ለመላው የክርስትና እምነት ተከታታይ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለጌታችን መድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሠላም አደረሳችሁ ፡፡ በዓሉ የሠላም የጤናና የፍቅር እንዲሆንላችሁ እንመኛለን ፡፡
መልካም ገና
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
መልካም ገና
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
Forwarded from ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
🌼ንገሩአት ለናቴ🌼
ንገሩአት ለናቴ
ብርዱ ቢበረታም
ሀሩሩ ቢያይልም
ብርሀን ፊቷን ነስታ
ጨለማው ቢበዛም
ንገሩአት እሷነቷ ለኔ
መቼም አይቀየርም።
አግኝቶ ማጣት ጦስ
ክብሯን ቢነግፋትም
እናትነቷ ህያው ነው
መቼም አይፋቅም።
ንገሩአት ለናቴ
የናትነት ፍቅሯን
ለመቅመስ ባልታደልም
ሲከፋት እንባዋን
ከአይኗ ባልጠርግም
ንገሩአት በውሎዬ
ረስቼአት አላውቅም።
በእጆቿ ዳሳኝ፣
እደግ ብላ ባትመርቀኝም
የናትነት ጠረኗ ቃናዋ ባይታወቀኝም
ንገሩአት እናቴ ፣
እናቴው ናት፣
የፈጣሪ ሀብቴ፣
ጣእሟን ማላውቅ፣
የመኖሬ ዳሯ ሰገነቴ።
እሷው ናት እሷው ናት፣
ቢከፋም ቢለማም፣
የእኔነቴ ማህተም፤እሷው ናት ንገሩአት ንገሩአት
ምንም ሳትደብቁ...
ሀይለመለኮት ተስፋዬ
ንገሩአት ለናቴ
ብርዱ ቢበረታም
ሀሩሩ ቢያይልም
ብርሀን ፊቷን ነስታ
ጨለማው ቢበዛም
ንገሩአት እሷነቷ ለኔ
መቼም አይቀየርም።
አግኝቶ ማጣት ጦስ
ክብሯን ቢነግፋትም
እናትነቷ ህያው ነው
መቼም አይፋቅም።
ንገሩአት ለናቴ
የናትነት ፍቅሯን
ለመቅመስ ባልታደልም
ሲከፋት እንባዋን
ከአይኗ ባልጠርግም
ንገሩአት በውሎዬ
ረስቼአት አላውቅም።
በእጆቿ ዳሳኝ፣
እደግ ብላ ባትመርቀኝም
የናትነት ጠረኗ ቃናዋ ባይታወቀኝም
ንገሩአት እናቴ ፣
እናቴው ናት፣
የፈጣሪ ሀብቴ፣
ጣእሟን ማላውቅ፣
የመኖሬ ዳሯ ሰገነቴ።
እሷው ናት እሷው ናት፣
ቢከፋም ቢለማም፣
የእኔነቴ ማህተም፤እሷው ናት ንገሩአት ንገሩአት
ምንም ሳትደብቁ...
ሀይለመለኮት ተስፋዬ
Forwarded from ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian (Haile Melekot)
።።።ምን አገባኝ ።።።
እኔ ምን አገባኝ
የምትሉት ሀረግ
እሱ ነዉ አገሬን
ያረዳት እንደ በግ
ብዬ ግጥም ልፅፍ
ብድግ አልኩኝና
ምን አገባኝ ብዬ
ቁጭ አልኩ እንደገና
(በእውቀቱ ስዩም)
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ይሄ አነሰ ይሄ ጎደለ ምትሉን ካለ ወይም
ግጥሞች
ጠቃሚ መልእክቶች
ወጎችም ከላችሁ
@Simetin_Begitimbot
ይላኩልን እኛ ደግሞ መልሠን ወደ እናንተ እናደርሳለን፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ተከብራ ትኑር 🇪🇹
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
እኔ ምን አገባኝ
የምትሉት ሀረግ
እሱ ነዉ አገሬን
ያረዳት እንደ በግ
ብዬ ግጥም ልፅፍ
ብድግ አልኩኝና
ምን አገባኝ ብዬ
ቁጭ አልኩ እንደገና
(በእውቀቱ ስዩም)
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ይሄ አነሰ ይሄ ጎደለ ምትሉን ካለ ወይም
ግጥሞች
ጠቃሚ መልእክቶች
ወጎችም ከላችሁ
@Simetin_Begitimbot
ይላኩልን እኛ ደግሞ መልሠን ወደ እናንተ እናደርሳለን፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ተከብራ ትኑር 🇪🇹
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
Forwarded from ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian (Haile Melekot)
Haile_Melekot_አይ_እቺ_አለም.mp4
1.3 MB
Forwarded from ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian (Haile Melekot)
አጠር_ያለች_የፍቅር_ደብዳቤHaile_Melekot.mp4
2.9 MB
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ለለውጥ እንነሳ‼️
መጠላላቱን፣ በብሄር በዘር መከፋፈሉን፣ መሠዳደቡን፣ መተነኳኮሉን፣ እርስ በእርስ ለመጠፋፋት መሮጡን፣ ጦርነት ውስጥ ለመግባት መሽቀዳደሙን ትተን ይህ እጅግ #አሳፋሪ እና #አስነዋሪ በዓለም ደረጃ አንገት የሚያስደፋንን ታሪክ ለመቀየር 24 ሰዓት እንስራ‼️
Half of the world's poor live in these 5 countries:
🔹India
🔹Nigeria
🔹Democratic Republic of Congo
🔹Ethiopia(#ኢትዮጵያ)
🔹Bangladesh
http://wrld.bg/Oeak30nhefz
መጠላላቱን፣ በብሄር በዘር መከፋፈሉን፣ መሠዳደቡን፣ መተነኳኮሉን፣ እርስ በእርስ ለመጠፋፋት መሮጡን፣ ጦርነት ውስጥ ለመግባት መሽቀዳደሙን ትተን ይህ እጅግ #አሳፋሪ እና #አስነዋሪ በዓለም ደረጃ አንገት የሚያስደፋንን ታሪክ ለመቀየር 24 ሰዓት እንስራ‼️
Half of the world's poor live in these 5 countries:
🔹India
🔹Nigeria
🔹Democratic Republic of Congo
🔹Ethiopia(#ኢትዮጵያ)
🔹Bangladesh
http://wrld.bg/Oeak30nhefz
World Bank Blogs
Half of the world’s poor live in just 5 countries
Of the world’s 736 million extreme poor in 2015, 368 million lived in just 5 countries. The 5 countries with the highest number of extreme poor are: India, Nigeria, Democratic Republic of Congo, Ethiopia, and Bangladesh.
©ዝንቅ
🙂አሁን ስንት ገባሽ
አፍቅሬሽ ከልቤ ያኔ ስጠይቅሽ
አሻፈረኝ ያልሽው ብር የለህም ብለሽ
እድሜ ላንቺ ውዴ አሁን ብር ይዣለው
አሁን ስንት ገባሽ ይኧው ልገዛሽ ነው😂
😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂?
?😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂
@Simetin_Begitim
🙂አሁን ስንት ገባሽ
አፍቅሬሽ ከልቤ ያኔ ስጠይቅሽ
አሻፈረኝ ያልሽው ብር የለህም ብለሽ
እድሜ ላንቺ ውዴ አሁን ብር ይዣለው
አሁን ስንት ገባሽ ይኧው ልገዛሽ ነው😂
😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂?
?😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂
@Simetin_Begitim
# ላፍቃሪ_ንዋይ
፧
የቀናው ሲጠፋ
እየገነነ ጎብጦ፣
አቀነቀነልን
ጥበብን ገልብጦ፣
የነቀዘው ሁሉ
ዛሬ ላይ ወዛና፣
አሁን ዘመነልን
ቅን'ቅኑን ፈጀና !!
፨
# ሀብታሙ_ወዳጅ
@Simetin_Begitim
፧
የቀናው ሲጠፋ
እየገነነ ጎብጦ፣
አቀነቀነልን
ጥበብን ገልብጦ፣
የነቀዘው ሁሉ
ዛሬ ላይ ወዛና፣
አሁን ዘመነልን
ቅን'ቅኑን ፈጀና !!
፨
# ሀብታሙ_ወዳጅ
@Simetin_Begitim
©Fiker_love
#ስርዝ_ድልዝ_ደብዳቤ 🌷
እዚ ደብዳቤ ላይ
💚 ልነግርሽ ያሰብኩት
💛 አስቤ የፃፍኩት
❤️ ፅፌ የሰረዝኩት
ሰርዤ የላኩት
ስርዝ ድልዝ ሆኖ አልነበብ ካለሽ
ሳልሰርዘው በፊት
ምን ይላል መሰለሽ…
መግቢያውም
መደምደምያው ሀተታው በሞላ
ሌላ አይናገርም
ከናፈቅሽኝ እና ካፈቀርኩሽ ሌላ።
@Simetin_Begitim
#ስርዝ_ድልዝ_ደብዳቤ 🌷
እዚ ደብዳቤ ላይ
💚 ልነግርሽ ያሰብኩት
💛 አስቤ የፃፍኩት
❤️ ፅፌ የሰረዝኩት
ሰርዤ የላኩት
ስርዝ ድልዝ ሆኖ አልነበብ ካለሽ
ሳልሰርዘው በፊት
ምን ይላል መሰለሽ…
መግቢያውም
መደምደምያው ሀተታው በሞላ
ሌላ አይናገርም
ከናፈቅሽኝ እና ካፈቀርኩሽ ሌላ።
@Simetin_Begitim
ቃናዝ(ልዑል ሀይሌ)
.
ነግሬሽ ነበረ...
አልነግርሽም ብዬ፤
እንደማልጠብቅሽ ከመንገድ ተጥዬ፤
እንደማልነሳ ከጣልሽኝ ሜዳ ላይ፤
እንደማልመለስ
እየተንጠራራሁ ሳልነካው ያን ሰማይ፤
እንደማላወራ
እንዳልጠራ ስምሽን ዳግም ተመልሼ፤
ነግሬሽ ነበረ አልነግርሽም ብዬ ቃልሽን አስታውሼ።
.
ነግሬሽ ነበረ...
የምነግርሽን ቃል፤
ብቻ ምን አለፋሽ
አልነግርሽም ያልኩት ብነግርሽ ይበቃል፤
ሌላው ያስተረፍኩት
የማይነገረው ያልነገርኩሽ ነገር፤
እነግርሽ ነበረ
ቀድሜ ባልነግርሽ እንደማልናገር።
.
ግን እነግርሻለሁ!!
የብሶቴን ዳር ዳር የቁጭቴን ጫፉ፤
እንደማላዋይሽ
አዋይቼሻለሁ በግርድፍ ግርድፉ።
.
ነግሬሽ ነበረ...
ዳግመኛ እንደማይሽ ዓይኖቼ ከጠፉ፤
በፅልመቴ ነዪ
በብርሃኔ አትኖሪም ምን ዘመናት ቢያልፉ።
.
ነይ ያኔ!
ነይ ያኔ!
አይሻለሁ ብዬ የገባሁልሽ ቃል፤
በጣልሺኝ ፅልመት ውስጥ
እየሟሟ ያልቃል፤
ስለዚህ ነይ ልየው
ቀና ብዬ ዓይንሽን፤
ያልኩሽን አትዪው አጥፊ ዓይኖችሽን።
.
ነግሬሽ ነበረ....
የማልነግርሽን ቃል፤
ከምነግርሽ ነገር
አልነግርሽም ብዬ ብነግርሽ ይበቃል።
.
ነግሬሽ ነበረ...
አልነግርሽም ብዬ፤
በተከልሽው ጎጆ ባጥር ተንጠልጥዬ፤
ያ ፅልመት ሚመስል ቀኑ እንደሚገፈፍ፤
ሐጢያት፣ዕዳ፣ጦሱ ላንቺ እንደሚተርፍ፤
በአርምሞዬ ቅጣት እንደምትቀጪ፤
ነግሬሽ ነበረ.....
አልነግርሽም ብዬ ከቤቴ ስትወጪ፤
እናም እነግርሻለሁ የስንብቴን ቃል፤
ብቻ ምን አለፋሽ
አልነግርሽም ብዬ ብነግርሽ ይበቃል።
፲፪-፭-፳፻፲፩ ዓ.ም.
@Simetin_Begitim
.
ነግሬሽ ነበረ...
አልነግርሽም ብዬ፤
እንደማልጠብቅሽ ከመንገድ ተጥዬ፤
እንደማልነሳ ከጣልሽኝ ሜዳ ላይ፤
እንደማልመለስ
እየተንጠራራሁ ሳልነካው ያን ሰማይ፤
እንደማላወራ
እንዳልጠራ ስምሽን ዳግም ተመልሼ፤
ነግሬሽ ነበረ አልነግርሽም ብዬ ቃልሽን አስታውሼ።
.
ነግሬሽ ነበረ...
የምነግርሽን ቃል፤
ብቻ ምን አለፋሽ
አልነግርሽም ያልኩት ብነግርሽ ይበቃል፤
ሌላው ያስተረፍኩት
የማይነገረው ያልነገርኩሽ ነገር፤
እነግርሽ ነበረ
ቀድሜ ባልነግርሽ እንደማልናገር።
.
ግን እነግርሻለሁ!!
የብሶቴን ዳር ዳር የቁጭቴን ጫፉ፤
እንደማላዋይሽ
አዋይቼሻለሁ በግርድፍ ግርድፉ።
.
ነግሬሽ ነበረ...
ዳግመኛ እንደማይሽ ዓይኖቼ ከጠፉ፤
በፅልመቴ ነዪ
በብርሃኔ አትኖሪም ምን ዘመናት ቢያልፉ።
.
ነይ ያኔ!
ነይ ያኔ!
አይሻለሁ ብዬ የገባሁልሽ ቃል፤
በጣልሺኝ ፅልመት ውስጥ
እየሟሟ ያልቃል፤
ስለዚህ ነይ ልየው
ቀና ብዬ ዓይንሽን፤
ያልኩሽን አትዪው አጥፊ ዓይኖችሽን።
.
ነግሬሽ ነበረ....
የማልነግርሽን ቃል፤
ከምነግርሽ ነገር
አልነግርሽም ብዬ ብነግርሽ ይበቃል።
.
ነግሬሽ ነበረ...
አልነግርሽም ብዬ፤
በተከልሽው ጎጆ ባጥር ተንጠልጥዬ፤
ያ ፅልመት ሚመስል ቀኑ እንደሚገፈፍ፤
ሐጢያት፣ዕዳ፣ጦሱ ላንቺ እንደሚተርፍ፤
በአርምሞዬ ቅጣት እንደምትቀጪ፤
ነግሬሽ ነበረ.....
አልነግርሽም ብዬ ከቤቴ ስትወጪ፤
እናም እነግርሻለሁ የስንብቴን ቃል፤
ብቻ ምን አለፋሽ
አልነግርሽም ብዬ ብነግርሽ ይበቃል።
፲፪-፭-፳፻፲፩ ዓ.ም.
@Simetin_Begitim
©ዝንቅ
ደመቀ ሲፀልይ፣ ገዱ እየሰገደ፤
ከአማራ ሰማይ ላይ፣ #በረከት ወረደ፤
የክፋት በረከት መርገምት ከራቀ፣
ገዳችን ውል ይዞ ፍቅራችን ደመቀ።
Credit - ኮማቹ
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ደመቀ ሲፀልይ፣ ገዱ እየሰገደ፤
ከአማራ ሰማይ ላይ፣ #በረከት ወረደ፤
የክፋት በረከት መርገምት ከራቀ፣
ገዳችን ውል ይዞ ፍቅራችን ደመቀ።
Credit - ኮማቹ
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
😂ለፈገግታ
"ቡና ጠፋ ብለሽ ፣ ስታለቃቅሽ
በጅማ ተገኘ ፣ ያውም በርካሽ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ለሊት ካስቸገረሽ ፣ የቡና ሱስሽ
እኔ እወቅጠዋለሁ ፣ አንቺ ከቆላሽ፡፡
😂😂😂😂😂
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
"ቡና ጠፋ ብለሽ ፣ ስታለቃቅሽ
በጅማ ተገኘ ፣ ያውም በርካሽ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ለሊት ካስቸገረሽ ፣ የቡና ሱስሽ
እኔ እወቅጠዋለሁ ፣ አንቺ ከቆላሽ፡፡
😂😂😂😂😂
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
<<በላይ በቀለ ወያ>>
ከነዚህ ውጪ
ነፃ አውጪ
ህዝቡን ጥሎ ፣ ሸሽቶ ነበር ፣ ወደ ውጪ (ኢመኑኝ ርዕስ ነው)
(ታላቁ ሩስያዊ ፈላስፋ በበወቪስኪ እንደፃፈው)
.
.
እውነት ግን እውነት ግን
ነፃ አውጪ ነኝ ብሎ ፣ ወደ ሀገር የመጣው
ድንገት የለማ ቲም ፣ ነፃ ባያወጣው
ምንድን ነበር እጣው?
።።።
ዛሬ እንደልባቸው
ነፃ አውጪ ነን ብለው ፣ ሀገር ሚቀውጡት
ያኔ የት ነበሩ...
ደርግ ጥሎት ሲሔድ ፣ ደርግ ሆነው የመጡት
ህዝቡን እንደጫማ ፣ ሲያስሩና ሲረግጡት?
የድል አጥቢያ አርበኞች ፣
የት ጠፍተው ነው ያኔ ፣ ዛሬ የሚቀብጡት?
ብዬ አልጠይቅም ፣ ምላሹን ሳላጣው
ነፃ አውጪ ነኝ በሚል...
መጨቆን ነውና ፣ የዚህ ህዝብ እጣው
እስከማውቀው ድረስ
ባለሁበት ሀገር
ነፃ አውጪ ብቻ ነው ፣ ነፃ የሚወጣው!
(እኔ ነፃ አውጪ ሳውቅ
የህዝቡን ደም ሳይሆን
እንደ አጤ ቴዎድሮስ ፣ ሽጉጥ ነው ሚጠጣው
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ከነዚህ ውጪ
ነፃ አውጪ
ህዝቡን ጥሎ ፣ ሸሽቶ ነበር ፣ ወደ ውጪ (ኢመኑኝ ርዕስ ነው)
(ታላቁ ሩስያዊ ፈላስፋ በበወቪስኪ እንደፃፈው)
.
.
እውነት ግን እውነት ግን
ነፃ አውጪ ነኝ ብሎ ፣ ወደ ሀገር የመጣው
ድንገት የለማ ቲም ፣ ነፃ ባያወጣው
ምንድን ነበር እጣው?
።።።
ዛሬ እንደልባቸው
ነፃ አውጪ ነን ብለው ፣ ሀገር ሚቀውጡት
ያኔ የት ነበሩ...
ደርግ ጥሎት ሲሔድ ፣ ደርግ ሆነው የመጡት
ህዝቡን እንደጫማ ፣ ሲያስሩና ሲረግጡት?
የድል አጥቢያ አርበኞች ፣
የት ጠፍተው ነው ያኔ ፣ ዛሬ የሚቀብጡት?
ብዬ አልጠይቅም ፣ ምላሹን ሳላጣው
ነፃ አውጪ ነኝ በሚል...
መጨቆን ነውና ፣ የዚህ ህዝብ እጣው
እስከማውቀው ድረስ
ባለሁበት ሀገር
ነፃ አውጪ ብቻ ነው ፣ ነፃ የሚወጣው!
(እኔ ነፃ አውጪ ሳውቅ
የህዝቡን ደም ሳይሆን
እንደ አጤ ቴዎድሮስ ፣ ሽጉጥ ነው ሚጠጣው
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim