Senay Tech
356 subscribers
75 photos
23 videos
6 files
61 links
👉Owner @Senaymg

በዚህ የ Tech የቴሌግራም ቻናል
📱 #Android_Tricks
🚀 #Social_Media_secrets
📰 #Tech_News
🛠 #Useful_Apps
💡 #Quick_Tech_Tips በነፃ እናቀርባለን።
Download Telegram
በሀረር፣ ጅግጅጋ እና ሌሎች የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች ኃይል ተቋረጠ

በሀረር፣ ጅግጅጋ እና ሌሎች የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡

ከድሬዳዋ ቁጥር ሁለት - ሀረር- ጅግጅጋ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ባልታወቀ ምክንያት ኃይል ማስተላለፍ ማቋረጡን የምስራቅ አንድ ሪጅን የኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች መምሪያ ገልጿል።

የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ወርዲ መሐመድ፤ በተከሰተው ችግር ምክንያት በሀረር፣ ጅግጅጋ እና በሌሎች የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች ኃይል ተቋርጧል ብለዋል።

ችግሩን ለመለየት ፍተሻ መጀመሩን የተናገሩት ዳይሬክተሩ፤ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩን በመጠገን አገልግሎቱን ዳግም ለማስቀጠል ይሰራል ማለታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ ያመለክታል።

@senaytech
#senaytech
#technews
👍5🔥42👏1
በጣም የምትወዱት social Media የቱ ነው?
Anonymous Poll
5%
Facebook
18%
YouTube
28%
TikTok
49%
Telegram
👍1
ሞባይል ስልካችሁ በጣም እየተንቀራፈፈ ወይም Busy እየሆነ ከተቸገራችሁ የሚከተሉትን ስቴፖች በመከተል የስልካችሁን ፍጥነት ማሻሻል ይቻላል።

1ኛ፦ የሞባይላችሁ setting ውስጥ ትገባላችሁ፣

2ኛ፦ በመቀጠል Developer option የሚል አለ እሱን ክሊክ ማድረግ። ነገር ግን አንዳንድ ስልኮች ላይ developer option በቀጥታ ስለማናገኘው setting ውስጥ ከገባን በኋላ build number ብለን ሰርች እናደርጋለን ከዛ build number የሚለውን ደጋግመን(ከ6-8 ግዜ) ስንነካው developer option ይመጣልናል።

3ኛ፦ በመቀጠልም developer option ውስጥ በመግባት፦

   3.1 window animation scale

    3.2 transition animation scale እና

    3.3 animation duration scale

የሚሉ ምርጫዎች ታገኛላችሁ።እነዚህ 3ቱንም በየተራ ክሊክ እያደረጋችሁ OFF አድርጓቸው።

አሁን የስልካችሁ ፍጥነት በ አራት እጥፍ ያድጋል ማለት ነው።


ይህ መረጃ ለብዙዎች Share ማድረግ አይረሳ
#senaytech
#Tech_news
#How_to
👍73👏3🔥2🥰1😁1
እንዳቀርብላችሁ የምትፈልጉትን ማንኛውም የቴክኖሎጂ ሓሳብ ካላችሁ
👇👇👇
Comment አድርጉ
#Senaytech
👍6🔥43👏1
👍1
📞☎️☎️☎️☎️📞📞

የስማርትፎን ባትሪ አጠቃቀምን ለማሻሻል እና ባትሪው በፍጥነት እንዳያልቅ ለመከላከል ብዙ መንገዶች አሉ። ከእነዚህም እነሆ፦

1. ማያ ገፅ ብሩህነት (Brightness) መቀነስ፡- ከፍተኛ ብሩህነት ( Brithness)ባትሪ በፍጥነት እንዲበላ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል። የማያ ገጽ ብሩህነትን በተቻለ መጠን ዝቅ ማድረግ ባትሪውን ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ ይረዳል። ስለዚህ Brittnes ን መቀነስ ባትሪ በፍጥነት እንዳያልቅ ከሚረዱ ነገሮች ውስጥ ዋነኛው ነው።

2. የማያ ገጽ ጊዜ ማሳጠር (Screen Timeout): ስልኩ ለተወሰነ ጊዜ እንቅስቃሴ ከሌለው በራስ-ሰር እንዲጠፋ ማድረግ ባትሪ ይቆጥባል። የማያ ገጽ ጊዜን ወደ 15 ሰከንድ ወይም 30 ሰከንድ ማስቀመጥ ሌላው ባትሪያችን በፍጥነት እንዳያልቅ ከሚረዱ ነገሮች ውስጥ ሌለኛው ዘዴ ነው።

3. ቦታ (Location) አገልግሎቶችን ማጥፋት (off) ማድረግ፡- GPS እና ሌሎች የቦታ አገልግሎቶች ባትሪ በብዛት ይበላሉ። እነዚህን አገልግሎቶች በማይፈልጉበት ጊዜ ማሰናከል ይመከራል። አፕሊኬሽኖች ቦታ እንዲጠቀሙ ፈቃድ ከሰጡ ለጊዜው የማይጠቀመባቸውን መተግበሪያዎች ማሰናከል ይቻላል።

4. ዳታ (Data) አጠቃቀምን መቀነስ፡- ከፍተኛ የዳታ አጠቃቀም ባትሪ ይበላል። በማይፈልጉበት ጊዜ ዳታ ማሰናከል ወይም የዳታ አጠቃቀምን መቀነስ ይመከራል። የዳታ አጠቃቀምን ለመቀነስ የዳታ ሴቭ አማራጭን መጠቀም ይችላሉ።

5. ብሉቱዝ (Bluetooth) እና ዋይፋይ (Wi-Fi) ማሰናከል፡- እነዚህ አገልግሎቶች በማይፈለጉበት ጊዜ ማሰናከል ባትሪ ይቆጥባል።

6. አላስፈላጊ አፕሊኬሽኖችን ማራገፍ (Uninstall): ብዙ አፕሊኬሽኖች በስር አደራ ይሰራሉ ​​እና ባትሪ ይበላሉ። አላስፈላጊ አፕሊኬሽኖችን ማራገፍ ባትሪ ይቆጥባል።

7. ዳራ ላይ የሚሰሩ አፕሊኬሽኖችን መገደብ (Limit Background Apps): አንዳንድ አፕሊኬሽኖች ዳራ ላይ እንኳን ይሰራሉ ​​እና ባትሪ ይበላሉ። እነዚህን አፕሊኬሽኖች መገደብ ባትሪ ይቆጥባል።

8. አውቶማቲክ ማዘመን (Automatic Updates) ማሰናከል: አፕሊኬሽኖችን እና ስርዓተ ክወናውን በራስ-ሰር ማዘመን ባትሪ ይበላል። በWi-Fi ላይ ብቻ ማዘመን ወይም በእጅ ማዘመን ይመከራል።

9. የባትሪ ማስተካከያ (Battery Optimization): አብዛኛዎቹ አንድሮይድ ስልኮች የባትሪ ማስተካከያ አማራጭ አላቸው። ይህ አማራጭ ባትሪውን ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ ይረዳል።

10. ስልኩን እንደገና ማስነሳት (Restart): ስልኩን እንደገና ማስነሳት በስር አደራ የሚሰሩ አፕሊኬሽኖችን ያስቀምጣል እና ባትሪውን እንዲቆጥብ ይረዳል።


እነዚህ ምክሮች ባትሪህን ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ ይረዳሉ። ነገር ግን፣ በጣም አስፈላጊው ምክር አላስፈላጊ አፕሊኬሽኖችን ማራገፍ እና ዳራ ላይ የሚሰሩ አፕሊኬሽኖችን መገደብ ነው።

#senaytech
#android
#how_to
#application
4🔥2👍1🥰1👏1
የ14 ዓመት ታዳጊ መገደሉን ተከትሎ አልባንያ ቲክቶክን ለዓመት ልታግድ ነው

የ14 ዓመት ታዳጊ በስለት ተወግቶ መገደሉን ተከትሎ አልባንያ ለአንድ ዓመት ቲክቶክን እንደምታግድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ።

ባለፈው ወር ታዳጊው ከተገደለ በኋላ ማኅበራዊ ሚዲያ ልጆች ላይ የሚያሳድረው ጫና ስጋት ፈጥሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኤዲ ራማ እንዳሉት ቲክቶክ ለአንድ ዓመት ይታገዳል ብለዋል።

ይሁን እንጂ የ14 ዓመቱን ታዳጊ የገደለው ሰውም ይሁን ታዳጊው ቲክቶክ እንዳላቸው ማረጋገጫ እንዳልተገኘ ቲክቶክ ለቢቢሲ ገልጿል።
በአልባንያ መዲና ቲራና መምህራን፣ ወላጆችና የሥነ ልቦና ባለሙያዎች በተገኙበት ውይይት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቲክቶክ "የሰፈር ወሮበላ ነው" ነው ብለዋል።
"ለአንድ ዓመት ቲክቶክ እናግዳለን። ወላጆች የልጆቻቸውን የትምህርት ዕድገት የሚከታተሉበት አሠራር እንዘረጋለን" ሲሉም አክለዋል።

ፀቡ የተጀመረው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ነውም ተብሏል።

Source:BBC news
#senaytech
#tech_news
#tiktok
5👍3🔥1
☎️☎️ ✌️ #ቲክቶክ ላይ ያለምንም Watermark ወይም ያለ ምንም የቲክቶክ ምልክት እንዴት አድርገን Vidio ማውረድ እንደምንችል ታውቃላችሁ?

በመጀመሪያ ማውረድ የምትፈልጉትን የተክቶክ ቪዲዮ የShare➡️ ምልክት በመንካት Copylink ማድረግ።

በመቀጠል google በመግባት Snaptik ብላችሁ ሰርች ማድረግ ከዛም Copylink ያደረገችሁትን ቪዲዮ Paste በማድረግ ቪድዮውን DownloUd አድርጉት።

አሁን ያለምንም የቲክቶክ ምልክት ቪዲዮውን ያወርድላችኋል ማለት ነው።
#Tiktok
#tech_news
#senay_tech
5🔥2🥰1👏1
☎️☎️ 5 free apps all students should download in 2025:

1️⃣ Evernote: Evernote can help students who want to keep their notes organized.

You can create separate notebooks for different classes, save web pages for research, capture images, and even attach important documents, all of which can be accessed easily from any device.
2️⃣My study: Staying organized is key to your success in college, and that's where MyStudyLife comes into play.
3️⃣ Quizlet: This app allows you to create personalized flashcards and study sets, making it easier to remember important course information.
4️⃣Mathway:If you're taking a math class, Mathway can help! By simply inserting the math problem into the app or scanning it with your camera, Mathway will solve it and show you exactly how it did it. From basic math to linear algebra, the calculator can solve nearly any math problem.
5️⃣Helotak : This app connects you with native speakers from around the world. This app helps you practice your target language through interactions with native speakers, allowing for text, voice recordings, video calls, and live chat rooms.
#freeapps
#forstudents
#technews
4👍3🔥1🥰1
Lite apps ምንድን ነዉ?

🔯Lite app ማለት የአንድ አፕልኬሽን lighweignt version ማለት ሲሆን ይህ lite app design የተደረገው ትንሽ Storage እና በትንሽ network connection እንዲሰራ ታስቦ ነው።

እንዲሁም ከnormal መተግበሪያው ጋር ሲነፃፀር ለLow end hardware configuration ላላቸው ስልኮች (ለትናንሽ ስልኮች) በትንሽ performance እንዲሰራ ተደርጎ design የተደረገ app ነው።

ይህንን version አብዛኛውን ጊዜ እንደ
Tiktok
Instagram
Facebook የመሳሰሉ social media apps lite version አላቸው።

ነገርግን አንድ lite app በnormal or regular app ላይ ያለው feature በሙሉ ላይኖረው ይችላል።

እስኪ እናንተ የትኛውን የ social Media Platform Lite app እንደምትጠቀሙ Comment አድርጉልኝ
@senaytech
#senaytech
#Technews
5👍3🔥1🥰1
#ቲክቶክ
🔯ብዙዎቻችሁ የቲክቶክ ቪድዮ ስትጭት ቪድዮው ብዙ እይታ አያገኝም ትላላችሁ :-
ቪዲዮ ጭናችሁ ብዙ View(እይታ) የማያገኝበት ዋነኛው እና ትልቁ ችግር ይህ ነው።

እንደሚታወቀው ቲክቶክ እንደማንኛውም የሶሻል ሚዲያ የራሱ Community guideline( የማህበረሰብ መመሪያ) አለው።
ስለዚህ ይህን መመሪያ ተላልፋችሁ ማለትም የራሳችሁ ያልሆነን ቪዲዮ ፣ ፀብ አጫሪ ወይም ሌሎችን ሊጎዳ የሚችል ቪዲዮ ስትጭኑ ቪድዮው ብዙ View እንዳይኖረው ያደርጋል።

ይህንንም ለማስተካከል :-
በመጀመሪያ የቲክቶክ አፕሊኬሽናችሁን በመክፈት➡️ Me የሚለውን በመንካት➡️ Tiktok Studio➡️ ከዛ ትንሽ ዝቅ ስታደርጉት➡️ check account
አሁን የትኛው ቪድዮ Community gideline እንደጣሰ ያሳያችኋል
ከእናንተ የሚጠበቀው ቪድዮውን መደለት ብቻ ነው።

#Technews
4🔥3👍1👎1🥰1👏1
⚠️⚠️⚠️ ከኢንሳ የተላለፈ የጥንቃቄ መልዕክት

"ዛሬ ማለትም ታህሳስ 17 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች ከላይ በተጠቀሰው የማስገሪያ (phishing link) እና ሌሎች ተጨማሪ ማስገሪያዎች አማካኝነት መረጃዎች እየተመዘበሩ ስለሆነ ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከምታውቁት እና ከማታውቁት ) ግለሰብ ሊንክ ቢላክላችሁ መክፈት እንደሌለባችሁ እና ወዲያውኑ እንድታጠፉት እናሳስባለን ሲል የኢንፎርሜሽን እና መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /ኢንሳ/ገልጧል።

Source:addis insider_ETH

@senaytech
@tech_news
👏43👍3🔥1🥰1
በ #2025 #ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚሆኑ ምርጥ የአጠናን ዘዴዎችን እነሆ፦

1. #ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀም (Leveraging Technology):

#ዲጂታል ማስታወሻ መያዣ (Digital Note-Taking): እንደ OneNote፣ Evernote፣ Google Keep ያሉ አፕሊኬሽኖችን በመጠቀም ማስታወሻዎችን በኮምፒውተርህ፣ በስልክህ ወይም በታብሌትህ ላይ መፃፍ። ይህም ማስታወሻዎችህን በቀላሉ እንድታገኝ፣ እንድትከፋፍል እና እንድታጋራ ያስችልሃል።
• የአጠናን አፕሊኬሽኖች (Study #Apps): እንደ Anki (ለፍላሽ ካርዶች)፣ Forest (ትኩረት ለማድረግ)፣ Quizlet (ጥያቄዎችን ለመለማመድ) ያሉ አፕሊኬሽኖችን ተጠቀም።
• የኦንላይን ምንጮች (Online Resources): እንደ Coursera, edX, Khan Academy ያሉትን መድረኮች ተጠቀም። በነዚህ መድረኮች ትምህርቶችን መከታተል፣ ማብራሪያዎችን ማንበብ እና ቪዲዮዎችን መመልከት።
#ዩቲዩብ (YouTube): ለትምህርትህ ተስማሚ የሆኑ የዩቲዩብ ቻናሎችን ተጠቀም። ትምህርቶችን በተለያየ መንገድ ለማየትና ለመረዳት ይረዳሃል።

2. ንቁ ትምህርት (Active Learning):

• ራስህን መፈተሽ (Self-Testing): ትምህርቱን ካነበብክ በኋላ ራስህን በቃል ለመፈተሽ ሞክር። ያለማስታወሻ ለማስታወስ ሞክር።
• ለሌሎች ማስተማር (Teaching Others): አንድን ነገር በሚገባ ለመረዳት ለሌላ ሰው ለማስተማር መሞከር ትልቅ ጥቅም አለው።
• የጥያቄዎች ልምምድ (Practice Questions): ብዙ ጥያቄዎችን መለማመድ ትምህርቱን በደንብ ለመረዳትና ለፈተና ለመዘጋጀት ይረዳል።
• ማጠቃለያዎች (Summaries): ትልልቅ የትምህርት ክፍሎችን አንብበህ ስትጨርስ በራስህ ቃል አጠር አድርገህ ለመጻፍ መሞከር።

3. የተደራጀ የአጠናን እቅድ (Organized Study Plan):

• የጊዜ ሰሌዳ (Time Table): ለትምህርትህ፣ ለስራህ እና ለሌሎች ነገሮች ጊዜ የሚመድብበት የጊዜ ሰሌዳ ፍጠር።
• አላማን ማዘጋጀት (Setting Goals): ለአንድ ሳምንት፣ ለአንድ ወር ወይም ለአንድ ሴሚስተር ምን ያህል መማር እንደምትፈልግ ግልጽ አላማ አውጣ።
• እረፍት መውሰድ (Taking Breaks): ለረጅም ሰዓታት ያለእረፍት ከማጥናት ይልቅ በአጭር ጊዜ ውስጥ አጥንተህ እረፍት መውሰድህ ውጤታማ ያደርግሃል።
• ተለዋዋጭ መሆን (Flexibility): በአጠናንህ እቅድ ውስጥ ተለዋዋጭነትን ፍጠር። አንዳንድ ጊዜ ነገሮች እንዳሰብከው ላይሄዱ ይችላሉ፤ ስለዚህ ያንን ለመቀበል ዝግጁ ሁን።

4. የአዕምሮ ጤንነት (Mental Well-being):

• በቂ እንቅልፍ (Adequate Sleep): በቂ እንቅልፍ መተኛት ለአእምሮህ ጤንነት በጣም አስፈላጊ ነው።

• አካል ብቃት እንቅስቃሴ (Physical Exercise): የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለአእምሮህ ጤንነትና ለአጠናን ውጤታማነትህ ጠቃሚ ነው።
• ማህበራዊ ግንኙነት (Socialization): ከጓደኞችህ እና ከቤተሰብህ ጋር ጊዜ ማሳለፍ አእምሮህን ለማደስ ይረዳል።

5. ግብረመልስ ማግኘት (Seeking Feedback):

#ከመምህራን ጋር መወያየት (Discussing with Professors): ስለ ትምህርቱ ያልገቡህን ነገሮች ፕሮፌሰሮችህን ጠይቅ።
• ከጓደኞች ጋር መማር (Studying with Peers): ከጓደኞችህ ጋር አብረህ ማጥናት።
• በቡድን #ማጥናት (Study Groups): የጥናት ቡድኖችን በመፍጠር አብራችሁ ተወያዩና ተማማሩ።

ጠቃሚ ምክሮች:

• ለራስህ ተስማሚ የሆነውን ዘዴ ምረጥ: ሁሉም ሰው በተለያየ መንገድ ነው የሚማረው። ስለዚህ፣ ለአንተ የሚስማማህን የአጠናን ዘዴ መፈለግ አለብህ።
• ተከታታይ ሁን (Be Consistent): ውጤታማ ለመሆን በተከታታይነት ማጥናት አለብህ።
• አትጨነቅ (Don't Stress): ፈተና ሲመጣ ከመጨነቅ ይልቅ በተረጋጋ መንፈስ ለማጥናት ሞክር።

እነዚህን ዘዴዎች በመጠቀም በዩኒቨርሲቲ ቆይታህ ውጤታማ ተማሪ መሆን ትችላለህ። መልካም የትምህርት ጊዜ!

#senaytech
#howto_study
#tech_news
#universty_life
👍43🥰1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
☎️☎️#ዳታ ስንጠቀም በጣም ዳታ ከሚበሉብን ነገሮች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው አንዳንድ #Applications እኛ ሳንፈቅድላቸው በራሳቸው Update ስለሚያደርጉ ነው።

ስለዚህ ዛሬ ይህን ችግር እንዴት አድርገን እንደምናስተካክል እናያለን:-

1.በመጀመሪያ #Playstore እንገባና ፕሮፋይላችን (profile) እንነካለን

2.በመቀጠል ትንሽ ዝቅ ካደርግን በኋላ seetings የሚለውን መንካት

3. network preference የሚለውን መንካት

4.auto apdate apps የሚል መንካት

5. ከዛም Over WiFi only ወይም don't auto update apps የሚለውን ነክታችሁ Done ማለት።

ይህ መሆኑ የሚጠቅማው አፕሊኬሽኖች ከናንተ ፈቃድ ዉጭ Update እንዳያደርጉ በማድረግ በ #wi-Fi ወይም በእናንተ ፈቃድ ብቻ Update እንዲሆኑ ይፈቅዳል።

ማንኛውም ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥያቄ ካላችሁ Comment አድርጉ።
👇👇👇

#senaytech
#Technology
#ቴክኖሎጂ
#android
4👍4🥰1
Senay Tech pinned a photo
ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በማቋረጥ ከአለም #ስምንተኛ ከአፍሪካ #ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ተገለፀ።

በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2024 አመት የኢንተርኔት መዘጋት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ሲገለጽ፤ በ 28 ሀገራት 167 የኢንተርኔት መዘጋቶች መመዝገባቸው ተነግሯል፡፡

በኢንተርኔት አጠቃቀም እና ደረጃ ላይ ሪፖርቶችን የሚያወጣው “ቶፕ ቴን ቪፒኤን” እንዳለው እነዚህ በመንግስት ተግባራዊ የሚደረጉ የኢንተርኔት መቆራረጦች 7.69 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራን በማድረስ በአለም ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድረዋል።

በአለም አቀፍ ደረጃ 648.4 ሚሊዮን ሰዎች በቀጥታ በነዚህ መስተጓጎሎች ከተለያዩ የኢንተርኔት አገልግሎቶች የተቋረጡ ናቸው ተብሏል፡፡
ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ለ32,938 ሰዓታት የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ምክንያት 1.56 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ኪሳራን ያስከተለ ሲሆን ይህም 111.2 ሚሊየን ሰዎች ላይ ተጽዕኖ ማድረሱ ነው የተዘገበው፡፡

የኢንተርኔት መዘጋት ከበይነመረብ ሳንሱር ዓይነቶች አንዱን ይወክላል ያለው ሪፖርቱ፤ የመረጃ ተደራሽነትን ፣ አስፈላጊ አገልግሎቶችን እና የዲጂታል መሠረተ ልማትን ማቋረጥ እንደሚያጠቃልል ያትታል፡፡

በ2024 የኢንተርኔት መዘጋት ያደረሰው ኪሳራ ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ15.8 በመቶ የቀነሰ ቢሆንም ፤ ሆን ተብሎ የሚደረግ የኢንተርኔት መዘጋት ከበፊቱ በበለጠ ለብዙ ሰአታት መቆራረጡን የ”ቶፕ ቴን ቪፒኤን” ሪፖርት ጠቅሷል፡፡

አንድ ሶስተኛው የመንግስት የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ በ2024 ከተጨማሪ የሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር የተቆራኘ ሲሆን ይህም ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ እና መረጃ የማግኝት ነፃነትን የሚገድብ ስለመሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በአፍሪካ ኢንተርኔትን በማቋረጥ ቀዳሚዋ የሆነችው ሱዳን ስትሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ በሶስተኛነት ተቀምጣለች፡፡
ሱዳን ለ12,707 ሰአታት ኢንተርኔትን በማቋረጥ 1.12 ቢሊየን ዶላር ኪሳራ ስታስተናግድ 23.4 ሚሊየን ሰዎች ደግሞ አገልግሎት ተቋርጦባቸዋል፡፡

በሁለተኛነት የምትገኝው ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ በስምነተኛነት ስትቀመጥ የደረሰባት ኪሳራ ደግሞ 211.2 ሚሊየን ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
ኬኒያ ፣ አልጄሪያ ፣ ጊኒ ፣ሞሪታንያ ፣ ሴኔጋል ፣ ሞዛምቢክ ፣ ቻድ እና ማውሪሽየስ በአፍሪካ ከ3-10 ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

Source:- Al ain

#Technews
#Senay_tech

https://t.me/senaytech
👍53🔥1🥰1😁1
ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ !

#Technews
👍5🔥1
🤙 Hi guys እንዴት ናችሁ ከዚህ ቀደም በነገርናችሁ መሰረት ስልጠናዎን በቴሌግራም ላይቭ ለመስጠት አስበናል ምን ትላላችሁ?

ከዚህ በታች የምጠይቀውን ጥያቄ በትክክል ሙሉት
👍41🔥1🥰1
ስልጠናውን በቴሌግራም ላይቭ ለመስጠት አስበናል ምን ትላላችሁ?
Anonymous Poll
81%
ኧረ ይጀመር🤜🤛
19%
አይጀምር
👍3
Senay Tech pinned «ስልጠናውን በቴሌግራም ላይቭ ለመስጠት አስበናል ምን ትላላችሁ?»