Senay Tech
357 subscribers
75 photos
23 videos
6 files
61 links
👉Owner @Senaymg

✨ በዚህ የ Tech የቴሌግራም ቻናል
•📱 #Android_Tricks
•🚀 #Social_Media_secrets
•📰 #Tech_News
•🛠 #Useful_Apps
•💡 #Quick_Tech_Tips በነፃ እናቀርባለን።
Download Telegram
The social dilemma ሲባል ሰምታችሁ ታውቃላችሁ?

"The Social Dilemma" የሚለው ቃል በተለይ በ2020 በተለቀቀው ዘጋቢ ፊልም (documentary film) ታዋቂነትን ያገኘ ሲሆን፣ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች በግለሰቦች፣ በማኅበረሰቦች እና በዲሞክራሲ ላይ የሚያደርሱትን አሉታዊ ተፅዕኖዎች የሚመለከት ጽንሰ-ሐሳብ ነው።

በአጭሩ፣ "The Social Dilemma" ማለት የማኅበራዊ ሚዲያ (እና ሌሎች ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች) ጥቅሞች ቢኖራቸውም፣ በውስጣቸው የተገነቡት የአሠራር ሥርዓቶች (algorithms) እና የንግድ ሞዴሎች (business models) በሰዎች እና በኅብረተሰብ ላይ ከባድ አሉታዊ ተፅዕኖዎችን እየፈጠሩ መሆኑን የሚያመለክት (dilemma) ወይም አጣብቂኝ ማለት ነው።

ዋና ዋናዎቹ ነጥቦች እና የሚያስከትላቸው ችግሮች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. ሱስ የመፍጠር ባህሪ (Addiction): የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች ተጠቃሚዎች በመድረኮቻቸው ላይ በተቻለ መጠን ብዙ ጊዜ እንዲያሳልፉ ተብሎ የተነደፉ መሆናቸው።
2. የመረጃ መዛባት እና የሐሰት ዜና (Misinformation & Fake News): የማኅበራዊ ሚዲያ አልጎሪዝሞች ተጠቃሚዎች በስሜት የሚቀሰቀሱ እና በቀላሉ የሚሰራጩ ይዘቶችን (በተለይ አከራካሪ እና የሐሰት መረጃዎችን) የማሳየት ዝንባሌ እንዲኖራቸው መደረጉን።
3. ፖላራይዜሽን እና የኅብረተሰብ መከፋፈል (Polarization & Societal Division): ሰዎች ከራሳቸው አመለካከት ጋር የሚጣጣሙ መረጃዎችን ብቻ እንዲያዩ በማድረግ (echo chambers) እና የተለያዩ አመለካከቶችን ከሚያሳዩ ይዘቶች በመለየት፣ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች የኅብረተሰቡን ክፍሎች እርስ በርስ እንዲራራቁና እንዲከፋፈሉ ያደርጋሉ።
4. የአእምሮ ጤና ችግሮች (Mental Health Issues): በተለይ በወጣቶች ላይ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ከጭንቀት፣ ከድብርት፣ ከራስ የመተማመን ስሜት ማጣት እና ከሳይበር ጉልበተኝነት ጋር ተያይዟል። ሰዎች የሌሎችን "ፍጹም" ህይወት በማየት ራሳቸውን ከሌሎች ጋር ማወዳደር ይጀምራሉ።
5. የግላዊነት ጥሰት እና መረጃን መሰብሰብ (Privacy Violations & Data Collection): የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች ስለ ተጠቃሚዎቻቸው እጅግ በጣም ብዙ መረጃዎችን ይሰበስባሉ። ይህ መረጃ የተጠቃሚዎችን ባህሪ ለመተንበይ እና ለእያንዳንዱ ሰው በተናጠል ማስታወቂያዎችን እና ይዘቶችን ለማሳየት እንደሚጠቀሙበት።

6. የሰው ልጅን ትኩረት እና ባህሪ መቆጣጠር (Manipulation of Human Attention & Behavior): የመድረኮቹ ዋና ዓላማ የሰዎችን ትኩረት መያዝ እና እሱን ወደ ገንዘብ መቀየር ሲሆን ይህ የሚሆነው የሰዎችን ስነ-ልቦናዊ ድክመቶች በመጠቀም ባህሪያቸውን በተዘዋዋሪ መንገድ በመቆጣጠር ነው።

በአጠቃላይ፣ "The Social Dilemma" የተሰኘው ዶክመንታሪ ፊልም የማኅበራዊ ሚዲያ ቴክኖሎጂዎች የሰውን ልጅ ከተፈጥሮአዊ ባህሪው እና ከኅብረተሰቡ ጋር ካለው ግንኙነት እያራቁ፣ በርካታ አደጋዎችን እየፈጠሩ መሆኑን የሚያጎላ አጣብቂኝ ነው።

* ፊልሙ ተሰርቶ የተለቀቀው Netflix ላይ ሲሆን ፊልሙን የሚደስስ ዘገባ ከፈለጋችሁ በ👍 አሳዩኝ በ Part በ Part እለቅላችኋላሁ።
👍4
ሰበር ዜና!!
የYouTube የMonitization መስፈርት ጭማሪ ተደረገበት።

YouTube የዩትዩብ ክሬተሮች ከቻናላቸው ገንዘብ ለማግኘት (Monetized) ለመሆን የሚያስፈልገውን የWatch Hours መስፈርት በእጥፍ ማሳደጉን ይፋ አደረገ።

ከዚህ ቀደም አንድ ቻናል Monetize ለመሆን ባለፉት 12 ወራት ውስጥ 4,000 Watch Hoursና 1,000 Subscribers እንዲሁም በshorts በ90 ቀናት ውስጥ 10 Million እይታ ማሟላት ይጠበቅበት ነበር።
አሁን በተሻሻለው ህግ መሰረት ግን የMonetization ማመልከቻ ለማስገባት ባለፉት 12 ወራት ውስጥ 8,000 Watch Hoursና 20 Million የshorts ዕይታ ማሟላት ይኖርባቸዋል። የSubscribers መስፈርት ከ1,000 Subscribers ጭማሪ አልተደረገበትም።

ይህም ተግባራዊ የሚሆነው ከFebruary 1 ጀምሮ ነው።

ይህ አዲስ መመሪያ በተለይም ገና በማደግ ላይ ላሉ Small Creators ትልቅ መሰናክል የሚፈጥር ሲሆን Monetized ለመሆን የሚወስደውን ጊዜ በእጥፍ ያራዝመዋል። ሆኖም ግን አስቀድመው Monetized የሆኑ ቻናሎች ላይ ተግባራዊ አይደሩግም ተብሏል።

✍️YouTube መስራት የጀመራችሁ ወይም ለመጀመር ያሰባችሁ ምን ተሰማችሁ?

@senaytech
🥰1😢1
Senay Tech
The social dilemma ሲባል ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? "The Social Dilemma" የሚለው ቃል በተለይ በ2020 በተለቀቀው ዘጋቢ ፊልም (documentary film) ታዋቂነትን ያገኘ ሲሆን፣ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች በግለሰቦች፣ በማኅበረሰቦች እና በዲሞክራሲ ላይ የሚያደርሱትን አሉታዊ ተፅዕኖዎች የሚመለከት ጽንሰ-ሐሳብ ነው። በአጭሩ፣ "The Social Dilemma" ማለት የማኅበራዊ ሚዲያ…
Social dilemma
ክፍል 1
(ከወንድዬ እንግዳ የFacebook page የተወሰደ)

እንደምነህ ጌታዬ? እንዴት ነሽ እናቴ? የዚህ ሳምንት ቀደዳችን ደግሞ ይለያል! የፀዳ ነው! ይጠቅምሃል አንብበው!😀
.
.
ጠዋት ስትነሳ ግራ እግርህ ይስራ አይስራ ሳታረጋግጥ መጀመርያ ስልክህን አንስተህ "facebook" ቼክ ታደርጋለህ። ሽንት ቤት ቁጭ ብለህ "Instagram" ላይ ቆንጆ ቆንጆ ሴቶችን "scroll" እያደረክ ትኮሞኩማለህ። ስልክህ ካርድ ከሌለው ቶሎ ገዝተህ "ማህበራዊ ሚድያ" ላይ እስክትጣድ ያንቀለቅልሃል! የሆነ ፅሁፍ ለጥፈህ ምን ያህል "like" እና "comment" እንዳገኘህ ለማወቅ በየደቂቃው "Refresh" እያደረክ ታያለህ። የለጠፍሽው ፎቶ ምን ያህል "like" እንዳገኘ ለማወቅ ያቅበዘብዝሻል። የጠበቅሽውን ያህል "Reaction" ካላገኘ ተበሳጭተሽ ፎቶውን ታጠፊዋለሽ። "ማህበራዊ ሚድያ" ላይ የምታውቃቸው ሰዎች ለተወሰነ ግዜ ሲጠፉብህ ይጨንቅሃል። ስማቸውን ሳይቀር ፅፈህ ትፈልጋቸዋለህ።

ፎቶሽ ላይ ሁል ግዜ "...የኔ ቆንጆ፣ የኔ ልዕልት፣ ስታምሪ.." ምናምን እያለ "comment" የሚያደርግልሽ ልጅ በሆነ አጋጣሚ አዲስ የለጠፍሽው ፎቶ ላይ "comment" ካላደረገ ያሳስብሻል። የለጠፍከው ፎቶ ወይም ፅሁፍ "like" ብዙም ካላገኘ እራስህ "like" ታደርጋለህ። መስሪያ ቤትህ በሰጠህ ኮምፒውተር "facebook" ትጠቀማለህ። ከሰዓት ማስገባት ያለብህ ወሳኝ ስራ እያለ አንተ "tiktok" ላይ ትጣዳለህ። ጠዋት ተነስተህ ወደ ስራ መሄድ እንዳለብህ እያወቅ ማታ ላይ አንድ ሰላሳ ደቂቃ "Tiktok" ልይ ብለህ እስከ ለሊቱ 9 ሰዓት ድረስ ተጥደሃል።

በንጋታው ስራ ረፍዶብሃል ወይም "Tiktok" ላይ ለሊቱን ሙሉ ተጥደህ በቂ እንቅልፍ ባለማግኘትህ ምክንያት ጠዋት ታክሲ ውስጥ አንቀላፍተሃል፣ ቀንህ ተጦልቧል። አንድ ቪድዮ "YouTube" ላይ አያለው ብለህ የገባህ ሰውዬ ሳታስበው "30 ቪድዮ" አይተሃል። "Facebook" ላይ ተጀናጅናችሁ፣ የባጥ የቆጡን ሳትተፋፈሩ አውርታችሁ፣ ተዋዳችሁ፣ ሳትገናኙ እዛው "Facebook" ላይ ተጣብሳችሁ በመጨረሻም በአካል ስትገናኙ ተሽኮርምመሃል፣ አፍረሃል፣ መሬት መሬት አይተሃል፣ ተንተባትበሃል። ከጓደኞችህ ጋር ምሳ ለመብላት ተገናኝታችሁ ምግቡ እስኪመጣ በፊት ስለ ውሏቹ፣ ገጠመኞቻችሁ፣ ስለ ቤተሰቦቻችሁ፣ ስለ ስራችሁ ምናምን በሰፊው የምትቀዱ ሰዎች አሁን ሁላችሁም ስልካችሁ ላይ አቀርቅራችኃል። እየበላችሁ ሳይቀር ከስልኩ ጋር የሚበላ ከመካከላችሁ አይጠፋም።

ስልክህን አብዝተህ ከመውደድህ የተነሳ ትራስህ ስር ወሽቀኸው ትተኛለህ። መብራት ሲጠፋ መጀመርያ የሚያሳስብህ ምግብ ማብሰል አለመቻልህ፣ ቴሌቪዥን ማየት አለመቻልህ ወይም ጨለማ መሆኑ ሳይሆን ስልክህን ቻርጅ ማድረግ አለመቻልህ ነው። ስልክህ ላይ ተጥደህ በመዋልህ ምክንያት ለሚስትህ የምትሰጣት ግዜ ቀንሷል፣ የምትተኙበት እና የምትነሱበት ሰዓት ተለያይቷል፣ ከልጅህ ጋር የምትጫወትበት ግዜ ወርዳል። ማህበራዊ ህይወትህ ተመቷል።

ሰዎችን በአካል አግኝተህ ከምታወራቸው ይልቅ በ "Telegram" ወይም "Messanger" ብታወራቸው ይቀልሃል፣ በአካል መገናኘት ይጨንቅሃል። ጆሮህ ላይ የምትተክለው "Earphone" መገለጫህ እስኪሆን ድረስ ተጣብቆብሃል። የ "Internet' መቋረጥ ሞት እስኪመስልሽ ድረስ ያስጨንቅሻል። ብቻ ምን አለፋህ ስልክህ ህይወት ሆኗል!

አባዬ! ወደ ዋናው ጉዳይ ላምጣህ!

ይቀጥል.......?

@Senaytech
👍4❤1
Social Dilemma
Part 2

አባዬ! ወደ ዋናው ጉዳይ ላምጣህ!
ዓለማችን ካላት ወደ 7 ቢልዮን ከሚገመት ህዝብ ቁጥር ውስጥ ወደ 3 ቢልዮን የሚሆነው ማህበራዊ ሚድያ (facebook, Instagram, snapchat, twitter, tiktok.....) ይጠቀማል። በቅርቡ በ"Netflix" የተሰራ "The Social Dilemma" የሚል ዶክመንተሪ አየሁ። ተራ ዶክመንተሪ አይደለም ጌታዬ! እዚህ ዶክመንተሪ ላይ ቃለ መጠይቅ የሚደረግላቸው ግለሰቦች ከባድ ሚዛን ናቸው። "Instagram" መጀመርያ ላይ ሃሳቡ ሲጠነሰስ አብረው የነበሩ ፣ "Twitter" ውስጥ ለአመታት በኢንጅነርነት ያገለገሉ፣ "pintrest" የመጣ ሰሞን ፕሬዝዳንት ሆኖ የሰራ፣ "Facebook" ውስጥ የ "monetization" ክፍል ዳይሬክተር የነበረ፣ "Google Drive"ን የፈጠሩ፣ "Facebook" ላይ ያለችውን "Like button" የሰራ፣ "Google" ውስጥ በዲዛይነርነት የሰሩ ፣" Gmail" መጀመርያ ሲፈጠር አብረው የነበሩ እና የ "Facebook" ስራ አስፈፃሚ(Executive) ቡድን ውስጥ ሳይቀር የነበሩ ሰዎች ናቸው።

ከነዚህ ከባባድ ሰዎች ውስጥ አንዳንዶቹ በፍቃደኝነት ስራቸውን የለቀቁ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ እነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች የሚሰሩት ትውልድን ሽባ የሚያደርግ ስራ ስለቀፈፋቸው ተጣልተው ወይ ተባረው የወጡ ናቸው።

የሚያስደነግጥ ነገር!

ሁሉም የሚያወሩት አንድ አይነት ነገር ነው። ምን ይላሉ መሰለህ ጌታዬ!

"....የየትኛውም ማህበራዊ ሚድያ የ " Business Model" እንዴት ተጠቃሚዎቻችንን ስክሪን ላይ ማቆየት እንችላለን የሚል ነው! አንድን ተጠቃሚ "Facebook" ወይም "Youtube" ላይ ለማቆየት እና በይበልጥ ትኩረቱን ለመሳብ ምን እናድርግ? የህይወቱን ስንት አመታት ለኛ እንዲሰጠን እናድርግ? የሚለውን ታሳቢ አድርገው ነው የሚሰሩት! እነዚህ "Tech ካምፓኒዎች" ተጠቃሚዎቻቸው "Online" የሚመለከቱትን ማንኛውንም ነገር ያያሉ፣ ይከታተላሉ፣ ይመዝናሉ፣ ያጠናሉ። አንድን ፎቶ ለምን ያህል ደቂቃ ቆም ብለህ እንዳየህ እና የሆነን ቪድዮ እስከ ስንተኛው ደቂቃ ድረስ እንደተከታተልክ ሳይቀር ያውቃሉ! ሲከፋህ ያውቃሉ፣ ሲጨንቅህ ያውቃሉ፣ ስትጓዝ ያውቃሉ፣ ማታ ማታ ምን እንደምታይ ያውቃሉ፣ ቀን ቀን ምን አዘውትረህ እንደምታይ ያውቃሉ። እኛ ከምናስበው በላይ እነዚህ ካምፓኒዎች ጋር ስለኛ ብዙ መረጃ አለ!...."

አባዬ! "Youtube" ልትገዛው ያሰብከውን እቃ መሃል ላይ አስተዋውቆት አስደንግጦህ ያውቃል? የሆነ ልትማር ያሰብለውን ትምህርት በምታየው "Video" መሃል በማስታወቂያ መልክ አምጥቶብህ አልተገረምክም? "Facebook" የዛሬ 10 ዓመት የምታውቀውን እና ከዛ በኃላ አግኝተኸው የማታውቀውን ሰውዬ "people you may know" ላይ ገጭ አድርጎት አይተህ ገርሞህ አታውቅም? "Google" ላይ የሆነ "lipstick" "Search" አድርገሽ ከወጣሽ በኃላ በንጋታው ሌሎች ማህበራዊ ሚድያዎችን ስትከፍቺ የ"lipstick" ማስታወቂያዎች አስሬ እየመጡ አዝገውሽ አያውቁም?

ሰዎቹ እንዲህ ይላሉ!

ይቀጥላል.....

@Senaytech
👍3❤1
Social Dilemma
Part 3

ሰዎቹ እንዲህ ይላሉ!

"...አብዛኛዎቻችን የምንጠቀማቸው የማህበራዊ ሚድያ መተግበርያዎች ነፃ ይመስሉናል! ነገር ግን አይደሉም! ለነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች ማስታወቂያ ድርጅቶች ብዙ ሚልዮን ዶላሮችን ይከፍላሉ! እኛ ልክ እንደ እቃ(product) ነን! እነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች የምንወደውን፣ የምንጠላውን፣ የምናደርገውን እና ያቀድነውን ስለሚያውቁ ለነዚህ ማስታወቂያ ድርጅቶች የኛን መረጃ(data) ይሸጡላቸዋል!...በቀላሉ ካሌንደርህ ላይ በቀጣይ ወር መነፅር እንደምትገዛ ከፃፍክ ቀኑ እየቀረበ ሲመጣ ብዙ የመነፅር ማስታወቂያዎች ይመጡብሃል! ኢሜልክ ላይ የሆነ ሃገር የምትሄድበት ትኬት ካለ እዛ የምትሄድበት ሃገር ላይ ያሉ የሆቴሎች ማስታወቂያ ይመጣብሃል!..."
ጌታዬ! "Algorithm" የሚባል ነገር አለ! በአጭሩ አዘውትረህ የምትመለከታቸውን ቪድዮዎች፣ ዜናዎች፣ መረጃዎች እና ፅሁፎች እነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች በደንብ ካጠኑ እና ከመዘገቡ በኃላ ማንነትህን የሚያውቁበት መንገድ ማለት ነው። ለምሳሌ "Youtube" ከፍተህ አንድ ሁለት ቪድዮ ስለ የሆነ ነገር ካየህ በቀጣይ "YouTube" ላይ ስትገባ ስለእዛ ጉዳይ ተመሳሳይ 100 ቪድዮዎችን " Recommended" ላይ ያመጣብሃል! "Facebook" ላይ ስለ አንድ ጉዳይ በተደጋጋሚ የምታነብ ከሆነ በቀጣይ ስትገባ ስለእዛ ጉዳይ ብዙ መረጃዎችን ያዘንብብሃል! የአንድ አካባቢ ሰዎችን ጓደኛ ካደረክ በቀጣይ እዛ አካባቢ ያሉ ብዙ ሰዎችን ጓደኛ እንድታደርግ ያመጣልሃል! ለምሳሌ "Tiktok" ላይ ገብተህ ተገላልጠው የሚደንሱ ሴቶችን አንድ ሁለት ቪድዮ ካየህ ከዛ በኃላ "tiktok" ተቆጥረው የማያልቁ ተመሳሳይ ቪድዮዎችን ያዥጎደጉድልሃል! የ "Tiktok" "Algorithm" ደግሞ ይለያል! ፍላጎትህን ለመለየት አንድን ቪድዮን ለምን ያህል ደቂቃ እንዳየህ ሳይቀር ያሰላሉ!

ሰዎቹ እንዲህ ይላሉ!

"...ስራችን የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎችን ልክ እንደ "ማሽን/ኮምፒተሮች" "program" ማድረግ ነው። ሰዎች አዲስ ማንነት እና ባህሪን እንዲላበሱ ማድረግ ነው። አንተ ለኛ ልክ እንደ የላብራቶሪ አይጥ ነህ። ዓለም ላይ ሁለት ኢንደስትሪዎች ብቻ ተጠቃሚዎቻቸውን "users" ብለው ይጠራሉ። አንደኛው የአደንዛዥ እፅ ኢንደስትሪ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የማህበራዊ ሚድያው ኢንደስትሪ ነው። ሌሎች ኢንደስትሪዎች ተጠቃሚዎቻቸውን "Customers(ደንበኞች)" ወይንም "Buyers(ገዢዎች)" ነው የሚሉት!
"Refresh" ባደረክ ቁጥር አዲስ ዜና፣ አዲስ መረጃ፣ አዲስ ፎቶ እንድታይ ነው የሚፈልገው። ምክንያቱም ግባቸው አንተን ከስልክህ አጣብቆ ማቆየት ነው።

ይቀጥላል.....

@Senaytech
❤3👍1
📱 በጣም ጠቃሚ የEthio telecom ሚስጥራዊ USSD/SMS Codes

ኮድ ምን ያደርጋል?
*804#
የairtime ቀሪ ሂሳብ፣ credit limit እና ያለህን package ለማየት

*999#
Voice, Data, SMS እና ሌሎች mobile packages ለመግዛት

*806*
ስልክ ቁጥር*መጠን#
Airtime ለሌላ ሰው ለመላክ

*807*ስልክ ቁጥር#
“Call me back” መልዕክት ለመላክ

*810#
Airtime/package credit ለመጠየቅ

A / C / L → 810
የcredit አገልግሎት በSMS ለመጠየቅ

*805*Voucher#
Airtime በvoucher ለመሙላት

*805*
Voucher*ስልክ ቁጥር*መጠን#
በvoucher ለሌላ ሰው airtime ለመላክ

989
Prepaid mobile service ለማንቃት

@Senaytech
👍1👏1
Ethio_Telecom_USSD_Codes_Guide በ @Senaytech.pdf
48.5 KB
Share Ethio_Telecom_USSD_Codes_Guide በ @Senaytech.pdf
❤2👍1
እዚህ ቻናል ላይ ከአሁን በፊት የለቀቅናቸው ጠቃሚ መጣጥፎች

ስልካችሁ እየተንቀራፈፈ ለምትቸገሩ
https://t.me/Senaytech/18

የስልካችሁን ባትሪ አጠቃቀም ለማሻሻል
https://t.me/Senaytech/30

ቲክቶክ ቪድዮ እይታ ከቀነሰባችሁ
https://t.me/Senaytech/42

ዳታ ስንጠቀም በፍጥነት እንዳያልቅብን
https://t.me/Senaytech/46

ለቪድዮ ኤዲቲንግ የሚጠቅሟችሁ የተለያዩ sound effects
https://t.me/Senaytech/252?single

ምርጥ እና ጠቃሚ የሆኑ 5 የቴሌግራም ቦቶችን
https://t.me/Senaytech/277

የስልካችሁን ሚስጥር ለመጠበቅ
https://t.me/Senaytech/286

ይቀጥል...?
👍2
Senay Tech
Social Dilemma Part 3 ሰዎቹ እንዲህ ይላሉ! "...አብዛኛዎቻችን የምንጠቀማቸው የማህበራዊ ሚድያ መተግበርያዎች ነፃ ይመስሉናል! ነገር ግን አይደሉም! ለነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች ማስታወቂያ ድርጅቶች ብዙ ሚልዮን ዶላሮችን ይከፍላሉ! እኛ ልክ እንደ እቃ(product) ነን! እነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች የምንወደውን፣ የምንጠላውን፣ የምናደርገውን እና ያቀድነውን ስለሚያውቁ ለነዚህ ማስታወቂያ…
Social Dilemma
Part 4 (የመጨረሻው ክፍል)

እቅዳቸው ተጠቃሚዎቻችን "perfection(ፍፁማዊነት)" እና "Social Approval(ማህበራዊ ተቀባይነት)" እንዲሰማቸው ማድረግ ነው።አንዲት ሴት ዝም ብላ አንድ የራሷን ፎቶ ምንም ሳትጨምርበት ብትለጥፍ የምታገኘው "like" ያንሳል። ነገር ግን የተለያዩ የውበት መጨመርያ ፊልተሮችን ተጠቅማ ፎቶዋን ብታሳምር፣ ሻዶው ብትጨምር፣ የቆዳ ቀለሟን ፈካ ብታደርግ እና ፊቷ ላይ ያለውን ብጉር ብታጠፋ የምታገኘው "like" እና "comment" ይበዛል። "...ቆንጆ፣ ስታምሪ፣ ከንፈርሽ፣ ፊትሽ..." ምናምን የሚሏት ሰዎች ይጨምራሉ። ግባችን የተወደደች፣ ሰዎች በውበቷ የሚቀኑባት፣ ከሌሎች ጓደኞቿ የተሻለ ተከታይ እና "social approval" ያላት ሴትን መፍጠር ነው። የሚያሳዝነው ልጅቷ ያንን ሁሉ "comment" እና "like" ያገኘችው እሷን ሆና አይደለም! የውሸት/የተጋነነ ማንነትን እንድትፈጥር አድርገናታል። ትክክለኛ መልኳን እና ማንነቷን እንድትጠላው አመቻችተናል! ለዛም ነው ብዙ ሴቶች ጭንቀት እና የአዕምሮ መታወክ የሚያጋጥማቸው። የሚለጥፉትን ፎቶ ለመምሰል ብዙ ሴቶች ቀዶ ጥገና እስከማድረግ ደርሰዋል!ማህበራዊ ሚድያዎች ዋነኛ አላማቸው የተጠቃሚዎችን "Social Media Engagement (ማህበራዊ ሚድያ ቆይታ)" ማሳደግ ነው። በአሁኑ ሰዓት ወደ 214 ሚልዮን የሚጠጉ ሰዎች የማህበራዊ ሚድያ ሱሰኞች ሆነዋል። የማህበራዊ ሚድያ ሱስ ከ "Cocaine" ሱስ ጋር አንድ ነው። የሰው ልጅ አዕምሮ ውስጥ "Dopamine" የሚባል የደስታ ስሜትን የሚረጭ ሆርሞን አለ! ሱሰኛ ሰዎች ሲጋራ፣ ኮኬይን ወይም ሌላ አደንዛዥ እፅን ሲያስቡ አዕምሮዋቸው "Dopamine" ይረጫል፣ ደስታ ይሰማቸዋል። ማህበራዊ ሚድያም እንደዛ ነው! ማህበራዊ ሚድያን ከፍተህ ለማየት እንድትንቀለቀል የሚያደርገህ ወደ ሰውነትህ የሚረጨው "dopamine" ነው! በአማካይ ሰዎች በቀን 2 ሰዓት ማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚጠቅማቸውንም የማይጠቅማቸውንም ነገር በማየት ግዜያቸውን ያጠፋሉ! ይህ ማለት ከአጠቃላይ እድሜያቸው ድፍን አምስት አመታትን ያባክናሉ ማለት ነው! አሁን ላይ ከሶስት ፍቺዎች ውስጥ አንዱ ከማህበራዊ ሚድያ ሱስ ጋር በተያያዘ ሆንዋል!...." እያሉ ይቀጥላሉ! ከዚህ በላይ ከቀጠልኩ ሙሉ ዶክመንተሪውን መጨረሴ ነው!😀

ማጠቃለያ!

ይህንን ሁሉ ካወሩ በኃላ እንደ መፍትሄ ከሚያስቀምጧቸው ሃሳቦች ውስጥ አንዱን ላስቀምጥ እና ልውጣ!

"Notification" የሚባል ነገርን "off" ማድረግ! በየደቂቃው ስልክህ ላይ "እንትና አዲስ ፅሁፍ ለጠፋ፣ እንትና አዲስ ፎቶ ለቀቀች፣ እገሌ እንዲህ ሆነ..." እያሉ "Notification" የሚልኩልህ ትኩረትህን ለመሳብ ነው። የቆይታ ግዜህን ለማሳደግ ነው። ያንተን "Algorithm" በደንብ ቀርጥፈው ስለበሉት ነው። አንተ ተቆጣጠራቸው እንጂ እነሱ እንዲቆጣጠሩህ አታድርግ! ማየት ስትፈልግ እራስህ ግባ እንጂ "Notification" አይቆስቁስህ!

ጌታዬ! ተጨማሪ መፍትሄዎቹን ማወቅ ከፈለክ ዶክመንተሪውን እይ! ትጠቀማለህ፣ ታተርፋለህ፣ ብዙ ነገር ትባንናለህ! በይበልጥ ማንበብ ከፈለክ እዛው ዶክመንተሪ ላይ ቃለ መጠይቅ ከሚደረግላቸው ሰዎች መካከል "Jaron Lanier" የሚባል ፀዴ ሰውዬ የፃፈው መነጋገርያ የሆነ "Ten Arguments for deleting your social Media accounts right now!"የሚል መፅሃፍ አለ! አንብበው! ከፈለክ እንደ ሁል ግዜው በውስጥ መስመር አቀብልሃለሁ!

መልካም ምሽት!🙏

✍️ወንድዬ እንግዳ

Big Habesha

@Senaytech
❤4
👍2
ቤተሰቦች እንደሚታወቀው የቲክቶክ አካውንት ከፍተናል እየገባችሁ Follow ምናምን አድርጉ እንጅ በጣም በሚገርም ስራ ተመልሰናል💪

https://www.tiktok.com/@senaytech1?_r=1&_t=ZS-990u0m15w99
❤1🙏1
በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 563 ሺ 960 ተማሪዎች ተመዝግበው 550 ሺ 210 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።

ፈተናውን ከወሰዱት ውስጥ 12.8 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ማምጣት ችለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ/ም

@Senaytech
ቴሌግራም ላይ ስልክ ቁጥርዎን ለመደበቅ እነዚህን ደረጃዎች ይከተሉ፦

• ቴሌግራምን ይክፈቱ።
• በታችኛው ጥግ ላይ የሚገኘውን የቅንብሮች Settings ምልክት ይንኩ።
• ከዛም "ግላዊነት እና ደህንነት" (Privacy and Security) የሚለውን ይምረጡ።
• በመቀጠል "ስልክ ቁጥር" (Phone Number) የሚለውን ይንኩ።
• እዚያ ስልክ ቁጥርዎን ማን ማየት እንደሚችል የሚገልጹ አማራጮች ያገኛሉ:
• "ሁሉም" (Everybody)፦ ሁሉም ሰው ስልክ ቁጥርዎን ማየት ይችላል።
• "የእኔ እውቂያዎች" (My Contacts)፦ በእውቂያ ዝርዝርዎ ውስጥ ያሉ ሰዎች ብቻ ማየት ይችላሉ።
• "የለም" (Nobody)፦ ማንም ስልክ ቁጥርዎን ማየት አይችልም።

ከነዚህ አማራጮች ውስጥ የሚፈልጉትን መምረጥ ይችላሉ።

video click here
👏2
📚 ያልተነበቡ ሚልዮን መፅሀፍት
🏞️ ያልታዩ ውብ ቦታዎች
🤝 ያልተዋወቅናቸው አስገራሚ ሰዎች
💪 ያልሰሩ ጡንቻዎች
🧠 ያልተማርናቸው በሺህ የሚቆጠሩ skills እያሉ
ድብርት የሚሰማን ከሆነ 😔
የተሻለ ኑሮ ለመኖር ሙከራ አላደርግህም ማለት ነው።

✍️ @Senaytech
💯3
አስገራሚ እና አስቂኝ የጎግል ባህሪያት እነሆ፡-

1. "Do a barrel roll": ይህን ሐረግ በጎግል ፍለጋ ውስጥ ሲጽፉ እና ሲፈልጉ፣ የፍለጋ ገጹ በአንድ ዙር ይሽከረከራል።
2. "Askew" or "Tilt": እነዚህን ቃላት በጎግል ፍለጋ ውስጥ ሲያስገቡ፣ የፍለጋ ውጤት ገጹ በትንሹ ወደ ጎን ያዘነብላል።
3."Super Mario Bros" ብላችሁ ብትፈልጉ፣ በቀኝ በኩል በሚመጣው መረጃ ላይ የሚበራና የሚጠፋ የጥያቄ ምልክት (?) ሳጥን አለ።ያንን ሳጥን ስትነካው ልክ እንደ ጨዋታው ሳንቲም እያወጣ ድምፅ ያሰማል። ።

#google
#tech_tips
👍2
የአፕል (Apple) ኩባንያ ታሪካዊ የሊደርሺፕ ለውጥ ይፋ ተደረገ!🍏🔥

የአፕል ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ (CEO) የሆኑት ቲም ኩክ (Tim Cook) ከሃላፊነታቸው ሊለቁ መሆኑን እና አዲሱ ተተኪያቸው ይፋ መደረጉን የአፕል ቦርድ በይፋ ተረጋግጧል።

ይህ ታሪካዊ ሽግግር በሚቀጥለው ሳምንት September 1, 2026 በይፋ ተግባራዊ ይሆናል።

ቲም ኩክ እ.ኤ.አ በ2011 ከስቲቭ ጆብስ ስልጣን ከተረከቡ በኋላ ኩባንያውን ለ15 ዓመታት በስኬት መርተዋል። ከCEOነታቸው ቢለቁም የአፕል የቦርድ ሊቀመንበር (Executive Chairman) በመሆን ስራቸውን ይቀጥላሉ።

በዚህም እስካሁን የአፕል የሃርድዌር ኢንጂነሪንግ ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ጆን ተርነስ (John Ternus) ሙሉ በሙሉ የCEOነቱን ቦታ ይረከባሉ።ጆን ከ2001 ጀምሮ በአፕል ውስጥ የቆዩ ሲሆን፣ ማክ (Mac) እና አይፎን (iPhone) ጨምሮ በርካታ ታዋቂ ምርቶችን በመስራት ትልቅ ሚና የነበራቸው አንጋፋ መሃንዲስ ናቸው።

Š @senaytech
👍2
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Meta_ኩባንያ

የፌስቡክ (Facebook) እና ኢንስታግራም (Instagram) እህት ኩባንያ የሆነው ሜታ (Meta) ከህፃናት እና ወጣቶች ደህንነት ጋር በተያያዘ የተመሰረተበትን ክስ ለመፍታት ግዙፍ የስምምነት ማዕቀፍ (Settlement Framework) ተቀብሏል።የዚህ ስምምነት ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦
ቢሊዮን ዶላሮች የሚደርስ የካሳ ክፍያ ኩባንያው በክሱ ምክንያት እስከ 18 ቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ሊከፍል የሚችልበት ስምምነት ላይ ደርሷል።አዳዲስ ጥብቅ ገደቦች፦ ወጣቶች እና ህጻናት ማህበራዊ ሚዲያዎችን ሲጠቀሙ ከጥቃት፣ ከሱስ እና ካልተገቡ ይዘቶች ለመጠበቅ ሜታ በመድረኮቹ ላይ እጅግ ጥብቅ የሆኑ የደህንነት ገደቦችን ለማስተካከል ተሰማምቷል።

የክሱ መነሻ ምክንያት ሜታ ታዳጊዎች በማህበራዊ ሚዲያ ሱስ እንዲያዙ በማድረግ እና የአእምሮ ጤናቸው ላይ ጉዳት በማድረስ በተለያዩ የዓለም ሀገራት (በተለይም በአሜሪካ ግዛቶች) ክስ ቀርቦበት የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

@Senaytech
🙏2
🚨 AI የሳይበር ስጋት፦ ከ100+ ተቋማት ማስጠንቀቂያ! 🤖⚠️
እ.ኤ.አ. ነሐሴ 2026 ከ100 በላይ ትልልቅ የቴክኖሎጂና የፋይናንስ ተቋማት — OpenAI, Anthropic, Google, Microsoft እና Amazon ጨምሮ — AI የሚመራቸው የሳይበር ጥቃቶች እየተወሳሰቡ በመምጣታቸው የጋራ እርምጃ ጠይቀዋል።
🔴 በቅርብ የተደረጉ ሙከራዎችም AI agents የሳይበር ጥቃት ኮድ መፍጠር፣ የተጋለጡ ሲስተሞችን መድረስ እና ሰዎችን ለማታለል የሐሰት ማንነት መጠቀም እንደሚችሉ አሳይተዋል።
⚠️ ስለዚህ ባለሙያዎች የAI ልማት ከሳይበር ደህንነት ጋር ተመጣጣኝ እንዲሆን አስቸኳይ የጋራ ስራ እንዲደረግ እየጠየቁ ነው።

#AI #CyberSecurity #TechNews #SenayTech

📌 @Senaytech
👍2
በየቀኑ ልትጠቀሟቸው የምትችሏቸው እና ስራችሁን የሚያቀሉ Websites:-

1. www.ilovepdf.com/
የ PDF ፋይሎችን በቀላሉ ለመስራት እና ለመቀየር የሚያስችል PDF tool ነው። pdf ወደ word, pdf ወደ power point, word ወደ pdf, pdf መጠን ለመቀነስ, ብዙ የ pdf ፋይሎችን አንድ ለማድረግ, pdf ላይ ለመፈረም ወዘተ እጅግ ጠቃሚ ነው።

2. www.canva.com/ Graphic design እና document creation ለማድረግ የሚያስችል platform ነው።Presentation, CV, Poster, Flyer, Logo, Social media post,
E-book, PDF, Certificate ለማዘጋጀት ይጠቅማል።

3. www.remove.bg/ ከፎቶ ላይ Background በAutomatic የሚያስወግድ AI-powered tool ነው ሲሆን Thumbnail designers፣ Poster designers፣ Online sellers በጣም ይጠቀሙበታል።

4. www.qr-code-generator.com/
Link፣ text ወይም ሌላ መረጃን ወደ Scan ወደ ሚደረግ QR Code የሚቀይር website ነው። Business, Restaurant menu, Telegram channel, Website, Event registration ወዘተ ለማጋራት በጣም ይጠቅማል።

5. www.photopea.com/ በBrowser ውስጥ የሚሰራ Advanced photo/image editor ነው። የ Photoshop ትንሽ ወንድም ልትሉት ትችላላችሁ፤ Photoshop የሚያውቅ ሰው ብዙ የሚተዋወቃቸውን tools ያገኛል።

ተጨማሪ ከፈለጋችሁ👍 ይደረግ።

@Senaytech
👍2