Senay Tech
356 subscribers
75 photos
23 videos
6 files
61 links
👉Owner @Senaymg

በዚህ የ Tech የቴሌግራም ቻናል
📱 #Android_Tricks
🚀 #Social_Media_secrets
📰 #Tech_News
🛠 #Useful_Apps
💡 #Quick_Tech_Tips በነፃ እናቀርባለን።
Download Telegram
22 ዓመታትን በፅናት ስትደግፉ ለነበራችሁ የአርሰናል ደጋፊዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!!
🏆6👍2👎1
🚨 የCell Broadcast ቴክኖሎጂ ምንድነው?

በአለም ዙሪያ የአየር ንብረት ለውጥ እና የተፈጥሮ አደጋዎች እየጨመሩ ባለበት በዚህ ወቅት፣ የድንገተኛ ጊዜ ማስጠንቀቂያዎች ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። ከእነዚህም ውስጥ አንዱ Cell Broadcast Service (CBS) የተባለው ቴክኖሎጂ ነው።

Cell Broadcast ምንድነው?
ይህ ቴክኖሎጂ በተወሰነ አካባቢ ላይ ለሚገኙ ስልኮች ሁሉ የድንገተኛ ጊዜ ማስጠንቀቂያዎችን በአንድ ጊዜ ለመላክ የሚያስችል ነው።

🌍 እንደ አውሎ ንፋስ፣ ከባድ ጎርፍ፣ የመሬት መንሸራተት፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ሱናሚ ወይም ሌሎች አስቸኳይ አደጋዎች ሲከሰቱ፣ በዚያ አካባቢ ያሉ ሰዎችን በፍጥነት ለማስጠንቀቅ ይጠቅማል።

💡 ዋና ጥቅሞቹ ምንድናቸው?
📶 ስልክዎ ኢንተርኔት ባይኖረውም መልዕክቱ ይደርሰዋል።
•መልዕክቱን ለመላክ የግል ስልክ ቁጥርዎ ወይም ስምዎ በፍጹም አያስፈልግም።
ፈጣንና ውጤታማ: በአጭር ጊዜ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በአንድ ጊዜ ማድረስ ይችላል።

አንድ የስልክ ቀፎ ሲም ካርድ እስካለው እና ከሞባይል ኔትወርክ ጋር እስከተገናኘ ድረስ፣ ኢንተርኔት ባይኖረውም በአቅራቢያው ካለ የስልክ ታወር (Cell Tower) ጋር በሬዲዮ ሲግናል መገናኘት ይችላል። የ Cell Broadcast ቴክኖሎጂም ይህንን ግንኙነት በመጠቀም፣ የአገልግሎት ሰጪው ድርጅት የጥንቃቄ መልዕክቶችን ወደዚያ ታወር ክልል ውስጥ ላሉ ስልኮች ሁሉ ያሰራጫል።

#CellBroadcast #ቴክኖሎጂ #tech_tips

https://t.me/Senaytech
👍5👏1
#ታላቅ_ቅናሽ (50%)

ለተለያዩ ስራዎች የግራፊክ ዲዛይን ማሰራት የምትፈልጉ ሰዎች 50% ቅናሽ አድርገናል።
Logo
YouTube thumbnail
Social media poster
Banner
Profile picture እንሰራለን።

🔥 ፈጣን አቅርቦት ተመጣጣኝ ዋጋ!

📩 Contact @Senaymg
5👍2
☎️☎️#ዳታ ስንጠቀም በጣም ዳታ ከሚበሉብን ነገሮች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው አንዳንድ #Applications እኛ ሳንፈቅድላቸው በራሳቸው Update ስለሚያደርጉ ነው።

ስለዚህ ዛሬ ይህን ችግር እንዴት አድርገን እንደምናስተካክል እናያለን:-

1.በመጀመሪያ #Playstore እንገባና ፕሮፋይላችን (profile) እንነካለን

2.በመቀጠል ትንሽ ዝቅ ካደርግን በኋላ seetings የሚለውን መንካት

3. network preference የሚለውን መንካት

4.auto apdate apps የሚል መንካት

5. ከዛም Over WiFi only ወይም don't auto update apps የሚለውን ነክታችሁ Done ማለት።

ይህ መሆኑ የሚጠቅማው አፕሊኬሽኖች ከናንተ ፈቃድ ዉጭ Update እንዳያደርጉ በማድረግ በ #wi-Fi ወይም በእናንተ ፈቃድ ብቻ Update እንዲሆኑ ይፈቅዳል።

ማንኛውም ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥያቄ ካላችሁ Comment አድርጉ።

@Senaytech
👍62
ሰላም ቤተሰብ እንዴት ናችሁ🖐️
ሰሞኑን ትንሽ በአንዳንድ ችግሮች ምክንያት ጠፍተን ነበር። አሁን በተሻለ እና በጥሩ ሁኔታ ተመልሰናል እስኪ ፍቅራችሁን በ 👍 ግለፁልኝ።
👍8
​​✳️ ሰላም Families ዛሬ ኢንተርኔት ስትጠቀሙ ካርድ መቆጠቢያ አጠቃቀም ምክሮች ይዘን መተናል፡

🔺የዳታ አጠቃቀምዎን ይገድቡ፡

◽️ Data usage limit፡ ሴቲንግ ዉስጥ በመግባት ሪስትሪክት ዳታን ይክፈቱት በተጨማሪም ዳታ ሮሚንግን አጥፍተው የማትጠቀሙባቸዉን አፕሊኬሽኖች አስወግዱ።

🔺አዉቶማቲክ አፕዴትን ይዝጉ፡

◽️ አንዳንድ አፕሊኬሽኖች ወይም ቀፎዎች ኢንተርኔት ኮኔክሽን ሲከፈትላቸዉ ወዲያዉ ራሳቸዉን አፕዴት ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ ስለዚህ Setting ዉስጥ በመግባት Automatic Updater Turn Off ያድጉ በተጨማሪም Wi-Fi እየተጠቀማችሁ ከሆነ የሞባይል ዳታችሁን ኦፍ አድርጉት።

🔺Background Data ማጥፋት፡

◽️ አንዳንድ አፕሊኬሽኖች ኢንተርኔት ኮኔክሽን ሲከፈትላቸዉ ወዲያዉ ስለራሳቸዉ መረጃ የሚሰጡ ኮኔክሽንኖችን ይልካሉ፡፡ ስለዚህ እነዚህን አፕሊኬሽኖች (የሚመጡ ኖቲፊኬሽኖችን ጫን ብሎ በመያዝ Turn off ያድርጉት፡፡

🔺ያልተላኩ ኢሜሎችን ማጥፋት፡

◽️ ለመላክ የተዘጋጁ (ድራፍት) የኢሜይል መረጃዎቻችሁን ወይ ላኩ ወይ አስወግዱ፡፡ ያለበለዚያ ኢንተርኔት ኮኔክሽን በተከፈተ ቁጥር እንቅስቃሴ ስሚያደርጉ ሳንቲም ይጨርሳሉ፡፡

🔺Online Streaming አለማድረግ፡

◽️ ኢንተርኔት ኮኔክሽን ላይ ሆናችሁ ሙዚቃ ፣ ቪዲዮችን ጌሞችን ኦንላየን የምትከታተሉ ከሆነ ወይም ከፍተኛ ሳንቲም ይጨርሳሉ፡፡

🔺የGPS እና መሰል አገልግሎቶችን መዝጋት፡

◽️ ያላችሁበትን አካባቢ መረጃ ፣ የአየር ንብረት እና ሌሎች ሁኔታዎችን ኢንተርኔት ኮኔክሽን ሲከፈትላቸዉ ወዲያዉ መረጃ መስጠት ይጀምራሉ፡፡ ስለዚህ ሴቲንግ ዉስጥ በመግባት Turn Off ያድርጉት።

🔺የኢሜይል ሴቲንግ ማስተካከል፡

አዳዲስ የሚመጡ ኤሜሎችን በየስንት ደቂቃ ኢንተርቫል እንደሚያሳውቃችሁ አስተካክሉለት። ሲንክሮናይዝ የሚደረግበት የጊዜ ምጣኔ ማለት ነዉ፡፡ ኤሜይል ሴቲንግ ዉስጥ በመግባት Synchronizing Schedule interval በየስንት ደቂቃ ኢንተርቫል እንደሚያሳውቃችሁ አስተካክሉለት።

🔺Hotspots and tethering መጠንቀቅ፡

◽️ እናንተ ለራሳችሁ ኢንተርኔት ኮኔክሽን ከፍታችሁ በምትጠቀሙ ሰአት ከአቅራቢችሁ ያለሰዉ በእናንተ ኢንተርኔት ኮኔክሽን ሊጠቀም ይችላል፡፡ ወይም በኬብል ከላፕቶፕ ጋር ተገናኝቶ ከሆነ ላፕቶፑ ራሱን Update ማድረግ ይጀምራል ስለዚህ ሴቲንግ ዉስጥ በመግባት Turn Off ያርጉት።
👍4
"አእምሮህ ሲደክምህ ስራህን አታቁም፤ ስራህን የምታቆመው ሙሉ በሙሉ ስትጨርስ ብቻ ነው።" ዴቪድ ጎጊንስ (David Goggins)

keep going your journey 💪
👏3💯1
✳️ የስልካችሁ ባትሪ ለምን እንደ ሚሞቅ (እንደሚያብጥ) ታውቃላችሁ

🔺 Litium-ion ባትሪዎች ሀይል ለማመንጨት Chemical Reaction ይጠቀማሉ። የባትሪያችን እድሜ እየቆየ ሲሄድ ይሄ Chemical Reaction በትክክል አይካሄድም ይህም ጋዝ ይፈጥርና ባትሪያችን እንዲያብጥ ያደርገዋል።

🔺በተጨማሪ ባትሪያችን ጉዳት ሲደርስበት የባትሪውን የዉስጠኛ Layer በትክክል መለያየት አይችልም፤ በዚህ ጊዜ ጋዝ ማዉጣት፣ ማበጥ እንዲሁም መፈንዳት ይከሰታል።

🔷ባትሪያችን እንዳይሞቅ ወይም እንዳያብጥ ማድረግ ያለብን ጥንቃቄ!

🔺ባትሪያችን እንዳያብጥ ለረጅም ጊዜ ቻርጅ ሳናደርገዉ መቆየት የለብንም ምክንያቱንም ባትሪዉ ለረጅም ጊዜ ቻርጅ ካልተደረገ ጋዝ እንዲፈጠር ያደርጋል።

🔺ባትሪያችንን ለከፍተኛ ሙቀት ማጋለጥና ከመጠን በላይ ቻርጅ ማድረግ የለብንም።

🔺ጥራት ያለው ቻርጀር መግዛት (ስልኮን ሁል ጊዜ ከስልኩ ጋር አብሮ በመጣዉ ቻርጀር ቻርጅ ቢያደርጉ ይመረጣል)።

🔺Internet ብዙ አለመጠቀም ዳታ ባበራን ቁጥር ስልካችን እየጋለ ነው የሚሄደው ይህ ደሞ ባትሪያችንን ከጥቅም ውጪ ያደርገዋል በተቻለ መጠን ሁል ጊዜ ዳታን አለማብራት።

🔺ቻርጀር ሰክቶ በፍፁም አለ መጠቀም፤ ባትሪውን ከመበላሸት አልፎ ስልኩን ሊፈነዳ ሁላ ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ አለብን።
2
ሰዎች ቲክቶክ ወይም ኢንስታግራም ላይ የሚለጥፉት የህይወታቸውን 1% ምርጥ፣ ያማረ እና የተደላደለ ክፍል ብቻ ነው። ማንም ሰው ተስፋ የቆረጠበትን፣ ሌሊት ተነስቶ ሲያጠና ያነባውን፣ ወይም ስራው አልሳካ ብሎት ሲጨነቅ የነበረበትን ክፍል አይለጥፍም። በዚህ የተነሳ ወጣቶች "የሁሉም ህይወት ተስተካክሏል፣ እኔ ብቻ ነኝ struggle የማደርገው" ብለው የሌለ ውጥረት ውስጥ ይገባሉ።

አሁን ያለህበት ህመም ፈተና እና ትግል ነገ ለሚወለደው ስኬት የሚሆን ምጥ እንጂ የህይወትህ መጨረሻ አይደለም።

keep going my brother 💪
👏5
🔴 የቪዲዮ አፍቃሪያን ኔትፍሊክስ (Netflix) የነፃ መሞከሪያ ቀናትን በድጋሚ መመለሱ ተሰማ! 🎬

ኔትፍሊክስ ከዚህ ቀደም አቁሞት የነበረውን የነፃ መሞከሪያ ጊዜ (Free Trials) በድጋሚ መስጠት ጀምሯል።
💡 ይህን እድል እንደ ተጠቃሚው ሁኔታ እና እንደ አጋጣሚው ከ 7 እስከ 30 ቀናት የሚቆይ የነፃ እድል ማግኘት ይቻላል።

በጣም ውድ የሆነውን የ 4K HDR Premium ፕላን ጭምር መርጣችሁ በነፃ መሞከር ትችላላችሁ።
ነገር ግን ይህ እድል በአሜሪካ (US) እና በዩናይትድ ኪንግደም (UK) አይሰራም።

⚠️ 1. እድሉን ለመጠቀም ከዚህ ቀደም በኔትፍሊክስ ላይ ተመዝግቦ የማያውቅ አዲስ የኢሜይል አድራሻ መጠቀም ያስፈልጋል።
2. እንዲሁም ለመመዝገብ የቪዛ (Visa) ወይም ማስተርካርድ መረጃ ማስገባት ግድ ነው።


የነፃ ሙከራው ጊዜ ሲያበቃ ኔትፍሊክስ በራሱ ጊዜ ከካርድዎ ላይ ብር መቁረጥ ይጀምራል። ስለዚህ ምንም ክፍያ እንዳይቆርጥባችሁ የነፃ ቀናቱ ሳያልቁ በፊት አካውንታችሁ ውስጥ ገብታችሁ Subscription መሰረዝ (Cancel ማድረግ) እንዳትረሱ!
ካንስል ብታደርጉት እንኳ የነፃ ቀናቱ እስኪያልቁ ድረስ ማየት ትችላላችሁ።

💡 ተጨማሪ ቲፕ
የ30 ቀኑን ሙሉ የነፃ እድል የማግኘት ዕድላችሁን ከፍ ለማድረግ፣ በስልካችሁ ወይም በኮምፒውተራችሁ ላይ Incognito (Private) Window ከፍታችሁ ለመመዝገብ ሞክሩ።

💬 ለጓደኞቻችሁ Share አድርጉላቸው!

https://t.me/Senaytech
👍31
2026 CREATOR ECONOMY SURVEY Midia

የተሰኘ ድርጅት ማህበራዊ ሚዲያን በተመለከተ አስገራሚ ጥናት አውጥቷል።

ጥናቱ ስለ creator economy በዝርዝር የሚያስረዳ ሲሆን በትልልቅ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያለውን የፆታና የዕድሜ ክፍፍል በቁጥር አስደግፎ አውጥቷል።

አብዛኛው ፕላትፎርሞች ላይ ከወንድ ተጠቃሚዎች ይልቅ የሴት ተጠቃሚዎች ቁጥር የሚበልጥ ሲሆን ብቸኛው የወንድ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከሴቶች የበለጠበት ፕላትፎርም YouTube ሆኗል።

Instagram = 44.2% ወንዶች, 55.8% ሴቶች
TikTok = 35.1% ወንዶች, 64.9% ሴቶች
YouTube = 54.4% ወንዶች, 45.5% ሴቶች

እስከዚህ አመት መጨረሻ 2026
ትልልቅ ማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞች ያላቸው የfollowerና የsubscriber መጠን
ከ10K Followers በታች
Instagram = 82%
TikTok = 72.4%
YouTube = 64.8%

ከ10K - 50K Followers
Instagram = 13%
TikTok = 19.1%
YouTube = 20.1%

በጥናቱ መሰረት ከአጠቃላይ ተጠቃሚዎች ውስጥ ከ50ሺ በታች የfollower ቁጥር ያላቸው
Instagram = 95%
TikTok = 91.5%
YouTube = 84.9%

ጥናቱ ላይ እንደተገለፀው ከ10ሺ በታች follower ያላቸው አካውንቶች ከፍተኛ የሆነ ውድድር (competition) የሚገጥማቸው ሲሆን የfollower መጠናቸው ከፍ እያለ ሲሄድ ግን ይሄ ውድድር እንደሚቀን ያትታል።
4👍1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍3
Forwarded from Senay Wisdom
አሰባችሁታል ግን!

እስከዛሬ ድረስ መስራት እና መጀመር የፈለጋችሁትን ማንኛውም ነገር ያለምንም ይሉኝታ እና ፍራት ብትሰሩ የት ትደርሱ እንደነበር?🤔
👍32
#ethiotelecom 🎁

ኢትዮ ቴሌኮም ለ2 ቀን የሚቆይ ነጻ የዳታ , የድምፅ እና የመልእክት ስጦታ ለሁሉም ተጠቃሚ አበርክቷል ።

ስጦታው :- 1.5GB ዳታ : 15 ደቂቃ የድምፅ እና 30 የመልእክት (SMS) : ለቴሌብር ሱፐርአፕ ተጠቃሚዎች ተጨማሪ 500 ሜ.ባ እና ለ ያልተገደበ ጥቅል ተጠቃሚ ደምበኞች 10 ደቂቃ ነፃ ዓለም አቀፍ ጥሪ ያበረከተ ሲሆን ከሀምሌ 17-19 ከሌሊት 6:00 እስከ ምሽት 12:00 ድረስ ይቆያል ።

ይህንን ይፋ ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ሲሆኑ የ2018 በጀት አመት ሪፖርት ባቀረቡብት ወቅት ነው።

@Senaytech


#ethiotelecom #telebirr
👍31
#OpenAI

በደኅንነት ፍተሻ ወቅት የAI ሞዴል ከሙከራ ገደቡ አምልጦ በሌላ የAI ተቋም ላይ የሳይበር ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ።

የChatGPT አምራች የሆነው OpenAI እጅግ የላቁ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴሎቹ በደኅንነት ፍተሻ ወቅት ያልተጠበቀ ባህሪ በማሳየት ሌላ የAI ተቋም የሳይበር ጥቃት መፈጸማቸውን (ሀክ ማድረጋቸውን) ይፋ አድርጓል።

ኩባንያው እንደገለጸው፣ የሰው ልጅ መመሪያ ከሰጠው በኋላ ብቻውን ሊሠራ የሚችል የAI ሥርዓት ቁጥጥር በሚደረግበት አካባቢ ፍተሻ እየተደረገለት ሳለ ድክመቶችን በማግኘቱ ከሙከራ ገደቦቹ ማምለጥ ችሏል።

ጥቃቱ የደረሰው በዓለም ላይ ካሉት ትላልቅ የሰው ሠራሽ (AI) ሞዴሎች አምራች በሆነው Hugging Face ላይ ሲሆን የኮምፒውተር ሥርዓቱ ውስጥ ዘልቀው መግባት መቻላቸው ተነግሯል።

OpenAI ክስተቱ " ከዚህ በፊት ያልታየ " መሆኑን ገልጾ፣ ከHugging Face ጋር በመተባበር ምርመራ እያካሄደ መሆኑን አስታውቋል።

የHugging Face ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክሌመንት ዴላንጌም "ይህ ሁሉ በራሱ መከሰቱ በጣም አስደንጋጭ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

በሳይበር ደኅንነት ዘርፍ የሚሰሩ ባለሙያዎች ይህ ክስተት የAI አቅም በፍጥነት እየጨመረ በመምጣቱ አሁን ያሉት የደኅንነት መከላከያዎች በቂ ስለመሆናቸው አዲስ ጥያቄዎችን እንዳስነሳ ይገልጻሉ።

የSonicWall ሥራ አስፈጻሚ ስፔንሰር ስታርኪ፣ ድርጅቶች የሳይበር መከላከያቸውን ማጠናከርና ለዚህ ዘርፍ ቅድሚያ መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ክስተቱ የላቁ የAI ሥርዓቶች እየተሻሻሉ በሚሄዱበት ወቅት የደኅንነት መስፈርቶችንና የቁጥጥር ሥርዓቶችን የበለጠ ማጠናከር እንዳለባቸው የሚያሳይ አዲስ ውይይት ማስነሳቱን #ቢቢሲ ዘግቧል።

Source: tikvahethiopia
3🔥1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዩቲዩብ የምትሰሩ ወይም መስራት የምትፈልጉ ሰዎች ዩቲዩብ ላይ አንድ ቪድዮ እንዴት ነው viral የሚሆነው? viral ለመሆንስ ምን ምን ያስፈልጋል የሚለውን በዝርዝር ልፃፍላችሁ?
👍51
Senay Tech
Photo
🚀 ዩቲዩብ ላይ ብዙ እይታ (View) ማግኘት እና አሪፍ ገንዘብ መስራት የሚቻለው እንዴት ነው?
👉 ስለ ዩቲዩብ ካነሳን በዩቲዩብ ስለምናገኘው ዶላር፣ ስለ ዶላር ካነሳን ደግሞ ስለ ቪዲዮ እይታ (View) ማንሳታችን አይቀርም፤ ምክንያቱም ዩቲዩብ የሚከፍለው በአንድ ቪዲዮ በምናገኘው እይታ ልክ ስለሆነ ነው።
🧠 ዛሬ ዩቲዩብ አንድን ቪዲዮ እንዴት Viral እንደሚያወጣው ወይም ለብዙ ሺህ ሰዎች በነፃ "Push" እንደሚያደርገው በግልጽ እና በቀላል ቋንቋ እንያለን።
🤔 ብዙ ሰዎች "ዩቲዩብ የእኔን ቪዲዮ አልወደደውም" ምናምን ሲሉ ይሰማሉ፤ ነገር ግን ዩቲዩብ አንድ ቪዲዮ ጥሩ ይሁን አይሁን፣ ጠቃሚ ይሁን ጎጂ በጭራሽ አያውቅም! ዩቲዩብ ማሽን ነው። እሱ የቪዲዮአችሁን ጥራት የሚያውቀው ሰዎች ለቪዲዮአችሁ በሚሰጡት ግብረ-መልስ (Behavior) ብቻ ነው።

ባጭሩ ዩቲዩብ አንድን ቪዲዮ ቪው የሚያበዛው በዕድል ሳይሆን በሰዎች ባህሪ ላይ በተመሰረተ ሒሳባዊ ቀመር (Algorithm) ነው።
👀 አልጎሪዝሙ ለአንድ ቪዲዮ አረንጓዴ መብራት አብርቶ ለሚሊዮን ሰዎች እንዲደርስ የሚያደርግበትን 4ቱን ታላላቅ ምስጢሮች በጥንቃቄ ተከታተሉኝ፦
1️⃣ CTR (Click-Through Rate)፦ ሰዎች ቪዲዮአችሁን ነክተው እንዲገቡ ማድረግ

​ይህ ማለት ዩቲዩብ የእናንተን ቪዲዮ ለ 100 ሰዎች በስክሪናቸው ላይ በ"ማስታወቂያ" መልክ ቢያሳያቸው፣ ከነሱ ውስጥ ስንት ሰው ነክቶት ገባ? የሚለው ስሌት ነው። ለምሳሌ ከ 100 ሰው 10 ሰው ቢያየው፣ CTR 10% ነው ማለት ነው።
​የባለሙያ ምክር፦ የምትሰሩት ቪዲዮ CTR ቢያንስ 6% ወይም 7% እና ከዚያ በላይ ቢሆን ይመከራል። 10% ማድረስ ከቻላችሁ ግን በእርግጠኝነት ቪዲዮአችሁ ፍንዳታ (Viral) ይሆናል!

CTR ከፍ እንዲል የሚያደርጉት 2ቱ ቁልፎች ምንድን ናቸው?

📸 ተምኔል (Thumbnail)፦ ይህ ብዙ ሰዎች ላይ በተደጋጋሚ የማየውና ሁልጊዜ "አስተካክሉ" እያልኩ ስለፈልፍበት የነበረው ጉዳይ ነው! ቆም ብላችሁ አስቡት፤ አንድ የማታውቁት ከተማ በአጋጣሚ ገብታችሁ ቡና መጠጣት ብትፈልጉ፣ የትኛውን ካፌ ትመርጣላችሁ? በእርግጠኝነት ከበር ላይ የስኒ ቡና ሥዕል ወይም "እከሌ ቡና ቤት" የሚል ማራኪ ጽሑፍ ያለበትን ነው። ተምኔል ማለት የቪዲዮአችሁ የበር ላይ ሥዕል ነው! ሰው ሳያየው የሚስብ ሳቢ ተምኔል መሥራት ቸል የማይባል ታላቅ ሥራ ነው።

✍️ ርዕስ (Title)፦ ለቪዲዮአችሁ የምትሰጡት ርዕስ አጭር፣ ግልጽና ስሜት ቀስቃሽ መሆን አለበት። ለምሳሌ በደፈናው "የምግብ አሰራር" ከማለት ይልቅ "በ 20 ደቂቃ ብቻ ጣፋጭ የሩዝ ምግብ አሰራር" ማለት ይበልጥ አጓጊ ያደርገዋል። (ከ 60 ፊደላት ባይበልጥ ይመረጣል፤ ምክንያቱም ዩቲዩብ ስለሚቆርጠው)።

2️⃣ AVD (Average View Duration)፦ ሰዎችን ከፍቶ ይዞ መቆየት
​ይህ ለአልጎሪዝሙ ትልቁና ዋናው መለኪያ ነው። አንድ 15 ደቂቃ የሚረዝም ቪዲዮ ሰርታችሁ ብትጭኑት፣ ሰዎች በአማካይ ምን ያህል ደቂቃ አብረውት ቆዩ የሚለው ነው።
​ከቪዲዮው ርዝመት ከ50% (ግማሽ) እና ከዚያ በላይ (ለምሳሌ 7-8 ደቂቃ) ካዩላችሁ፣ ዩቲዩብ "ይህ ቪዲዮ ወርቅ ነው" ብሎ ለብዙ ሺህ አዳዲስ ሰዎች ያሰራጨዋል። ስለዚህ ተመልካች እንዳይሰለች ጥራትና ጠቃሚነቱን ጠብቁ።

3️⃣ የመጀመሪያዎቹ 15 ሰከንዶች (The Hook)
​አንድ ሰው ቪዲዮአችሁን ነክቶ ከገባ በኋላ፣ እስከ 15 ሰከንድ ባለው ጊዜ ውስጥ ቪዲዮውን መተው ወይም አለመተውን ይወስናል።

⚠️ ትልቅ ስህተት፦ ቪዲዮ ስትጀምሩ "ሰላም ናችሁ? እንዴት ናችሁ? እከሌ እባላለሁ፣ ሰብስክራይብ አድርጉ..." የሚሉ የተንዛዙ ንግግሮችን በፍጹም አስወግዱ! አንድ የማያውቃችሁ ሰው የሚፈልገው የእናንተን ሰላምታ ሳይሆን፣ በቪዲዮው በርዕሱ ላይ ያየውን ጥቅምና ይዘት ነው። መጀመሪያው አሰልቺ ከሆነ ወዲያው ይወጣል፤ ዩቲዩብም ቪዲዮውን መግፋቱን ያቆማል።

4️⃣ የሰዎች ተሳትፎ (Engagement)
​ይህ ደግሞ አልጎሪዝሙ ተመልካቾች በቪዲዮው ላይ ያላቸውን ንቁ ተሳትፎ ማለትም Comment, Like እና Share የሚገመግምበት ነው።
​የብልህ ስልት፦ ሁልጊዜም ቪዲዮ ስትሰሩ "የእናንተ ሐሳብ ምንድን ነው?"፣ "እናንተ በኔ ቦታ ብትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?" እያላችሁ ጥያቄ ጠይቁ፤ ኮሜንት እንዲጽፉ በቅንነት አበረታቱ።

⚠️ አደራችሁን! ይህንን ጽሑፍ ለእናንተ ለማዘጋጀት በጣም ብዙ ጊዜ ወስጄና ደክሜበት ነው የጻፍኩት። በደንብ አንብባችሁ በተግባር ካደረጋችሁት በእርግጠኝነት በአጭር ጊዜ ውጤታማ መሆናችሁ አይቀሬ ነው!
​በዚህ ዙሪያ ያላችሁን ሐሳብ ኮሜንት ላይ አጋሩኝ። ይመቻችሁ! ✌️🔥

@Senaytech
👏4
ጥራት ወይስ ብዛት?

አንድ ጊዜ የስነ ልቦና ባለሙያዎች
​የሸክላ ተማሪዎችን ለሁለት ቦታ ከፈሏቸው። የመጀመሪያዎቹን "በቀጣይ ወር 1 ምርጥ ጥራት ያለው ሸክላ ስሩ" ብለው አዘዟቸው። ሁለተኛዎቹን ተማሪዎች ደግሞ "በቀጣይ ወር በብዛት 50 ኪሎ ግራም የሚመዝን ሸክላ ስሩ" አሏቸው።
በወሩ መጨረሻ ላይ እጅግ አሪፍ እና ጥራት ያለው ሸክላ የሰሩት በብዛት እንዲሰሩ የተነገራቸው ተማሪዎች ነበሩ!

ምክንያቱም በየቀኑ ሲሰሩ ሲያበላሹ መለሰው ሲያስተክክሉ እና ሲደጋግሙት እና ጥራቱ በራሱ ጊዜ መጣ።

መስራት የምትፈልጉትን ነገር አልችለውም, ሙሉ አይደለሁም ወዘተ እያላችሁ ጊዜያችሁትን አታባክኑ፤ ብዛት ጥራትን ይወልዳል።

✍️ @Senaywisdom
👏32
Google ብዙ የማናውቃቸውና ሚስጢራዊ የመረጃ መፈለጊያ ዘዴውች ያሉት ሲሆን ከነዚህ መካከል የተወሰኑትን ላካፍላችሁ።

8️⃣. Weather Forecast: የፈለጋችሁትን አካባቢ የአየር ንብረት ትንበያ ማዎቅ ከፈለጋችሁ "weather [city]" ብላችሁ መፃፍ ትችላላችሁ። ለምሳሌ weather Addis ababa
9️⃣. Calculator: ቀለል ያሉ የሂሳብ ጥያቄዎችን መስራት ከፈለጋችሁ ጉግልን መጠየቅ ትችላላችሁ። ለምሳሌ "8 * (5 + 2)" ይህን መፈለጊያው ላይ ብታስገቡ መልሱን ቀጥታ ታገኛላችሁ።
🔟. Related Sites: ከአንድ ድረገፅ ተመሳሳይ ስራ የሚሰራ ሌላ ድረገፅ ከፈለግን ከምናውቀው ድረገፅ በፊት related የሚል ቃል መጨመር እንችላለን። ለምሳሌ "related:wikihow.com" ከwikihow ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ድረገፆች ይዘረዝርልናል።
1️⃣1️⃣. Advanced search: Google home page ላይ settings የሚለውን ነክተን advanced search የሚለውን ከመረጥን ዝርዝር ሰርች ማድረጊያ ገፅ ይከፍትልናል።

ሌሎችም የቻናሉ ቤተሰብ እንዲሆኑ ሼር አድርጉ👇
https://t.me/Senaytech
1🔥1