Senay Tech
356 subscribers
75 photos
23 videos
6 files
61 links
👉Owner @Senaymg

በዚህ የ Tech የቴሌግራም ቻናል
📱 #Android_Tricks
🚀 #Social_Media_secrets
📰 #Tech_News
🛠 #Useful_Apps
💡 #Quick_Tech_Tips በነፃ እናቀርባለን።
Download Telegram
🔺ፎቶው ላይ ያለችው ሴት ሕሊና ተፈራ ትባላለች

📲 ስልክ ስንደውል "ያለዎት ቀሪ ሒሳብ አነስተኛ ነው"
"የደወሉላቸውን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም" የምትለን እሷ ነች።🤩
#GeneralKnowledge
5😍3🔥1
📸 📸 ቪድዮ ኤዲተር ከሆናችሁ እና ለመሆን ካሰባችሁ የግድ እነዚህን ዌብሳይቶች መጠቀም አለባችሁ።

#Free_websites

Top 5 free websites for YouTube videos

1 @vecteezy.com የተለያዩ ነፃ Vidios and Photos ታገኙባቸዋላችሁ ።

2 @Unsplash.com እነዚህም የተለያዩ Vidios and Photos ማግኘት እንዲሁም በአሁኑጊዜ hapen እያደረጉ ያሉ ነገሮችን ማግኘት ትችላላችሁ ።

3 @Videezy.com ጥራት ያላቸው mostly 4k and HD tools ታገኛላችሁ ።

4 @Pixabay.com እዚህ ላይ #Free_Vidios, Photos, illustration, sound effects የመሳሰሉ Free tools ታገኛላችሁ።

5 @pexels.com clear and quality free videos ታገኙበታላችሁ ።

#Tech_news
#Senay_Tech
#Ai_Tools
#TechTips
#google
👍62
Video editing እና graphics design መማር የምትፈልጉ ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ምርጥ ቻናሎችን ልጠቁማችሁ?
Anonymous Poll
93%
አዎ ጠቁመን
7%
አይ ተወው
0%
መማር አልፈልግም
ኢትዮጵያ ውስጥ በዩቲዩብ በነፃ Video editing እና graphics design መማር ከፈለጋችሁ ሁለት ቻናሎችን ልጠቁማችሁ።

🥇. 📸#Etubers የሚባል ቻናል ሲሆን በሚገባችሁ የአማርኛ ቋንቋ በሚገርም አቀራረብ እና ግልፅ በሆነ ማብራሪያ ከ ጀማሪ እስከ መካከለኛ ደረጃ የሚያደረሳችሁን ትምህርት በነፃ ያቀርብላችኋል።

🥈. 📸#Nile_graphix_and_design የሚባል ቻናል ሲሆን ከ 3፡ዐዐ ሰዓት እስከ 10:00 ሰዓት የሚደርሱ ኮርሶችን በነፃ በሚገርም አቀራረብ ተገኛላችሁ።

💰ጊዜያችሁን በማይረባ ነገር ከምታጠፉ በእነዚህን ቻናሎች የሚቀርቡትን ነፃ ኮርሶች በደንብ ብትማሩ ነገ ራሳችሁንም ቤተሰባችሁንም መለወጥ የምትችሉበትን አጋጣሚ ትፈጥራላችሁ።

እስኪ እናንተ የተመቻችሁን ወይም ሌላ ተጨማሪ የምታውቁትን ቻናል Comment አድርጉልን✌️

#TechTips #Tricks #Technews
💯7👍21
🔹 Ctrl + Shift + 4 – Currency format
🔹 Ctrl + Shift + 2 – Time format
🔹 Ctrl + Page Down – Next sheet
🔹 Ctrl + Space – Select entire column
🔹 Ctrl + Alt + = – Insert rows/columns
🔹 Alt + F8 – Open macro editor (Google Apps Script)
🔹 Ctrl + Shift + L – Toggle filters
🔹 Ctrl + T – Create table
🔹 Alt + O + R + A – Auto-fit row height
🔹 Ctrl + Shift + 1 – Number format
🔹 Ctrl + + (Plus) – Insert cells dialog
🔹 Alt + O + C + A – Auto-fit column width
🔹 Alt + A + M – Remove duplicates
🔹 Alt + V + Z – Freeze panes
🔹 Shift + Space – Select entire row
🔹 Ctrl + Shift + \ – General number format
🔹 F9 – Recalculate formulas
🔹 Ctrl + Page Up – Previous sheet
🔹 F2 – Edit active cell
🔹 Alt + W + S – Split window
🔹 Alt + N + P – Create PivotTable
🔹 Alt + Tab – Switch between applications
🔹 Ctrl + Shift + 3 – Date format
🔹 Ctrl + - (Minus) – Delete selection
🔹 Ctrl + Tab – Switch browser tabs
🔹 Ctrl + Shift + V – Paste values only
🔹 Shift + F3 – Insert function dialog
🔹 Ctrl + F3 – Open named ranges manager
🔹 Ctrl + Shift + 5 – Percentage format
🔹 F4 – Toggle absolute/relative references

💡 Pro Tip: Use Ctrl + Shift + L` to instantly add or remove filters from your data headers!

Here are 30 Windows Google Sheets shortcuts


#techtips #reelindia #laptoptips #pctips #window11 #googlesheet #googlesheetstips
👏73
ሀይ✌️ ጋይስ እንዴት ናችሁ ሰሞኑን ትንሽ ጠፍቸ ነበር እና ተመልሻለሁ።
እንቀጥላለን Share እያደረጋችሁ
👍62
#እንድታውቁት

ከዚህ በፊት ቴሌግራም አካውንታችንን ካልተጠቀምን በራሱ አካውንቱን የሚያጠፋበት የጊዜ ገደብ ከፍተኛው 12 ወር (1 አመት) የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን ወደ 24 ወር ከፍ ብሏል።

ይህም እስከ 2 አመት ድረስ ወደ አካውንታችሁ ካልተመለሳችሁ ወይም አካውንታችሁን ካልተጠቀማችሁት አካውንታችሁን ሳይጠፋ ልታገኙት ትችላላችሁ።

ይህንንም ለማድረግ settinga> privacy and security> if away for የሚለውን በመንካት እናንተ የፈለጋችሁትን የወር መጠን መምረጥ።

©@senaytech
👍62
We are back.

ሰሞኑን ትንሽ ጠፋቸ ነበር እና አሁን ተመልሻለሁ። እዚህ ቻናል ላይም እንደተለመደው ጠቃሚ እና አስተማሪ ይዘቶችን መለጠፋችንን እንቀጥላለን🙏

በተለይም Video editing መማር የምትፈልጉ እና እየተማራችሁ ያላችሁ👊
አብረን እንማማራለን መልካም ቀን🙏
ስንቶቻችሁ Video editing መማር ትፈልጋላችሁ?
Anonymous Poll
91%
መማር እፈልጋለሁ
3%
እየተማርሁ ነው
6%
መማር አልፈልግም
የ2017  የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል፡፡

የ2017 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በሚከተሉት አማራጮች ከዛሬ መስከረም 05/2018  ከሰዓት ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል

ውጤት በምን ማየት ይቻላል ?

ዌብ ሳይትና ቴሌግራም አድራሻ የሚጠቀሙ ተፈታኞች ጊዜያዊ ሰርቲፊኬታቸውን ወዲያውኑ አውርደው (download አድርገው) መውሰድና መጠቀም ይችላሉ፡፡

አድራሻዎቹ፡
1. ዌብ ሳይት፡ https://result.eaes.et
2. ቴሌገራም፡ https://t.me/EAESbot
3.  አጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS)፡  6284

(የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት)
©tikvahethiopia
6👍2
Hello Family!

እንዴት ናችሁ በዚህ ቻናል ከጠፋሁ በጣም ብዙ ጊዜ ሆኖኛል እናም ከብዙ ጊዜ በኋላ ተመልሰናል።

በቀጠይ ጥሩ ጥሩ ሀሳቦችን እያነሳን አብረን እንዘልቃለን። እናንተም ሀሳባችሁን በኮሜንት ግለፁልኝ።
👍63👏1
Hi family 👋 እንዴት ናችሁ በዚህ ቻናል እናንተን ቪድዮ ኤዲቲንግ እና ግራፊክ ዲዛይን ለማስተማር የማውቀውን ለማካፈል አስቤያለሁ። ምን ትላላችሁ ከታች ያለውን ጥያቄ ሙሉ👍
7🔥2
Video editing and graphic design መማር ትፈልጋላችሁ?
Anonymous Poll
90%
አዎ እፈልጋለሁ
10%
አልፈልግም
የቪድዮ ኤዲቲንግ ትምህርታችንን ለመጀመር አንድ እርምጃ ወደፊት!

#videoediting ቪድዮ ኤዲቲንግ

ቪዲዮ ኤዲቲንግ ምንድን ነው? በየቀኑ የምናያቸው ቪዲዮዎች ጀርባ ያለው ጥበብስ? ለምንስ ልንማረው ይገባል? የስራ እድሉስ ምን ይመስላል? አብረን እንየው!


ቪዲዮ ኤዲቲንግ ምንድን ነው? (What is Video Editing?)

ቪዲዮ ኤዲቲንግ ማለት የተቀረፁ የቪዲዮ ክሊፖችን (raw footage)፣ የድምፅ ፋይሎችን (audio)፣ ፎቶዎችን እና ግራፊክሶችን በመምረጥ፣ በማደራጀት፣ በመቁረጥ፣ በማስተካከል እና በማቀናበር አንድ ወጥ የሆነ፣ የተሟላ እና ማራኪ ቪዲዮ የመፍጠር ሂደት ነው። ዋና አላማው ታሪክን መተረክ፣ መረጃን ማስተላለፍ፣ ስሜትን መፍጠር እና የተመልካችን ትኩረት መያዝ ነው።


💳 በቀላል አነጋገር፣ ቪዲዮ ኤዲቲንግ ልክ እንደ ፊልም ዳይሬክተር ወይም መፅሀፍ አዘጋጅ መሆን ነው። የተበታተኑ የቪዲዮ "ቃላትን" እና "አረፍተ ነገሮችን" (ክሊፖችን) ወስዶ፣ ትርጉም ባለው እና በሚስብ መልኩ በማቀናጀት የተሟላ "ታሪክ" (ቪዲዮ) መፍጠር ነው። ከጥሬ ቀረፃ (raw footage) ወደ ተጠናቀቀ ምርት (final video) የሚደረግ ጉዞ ነው። ይቀጥላል ....

ይቀጥል የምትሉ👍
ይቅር የምትሉ❤️
👍72
ለቪድዮ ኤዲቲንግ የሚሆኑ የተለያዩ ምርጥ ምርጥ Transitions ከፈለጋችሁ ከታች ባለው ሊንክ አውርዳችሁ መጠቀም ትችላላችሁ።

https://t.me/Senaytech/185?single
👍63🔥1
Senay Tech
የቪድዮ ኤዲቲንግ ትምህርታችንን ለመጀመር አንድ እርምጃ ወደፊት! #videoediting ቪድዮ ኤዲቲንግ ቪዲዮ ኤዲቲንግ ምንድን ነው? በየቀኑ የምናያቸው ቪዲዮዎች ጀርባ ያለው ጥበብስ? ለምንስ ልንማረው ይገባል? የስራ እድሉስ ምን ይመስላል? አብረን እንየው! ቪዲዮ ኤዲቲንግ ምንድን ነው? (What is Video Editing?) ቪዲዮ ኤዲቲንግ ማለት የተቀረፁ የቪዲዮ ክሊፖችን (raw footage)፣…
ቪዲዮ ኤዲቲንግ በህይወታችን ውስጥ (Video Editing in Our Daily Lives):

ቪዲዮ ኤዲቲንግ በዘመናዊው አለም በሁሉም ቦታ አለ። የምንመለከታቸው አብዛኛዎቹ ተንቀሳቃሽ ምስሎች የኤዲቲንግ ውጤቶች ናቸው፦

➡️ ፊልሞች እና የቴሌቪዥን ድራማዎች (Movies & TV Shows): ትዕይንቶችን መቁረጥ፣ ማቀናበር፣ የድምፅ እና የምስል ተፅዕኖዎችን (effects) መጨመር።

➡️ የዩቲዩብ ቪዲዮዎች እና የሶሻል ሚዲያ ይዘቶች (YouTube, TikTok, Instagram Reels): የምንመለከታቸው አጫጭር እና ረጅም ቪዲዮዎች፣ ቭሎጎች (Vlogs)።

➡️ የቴሌቪዥን እና የኦንላይን ማስታወቂያዎች (TV Commercials & Online Ads): ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅ የሚዘጋጁ አጫጭር ቪዲዮዎች።


➡️ ዶክመንተሪዎች እና የዜና ዘገባዎች (Documentaries & News Reports): እውነተኛ ታሪኮችን ወይም ክስተቶችን በምስል እና በድምፅ መተረክ።

➡️ የሰርግ እና የልዩ ዝግጅቶች ቪዲዮዎች (Wedding & Event Videography): የተቀረፁ የዝግጅት ምስሎችን በማቀናበር ቪዲዮዎችን መፍጠር።
ይቀጥላል👍
👍84🔥1
Senay Tech
ቪዲዮ ኤዲቲንግ በህይወታችን ውስጥ (Video Editing in Our Daily Lives): ቪዲዮ ኤዲቲንግ በዘመናዊው አለም በሁሉም ቦታ አለ። የምንመለከታቸው አብዛኛዎቹ ተንቀሳቃሽ ምስሎች የኤዲቲንግ ውጤቶች ናቸው፦ ➡️ ፊልሞች እና የቴሌቪዥን ድራማዎች (Movies & TV Shows): ትዕይንቶችን መቁረጥ፣ ማቀናበር፣ የድምፅ እና የምስል ተፅዕኖዎችን (effects) መጨመር። ➡️ የዩቲዩብ ቪዲዮዎች…
➡️ የትምህርት እና የስልጠና ቪዲዮዎች (Educational & Tutorial Videos): መረጃን ወይም ክህሎትን ለማስተማር የሚዘጋጁ ቪዲዮዎች።

➡️ የኮርፖሬት ቪዲዮዎች (Corporate Videos): የድርጅት መግለጫዎች፣ የስልጠና ቪዲዮዎች፣ የውስጥ ግንኙነት ቪዲዮዎች።


የቪዲዮ ኤዲቲንግ ትምህርት ጥቅሞች (Benefits of Learning Video Editing):

🔼 የምስል ታሪክ ተራኪ መሆን (Visual Storytelling): ሀሳብን እና ታሪክን በተንቀሳቃሽ ምስል እና ድምፅ የመተረክ ችሎታ ማዳበር።

🔼 ቴክኒካል ክህሎት ማግኘት (Technical Proficiency): የቪዲዮ ኤዲቲንግ ሶፍትዌሮችን እና ቴክኒኮችን መማር።

🔼 የፈጠራ አቅምን ማስፋት (Boosting Creativity): ጥሬ ቀረፃን ወደ ማራኪ እና ትርጉም ያለው ቪዲዮ የመቀየር ጥበብ።

🔼 በዲጂታል ዘመን ተፈላጊ መሆን (High Demand in Digital Age): የቪዲዮ ይዘት ፍላጎት በየጊዜው እያደገ በመምጣቱ የኤዲተሮች ፍላጎት ከፍተኛ ነው።

🔼 ሰፊ የፍሪላንስ እድሎች (Abundant Freelance Opportunities): ለአገር ውስጥ እና ለውጭ ደንበኞች በግል የመስራት እድል (ዩቲዩበሮች፣ ቢዝነሶች፣ ወዘተ)።

🔼 ከሌሎች ሙያዎች ጋር መቀናጀት (Complements Other Skills): ከግራፊክ ዲዛይን፣ ከማርኬቲንግ፣ ከፎቶግራፊ እና ከማህበራዊ ሚዲያ አስተዳደር ጋር በቀላሉ ይጣመራል።

🔼 የግል እና የንግድ ፕሮጀክቶችን ማሳመር (Enhancing Personal & Business Projects): ለራስዎ ወይም ለድርጅትዎ ፕሮፌሽናል የሚመስሉ ቪዲዮዎችን መፍጠር።



በቪዲዮ ኤዲቲንግ ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ ቁልፍ መሳሪያዎች እና ፅንሰ-ሀሳቦች:

ሶፍትዌሮች (Software - Non-Linear Editors - NLEs):
➡️ Adobe Premiere Pro: በኢንዱስትሪው ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል፣ ፕሮፌሽናል የቪዲዮ ኤዲቲንግ ሶፍትዌር (በስልጠናችን ትኩረት የምናደርግበት)።

➡️ Adobe After Effects: ለሞሽን ግራፊክስ (Motion Graphics) እና ለቪዥዋል ኢፌክትስ (Visual Effects - VFX) የሚያገለግል፣ ከ Premiere Pro ጋር አብሮ በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል።

➡️ Final Cut Pro: በአፕል ማክ ኮምፒውተሮች ላይ በስፋት የሚታወቅ ፕሮፌሽናል ሶፍትዌር።

➡️ DaVinci Resolve: ለፕሮፌሽናል ኤዲቲንግ እና በተለይ ለከለር ግሬዲንግ (Color Grading) በጣም የታወቀ፣ ኃይለኛ እና ነፃ ስሪት ያለው ሶፍትዌር።

➡️ (CapCut, Filmora): ለጀማሪዎች፣ ለማህበራዊ ሚዲያ እና ለፈጣን ኤዲቲንግ ተስማሚ የሆኑ ቀላል ሶፍትዌሮች።


ፅንሰ-ሀሳቦች (Key Concepts):
➡️ የስራ ሂደት (Workflow): ከቀረፃ እስከ መጨረሻው ቪዲዮ ድረስ ያሉ ደረጃዎች (ማስገባት፣ መምረጥ፣ መቁረጥ፣ ማስተካከል፣ መላክ)።

➡️ ታይምላይን (Timeline): ቪዲዮ እና ድምፅ የሚደራጁበት ዋና የስራ ቦታ።

➡️ መቁረጥ እና ማቀናበር (Cutting & Sequencing): ክሊፖችን መቁረጥ፣ ማሳጠር፣ ማዛወር እና በትክክለኛ ቅደም ተከተል ማስቀመጥ።

➡️ ሽግግሮች (Transitions): በአንድ ክሊፕ እና በሚቀጥለው መካከል ያሉ ለስላሳ ወይም ድንገተኛ መሸጋገሪያዎች (Cuts, Dissolves, Wipes)።

➡️ የድምፅ ኤዲቲንግ (Audio Editing): የድምፅ ጥራትን ማስተካከል፣ ሙዚቃ መጨመር፣ የድምፅ ተፅዕኖዎችን (Sound Effects - SFX) መጠቀም፣ ድምፅን ማመጣጠን (Mixing)።

➡️ ከለር ኮሬክሽን እና ግሬዲንግ (Color Correction & Grading): የቪዲዮን የቀለም ትክክለኛነት ማስተካከል (Correction) እና ለስሜት ወይም ለስታይል ቀለሙን መለወጥ (Grading)።

➡️ ፅሁፎች እና ግራፊክሶች (Titles & Graphics): ርዕሶችን፣ ስሞችን፣ እና ሌሎች ግራፊክሶችን በቪዲዮ ላይ መጨመር።

➡️ ሞሽን ግራፊክስ (Motion Graphics): ተንቀሳቃሽ ግራፊክስ እና አኒሜሽኖች (በ After Effects)።....
#videoediting
#videoeditor
#editing
👍83🔥1👏1
ቴሌግራም አካውንታችሁን ሀክ እንዳትደረጉ ማድረግ ያለባችሁ maximum security እና privacy level

1️⃣. Device Passcode ተጠቀሙ። ማንኛውም ሰው ስልካችሁን አንስቶ የተላላካችሁትን ሚሴጅ እንዳያይ ወይም ቴሌግራም የሚልከውን የሚስጠር ቁጥር እንዳያገኝ እናንተ ብቻ የምታውቁት የሚስጢር ቁጥር ይኑራችሁ።
ይህን ለማስተካካል
Settings - privacy and security - passcode

2️⃣. 2-step verification ተጠቀሙ።
2-step verification የማይጠቀም ሰዉ ሀክ የመደረግ እድሉ ከፍተኛ ነው።
Settings - privacy and security - 2-step verification ላይ በመግባት on አድርጉት።
ምናልባት ሀክ ብትደረጉ አካውንታችሁን መልሳችሁ ለማግኘት recovery email መሙላት አለባችሁ።

3️⃣. ከ2 በላይ device ላይ login አታድርጉ።
Login ያደረገችሁበት device በጨመረ ቁጥር ሀክ የመደረግ እድላችሁ ይጨምራል።
ስለዚህ privacy and security -device ላይ ግቡና የተዘረዘሩት ዲቫይሶችን terminate sessions እያደረጋችሁ ቀንሷቸው።

4️⃣. በDesktop ስትጠቀሙ official የDesktop ሶፍትዌሩን ተጠቀሙ እንጂ web ላይ አትጠቀሙ።

5️⃣. ከofficial የtelegram አፕሊኬሽኖች ውጪ ሰዉ በላከላችሁ Link ላይ login ለማድረግ አትሞክሩ።

6️⃣. የቴሌግራም ኮንታክታችሁን ለሰዎች ስትሰጡ username ወይም የአካውንታችሁን qr-code Share አድርጉ እንጂ ስልክ ቁጥር አትስጡ።

7️⃣. ለማታቁትና ለማታምኑት ሰዉ ፎቷችሁን፣ የድምፅ መልዕክት እንዲሁም ሌሎች ሚስጢራዊ የሆኑ መጃዎችን በፍፁም መላክ የለባችሁም። የግድ መላክ ካለባችሁም በsecret message ወይም self destruct ( የተላከለት ሰው 1ዴ ካየው በኋላ የሚጠፋ) ሚሴጆችን ላኩ።

8️⃣. የስልካችሁ status bar ላይ notification እንዳይታይ off አድርጉት።

9️⃣. በመጨረሻም የPrivacy settings ላይ በዚህ መልኩ አስተካክሉ።
Phone number - Nobody
Last seen & online - My contacts
Profile photos - My contacts
Forwarded message - Nobody
Calls - My contacts
Group & channels - My contacts

1️⃣0️⃣. በተለያየ ምክንያት ለረጅም ጊዜ አካውንታችሁ ላይ ሳትገቡ ብትቀሩ በራሱ Delete እንዳይሆንባችሁ self district የሚያደርግበትን ቀን አስርዝሙት።
ይህን ለማድረግ
Settings - privacy and security- delete my account - 24 months

©️@senaytech
👍73👏2🔥1
#ethiotelecom

Ethiotelecom በተለያዩ ፓኬጆች ላይ የዋጋ ማሻሻያ አድርጓል።

የ1 ሰአት Unlimited Internet ከ13 ብር ወደ 18 ብር
የቀን Unlimited internet ከ63 ብር ወደ 85 ብር
የቀን unlimited voice 36 ብር
ሳምንታዊ Unlimited internet 550 ብር
ወርሃዊ premium voice + internet 2375 ብር

Ethiotelecom ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ላይ እንደተገለፀው በርካታ ደንበኞች የሚጠቀሙባቸው 38 የተለያዩ ጥቅሎች ላይ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ እንዳልተደረገባቸው አሳውቋል።
ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የሚጠቀሙባቸው የ1 ብር፣ የ2 ብር፣ የ5 ብር እና የ1 ሰዓት ጥቅሎች ባሉበት መቀጠላቸውን ገልጿል።
ለአካል ጉዳተኞች፣ ለተማሪዎች እና ለመምህራን የተዘጋጁ ልዩ ጥቅሎች ላይ ምንም ዓይነት ጭማሪ አለመደረጉን ኢትዮ ቴሌኮም አሳውቋል።

በቴሌብር ጥቅል ሲገዙ የነበረው የ10% ቅናሽ ወደ 20% ከፍ እንዲል መደረጉን ገልጿል።

✍️ እናንተ የየትኛው ተጠቃሚ ናችሁ?

©@Senaytech
🔥63🤔3👍1