++የዚህ አለም ሰው++
ከሀቅ ይልቅ ለሀሰት የኖረ፣
ለፍቅር መኖር ሲችል ለፀብ ያደረ፣
ህሊናውን ሽጦ በምላሱ የከበረ፣
ደግነትን ትቶ ክፋትን እያጫረ፣
እኛነትን ረስቶ በኔነት የታጠረ፣
የበላይተትን እጅጉኑ ያፈቀረ፣
የትለመድረስ ይሁን እንዲ የፈነጨ፣
ከፈጣሪም ህግጋት ከምድራዊዉም የተጋጨ።
ዘነጋው መሰለኝ የዘላለም ቤቱን፣
ወደመጣበት አፈር መልሶ መግባቱን።
አብረሀም ተስፋዬ 29/02/2008 e.c
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ከሀቅ ይልቅ ለሀሰት የኖረ፣
ለፍቅር መኖር ሲችል ለፀብ ያደረ፣
ህሊናውን ሽጦ በምላሱ የከበረ፣
ደግነትን ትቶ ክፋትን እያጫረ፣
እኛነትን ረስቶ በኔነት የታጠረ፣
የበላይተትን እጅጉኑ ያፈቀረ፣
የትለመድረስ ይሁን እንዲ የፈነጨ፣
ከፈጣሪም ህግጋት ከምድራዊዉም የተጋጨ።
ዘነጋው መሰለኝ የዘላለም ቤቱን፣
ወደመጣበት አፈር መልሶ መግባቱን።
አብረሀም ተስፋዬ 29/02/2008 e.c
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ሀ ገ ሬ
፠፠፠
ሀገሬ ውበት ነው፣
ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት፣
ፀሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት።
ሀገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ፣
እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ እስኪነጋ።
ሀገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ፣
ሀገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ፣
ውበት ነው በበጋ ፀሃይ አትፋጅም፣
ክረምቱም አይበርድም፣
አይበርድም፣ አይበርድም።
ሀገሬ ጫካ ነው፣
እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት፣
በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት።
እዚያ አለ ነፃነት፣
በሃገር መመካት፣
በተወላጅነት፣
በባለቤትነት፣
እዚያ አለ ነፃነት።
ሀገሬ ሃብት ነው፤
ጎመኑ ስብ ጮማ፣ ቆሎ ክትፎ ስጋ፣
ድርቆሹ ፍትፍት ነው፣ ቃሪያው ሙክት ሠንጋ፣
ጠጁ ነው ወለላ፣
ከኮኛክ ያስንቃል የመንደሩ ጠላ።
እህሉ ጣእም አለው እንጀራው ያጠግባል፣
ከቢራ ከሻምፓኝ ውሃው ይጣፍጣል፣
በዓሉ ይደምቃል፣
ሙዚቃው ያረካል፣
ጭፈራው ዘፈኑ ችግርን ያስረሳል።
እዚያ ዘመድ አለ፣
ሁሉም የናት ልጅ ነው፣
ሁሉም ያባት ልጅ ነው፣
ጠላትም አንዳንዴ ይመጣል መቃብር፣
ባለጋራም ቸር ነው “ያገር ልጅ ሲቸገር” ፤
ገነት ነው ሀገሬ።
ምነው ምን ሲደረግ ?
ምነው ለምን እንዴት ?
ዘራፊ ቀማኛ ምቀኛ ወንበዴ፣
ጥርኝ አፈር በጁ ስንዝር ወሰን አልፎ፣
የተቀደሰውን ያፍሪቃ ላይ ደሴት፣
ባያገኝ ለማርከስ ጠላት ይመኝ እንዴት።
እምቢኝ አሻፈረኝ፣
አሻፈረኝ እምቢ፣
መቅደስ ነው ሀገሬ፣
አድባር ነው ሀገሬ፣
እናትና አባት ድኸው ያደጉበት፣
ካያት ከቅደም አያት የተረካከቡት፣
አፈር የፈጩበት፣
ጥርስ የነቀሉበት።
ሀገሬ ዓርማ ነው፣ የነጻነት ዋንጫ፣
በቀይ የተጌጠ ባረንጓዴ ቢጫ።
እሾህ ነው ሀገሬ፣
በጀግናው ልጅ አጥንት የተከሰከሰ፣
ጠላት ያሳፈረ አጥቂን የመለሰ።
አገሬ ታቦት ነው ፣ መቅደስ የሃይማኖት፣
ዘመን የፈተነው በጠበል በጸሎት።
ለምለም ነው ሀገሬ፣
ውበት ነው ሀገሬ፣
ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ፣
እዚያ ነው አፈሩ፣ የማማ ያባባ።
ስሳብ እሔዳለሁ ቢሰበርም እግሬ፣
አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ ሀገሬ።
አለብኝ ቀጠሮ
ከትውልድ ሀገሬ፣
ካሳደገኝ ጓሮ።
፠፠
ሰዓሊና ገጣሚ ገብረ ክርስቶስ ደስታ
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ሀ ገ ሬ
፠፠፠
ሀገሬ ውበት ነው፣
ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት፣
ፀሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት።
ሀገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ፣
እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ እስኪነጋ።
ሀገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ፣
ሀገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ፣
ውበት ነው በበጋ ፀሃይ አትፋጅም፣
ክረምቱም አይበርድም፣
አይበርድም፣ አይበርድም።
ሀገሬ ጫካ ነው፣
እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት፣
በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት።
እዚያ አለ ነፃነት፣
በሃገር መመካት፣
በተወላጅነት፣
በባለቤትነት፣
እዚያ አለ ነፃነት።
ሀገሬ ሃብት ነው፤
ጎመኑ ስብ ጮማ፣ ቆሎ ክትፎ ስጋ፣
ድርቆሹ ፍትፍት ነው፣ ቃሪያው ሙክት ሠንጋ፣
ጠጁ ነው ወለላ፣
ከኮኛክ ያስንቃል የመንደሩ ጠላ።
እህሉ ጣእም አለው እንጀራው ያጠግባል፣
ከቢራ ከሻምፓኝ ውሃው ይጣፍጣል፣
በዓሉ ይደምቃል፣
ሙዚቃው ያረካል፣
ጭፈራው ዘፈኑ ችግርን ያስረሳል።
እዚያ ዘመድ አለ፣
ሁሉም የናት ልጅ ነው፣
ሁሉም ያባት ልጅ ነው፣
ጠላትም አንዳንዴ ይመጣል መቃብር፣
ባለጋራም ቸር ነው “ያገር ልጅ ሲቸገር” ፤
ገነት ነው ሀገሬ።
ምነው ምን ሲደረግ ?
ምነው ለምን እንዴት ?
ዘራፊ ቀማኛ ምቀኛ ወንበዴ፣
ጥርኝ አፈር በጁ ስንዝር ወሰን አልፎ፣
የተቀደሰውን ያፍሪቃ ላይ ደሴት፣
ባያገኝ ለማርከስ ጠላት ይመኝ እንዴት።
እምቢኝ አሻፈረኝ፣
አሻፈረኝ እምቢ፣
መቅደስ ነው ሀገሬ፣
አድባር ነው ሀገሬ፣
እናትና አባት ድኸው ያደጉበት፣
ካያት ከቅደም አያት የተረካከቡት፣
አፈር የፈጩበት፣
ጥርስ የነቀሉበት።
ሀገሬ ዓርማ ነው፣ የነጻነት ዋንጫ፣
በቀይ የተጌጠ ባረንጓዴ ቢጫ።
እሾህ ነው ሀገሬ፣
በጀግናው ልጅ አጥንት የተከሰከሰ፣
ጠላት ያሳፈረ አጥቂን የመለሰ።
አገሬ ታቦት ነው ፣ መቅደስ የሃይማኖት፣
ዘመን የፈተነው በጠበል በጸሎት።
ለምለም ነው ሀገሬ፣
ውበት ነው ሀገሬ፣
ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ፣
እዚያ ነው አፈሩ፣ የማማ ያባባ።
ስሳብ እሔዳለሁ ቢሰበርም እግሬ፣
አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ ሀገሬ።
አለብኝ ቀጠሮ
ከትውልድ ሀገሬ፣
ካሳደገኝ ጓሮ።
፠፠
ሰዓሊና ገጣሚ ገብረ ክርስቶስ ደስታ
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ከቶ ጊዜ አትስጥ ማድረግ ያለብህን ሁሉ ዛሬውኑ አድርግ፡፡ ለነገ አታሳድር ምክንያቱም ዛሬ እንጅ ነገ ያንተ ላይሆን ይችላል ፡፡
Forwarded from ፈለገ ምሕረት (Yeshwas Dinku)
የአፄ ቴዎድሮስ ችሎት
አንድ ሲራራ ነጋዴ መንገድ ሲሔድ ቆይቶ ቀን በምሳ ሰዓት ከአንድ ዛፍ ሥር አረፍ ብሎ ምሳውን ቆሎ ቆርጥሞና ውሃ ጠጥቶ ጉዞውን ሲቀጥል ሁለት መቶ ጠገራ ብር ረስቶ ሄደ።
አንድ ገበሬ አግኝቶለት ያንን ገንዘብ ሊሰጠው ከኋላ እየሮጠ ተከተለውና ‹‹ሰውዬ ቆም ብለህ ጠብቀኝ፤ ጥለኸው የሔድከው ገንዘብህን አግኝቼልሃለሁ፤›› አለው።
ነጋዴውም ‹‹ያገኘኸው ገንዘብ ስንት ነው?›› ሲለው ‹‹ሁለት መቶ ብር›› አለው። ነጋዴው ግን ‹‹እኔ የጠፋብኝ ገንዘብ ሦስት መቶ ብር ነው።
አንዱን መቶ ብር የት ደብቀህ ነው ሁለት መቶ ብር
የምትሰጠኝ። ሞልተህ ካላመጣህ አልቀበልህም እከስሃለሁ። እንዲህ በዋዛ አንላቀቅም›› አለው።
ገበሬውም ገንዘቡን እንደያዘ ወደ ኋላ ተመለሰ።
ነጋዴው የመሠረተው የውሸት ክስ በይግባኝ ተይዞ ወደ አፄ ቴዎድሮስ ሲቀርብ የሁለቱን አባባል ካዳመጡ በኋላ ነጋዴውን ምን ያህል ገንዘብ ነው የጠፋህ? ሲሉት ‹‹ሦስት መቶ ጠገራ ብር ነው›› አላቸው።
ገበሬውንም ‹‹ምን ያህል ገንዘብ አገኘህ?›› ሲሉት ‹‹ሁለት መቶ ጠገራ ብር ብቻ ነው›› አለ።
ከዚያ በኋላ ‹‹አንተ ነጋዴው ጠፋብኝ የምትለውን ሦስት መቶ ብር ከጣልህበት ቦታ ፈልገህ አግኝ። ሁለት መቶ ብር ያገኘኸው ገበሬ ደግሞ ሁለት መቶ ብር ጠፋኝ የሚል ሌላ ሰው እስከሚመጣ ድረስ ራስህ ልትጠቀምበት ትችላለህ›› ሲሉ
ፈርደው ፋይሉ ተዘጋ።
መክብብ አጥናው ‹‹የአባቶች ጨዋታ›› (2005)
የቆጡን አወርድ ብላ.......ይላል የሀገሬ ሰው። ክርስቲያን ያለኝ ይበቃኛል ሊል ይገባዋል
#ለመቀላቀል_ከታች_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇
💚 @FMhret 💚
💛 @FMhret 💛
❤️ @FMhret ❤️
👆👆👆👆👆👆
አንድ ሲራራ ነጋዴ መንገድ ሲሔድ ቆይቶ ቀን በምሳ ሰዓት ከአንድ ዛፍ ሥር አረፍ ብሎ ምሳውን ቆሎ ቆርጥሞና ውሃ ጠጥቶ ጉዞውን ሲቀጥል ሁለት መቶ ጠገራ ብር ረስቶ ሄደ።
አንድ ገበሬ አግኝቶለት ያንን ገንዘብ ሊሰጠው ከኋላ እየሮጠ ተከተለውና ‹‹ሰውዬ ቆም ብለህ ጠብቀኝ፤ ጥለኸው የሔድከው ገንዘብህን አግኝቼልሃለሁ፤›› አለው።
ነጋዴውም ‹‹ያገኘኸው ገንዘብ ስንት ነው?›› ሲለው ‹‹ሁለት መቶ ብር›› አለው። ነጋዴው ግን ‹‹እኔ የጠፋብኝ ገንዘብ ሦስት መቶ ብር ነው።
አንዱን መቶ ብር የት ደብቀህ ነው ሁለት መቶ ብር
የምትሰጠኝ። ሞልተህ ካላመጣህ አልቀበልህም እከስሃለሁ። እንዲህ በዋዛ አንላቀቅም›› አለው።
ገበሬውም ገንዘቡን እንደያዘ ወደ ኋላ ተመለሰ።
ነጋዴው የመሠረተው የውሸት ክስ በይግባኝ ተይዞ ወደ አፄ ቴዎድሮስ ሲቀርብ የሁለቱን አባባል ካዳመጡ በኋላ ነጋዴውን ምን ያህል ገንዘብ ነው የጠፋህ? ሲሉት ‹‹ሦስት መቶ ጠገራ ብር ነው›› አላቸው።
ገበሬውንም ‹‹ምን ያህል ገንዘብ አገኘህ?›› ሲሉት ‹‹ሁለት መቶ ጠገራ ብር ብቻ ነው›› አለ።
ከዚያ በኋላ ‹‹አንተ ነጋዴው ጠፋብኝ የምትለውን ሦስት መቶ ብር ከጣልህበት ቦታ ፈልገህ አግኝ። ሁለት መቶ ብር ያገኘኸው ገበሬ ደግሞ ሁለት መቶ ብር ጠፋኝ የሚል ሌላ ሰው እስከሚመጣ ድረስ ራስህ ልትጠቀምበት ትችላለህ›› ሲሉ
ፈርደው ፋይሉ ተዘጋ።
መክብብ አጥናው ‹‹የአባቶች ጨዋታ›› (2005)
የቆጡን አወርድ ብላ.......ይላል የሀገሬ ሰው። ክርስቲያን ያለኝ ይበቃኛል ሊል ይገባዋል
#ለመቀላቀል_ከታች_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇
💚 @FMhret 💚
💛 @FMhret 💛
❤️ @FMhret ❤️
👆👆👆👆👆👆
Micky Admassu ▶ Book for ALL
፨፨፨
እቃ እቃ
(ሚኪ )
"እንቆቅልሽ"
"ምናውቅልሽ"
ቢጠይቁ ቢጠይቁ
ጠይቆ ማይዘልቋት
ቢያውቁ ቢያውቁ
አውቆ ማይጨርሷት
ቢጠበቡ ፣ የቱን ያህል ቢካኑ
አይዳሰስ እውቀት እርቃኑ ፤
ህይወት ማለት ጥሬ
ማትጎመራ ፍሬ
ኑሮ ማለት ትርዒት
ለሰርክ ጨቅላነት
የዘወትር ልምምድ ናት ፤
የሆኑትን ላለመሆን
ያልሆኑትን ለመሆን
ጨቅላ ሆኖ መተወን፡፡
ፈጣጣ ግንባርን
መከለያ ሻሽ
የማይረሳውን
መርሻ ድብብቆሽ፤
ለራስ ጥያቄ የራስ ምላሽ
አታካች ፍለጋን
እያዋዙ በአበባዮሽ
በዘመን ሁዳድ ቃቃ
በኃሊት አባሮሽ፡፡
ላይ ላዩን 'ሚፈኩበት
በልጅነት ዜማ
ውስጥ ውስጡን 'ሚደሙበት
የፍልሚያ አውድማ ፤
ህይወት ማለት እንድህ ነች
ተጥዳ እያረረች
ማትበስል ጨቅላነት ፤
ኑሮ ማለት ትወና
የዘወትር ትርዒት
አይበርዴውን እሳት
ለመልመድ ፡ አሊያም ለመርሳት፡፡
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
፨፨፨
እቃ እቃ
(ሚኪ )
"እንቆቅልሽ"
"ምናውቅልሽ"
ቢጠይቁ ቢጠይቁ
ጠይቆ ማይዘልቋት
ቢያውቁ ቢያውቁ
አውቆ ማይጨርሷት
ቢጠበቡ ፣ የቱን ያህል ቢካኑ
አይዳሰስ እውቀት እርቃኑ ፤
ህይወት ማለት ጥሬ
ማትጎመራ ፍሬ
ኑሮ ማለት ትርዒት
ለሰርክ ጨቅላነት
የዘወትር ልምምድ ናት ፤
የሆኑትን ላለመሆን
ያልሆኑትን ለመሆን
ጨቅላ ሆኖ መተወን፡፡
ፈጣጣ ግንባርን
መከለያ ሻሽ
የማይረሳውን
መርሻ ድብብቆሽ፤
ለራስ ጥያቄ የራስ ምላሽ
አታካች ፍለጋን
እያዋዙ በአበባዮሽ
በዘመን ሁዳድ ቃቃ
በኃሊት አባሮሽ፡፡
ላይ ላዩን 'ሚፈኩበት
በልጅነት ዜማ
ውስጥ ውስጡን 'ሚደሙበት
የፍልሚያ አውድማ ፤
ህይወት ማለት እንድህ ነች
ተጥዳ እያረረች
ማትበስል ጨቅላነት ፤
ኑሮ ማለት ትወና
የዘወትር ትርዒት
አይበርዴውን እሳት
ለመልመድ ፡ አሊያም ለመርሳት፡፡
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ጣይ እና አንሺ
(በእዉቀቱ ስዩም)
*
ደሞዙን ቢጥል
አንስተዉ ጠጡበት
ባርኔጣዉን ቢጥል
ወስደዉ ደመቁበት
ከዘራዉን ቢጥል
ተመረኮዙበት
በሄደበት ሲያልፉ
በጣለዉ ሲያተርፉ
*
*
ራሱን ሲጥል ግን
አይተዉት አለፉ ።
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
(በእዉቀቱ ስዩም)
*
ደሞዙን ቢጥል
አንስተዉ ጠጡበት
ባርኔጣዉን ቢጥል
ወስደዉ ደመቁበት
ከዘራዉን ቢጥል
ተመረኮዙበት
በሄደበት ሲያልፉ
በጣለዉ ሲያተርፉ
*
*
ራሱን ሲጥል ግን
አይተዉት አለፉ ።
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
©Belay Bekele Weya
ልጄ...
"ሀገር ማለት ሰው ነው " ፣ ያሉህን ተቀበል
ሰው በሞተ ቁጥር ፣ "ሀገሬ ሞተች " በል!
።።።
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ልጄ...
"ሀገር ማለት ሰው ነው " ፣ ያሉህን ተቀበል
ሰው በሞተ ቁጥር ፣ "ሀገሬ ሞተች " በል!
።።።
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
©Yam Dag
"የማይባል"
የሴት ልጅም ፀጉሯ ...
የወንድ ልጅ ጫማው...
ካልገማ ጠረኑ፣
ምኑን ኮረደደች...
ምኑን ጎረመሰ...
ሴትና ወንድ ሆኑ።
@Simetin_Begitim
For ur comment
For ur advice
For ur reccomendation
contact us via our bot
@Simetin_Begitimbot
@Simetin_Begitimbot
@Simetin_Begitimbot
"የማይባል"
የሴት ልጅም ፀጉሯ ...
የወንድ ልጅ ጫማው...
ካልገማ ጠረኑ፣
ምኑን ኮረደደች...
ምኑን ጎረመሰ...
ሴትና ወንድ ሆኑ።
@Simetin_Begitim
For ur comment
For ur advice
For ur reccomendation
contact us via our bot
@Simetin_Begitimbot
@Simetin_Begitimbot
@Simetin_Begitimbot
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
ሀገረ ፀጉር ቤት
××××××××××××
በፀጉር ቤት ስርዓት በፀጉር ቤት ህግ
ሀገር ማለት ሰው ነው ፀጉሩን ’ሚያሳድግ
ብዬ የነገርኩሽ እውነት ነው ፍቅሬ
ላረጋግጥ ብዬ ይሄውልሽ ዛሬ
ፀጉር ቤት ብሄድ ባላደገው ፀጉሬ
ከንፈር መጠጠልኝ እድምተኛው ሁላ
በደሃው ፀጉሬ አንጀቱ ተበላ
ለካስ በፀጉር ቤት ስርዓት
በስልጣን ወንበር ላይ ወጥቶ ለመቀመጥ
ፀጉር ያስፈልጋል ከራስ የሚመለጥ
ሀብተ ፀጉርን ካላደለሽ ጌታ
ጥረሽ ካላፈራሽ የፀጉር ክምርታ
በፀጉር ቤት ሀገር አታገኝም ቦታ
እናም
እንደ ፀጉር ቤት ስርዓት እንደ ፀጉር ቤት ህግ
ሀገር ማለት ሰው ነው ፀጉሩን ’ሚያሳድግ
የሀብቱን ርዝራዥ በማሽን ቀንሶ
ራሱን ሚያሳምር መሬት ላይ አፍሶ
ለድሃው ወገኑ ቅንጣት ’ማይሳሳ
በዙፋን ልብሱ ሌላውን የረሳ
ብዬ የነገርኩሽ እውነት ነው ፍቅሬ
ካላመንሽ ጠይቂው
ይነግርሻል መስታውቱ እሱት ምስክሬ
© ዳንኤል ከበደ
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ሀገረ ፀጉር ቤት
××××××××××××
በፀጉር ቤት ስርዓት በፀጉር ቤት ህግ
ሀገር ማለት ሰው ነው ፀጉሩን ’ሚያሳድግ
ብዬ የነገርኩሽ እውነት ነው ፍቅሬ
ላረጋግጥ ብዬ ይሄውልሽ ዛሬ
ፀጉር ቤት ብሄድ ባላደገው ፀጉሬ
ከንፈር መጠጠልኝ እድምተኛው ሁላ
በደሃው ፀጉሬ አንጀቱ ተበላ
ለካስ በፀጉር ቤት ስርዓት
በስልጣን ወንበር ላይ ወጥቶ ለመቀመጥ
ፀጉር ያስፈልጋል ከራስ የሚመለጥ
ሀብተ ፀጉርን ካላደለሽ ጌታ
ጥረሽ ካላፈራሽ የፀጉር ክምርታ
በፀጉር ቤት ሀገር አታገኝም ቦታ
እናም
እንደ ፀጉር ቤት ስርዓት እንደ ፀጉር ቤት ህግ
ሀገር ማለት ሰው ነው ፀጉሩን ’ሚያሳድግ
የሀብቱን ርዝራዥ በማሽን ቀንሶ
ራሱን ሚያሳምር መሬት ላይ አፍሶ
ለድሃው ወገኑ ቅንጣት ’ማይሳሳ
በዙፋን ልብሱ ሌላውን የረሳ
ብዬ የነገርኩሽ እውነት ነው ፍቅሬ
ካላመንሽ ጠይቂው
ይነግርሻል መስታውቱ እሱት ምስክሬ
© ዳንኤል ከበደ
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
©ግጥም ብቻ
........መፅናኛ ለሰካራምች.......
✍ጌትነት እንየው
በቀን እንግድነት - ከአለም እልፍኝ ገብቶ
ባይተዋር ሲሆኑ የሚመስል ጠፍቶ
ህሊናን ሲሸብብ ፣ የሰው ተንኮል ደርቶ
መንፈስን ሲደፍቅ ፣ የሰው ግፉ ምልቶ
ንፁህ ልብ ሲያፍን ፣ ክፋቱ ከርፍቶ
ሚዛንን ሲስቱ ፣ በቀን ሰው ተገፍቶ
ይሄን ጊዜ ሰውን፦
ባይጠሉትም ፈርቶ
ባይፈሩትም ሰግቶ
ከምላሱ ሸሽቶ
ይህንን የቀን ሰው ፣ ከቀን ጋራ ትቶ
ምሽት ተከናንቦ ፣ መሸታ ቤት ገብቶ
ብርሌ አንደቅድቆ ፣ መለኪያ ለግቶ
ለግቶ ለግቶ
ጨልጦ ጠጥቶ
ቢሰደቡም ሰምቶ
ቢመቱም ተመቶ
ቢገደሉም ሞቶ
ብቻ እርሱ ፈጣሪ፦
"ይቅር" እንዲላቸው ፣ ለማርያም ልጅ ሰቶ
ጥንብዝ ብሎ ሰክሮ ፣ ጨርቅ ሆኖ ቡትቶ
እንደ ህፃን ድሆ ፣ ተማደሪያ ገብቶ
ቢቻል በር ዘግቶ
ካልተቻለም ትቶ
ቀበቶ ሳይፈቱ፦
ጫማ ሳያወልቁ ፣ ታልጋ ተዘርግቶ
ከሞት ከፍ የሚል ፣ እንቅልፍ አንቀላፍቶ
ተ...ኝ...ቶ ተ....ኝ....ቶ
አሁንም ተኝቶ
ሌቱ አልቆ ቀን ሲሆን ፣ ማለዳ ነቅቶ
ማታ በጠጅ ጠርቶ
ማታ በጠጅ ነፅቶ
እራስን ካገኙት
ጠዋት እንደ ክፃን ሁሉንም እረስቶ
ንጡህ ወደኔ ይቅረቡ
ብሎ እንዳላላቸው ጌታ በመዝገቡ
የየዋህነት ገፅ የፍቅር ድርሳኑ
አርጎ እንደፃፋቸው ህፃናት ከሆኑ
ምናለ ቢጠጡ
ምናለ ቢሰክሩ
በቀን ያደፈትን በምሽት ካጠሩ
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
........መፅናኛ ለሰካራምች.......
✍ጌትነት እንየው
በቀን እንግድነት - ከአለም እልፍኝ ገብቶ
ባይተዋር ሲሆኑ የሚመስል ጠፍቶ
ህሊናን ሲሸብብ ፣ የሰው ተንኮል ደርቶ
መንፈስን ሲደፍቅ ፣ የሰው ግፉ ምልቶ
ንፁህ ልብ ሲያፍን ፣ ክፋቱ ከርፍቶ
ሚዛንን ሲስቱ ፣ በቀን ሰው ተገፍቶ
ይሄን ጊዜ ሰውን፦
ባይጠሉትም ፈርቶ
ባይፈሩትም ሰግቶ
ከምላሱ ሸሽቶ
ይህንን የቀን ሰው ፣ ከቀን ጋራ ትቶ
ምሽት ተከናንቦ ፣ መሸታ ቤት ገብቶ
ብርሌ አንደቅድቆ ፣ መለኪያ ለግቶ
ለግቶ ለግቶ
ጨልጦ ጠጥቶ
ቢሰደቡም ሰምቶ
ቢመቱም ተመቶ
ቢገደሉም ሞቶ
ብቻ እርሱ ፈጣሪ፦
"ይቅር" እንዲላቸው ፣ ለማርያም ልጅ ሰቶ
ጥንብዝ ብሎ ሰክሮ ፣ ጨርቅ ሆኖ ቡትቶ
እንደ ህፃን ድሆ ፣ ተማደሪያ ገብቶ
ቢቻል በር ዘግቶ
ካልተቻለም ትቶ
ቀበቶ ሳይፈቱ፦
ጫማ ሳያወልቁ ፣ ታልጋ ተዘርግቶ
ከሞት ከፍ የሚል ፣ እንቅልፍ አንቀላፍቶ
ተ...ኝ...ቶ ተ....ኝ....ቶ
አሁንም ተኝቶ
ሌቱ አልቆ ቀን ሲሆን ፣ ማለዳ ነቅቶ
ማታ በጠጅ ጠርቶ
ማታ በጠጅ ነፅቶ
እራስን ካገኙት
ጠዋት እንደ ክፃን ሁሉንም እረስቶ
ንጡህ ወደኔ ይቅረቡ
ብሎ እንዳላላቸው ጌታ በመዝገቡ
የየዋህነት ገፅ የፍቅር ድርሳኑ
አርጎ እንደፃፋቸው ህፃናት ከሆኑ
ምናለ ቢጠጡ
ምናለ ቢሰክሩ
በቀን ያደፈትን በምሽት ካጠሩ
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ስሜትን በግጥም + ትምህርታዊ አጫጫጭር ታሪኮች ♥♥♥:
😳እኔ እና ሲቄ😳
በህንፃ ለይ ህንጻ
ወደ ላይ ደርድሬ
መኪና በመኪና
አንዱን ከአንዱ ቀያይሬ
ቀዳዳ ቡቱቶዬን
ካለዬ ወርውሬ
በተድላ በምቾት
ስኖር ተንቀባርሬ
ምቾት አሰቃይቶኝ
ያለ ቅጥ ወፍሬ
በውስኪ ፣ በውድ አረቄ
እራሴን እስክስት ሰክሬ
ያለ ቅጥ ስቸር
ገንዘቤን መንዝሬ
በችሮታ ብዛት
ከእንቅልፌ ስባንን
እራሴን አገኘውት
በሲቄ ሰመመን
ከዱካዬ ተጣብቄ
በሀሳብ ስኳትን፡፡
ሀይለመለኮት:ተ
😄😄😄😄😄
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
😳እኔ እና ሲቄ😳
በህንፃ ለይ ህንጻ
ወደ ላይ ደርድሬ
መኪና በመኪና
አንዱን ከአንዱ ቀያይሬ
ቀዳዳ ቡቱቶዬን
ካለዬ ወርውሬ
በተድላ በምቾት
ስኖር ተንቀባርሬ
ምቾት አሰቃይቶኝ
ያለ ቅጥ ወፍሬ
በውስኪ ፣ በውድ አረቄ
እራሴን እስክስት ሰክሬ
ያለ ቅጥ ስቸር
ገንዘቤን መንዝሬ
በችሮታ ብዛት
ከእንቅልፌ ስባንን
እራሴን አገኘውት
በሲቄ ሰመመን
ከዱካዬ ተጣብቄ
በሀሳብ ስኳትን፡፡
ሀይለመለኮት:ተ
😄😄😄😄😄
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
500 ሞልተናል እናመሠግናለን ገና ሺዎች ሆነን ኢትዮጵያዊነትን እንሠብካለን፡፡ ኢትዮጵያዊነት ይለምልም ፡፡
@Simetin_Begitimን ለወዳጅዎ 1Second ከጊዜዎት ወስደው ያጋሩ፡፡
እናመሠግናለን
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹Ethiopiaan🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@Simetin_Begitimን ለወዳጅዎ 1Second ከጊዜዎት ወስደው ያጋሩ፡፡
እናመሠግናለን
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹Ethiopiaan🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አገባሽ ነበረ
------
የቁመቴን ማጠር የመልኬን ማስከፋት
ከጉዳይ ባትቆጥሪው የገፄን ደምግባት
ኮልታፋ አንደበቴን ሸካራውን ድምፄን
ሰምተሸ ባትንቂያቸው ለዛ አልባ ቃላቴን፣
ፍፁም ድህነቴን አምነሽ ብትቀበይ
ፍቅርን ብታስበልጭ ከዚች ምድር ሲሳይ፤
አገባሽ ነበረ እሽ ብትይ አንቺ
በተለይ በተለይ ባልሽን ብትፈቺ፡፡
source :-YBnews fb page
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
------
የቁመቴን ማጠር የመልኬን ማስከፋት
ከጉዳይ ባትቆጥሪው የገፄን ደምግባት
ኮልታፋ አንደበቴን ሸካራውን ድምፄን
ሰምተሸ ባትንቂያቸው ለዛ አልባ ቃላቴን፣
ፍፁም ድህነቴን አምነሽ ብትቀበይ
ፍቅርን ብታስበልጭ ከዚች ምድር ሲሳይ፤
አገባሽ ነበረ እሽ ብትይ አንቺ
በተለይ በተለይ ባልሽን ብትፈቺ፡፡
source :-YBnews fb page
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
😂😂😂😂😂😂😂😂
እንሂድ እንሂድ በጫካ አያ ጅቦ ሳይመጣ
ጅቦ(ኦ) አለህ?!
አውው
ምን ትሰራለህ?
ከታላቋ እንግላጣን የስጋ መቁረጫ ትልቅ ቢላ እየሳልኩ አውው
እንዴ ጅቦ ጥርስህ አልበቃ ብሎህ ስጋ በቢላ ልትበላ?
አውው አውው ልኳንዳ ቤቱ በዝቶ 80 ምናምን ቢሞላ ጥርሴን
ከማደክመው አስፈለገኝ ቢላ አውውው ውው
እንሂድ እንሂድ በጫካ አያ ጅቦ ሳይመጣ ጅቦ አ ለህ?!
አውውው
ምን ትሰራለህ?
ከጥንታዊ ምድር ምሰር አለኝ ወዳጅ
ልኳንዳ ለመስራት ከኔ የሚወዳጅ
"እን .... ዴ ጅቦ ተካፍለህ ልተበላ?"
አውው ውው ስጋን ቢመትሩት በአይነት በፈርጅ
ምን ያደርጋል ማስጎምጀት ለተራበ ወዳጅ?
እንሂድ እንሂድ በጫካ አያ ጅቦ ሳይ መጣ
አያ ጅቦ አለህ? አ*** ው
ምን ትሰራለህ? እና*** ንተን ልበላ
ሀሀሀሀ አአአ አያ ጅቦ መጣ አ ሀሀ
.....
ሀም!!! አው ውው
እንዴ ጅቦ የምር ነው እንዴ?
እ***እም አውውውውው ። 14/02/11 መአለም
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
እንሂድ እንሂድ በጫካ አያ ጅቦ ሳይመጣ
ጅቦ(ኦ) አለህ?!
አውው
ምን ትሰራለህ?
ከታላቋ እንግላጣን የስጋ መቁረጫ ትልቅ ቢላ እየሳልኩ አውው
እንዴ ጅቦ ጥርስህ አልበቃ ብሎህ ስጋ በቢላ ልትበላ?
አውው አውው ልኳንዳ ቤቱ በዝቶ 80 ምናምን ቢሞላ ጥርሴን
ከማደክመው አስፈለገኝ ቢላ አውውው ውው
እንሂድ እንሂድ በጫካ አያ ጅቦ ሳይመጣ ጅቦ አ ለህ?!
አውውው
ምን ትሰራለህ?
ከጥንታዊ ምድር ምሰር አለኝ ወዳጅ
ልኳንዳ ለመስራት ከኔ የሚወዳጅ
"እን .... ዴ ጅቦ ተካፍለህ ልተበላ?"
አውው ውው ስጋን ቢመትሩት በአይነት በፈርጅ
ምን ያደርጋል ማስጎምጀት ለተራበ ወዳጅ?
እንሂድ እንሂድ በጫካ አያ ጅቦ ሳይ መጣ
አያ ጅቦ አለህ? አ*** ው
ምን ትሰራለህ? እና*** ንተን ልበላ
ሀሀሀሀ አአአ አያ ጅቦ መጣ አ ሀሀ
.....
ሀም!!! አው ውው
እንዴ ጅቦ የምር ነው እንዴ?
እ***እም አውውውውው ። 14/02/11 መአለም
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
©ግጥም ብቻ
ሎሬት ፀጋየ ገብረ መድህን
ቆንጆ ግጥም...
.
ልደት በኛ መንደር
====////=======
ባደግንበት ቀዬ፣ በኖርንበት መንደር
እንኳን ኬክ ተቆርሶ፣
ድግስ ተደግሶ፣
ሻማ ተለኩሶ፣
ልዩ ልብስ ተለብሶ፣
"መልካም ልደት" በሚል አንድ ሺ ሙዚቃ
የልደት ቀን ደምቃ
እንኳን ልትከበር
ከና'ካቴው ቀኗስ መች ትታወቅ ነበር፡፡
.
አሁን የኔ ልደት፣ የተወለድሁበት፣
መቸ እንደነበረ፣ እናቴ ዘንድ ሂደን፣ ንገሪን ብንላት
.
“መንግስቱ ኃይለ ማርያም መንደራችን መጥቶ
በጎበኘ ማግስት
ነበር የወለድሁት፡፡
ይሰማኝ ነበረ፣ የወታደር ሆታ
የተማሪ ጩኸት፣ ያይሴማ እልልታ
ምጥ የያዘኝ ሌሊት፣ ምጥ የያዘኝ ማታ፡፡
ታዲያ በዚህ መሃል፣ ኢሃፓ ተኩስ ከፍታ
የአቶ አበበን ድርቆሽ፣ ባብሪ ጥይት መትታ
የመስቀል ደመራ፣ ሲመስል መንደሩ
ወንዱ ተኩስ ሲገጥም፣ በየ ጉራንጉሩ
ነበር የወለድሁት፡፡
.
በዚያ ጭንቅ ጨለማ
የአካሌን ክፋይ
ጨቅላውን ታቅፋ፣ አዋላጇ ቁማ
'‘ተነሽ መዓት መጥቷል፣ እንውጣ ከዚህ ቤት
ካ'ዲሱ ፍጡር ጋር፣ እንዳይበላን እሳት’'
ስትለኝ ብነሳ፣ ወገቤን አስሬ
በነበልባል እሳት፣ ጠፍታለች መንደሬ
የምጤን ሁኔታ
ያችን የ’ሳት ማታ
ዘወትር እንዲኖር ልቤ እያስታወሰ
የወለድሁትን ልጅ አልሁት እሳቱ ሰ”
ነው ምትል፡፡
እና...
ባደግንበት ቀዬ፣ በኖርንበት መንደር
የልደታችን ቀን፣ እንኳን ልትከበር
ከናካቴው ቀኗስ መች ትታወቅ ነበር፡፡
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ሎሬት ፀጋየ ገብረ መድህን
ቆንጆ ግጥም...
.
ልደት በኛ መንደር
====////=======
ባደግንበት ቀዬ፣ በኖርንበት መንደር
እንኳን ኬክ ተቆርሶ፣
ድግስ ተደግሶ፣
ሻማ ተለኩሶ፣
ልዩ ልብስ ተለብሶ፣
"መልካም ልደት" በሚል አንድ ሺ ሙዚቃ
የልደት ቀን ደምቃ
እንኳን ልትከበር
ከና'ካቴው ቀኗስ መች ትታወቅ ነበር፡፡
.
አሁን የኔ ልደት፣ የተወለድሁበት፣
መቸ እንደነበረ፣ እናቴ ዘንድ ሂደን፣ ንገሪን ብንላት
.
“መንግስቱ ኃይለ ማርያም መንደራችን መጥቶ
በጎበኘ ማግስት
ነበር የወለድሁት፡፡
ይሰማኝ ነበረ፣ የወታደር ሆታ
የተማሪ ጩኸት፣ ያይሴማ እልልታ
ምጥ የያዘኝ ሌሊት፣ ምጥ የያዘኝ ማታ፡፡
ታዲያ በዚህ መሃል፣ ኢሃፓ ተኩስ ከፍታ
የአቶ አበበን ድርቆሽ፣ ባብሪ ጥይት መትታ
የመስቀል ደመራ፣ ሲመስል መንደሩ
ወንዱ ተኩስ ሲገጥም፣ በየ ጉራንጉሩ
ነበር የወለድሁት፡፡
.
በዚያ ጭንቅ ጨለማ
የአካሌን ክፋይ
ጨቅላውን ታቅፋ፣ አዋላጇ ቁማ
'‘ተነሽ መዓት መጥቷል፣ እንውጣ ከዚህ ቤት
ካ'ዲሱ ፍጡር ጋር፣ እንዳይበላን እሳት’'
ስትለኝ ብነሳ፣ ወገቤን አስሬ
በነበልባል እሳት፣ ጠፍታለች መንደሬ
የምጤን ሁኔታ
ያችን የ’ሳት ማታ
ዘወትር እንዲኖር ልቤ እያስታወሰ
የወለድሁትን ልጅ አልሁት እሳቱ ሰ”
ነው ምትል፡፡
እና...
ባደግንበት ቀዬ፣ በኖርንበት መንደር
የልደታችን ቀን፣ እንኳን ልትከበር
ከናካቴው ቀኗስ መች ትታወቅ ነበር፡፡
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
የምን ገዜውም ጠቃሚ መልእክት ሳይነበብ እና share ሳይደረግ እንዳይታለፍ
👍👍👍👍🙏🙏🙏👍👍👍👍
Mesge D🇪🇹:
የህይወት ጎበዝ ሁን!
(Samuel Geda )
ከክፍል አንደኛ መውጣትህ፣ ሰቃይ ተማሪ መሆንህ፣ በማዕረግ መጨረስህ- በህይወትህ ስኬታማ እንድትሆን ዋስትና ይሆንሃል ማለት አይደለም።
በኢኮኖሚክስ በማዕረግ ልትመረቅ ትችል ይሆናል፣ ይሁንና ከሁሉ የተሻለ ገቢ ታገኛለህ ማለት አይደለም። ጎበዝ የህግ ተማሪ ነበርክ ማለት ጎበዝ ጠበቃ ትሆናለህ ማለትም አይደለም። ይሀውልህ፤ ህይወት- ፅንሰ ሃሳብን (concept) ከመረዳት፣ ነገሮችን ከማስታወስ (Memoriase ize)ና፣ ፈተና ላይ ከመተግበር (reproduce) በላይ አቅም ትፈልጋለች።
• ትምህርት ቤቶች፣ ሰዎችን 'ለማስታወስ ችሎታቸው' ዕውቅና ሲሰጡ፤ ህይወት ግን፣ ሰዎችን 'ለተግባራቸው' ዕውቅና ትሰጣለች።
• ትምህርት ቤቶች ማስጠንቀቂያ (caution) ሲሰጡ፤ ህይወት ግን ድፍረትን ትሰጣለች።
• ትምህርት ቤቶች በ"ደንብ" የሚኖሩትን ሲያመሰግኑ፤ ህይወት ግን ደንብን ጥሰው፣ አዲስ ህግን ያስቀመጡትን ታወድሳለች።
ታዲያ ሰዎች በትምህርት ቤት ጠንክረው መማር የለባቸውም እያልኩ ነው?- በፍፁም። መማርህ የግድ ነው። ይሁንና "አንደኛ" ለመውጣት ብለህ ሌሎች ነገሮችን ሁሉ መስዋእት አታድርግ እያልኩህ ነው።
ያንተ ጉብዝና በ10ኛ ክፍል ውጤት አዘለለህ፣ በ12ኛ ክፍል ውጤት አስፈነደቀህ፣ በከፍተኛ ትምህርት ውጤትህ አስወደሰህ...ከዛስ? - ከዛማ ቅጥረኛ ሆነሃል። የወር ደሞዝ ትጠብቃለህ፣ ፍቃድህ በአለቃህ (ሰቃይ ተማሪ ባልነበረው) ላይ ወድቋል።
ትላንት ግብረገብ ላይ ጥሩ ሆኖ በሌላ ዘርፍ ግን ደክሞ የናቅከው ተማሪ፣ ዛሬ የሞራል አለቃህ (የሃይማኖት ሰው) ሆኖ ይመራሃል፤
ትላንት ስነ-ዜጋ ላይ በርትቶ በሌላው ግን ደክሞ የተቸኸው ተማሪ፣ ዛሬ ባለስልጣን ሆኖ አጠገቡ ለመድረስ የምትናፍቀው ሰው ሆኗል፤
ትላንት ስእልና ሙዚቃ ላይ ጊዜውን እያጠፋ በሌላው ግን ስለደከመ የናቅከው ተማሪ፣ ዛሬ የምታደንቀው አርቲስት ነው፤
ትላንት ሽቦ ሲወጥር፣ እንጨት ሲቆርጥ- ከነጓደኞችህ ያሾፍክበት ተማሪ፣ ዛሬ እርሱ ጋር ለመቀጠር በብርቱ የምትፈልገው የትልቅ ኢንዱስትሪ ባለቤት ሆኗል።
የትምህርቱ ጎበዝ በህይወት ጎበዞች ተበልጠሃል። ዛሬ ላይ ቆመህ የነርሱን ህይወት ትናፍቃለህ። ደስታህ በደስታቸው፣ ሀዘንህ በሀዘናቸው ላይ ተመሥርቷል።
አሁንም ግን ጊዜው አልረፈደም። እስትንፋስህ እስካለች ህይወት ትቀጥላለች። ራስህን በክፍል አትገድበው፤ በምግባርህ ጎልተህ ውጣ፤ የመሪነቱንም ድርሻ ውሰድ።
እስቲ የንግድ ሥራ ጀምርና አይሳካልህ፣ ብዙ አማራጮችን ትቀስምበታለህ። ለምርጫ ተወዳደርና ተሸነፍ፣ የፓለቲካ ሳይንቲስት የማያስተምርህን ነገር ያስተምርሃል። ውስጥህ ያለውን ተሰጥኦ አውጣውና ይታይ፣ አጎልብተውም፤ በሙያህ ዘርፍ ብቻ ሳትገደብ መፅሐፍትን አንብብ፣ ያመንክበትን ነገርም አድርግ። በቃ! ጎበዝ ተማሪ ለመሆን ከማሰብ ይልቅ፣ ጎበዝ ሰው ለመሆን አስብ። ትምህርት ቤትህን አለምህ አታድርገው፣ አለምህን ትምህርት ቤትህ እንጂ!።
ወደፊት ተራመድ፤
ፓለቲካውን ሞክር፤
ኪነጥበቡን ሞክር፤
ግብርናውን ሞክር፤
ንግዱን ሞክር፤
በቃ ተጨማሪና አዲስ ነገር ሞክር!!
ልብ በል፤ ፈጣሪም የሚረዳው የሚሞክሩትን ነው። ከሰማይ ይልቅ በምድር ያስቀመጠህም በአላማ ነው። የምትበርበት ክንፍ ያልሰጠህ አውሮፕላን ሰርተህ እንድትበር፣ ተሽከርካሪ እግር ያላደለህ መኪና ሰርተህ እንድትሽከረከር ነው። ከርሱ ዘንድ፣ በየቀኑ የሚሰጥህን ዕድል ያለመሰሰት ተጠቀምበትና የህይወት ጎበዝ ሁን!
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
👍👍👍👍🙏🙏🙏👍👍👍👍
Mesge D🇪🇹:
የህይወት ጎበዝ ሁን!
(Samuel Geda )
ከክፍል አንደኛ መውጣትህ፣ ሰቃይ ተማሪ መሆንህ፣ በማዕረግ መጨረስህ- በህይወትህ ስኬታማ እንድትሆን ዋስትና ይሆንሃል ማለት አይደለም።
በኢኮኖሚክስ በማዕረግ ልትመረቅ ትችል ይሆናል፣ ይሁንና ከሁሉ የተሻለ ገቢ ታገኛለህ ማለት አይደለም። ጎበዝ የህግ ተማሪ ነበርክ ማለት ጎበዝ ጠበቃ ትሆናለህ ማለትም አይደለም። ይሀውልህ፤ ህይወት- ፅንሰ ሃሳብን (concept) ከመረዳት፣ ነገሮችን ከማስታወስ (Memoriase ize)ና፣ ፈተና ላይ ከመተግበር (reproduce) በላይ አቅም ትፈልጋለች።
• ትምህርት ቤቶች፣ ሰዎችን 'ለማስታወስ ችሎታቸው' ዕውቅና ሲሰጡ፤ ህይወት ግን፣ ሰዎችን 'ለተግባራቸው' ዕውቅና ትሰጣለች።
• ትምህርት ቤቶች ማስጠንቀቂያ (caution) ሲሰጡ፤ ህይወት ግን ድፍረትን ትሰጣለች።
• ትምህርት ቤቶች በ"ደንብ" የሚኖሩትን ሲያመሰግኑ፤ ህይወት ግን ደንብን ጥሰው፣ አዲስ ህግን ያስቀመጡትን ታወድሳለች።
ታዲያ ሰዎች በትምህርት ቤት ጠንክረው መማር የለባቸውም እያልኩ ነው?- በፍፁም። መማርህ የግድ ነው። ይሁንና "አንደኛ" ለመውጣት ብለህ ሌሎች ነገሮችን ሁሉ መስዋእት አታድርግ እያልኩህ ነው።
ያንተ ጉብዝና በ10ኛ ክፍል ውጤት አዘለለህ፣ በ12ኛ ክፍል ውጤት አስፈነደቀህ፣ በከፍተኛ ትምህርት ውጤትህ አስወደሰህ...ከዛስ? - ከዛማ ቅጥረኛ ሆነሃል። የወር ደሞዝ ትጠብቃለህ፣ ፍቃድህ በአለቃህ (ሰቃይ ተማሪ ባልነበረው) ላይ ወድቋል።
ትላንት ግብረገብ ላይ ጥሩ ሆኖ በሌላ ዘርፍ ግን ደክሞ የናቅከው ተማሪ፣ ዛሬ የሞራል አለቃህ (የሃይማኖት ሰው) ሆኖ ይመራሃል፤
ትላንት ስነ-ዜጋ ላይ በርትቶ በሌላው ግን ደክሞ የተቸኸው ተማሪ፣ ዛሬ ባለስልጣን ሆኖ አጠገቡ ለመድረስ የምትናፍቀው ሰው ሆኗል፤
ትላንት ስእልና ሙዚቃ ላይ ጊዜውን እያጠፋ በሌላው ግን ስለደከመ የናቅከው ተማሪ፣ ዛሬ የምታደንቀው አርቲስት ነው፤
ትላንት ሽቦ ሲወጥር፣ እንጨት ሲቆርጥ- ከነጓደኞችህ ያሾፍክበት ተማሪ፣ ዛሬ እርሱ ጋር ለመቀጠር በብርቱ የምትፈልገው የትልቅ ኢንዱስትሪ ባለቤት ሆኗል።
የትምህርቱ ጎበዝ በህይወት ጎበዞች ተበልጠሃል። ዛሬ ላይ ቆመህ የነርሱን ህይወት ትናፍቃለህ። ደስታህ በደስታቸው፣ ሀዘንህ በሀዘናቸው ላይ ተመሥርቷል።
አሁንም ግን ጊዜው አልረፈደም። እስትንፋስህ እስካለች ህይወት ትቀጥላለች። ራስህን በክፍል አትገድበው፤ በምግባርህ ጎልተህ ውጣ፤ የመሪነቱንም ድርሻ ውሰድ።
እስቲ የንግድ ሥራ ጀምርና አይሳካልህ፣ ብዙ አማራጮችን ትቀስምበታለህ። ለምርጫ ተወዳደርና ተሸነፍ፣ የፓለቲካ ሳይንቲስት የማያስተምርህን ነገር ያስተምርሃል። ውስጥህ ያለውን ተሰጥኦ አውጣውና ይታይ፣ አጎልብተውም፤ በሙያህ ዘርፍ ብቻ ሳትገደብ መፅሐፍትን አንብብ፣ ያመንክበትን ነገርም አድርግ። በቃ! ጎበዝ ተማሪ ለመሆን ከማሰብ ይልቅ፣ ጎበዝ ሰው ለመሆን አስብ። ትምህርት ቤትህን አለምህ አታድርገው፣ አለምህን ትምህርት ቤትህ እንጂ!።
ወደፊት ተራመድ፤
ፓለቲካውን ሞክር፤
ኪነጥበቡን ሞክር፤
ግብርናውን ሞክር፤
ንግዱን ሞክር፤
በቃ ተጨማሪና አዲስ ነገር ሞክር!!
ልብ በል፤ ፈጣሪም የሚረዳው የሚሞክሩትን ነው። ከሰማይ ይልቅ በምድር ያስቀመጠህም በአላማ ነው። የምትበርበት ክንፍ ያልሰጠህ አውሮፕላን ሰርተህ እንድትበር፣ ተሽከርካሪ እግር ያላደለህ መኪና ሰርተህ እንድትሽከረከር ነው። ከርሱ ዘንድ፣ በየቀኑ የሚሰጥህን ዕድል ያለመሰሰት ተጠቀምበትና የህይወት ጎበዝ ሁን!
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
©ግጥም ብቻ
#ጠብቄሽ_ነበረ
➖➖➖
ደበበ_ሰይፉ
መንፈሴን አፅንቼ
ገላዬን አጥርቼ
አበባ አሳብቤ
አዱኛ ሰብስቤ
ጠብቄሽ ነበረ ፤
ብትቀሪ ግዜ ፤
መንፈሴን አሳደፍኩ
ገላዬን አጎደፍኩ
አበባው ደረቀ
አዱኛው አለቀ ፤
ብትቀሪ ጊዜ ፤
የጣልኩብሽ ተስፋ
እኔን ይዞ ጠፋ። 😓
1962
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
#ጠብቄሽ_ነበረ
➖➖➖
ደበበ_ሰይፉ
መንፈሴን አፅንቼ
ገላዬን አጥርቼ
አበባ አሳብቤ
አዱኛ ሰብስቤ
ጠብቄሽ ነበረ ፤
ብትቀሪ ግዜ ፤
መንፈሴን አሳደፍኩ
ገላዬን አጎደፍኩ
አበባው ደረቀ
አዱኛው አለቀ ፤
ብትቀሪ ጊዜ ፤
የጣልኩብሽ ተስፋ
እኔን ይዞ ጠፋ። 😓
1962
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ጠቃሚ መልክት
👍👍👍👍👍👍
©Hussen say's
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ሁለት የሚዋደዱ ጓደኛሞች ጉዞ ላይ ሳሉ አንደኛው ያማረ ቪላ ቤቶችን ያይና ለጓደኛው እንዲህ አለው።
«ፈጣሪ ይህን ሁሉ ሀብት ለእነዚህ ሰዎች ሲያድል እኛ የት ነበርን?»
ጓደኛውም አጠገቡ ነበረና ና ብሎ ወደ ሆስፒታል ይዞት ሔዶ እንዲህ አለው።
«ለእነዚህ ሰዎች ሁሉ ፈጣሪ በሽታን ሲያድል እኛ የት ነበርን?»
"ያለንን ብናውቅ የጎደለን የለም!!"
"ምንግዜም ባለን ነገር እናመሥግን።"
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
👍👍👍👍👍👍
©Hussen say's
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ሁለት የሚዋደዱ ጓደኛሞች ጉዞ ላይ ሳሉ አንደኛው ያማረ ቪላ ቤቶችን ያይና ለጓደኛው እንዲህ አለው።
«ፈጣሪ ይህን ሁሉ ሀብት ለእነዚህ ሰዎች ሲያድል እኛ የት ነበርን?»
ጓደኛውም አጠገቡ ነበረና ና ብሎ ወደ ሆስፒታል ይዞት ሔዶ እንዲህ አለው።
«ለእነዚህ ሰዎች ሁሉ ፈጣሪ በሽታን ሲያድል እኛ የት ነበርን?»
"ያለንን ብናውቅ የጎደለን የለም!!"
"ምንግዜም ባለን ነገር እናመሥግን።"
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
©ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
አትሄድም ብዬ
አትሄድም ብዬ፣
ጎጆዬን ላሰፋ፣
ግርግዳ ስገፋ፣
ጥሪት ላጠራቅም፣
ጥሬ ስቆረጥም፣
አትሄድም ብዬ፣
የብቻ ጎጆዬን፣ሰው ልመጂ ስላት፣
ቡናው ሳያከትም፣
ካፊያው ሳያባራ፣
•••••••ከአጠገቤ አጣኋት።
በል ተከተል ልቤ ••
ማግኘት ነበር ጣሩ፣ማጣት መች ይደንቃል፣
እንኳን በጅ ያልያዙት፣ጥሬ ካፍ ይወድቃል።
✍በድሉ ዋቅጅራ
🙏ህዳር 2008 ዓ·ም አድስ አበባ
👆የወይራ ስር ፀሎት👆
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
አትሄድም ብዬ
አትሄድም ብዬ፣
ጎጆዬን ላሰፋ፣
ግርግዳ ስገፋ፣
ጥሪት ላጠራቅም፣
ጥሬ ስቆረጥም፣
አትሄድም ብዬ፣
የብቻ ጎጆዬን፣ሰው ልመጂ ስላት፣
ቡናው ሳያከትም፣
ካፊያው ሳያባራ፣
•••••••ከአጠገቤ አጣኋት።
በል ተከተል ልቤ ••
ማግኘት ነበር ጣሩ፣ማጣት መች ይደንቃል፣
እንኳን በጅ ያልያዙት፣ጥሬ ካፍ ይወድቃል።
✍በድሉ ዋቅጅራ
🙏ህዳር 2008 ዓ·ም አድስ አበባ
👆የወይራ ስር ፀሎት👆
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim