ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን እንኳን ለገና በዓል በሠላም አደረሳችሁ ፡፡ መልካም በዓል
ካላይ የለችዋን መዝሙር ተጋበዙልን
ካላይ የለችዋን መዝሙር ተጋበዙልን
እንኳንለብርሃነ
🕯🕯ል🕯🕯
🕯🕯ደ🕯🕯
🕯🕯ቱ🕯🕯
🌹አ
🌹🌹ደ
🌹🌹🌹ረ
ሳ🌹
ች🌹🌹
ሁ🌹🌹🌹
"በጎል ሰከበ አፅርቅት ተጠብለለ
ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ"
በበረት ተኛ በጨርቅ ተጠቅለለ፡
የዓለም መድኃኒት ዛሬ ተወለደ
🕯🕯📖📖🕯🕯
📖📖📖
" ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።"
(ኢሳ 7: 14)
📖📖📖
" እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።"
(ማቴ 1: 23)
📖📖📖
" ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር" ኃያል "አምላክ" የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።"
(ኢሳ 9: 6
🕯🕯🕯🕯🕯
ውድ አባቶቼ እናቶቼ ወንድም እህቶቼ፡ህፃናት የተዋህዶ ልጆች
🌷በሀገርም🌷
💜ውስጥ💜
🌹ከሀገርም🌹
💜ውጭ💜
🌷ያላችሁ🌷
🌹በስደት🌹
🌳በእስራት🌳
🌳በጎዳና🌳
🌳በጭንቅ🌳
🌳በአልጋ🌳
🌳በዱር🌳
🌳በበረሃ🌳
🌳በዋሻ🌳
🌳ያላችሁ🌳
💜ለመላው💜
🌹የክርስትና🌹
💜እምነት💜
🌷ተከታይ🌷
💜በሙሉ💜
🌹እንኳን🌹
💜ለ💜
ለብርሃነ ልደቱ
ለጌታችን ልደት
💙በዓል 💜
🌹በሰላም🌹
💜አደረሳችሁ💜
🌷በ🌷
💜ዓ💜
🌹ሉ🌹
💜መ💜
🌷ል🌷
💜ካ💜
🌹ም🌹
💜የ💜
🌷ተ🌷
💜ቀ💜
🌹ደ🌹
💜ሰ💜
🌷በ🌷
💜ዓ💜
🌹ል🌹
💜ይ💜
🌷ሁ🌷
💜ን💜
🌹ል🌹
💜ን💜
🌷አ🌷
💜ሜ💜
🌹ን🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
ባ ለ ው ለ ታ ች ን
🌷🌷🌷🌷🌷
ጌ ታ ች ን
🌹🌷🌹🌷
አ ም ላ ካ ች ን
🌹🌳🌹🌳🌹
መ ዳ ኒ ታ ች ን
🌹🕯🌹🕯🌹
🍸ኢ🍸
🍸የ🍸
🍸ሱ🍸
🍸ስ🍸
🕯🕯 ክርስቶስ🕯🕯
🕯🌳🌹የእናታችን 🍸
🕯🌳🌹የቅድስት 🍸
🕯🌳🌹ድንግል🍸
🕯🌳🌹ማሪያም🍸
📖ል📖
📖ጅ📖
🕯 አ🕯
🕯ማ🕯
🕯ኑ🕯
🕯ኤ🕯
🕯ል🕯
🌺🌺በቸርነቱ 🌺🌺
🌺 ይ
🌺🌺ባ
🌺ር🌺🌺
ከ🌺
ን 🌺
🌷💜🌷 🌹🌳🌹
🌹 የሰላም 🌳
🌹የደስታ 🌳
🌹 የፍቅር🌳
🌹የበረከት🌳
🌹የአንድነት 🌳
🌳🌳🌳🌳🌳🌳
🌳በዓል
🌳🌳ይሁንልን
🌳አሜን!!!🌳
🌳አማን!!!🌳
🌳አማን!!!🌳
🌳
🌹
🕯
🍸
📖
🌹🌳🌹🌳
@Simetin_Begitim
@Geezworld1

የካፊያ ምች
✍ ተፈሪ ዓለሙ(1974)
ሳልላክ ተልካ እንሂድ አለቺኝ
ካላጣችው ሰዓት ከቤት አስወጣችኝ
ጥርቅም እቅፍ አድርጋ በካፊያ ሳመቺኝ
የእድሜ ልክ ልክፍቱን ያኔ አስለከፈችኝ
መብረቅ እየጮኸ ዝናብ እያካፋ
የእኔ ልብ በሷ የሷ በእኔ ጠፋ
የሰማዩ ባህር ቁልቁል ተንዶብን
ውሃ ጠማኝ ውሃ እዘነበብን
ጠፍቼ ስመለስ ከእቅፏ ስወጣ
በርዶኝ አተኮሰኝ እቤቴ ስመጣ
እያደር አደረ ከርሞ ከረመብኝ
የዘመን ህመሜን ያን እለት ታመምኩኝ
አሁን አሁን ታዲያ!
ደመናው ሲጠቁር ነጎድጓድ ሲያጓራ
ነፋስ ሲያጉረመርም ክረምቱን ሲጠራ
ግንቦት ማለቂያ ላይ ይነሳል ህመሜ
ሲያቀብጠኝ በዝናብ በካፊያ ተስሜ
..........................ምች ተሳልሜ
©ግጥም ብቻ
@Simetin_Begitim
✍ ተፈሪ ዓለሙ(1974)
ሳልላክ ተልካ እንሂድ አለቺኝ
ካላጣችው ሰዓት ከቤት አስወጣችኝ
ጥርቅም እቅፍ አድርጋ በካፊያ ሳመቺኝ
የእድሜ ልክ ልክፍቱን ያኔ አስለከፈችኝ
መብረቅ እየጮኸ ዝናብ እያካፋ
የእኔ ልብ በሷ የሷ በእኔ ጠፋ
የሰማዩ ባህር ቁልቁል ተንዶብን
ውሃ ጠማኝ ውሃ እዘነበብን
ጠፍቼ ስመለስ ከእቅፏ ስወጣ
በርዶኝ አተኮሰኝ እቤቴ ስመጣ
እያደር አደረ ከርሞ ከረመብኝ
የዘመን ህመሜን ያን እለት ታመምኩኝ
አሁን አሁን ታዲያ!
ደመናው ሲጠቁር ነጎድጓድ ሲያጓራ
ነፋስ ሲያጉረመርም ክረምቱን ሲጠራ
ግንቦት ማለቂያ ላይ ይነሳል ህመሜ
ሲያቀብጠኝ በዝናብ በካፊያ ተስሜ
..........................ምች ተሳልሜ
©ግጥም ብቻ
@Simetin_Begitim
ጉዴ -ጉድሽ - ጉዳቸው
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ጉዴ...
ከድፍን አለም ሴት ፣ አንድ አንቺን መውደዴ
ማፍቀሬን ስነግርሽ ..
የሰው መሆንሽን ፣ ስትነግርሪኝ ማበዴ
እብድ ስሆን ደሞ...
አለምን አጥፍቼ ፣ መኖር ነው እቅዴ ፡፡
፡
ጉድሽ...
ካላጣሽው እኔ ፣ ሌላ ሰው መውደድሽ
ኮከብን አክብረሽ ፣ ፀሐይ ማዋረድሽ
ስዋረድ ወስኜ...
አለምን ሳጠፋት ፣
አንቺም ከዓለም ጋር ፤ መቃብር መውረድሽ፡፡
፡
ጉዳቸው...
ባለም እየኖሩ ፣ ስትሔጂ ተመለሽ ፣ ባለማለታቸው
ንፁሀን ቢሆኑም
በኔና'ንቺ ጉዳይ ፣ ስላልገቡ ጣልቃ
አለምን ሳጠፋት...
እነሱም አንድ ላይ ፣ ይጠፋሉ በቃ፡፡
ያውም በደቂቃ!!!
:
ቡንንንንን!
ይኸው አጠፋኀት ፣ አሁን ምንም የለም
አንቺ የኔ ካልሆንሽ ፣ ምን ያደር ጋል አለም?!!
@Simetin_Begitim
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ጉዴ...
ከድፍን አለም ሴት ፣ አንድ አንቺን መውደዴ
ማፍቀሬን ስነግርሽ ..
የሰው መሆንሽን ፣ ስትነግርሪኝ ማበዴ
እብድ ስሆን ደሞ...
አለምን አጥፍቼ ፣ መኖር ነው እቅዴ ፡፡
፡
ጉድሽ...
ካላጣሽው እኔ ፣ ሌላ ሰው መውደድሽ
ኮከብን አክብረሽ ፣ ፀሐይ ማዋረድሽ
ስዋረድ ወስኜ...
አለምን ሳጠፋት ፣
አንቺም ከዓለም ጋር ፤ መቃብር መውረድሽ፡፡
፡
ጉዳቸው...
ባለም እየኖሩ ፣ ስትሔጂ ተመለሽ ፣ ባለማለታቸው
ንፁሀን ቢሆኑም
በኔና'ንቺ ጉዳይ ፣ ስላልገቡ ጣልቃ
አለምን ሳጠፋት...
እነሱም አንድ ላይ ፣ ይጠፋሉ በቃ፡፡
ያውም በደቂቃ!!!
:
ቡንንንንን!
ይኸው አጠፋኀት ፣ አሁን ምንም የለም
አንቺ የኔ ካልሆንሽ ፣ ምን ያደር ጋል አለም?!!
@Simetin_Begitim
Deleted Account:
ድሮ ድሮ ነው አሉ....ያኔ በጥንት ዘመን:: ገና አለም ሳይፈጠር
ሰው የሚሉት ፍጥረት ሳይኖር! እግዚአብሔር የሰው ልጅ ባህርያት
የሚባሉትን ሁሉ ባንድ የተወሰነ ቦታ ከልሎ አስቀምጧቸው ነበር::
ለረጅም ጊዜ ባንድ ቦታ ተከርችመው መቀመጥ የሰለቻቸው
ባህርያት ድብርቱን ለመግፈፍ ጨዋታ አመጡ:: ድብብቆሽ
ሊጫወቱ ተነሱ::
ከባህሪያቶቹ መካከል ድንገት እብደት ተብየው ተነሳና እኔ
እቆጥራለሁ እናንተ ተደበቁ አለ::
ወድያው ነው ሁሉም የተስማማው:: አዎና....ማን ሞኝ አለ
እብደትን ተደበቅ ብሎ እሱን የሚፈልግ:: ከዚያ በኋላ እንግዲህ
እብደት ፊቱን አዙሮ መቁጠር ጀመረ::
አንድ...ሁለት...ሦስት ያኔ ባህሪያቱ ለመደበቅ ይጣደፉ ጀመር::
ሁሉም በአገኘው ስርቻ ተሸጎጠ...ለምሳሌ ያህል ውሸት ድንጋይ
ስር እደበቃለሁ ብሎ ለፍፎ ሲያበቃ ሀይቅ ውስጥ ገብቶ ተደበቀ::
እብደት መቁጠሩን ቀጥሏል...ሰባ ዘጠኝ...ሰማንያ..ሰማንያ
አንድ.....ይሄኔ ከፍቅር በስተቀር ሁሉም ባህሪያቶች በየስርቻው
ተደብቀዋል:: ጅሉ ፍቅር ብቻ ሳይደበቅ ተንከርፍፎ ቀረ::
ለነገሩ ይሄ አይደንቅም የፍቅር ባህሪው ይሀውም አይደል::
ፍቅርን መደበቅ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ አይጠፋንም
ለማንኛውም እብደት መቁጠሩን ቀጥሏል:: ዘጠና አምስት..ዘጠና
ስድስት...ዘጠና ሰባት... እያለ ነው:: እብደት ልክ መቶ ሲደርስ
ፍቅር ዘልሎ የፅጌረዳ ቁጥቋጦው ውስጥ ገብቶ ተደበቀ:: እብደት
መቁጠሩን ጨርሶ መጣሁላችሁ እያለ መጮህ ጀመረ::
መጀመርያ የተያዘው ስንፍና ነበረ:: ዳተኛው ስንፍና የተደበቀው
እብደት ካለበት ቦታ ብዙም ሳይርቅ ስለነበር ባንዴ ተያዘ ::
እብደት ባለ በሌለ ሃይሉ በጥልቀት ውስጥ ውሸትን ፈልፍሎ
አወጣ:: እብደት አንድ በአንድ ሁሉንም ባህሪያቶች መንጥሮ
ሲያወጣ አንድ ባህሪ ብቻ ግን እንደተደበቀ ቀረ:: ፍቅር ነበር
የቀረው እብደት ፍቅርን ፈልጎ ሊያገኘው ባለመቻሉ ተስፋ ወደ
መቁረጥ አዘንብሎ ነበር:: በስተመጨረሻ ግን በፍቅር ላይ ቅናት
ያደረበት ባህሪ ወደ እብደት ጠጋ ብሎ ፍቅር የተደበቀው
በፅጌረዳው ቁጥቋጦው ውስጥ ነው ሲል አንሾካሾከለት ይሄኔ
እብደት ዘሎ ፅጌሬዳው ቁጥቋጦ ውስጥ ሲገባ ፍቅር
ከቁጥቋጦው ውስጥ ታላቅ ጩሀት አሰማ:: የፅጌሬዳው እሾህ
የፍቅርን አይኖች ደንቁለው አጥፍተውታል:: እንግዲህ ከዚህ
በኋላ ፍቅር እውር ሆነ::
የፍቅርን የስቃይ ጩሀት ሰምቶ የመጣው ፈጣሪ ባየው ነገር አዘነ
እናም እብደትን ፈጣሪ እንዲህ አለው...........................
" ፍቅር እውር የሆነው ባንተ የተነሳ ነው:: በመሆኑም ከዛሬ
ጀምሮ ፍቅርን የገባበት ቦታ እየተከታተልክ የምትመራው አንተ
ትሆናለህ ::
መቼም ቢሆን አብራችሁ ትሆናላችሁ::
እናም አንተ መንገድ ታሳየዋለህ::
.....እንግዲህ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እውሩ ፍቅር በእብደት
እየተመራ ያላሰሰው የምድር ክፍል ያልጎበኘው ጎጆ የለም::
ከዚያን ዘመን አንስቶ የዕውሩ ፍቅር ክንፍ ምንግዴው እብደት
ሆነ:: እናም ከዚያ ጊዜ አንስቶ የንጉስ ቤተ መንግስት ከደሳሳው
ጎጆ : የሩህሩሁን ልብ ከጨካኙ: ቸሩን ከንፉግ: ምህሩን
ከመሃይም: ደፋሩን ከፈሪ እንደቀየጠ አለ:: አለምም በዚህ ቅይጥ
ሳብያ ይበልጥ ህብረቀለማዊ እንደሆነች አለች::
[የአለማችን ምርጥ የፍቅር ታሪኮች በግሩም ተበጀ]
©Book for All
መልካም ቀን ውብ ውሎ !💚💛❤️

" ፍቅር እና ፍቅርን የሚመስል ስሜት ይለያያል...ልክ በደመና የተሸፈነ ተራራን ኮረብታ እንደማንለው ሁሉ ፤ አልያም ዝናብ እየወረደበት ያለ ዛፍ እያለቀሰ ነው እንደማይባለው ሁሉ ። የሚሰማህን ስሜት ሳታረጋግጥ ፍርድ አትስጥ ። "
/ ካህሊል ጂብራን /
©ፍልስፍና
@Geezworld1
@Simetin_Begitim
/ ካህሊል ጂብራን /
©ፍልስፍና
@Geezworld1
@Simetin_Begitim
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘
ወጣት አብርሀም ጌታቸው የማኔጅመንት 3 አመት ተመራቂ ተማሪ ሲሆን በድንገት ሁለቱም ኩላሊቶቹ ስራ ስላቆሙ በሳምንት ሶስቴ ዳያሊሲስ ያደርጋል፡፡ የዳያሊሲሱ ወጪ በሳምንት 6600 ነው፡፡ ይሄ ብቻ አይደለም በነበረበት የስኳር ህመም አይኖቹ ማየት አቁመዋል፡፡ ፈጣን እርዳታችንን ይፈልጋልና ምስጋና የማይፈልግ ወንድማዊ እገዛችሁን እንፈልጋለን፡፡
ለማገዝ የምትፈልጉ በ ወንድሙ የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000089414532 አግዙን!
ለማገዝ የምትፈልጉ በ ወንድሙ የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000089414532 አግዙን!
ለቅዳሚት መዳረሻ!
❤️
እኔ ለወዳጄ
አንዲት ናት ግዳጄ
ሲመጡ መቀበል
ሲሄድ መሸኘት
እንደልቡ ሲሆን
የልቡን ለማግኘት።
(ሙሉጌታ ተስፋዬ)አያ ሙሌ!❤
ሠናይ ውሎ!
©ግጥም ብቻ
@Simetin_Begitim
❤️
እኔ ለወዳጄ
አንዲት ናት ግዳጄ
ሲመጡ መቀበል
ሲሄድ መሸኘት
እንደልቡ ሲሆን
የልቡን ለማግኘት።
(ሙሉጌታ ተስፋዬ)አያ ሙሌ!❤
ሠናይ ውሎ!
©ግጥም ብቻ
@Simetin_Begitim
(በላይ በቀለ ወያ)
በተራበው ጎኔ፣ በተጎዳው ኪሴ
እኔም ሰው ነኝና፣
የከንፈር ወዳጄን ተጠምታብኝ ነበሴ
የጥምቀት ለት ሎሚ፣
ኪሴን በሚጎዳ በሚነርት ዋጋ
ይሁን ብየ ገዛሁ፣
ደረቷን ልመታ የዛችን ውብ ሸጋ።
ሎሚውን በእጄ ያዝኩ
ኮረዳዋን ፈለግኩ
ባ'ይኖቼ አማተርኩ
ከኋላዋ አየኋት...
ፀጉሯ ሹሩባ ነው፣ ፊቷ አይታይም
ኋላዋ ካማረ...
ፊቷ ምንም ይሁን እኔን አይጨንቀኝም
ዳሌዋ... ቢዮንሴን ያስንቃል
በንቅልፍ የቧዘዘን አጣድፎ ያነቃል
ስንት የወጣባትን፣
የኛን ሳተላይት ከቻይና ያመጥቃል (አንጥሮ😂)
ወገቧ... አካበድክ ባትሉኝ
ከቀጭኗ እግሬ ሚወፍር አይመስለኝ
ወይኔ ሹሩባዋ
ለመግለፅም እንኳን አንደበትን ያስራል
በቆሙበት መሬት አፍዞ ያስቀራል።
ወደራሴ መጣሁ...
ልወርውር አልወርውር?
ልወርውር አልወርውር?
ወረወርኩ...
ድምም... እዛው ዳሌዋ ላይ
አሟት ዩን ደስ ብሏት ዞር ብላ ብታይ
የኔ ልብ ደንግጣ ልትበር ወደ ሰማይ
እየሮጠች መጣች፣
እያነፈነፈች ትንፋሿ እስከሚያጥራት
ክፉ አስባ ይሆን ልሩጥ ልጠብቃት?
ደረሰች...
ፊቴ ከመድረሷ፣
አንድ ጊዜ በጥፊ አወላመመችኝ
ወደላይ ወደታች፣
መላ ሰውነቴን በደምብ ቃኘችኝ
ወደግራ ጆሮየ በጣም ተጠጋችኝ
ጊዜው የድንጋይ ነው ሎሚ አታባክን
ኪስህን አሟጠህ፣
በገዛኸው ሎሚ ፈፅሞ አትጨክን
አሁን ሳናቅማማ ቶሎ እንሽጠው
ይሄ ውድ ሎሚ፣
ላ'ዲሱ ጎጇችን ትልቅ መሰረት ነው
ብላ አቀፈችኝ
እሰየው ዘንድሮ ለኔም ተሳካልኝ።
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
በተራበው ጎኔ፣ በተጎዳው ኪሴ
እኔም ሰው ነኝና፣
የከንፈር ወዳጄን ተጠምታብኝ ነበሴ
የጥምቀት ለት ሎሚ፣
ኪሴን በሚጎዳ በሚነርት ዋጋ
ይሁን ብየ ገዛሁ፣
ደረቷን ልመታ የዛችን ውብ ሸጋ።
ሎሚውን በእጄ ያዝኩ
ኮረዳዋን ፈለግኩ
ባ'ይኖቼ አማተርኩ
ከኋላዋ አየኋት...
ፀጉሯ ሹሩባ ነው፣ ፊቷ አይታይም
ኋላዋ ካማረ...
ፊቷ ምንም ይሁን እኔን አይጨንቀኝም
ዳሌዋ... ቢዮንሴን ያስንቃል
በንቅልፍ የቧዘዘን አጣድፎ ያነቃል
ስንት የወጣባትን፣
የኛን ሳተላይት ከቻይና ያመጥቃል (አንጥሮ😂)
ወገቧ... አካበድክ ባትሉኝ
ከቀጭኗ እግሬ ሚወፍር አይመስለኝ
ወይኔ ሹሩባዋ
ለመግለፅም እንኳን አንደበትን ያስራል
በቆሙበት መሬት አፍዞ ያስቀራል።
ወደራሴ መጣሁ...
ልወርውር አልወርውር?
ልወርውር አልወርውር?
ወረወርኩ...
ድምም... እዛው ዳሌዋ ላይ
አሟት ዩን ደስ ብሏት ዞር ብላ ብታይ
የኔ ልብ ደንግጣ ልትበር ወደ ሰማይ
እየሮጠች መጣች፣
እያነፈነፈች ትንፋሿ እስከሚያጥራት
ክፉ አስባ ይሆን ልሩጥ ልጠብቃት?
ደረሰች...
ፊቴ ከመድረሷ፣
አንድ ጊዜ በጥፊ አወላመመችኝ
ወደላይ ወደታች፣
መላ ሰውነቴን በደምብ ቃኘችኝ
ወደግራ ጆሮየ በጣም ተጠጋችኝ
ጊዜው የድንጋይ ነው ሎሚ አታባክን
ኪስህን አሟጠህ፣
በገዛኸው ሎሚ ፈፅሞ አትጨክን
አሁን ሳናቅማማ ቶሎ እንሽጠው
ይሄ ውድ ሎሚ፣
ላ'ዲሱ ጎጇችን ትልቅ መሰረት ነው
ብላ አቀፈችኝ
እሰየው ዘንድሮ ለኔም ተሳካልኝ።
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
#የአራዳ_ልጅ_ፉከራ
]በላይ በቀለ ወያ]
.
.
ዘራፍ
አሁንም ዘራፍ ፣ ቅድምም ዘራፍ
ቢገርፈኝ እንኳ
ሱስ እንዳለንጋ ፣ ኑሮ እንደጅራፍ
ማልደራደር ፣ ባንዲት ሀገሬ
ልክ እንደ ፕሪም ፣ እንደ ፖም ፍሬ
መንግስትን ላወርድ ፣ ድንጋይ ወርውሬ
አልሳካ ሲል ፣
መንገድ ዘግቼ ፣ ጎማ ማቃጥል
የቀበሌ አጥር ፣ የምገነጥል
የመንግስትን ስም
በተቃውሞ ድምፅ ፣ የማብጠለጥል
በኮብልስቶን ፣ ጠብመንጃ ማስጥል፡፡
ዘራፍ
ዘራፍ
ዘራፍ
፡፡፡፡
በል በለውና ፣ የመጣው ይምጣ
ስንገዛው ሱሪ ፣ ስንቀደው ቁምጣ
ባንለው እንኳን ፣ ጉልበት ጉልበቱን
እንሰጠዋለን ፣ የየግምቱን
ዘራፍ
አንቺም እረፊ ፣ አንተም ተው እረፍ
እርምህን ታግለህ ፣ እኔን አትዝለፍ
ሰውን የማልጥል ፣ እኔ ለማለፍ
ያራዳ ልጅ ነኝ ፣ ስመ ቅምጥል
እቁብ ነው እንጂ ፣ ሰውን የማልጥል፡፡
እንደቻይና አስፖልት ፣ ፍቅሬ ሚያቃጥል፡፡
፡፡፡፡፡
ዘራፍ
ስታገል ስቀህ
አልሰማ ብለህ ፣ እያልኩህ ስማኝ
ያጊዜ አልፎ
እኔ አስተምሬው ፣ እኔን ለሚያማኝ
ስቄ ባልፈውም ፣ ቁጣዬ አይበርድም
ቃል የማይወጣኝ ፣ እጄ ሳይቀድም
አንድ ላራዳ ፣ ሺህ ለጠላቴ
አፍ የማዘጋ ፣ በመሐል ጣቴ፡፡
፡፡፡፡፡፡
ዘራፍ
"ያዲሳባ ልጅ ፣
ቢሻኝ የሸገር
ቢሻኝ አራዳ ፣ ቢሻኝ ፊንፊኔ
እንደ ክርስቶስ
ስሜ ቢበዛም ፣
ዘር የማልቆጥር ፣ አንድ ነኝ እኔ፡፡
፡፡፡፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡
ዘራፍ
ጠፍጥፈውና ፣ የመጣው ይምጣ
ፒዛ ሚሰራ ፣ በናቁት ቂጣ
በናቁት ዳቦ ፣ ሚሰራ በርገር
የአራዳ ልጅ ፣
ሚበላው ቢያጣም ፣ አይበላም ነገር፡፡
፡፡፡፡
ዘራፍ
ሳይሰነዝር ጣይ ፣ ሳይወድቅ መካች
በአንድ ኩርኩም ፣ ሺ አናት ፈንካች
ሺህ የሚገድል ፣ አንዴ ከሳቀ
እንደምንሽር ፣ ቀልድ የታጠቀ
መንግስትን ማውረድ...
አልሆንለት ሲል ፣ ለትግል ሔዶ
ፌስቡክ ሚጠቀም ፣ ኦፔራ አውርዶ
ዘራፍፍፍ!!!
© Belay Bekele Weya
@Simetin_Begitim
]በላይ በቀለ ወያ]
.
.
ዘራፍ
አሁንም ዘራፍ ፣ ቅድምም ዘራፍ
ቢገርፈኝ እንኳ
ሱስ እንዳለንጋ ፣ ኑሮ እንደጅራፍ
ማልደራደር ፣ ባንዲት ሀገሬ
ልክ እንደ ፕሪም ፣ እንደ ፖም ፍሬ
መንግስትን ላወርድ ፣ ድንጋይ ወርውሬ
አልሳካ ሲል ፣
መንገድ ዘግቼ ፣ ጎማ ማቃጥል
የቀበሌ አጥር ፣ የምገነጥል
የመንግስትን ስም
በተቃውሞ ድምፅ ፣ የማብጠለጥል
በኮብልስቶን ፣ ጠብመንጃ ማስጥል፡፡
ዘራፍ
ዘራፍ
ዘራፍ
፡፡፡፡
በል በለውና ፣ የመጣው ይምጣ
ስንገዛው ሱሪ ፣ ስንቀደው ቁምጣ
ባንለው እንኳን ፣ ጉልበት ጉልበቱን
እንሰጠዋለን ፣ የየግምቱን
ዘራፍ
አንቺም እረፊ ፣ አንተም ተው እረፍ
እርምህን ታግለህ ፣ እኔን አትዝለፍ
ሰውን የማልጥል ፣ እኔ ለማለፍ
ያራዳ ልጅ ነኝ ፣ ስመ ቅምጥል
እቁብ ነው እንጂ ፣ ሰውን የማልጥል፡፡
እንደቻይና አስፖልት ፣ ፍቅሬ ሚያቃጥል፡፡
፡፡፡፡፡
ዘራፍ
ስታገል ስቀህ
አልሰማ ብለህ ፣ እያልኩህ ስማኝ
ያጊዜ አልፎ
እኔ አስተምሬው ፣ እኔን ለሚያማኝ
ስቄ ባልፈውም ፣ ቁጣዬ አይበርድም
ቃል የማይወጣኝ ፣ እጄ ሳይቀድም
አንድ ላራዳ ፣ ሺህ ለጠላቴ
አፍ የማዘጋ ፣ በመሐል ጣቴ፡፡
፡፡፡፡፡፡
ዘራፍ
"ያዲሳባ ልጅ ፣
ቢሻኝ የሸገር
ቢሻኝ አራዳ ፣ ቢሻኝ ፊንፊኔ
እንደ ክርስቶስ
ስሜ ቢበዛም ፣
ዘር የማልቆጥር ፣ አንድ ነኝ እኔ፡፡
፡፡፡፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡
ዘራፍ
ጠፍጥፈውና ፣ የመጣው ይምጣ
ፒዛ ሚሰራ ፣ በናቁት ቂጣ
በናቁት ዳቦ ፣ ሚሰራ በርገር
የአራዳ ልጅ ፣
ሚበላው ቢያጣም ፣ አይበላም ነገር፡፡
፡፡፡፡
ዘራፍ
ሳይሰነዝር ጣይ ፣ ሳይወድቅ መካች
በአንድ ኩርኩም ፣ ሺ አናት ፈንካች
ሺህ የሚገድል ፣ አንዴ ከሳቀ
እንደምንሽር ፣ ቀልድ የታጠቀ
መንግስትን ማውረድ...
አልሆንለት ሲል ፣ ለትግል ሔዶ
ፌስቡክ ሚጠቀም ፣ ኦፔራ አውርዶ
ዘራፍፍፍ!!!
© Belay Bekele Weya
@Simetin_Begitim
Universeን እንደ ኢትዮጵያ ካየን 9ኙ ፕላኔቶቿ በ9ኙ ክልሎች ይወከላሉ። ፀሐይቷ አዲስ አበባ ስትሆን ጨረቃዋ ደግሞ ድሬ ናት።
ምን ለማለት ፈልጌ ነዉ "እናታችሁን ልቀፍና እናንት ፕላኔቶች ያለ ፀሐይ ሁላችሁም ጨለማ ናችሁ!! ፀሐይን ደግሞ አንዱ ፕላኔት ይቅርና ፀሐይ እራሷ የኔ ብቻ ናት ማለት አትችልም። ይልቅ ፀሐይ እንድትወጣላችሁ ከፈለጋችሁ በየምህዋራችሁ ተሽከርከሩ!!"
ተነካሁ ወይም ቀረሁ የሚል ፕላኔት ካለ ነገ ፀሐይ ስትወጣ ያናግራት።
ፌቄስ የ1640ዎቹ!! ✋✊

ለምሽታችን ....
_____________________________
‹ድንች ኃይል ይሰጣል›
____________
ድሮ ከልጆች ጋር ስንጫወት ተመትተን ከመጣን ወላጆቻችን ይቆጣሉ፡፡ ‹ለምን ታለቃቅሳለህ› የሚለው የመጀመሪያ ቁጣቸው ነው፡፡ ወይ እዚያው ታግለህ አሸንፈህ መምጣት ነው፤ አለያም ደግሞ መሸነፍህን አምነህ በቀጣይ እንዴት እንደምታሸንፍ ማሰብ ነው፡፡
________________________
ማለቃቀስ መፍትሔ አይሆንም፡፡
ሦስተኛ ክፍል እያለሁ ሙሉጌታ የሚባል ልጅ እኛ ክፍል ነበረ(ስሙ ተለውጧል)፡፡ ሙሉጌታ እንደ ጸጋዬ የሚፈራው አልነበረም፡፡ ልጆቹም ተንኮለኞች ናቸው መሳቅ ሲፈልጉ ሙሉጌታና ጸጋዬን ማጋጠም ይወዳሉ፡፡ ጸጋዬ ወፍራም ነው፡፡ ሙሉጌታን ከመሬት ጋር ይሰፋዋል፡፡ ሙሉጌታ ሦስት ጊዜ ይቀጣል፡፡ ጸጋዬ ያደባየዋል፡፡ ልጆቹ ይስቁበታል፡፡ እናቱ ደግሞ ‹እያለቃቀስክ አትምጣ፣ የአንተ እጅስ ሙቅ ይዟል ወይ!› ብለው ይገርፉታል፡፡
___________________________________
አንድ ቀን የሳይንስ አስተማሪያችን ስለ ኃይል ሰጭ ምግቦች አስተማረን፡፡ ድንች ኃይል እንደሚሰጥ ከነ ሥዕሉ አሳየን፡፡ የሙሉጌታ ዓይኖች በሩ፡፡ ልቡ ሞቀ፣ አዲስ ሐሳብ የተገለጠለት መሰለው፡፡ እናቱ የድንች ነጋዴ ናቸው፡፡ ቤቱ የቅዳሜ ገበያ ፊት ለፊት ነበር፡፡
___________________________
ቤቱ እንደገባ ድስት ሙሉ የድንች ቅቅል በሚጥሚጣ አስቀርቦ ራቱን በላ፡፡ ጠዋትም ቁርሱ እርሱ ነበር፡፡ ከዳንቴል በተሠራው ቦርሳው አንድ አምስት ድንች ይዞ መምጣቱ ትዝ ይለኛል፡፡
___________________________________
በዕረፍት ሰዓት ሙሉጌታ እጅጌውን እየሰበሰበ መጣ፡፡ ‹ዛሬ ከጸጋዬ ጋር መጋጠም እፈልጋለሁ› አለ፡፡ ተማሪዎቹ ሁሉ የሙሉጌታን ኮስማና ሰውነት እያዩ ደነገጡ፡፡ ምን ተፈጠረ? ‹ትናንት የተማርነውን ታስታውሳላችሁ› አለ ሙሉጌታ፡፡ ሁላችንም ከብበን እናየዋለን፡፡
_________________________________
‹ድንች ኃይል ይሰጣል› አለ ሙሉጌታ፡፡ ከዚያም በቦርሳው ያመጣውን ቅቅል ድንች ፈረካክሶ አከፋፈለን፡፡ እየበላን ራሳችንን በአድናቆት ነቀነቅንለት፡፡ ‹ትናንትና ዛሬ ጠዋት አንድ ድስት ሙሉ ድንች ነው የበላሁት› አለ ሙሉጌታ፡፡
__________________________________
እኛም በተማርነው መሠረት የሠፈረበትን ኃይል ለማወቅ መላ ሰውነቱን አየነው፡፡ አንድ ድስት ሙሉ ድንች ከበላማ ማን ይችለዋል፡፡ ለራሳችንም ፈራን፡፡ ልጆች ነበርንና አንዳች ኃይል ከድንች ማግኘቱን አመንን፡፡ እናቱ ድንች እንደሚነግዱ እናውቃለን፡፡ ደግሞ አስተማሪያችን ከድንች ኃይል እንደሚገኝ በሥዕል ጭምር አሳይተውናል፡፡
_________________________________
‹ወይኔ ጸጋዬ አለቀለት› አልን፡፡ ጸጋዬ መጣ፡፡ የተወሰኑ ልጆች ጠጋ ብለው የሆነው ነገር ነገሩት፡፡ ጸጋዬ ደነገጠ፡፡ እነ ሙሉጌታ ቤት ድንች እንደ ልብ መሆኑን ያውቃል፡፡ ድንች ደግሞ ኃይል ይሰጣል፡፡ ‹ግጠመው፣ ግጠመው› አልነው ተሰብስበን፡፡ ጸጋዬ ፈራ፡፡ ሙሉጌታ ትከሻውን ሰበቀ፡፡ ‹ፈሪ! ፈሪ! ፈሪ! ተንፈርፈሪ› ጩኸትና ጭብጨባ፡፡ ጸጋዬ አንገቱን ሰብሮ መጣ፡፡ ሙሉጌታ እግሮቹን አንፈራጠጠ፡፡ ተጋጠሙ፡፡ ሙሉጌታ በዚያች ቀጫጫ ሰውነቱ ጸጋዬን አነሣው፤ ተሸከመው፡፡ መሬት ላይ ጣለው፡፡ ሆሆሆሆሆሆ፤ ትምህርት ቤቱ አበደ፡፡
___________________________________
ጉድ ተባለ፡፡ መሬቱን በእግራችን እየረገጥን አጨበጨብንለት፡፡ የሙሉጌታ አልቃሻነት ከዚያ በኋላ ቀረ፡፡
ዛሬ ሳስበው ሙሉጌታ ኃይል ያገኘው ከበላው ድንች አይመስለኝም፡፡ ‹ድንች ኃይል ይሰጣል› ከሚለው ትርክት እንጂ፡፡ ጸጋዬንም ያስደነገጠው ያ ነው፡፡
__________________________________
የሙሉጌታ ሰውነት አልተለወጠም፡፡ ያው ቀጫጫው ሙሉጌታ ነው፡፡ እምነቱ ግን ተቀይሯል፡፡ ጸጋዬን ሲያየው እንዴት እንደሚሮጥ ነበር የሚያስበው፡፡ ለዚህ ነው ምንጊዜም ተመትቶ የሚያለቅሰው፡ ያውም ሮጦም ፣ ተመትቶም፣ ተሰድቦም፡፡
___________________________________
ዛሬ ግን ለማሸነፍ እንጂ ለማልቀስ አልመጣም፡፡ ሙሉጌታ ከዚህ በፊት እንዲህ አድርገኸኝ፣ እንዲህ ሆኜ፣ እንዲህ ተደርጌ እያለ ቢያላዝን ኖሮ በአእምሮው የሚመጣው ሽንፈቱ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ድንቹን ብቻ ነው ያሰበው፡፡ ‹ድንች ኃይል ይሰጣል፡፡›
__________________________________
ዋናው ጉዳይ ማን ነህ? አይደለም፡፡ ምን ታምናለህ? ነው፡፡ ዳዊትን በጎልያድ ፊት ያቆመው እምነቱ ነው፡፡ ዐቅሙ አይደለም፡፡
ምንጭ ዳንኤል ክብረት

#Only in Ethiopia
#እንደንተ አይነት ንፁህ ኢትዮጵያዊ ወገኑን አክባሪ ልጅ ሀገሬ ስላላት ኮረው!
💚💛❤️
ሀይማኖት እንድንከባበር ያደርገናል እንጂ አይለየንም፡፡
@Simetin_Begitim
@GeezWorld1
#እንደንተ አይነት ንፁህ ኢትዮጵያዊ ወገኑን አክባሪ ልጅ ሀገሬ ስላላት ኮረው!
💚💛❤️
ሀይማኖት እንድንከባበር ያደርገናል እንጂ አይለየንም፡፡
@Simetin_Begitim
@GeezWorld1
©90'S ልጆች
#እንደ ሀጂ አይነት ደግ አባት ወገኑን አክባሪ የኢትዮጵያዊነት ምሣሌ የሆኑ አባት ብዙዎች ስላሉን በኢትዮጵያችን ተስፋ አንቆርጥም ፡፡
#ሀይማኖት የከባብረናል እንጂ አይነጣጥለንም ፡፡
@Simetin_Begitim
@Geezworld1
#እንደ ሀጂ አይነት ደግ አባት ወገኑን አክባሪ የኢትዮጵያዊነት ምሣሌ የሆኑ አባት ብዙዎች ስላሉን በኢትዮጵያችን ተስፋ አንቆርጥም ፡፡
#ሀይማኖት የከባብረናል እንጂ አይነጣጥለንም ፡፡
@Simetin_Begitim
@Geezworld1
የአለም እምነቶች መሠረታቸው ፍቅር ነው ! በየትኛውም እምነት አስተምህሮት ውስጥ ሠውነት ይቀድማል ባንተ ላይ እንዲደረግ ማትፈልገውን በሌላው ላይ እንድታደርግም አይፈቅድም ፡፡ የንተን ሀሣብ በግድ ሌላው ላይ ለመጫን በጣርክ ቁጥር ተቀባይነት ታጣለህ ፡፡ ኢትዮጵያ እንደው በፈጣሪ ቸርነት እዚህ ደርሳለች እያነባች በየዘመኑ ልጆችዋን እየገበረች ከከፍታ ቁልቁል እየተምዘገዘገች ፈረሰች ሲሏት እየተገነባች በሀይማኖት አባቶቻችን ዱዓና ፀሎት የእኛ ዘመን ላይ ደርሳለች ፡፡ አባቶቻችን የሠጡንን ብዙ ዕሴቶች ብናጠፋቸውም እንደ አሁኑ በቤተ እምነት ላይ አፀያፊ ተግባር አልፈፀምንም ነበር መስጅድ ማቃጠል ቤተክርስቲያን መቃጠል አማኞችን ማረድ የለየለት እርኩሠት ውስጥ ገብተናል ፡፡ ሠከን እንበል ኢትዮጵያ አትፈርስም ብለን ማቅራራት ኢትዮጵያን ከመፈረካከስ አያድናትም መንግስት ሆይ ትግስትህ ገደብ አቷል ህዝቡን መጠበቅ ካልቻልክ ውረድ የእምነት አባቶች ተከታዮቻችሁን ስለ ሀገር ፍቅር ስበኩ በየመንደሩ እየዞራችሁ የእንትን ቤተክህነት የእንትን ድምፅ ይሠማ አትበሉ ፡፡ የኢትዮጵያ ህልውና በእኛ ልጆችዋ እጅ ነው ያለው፡፡
አበቃው ሠላም ለሀገሬ ሠላም ለሠው ዘር በሙሉ !
አበቃው ሠላም ለሀገሬ ሠላም ለሠው ዘር በሙሉ !
የእስክሽር ሱሰኛ
።
እስክትሽሪ ዘፍነሽ እስክሽር ላስቆምሽኝ
የድምፅሽን ውበት ሌት ተቀን አትንሺኝ
።
አንቺው ባለቅኔ አንቺው ሰው አሻሪ
እንባ ነው ጉልበትሽ ወደሽ ስታፈቅሪ
እኔም ያንቺ አድማጭ የእስክሽር ሱሰኛ
ድምፅሽን ካልሰማው እንቅልፍ ባይኔ አይዞር ለሊቱን አልተኛ
።
እናምልሽ አንቺ ቃልሽን አክባሪ
ባይገጥምሽ ጓደኛ ለቀለበት ኗሪ
ድምፅሽን ለአንድ አፍታ ሰምቶሽ የወደደ
አንድ ልብ አለልሽ ከውሸት አለም ርቆ ወቶ የተሰደደ
በሙዚቃም ሀይል
መከዳትን ዘፍነሽ ነፍስ የዘራሽበት
እስክሽር ላፈቅርሽ በልብሽ ላይ ልዝመት
።
ባትረሺው ትዝታን በልብሽ ተስሎ
ቢተውሽ ነካክቶ ፍቅርን ተመስሎ
በድምፅሽ ለሻረው የእስክሽር ሱሰኛ
በይ ቶሎ ዳኝለት ሰላም ውሎ ይተኛ
ቃልሽ ላይነካ ፍፁም የነበረ
እስክትሽሪ ረስቶሽ ወድያው የተሰበረ
ለእግዜሩ ሰላምታ ምን ቢኮራ ላንቺ
ብዙ አይኖች አሉ የሚያዩ ወዳንቺ
።
ልካስሽ ለማለት ያልኩት ፈራ ተባ
ጉዳትሽን ሳስብ ነው መሆኑን ጉልበትሽ የስብራት እንባ
።
ማልቀስ እና ውበት ፣ ቃላትን ቢነሱኝ ፣ ከድምፅሽ ባንድምታ
የእስክሽር ሱሰኛ አስባለኝ ዝምታ።
ተፃፈ በአኒታ
@endenaendena
።
እስክትሽሪ ዘፍነሽ እስክሽር ላስቆምሽኝ
የድምፅሽን ውበት ሌት ተቀን አትንሺኝ
።
አንቺው ባለቅኔ አንቺው ሰው አሻሪ
እንባ ነው ጉልበትሽ ወደሽ ስታፈቅሪ
እኔም ያንቺ አድማጭ የእስክሽር ሱሰኛ
ድምፅሽን ካልሰማው እንቅልፍ ባይኔ አይዞር ለሊቱን አልተኛ
።
እናምልሽ አንቺ ቃልሽን አክባሪ
ባይገጥምሽ ጓደኛ ለቀለበት ኗሪ
ድምፅሽን ለአንድ አፍታ ሰምቶሽ የወደደ
አንድ ልብ አለልሽ ከውሸት አለም ርቆ ወቶ የተሰደደ
በሙዚቃም ሀይል
መከዳትን ዘፍነሽ ነፍስ የዘራሽበት
እስክሽር ላፈቅርሽ በልብሽ ላይ ልዝመት
።
ባትረሺው ትዝታን በልብሽ ተስሎ
ቢተውሽ ነካክቶ ፍቅርን ተመስሎ
በድምፅሽ ለሻረው የእስክሽር ሱሰኛ
በይ ቶሎ ዳኝለት ሰላም ውሎ ይተኛ
ቃልሽ ላይነካ ፍፁም የነበረ
እስክትሽሪ ረስቶሽ ወድያው የተሰበረ
ለእግዜሩ ሰላምታ ምን ቢኮራ ላንቺ
ብዙ አይኖች አሉ የሚያዩ ወዳንቺ
።
ልካስሽ ለማለት ያልኩት ፈራ ተባ
ጉዳትሽን ሳስብ ነው መሆኑን ጉልበትሽ የስብራት እንባ
።
ማልቀስ እና ውበት ፣ ቃላትን ቢነሱኝ ፣ ከድምፅሽ ባንድምታ
የእስክሽር ሱሰኛ አስባለኝ ዝምታ።
ተፃፈ በአኒታ
@endenaendena
#አንበሳ_ቀነኒሳ
ኢትዮጵያዊነቴን እንዲነጥቀኝ ለማንም አልፈቅድም፡፡
ለኔ ብሄር እንደ ካልሲና ኮፍያ ተጨማሪ ጌጥ ነዉ፡፡ ሀገር ግን ሙሉ ልብስ ናት፡፡ ሰዉ በካልሲና ኮፍያ አደባባይ አይወጣም ብሔርም እንደዛዉ ነዉ፡፡ ሀገሬን ለብሼ ግን አለምን እዞራለሁ ፡፡
......
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ
©@እንደኔእይታ
ኢትዮጵያዊነቴን እንዲነጥቀኝ ለማንም አልፈቅድም፡፡
ለኔ ብሄር እንደ ካልሲና ኮፍያ ተጨማሪ ጌጥ ነዉ፡፡ ሀገር ግን ሙሉ ልብስ ናት፡፡ ሰዉ በካልሲና ኮፍያ አደባባይ አይወጣም ብሔርም እንደዛዉ ነዉ፡፡ ሀገሬን ለብሼ ግን አለምን እዞራለሁ ፡፡
......
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ
©@እንደኔእይታ