየ ፥ እንደ ቅጠል ቀሎ
፡፡፡፡
ሲበሉ ስንበላ
የነሱን አግዝፈን የኛን ስንጠላ
አብረን ስንጎተት ከኋላ እንደ ጥላ
ሲሄዱ ሳንጠይቅ ፥ እምዲው ስንከተል
የቆጥ ላይ አንጋጠን የብብቱን ስንጥል
ሲስቁ ስንስቅ ሲዘሉ ስንዘል
ሲያብዱ አብረን አብደን
በቀደዱት ትቦ እንደ ጅረት ፈሰን
ሲያለቅሱ አልቀስን
የሆኑትን ሆነን
ለሃገር ለእምነት ጠበቃ እንዳልሆንን
በሥስት ቁር ደርቀን ማህተብ አላላን
ሃይማኖትን ሽጠን ፥ ቁራሽ ዳቦ በላን
የነብስን ዘንግተን ፥ የስጋን ሞት ፈራን
አምላክ እንደሌለው እነሱ ሲፈሩ አብረናቸው ፈራን
፡፡፡፡፡
አቋራጭ ነው ብለህ በማታውቀው ልማድ
እንደ ግንደ ቆርቁር ፥ ሺ 'ባሕል ለመናድ
ተጉዘሃልና ፥ በሄዱበት መንገድ
እነሱን መከተል ፥ በበሽታም ልመድ
፡፡፡፡
ጊዜ ለምዶ ሩጫ
አብዝቶብን ጩጫ 
ሲወቅጠን ሰብስቦ በአንድ ሙቀጫ
የቀደመው መንገድ ቢጠፋን አቅጣጫ
ጠበሉን እረስተን ቁርባኑን ዘንግተን ፥ ወ'ዳልኮል ሩጫ
ይልቅ አትፈትነው
የእግዜርን ቁጣ ታጥበህ ላታጸዳው
ምናልባት እራርቶ ቁጣውን ቢተወው
ከደጁ ተደፍተህ ፥ ይቅር ይቅር በለው
ከ'እጅህም በላይ የህሊናህን ቋት ራስህን ታጠበው
.
( ሚካኤል እንዳለ )
ጥንቃቄ አሁንም ጥንቃቄ እራሳችውን ከcovid-19 ጠብቁ ፡፡ ሁሉንም የጥንቃቄ መንገድ ተከተሉ ፡፡ እራስዎን ጠበቁ ማለት ቤተሠቦን አካባቢዎን ብሎም ሀገሮን ጠበቁ ማለት ነው ፡፡
Forwarded from ዝንቅ መዝናኛ (Mr. Nobody)
ሁልሽም ፕሮፋይልሽን ወደ ጥቁር ከመቀየርሽ በፊት እንጠንቀቅ!!

ብዙ እድል ተሰጥቶናል፤ በአግባቡ እንጠቀምበት። ይህ በሽታ በመንግስት አቅምና ጥንካሬ ሳይሆን በግለሰቦች ጥንቃቄ ስለሆነ የጉዳት መጠኑ የሚወሰነዉ እያንዳንዳችን የግላችንን ጥንቃቄ እናድርግ። በኃላ ማንም ተወቃሽ ማንም ወቃሽ መሆን አይችልም በዚህ ጉዳይ። ጣሊያን፣ ስፔን፣ አሜሪካና ኢራን ከኛ የተሻለ የጤና አጠባበቅ system አላቸዉ፤ ግን አልዳኑም። ጣሊያን ዛሬ ከቻይና የበለጠ ሞት በትንሽ ጊዜ አስመዝግባለች። ወገኖቼ የአየር መንገድ በራራ በማስቆም ቢሆን ጣሊያንን አሜሪካ እንኳን አልቀደመቻትም። ግን የሚሆነዉን እያየን ነዉ። ትላንት ጣሊያን የአለም ሪከርድ የሆነዉን የሞት መጠን አስመዝግባለች። ስለዚህ ለሁሉም ነገር ሰበብ መፈለጉንና ጣት መጠቋቀሙን ትተን በግል እንዲሁም በቤተሰብ ደረጃ ጥንቃቄ እናድርግ። ይህ በንዝህላልነት በኢትዮጵያ ላይ ብቻ የመጣ ጋሬጣ ሳይሆን በአለማችን ላይ ዘር፣ ቀለም ሳይል የመጣ የሁላችንም ፈተና ነዉ። አንድ ላይ ከተባበርን፣ እያንዳንዳችን የየራሳችንን ኃላፊነት ከተወጣን ይህን ወረረሽኝ ብዙ እልቂት ሳያስከትል መቆጣጠር እንችላለን። ካልሆነ ግን ነገ ፕሮፋይል አይደለም ቆዳችንን ብንገለብጥ ምንም ለዉጥ አናመጣም። ዛሬም ያለንን ትንሽ ሰዓት ቁም ነገር እንስራበት።

የወረረሽኙን መጠንና ክብደት ያልተረዱ ብዙ ወገኖች ስላሉ ይህንን መልዕክት በሁሉም ሶሻል ሚድያ ላይ በማጋራት የበኩላችንን እንወጣ።

#Share
#Please
#BeSeriousCoronaIsSerious

@ZiniQ ዝንቅ መዝናኛ
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ለወጣቶች መልዕክት አስተላልፈዋል። ያዳምጡ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በመጨረሻም፦

ኮቪድ-19ን ማቆም ይቻላል!

• ሕመም ከተሰማዎ ፣ ትኩሣት ካለዎ ፣ የሚያስልዎና የሚያስነጥስዎ ከሆነ ፣ እባክዎ ለከፋ መዘዝ ጊዜና ዕድል አይስጡ።

• በቤት ውስጥ ማስታገሻዎችና በባሕላዊ ሕክምና አይተማመኑ፤ አይረዱዎትም። ፈጥነው ለጤና ባለሙያ ይጠቁሙ። ሌሎችንም ይጠብቁ።

• ሲያስሉ ወይም ሲያስነጥስዎ አፍዎ እና አፍንጫዎን በክንድዎ መጋጠሚያ በደንብ ይሸፍኑ፤ እጆችዎን አያነካኩ።

• ዐይኖችዎን ፣ አፍዎን ፣ አፍንጫዎን ጆሮዎችዎን ላለመነካካት ይንቁ፣ ይጠንቀቁ

• እጆችዎን በሣሙናና በብዙ ወራጅ ውኃ ይታጠቡ፤ ውኃና ሣሙና አጠገብዎ ከሌለ በማንኛውም አልኮሆል ያብሷቸው።

• ከልጆች ጋር ስለኮሮና ቫይረስ /ኮርቪድ-19/ ይነጋገሩ። ልጆች ሁልጊዜ እጆቻቸውን እንዲታጠቡ ያለመታከት ይምከሯቸው። ልጆች ከታመሙ ጓደኞቻችው እና ሌሎችም የታመሙ ሰዎች እንዲርቁ ይንገሯቸው።

• በአካባቢዎ የሚያስለው ወይም የሚያስነጥስ ሰው ካለ በአንድ ሜትር ያህል ይራቁ።

• መረጃዎችን ከባለሙያዎች፣ ከባለሥልጣናትና ከታመኑ ምንጮች ብቻ ያግኙ። ባልተጨበጠ ሹክሹክታና በ‘ይባላል’ አይተማመኑ

• ስለኮቪድ-19 ድብቅ ነገር የለም፤ በግልፅ ይወያዩ።

• ‘ለኖቬል ኮሮና ቫይረስ ተጋልጠዋል’ ወይም ‘ኮቪድ19 ጉንፋን ወይም ኢንፍሉዌንዛ ይዞዎታል’ ቢባሉ አይደንግጡ፤ አይረበሹ! አይረዱዎትምና። ይልቅ የጤና ባለሙያ የሚልዎትን ከልቦናዎና በትዕግሥት ይስሙ፤ ያዳምጡ። የሚሰጡዎትን የባለሙያ ምክሮች እንደተባሉት ይፈፅሙ።

ኮሮና ቫይረስን አንተ ማቆም ትችላለህ፤
ኮሮና ቫይረስን አንቺ ማቆም ትችያለሽ!
#VOA

ረጅም እንድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
ሰላም እደሩ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
(ገጣሚ በረከት በላይነህ)
............
እንደነገርኩሽ ነው
አፍሽም ለብቻው ስሙን እያወጣ
ጆሮሽም ለብቻው ስሙን እያወጣ
ወየው ወየው እንጂ ወዬ የሚል ታጣ
.
አምላክም እንደ ሰው
ባለመስጠት ሞላ ከመስጠት ጎደለ
ብጠራው ብጠራው አቤት አልል አለ
ማለትሽን ሰምቼ ምስኪን አመልሽን
ከመልክሽ አዛምደሽ ከምትጠረጥሪው
እስቲ ቅፅሉን ተይና በዋና ስም ጥሪው
.
ሰሚን ሲበድሉ ጠሪን ሲበድሉ
ለጌታም ቅፅል ስም አወጡለት አሉ
በልጥፍጥፍ መአት ዋናው ገፅ ፈረሰ
ስም አውጪው ሲበዛ አቤት ባይ አነሰ
አመሌን አመልሽን ለማያውቁ ሁሉ
ጠርቼው አልመጣም ትዪኛለሽ አሉ
.
እሷ የስም ሀብታም
ትጠራው አታጣ ትሸኘው አታጣ
እኔ ባለ አንድ ስም ምን ሰምቼ ልምጣ?
ሰሚን ሲያናንቁ ጠሪን ሲያቃልሉ
የስም ፋብሪካ ነው ጉራንጉሩ ሁሉ
....
እንደነገርኩሽ ነው
የላክሽው ፎቶ አንሺ
በጥላሽ ከልሎ ባንቺ ብርሃን ኩሎ
ፎቶ ነስቶኝ ሄደ ፎቶ አነሳሁ ብሎ
ፓ! ፓ! ፓ! ካሜራ ኧረረ !! ካሜራ
በሌሉበት ሁሉ ማንሳት የማይራራ
ሊያውም በክት ልብስ ጥለት አዛንቄ
ሊያውም በጀግና ልብስ በኒሻን ደምቄ
.....
እያገላበጠ
ተዟዟርር እያለ ሲያነሳኝ ሰንብቶ
በትኖልኝ ሄደ ልብስ የሌለው ፎቶ
ካሜራሽ ስልጡኑ ካንቺ እኩል ያወቀ
ፎቶ ያነሳል አሉኝ ልብስ እያወለቀ
.
እንደነገርኩሽ ነው
የማንም ያልሆነን ያንተ ነው ተብዬ
በመሠለኝ ፋንታ ፍሬምሽን ሰቅዬ
ግራ የገባው አይን ከዕርቃን ይፋጠጣል
የጀግና ፎቶዬ የበዓል ፎቶዬ ከሱቅሽ ይሸጣል
..
አንቺ የመልክ ሀብታም ቀለም የተረፈሽ
አንቺ የልክ ሀብታም መስመር የተረፈሽ
የተኩላዎች ክፋት በበጎች ስም ፅፈሽ
መጥቀሻል ይሉኛል በምኞት መሠላል
ግድየለም ምጠቂ
ቅዠት ሲደጋገም ከህልም ይማሰላል
.
እንደነገርኩሽ ነው
ቧልተኛው ዶክተርሽ በስላቁ ፈዞ
አከምኩ ይለኛል
የራሱን መዳኒት ለመምተኛው አዞ
.
የመምተኛሽ ጉዳይ
የመምተኛው ደሞ
ከዶክተርሽ ባሰ ሁለቴ ገደለኝ
ተመረመርኩልህ ይቺን ዋጣት አለኝ
በታመመ ልኩ ጤና ሲሰፍርልኝ
በሽተኛ ልጅሽ ተመረመረልኝ
..
መድሃኒት ከሰረ
ጤና ተቃወሰ በሽታ ተስፋፋ
ግብረ ገብ ጎደለን ስነ ምግባር ጠፋ
ጉባኤ ሰብስበው ሰበብ ሲያዳምቁ
እኔን የገደለኝ
ከበሽታው ይልቅ በሽተኛው በውል አለመታወቁ

ያንቺዬማ አይነቱ
ማድማቱን ደብቆ
መድማቱን ለብቻ እያስመረመረ
ፈውስ በስም ብቻ ተድበስብሶ ቀረ
.
በኔ ና አንቺ አለም
ከማዘን ማሳዘን ከመሳት ማሳሳት
ከደም ማነስ ደም ማሳነስ
ከመርሳት ማስረሳት በእጥፍ ይቀድማል
ከህመሙ በላይ ህመምተኛው ያማል
..
ኧረ ያንቺስ ነገር
ትንሽ እየሰፋ ብዙ መቅደድ ያውቃል
ክርሽ ሳይነካ መርፌሽ ብቻ ያልቃል
ኧረ ያንቺስ አራጅ ቅርጫውን ሳንበላው
ያልቅብሻል አሉ ሞረድ እና ቢላው
ጎዳናው ሳይጠበን አመል እያጋፋን
እንኳን አካሄዱ አቋቋሙ ጠፋን

@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
"ብዙ ሀገሮችም ልዩ ነን ብለው አስበው ነበር"
ዶ/ር ኪሩቤል ተስፋዬ ከስፔን፣ማድሪድ
.
የኢትዮጵያንም የስፔንንም የጤና አቅም በቅርበት እንደሚያዉቅ ባለሙያ ሰሞኑን የታዘብኩትን ላጋራቹ። የ ዛሬ ሳምንት ድረስ ምንም እንኳ መንግስት ነዋሪዉ እንዲጠነቀቅ ቢናገርም የሚሰማ ሰው አልነበረም ፤ የ ኳስ ጨዋታዎች በየከተማው ነበሩ ፤ ስብሰባዎች ነበሩ፤ዮኒቨርሲቲዎች ክፍት ነበሩ፤ የሚሰማ ሰው አልነበረም ።
.
ህዝቡ ከቻይና አልተማረም ፤ ጎረቤት ካለችው ጣልያንም አልተማረም። የሚይዘው አልመሰለውም ፣እራሱን ልዮ አድርጎ የሚያድነው የመሰለውን ምክንያት ደረደረ።
.
አሁን ሀገሪቷ ከተዘጋጋች ቀናቶች ተቆጠሩ መውጣት የሚቻለው ምግብ ወይ መዳኒት ለመግዛት ነው፤ የ አንቡላንስ ድምፅ በየቦታው ነው፤ ሰው በየቦታው እየሞተ ነው። ፈርተናል ፣ ፈርቻለው ፤ ያስፈራል።
.
ሀገሬም ተመሳሳይ መንገድ መከተሏ ያስጨንቃል፤ ኢትዮጵያውም እስካሁን ምክንያት መደርደራችንን ቀጥለናል። መጀመሪያ ቻይና ሀይማኖት ስለሌላት ተቀጣች አልን ፤ ከዛ ጣልያን እና ኢራንን ሲያስጨንቅ እኛ ሀገር ሙቀት ስለሆነ አይገባም ማለት ጀመርን ፣ ብራዚል እና አውስትራሊያ ገብቶ አየን ከዛም ሀገራችን ገብቶ አየን።
አሁንም ከተያዙት ብዙሀኑ ነጮች ናቸው ኢትዮጵያውያንን አይዝም የሚል ምክንያት ሰማን። ከ 4 ቀን በፊት ሁለት ኢትዮጵያውያን ጣልያን ውስጥ ሞቱ። ድንገት እዛ ስለኖሩ ነው የሞቱት የሚል ስለማይጠፉ ከሟቾች አንደኛዋ ከቀናት በፊት ከኢትዮጵያ የሄዱ ነበሩ።
.
እስከመቼ ልዩ እንደሆንን እንዲሰማን ምክንያት እንደረድራለን? ፈጣሪ ልዮ አድርጎ የመጠንቀቂያ ጊዜ ሰቶናል እንጠንቀቅ።
⬆️
በኮሮና ቫይረስ ዙርያ ያሉ የተሳሳቱ ግንዛቤዎች!

በዶ/ር መንግስቱ አሰፋ

1.ኮሮና ቫይረስ የሚያጠቃው አረጋዊያንን ብቻ ነው>> ስሕተት
የኮሮና ቫይረስ ዘርን፣ ቀለምን፣ ዕድሜን ሳይለይ ማንንም ይይዛል። ነገር ግን አረጋዊያንን ይበልጥ ለከፋ ጉዳት ያደርሳል የሚል አጠቃላይ ግምት ብቻ ነው ያለው።
በተጨማሪም የሳምባ፣ የጉበት፣ የኩላሊት፣ የልብ ሕመሞች፣ ካንሰር፣ ኤድስ፣ ስኳር በሽታ ወዘተ ያለባቸውን ሕሙማን በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳል። ወጣቶችም አናመልጥም፣ እንጠንቀቅ።

2. የቤት እንስሳት ኮሮናቫይረስን ያሰራጫሉ>> ስሕተት
እስካሁን ባለው ሁኔታ ከውሻ፣ ድመት ወዘተ ወደ ሰው ተላልፎ የተከሰተ የዚህ በሽታ ሪፖርት የለም። ሆኖም ግን ከነሱ ጋርም ሆነ ተቀምጠን ከተነሣንም፣ የእጃችንን ሁሉንም ክፍል በሳሙና ለ20 ሰኮንድ መታጠብ ለጥንቃቄ ያግዛል።

3. የተለያዩ ባሕላዊ መድኃኒቶች፣ ቫይታሚኖች ከቫይረሱ ያድናሉ>> ስሕተት (በጥንቃቄ)
እስካሁን በሳይንስ የተረጋገጠ መድኃኒትም፣ ክትባትም የለም። በቅርብ የምናይ ይሆናል። ቫይታሚንና የተለያዩ የሰውነት የመከላከል አቅምን የሚጨምሩ ምግቦችን መውሰድ ጥሩ ነው። ግን በሽታው እንዳይዘን አያደርጉንም።

4. መድኃኒቶች (antibiotics) ከኮሮና ቫይረስ በሽታ ያድናሉ>> ስሕተት
በኮሮና ቫይረስ በሽታ የታመሙ ሰዎች አንታይባዮቲክስ የሚወስዱት ተጨማሪ ኢንፌክሺን ሲኖራቸው ነው። አንታይባዮቲክስ ከኮረናቫይረስ እንደሚያድን ሳይንስ አላረጋገጠም።

5. Surgical Mask መጠቀም ከኮሮናቫይረስ በበቂ ሁኔታ ይከላከላል>> ስሕተት
የፊትና የአፍ ማስክ መጠቀም ያለበት በሽታው ያለበትና የጤና ባለሙያ ነው። ሌላ ሰው (N95 የሚባለውን ማስክ ጨምሮ) ባይጠቀም ይመረጣል። ምክንያት:
- disposable surgical masks በአየር የሚመጡ ጎጂ ኢንፌክሺኖችን ለመከላከል ፊትን ሙሉ በሙሉ አይሸፍኑም፣ ሰለዚህ በቀላሉ እንጠቃለን።
- በተደጋጋሚ እያወለቅን፣ እየነካካነው ለረጅም ጊዜ በተለይ ጸሐያማ ወይም ሙቀት ያለበት ቦታ ከተጠቀምነው ይበልጥ ለኢንፌክሽኑ ያጋልጡናል እንጂ አያድኑንም።

ዋናው!

እጃችሁን ታጠቡ፣ ማኅበራዊ ፈቀቅታን ተግባራዊ አድርጉ፣ ሰው የተሰበሰበት ቦታ አትሂዱ፣ እጅ መታጠቢያ ቦታ ለመታጠብ አትሰለፉ፣ አትጋፉ፣ የበሽታው ምልክት ያለበት ሰው ቶሎ የሕክምና አገልግሎትን ያግኝ።

©eliasmeseret
ኮሮናን ለመከላከልና ነፃ ስልክ
ኦሮሚያ: 6955
ትግራይ: 6244
አማራ: 6599
ድ/ደዋ: 6407

Koroonaa ittisuuf bilbila bilisaa
Oromia 6955
Tigray 6244
Amhara 6599
Diredawa 6407
የሚባለውን የሚሰማ ከከፋው አደጋ ይድናል!

- አትጨባበጡ
- ተራራቁ
- አትሰባሰቡ
- የእጃችሁን ንፅህና ጠብቁ
- አስገዳጅ ካልሆነ አርፋችሁ ቤታችሁ ተቀመጡ
- በጋራ ለመዝናናት ጊዜው አሁን አይደለም
- በቡድን እራት ለመብላት ጊዜው አሁን አይደለም
- የጤና ባለሞያዎችን ምክር ስሙ፣ ተግብሩ

ለእራሳችሁ፣ ለቤተሰባችሁ ጤና አስቡ!
Forwarded from Deleted Account
🖍አስርቱ ˝የመ˝ ሕጎች - ለኮሮና‼️

👉መታጠብ (በሳሙና / በሳኒታይዘር )
👉መጉመጥመጥ (ውሀ ለብ አርገህ በትንሽ ጨው)
👉መጥረግ (በአልኮል )
👉መራራቅ (ስትቆሙ/ስትቀመጡ )
👉መታቀብ (ከመጨባበጥ /ከንክኪ )
👉መተው (ስብሰባ/ህዝብ የሚበዛበት ቦታ
👉መቀመጥ (ቤትህ /ሆቴል ውስጥ )
👉መመገብ (በሽታ ለመቋቋም )
👉መከታተል (መረጃን ከታማኝ ምንጭ )
👉መፀለይ (ወደ ፈጣሪ )

VIA ዶክተር አለ 8809

#SHARE ይደረግ
⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉༄༄༄⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉

Still I Rise (MAYA ANGELOU)

You may write me down in history
With your bitter, twisted lies,
You may trod me in the very dirt
But still, like dust, I'll rise.

Does my sassiness upset you?
Why are you beset with gloom?
’Cause I walk like I've got oil wells
Pumping in my living room.

Just like moons and like suns,
With the certainty of tides,
Just like hopes springing high,
Still I'll rise.

Did you want to see me broken?
Bowed head and lowered eyes?
Shoulders falling down like teardrops,
Weakened by my soulful cries?

Does my haughtiness offend you?
Don't you take it awful hard
’Cause I laugh like I've got gold mines
Diggin’ in my own backyard.

You may shoot me with your words,
You may cut me with your eyes,
You may kill me with your hatefulness,
But still, like air, I’ll rise.

Does my sexiness upset you?
Does it come as a surprise
That I dance like I've got diamonds
At the meeting of my thighs?

Out of the huts of history’s shame
I rise
Up from a past that’s rooted in pain
I rise
I'm a black ocean, leaping and wide,
Welling and swelling I bear in the tide.

Leaving behind nights of terror and fear
I rise
Into a daybreak that’s wondrously clear
I rise
Bringing the gifts that my ancestors gave,
I am the dream and the hope of the slave.
I rise
I rise
I rise.

⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉༄༄༄⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉
©General Thoughts💭
Important note from WHO ⬆️

@eliasmeseret
ወጣቶች የጤና ባለሞያዎችን ምክር አዳምጡ!

በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያ ሪፖርት ካደረገቻቸው ተጨማሪ 3 ኬዞች ውስጥ የ26 ዓመት ወጣት እና የ14 ዓመት ታዳጊ ይገኙበታል። አሁን ሩቅ ሀገር መሄድ አይጠበቅብንም ይህ ቫይረሱ እድሜ፣ ፆታ፣ቀለም፣ የኑሮ ደረጃ እንደማይለይ ማሳያ ነው።

ወጣቶች የጤና ባለሞያዎች የሚሉትን ምክር አዳምጡ ፣ አስፈላጊ ካልሆነ ከቤታችሁ አትውጡ ፤ የግድ ለመጠንቀቅ የሰው ህይወት ማለፍ አለበት ? ወይስ ብዙ ሺ ሰው መታመም አለበት ? እባካችሁ ለእራሳችሁና ለቤተሰባችሁ ጤና የምትባሉትን አድምጡ።
ውድ ቤተሰቦቻችን እንዚህን ቁጥሮች እናስታውሳችሁ...

የኮሮና ቫይረስ በሽታን አስመልክቶ ጥቆማ ለመጠትና መረጃ ለማግኘት በእነዚህ የነፃ የስልክ ቁጥሮች መደወል ትችላላችሁ፦

ትግራይ ክልል - 6244
አፋር ክልል - 6220
አማራ ክልል - 6981
ኦሮሚያ ክልል - 6955
ሱማሌ ክልል - 6599
ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል - 6016
ደቡብ ክልል - 6929
ሀረሪ ክልል - 6864
ጋምቤላ ክልል - 6184
ድሬዳዋ ከተማ - 6407

ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
ሰላም እደሩ!
©tikvahethiopia
ጠቃሚ መልዕክት!

🧼 እጃችሁን በሳሙና እና በውሃ በደንብ ታጠቡ

👋🏾 አትጨባበጡ/አትሳሳሙ

🙅🏽‍♀️ ማህበራዊ መስተጋብርን በጣም ቀንሱ!

አስገዳጅ ካልሆነ በቀር ከቤት አትውጡ

☎️ ትኩሳት ፣ ሳል እና ትንፋሽ ማጠር...ምልክት ከታየባችሁ በቅድሚያ ከዚህ በታች ባሉት ነፃ የስልክ መስመሮች ይደውሉ ፦

አዲስ አበባ - 8335 /952 ፣ ትግራይ ክልል - 6244 ፣ አፋር ክልል - 6220 ፣አማራ ክልል - 6981 ፣ ኦሮሚያ ክልል - 6955 ፣ ሱማሌ ክልል - 6599 ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል - 6016፣ ደቡብ ክልል - 6929 ፣ ሀረሪ ክልል - 6864 ፣ ጋምቤላ ክልል - 6184፣ ድሬዳዋ ከተማ - 6407

#SHARE #ሼር

#HaymanotGirma
💐ጠዋት ጠዋት ትዳር ያምረኛል ! ..

ሁሌም ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ ሚስት ማግባት ያምረኛል። በቃ አለ አይደል ልክ እንደ
አማርኛ ፊልም ሚስቴ ቀድማኝ ተነስታ ሸሚዜን ለብሳ በዚያ ውብ እግሯ ቤት ውስጥ ሽር
ጉድ ብላ ሚገርም ቁርስ ከጁስ ጋር ሰርታልኝ በልቼ ምናምን ቡናዬን ጠጥቼ። የተተኮሰ
ልብስ ራሷ መርጣ አምጥታልኝ እሱን ለብሼ እስከበር ድረስ ሸኝታኝ ከንፈሯን ስሜ ቀኔን
ረሃ ሆኜ ብጀምር ደስ ይለኝ ነበር።
But ... life is not like z movie my brother!! ሁሉም ወንድ ሊያገባ ሲወስን የሚታየው
ከላይ የገለፅኩት አይነት ህይወት ነው። በርግጥ እህቶችም የሚሰሩን ሿሿ ቀላል አይደለም
ብራዘር ድንገት ቺክህ የወንደላጤ ቤትህ ከመጣች በምቾት ታጨናንቅሃለች።
ትንከባከብሃለች። በአንድ ድስት ሰባት አይነት ወጥ ስትሰራ “አረረረ ጆርዳና in the
house” ምናምን ብለህ ትቀውጠዋለህ። እየተሽከረከረች ያቺኑ አንድ ክፍል ቤትህን
ታፀዳለች። እንደ ስፓይደር ማን ግድግዳው ላይ ተራምዳ ሁሉ ኮርኒስህን ልትወለውል
ትችላለች። አንተ እያወለቅክ አልጋህ ስር የጣልከውን ካልሲ ፈገግታ ከፊቷ
ሳይጠፋ (በሆዷኮ ይሄ በስባሳ እያለችህ ነው) አውጥታ አጥባ እንደቋንጣ ታሰጣልሃለች።
በቃ ምን አለፋህ ከሷ ጋር መኖር ሰቨን ስታር ሆቴል አዘግቶ መዝናናት እንዲመስልህ
ታደርግሃለች። ባራት እንቁላል አምስት አይነት ወጥ ሰርታ ስታበላህ እነዚህ አድሃሪና ቡርዧ
የሆቴል ቤት ባለቤቶች ሲበዘብዙህ እንደኖሩ ይሰማሃል! እሷን ማግባት ትመኛለህ። ትዳር
ማለትኮ .... እያልክ ለጓደኞችህ ማብራራት ትጀምራለህ። የሙሽራ መኪና ስታይ አይንህ
ይንከራተታል። እንተዋወቃለን ወይ? የሚለው ፕሮግራም ቋሚ ደምበኛ ትሆናለህ። በቃ
ፋይናሊ ሽማግሌ ትልካለህ። እናትና አባቷ በየቀኑ « አንቺ ልጅ አግብተሽ አትፋቺንም
እንዴ ?» ሲሏት እንዳልኖሩ እየተጀነኑ ምን አለው? ማን ነው? ምናምን ብለው በመከራ
ይፈቅዱልሃል!
ከዛ መልአኳ እጮኛህ ስለሰርግ ትጀነጅንሃለች። እንደጀነጀነችህ ግን አትባንንባትም።
በስታየል ነው ምታሰምጥህ። አለ አይደል «እኔኮ ሰርግ አሎድም ግን እነማሚ
እንዳይከፋቸው አነስ ያለች አንድ መቶ ሰው ብቻ ጠርተን ቀለል አርገን እንደግስ .. ግን
ካልተመቸህ ይቅር» ትልሃለች! አረ ጣጣ የለውም ምናምን ብለህ እድሜ ልክህን ኢትዮጵያ
ንግድ ባንክ ተሰልፈህ የቆጠብካት ፍራንክህ ላይ ትፈርድባታለህ!
እናቱ ቀለል ያለ ያለችውን ሰርግ የ አንድ ሺ ሰው ካርድ በማሰራት ትጀምረዋለች
ቀለል አርጋ የሃያ ሺ ቬሎ፣ ቀለል አርጋ ሜካፕ ሰላሳ ሺ ፣ ቀለል አርጋ ሊሞ ሃምሳ ሺ ፣
ወዘተ ብላ በአንዴ ከአበዳሪ ሐገራት ተርታ አውጥታህ ኢኮኖሚህን በጠረባ ትጥለዋለች።
የሰርግህ ቀን በሰው መኪና እንደታቦት አደባባይ ሲያዞሩህ ይውሉና አንተ የማታውቀውን
አንድ ሺ ሰው ሆድ ሞልተህ እጅህን እያጠላለፍክ ኬክ ትጎራረስና በአደባባይ ሃብቴ ሃብትሽ
ነው ብለህ ፈርመህ ኮትህን አንጠልጥለህ ወደቤት ይዘሃት ትገባለህ!!
የመጨረሻው መጀመሪያ! እንዲል የድሮ ደራሲ the tragic part of your life begins :
ጠኋት ከእንቅልፍህ የሚገርም የጀነሬተር ድምፅ ያነቃሃል! ብንን ስትል እያንኮራፋች ነው
ካሁን አሁን ተነስታ ምርጥ ቁርስ ሰራችልኝ ብለህ ብትጠባበቅ እናቱ ተኝታ
ህልም እየቀያየረች ታያለች። ምርር ሲልህ ትቀሰቅሳታለህ። ጠላትህ ቅይር ይበል በዚያ
ሻካራ ድምጿ አፍጥጣ « ሰው ከእንቅልፌ ሲቀሰቅሰኝ ደስ አይለኝም » ብላ ተመልሳ
ትተኛለች። በሆድህ “ እቺ ነገር ያቺ ነገር ነች ?” እያልክ ፆምህን ወደስራ ስትወጣ በር ላይ
ለሰርግ ብር ጎሎህ የተበደርከው ሰውዬ ከቦክሰኛ ልጁ ጋር ይጠብቅሃል ... ......., ..
ምፅ እኔ አፈር ልብላ!
ማታ ቤት ስትገባ ካልሲዎችህ በር ላይ ተከምረው ይጠብቁሃል! እሱን አጥበህ
ስትጨርስ ጨው እንደ Dead sea የበዛበት ሽሮ ወጥ ይቀርብልህና “ከበላህ ብላ ካልበላህ
አፈር ብላ” ትባላለህ!
በዘጠኝ ወሯም አንድ ጩኸታም ፈልፈላ ትወልድልሃለች። በየደቂቃው ዋኣኣይ ነው።
በየሰከንዱ ኡኡ ነው። አናትህን ያዞረዋል። በመስኮት አውጥተህ ወርውረው ወርውረው
ይልሃል። ለሊት ይነሳና ይቀውጠዋል። እሷ ምርር ሲላት ላሽ ትለዋለች። ቢቸግርህ ተነስተህ
ጡጦ ትሰጠውና ተመልሰህ ተኝተህ እንቅልፍ ሸለብ ሲያደርግህ ጡጦውን ሻት አርጎት
እንደገና ዋኣኣይ ይላል። በቃ ትነቅላለህ! ይሄ ሰውዬ ለምን አይተወኝም ግን? ትላለህ።
የሶስት ወሩን ልጅ “ና ልብ ካለህ ወጥተን እንነጋገር ” ምናምን ሁሉ ልትለው ትችላለህ :
በገባህ በወጣህ ቁጥር ያ በደጉ ግዜ ስንት ነገር ያሳየህ ጡቷ ላይ እንደአልቂት ተጣብቆ
ሲመጠምጣት ደምህ ይፈላል። ዘመዶቿ አያልቁም ዛሬ አባቷ ፣ ነገ አጎቷ፣ ከነጎዲያ አክስቷ
እየመጡ ጠብ እርግፍ ብለህ ታስተናግዳለህ። እሱ ሳይበቃቸው ምነው ጠቆርሽ? ምነው
ከሳሽ? እያሉ ወፍራ ጆንሲናን ያከለችውን ሴትዮ ይጨቀጭቋታል። ፕራይቬት ላይፍ ብሎ
ነገርህ ይናፍቅሃል! ብቸኝነትህ በአይንህ ውል ይልብሃል!
ለሊት አንተ የልጅህን ዳይፐር ለመቀየር ስትታገል ፍሬንዶችህ ክለብ ሆነው ይደውሉልህና
ዘፈን ይጋብዙሃል! ሲኦል ሆነህ ከመንግስተሰማይ ሚደወልልህ ያህል ትቀናለህ ! ከዚያ
ህይወትህን መለስ ብለህ በትካዜ ታስታውሰዋለህ። ከዚያም ሴትየዋ ከትዳር በፊት የነበራት
ማራኪ ባህሪ የምርጫ ቅስቀሳ መሆኑ ይገባህና “All women are politicians ” ብለህ
መፈላሰፍ ትጀምራለህ።
😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂
#Share_share_it

🙌እጃችሁን መታጠብ እንዳረሱ😷

@endenaendena
@endenaendena

@simetin_begitim
@simetin_begitim
ኮኖናን በግጥም
#Share

እና እንደ ነገርኩሽ
የሚወዷትን ሴት ርቆ እንደመጠበቅ
ሰው እንደ ጠል ሲረግፍ ሰምቶ እንደመሳቀቅ
በወረርሽኝ ታሞ የትም እንደመውደቅ
በኮሮና ቫይረስ ተመትቶ እንደ መድቀቅ
ኮቪድ በወረራት በዚች ሚስኪን ዓለም
ከዚህ የበለጠ ምንም ህመም የለም
የማስክ ዋጋ ያማል
የአልኮል ዋጋ ያማል
ሳኒታይዘር ያማል
የሞት ሰጋር ፈረስ ደራሽ ማዕበሉ
የጁሴፔ ኮንቴ የዕንባ ቅጥልጥሉ
ምንብዬ ልንገርሽ ? ያማል ይሄ ሁሉ
እና እንደ ነገርኩሽ
ልብ የወደደው ሰው ርቀት ካልጠበቀ
ልብ ያፈቀረው ሰው ርቀት ካልጠበቀ
ነገር ተበላሸ ህዝብ ተላለቀ
ሳንባ ቆሳሰለ ጉሮሮ በገነ
ህይዎት ተቀጠፈ መተንፈስ ብርቅ ሆነ
የዓለም ሳቅ ሁካታ ተተካ በሲቃ
ምንብዬ ልንገርሽ? ይሄም ያማል በቃ
ምሁሩ ገበሬው
ምዕመኑ ካድሬው
አሁንም አሁንም እጅን ካልታጠቡ
አያድንም ምክንያት አይረባም ሰበቡ
ስግብግብ ነጋዴ ሊሞት መስገብገቡ
ተበተን ያሉት ህዝብ ዞሮ መሰብሰቡ
እልፍ አዕላፍ አክቲቪስት አጉል ማሟረቱ
ኮሮና እንዲስፋፋ ክፉ መመኘቱ
ደሞ ለሱ ግጥም እናቱን ኮሮና
እጅሽን ታጠቢ ያውልሽ ሳሙና
እና እንደ ነገርኩሽ
ያ'ስራ ሁለት ብር ማስክ መቶ ብር የሸጠ
ስግብግብ ነጋዴ ወደኔ አፈጠጠ
ጓንት የሸፈነውን መንታ እጁን አጣምሮ
አልኮል አልቋል!! ይላል በጓዳ ቀርቅሮ
አልኮል አልቋል ይላል…??
እንዴት ቅጥሉ ሰው በሰው ይጨክናል?
ሳኒታይዘር ልዘዝ?
ግብጦ አረቂ ልዘዝ?
ጥቁር ግላስ ልዘዝ?
ለምን ጓንት አላዝም?
በወገኑ ሞት ላይ ድህነቱን ሊያሳልፍ
ሲስገበገብ የሚያልፍ
በጓዳው ቀርቅሮ
ሞቱን ባንገት ቀብሮ
አልኮል አልቋል ይላል
አንድ ሳኒታይዘር ካንድ እሷ ጋር ልዘዝ?
አንድ ጥቁር ግላስ ካንድ እሷ ጋር ልበል?
ከእጅ ጓንት ጋር እሷን አምጣ ልበል?
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
መቃብር ይቆፈር
ብሎ የሚያሟርት የደደብ ዘገባ
ለሳሙና ያጣች የድሃ እናት እንባ
የነጋዴ ክፋት የመብዛቱን ያህል
ብዙ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
እና እንደ ነገርኩሽ
ጨካኝ ያገርሽ ሰው
አልኮል ነው እያለ የሬሳ ማድረቂያ ለገበያ አወጣ
እልቂትን የሚመኝ ጋዜጠኛ መጣ
ከተጠነቀቅን የት ያገኘንና
እ. . . .ና. . . .ቱን !
እናቱን ኮሮና
እጅሽን ታጠቢ ያውልሽ ሳሙና
እኔ አንቺን ስወድሽ - የልቤ ነሽ ስልሽ
ቤቴ በመዋል ነው - ፍቅሬን ምገልፅልሽ
ቢሆንም ግን ያማል !!!!


ደሱ ፍቅረኤል
#Share
@endenaendena
@simetin_begitim
@simetin_begitim