Senay Tech
357 subscribers
75 photos
23 videos
6 files
61 links
👉Owner @Senaymg

በዚህ የ Tech የቴሌግራም ቻናል
📱 #Android_Tricks
🚀 #Social_Media_secrets
📰 #Tech_News
🛠 #Useful_Apps
💡 #Quick_Tech_Tips በነፃ እናቀርባለን።
Download Telegram
📱 በጣም ጠቃሚ የEthio telecom ሚስጥራዊ USSD/SMS Codes

ኮድ ምን ያደርጋል?
*804#
የairtime ቀሪ ሂሳብ፣ credit limit እና ያለህን package ለማየት

*999#
Voice, Data, SMS እና ሌሎች mobile packages ለመግዛት

*806*
ስልክ ቁጥር*መጠን#
Airtime ለሌላ ሰው ለመላክ

*807*ስልክ ቁጥር#
“Call me back” መልዕክት ለመላክ

*810#
Airtime/package credit ለመጠየቅ

A / C / L → 810
የcredit አገልግሎት በSMS ለመጠየቅ

*805*Voucher#
Airtime በvoucher ለመሙላት

*805*
Voucher*ስልክ ቁጥር*መጠን#
በvoucher ለሌላ ሰው airtime ለመላክ

989
Prepaid mobile service ለማንቃት

@Senaytech
👍1👏1
Ethio_Telecom_USSD_Codes_Guide በ @Senaytech.pdf
48.5 KB
Share Ethio_Telecom_USSD_Codes_Guide በ @Senaytech.pdf
2👍1
እዚህ ቻናል ላይ ከአሁን በፊት የለቀቅናቸው ጠቃሚ መጣጥፎች

ስልካችሁ እየተንቀራፈፈ ለምትቸገሩ
https://t.me/Senaytech/18

የስልካችሁን ባትሪ አጠቃቀም ለማሻሻል
https://t.me/Senaytech/30

ቲክቶክ ቪድዮ እይታ ከቀነሰባችሁ
https://t.me/Senaytech/42

ዳታ ስንጠቀም በፍጥነት እንዳያልቅብን
https://t.me/Senaytech/46

ለቪድዮ ኤዲቲንግ የሚጠቅሟችሁ የተለያዩ sound effects
https://t.me/Senaytech/252?single

ምርጥ እና ጠቃሚ የሆኑ 5 የቴሌግራም ቦቶችን
https://t.me/Senaytech/277

የስልካችሁን ሚስጥር ለመጠበቅ
https://t.me/Senaytech/286

ይቀጥል...?
👍2
Senay Tech
Social Dilemma Part 3 ሰዎቹ እንዲህ ይላሉ! "...አብዛኛዎቻችን የምንጠቀማቸው የማህበራዊ ሚድያ መተግበርያዎች ነፃ ይመስሉናል! ነገር ግን አይደሉም! ለነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች ማስታወቂያ ድርጅቶች ብዙ ሚልዮን ዶላሮችን ይከፍላሉ! እኛ ልክ እንደ እቃ(product) ነን! እነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች የምንወደውን፣ የምንጠላውን፣ የምናደርገውን እና ያቀድነውን ስለሚያውቁ ለነዚህ ማስታወቂያ…
Social Dilemma
Part 4 (የመጨረሻው ክፍል)

እቅዳቸው ተጠቃሚዎቻችን "perfection(ፍፁማዊነት)" እና "Social Approval(ማህበራዊ ተቀባይነት)" እንዲሰማቸው ማድረግ ነው።አንዲት ሴት ዝም ብላ አንድ የራሷን ፎቶ ምንም ሳትጨምርበት ብትለጥፍ የምታገኘው "like" ያንሳል። ነገር ግን የተለያዩ የውበት መጨመርያ ፊልተሮችን ተጠቅማ ፎቶዋን ብታሳምር፣ ሻዶው ብትጨምር፣ የቆዳ ቀለሟን ፈካ ብታደርግ እና ፊቷ ላይ ያለውን ብጉር ብታጠፋ የምታገኘው "like" እና "comment" ይበዛል። "...ቆንጆ፣ ስታምሪ፣ ከንፈርሽ፣ ፊትሽ..." ምናምን የሚሏት ሰዎች ይጨምራሉ። ግባችን የተወደደች፣ ሰዎች በውበቷ የሚቀኑባት፣ ከሌሎች ጓደኞቿ የተሻለ ተከታይ እና "social approval" ያላት ሴትን መፍጠር ነው። የሚያሳዝነው ልጅቷ ያንን ሁሉ "comment" እና "like" ያገኘችው እሷን ሆና አይደለም! የውሸት/የተጋነነ ማንነትን እንድትፈጥር አድርገናታል። ትክክለኛ መልኳን እና ማንነቷን እንድትጠላው አመቻችተናል! ለዛም ነው ብዙ ሴቶች ጭንቀት እና የአዕምሮ መታወክ የሚያጋጥማቸው። የሚለጥፉትን ፎቶ ለመምሰል ብዙ ሴቶች ቀዶ ጥገና እስከማድረግ ደርሰዋል!ማህበራዊ ሚድያዎች ዋነኛ አላማቸው የተጠቃሚዎችን "Social Media Engagement (ማህበራዊ ሚድያ ቆይታ)" ማሳደግ ነው። በአሁኑ ሰዓት ወደ 214 ሚልዮን የሚጠጉ ሰዎች የማህበራዊ ሚድያ ሱሰኞች ሆነዋል። የማህበራዊ ሚድያ ሱስ ከ "Cocaine" ሱስ ጋር አንድ ነው። የሰው ልጅ አዕምሮ ውስጥ "Dopamine" የሚባል የደስታ ስሜትን የሚረጭ ሆርሞን አለ! ሱሰኛ ሰዎች ሲጋራ፣ ኮኬይን ወይም ሌላ አደንዛዥ እፅን ሲያስቡ አዕምሮዋቸው "Dopamine" ይረጫል፣ ደስታ ይሰማቸዋል። ማህበራዊ ሚድያም እንደዛ ነው! ማህበራዊ ሚድያን ከፍተህ ለማየት እንድትንቀለቀል የሚያደርገህ ወደ ሰውነትህ የሚረጨው "dopamine" ነው! በአማካይ ሰዎች በቀን 2 ሰዓት ማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚጠቅማቸውንም የማይጠቅማቸውንም ነገር በማየት ግዜያቸውን ያጠፋሉ! ይህ ማለት ከአጠቃላይ እድሜያቸው ድፍን አምስት አመታትን ያባክናሉ ማለት ነው! አሁን ላይ ከሶስት ፍቺዎች ውስጥ አንዱ ከማህበራዊ ሚድያ ሱስ ጋር በተያያዘ ሆንዋል!...." እያሉ ይቀጥላሉ! ከዚህ በላይ ከቀጠልኩ ሙሉ ዶክመንተሪውን መጨረሴ ነው!😀

ማጠቃለያ!

ይህንን ሁሉ ካወሩ በኃላ እንደ መፍትሄ ከሚያስቀምጧቸው ሃሳቦች ውስጥ አንዱን ላስቀምጥ እና ልውጣ!

"Notification" የሚባል ነገርን "off" ማድረግ! በየደቂቃው ስልክህ ላይ "እንትና አዲስ ፅሁፍ ለጠፋ፣ እንትና አዲስ ፎቶ ለቀቀች፣ እገሌ እንዲህ ሆነ..." እያሉ "Notification" የሚልኩልህ ትኩረትህን ለመሳብ ነው። የቆይታ ግዜህን ለማሳደግ ነው። ያንተን "Algorithm" በደንብ ቀርጥፈው ስለበሉት ነው። አንተ ተቆጣጠራቸው እንጂ እነሱ እንዲቆጣጠሩህ አታድርግ! ማየት ስትፈልግ እራስህ ግባ እንጂ "Notification" አይቆስቁስህ!

ጌታዬ! ተጨማሪ መፍትሄዎቹን ማወቅ ከፈለክ ዶክመንተሪውን እይ! ትጠቀማለህ፣ ታተርፋለህ፣ ብዙ ነገር ትባንናለህ! በይበልጥ ማንበብ ከፈለክ እዛው ዶክመንተሪ ላይ ቃለ መጠይቅ ከሚደረግላቸው ሰዎች መካከል "Jaron Lanier" የሚባል ፀዴ ሰውዬ የፃፈው መነጋገርያ የሆነ "Ten Arguments for deleting your social Media accounts right now!"የሚል መፅሃፍ አለ! አንብበው! ከፈለክ እንደ ሁል ግዜው በውስጥ መስመር አቀብልሃለሁ!

መልካም ምሽት!🙏

✍️ወንድዬ እንግዳ

Big Habesha

@Senaytech
4
👍2
ቤተሰቦች እንደሚታወቀው የቲክቶክ አካውንት ከፍተናል እየገባችሁ Follow ምናምን አድርጉ እንጅ በጣም በሚገርም ስራ ተመልሰናል💪

https://www.tiktok.com/@senaytech1?_r=1&_t=ZS-990u0m15w99
1🙏1
በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 563 ሺ 960 ተማሪዎች ተመዝግበው 550 ሺ 210 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።

ፈተናውን ከወሰዱት ውስጥ 12.8 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ማምጣት ችለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ/ም

@Senaytech
ቴሌግራም ላይ ስልክ ቁጥርዎን ለመደበቅ እነዚህን ደረጃዎች ይከተሉ፦

• ቴሌግራምን ይክፈቱ።
• በታችኛው ጥግ ላይ የሚገኘውን የቅንብሮች Settings ምልክት ይንኩ።
• ከዛም "ግላዊነት እና ደህንነት" (Privacy and Security) የሚለውን ይምረጡ።
• በመቀጠል "ስልክ ቁጥር" (Phone Number) የሚለውን ይንኩ።
• እዚያ ስልክ ቁጥርዎን ማን ማየት እንደሚችል የሚገልጹ አማራጮች ያገኛሉ:
• "ሁሉም" (Everybody)፦ ሁሉም ሰው ስልክ ቁጥርዎን ማየት ይችላል።
• "የእኔ እውቂያዎች" (My Contacts)፦ በእውቂያ ዝርዝርዎ ውስጥ ያሉ ሰዎች ብቻ ማየት ይችላሉ።
• "የለም" (Nobody)፦ ማንም ስልክ ቁጥርዎን ማየት አይችልም።

ከነዚህ አማራጮች ውስጥ የሚፈልጉትን መምረጥ ይችላሉ።

video click here
👏2
📚 ያልተነበቡ ሚልዮን መፅሀፍት
🏞️ ያልታዩ ውብ ቦታዎች
🤝 ያልተዋወቅናቸው አስገራሚ ሰዎች
💪 ያልሰሩ ጡንቻዎች
🧠 ያልተማርናቸው በሺህ የሚቆጠሩ skills እያሉ
ድብርት የሚሰማን ከሆነ 😔
የተሻለ ኑሮ ለመኖር ሙከራ አላደርግህም ማለት ነው።

✍️ @Senaytech
💯3
አስገራሚ እና አስቂኝ የጎግል ባህሪያት እነሆ፡-

1. "Do a barrel roll": ይህን ሐረግ በጎግል ፍለጋ ውስጥ ሲጽፉ እና ሲፈልጉ፣ የፍለጋ ገጹ በአንድ ዙር ይሽከረከራል።
2. "Askew" or "Tilt": እነዚህን ቃላት በጎግል ፍለጋ ውስጥ ሲያስገቡ፣ የፍለጋ ውጤት ገጹ በትንሹ ወደ ጎን ያዘነብላል።
3."Super Mario Bros" ብላችሁ ብትፈልጉ፣ በቀኝ በኩል በሚመጣው መረጃ ላይ የሚበራና የሚጠፋ የጥያቄ ምልክት (?) ሳጥን አለ።ያንን ሳጥን ስትነካው ልክ እንደ ጨዋታው ሳንቲም እያወጣ ድምፅ ያሰማል። ።

#google
#tech_tips
👍2
የአፕል (Apple) ኩባንያ ታሪካዊ የሊደርሺፕ ለውጥ ይፋ ተደረገ!🍏🔥

የአፕል ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ (CEO) የሆኑት ቲም ኩክ (Tim Cook) ከሃላፊነታቸው ሊለቁ መሆኑን እና አዲሱ ተተኪያቸው ይፋ መደረጉን የአፕል ቦርድ በይፋ ተረጋግጧል።

ይህ ታሪካዊ ሽግግር በሚቀጥለው ሳምንት September 1, 2026 በይፋ ተግባራዊ ይሆናል።

ቲም ኩክ እ.ኤ.አ በ2011 ከስቲቭ ጆብስ ስልጣን ከተረከቡ በኋላ ኩባንያውን ለ15 ዓመታት በስኬት መርተዋል። ከCEOነታቸው ቢለቁም የአፕል የቦርድ ሊቀመንበር (Executive Chairman) በመሆን ስራቸውን ይቀጥላሉ።

በዚህም እስካሁን የአፕል የሃርድዌር ኢንጂነሪንግ ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ጆን ተርነስ (John Ternus) ሙሉ በሙሉ የCEOነቱን ቦታ ይረከባሉ።ጆን ከ2001 ጀምሮ በአፕል ውስጥ የቆዩ ሲሆን፣ ማክ (Mac) እና አይፎን (iPhone) ጨምሮ በርካታ ታዋቂ ምርቶችን በመስራት ትልቅ ሚና የነበራቸው አንጋፋ መሃንዲስ ናቸው።

© @senaytech
👍2
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Meta_ኩባንያ

የፌስቡክ (Facebook) እና ኢንስታግራም (Instagram) እህት ኩባንያ የሆነው ሜታ (Meta) ከህፃናት እና ወጣቶች ደህንነት ጋር በተያያዘ የተመሰረተበትን ክስ ለመፍታት ግዙፍ የስምምነት ማዕቀፍ (Settlement Framework) ተቀብሏል።የዚህ ስምምነት ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦
ቢሊዮን ዶላሮች የሚደርስ የካሳ ክፍያ ኩባንያው በክሱ ምክንያት እስከ 18 ቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ሊከፍል የሚችልበት ስምምነት ላይ ደርሷል።አዳዲስ ጥብቅ ገደቦች፦ ወጣቶች እና ህጻናት ማህበራዊ ሚዲያዎችን ሲጠቀሙ ከጥቃት፣ ከሱስ እና ካልተገቡ ይዘቶች ለመጠበቅ ሜታ በመድረኮቹ ላይ እጅግ ጥብቅ የሆኑ የደህንነት ገደቦችን ለማስተካከል ተሰማምቷል።

የክሱ መነሻ ምክንያት ሜታ ታዳጊዎች በማህበራዊ ሚዲያ ሱስ እንዲያዙ በማድረግ እና የአእምሮ ጤናቸው ላይ ጉዳት በማድረስ በተለያዩ የዓለም ሀገራት (በተለይም በአሜሪካ ግዛቶች) ክስ ቀርቦበት የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

@Senaytech
🙏2
🚨 AI የሳይበር ስጋት፦ ከ100+ ተቋማት ማስጠንቀቂያ! 🤖⚠️
እ.ኤ.አ. ነሐሴ 2026 ከ100 በላይ ትልልቅ የቴክኖሎጂና የፋይናንስ ተቋማት — OpenAI, Anthropic, Google, Microsoft እና Amazon ጨምሮ — AI የሚመራቸው የሳይበር ጥቃቶች እየተወሳሰቡ በመምጣታቸው የጋራ እርምጃ ጠይቀዋል።
🔴 በቅርብ የተደረጉ ሙከራዎችም AI agents የሳይበር ጥቃት ኮድ መፍጠር፣ የተጋለጡ ሲስተሞችን መድረስ እና ሰዎችን ለማታለል የሐሰት ማንነት መጠቀም እንደሚችሉ አሳይተዋል።
⚠️ ስለዚህ ባለሙያዎች የAI ልማት ከሳይበር ደህንነት ጋር ተመጣጣኝ እንዲሆን አስቸኳይ የጋራ ስራ እንዲደረግ እየጠየቁ ነው።

#AI #CyberSecurity #TechNews #SenayTech

📌 @Senaytech
👍2
በየቀኑ ልትጠቀሟቸው የምትችሏቸው እና ስራችሁን የሚያቀሉ Websites:-

1. www.ilovepdf.com/
የ PDF ፋይሎችን በቀላሉ ለመስራት እና ለመቀየር የሚያስችል PDF tool ነው። pdf ወደ word, pdf ወደ power point, word ወደ pdf, pdf መጠን ለመቀነስ, ብዙ የ pdf ፋይሎችን አንድ ለማድረግ, pdf ላይ ለመፈረም ወዘተ እጅግ ጠቃሚ ነው።

2. www.canva.com/ Graphic design እና document creation ለማድረግ የሚያስችል platform ነው።Presentation, CV, Poster, Flyer, Logo, Social media post,
E-book, PDF, Certificate ለማዘጋጀት ይጠቅማል።

3. www.remove.bg/ ከፎቶ ላይ Background በAutomatic የሚያስወግድ AI-powered tool ነው ሲሆን Thumbnail designers፣ Poster designers፣ Online sellers በጣም ይጠቀሙበታል።

4. www.qr-code-generator.com/
Link፣ text ወይም ሌላ መረጃን ወደ Scan ወደ ሚደረግ QR Code የሚቀይር website ነው። Business, Restaurant menu, Telegram channel, Website, Event registration ወዘተ ለማጋራት በጣም ይጠቅማል።

5. www.photopea.com/ በBrowser ውስጥ የሚሰራ Advanced photo/image editor ነው። የ Photoshop ትንሽ ወንድም ልትሉት ትችላላችሁ፤ Photoshop የሚያውቅ ሰው ብዙ የሚተዋወቃቸውን tools ያገኛል።

ተጨማሪ ከፈለጋችሁ👍 ይደረግ።

@Senaytech
👍2
ሰላም እንዴት ናችሁ🖐️

Ai ን በተለይም chatgpt ስትጠቀሙ ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመጠቀም እና የተሻለ ምላሽ ለማግኘት ተገቢውን prompt መፃፍ ማለትም ግልጽ task፣ context፣ desired output መስጠት ጥሩ ውጤት እንደሚያመጣ OpenAI ይገልፃል።

ይህን በማስመልከት በትምህርት ፣ በስራ እና በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ የሚያግዟችሁን 10 የ chatgpt prompts ለማዘጋጀት አስቤያለሁ። ምን ትላላችሁ?

ይዘጋጅልን👍
ይቅር አይዘጋጅ❤️
እንደተመቸህ🔥
👍7