መስለውኝ ነበረ
የበቁ የነቁ
ያዉም የረቀቁ
የሰው ፍጡሮች
ለካ እነሱ ናቸው
ጥሬ ጨው .... ጥሬ ጨው
ጥሬ ጨዋዎች
መፈጨት...መሰለቅ..መደለዝ..መወቀጥ...መታሸት...መቀየጥ
ገና ሚቀራቸው
እኔ የለሁበትም!>
ዘወትር ቋንቋቸዉ፡፡
(( ደበበ ሰይፉ ))
@Simetin_Begitim
የበቁ የነቁ
ያዉም የረቀቁ
የሰው ፍጡሮች
ለካ እነሱ ናቸው
ጥሬ ጨው .... ጥሬ ጨው
ጥሬ ጨዋዎች
መፈጨት...መሰለቅ..መደለዝ..መወቀጥ...መታሸት...መቀየጥ
ገና ሚቀራቸው
እኔ የለሁበትም!>
ዘወትር ቋንቋቸዉ፡፡
(( ደበበ ሰይፉ ))
@Simetin_Begitim
ወዳጄ ስማኝ ፤ አንቺንም ይመለከታል!
👍❤️👍❤️👍❤️👍❤️👍❤️👍
ህይወት 3 ቀን ናት... "ትላንት" ፣ "ዛሬ"፣ "ነገ"
#ከትናንት ተማር #ዛሬን ኑር #ነገን አቅድ
መልካም እሁድ ይሁንላችሁ ይሁንልን
@Simetin_Begitim
👍❤️👍❤️👍❤️👍❤️👍❤️👍
ህይወት 3 ቀን ናት... "ትላንት" ፣ "ዛሬ"፣ "ነገ"
#ከትናንት ተማር #ዛሬን ኑር #ነገን አቅድ
መልካም እሁድ ይሁንላችሁ ይሁንልን
@Simetin_Begitim
ለጊዜ ተዋቸው!
(Samuel Geda)
በአንድ ትንሽ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው ነበር። ታዲያ ይህ
ሰው፣ በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በኑሮው ከሚገጥመው ችግር
የተነሳ፣ ሁልጊዜም በህይወቱ ደስተኛ አልነበረም። አንድ ቀን ግን
ከሚኖርበት ሥፍራ በቅርብ ርቀት የምትገኝ ከተማ ዘንድ፣ አንድ ታላቅ
የኃይማኖት አባት ከአጃቢዎቻቸው ጋር እንደመጡ ይሰማል። ይህን
ጊዜም እኚህን አባት ማግኘት አለብኝ ብሎ ይወስናል።
በመሸም ጊዜ እኚህ አባት ያሉበት ሥፍራ ይደርስና፡ እሳቸውን
ለማግኘት ቁጭ ብሎ መጠባበቁን ይይዛል። ከረጅም ቆይታ በኋላም
እኒያን አባት ያገኝና ጥያቄውን ይጀምራል። "አባቴ ሆይ፥ በህይወቴ
ፍፁም ደስተኛ አይደለሁም፤ በቃ ሁሌም በችግር የተከበብኩኝ ሰው
ነኝ... በዚህ በኩል የሥራ ጭንቀት፣ በዚህ ደግሞ የጤና ቀውስ፣
በዛላይ የቤቴ ውስጥ ችግር... ብቻ ተደማምሮ እረፍት ነስቶኛል፣
ደስታም ርቆኛል፤ እባክዎትን አንዳች የመፍትሄ ሀሳብ ይስጡኝና፡
ደስተኛና የሰላም ኑሮ እንድኖር ይርዱኝ!"
ሽማግሌውም ፈገግ ብለው፤ "ልጄ፥ ለችግርህ ነገ ጠዋት ላይ መፍትሄ
እሰጥሃለሁ፤ ነገር ግን አሁን ባዝህ፣ ጥቂት የኔን ሥራ ልትሠራልኝ
ትችላለህን?፤ ሰውዬውም በዚህ ይስማማል። እሳቸውም ቀጥለው፦
"በጉዞአችን የያዝናቸው መቶ ግመሎች በዚህ ይገኛሉ፤ እናም ዛሬ
ምሽት የነርሱን ነገር፡ አደራውን ላንተ ሰጥቻለሁ፤ ሁሉንም ግመሎች
እመሬት ላይ ካስቀመጥክ በኋላ ወደ መኝታ መሄድ ትችላለህ"።
ይህንንም ብለው ወደ ድንኳናቸው ሲያቀኑ፣ ሰውዬውም የታዘዘውን
ሊያደርግ ምሽቱን ግመሎቹ ዘንድ አመራ።
በቀጣይ ቀንም ሽማግሌው ማልደው ወደ ሰውዬው በማቅናት "ልጄ፥
ሌሊቱን ጥሩ ተኝተህ አደርክ?" ብለው ይጠይቁታል። ሰውዬው ግን
ኅዘን በተሞላበት ስሜት ሆኖ "አባቴ፥ ለዐፍታ እንኳን እንቅልፍ
ሳይወስደኝ ነው ሌሊቱ የነጋው። ብዙ ለፋሁ፣ ብዙም ጣርኩኝ፡ ይሁንና
በአንድ ጊዜ ሁሉንም ግመሎች እንዲቀመጡ ማድረግ አልቻልኩም።
አንዳንዶቹ ራሳቸው ይቀመጣሉ፤ አንዳንዶቹ ግን ላስቀምጣቸው
ብሞክርም እንኳን አይቀመጡም፤ አንዱ በዚህ በኩል ሲቀመጥ፡ በሌላ
በኩል ያሉት ይነሣሉ"።
ይህን ጊዜ ሽማግሌው ፈገግ እያሉ እንዲህ አሉ፦ "ካልተሳሳትኩኝ፡ ይህ
የሆነው ትላንት ማታ ነው አይደል?"
- ራሳቸውን በራሳቸው ያስቀመጡ ብዙ ግመሎች ነበሩ!?
- ብዙዎቹ ደግሞ በአንተ ጥረት ሊቀመጡ ችለዋል!?
- ቀሪዎቹ ልታስቀምጣቸው ሞክረህ እንኳን አልተቀመጡም፤ ከቆይታ
በኋላ ግን በጊዜ ውስጥ ራሳቸውን አስቀምጠው አግኝተሃቸዋል!?
ሰውዬውም፦ "አዎ! አዎ!...ትክክል!" ብሎ መለሰ።
ሽማግሌውም ቀጠሉና፦ "ስለዚህ አሁን አንድ ነገር ተረዳህን?፤
በህይወት ያሉም ችግሮች እንዲሁ ናቸው...
- አንዳንዶቹ በራሳቸው መፍትሄ ያገኛሉ።
- አንዳንዶቹ በአንተ ጥረት መፍትሄ ያገኛሉ።
- አንዳንዶቹ ደግሞ በአንተ ጥረት እንኳን አይፈቱም፤ እነዚህን ችግሮች
ለጊዜ ተዋቸው። ትክክለኛው ጊዜ ሲደርስ በራሳቸው ይፈታሉና/
መፍትሄ ያገኛሉና/።
ትላንት ማታ፣ ምን ያህል ብትሞክር በአንድ ጊዜ ሁሉንም ግመሎች
ማስቀመጥ እንዳልቻልክ ትምህርት ወስደሃል። አንዱን ግመል በዚህ
ጋር ስታስቀምጥ በሌላ በኩል ያሉት ይነሣሉ። ልክ እንዲሁ፤ እዚህ ጋር
አንዱን ችግር ፈታሁ/ተፈታ ስትል እዛ ደግሞ ሌላ ችግር ተነስቶ
ይጠብቅሃል። ህይወት እንዲህ ነውና!። ችግሮች የህይወት አካል
ናቸው፤ አንዳንድ ጊዜ ጥቂት፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ በርካታ ችግሮች
ይኖራሉ። ይሄ ማለት ግን ስለነሱ ሁሌ ማሰብ አለብህ ማለት
አይደለም። እነሱን ለጊዜ እየተወክ ወደፊት ተጓዝ። በእያንዳንዱ
እርምጃም ወደ ዓላማ-ህይወት (Purpose of life/self-
realization/) ማደግን ተማር።
ልብ በል፤
• አንዳንድ ጊዜ፤ ደስታን ለማወቅ በኅዘን፣ ዝምታን ለማድነቅ በጩኸት፣
የመኖርን ዋጋ ለማወቅ ባለመኖር መንገድ ልታልፍ ግድ ነው።
ይኸውልህ፤ ህይወት በተቃርኖ የተሞላች ነች። እያንዳንዱ ስኬት
ከሸክም ጋር ነው የሚመጣው። ትልቅ ቤት ማግኘት ስኬት ሲሆን፣ ብዙ
የሚጸዳ መኖሩ ሸክም ነው። ልጅ መውለድ ስኬት ሲሆን፣ በእኩለ
ሌሊት መነሳቱ ሸክም ነው። ባለስልጣን መሆን ስኬት ሲሆን፣ የህዝብን
ጩኸት ማስተናገዱ ሸክም ነው።
ብዙ ጊዜ የምንሠራው ስህተት- ስኬቱን ያለ ሸክም ከመፈለግ
የሚመጣ ነው። ይህ ግን እውነታው አይደለም። የሚመጡት በጥቅል
(package) ነው። ዋናው ነገር፣ ሸክሙም እያለ በስኬቱ/በበረከቱ
መደሰትን መማሩ ላይ ነው!!
ሰናይ ዕለት!
via:- Book for All fb page
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
(Samuel Geda)
በአንድ ትንሽ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው ነበር። ታዲያ ይህ
ሰው፣ በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በኑሮው ከሚገጥመው ችግር
የተነሳ፣ ሁልጊዜም በህይወቱ ደስተኛ አልነበረም። አንድ ቀን ግን
ከሚኖርበት ሥፍራ በቅርብ ርቀት የምትገኝ ከተማ ዘንድ፣ አንድ ታላቅ
የኃይማኖት አባት ከአጃቢዎቻቸው ጋር እንደመጡ ይሰማል። ይህን
ጊዜም እኚህን አባት ማግኘት አለብኝ ብሎ ይወስናል።
በመሸም ጊዜ እኚህ አባት ያሉበት ሥፍራ ይደርስና፡ እሳቸውን
ለማግኘት ቁጭ ብሎ መጠባበቁን ይይዛል። ከረጅም ቆይታ በኋላም
እኒያን አባት ያገኝና ጥያቄውን ይጀምራል። "አባቴ ሆይ፥ በህይወቴ
ፍፁም ደስተኛ አይደለሁም፤ በቃ ሁሌም በችግር የተከበብኩኝ ሰው
ነኝ... በዚህ በኩል የሥራ ጭንቀት፣ በዚህ ደግሞ የጤና ቀውስ፣
በዛላይ የቤቴ ውስጥ ችግር... ብቻ ተደማምሮ እረፍት ነስቶኛል፣
ደስታም ርቆኛል፤ እባክዎትን አንዳች የመፍትሄ ሀሳብ ይስጡኝና፡
ደስተኛና የሰላም ኑሮ እንድኖር ይርዱኝ!"
ሽማግሌውም ፈገግ ብለው፤ "ልጄ፥ ለችግርህ ነገ ጠዋት ላይ መፍትሄ
እሰጥሃለሁ፤ ነገር ግን አሁን ባዝህ፣ ጥቂት የኔን ሥራ ልትሠራልኝ
ትችላለህን?፤ ሰውዬውም በዚህ ይስማማል። እሳቸውም ቀጥለው፦
"በጉዞአችን የያዝናቸው መቶ ግመሎች በዚህ ይገኛሉ፤ እናም ዛሬ
ምሽት የነርሱን ነገር፡ አደራውን ላንተ ሰጥቻለሁ፤ ሁሉንም ግመሎች
እመሬት ላይ ካስቀመጥክ በኋላ ወደ መኝታ መሄድ ትችላለህ"።
ይህንንም ብለው ወደ ድንኳናቸው ሲያቀኑ፣ ሰውዬውም የታዘዘውን
ሊያደርግ ምሽቱን ግመሎቹ ዘንድ አመራ።
በቀጣይ ቀንም ሽማግሌው ማልደው ወደ ሰውዬው በማቅናት "ልጄ፥
ሌሊቱን ጥሩ ተኝተህ አደርክ?" ብለው ይጠይቁታል። ሰውዬው ግን
ኅዘን በተሞላበት ስሜት ሆኖ "አባቴ፥ ለዐፍታ እንኳን እንቅልፍ
ሳይወስደኝ ነው ሌሊቱ የነጋው። ብዙ ለፋሁ፣ ብዙም ጣርኩኝ፡ ይሁንና
በአንድ ጊዜ ሁሉንም ግመሎች እንዲቀመጡ ማድረግ አልቻልኩም።
አንዳንዶቹ ራሳቸው ይቀመጣሉ፤ አንዳንዶቹ ግን ላስቀምጣቸው
ብሞክርም እንኳን አይቀመጡም፤ አንዱ በዚህ በኩል ሲቀመጥ፡ በሌላ
በኩል ያሉት ይነሣሉ"።
ይህን ጊዜ ሽማግሌው ፈገግ እያሉ እንዲህ አሉ፦ "ካልተሳሳትኩኝ፡ ይህ
የሆነው ትላንት ማታ ነው አይደል?"
- ራሳቸውን በራሳቸው ያስቀመጡ ብዙ ግመሎች ነበሩ!?
- ብዙዎቹ ደግሞ በአንተ ጥረት ሊቀመጡ ችለዋል!?
- ቀሪዎቹ ልታስቀምጣቸው ሞክረህ እንኳን አልተቀመጡም፤ ከቆይታ
በኋላ ግን በጊዜ ውስጥ ራሳቸውን አስቀምጠው አግኝተሃቸዋል!?
ሰውዬውም፦ "አዎ! አዎ!...ትክክል!" ብሎ መለሰ።
ሽማግሌውም ቀጠሉና፦ "ስለዚህ አሁን አንድ ነገር ተረዳህን?፤
በህይወት ያሉም ችግሮች እንዲሁ ናቸው...
- አንዳንዶቹ በራሳቸው መፍትሄ ያገኛሉ።
- አንዳንዶቹ በአንተ ጥረት መፍትሄ ያገኛሉ።
- አንዳንዶቹ ደግሞ በአንተ ጥረት እንኳን አይፈቱም፤ እነዚህን ችግሮች
ለጊዜ ተዋቸው። ትክክለኛው ጊዜ ሲደርስ በራሳቸው ይፈታሉና/
መፍትሄ ያገኛሉና/።
ትላንት ማታ፣ ምን ያህል ብትሞክር በአንድ ጊዜ ሁሉንም ግመሎች
ማስቀመጥ እንዳልቻልክ ትምህርት ወስደሃል። አንዱን ግመል በዚህ
ጋር ስታስቀምጥ በሌላ በኩል ያሉት ይነሣሉ። ልክ እንዲሁ፤ እዚህ ጋር
አንዱን ችግር ፈታሁ/ተፈታ ስትል እዛ ደግሞ ሌላ ችግር ተነስቶ
ይጠብቅሃል። ህይወት እንዲህ ነውና!። ችግሮች የህይወት አካል
ናቸው፤ አንዳንድ ጊዜ ጥቂት፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ በርካታ ችግሮች
ይኖራሉ። ይሄ ማለት ግን ስለነሱ ሁሌ ማሰብ አለብህ ማለት
አይደለም። እነሱን ለጊዜ እየተወክ ወደፊት ተጓዝ። በእያንዳንዱ
እርምጃም ወደ ዓላማ-ህይወት (Purpose of life/self-
realization/) ማደግን ተማር።
ልብ በል፤
• አንዳንድ ጊዜ፤ ደስታን ለማወቅ በኅዘን፣ ዝምታን ለማድነቅ በጩኸት፣
የመኖርን ዋጋ ለማወቅ ባለመኖር መንገድ ልታልፍ ግድ ነው።
ይኸውልህ፤ ህይወት በተቃርኖ የተሞላች ነች። እያንዳንዱ ስኬት
ከሸክም ጋር ነው የሚመጣው። ትልቅ ቤት ማግኘት ስኬት ሲሆን፣ ብዙ
የሚጸዳ መኖሩ ሸክም ነው። ልጅ መውለድ ስኬት ሲሆን፣ በእኩለ
ሌሊት መነሳቱ ሸክም ነው። ባለስልጣን መሆን ስኬት ሲሆን፣ የህዝብን
ጩኸት ማስተናገዱ ሸክም ነው።
ብዙ ጊዜ የምንሠራው ስህተት- ስኬቱን ያለ ሸክም ከመፈለግ
የሚመጣ ነው። ይህ ግን እውነታው አይደለም። የሚመጡት በጥቅል
(package) ነው። ዋናው ነገር፣ ሸክሙም እያለ በስኬቱ/በበረከቱ
መደሰትን መማሩ ላይ ነው!!
ሰናይ ዕለት!
via:- Book for All fb page
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
መልክዓ እናት
(በእውቀቱ ስዩም)
ሰላም ለኪ እናታችን
ባለሽበት እንዳለሽ
ከዘመኑ ሴቶች ተለይተሽ
አንቺ የተባረክሽ ነሽ
ሰላም ለዓይኖችሽ
ከጭስ ጋር ለሚሟገቱ
ከእንቅልፍ ጋር ለተፋቱ
ተቅበዝባዥ ፍጡር ሆኜ ኑሮዬን ከምገፋ
ምነው እንባሽን በሆንኩ
ካ'ይኖችሽ ስር እንዳልጠፋ
ሰላም ለከንፈሮችሽ
ትላንት ለማውቃቸው
ዛሬ ለምናፍቃቸው
ውዳሴ ክብር ምርቃት
ጭብጨባ ሙገሳ ሽልማት በተረፈበት ቀዬ
ምነው ያንቺን እርግማን ይናፍቃል ጆሮዬ
ከሌሎች ውዳሴና ክብር እልፍ ግዜ የተሻለ
ለካ በ'ርግማንሽ ውስጥ እናትነትሽ አለ
ሰላም ለጣቶችሽ
ለሰዎች የቀረቡ ፣ከራስሽ ግን የራቁ
መስጠት መለገስን እንጂ መቀበልን ለማያቁ
ሰላም ለኪ
ባለሽበት እንዳለሽ።
For ur comment and complain on the channel contact
@Haile_melekot
Or
@Simetin_Begitimbot
& Share your channel to ur friends
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
(በእውቀቱ ስዩም)
ሰላም ለኪ እናታችን
ባለሽበት እንዳለሽ
ከዘመኑ ሴቶች ተለይተሽ
አንቺ የተባረክሽ ነሽ
ሰላም ለዓይኖችሽ
ከጭስ ጋር ለሚሟገቱ
ከእንቅልፍ ጋር ለተፋቱ
ተቅበዝባዥ ፍጡር ሆኜ ኑሮዬን ከምገፋ
ምነው እንባሽን በሆንኩ
ካ'ይኖችሽ ስር እንዳልጠፋ
ሰላም ለከንፈሮችሽ
ትላንት ለማውቃቸው
ዛሬ ለምናፍቃቸው
ውዳሴ ክብር ምርቃት
ጭብጨባ ሙገሳ ሽልማት በተረፈበት ቀዬ
ምነው ያንቺን እርግማን ይናፍቃል ጆሮዬ
ከሌሎች ውዳሴና ክብር እልፍ ግዜ የተሻለ
ለካ በ'ርግማንሽ ውስጥ እናትነትሽ አለ
ሰላም ለጣቶችሽ
ለሰዎች የቀረቡ ፣ከራስሽ ግን የራቁ
መስጠት መለገስን እንጂ መቀበልን ለማያቁ
ሰላም ለኪ
ባለሽበት እንዳለሽ።
For ur comment and complain on the channel contact
@Haile_melekot
Or
@Simetin_Begitimbot
& Share your channel to ur friends
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ቅጣት ምት
✍አንዱዓለም ኪዳኔ
ልቤን ኳስ አርጋችሁ ሰትጫወቱበት
ስትቀባበሉ ስታንቀራቅቧት
ስታንከባልሉ ደሞም ስጠልዟት
ቅጣት ላይ አደራ
ሀይል አብዝታችሁ እንዳታፈነዷት ፡፡
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
✍አንዱዓለም ኪዳኔ
ልቤን ኳስ አርጋችሁ ሰትጫወቱበት
ስትቀባበሉ ስታንቀራቅቧት
ስታንከባልሉ ደሞም ስጠልዟት
ቅጣት ላይ አደራ
ሀይል አብዝታችሁ እንዳታፈነዷት ፡፡
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
በዕውቀቱ ስዩም
//ከተመኙ ላይቀር//
ከተመኙ ላይቀር ወንዝነት መመኘት....
ሀገርን ሳይለቁ ሌላ ሀገር መገኘት.....::
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
//ከተመኙ ላይቀር//
ከተመኙ ላይቀር ወንዝነት መመኘት....
ሀገርን ሳይለቁ ሌላ ሀገር መገኘት.....::
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
##ሃገረ_ኢትዮጵ
በታላቁ መፅሃፍ ፥ ታሪኩ የሰፈረ
እዮብ ሰው አይደለም ፥ በምድር የኖረ።
°
"እዮብ" የተባለች
ምስኪን ሀገሬ ነች፤
ልጆች ሞተውባት
ገላዋ ተልቶባት
አመድ ላይ የተኛች።
°
በእምነት ተንበርክካ ፥ እጆቿን ዘርግታ
ምህረት የምትለምን ፥ ከሠራዊት ጌታ።
ወዳጅ ዘመዶቿ ፥ ሰድበሽው ሙች ሲሏት
"ሰጠ! -- ነሳ!" ብላ ፥ የምትኖር በፅናት።
~~~~~~~~~//~~~~~~~~~
( በርናባስ ከበደ )
©ግጥም ብቻ
@Simetin_Begitim
በታላቁ መፅሃፍ ፥ ታሪኩ የሰፈረ
እዮብ ሰው አይደለም ፥ በምድር የኖረ።
°
"እዮብ" የተባለች
ምስኪን ሀገሬ ነች፤
ልጆች ሞተውባት
ገላዋ ተልቶባት
አመድ ላይ የተኛች።
°
በእምነት ተንበርክካ ፥ እጆቿን ዘርግታ
ምህረት የምትለምን ፥ ከሠራዊት ጌታ።
ወዳጅ ዘመዶቿ ፥ ሰድበሽው ሙች ሲሏት
"ሰጠ! -- ነሳ!" ብላ ፥ የምትኖር በፅናት።
~~~~~~~~~//~~~~~~~~~
( በርናባስ ከበደ )
©ግጥም ብቻ
@Simetin_Begitim
ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
የኔ መሪ ❤️🇪🇹
አንተ አልቻልክም ይሉሃል::
አዎ አንተ አትችልም!
በሰይፍ መቅላት፣ረግጦ መግዛት አልቻልክም፤
አንተ እጅ መቁረጥ፣ እግር መንሳት አልቻልክም፤
ዘር ማጥፋት፣ ደሃን መግፋት ፈጽሞውኑ አልቻልክም፤
የኔን ተቀበል ያንተን ወዲያ ጣል፤
በአንተ ወርቅ እኔ ልድመቅ ማለት፤
ምን በወጣህ አንተ አትችልም፤
ስለዚህ አንተ አልቻልክም::
ጀግናን በስቅላት፣ ገሎ ለጅብ መስጠት
40 ምሁር ከወደቁበት አንስቶ ማክበር እንጂ 60 ምሁር ባንዴ መቅበር
እንዴት ይቻልሃል? አልፈጠረብህማ!
ለመላው አፍሪካ መስራት እንጂ ምስኪኑን የኤርትራ ህዝብ መውጋት
አይሆንልህም::
ማስታረቅ እንጂ ማራራቅ፤
ወንድም ህዝብ ደም አይፋሰስ እንጂ የህጻናት ደም ይፍሰስ አትልም!
ስለዚህ አልቻልክም::
የእናቶችን እንባ ማበስ እንጂ የራሔልን እንባ ማፍሰስ፤
የልጅ እሬሳ ላይ አስቀምጦ በሰደፍ አናቷን ማፍረስ፤
አንተ አይሆንልህም አመድ አፋሽ ቢያረጉህም::
የችሎታ ስሌቱ ይሄ ለሆነ ህዝብ አንተ አትችልም::
በቃ አትችልማ!!!
ሞታቸውን የሚጠባበቁትን ከእስር ለቀሃል::
ስለዚህ አልቻልክም:: ምክንያቱም ጀግንነት ለእነሱ መግደል ነዋ!
የተበተኑትን ከአለም ዙርያ ሰብሰበሃል፤
በፍቅር አቅፈህ አብረህ አልቅሰሃል፤
ያለመዱትን? የማያዉቁትን?
ስለሆነም አልቻልክም::
ለአህያ ማር እየሰጠህ አስቸግረሃል፤
አህያ የለመደችው ሳር እንጂ ማር አይጥማትም፤
ስለዚህ ችሎታ ይጎለሃል::
ፒንሳ የልህም፣ የሃይላንድ ዉሃ የለህም፤
የምድር ስር ጉድጓድ፣ጫለማ ቤት የለህም፤
ማስፈራርያ አውሬ የለህም፤
ሽንት የምትሸና የመብራቱ ልጅ የለችህም፤
ታዲያ ችሎታህ ምኑ ጋር ነው???
ሚድያውን ማፈን፣ የባለጌን አፍ መድፈን፤
እጅግ ተስኖሃል:: ስለዚህ አንተ ሳትቀር ባደባባይ ይሰድቡሃል::
ያሻቸውን ይጽፋሉ ይናገራሉ፤ሲሻቸው ይሰለፋሉ፤ ሲሻቸው ይሸልላሉ
(አንተምላይ ሳይቀር)
“ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ ” ሲል ለኖረ ሰው፤
ለገዢዎች የአምልኮ ስግደት ሲሰግድ ለኖረ ህዝብ፤
የአጋዚን ዱላ ለጠገበ ሰውነት ይሄ እንዴት ይሰማሟል???
ስለዚህ አትችልም ይለሃል::
እጅ መንሻ ሲሰጥ ለኖረ ጉቦ ለለመደ፤
ሌባ ይጥፋ ስትል ሀገሩን የካደ፤
ባዕድ ነው ለሱ፣ የችሎታ ማነስ፣ ባህሉን የናደ::
እሱ ችሎት ለኖረው አንተ ምን አነካከህ?
ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው እየሞተ ያገኛታል መተው ነበረብህ::
እኔ ልንገርህ ዶ/ር አብይ አንተ አትችልም!
ብዙ ሚሊዮን ህዝብ መምራት እንጂ ብዙ ሚሊዮን እብድ መንዳት
አትችልም!Ephreme Gelgela
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
አዎ አንተ አትችልም!
በሰይፍ መቅላት፣ረግጦ መግዛት አልቻልክም፤
አንተ እጅ መቁረጥ፣ እግር መንሳት አልቻልክም፤
ዘር ማጥፋት፣ ደሃን መግፋት ፈጽሞውኑ አልቻልክም፤
የኔን ተቀበል ያንተን ወዲያ ጣል፤
በአንተ ወርቅ እኔ ልድመቅ ማለት፤
ምን በወጣህ አንተ አትችልም፤
ስለዚህ አንተ አልቻልክም::
ጀግናን በስቅላት፣ ገሎ ለጅብ መስጠት
40 ምሁር ከወደቁበት አንስቶ ማክበር እንጂ 60 ምሁር ባንዴ መቅበር
እንዴት ይቻልሃል? አልፈጠረብህማ!
ለመላው አፍሪካ መስራት እንጂ ምስኪኑን የኤርትራ ህዝብ መውጋት
አይሆንልህም::
ማስታረቅ እንጂ ማራራቅ፤
ወንድም ህዝብ ደም አይፋሰስ እንጂ የህጻናት ደም ይፍሰስ አትልም!
ስለዚህ አልቻልክም::
የእናቶችን እንባ ማበስ እንጂ የራሔልን እንባ ማፍሰስ፤
የልጅ እሬሳ ላይ አስቀምጦ በሰደፍ አናቷን ማፍረስ፤
አንተ አይሆንልህም አመድ አፋሽ ቢያረጉህም::
የችሎታ ስሌቱ ይሄ ለሆነ ህዝብ አንተ አትችልም::
በቃ አትችልማ!!!
ሞታቸውን የሚጠባበቁትን ከእስር ለቀሃል::
ስለዚህ አልቻልክም:: ምክንያቱም ጀግንነት ለእነሱ መግደል ነዋ!
የተበተኑትን ከአለም ዙርያ ሰብሰበሃል፤
በፍቅር አቅፈህ አብረህ አልቅሰሃል፤
ያለመዱትን? የማያዉቁትን?
ስለሆነም አልቻልክም::
ለአህያ ማር እየሰጠህ አስቸግረሃል፤
አህያ የለመደችው ሳር እንጂ ማር አይጥማትም፤
ስለዚህ ችሎታ ይጎለሃል::
ፒንሳ የልህም፣ የሃይላንድ ዉሃ የለህም፤
የምድር ስር ጉድጓድ፣ጫለማ ቤት የለህም፤
ማስፈራርያ አውሬ የለህም፤
ሽንት የምትሸና የመብራቱ ልጅ የለችህም፤
ታዲያ ችሎታህ ምኑ ጋር ነው???
ሚድያውን ማፈን፣ የባለጌን አፍ መድፈን፤
እጅግ ተስኖሃል:: ስለዚህ አንተ ሳትቀር ባደባባይ ይሰድቡሃል::
ያሻቸውን ይጽፋሉ ይናገራሉ፤ሲሻቸው ይሰለፋሉ፤ ሲሻቸው ይሸልላሉ
(አንተምላይ ሳይቀር)
“ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ ” ሲል ለኖረ ሰው፤
ለገዢዎች የአምልኮ ስግደት ሲሰግድ ለኖረ ህዝብ፤
የአጋዚን ዱላ ለጠገበ ሰውነት ይሄ እንዴት ይሰማሟል???
ስለዚህ አትችልም ይለሃል::
እጅ መንሻ ሲሰጥ ለኖረ ጉቦ ለለመደ፤
ሌባ ይጥፋ ስትል ሀገሩን የካደ፤
ባዕድ ነው ለሱ፣ የችሎታ ማነስ፣ ባህሉን የናደ::
እሱ ችሎት ለኖረው አንተ ምን አነካከህ?
ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው እየሞተ ያገኛታል መተው ነበረብህ::
እኔ ልንገርህ ዶ/ር አብይ አንተ አትችልም!
ብዙ ሚሊዮን ህዝብ መምራት እንጂ ብዙ ሚሊዮን እብድ መንዳት
አትችልም!Ephreme Gelgela
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ❤️🇪🇹❤️
ከ“እናት ዓለም ጠኑ” ቃለ ተውኔት የተወሰደ
(ብላቴን ጌታ ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን)
አፋዊ ሆንን!
ሕያዊ ሳንሆን አፋዊ!
ቃለ ሕይወት ሳንሆን፣ ብኩን ቃለ-አፍ ብቻ!
እንጂ! ቤታችን አንድ ነው፡፡
“ቤት” ብለን ለልጆቻችን ያወረስናቸው
ፍቅር የሞተበት ቤታችን! አንድ ነው፡፡
አባቶቻችን ልባም
እኛ አፋም፡፡
እሳት ዐመድ ወለደ ሆንን እንጂ- ቤታችንስ አንድ ነው፡፡
ነፃነት ብለን ባርነት
ሕይወት ብለን ሞት - ለልጆቻችን አወረስን፡፡
ብኩን ቃለ-አፍ!
ህይወት ብለን ንፍገት
ጀግንነት ብለን ፍርሃት - ከተብናቸው!
በወረረን ባዕድ ሞት ማግስት፣
አዲስ ተስፋ ለተራበ ህልውና፤ አዲስ የሃገር ውስጥ ሞት!
ለአዲስ ትንሳዔ በቃተተ ዓይን
አዲስ መቃብር ከፈትን!
አፋዊ! ጋዜጣዊ!- ብኩን የሃሰት ነፃነት ዘረጋን!
ልጆቻችን በተስፋ ልክፍት ቃ‘ተው መከኑ!!
አንዲት የዱር አውሬ - በምትወልድበት ሰሞን
ልጇን ትበላለች ይላሉ - ምጥ የበዛባት እንደሆን
ልጆቻችንን በላን!
ትናንት የነፃነትን ምጥ ከአፋፍ መንግለን
የጥላቻ ውርስ አቆይተን
አፋዊ ነፃነት አውርሰን
“ምነው?” ባሉ! ልጆቻችንን ገፍተን
አፋዊ እኩልነት- አፋዊ ክትባት ከትበን
ፍርሃት ወርሰን - ፍርሃት አውርሰን
ጥላቻ ወርሰን - ጥላቻ አውርሰን
ሕያው ሳንሆን አፋዊ
ቃለህይወት ሳንሆን ብኩን ቃለ አፍ
እንጂ ቤታችንስ አንድ ነው፡፡
ትናንት የነፃነትን ምጥ ከአፋፍ መንግለን
የጥላቻ ውርስ አቆይተን
አፋዊ ነፃነት አውርሰን
“ምነው?” ባሉ! ፈረድንባቸው!
በልጆቻችን ፈረድንባቸው!!
የህይወት ጣሙን ሳይሆን - ወጉን
የፍቅር ወዙን ሳይሆን - ስሙን
የነፃነት ግብሩን ሳይሆን - ተረቱን
እንዳወረስናቸው ባወቁብን
በነቁብን
ፈረድንባቸው፡፡
ፍቅራችን የሻል ወርቅ፣ የነጭ ጓንቲ፡ የተከፈለ ፎቶግራፍና የድግስ ጃዝ
እንጂ የልብ እውነት፣ የእሳትና አበባ ጉዳይ አለመሆኑን ባወቁብን፣
በነቁብን፤ ፈረድንባቸው፡፡
የዕውቀት ሙቀታቸውን
በበድን ቅዝቃዜያችን
ቸስቸስ አድርገን - አቀዘቅዝናቸው!
መንፈሳቸውን አኮላሸናቸው፡፡
አበው ያወረሱንን ሰብዓዊ የፍቅር ግለት በውስጣችን አክስለን
እንደመንጋ በዘፈቀደ መፈቃቀዳችንን
በልተን ጠጥተን - ጓሮ እንደመዞር መገናኘታችንን
ሆድሞልተን - ሜዳ እንደመውጣት መፈቃቀዳችንን
ፍቅርን እንደዐቃቢት ቃል ኑዛዜ፣ ምላሳችን ላይአሻግተን ማነብነባችንን
ልጆቻችን ነቅተው ባዩብን - ፈረድንባቸው!
አዎ! - እንጂ ቤታችንስ አንድ ነው፡፡
እኛ ፈላስሞቹ
እኛ ከተሜዎቹ
አዋጅ ነጋሪዎቹ
የዘመናዊ ስልጣኔ ሸቃጮቹ
ታደምንበት!
እኛ የአውሮፓ አደባባይ ጓሮ ቁራዎቹ
የየዩኒቨርስቲዎቻቸው ምሩቃኖቹ
ምሁራኑ!
የጉድ አዋጆቻቸው ተክሎች እኛ!
እኛ ታደምን!
የዘመኑ ድልድይ መሆናችን ቀርቶ - የዘመኑ አዘቅት
ናዳ ግድግዳ ሆነን - በብዙሃኑ ድል ተገደገድንበት!
ጨለማው ቀናችን!
ጭጋጉ ፀሃያችን!
ምሽቱ ንጋታችን ሆነንና ታደምንበት!
በነፍሳችንም አደፍን!
ፍቅር ደከመንና - የቁም ሞት ተወራረስን
ከልጆቻችን ዋጋ ይልቅ- የቀብራችንን ዋጋ አከበድን
የህይወት ቀርቶ - የመቃብር አምላኪዎች ሆንን
እንጂ….!
ፍቅር የሞተበት- ቤታችንስ ያው አንድ ነው!
ዱሮ ዱሮ፤ ሰው በሰው ነው አሉ ራሱን ፈልጎ ሚያገኝ
የራሱን ጉድለት፣
የራሱን ማንነትና ምንነት የሚረዳው
የሌላውን ቀርቦ መርምሮ አጥንቶ ነው ይባላል
እኛ ግን በተቀራረብን ቁጥር እንተጣጣለን
እንጠፋፋለን
አንገናኝም
በተጠጋጋን ቁጥር እንራራቃለን
የቃላት ክምችት ኳኳታ ብቻ ነን
የግስ ግሳንግስ እርባታ ቀፎዎች
ለዚህም ነው እንደአሸዋ ባህር
በቃላት ውጥንቅጥ! በቋንቋ ሽብር
በግስ ግሳንግስ ተጥለቅልቀን!
በቁምና በቅዠት አፋዊ ውዝግብ ስንንኳኳ የቀረን!
ላንግባባ! ቤታችን በቃላት ግሳንግስ ታጥኖ ታፍጎ
ለህሊናችን መተናፈሻ ቀዳዳ የጠፋብን ለዚሁ ነው
በዘፈቀደ ከየፍልስፍናው የአንቡላ ጭልጭ ፉት ያልነውን ጠራዝ ነጠቅ
የቋንቋ ብልጭታ ሌትና ቀን እያንባቧቸርን ስናስጎነብት አንድያችንን
ተጠፋፋን
ዓይናችንም እንደ አንደበታችን ግሳንግስ የደም ፍትወትን ለመደ!
የአይን ወረት ጭዳ የሰሰቀኑን ሱስ ለመደ!
ዓይናችን ጭምር!
የሰው ትራፊ - የሰው ዕድፍ - የሰው ጥንብ ማስተዋል ምሳችን ሆነ!
የሰዉን ጣር እንባ መሻት- የሰው ሰቀቀን ማነፍነፍ - ውሎ አድሮ
ባህላችን ሆነ!
ሌላው ካላደፈ የኛ ንፅህና!
ሌላው ካልተጎሳቆለ የእኛ ጥጋብ ጎልቶ አልታየን አለ!
ዓይናችንን የደም ፍትወት - የሰው ሰቀቀን ጭዳ አስለምደን
አይለከፉት ልክፍት ተለከፍን!
አዎን ፈራን!
የነፍሳችንን አንደበት ዘጋን!
ሰብአዊነታችንን ራሳችን - ከውስጣችን ነደን አክስመን
ሰው የምንለው ሰብአዊ ፍጡር ቢጤአችን
እያደር ከቶም አልገባን አለ!
በዘልማድ ብቻ! ሰውን ሰው - ውሻን ውሻ ብለን
አሜን ብለን እንቀበል እንጂ!
ሰው የሚባል - ረቂቅ ሰብአዊ ፍጡር
ሰው የሚባል - የእግዚአበሄር ተፈጥሮ ተዓምር
ከቶም አልገባን አለ!
እንጂ ቤታችንስ አንድ ነው!
ፍርሃት አስገብተን
ፍርሃት ፀነስን
በቁማችን ፍቅር ሞቶ
በቁማችን ህያውነት ሞቶ
ፍርሃት ባርነት
አፍአዊ ንፍገት
ብካይ ፀነስን
ብካይ!
ከዘመን ዘመን አንሰን
ቁልቁል አደግን
በመንፈስና በባህርይ አይጥ አከልን!
አይጥ አክለን
የነገን ተስፋ
የልጆቻችንን ተስፋ ሰርስረን
ቦርቡረን - ገዝግዘን በላን!
የሀፍረት እድሜ እርሻችንን ጨርሰን
ይኸው በነገው ትውልድ እድሜ ሰርገን
የልጆቻችንን ተስፋ በቁም ገንዘን በላን!
ብካይ ፀነስን
ፍርሃት ፀነስን
አፋዊ ሆንን!
ያም ሆኖ! ለልጆቻችን ሕይወት ብለን ያወረሰናቸው
ፍርሃት የሰፈነበት ቤታችን! ያው አንድ ነው!
ፍቅር የሞተበት
ብካይ የነገሰበት
ሕይወት ብለን ያወረስናቸው ወህኒ ቤታችን! ያው አንድ ነው!
አዎ እንጂ! ቤታችንስ አንድ ነው!
source #Tesfa Zion fb account
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
(ብላቴን ጌታ ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን)
አፋዊ ሆንን!
ሕያዊ ሳንሆን አፋዊ!
ቃለ ሕይወት ሳንሆን፣ ብኩን ቃለ-አፍ ብቻ!
እንጂ! ቤታችን አንድ ነው፡፡
“ቤት” ብለን ለልጆቻችን ያወረስናቸው
ፍቅር የሞተበት ቤታችን! አንድ ነው፡፡
አባቶቻችን ልባም
እኛ አፋም፡፡
እሳት ዐመድ ወለደ ሆንን እንጂ- ቤታችንስ አንድ ነው፡፡
ነፃነት ብለን ባርነት
ሕይወት ብለን ሞት - ለልጆቻችን አወረስን፡፡
ብኩን ቃለ-አፍ!
ህይወት ብለን ንፍገት
ጀግንነት ብለን ፍርሃት - ከተብናቸው!
በወረረን ባዕድ ሞት ማግስት፣
አዲስ ተስፋ ለተራበ ህልውና፤ አዲስ የሃገር ውስጥ ሞት!
ለአዲስ ትንሳዔ በቃተተ ዓይን
አዲስ መቃብር ከፈትን!
አፋዊ! ጋዜጣዊ!- ብኩን የሃሰት ነፃነት ዘረጋን!
ልጆቻችን በተስፋ ልክፍት ቃ‘ተው መከኑ!!
አንዲት የዱር አውሬ - በምትወልድበት ሰሞን
ልጇን ትበላለች ይላሉ - ምጥ የበዛባት እንደሆን
ልጆቻችንን በላን!
ትናንት የነፃነትን ምጥ ከአፋፍ መንግለን
የጥላቻ ውርስ አቆይተን
አፋዊ ነፃነት አውርሰን
“ምነው?” ባሉ! ልጆቻችንን ገፍተን
አፋዊ እኩልነት- አፋዊ ክትባት ከትበን
ፍርሃት ወርሰን - ፍርሃት አውርሰን
ጥላቻ ወርሰን - ጥላቻ አውርሰን
ሕያው ሳንሆን አፋዊ
ቃለህይወት ሳንሆን ብኩን ቃለ አፍ
እንጂ ቤታችንስ አንድ ነው፡፡
ትናንት የነፃነትን ምጥ ከአፋፍ መንግለን
የጥላቻ ውርስ አቆይተን
አፋዊ ነፃነት አውርሰን
“ምነው?” ባሉ! ፈረድንባቸው!
በልጆቻችን ፈረድንባቸው!!
የህይወት ጣሙን ሳይሆን - ወጉን
የፍቅር ወዙን ሳይሆን - ስሙን
የነፃነት ግብሩን ሳይሆን - ተረቱን
እንዳወረስናቸው ባወቁብን
በነቁብን
ፈረድንባቸው፡፡
ፍቅራችን የሻል ወርቅ፣ የነጭ ጓንቲ፡ የተከፈለ ፎቶግራፍና የድግስ ጃዝ
እንጂ የልብ እውነት፣ የእሳትና አበባ ጉዳይ አለመሆኑን ባወቁብን፣
በነቁብን፤ ፈረድንባቸው፡፡
የዕውቀት ሙቀታቸውን
በበድን ቅዝቃዜያችን
ቸስቸስ አድርገን - አቀዘቅዝናቸው!
መንፈሳቸውን አኮላሸናቸው፡፡
አበው ያወረሱንን ሰብዓዊ የፍቅር ግለት በውስጣችን አክስለን
እንደመንጋ በዘፈቀደ መፈቃቀዳችንን
በልተን ጠጥተን - ጓሮ እንደመዞር መገናኘታችንን
ሆድሞልተን - ሜዳ እንደመውጣት መፈቃቀዳችንን
ፍቅርን እንደዐቃቢት ቃል ኑዛዜ፣ ምላሳችን ላይአሻግተን ማነብነባችንን
ልጆቻችን ነቅተው ባዩብን - ፈረድንባቸው!
አዎ! - እንጂ ቤታችንስ አንድ ነው፡፡
እኛ ፈላስሞቹ
እኛ ከተሜዎቹ
አዋጅ ነጋሪዎቹ
የዘመናዊ ስልጣኔ ሸቃጮቹ
ታደምንበት!
እኛ የአውሮፓ አደባባይ ጓሮ ቁራዎቹ
የየዩኒቨርስቲዎቻቸው ምሩቃኖቹ
ምሁራኑ!
የጉድ አዋጆቻቸው ተክሎች እኛ!
እኛ ታደምን!
የዘመኑ ድልድይ መሆናችን ቀርቶ - የዘመኑ አዘቅት
ናዳ ግድግዳ ሆነን - በብዙሃኑ ድል ተገደገድንበት!
ጨለማው ቀናችን!
ጭጋጉ ፀሃያችን!
ምሽቱ ንጋታችን ሆነንና ታደምንበት!
በነፍሳችንም አደፍን!
ፍቅር ደከመንና - የቁም ሞት ተወራረስን
ከልጆቻችን ዋጋ ይልቅ- የቀብራችንን ዋጋ አከበድን
የህይወት ቀርቶ - የመቃብር አምላኪዎች ሆንን
እንጂ….!
ፍቅር የሞተበት- ቤታችንስ ያው አንድ ነው!
ዱሮ ዱሮ፤ ሰው በሰው ነው አሉ ራሱን ፈልጎ ሚያገኝ
የራሱን ጉድለት፣
የራሱን ማንነትና ምንነት የሚረዳው
የሌላውን ቀርቦ መርምሮ አጥንቶ ነው ይባላል
እኛ ግን በተቀራረብን ቁጥር እንተጣጣለን
እንጠፋፋለን
አንገናኝም
በተጠጋጋን ቁጥር እንራራቃለን
የቃላት ክምችት ኳኳታ ብቻ ነን
የግስ ግሳንግስ እርባታ ቀፎዎች
ለዚህም ነው እንደአሸዋ ባህር
በቃላት ውጥንቅጥ! በቋንቋ ሽብር
በግስ ግሳንግስ ተጥለቅልቀን!
በቁምና በቅዠት አፋዊ ውዝግብ ስንንኳኳ የቀረን!
ላንግባባ! ቤታችን በቃላት ግሳንግስ ታጥኖ ታፍጎ
ለህሊናችን መተናፈሻ ቀዳዳ የጠፋብን ለዚሁ ነው
በዘፈቀደ ከየፍልስፍናው የአንቡላ ጭልጭ ፉት ያልነውን ጠራዝ ነጠቅ
የቋንቋ ብልጭታ ሌትና ቀን እያንባቧቸርን ስናስጎነብት አንድያችንን
ተጠፋፋን
ዓይናችንም እንደ አንደበታችን ግሳንግስ የደም ፍትወትን ለመደ!
የአይን ወረት ጭዳ የሰሰቀኑን ሱስ ለመደ!
ዓይናችን ጭምር!
የሰው ትራፊ - የሰው ዕድፍ - የሰው ጥንብ ማስተዋል ምሳችን ሆነ!
የሰዉን ጣር እንባ መሻት- የሰው ሰቀቀን ማነፍነፍ - ውሎ አድሮ
ባህላችን ሆነ!
ሌላው ካላደፈ የኛ ንፅህና!
ሌላው ካልተጎሳቆለ የእኛ ጥጋብ ጎልቶ አልታየን አለ!
ዓይናችንን የደም ፍትወት - የሰው ሰቀቀን ጭዳ አስለምደን
አይለከፉት ልክፍት ተለከፍን!
አዎን ፈራን!
የነፍሳችንን አንደበት ዘጋን!
ሰብአዊነታችንን ራሳችን - ከውስጣችን ነደን አክስመን
ሰው የምንለው ሰብአዊ ፍጡር ቢጤአችን
እያደር ከቶም አልገባን አለ!
በዘልማድ ብቻ! ሰውን ሰው - ውሻን ውሻ ብለን
አሜን ብለን እንቀበል እንጂ!
ሰው የሚባል - ረቂቅ ሰብአዊ ፍጡር
ሰው የሚባል - የእግዚአበሄር ተፈጥሮ ተዓምር
ከቶም አልገባን አለ!
እንጂ ቤታችንስ አንድ ነው!
ፍርሃት አስገብተን
ፍርሃት ፀነስን
በቁማችን ፍቅር ሞቶ
በቁማችን ህያውነት ሞቶ
ፍርሃት ባርነት
አፍአዊ ንፍገት
ብካይ ፀነስን
ብካይ!
ከዘመን ዘመን አንሰን
ቁልቁል አደግን
በመንፈስና በባህርይ አይጥ አከልን!
አይጥ አክለን
የነገን ተስፋ
የልጆቻችንን ተስፋ ሰርስረን
ቦርቡረን - ገዝግዘን በላን!
የሀፍረት እድሜ እርሻችንን ጨርሰን
ይኸው በነገው ትውልድ እድሜ ሰርገን
የልጆቻችንን ተስፋ በቁም ገንዘን በላን!
ብካይ ፀነስን
ፍርሃት ፀነስን
አፋዊ ሆንን!
ያም ሆኖ! ለልጆቻችን ሕይወት ብለን ያወረሰናቸው
ፍርሃት የሰፈነበት ቤታችን! ያው አንድ ነው!
ፍቅር የሞተበት
ብካይ የነገሰበት
ሕይወት ብለን ያወረስናቸው ወህኒ ቤታችን! ያው አንድ ነው!
አዎ እንጂ! ቤታችንስ አንድ ነው!
source #Tesfa Zion fb account
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ማን ይቀጣ
°°°°°°°°°°°°
ዳኛው ተቀምጧል በዙፋኑ ድንበር
ክሱም ተዘርግቷል በዕልህ ሊከራከር
ከሳሽ እስዋም አለች ተከሳሹም እኔ
እሷ ባለ ዘመድ ብቸኛው እኔ አለሁ ሰው የለኝ ከጎኔ
ክሱ ተጀመረ እንስቷ ቀደመች
ክቡር ፍርድ ቤቱን እያመሰገነች
ደጋግማ ደጋግማ አይኑ ነው ትላለች
እራሷም ወደ እሱ እያጉረጠረጠች
ስወጣ ስገባ ስቀመጥ ስነሳ
ስለሰው ሳወሳ ስራዬን ሳነሳ
እንዲያው በየቦታው ያፈጣል ይህ አይኑ
ዳኛው ይፍረድልኝ ለውነት ከወገኑ
ብላ ተቀመጠች ክሷን አስረድታ
ተራዬ ደረሰ
ክሱም ተደራርቦ በኔ ላይ በረታ
የሷ ብዙ ዘመድ
ባይኑ ዱላ ሰነድ
ድብደባው ቀጠለ
ለኔ የሚወግን አንድም ስለሌለ
ክርክር ሙግቱን ማሸነፍ ቢያቅተኝ
ክቡርፍርድቤቱን ላንዴ አስፈቀድኩና
"ስትወጪ ስትገቢ ስራ ስትሰሪ
እየተከተለ አይኔ ሲያስቸግርሽ
ማን አይቶ ነገረሽ?"
መልስ አጥታ በግርምት ራሷን በመነቅነቅ
ትጣጣር ጀመረ ከጥያቄው ልትርቅ
ብሎ ሲጠይቃት ጥያቄዋን በመልስ
ክሱን አነሳችው ዳኛውን ሻረችው
ካፏ በላይ ላለው ለልቧ ሰጠችው
ፋይሉን አዘጋችመዝገብ ቤት ላከችው
በልቧ ዙፋን ላይ የኔን ልብ ሾመችው
ጥፋትዋን አመነች ሲያያት እንዳየችው።
ተፃፈ B.Sh
ምንጭ ፦ TG ቃርምያ
@endenaendena
@endenaendena
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
°°°°°°°°°°°°
ዳኛው ተቀምጧል በዙፋኑ ድንበር
ክሱም ተዘርግቷል በዕልህ ሊከራከር
ከሳሽ እስዋም አለች ተከሳሹም እኔ
እሷ ባለ ዘመድ ብቸኛው እኔ አለሁ ሰው የለኝ ከጎኔ
ክሱ ተጀመረ እንስቷ ቀደመች
ክቡር ፍርድ ቤቱን እያመሰገነች
ደጋግማ ደጋግማ አይኑ ነው ትላለች
እራሷም ወደ እሱ እያጉረጠረጠች
ስወጣ ስገባ ስቀመጥ ስነሳ
ስለሰው ሳወሳ ስራዬን ሳነሳ
እንዲያው በየቦታው ያፈጣል ይህ አይኑ
ዳኛው ይፍረድልኝ ለውነት ከወገኑ
ብላ ተቀመጠች ክሷን አስረድታ
ተራዬ ደረሰ
ክሱም ተደራርቦ በኔ ላይ በረታ
የሷ ብዙ ዘመድ
ባይኑ ዱላ ሰነድ
ድብደባው ቀጠለ
ለኔ የሚወግን አንድም ስለሌለ
ክርክር ሙግቱን ማሸነፍ ቢያቅተኝ
ክቡርፍርድቤቱን ላንዴ አስፈቀድኩና
"ስትወጪ ስትገቢ ስራ ስትሰሪ
እየተከተለ አይኔ ሲያስቸግርሽ
ማን አይቶ ነገረሽ?"
መልስ አጥታ በግርምት ራሷን በመነቅነቅ
ትጣጣር ጀመረ ከጥያቄው ልትርቅ
ብሎ ሲጠይቃት ጥያቄዋን በመልስ
ክሱን አነሳችው ዳኛውን ሻረችው
ካፏ በላይ ላለው ለልቧ ሰጠችው
ፋይሉን አዘጋችመዝገብ ቤት ላከችው
በልቧ ዙፋን ላይ የኔን ልብ ሾመችው
ጥፋትዋን አመነች ሲያያት እንዳየችው።
ተፃፈ B.Sh
ምንጭ ፦ TG ቃርምያ
@endenaendena
@endenaendena
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ጥቋቁር ዳመና
@jemal seid ከጥቋቁር ደመና መድብል ገፅ 44
በሰፊ ሰማይ ላይ ዳመና ያዘለን
ጭልም ያለ ሰማይ ከኛ በላይ ያለን
ልብ ብዬ አየው አየው አየውና
ሰማዩ ላይ ያለውን ጥቋቁር ደመና
እንዲ ይመስለኛል
ከልብ ተመስጫ አንጋጥጫ እያየሁ
የተከፉ ሰማይ ቢሆንስ እላለሁ
ከደመናው መሀል ጠብጠብ የምትል
የተጨቆነን ሰው አንባ የምትመስል
የዝናብ ጠብታ ከሰማይ ይወርዳል
የመብረቁ ጭኸት ልብን ያሸብራል
አዛም አፍሪካ አለ ሰማይ ሚባለው ላይ?
ፍትህ የሚናፍቅ አለ የታፈነ አገልጋይ?
እዛ ሰማይ ላይስ አለ ብዙ ነዋሪ ?
አነሱን ሚያስለቅስ
ይኖር ይሆን እንዴ አምባገነን መሪ?
ተወርዋሪ ከኮብ አኛ የምንለው
በደሉ በዝቶበት ከላይ ተወርውሮ
እራሱን ገሎ ነው ወደታች ሚወርደው?
መብረቅ የምንለው
በደል ይበቃናል ያሉ ከዋክብትን
አሰለቃሽ ጭስ ይሆን እነሱን ሚበትን
እንደዛ ካልሆነ ሰማይ የሚጠቁረው
ለሰው የማይገባ ስውር ሚስጥር አለው?
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@jemal seid ከጥቋቁር ደመና መድብል ገፅ 44
በሰፊ ሰማይ ላይ ዳመና ያዘለን
ጭልም ያለ ሰማይ ከኛ በላይ ያለን
ልብ ብዬ አየው አየው አየውና
ሰማዩ ላይ ያለውን ጥቋቁር ደመና
እንዲ ይመስለኛል
ከልብ ተመስጫ አንጋጥጫ እያየሁ
የተከፉ ሰማይ ቢሆንስ እላለሁ
ከደመናው መሀል ጠብጠብ የምትል
የተጨቆነን ሰው አንባ የምትመስል
የዝናብ ጠብታ ከሰማይ ይወርዳል
የመብረቁ ጭኸት ልብን ያሸብራል
አዛም አፍሪካ አለ ሰማይ ሚባለው ላይ?
ፍትህ የሚናፍቅ አለ የታፈነ አገልጋይ?
እዛ ሰማይ ላይስ አለ ብዙ ነዋሪ ?
አነሱን ሚያስለቅስ
ይኖር ይሆን እንዴ አምባገነን መሪ?
ተወርዋሪ ከኮብ አኛ የምንለው
በደሉ በዝቶበት ከላይ ተወርውሮ
እራሱን ገሎ ነው ወደታች ሚወርደው?
መብረቅ የምንለው
በደል ይበቃናል ያሉ ከዋክብትን
አሰለቃሽ ጭስ ይሆን እነሱን ሚበትን
እንደዛ ካልሆነ ሰማይ የሚጠቁረው
ለሰው የማይገባ ስውር ሚስጥር አለው?
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
##ሃገረ_ኢትዮጵ
በታላቁ መፅሃፍ ፥ ታሪኩ የሰፈረ
እዮብ ሰው አይደለም ፥ በምድር የኖረ።
°
"እዮብ" የተባለች
ምስኪን ሀገሬ ነች፤
ልጆች ሞተውባት
ገላዋ ተልቶባት
አመድ ላይ የተኛች።
°
በእምነት ተንበርክካ ፥ እጆቿን ዘርግታ
ምህረት የምትለምን ፥ ከሠራዊት ጌታ።
ወዳጅ ዘመዶቿ ፥ ሰድበሽው ሙች ሲሏት
"ሰጠ! -- ነሳ!" ብላ ፥ የምትኖር በፅናት።
~~~~~~~~~//~~~~~~~~~
( በርናባስ ከበደ )
©ግጥም ብቻ
@Simetin_Begitim
በታላቁ መፅሃፍ ፥ ታሪኩ የሰፈረ
እዮብ ሰው አይደለም ፥ በምድር የኖረ።
°
"እዮብ" የተባለች
ምስኪን ሀገሬ ነች፤
ልጆች ሞተውባት
ገላዋ ተልቶባት
አመድ ላይ የተኛች።
°
በእምነት ተንበርክካ ፥ እጆቿን ዘርግታ
ምህረት የምትለምን ፥ ከሠራዊት ጌታ።
ወዳጅ ዘመዶቿ ፥ ሰድበሽው ሙች ሲሏት
"ሰጠ! -- ነሳ!" ብላ ፥ የምትኖር በፅናት።
~~~~~~~~~//~~~~~~~~~
( በርናባስ ከበደ )
©ግጥም ብቻ
@Simetin_Begitim
ለኔ ስል
✍አንዱአለም ኪዳኔ
ሰላም ሆና እንዳያት እኔ 'ምፀልየው
መቼ ለሷ አዝኜ ደርሶ 'ምጨነቀው
ብቻ ደስ ይበላት ፍቅሬ ትሁን ጤና
በሷ ፈገግታ ውስጥ ሰላም አለኝና፡፡
@Simetin_Begitim
✍አንዱአለም ኪዳኔ
ሰላም ሆና እንዳያት እኔ 'ምፀልየው
መቼ ለሷ አዝኜ ደርሶ 'ምጨነቀው
ብቻ ደስ ይበላት ፍቅሬ ትሁን ጤና
በሷ ፈገግታ ውስጥ ሰላም አለኝና፡፡
@Simetin_Begitim
መልክዓ እናት
(በእውቀቱ ስዩም)
ሰላም ለኪ እናታችን
ባለሽበት እንዳለሽ
ከዘመኑ ሴቶች ተለይተሽ
አንቺ የተባረክሽ ነሽ
ሰላም ለዓይኖችሽ
ከጭስ ጋር ለሚሟገቱ
ከእንቅልፍ ጋር ለተፋቱ
ተቅበዝባዥ ፍጡር ሆኜ ኑሮዬን ከምገፋ
ምነው እንባሽን በሆንኩ
ካ'ይኖችሽ ስር እንዳልጠፋ
ሰላም ለከንፈሮችሽ
ትላንት ለማውቃቸው
ዛሬ ለምናፍቃቸው
ውዳሴ ክብር ምርቃት
ጭብጨባ ሙገሳ ሽልማት በተረፈበት ቀዬ
ምነው ያንቺን እርግማን ይናፍቃል ጆሮዬ
ከሌሎች ውዳሴና ክብር እልፍ ግዜ የተሻለ
ለካ በ'ርግማንሽ ውስጥ እናትነትሽ አለ
ሰላም ለጣቶችሽ
ለሰዎች የቀረቡ ፣ከራስሽ ግን የራቁ
መስጠት መለገስን እንጂ መቀበልን ለማያቁ
ሰላም ለኪ
ባለሽበት እንዳለሽ።
For ur comment and complain on the channel contact
@Haile_melekot
Or
@Simetin_Begitimbot
& Share your channel to ur friends
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
(በእውቀቱ ስዩም)
ሰላም ለኪ እናታችን
ባለሽበት እንዳለሽ
ከዘመኑ ሴቶች ተለይተሽ
አንቺ የተባረክሽ ነሽ
ሰላም ለዓይኖችሽ
ከጭስ ጋር ለሚሟገቱ
ከእንቅልፍ ጋር ለተፋቱ
ተቅበዝባዥ ፍጡር ሆኜ ኑሮዬን ከምገፋ
ምነው እንባሽን በሆንኩ
ካ'ይኖችሽ ስር እንዳልጠፋ
ሰላም ለከንፈሮችሽ
ትላንት ለማውቃቸው
ዛሬ ለምናፍቃቸው
ውዳሴ ክብር ምርቃት
ጭብጨባ ሙገሳ ሽልማት በተረፈበት ቀዬ
ምነው ያንቺን እርግማን ይናፍቃል ጆሮዬ
ከሌሎች ውዳሴና ክብር እልፍ ግዜ የተሻለ
ለካ በ'ርግማንሽ ውስጥ እናትነትሽ አለ
ሰላም ለጣቶችሽ
ለሰዎች የቀረቡ ፣ከራስሽ ግን የራቁ
መስጠት መለገስን እንጂ መቀበልን ለማያቁ
ሰላም ለኪ
ባለሽበት እንዳለሽ።
For ur comment and complain on the channel contact
@Haile_melekot
Or
@Simetin_Begitimbot
& Share your channel to ur friends
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim