Senay Tech
357 subscribers
75 photos
23 videos
6 files
61 links
👉Owner @Senaymg

በዚህ የ Tech የቴሌግራም ቻናል
📱 #Android_Tricks
🚀 #Social_Media_secrets
📰 #Tech_News
🛠 #Useful_Apps
💡 #Quick_Tech_Tips በነፃ እናቀርባለን።
Download Telegram
Senay Tech
የቪድዮ ኤዲቲንግ ትምህርታችንን ለመጀመር አንድ እርምጃ ወደፊት! #videoediting ቪድዮ ኤዲቲንግ ቪዲዮ ኤዲቲንግ ምንድን ነው? በየቀኑ የምናያቸው ቪዲዮዎች ጀርባ ያለው ጥበብስ? ለምንስ ልንማረው ይገባል? የስራ እድሉስ ምን ይመስላል? አብረን እንየው! ቪዲዮ ኤዲቲንግ ምንድን ነው? (What is Video Editing?) ቪዲዮ ኤዲቲንግ ማለት የተቀረፁ የቪዲዮ ክሊፖችን (raw footage)፣…
ቪዲዮ ኤዲቲንግ በህይወታችን ውስጥ (Video Editing in Our Daily Lives):

ቪዲዮ ኤዲቲንግ በዘመናዊው አለም በሁሉም ቦታ አለ። የምንመለከታቸው አብዛኛዎቹ ተንቀሳቃሽ ምስሎች የኤዲቲንግ ውጤቶች ናቸው፦

➡️ ፊልሞች እና የቴሌቪዥን ድራማዎች (Movies & TV Shows): ትዕይንቶችን መቁረጥ፣ ማቀናበር፣ የድምፅ እና የምስል ተፅዕኖዎችን (effects) መጨመር።

➡️ የዩቲዩብ ቪዲዮዎች እና የሶሻል ሚዲያ ይዘቶች (YouTube, TikTok, Instagram Reels): የምንመለከታቸው አጫጭር እና ረጅም ቪዲዮዎች፣ ቭሎጎች (Vlogs)።

➡️ የቴሌቪዥን እና የኦንላይን ማስታወቂያዎች (TV Commercials & Online Ads): ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅ የሚዘጋጁ አጫጭር ቪዲዮዎች።


➡️ ዶክመንተሪዎች እና የዜና ዘገባዎች (Documentaries & News Reports): እውነተኛ ታሪኮችን ወይም ክስተቶችን በምስል እና በድምፅ መተረክ።

➡️ የሰርግ እና የልዩ ዝግጅቶች ቪዲዮዎች (Wedding & Event Videography): የተቀረፁ የዝግጅት ምስሎችን በማቀናበር ቪዲዮዎችን መፍጠር።
ይቀጥላል👍
👍84🔥1
Senay Tech
ቪዲዮ ኤዲቲንግ በህይወታችን ውስጥ (Video Editing in Our Daily Lives): ቪዲዮ ኤዲቲንግ በዘመናዊው አለም በሁሉም ቦታ አለ። የምንመለከታቸው አብዛኛዎቹ ተንቀሳቃሽ ምስሎች የኤዲቲንግ ውጤቶች ናቸው፦ ➡️ ፊልሞች እና የቴሌቪዥን ድራማዎች (Movies & TV Shows): ትዕይንቶችን መቁረጥ፣ ማቀናበር፣ የድምፅ እና የምስል ተፅዕኖዎችን (effects) መጨመር። ➡️ የዩቲዩብ ቪዲዮዎች…
➡️ የትምህርት እና የስልጠና ቪዲዮዎች (Educational & Tutorial Videos): መረጃን ወይም ክህሎትን ለማስተማር የሚዘጋጁ ቪዲዮዎች።

➡️ የኮርፖሬት ቪዲዮዎች (Corporate Videos): የድርጅት መግለጫዎች፣ የስልጠና ቪዲዮዎች፣ የውስጥ ግንኙነት ቪዲዮዎች።


የቪዲዮ ኤዲቲንግ ትምህርት ጥቅሞች (Benefits of Learning Video Editing):

🔼 የምስል ታሪክ ተራኪ መሆን (Visual Storytelling): ሀሳብን እና ታሪክን በተንቀሳቃሽ ምስል እና ድምፅ የመተረክ ችሎታ ማዳበር።

🔼 ቴክኒካል ክህሎት ማግኘት (Technical Proficiency): የቪዲዮ ኤዲቲንግ ሶፍትዌሮችን እና ቴክኒኮችን መማር።

🔼 የፈጠራ አቅምን ማስፋት (Boosting Creativity): ጥሬ ቀረፃን ወደ ማራኪ እና ትርጉም ያለው ቪዲዮ የመቀየር ጥበብ።

🔼 በዲጂታል ዘመን ተፈላጊ መሆን (High Demand in Digital Age): የቪዲዮ ይዘት ፍላጎት በየጊዜው እያደገ በመምጣቱ የኤዲተሮች ፍላጎት ከፍተኛ ነው።

🔼 ሰፊ የፍሪላንስ እድሎች (Abundant Freelance Opportunities): ለአገር ውስጥ እና ለውጭ ደንበኞች በግል የመስራት እድል (ዩቲዩበሮች፣ ቢዝነሶች፣ ወዘተ)።

🔼 ከሌሎች ሙያዎች ጋር መቀናጀት (Complements Other Skills): ከግራፊክ ዲዛይን፣ ከማርኬቲንግ፣ ከፎቶግራፊ እና ከማህበራዊ ሚዲያ አስተዳደር ጋር በቀላሉ ይጣመራል።

🔼 የግል እና የንግድ ፕሮጀክቶችን ማሳመር (Enhancing Personal & Business Projects): ለራስዎ ወይም ለድርጅትዎ ፕሮፌሽናል የሚመስሉ ቪዲዮዎችን መፍጠር።



በቪዲዮ ኤዲቲንግ ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ ቁልፍ መሳሪያዎች እና ፅንሰ-ሀሳቦች:

ሶፍትዌሮች (Software - Non-Linear Editors - NLEs):
➡️ Adobe Premiere Pro: በኢንዱስትሪው ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል፣ ፕሮፌሽናል የቪዲዮ ኤዲቲንግ ሶፍትዌር (በስልጠናችን ትኩረት የምናደርግበት)።

➡️ Adobe After Effects: ለሞሽን ግራፊክስ (Motion Graphics) እና ለቪዥዋል ኢፌክትስ (Visual Effects - VFX) የሚያገለግል፣ ከ Premiere Pro ጋር አብሮ በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል።

➡️ Final Cut Pro: በአፕል ማክ ኮምፒውተሮች ላይ በስፋት የሚታወቅ ፕሮፌሽናል ሶፍትዌር።

➡️ DaVinci Resolve: ለፕሮፌሽናል ኤዲቲንግ እና በተለይ ለከለር ግሬዲንግ (Color Grading) በጣም የታወቀ፣ ኃይለኛ እና ነፃ ስሪት ያለው ሶፍትዌር።

➡️ (CapCut, Filmora): ለጀማሪዎች፣ ለማህበራዊ ሚዲያ እና ለፈጣን ኤዲቲንግ ተስማሚ የሆኑ ቀላል ሶፍትዌሮች።


ፅንሰ-ሀሳቦች (Key Concepts):
➡️ የስራ ሂደት (Workflow): ከቀረፃ እስከ መጨረሻው ቪዲዮ ድረስ ያሉ ደረጃዎች (ማስገባት፣ መምረጥ፣ መቁረጥ፣ ማስተካከል፣ መላክ)።

➡️ ታይምላይን (Timeline): ቪዲዮ እና ድምፅ የሚደራጁበት ዋና የስራ ቦታ።

➡️ መቁረጥ እና ማቀናበር (Cutting & Sequencing): ክሊፖችን መቁረጥ፣ ማሳጠር፣ ማዛወር እና በትክክለኛ ቅደም ተከተል ማስቀመጥ።

➡️ ሽግግሮች (Transitions): በአንድ ክሊፕ እና በሚቀጥለው መካከል ያሉ ለስላሳ ወይም ድንገተኛ መሸጋገሪያዎች (Cuts, Dissolves, Wipes)።

➡️ የድምፅ ኤዲቲንግ (Audio Editing): የድምፅ ጥራትን ማስተካከል፣ ሙዚቃ መጨመር፣ የድምፅ ተፅዕኖዎችን (Sound Effects - SFX) መጠቀም፣ ድምፅን ማመጣጠን (Mixing)።

➡️ ከለር ኮሬክሽን እና ግሬዲንግ (Color Correction & Grading): የቪዲዮን የቀለም ትክክለኛነት ማስተካከል (Correction) እና ለስሜት ወይም ለስታይል ቀለሙን መለወጥ (Grading)።

➡️ ፅሁፎች እና ግራፊክሶች (Titles & Graphics): ርዕሶችን፣ ስሞችን፣ እና ሌሎች ግራፊክሶችን በቪዲዮ ላይ መጨመር።

➡️ ሞሽን ግራፊክስ (Motion Graphics): ተንቀሳቃሽ ግራፊክስ እና አኒሜሽኖች (በ After Effects)።....
#videoediting
#videoeditor
#editing
👍83🔥1👏1
ቴሌግራም አካውንታችሁን ሀክ እንዳትደረጉ ማድረግ ያለባችሁ maximum security እና privacy level

1️⃣. Device Passcode ተጠቀሙ። ማንኛውም ሰው ስልካችሁን አንስቶ የተላላካችሁትን ሚሴጅ እንዳያይ ወይም ቴሌግራም የሚልከውን የሚስጠር ቁጥር እንዳያገኝ እናንተ ብቻ የምታውቁት የሚስጢር ቁጥር ይኑራችሁ።
ይህን ለማስተካካል
Settings - privacy and security - passcode

2️⃣. 2-step verification ተጠቀሙ።
2-step verification የማይጠቀም ሰዉ ሀክ የመደረግ እድሉ ከፍተኛ ነው።
Settings - privacy and security - 2-step verification ላይ በመግባት on አድርጉት።
ምናልባት ሀክ ብትደረጉ አካውንታችሁን መልሳችሁ ለማግኘት recovery email መሙላት አለባችሁ።

3️⃣. ከ2 በላይ device ላይ login አታድርጉ።
Login ያደረገችሁበት device በጨመረ ቁጥር ሀክ የመደረግ እድላችሁ ይጨምራል።
ስለዚህ privacy and security -device ላይ ግቡና የተዘረዘሩት ዲቫይሶችን terminate sessions እያደረጋችሁ ቀንሷቸው።

4️⃣. በDesktop ስትጠቀሙ official የDesktop ሶፍትዌሩን ተጠቀሙ እንጂ web ላይ አትጠቀሙ።

5️⃣. ከofficial የtelegram አፕሊኬሽኖች ውጪ ሰዉ በላከላችሁ Link ላይ login ለማድረግ አትሞክሩ።

6️⃣. የቴሌግራም ኮንታክታችሁን ለሰዎች ስትሰጡ username ወይም የአካውንታችሁን qr-code Share አድርጉ እንጂ ስልክ ቁጥር አትስጡ።

7️⃣. ለማታቁትና ለማታምኑት ሰዉ ፎቷችሁን፣ የድምፅ መልዕክት እንዲሁም ሌሎች ሚስጢራዊ የሆኑ መጃዎችን በፍፁም መላክ የለባችሁም። የግድ መላክ ካለባችሁም በsecret message ወይም self destruct ( የተላከለት ሰው 1ዴ ካየው በኋላ የሚጠፋ) ሚሴጆችን ላኩ።

8️⃣. የስልካችሁ status bar ላይ notification እንዳይታይ off አድርጉት።

9️⃣. በመጨረሻም የPrivacy settings ላይ በዚህ መልኩ አስተካክሉ።
Phone number - Nobody
Last seen & online - My contacts
Profile photos - My contacts
Forwarded message - Nobody
Calls - My contacts
Group & channels - My contacts

1️⃣0️⃣. በተለያየ ምክንያት ለረጅም ጊዜ አካውንታችሁ ላይ ሳትገቡ ብትቀሩ በራሱ Delete እንዳይሆንባችሁ self district የሚያደርግበትን ቀን አስርዝሙት።
ይህን ለማድረግ
Settings - privacy and security- delete my account - 24 months

©️@senaytech
👍73👏2🔥1
#ethiotelecom

Ethiotelecom በተለያዩ ፓኬጆች ላይ የዋጋ ማሻሻያ አድርጓል።

የ1 ሰአት Unlimited Internet ከ13 ብር ወደ 18 ብር
የቀን Unlimited internet ከ63 ብር ወደ 85 ብር
የቀን unlimited voice 36 ብር
ሳምንታዊ Unlimited internet 550 ብር
ወርሃዊ premium voice + internet 2375 ብር

Ethiotelecom ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ላይ እንደተገለፀው በርካታ ደንበኞች የሚጠቀሙባቸው 38 የተለያዩ ጥቅሎች ላይ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ እንዳልተደረገባቸው አሳውቋል።
ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የሚጠቀሙባቸው የ1 ብር፣ የ2 ብር፣ የ5 ብር እና የ1 ሰዓት ጥቅሎች ባሉበት መቀጠላቸውን ገልጿል።
ለአካል ጉዳተኞች፣ ለተማሪዎች እና ለመምህራን የተዘጋጁ ልዩ ጥቅሎች ላይ ምንም ዓይነት ጭማሪ አለመደረጉን ኢትዮ ቴሌኮም አሳውቋል።

በቴሌብር ጥቅል ሲገዙ የነበረው የ10% ቅናሽ ወደ 20% ከፍ እንዲል መደረጉን ገልጿል።

✍️ እናንተ የየትኛው ተጠቃሚ ናችሁ?

©@Senaytech
🔥63🤔3👍1
#Telegram_tip

የቴሌግራም ቻናል ባለቤት ከሆናችሁ ሌሎች ሰዎችን አድሚን በምታደርጉበት ጊዜ ይህን ነገር ብታስተውሉ መልካም ነው።

ሁለት እና ከዚያ በላይ አካውንት ካላችሁ ቻናል owner ከሆናችሁበት አካውንት በተጨማሪ ሌላ አካውንት (ሙሉ permission በመስተጠት) admin አድርጋችሁ ሌሎች ሰዎችንም owner ባልሆናችሁበት አካውንት admin ብታደርጉ እንመክራችኋለን።

ይህም እንደ አጋጣሚ አንዱን አካውንት ብታጡት admin ያደረጋችኋቸውን ሰዎች ለመቆጣጠር እንዲያመቻችሁ ነው። ለምሳሌ owner በሆናችሁበት አካውንት ሰዎችን አድሚን አድርጋችሁ owner የሆናችሁበትን አካውንት ብታጡት አድሚን ያደረጋችኋቸውን ሰዎች ለማስወጣት ወይም permission መቀያየር አይቻልም። በምትኩ በአድሚን በሆናችሁበት አካውንት ሌላ ሰው አድሚን ካደረጋችሁ አንዱ አካውንት ብታጡት እንኳን አድሚን የተደረጉትን ሰዎች መቆጣጠር ትችላላችሁ።

© @senaytech
👍7👏32🔥1
ቪድዮ ኤዲተር ከሆናችሁ ለኤዲቲንግ የሚጠቅሙ የተለያዩ sound effects ልላክላችሁ።
ከፈለጋችሁ👍
ካልፈለጋችሁ❤️
👍103👏2🔥1
- ቪድዮ ኤዲተር ለመሆን የግድ computer ወይም PC ያስፈልጋል ብላችሁ ካሰባችሁ ተሳስታችኋል🙅

- graphic designer ለመሆንም እንዲሁ።

በስልካችሁ ብቻ ቪድዮ ኤዲት ለማድረግ Capcut, Inshot, KineMaster etc the best tools

ግራፊክ ዲዛይን ለመስራት ማለትም YouTube thumbnail, logo, banner etc (pixelab, Canva, pixelart ...

ከእነዚህ ውስጥ እናንተ የምትጠቀሙት የትኛውን ነው?
👍84🔥2👏1
በኦንላይን የባንክ ሒሳብን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር ከታች ያሉትን ሊንኮች መጠቀም ትችላላችሁ።

መረጃው Official የናሽናል መታወቂያ መስሪያ ቤት የX አካውንት ነው።

ልብ ይበሉ፦ ሲስተም ላይ በነበረ መጨናነቅ ለቀናት ቆይቶ የነበረውም የመዘግየት ችግር በመፈታቱ ፣ ደንበኛ የሆኑበትን ባንክ ከታች በተዘረዘሩት ዝርዝር በመምረጥ ባለ 16 አኃዝ የፋይዳ ቁጥርዎን (FAN/FCN) በመጠቀም ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ለማጣመር (Harmonization) በነዚህ ሊንኮች ይጠቀሙ።

አቢሲኒያ ባንክ
cs.bankofabyssinia.com/fayda_connect

አዋሽ ባንክ
fayda.awashbank.com

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ:
my.coopbankoromiasc.com/harmonization

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
cbefayda.cbe.com.et

ኦሮሚያ ባንክ
bfayda.oromiabank.com

ወጋገን ባንክ
fayda.wegagenbanksc.com.et/harmonization

ንብ ባንክ
fayda.nibbank.com.et

ፀሀይ ባንክ
fayda.tsehaybank.com.et/FAYDA/home

ስንቄ ባንክ :
fayda.siinqeebank.com:7443

ዘምዘም ባንክ
fayda.zamzambank.com.et

አማራ ባንክ :
fayda.amharabank.com.et
👍84🔥1
የስልካችሁ operating system ምንድን ነው?
Anonymous Poll
7%
iOS
93%
android
2👍2
base (1).apk
95.1 MB
በክፍያ የሚገኘው premium Truecaller ነው ጠጠቀሙበት
👍73🔥1
በሚቀጥሉት ሳምንታት OpenAI chatGPT ላይ ማስታወቂያ መልቀቅ እንደሚጀምር አስታወቀ።

AIን ለሁሉም ሰዉ ተደራሽ ለማድረግ በማሰብ በታማኝነትና በግልፅነት የነጻ ተጠቃሚዎች ላይ ማስታዎቂያዎችን ለመልቀቅ እንዳሰቡ ተናግረዋል።

OpenAI እንዳስታወቀው
በChatGPT ውስጥ ያሉ ምላሾች በማስታወቂያዎች ላይ ተጽዕኖ አይኖራቸውም።
ማስታወቂያዎች ሁል ጊዜ የተለዩ እና በግልጽ የተቀመጡ ናቸው።
የተጠቃሚዎች chat historyና ንግግሮች ለማስታቀቂያ አስነጋሪዎች ተላልፈው አይሰጡም።
በተጨማሪም፣ ፕሮ፣ ቢዝነስ እና ኢንተርፕራይዝ ደረጃዎች ማስታወቂያ አይኖራቸውም።


@senaytech
👍73🔥2