ሰብዓዊ ምህንድስና 💚 Self Engineering
2.49K subscribers
720 photos
93 videos
3 files
309 links
በዚህ የሰብዓዊ ምህንድስና ቅኝት፣አርክቴክት/መሃንዲስ የሰዉነትና የአዕምሮ አለም አቀፍ አሰልጣኝ እንዲሁም የክሁል @KhulWorld ሁለንተናዊ እድገት ማዕከል መስራች እና ባለ ራዕይ የሆነዉ ዮፍታሔ ማንያዘዋል የሚያደርጋቸዉን ሳይንሳዊና ተግባራዊ የህይወት ማበልፀጊያ ፕሮግራሞችን በነፃ እንዲታደሙ እና ራስዎን ወደላቀ ማንነትዎ በማሳደግ የህይወትዎ ማህንዲስ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል +251932333382
Download Telegram
እንኳን የካቲት 29 (March 8 ) የሴቶች ቀን በሰላም አደረሳችሁ! 🎉

​ዛሬ ዓለማችንን በብርሃን ለሚያደምቁ፣ ለሚንከባከቡ እና ለሚለውጡ እናቶቻችን፣ እህቶቻችን፣ ሚስቶቻችንና ሴት ልጆቻችን የላቀ ክብር እንሰጣለን። 🙏🏾 የእናንተ ጥንካሬና ፍቅር የሁላችንም መሰረት ነው።

ቀኑ የፍቅር እና ብርሃን ይሁንላችሁ! ✨

​#ዓለምአቀፍየሴቶችቀን
ጤና💚ደስታ😁ልህቀት🧠
ሰብዓዊ ምህንድስና
@SelfEngineering
❤4🔥1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
​"ስሜት እንደ ሶዳ ( ለስላሳ) ነው፤ ካፈንከው መፈንዳቱ አይቀርም።

​ቀስ ብለህ ብትከፍተው ግን (Allowing emotions)፣ በሰላም ይቀዳል።

ሁልጊዜ መፍትሄው ስሜትን አፍኖ መያዝ (Suppressing emotions) ሳይሆን፣ ተረድቶና አስተናግዶ ማለፍ ነው።"

መልካም ሰኞ 🫶

ጤና💚ደስታ😁ልህቀት🧠
ሰብዓዊ ምህንድስና
@SelfEngineering
❤2🔥1
💡

​ስለ ራስዎ ምህንድስና ጠይቀው የማያውቁትን ለመጠየቅና አዳዲስ ግንዛቤዎችን ለማግኘት ልዩ የጥያቄና መልስ (Q&A) ምሽት አዘጋጅተናል።

በዚህ ረቡዕ በ @KhulWorld ቻናል እንገናኝና በሰዋዊ ጉዳዮች ላይ በዝርዝር እንወያይ።

​መቼ፦ ዛሬ ማታ
​ሰዓት፦ 1:00 ሰዓት (ምሽት)

ጥያቄና መልስ ​በቀጥታ ስርጭቱ ላይ ተገኝተው የውይይቱ ንቁ ተሳታፊ ይሁኑ!

ጤና💚ደስታ😁ልህቀት🧠
ሰብዓዊ ምህንድስና
@SelfEngineering | @KhulWorld
አንዳንዶቻችን በቡና ጠረን ቀናችን ይበራል፤ ሌሎች ደግሞ በሻይ ረጋ ብለው መጀመርን ይመርጣሉ።

የእናንተ ምርጫ የትኛው ነው? ☕️🍵

​"ቡና ወይስ ሻይ ትመርጣለህ/ትመርጫለሽ? እንዴትስ ነው የምትጠጣው/የምትጠጪው?" 👇

ይህንን ካርድ ለቡና ወይም ለሻይ አፍቃሪ ጓደኛህ ላክለት/ላት።" ✨

አስተያየታችሁን በኮሜንት አጋሩን! ☕️🍵

ጤና💚ደስታ😁ልህቀት🧠
ሰብዓዊ ምህንድስና
@SelfEngineering | @KhulWorld
👏1
በዚ ሳምንት ምን አለ? 🤔

​እራስን ለማሳደግና ለማስተዋል የሚረዱ የሰብዓዊ ምህንድስና መርሃ ግብሮቻችን እንደሚከተለው ቀርበዋል፦

​🔹 ቅኝተ ህይወት | የንቃተ ህሊና ልምምድ (Awareness Practice)

​ውስጣዊ ማንነታችንን የምናስተካክልበት ልዩ መርሃ ግብር። ሙሉ በሙሉ በልምምድ እና በወቅታዊ መገኘት (Presence) ላይ ያተኩራል።

​👉 መቼ፦ በዚህ ረቡዕ
👉 ሰዓት፦ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት
👉 ለመሳተፍ፦ ምዝገባ ያስፈልገዋል (ቦታዎን በ @Khulservice ያስይዙ)

​🔹 የሰብዓዊ ምህንድስና (Self Engineering ) | የቀጥታ የጥያቄና መልስ ውይይት

​ይህ የተለመደ የጥያቄና መልስ መርሃ ግብር አይደለም፤ በጋራ የምንወያይበት፣ ሃሳቦችን የምናንሸራሽርበት የቀጥታ ስርጭት
ነው።

​👉 መቼ፦ በዚህ ረቡዕ
👉 ሰዓት፦ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት
👉 መግቢያ፦ በቴሌግራም (@khulworld) በነፃ ይቀርባል

​በጥያቄና መልስ ውይይቱ ወይስ በልምምዱ ላይ ይሳተፋሉ? ወይስ በሁለቱም? ከታች ባለው አስተያየት ያሳውቁን! 👇

ጤና💚ደስታ😁ልህቀት🧠
ሰብዓዊ ምህንድስና
@SelfEngineering | @KhulWorld
❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ርህራሄና አድናቆት ለምናከናውነው ነገር ሁሉ መሰረት ናቸው። ✨

​የሁላችንንም ስኬትና ደህንነት የሚያረጋግጠው የእለት ተእለት ቁርጠኝነታችን ነው። ❤️

​ሁላችሁንም እንወዳችኋለን!✨

ዛሬ ቀኑን ለየት ያለ ቦታ ላላችሁ ሰዎች ያላችሁን ፍቅር በመግለጽ እንድትጀምሩ እንጋብዛችኋለን። ✨

​መልካም ሰኞ 😊

​ጤና💚ደስታ😁ልህቀት🧠
ሰብዓዊ ምህንድስና
@SelfEngineering | @KhulWorld
❤3🔥1
ልዩ የጥያቄና መልስ ምሽት✨

በየሳምንቱ ረቡዕ እንደምናደርገው፣ በዚህም ሳምንት በሰውኛ ጉዳዮች ዙሪያ ሀሳቦችን ለማንሸራሸር ቀጠሮ ይዘናል።

📅 ቀን፦ ረቡዕ (መጋቢት 16)
⏰ ሰዓት፦ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ
📍 ቦታ፦
@KhulWorld የቴሌግራም ቻናል

🦋 ልዩ ማሳሰቢያ፦ በውይይቱ ወቅት በቀጥታ ለመሳተፍ ካልተመቻችሁ በ @khulservice በኩል በጽሁፍ መላክ ትችላላችሁ።

የቀጥታ ስርጭቱን ተቀላቅለው የለውጥ አካል ይሁኑ!

ጤና💚 ደስታ😁 ልህቀት🧠
ሰብዓዊ ምህንድስና
@SelfEngineering | @KhulWorld
❤1
የልቦና ልህቀት — ዛሬ ምሽት! ✨

​በህይወት ሩጫ ውስጥ ራሳችንን የምናዳምጥበት፣ የውስጥ ሰላማችንን የምንፈልግበት እና አዳዲስ የህይወት ቅኝቶችን የምንማርበት ልዩ ጊዜ ያስፈልገናል።


"ቅኝተ ህይወት" የልቦና ልህቀት የልምምድ ሳምንት ለዚህ ትልቅ ዕድል ይዞላችሁ ቀርቧል።
​ይህ ፕሮግራም ሙሉ በሙሉ በኦንላይን (Online) የሚካሄድ በመሆኑ፣ ባላችሁበት ሆናችሁ መካፈል ትችላላቹ ::

​📅 ቀን፦ ዛሬ ረቡዕ፣ መጋቢት 16 ቀን 2018
🕑 ሰዓት፦ ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ
📍 ቦታ፦ በዝግ የኦንላይን ግሩፕ (Online Private Group)


​🔗 ለመመዝገብ እና የግሩፑን ሊንክ ለማግኘት፦ ስምዎን እና #ቅኝተህይወት ብለው በቴሌግራም ለ @khulservice ይላኩ።

ወይም በስልክ መስመራችን +251932333382 ላይ ይደውሉልን።

​የነገው ዕለት የለውጥ ጅምር እንዲሆንላችሁ ቀጠሮአችሁን ከእኛ ጋር አድርጉ። በኦንላይን እንገናኝ! 🌿

ጤና💚 ደስታ😁 ልህቀት🧠
ሰብዓዊ ምህንድስና
@SelfEngineering | @KhulWorld
❤3
🌟 የሐሙስ ጉርሻ | Tips Thursday 💧

🏗 የሰብዓዊ ምህንድስና አምድ፡ ንቃተ አካል (Body Consciousness)

"በቀን 8 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት ይመከራል"

የሚለው ምክር በጣም የተለመደ ቢሆንም፣ በንቃተ አካል እይታ ስለ ጉዳዩ ማወቅ ያለብን ጥቂት እውነታዎች አሉ፦

📌 መነሻው፦ ይህ "8x8" የሚባለው ሕግ ለመያዝ ቀላል ስለሆነ የተፈጠረ እንጂ፣ ለሁሉም ሰው የሚሰራ ጥብቅ የሳይንስ ቀመር አይደለም።

⚖️ የሰውነት ልዩነት፦ የሚያስፈልግህ የውሃ መጠን እንደ ክብደትህ፣ ለሚሰራው ስራ (እንቅስቃሴ) እና እንደ አየር ንብረቱ ይለያያል። ዛሬ መጋቢት 29 አየሩ እየሞቀ ስለሆነ ሰውነትህ ተጨማሪ ውሃ ሊፈልግ ይችላል።

🍉 ከምግብ የሚገኝ ውሃ፦ በቀን ውስጥ ከምንወስደው የውሃ መጠን 20% የሚሆነው ከምንመገባቸው ምግቦች (እንደ ፍራፍሬና አትክልት) የሚገኝ ነው።

🔍 ዋናው መለኪያ፦ የሰውነትህ ምርጥ የውሃ መለኪያ ጥማት ነው። ንቃተ አካል ማለት የሰውነትህን ፍላጎት ማዳመጥ ነው። ጥማት ሲሰማህ መጠጣትና የሽንት ቀለምህን ማየት (ቀለሙ ነጭ ወይም ፈዘዝ ያለ ቢጫ ከሆነ በቂ ውሃ አግኝተሃል) በቂ ነው።

💡 የዛሬው መልዕክት፦ ውሃን አንዴ አዝርቶ ከመጠጣት ይልቅ፣ ቀኑን ሙሉ በየመሃሉ መጠጣቱ ለሰውነት የተሻለ ጥቅም ይሰጣል። አካላችንን በመንከባከብ የውስጥ ሰላማችንን እናሳድግ።

#TipsThursday #SelfEngineering #ንቃተአካል #BodyConsciousness

ጤና💚 ደስታ😁 ልህቀት🧠
ሰብዓዊ ምህንድስና
@SelfEngineering | @KhulWorld
❤4
መልካም አዲስ ሳምንት! 🌟

የሰብዓዊ -ምህንድስና (Self-Engineering) አምስቱ ክንፎች!


በየሳምንቱ በእነዚህ አምስት ዋና ዋና የግንዛቤ ዘርፎች ላይ ትኩረት በማድረግ ራሳችንን እንገነባለን፦

👉 ንቃተ አካል — ለጤናችንና ለሰውነታችን ትኩረት መስጠት።

👉 ንቃተ ኣእምሮ — አመለካከታችንን ማሳደግና አዳዲስ ነገሮችን መማር።

👉 ንቃተ ልቦና — ስሜታችንን መረዳትና ውስጣዊ ሰላም ማግኘት።


👉 ንቃተ ህሊና — በቅንነትና በንቃት መኖር።

👉 ንቃተ ህይወት — የአራቱ ቁርኝት ።


የዚህ ሳምንት ትኩረታችን ንቃተ አካል ይሆናል።

አብራችሁን ሁኑ! 🔥

ጤና💚 ደስታ😁 ልህቀት🧠
ሰብዓዊ ምህንድስና
@SelfEngineering | @KhulWorld
❤5
የሽልማት ጥያቄ! 🏃‍♂️🏃‍♀️

ይሳተፉ! ያሸንፉ! 🎟️

​ጥያቄ፦ ከአራቱ የክሁል ክንፎች (4 Wings) ውስጥ ቢያንስ አንዱን ጥቀሱ?

Hint ❤️

​ትክክለኛውን መልስ ከሚሰጡት መካከል 2 እድለኞችን መርጠን የነገውን ልዩ የ"ቅኝተ ህይወት " (Life Tuning) ዝግጅት ቲኬት እንሸልማለን።


እድሉ እንዳያመልጥዎ! ✨

​👉 ቦታ ለመያዝ፦ #ቅኝተህይወት ብለው ስም እና ስልክ ቁጥርዎን በ @khulservice ይላኩ።

📞 ለበለጠ መረጃ፦ 0932333382

ጤና💚ደስታ😁ልህቀት🧠
ሰብዓዊ ምህንድስና
@SelfEngineering | @KhulWorld
👏1
ሰብዓዊ ምህንድስና 💚 Self Engineering
የሽልማት ጥያቄ! 🏃‍♂️🏃‍♀️ ይሳተፉ! ያሸንፉ! 🎟️ ​ጥያቄ፦ ከአራቱ የክሁል ክንፎች (4 Wings) ውስጥ ቢያንስ አንዱን ጥቀሱ? Hint ❤️ ​ትክክለኛውን መልስ ከሚሰጡት መካከል 2 እድለኞችን መርጠን የነገውን ልዩ የ"ቅኝተ ህይወት " (Life Tuning) ዝግጅት ቲኬት እንሸልማለን። እድሉ እንዳያመልጥዎ! ✨ ​👉 ቦታ ለመያዝ፦ #ቅኝተህይወት ብለው ስም እና ስልክ ቁጥርዎን በ @khulservice…
🏃‍♂️🏃‍♀️ ትላንት በጠየቅነው የሽልማት ጥያቄ ላይ የተሳተፋችሁ ሁሉ እናመሰግናለን! 🏃‍♂️🏃‍♀️

🎉 እንኳን ደስ አላችሁ! 2 እድለኞች መርጠናል! 🎉

1.Tigist
2. Sara

ዛሬ ማታ ለሚካሄደው ልዩ የ"ቅኝተ ህይወት" (Life Tuning) ዝግጅት ቲኬት ተሸልማችኋል! የዝግጅቱ ቲኬታችሁን በ @khulservice ላይ በውስጥ መስመር በመጠየቅ መውሰድ ትችላላችሁ።

ሰፋ ያለ ማብራሪያ:

ክሁል ወርልድ (Khul World) አራት ዋና ዋና የስራ ክንፎች አሉት።

ክሁል ዌልቢንግ (Breathe love)፡- የአካል እና የአእምሮ ጤናን ለማሻሻል የሚያግዙ ፕሮግራሞች እና ዝግጅቶች (ለምሳሌ፡ ዮጋ፣ paint and meditate, wholeness retreat, Ecstatic Dancing....)

👉 ይከተሉ፦ @KhulWorld

ሰብዓዊ ምህንድስና (Self Engineering)፡- ራሳችንን እንድንረዳ፣ ጤንነታችንን እንድናሻሽል እና ህይወታችንን እንድንለውጥ የሚረዱ የመስመር ላይ ፕሮግራሞች (ለምሳሌ፡ ቅኝተ ህይወት, ፖድካስቶች፣ ትምህርቶች... )።

👉 ይከተሉ፦ @SelfEngineering

ክሁል ኮርፖሬት (Khul Corporate)፡- ለድርጅቶች የተዘጋጁ የለውጥ እና የዌልቢንግ ፕሮግራሞች። ( ከቀናቶች እስከ አመታቶች)

👉 ይከተሉ፦ @KhulCorporate

ክሁል ስቶር (Khul Store)፡- ለConscious Living የሚያስፈልጉ የጤና እና የአኗኗር ዘይቤ ምርቶች እና መለዋወጫዎች።

👉 ይከተሉ፦ @KhulStore11

ዛሬ ማታ በ"ቅኝተ ህይወት" ዝግጅት ላይ እንገናኝ!

👉 ቦታ ለመያዝ፡- #ቅኝተህይወት ብለው ስም እና ስልክ ቁጥርዎን በ @khulservice ይላኩ።
📞 ለበለጠ መረጃ፦ 0932333382

ሰብዓዊ ምህንድስና
@SelfEngineering | @KhulWorld
👌1
🔍 ስለ "ንቃት አካል" (Niqate Akal) ?

​ዛሬ ትኩረታችን ንቃት አካል ላይ ነው። ሰብዓዊ ምህንድስናን (Self-Engineering) ለመረዳት የመጀመሪያው እርምጃ የሰውነታችንን አሠራር፣ ፍላጎት እና የሚሰጠንን ምልክቶች በንቃት መከታተል ነው።

​ይህ ምስል ንቃት አካልን በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ያብራራል፦

​1️⃣ ክፍል 1፦ የአካል ንቃት (Body Awareness)

✨ ​ይህ ማለት በሰውነትዎ ውስጥ "መገኘት" (Being inside your physical self) ማለት ነው።
✨ ​የአእምሮ እና የአካል ትስስር፦ የልብ ትርታዎን፣ የአተነፋፈስዎን ሁኔታ እና የውስጥ ስሜትዎን በትኩረት ማዳመጥ።

​2️⃣ ክፍል 2፦ የሰውነት ምልክቶችን መፍታት (Decoding Body Signals)

🫳 ​ሰውነትዎ በቋንቋ ሳይሆን በምልክት ይናገራል፤ እነዚህን "ኮዶች" ለማወቅ 👇

✨ ​የጭንቀት ምልክት (Stress)፦ ለምሳሌ የትከሻ መወጠር ወይም መንገጭላን ማጥበቅ።
✨ ​የውሃ ማነስ (Brain Fog)፦ የትኩረት ማጣትና የአእምሮ መጋረድ ስሜት።
​ጥቅሙ፦ ምልክቶቹን ሲረዱ ለሰውነትዎ የሚሰጡት ምላሽ ትክክለኛ ይሆናል

​3️⃣ ክፍል 3፦ ንቁ ጥገና (Active Maintenance)

🫳 ​ሰውነትዎ እንደ መኪና ወይም ማሽን መደበኛ ጥገና ይፈልጋል።
✨ ​ተግባራዊ እንቅስቃሴ፦ ሰውነትዎን ማሳሳብ (Stretching) እና ተንቀሳቃሽነትን መጠበቅ።
✨ ​ንቁ እረፍት፦ እንቅልፍ ማለት የጠፋ ጊዜ ሳይሆን ሰውነት ራሱን የሚጠግንበት (Active Repair) ሂደት ነው።

መልካም ሰኞ 👐
​መልካም የንቃት ሳምንት! ✨
ሰብዓዊ ምህንድስና
@SelfEngineering | @KhulWorld
❤3🔥1
​🌟 ቅኝት ህይወት
​
ራሳችንን የምናገኝበት፣ የምናድግበትና የደስታ ምንጫችንን የምንቃኝበት የረቡዕ ምሽት ፕሮግራማችን እነሆ ደርሷል!

​በክሁል የሁለንተናዊነት ማዕከል (Khul Wholeness Center) የሚዘጋጀው ሳምንታዊው የሰብዓዊ ምህንድስና ፕሮግራም የፊታችን ረቡዕ ይጠብቆታል።

​📅 ቀን፦ ረቡዕ መጋቢት 30
🕗 ሰዓት፦ ምሽት 2:00
📍 ቦታ፦ በኦንላይን (ከአሉበት ሆነው)

​ጠቃሚ መረጃ፦ ፕሮግራሙ በክፍያ (Commitment Fee) የሚቀርብ መሆኑን እንገልጻለን።

​እንዴት መመዝገብ ይቻላል?

ለበለጠ መረጃ እና ለመመዝገብ በውስጥ መስመር (DM) ስሞ እና #ቅኝተህይወት ብለዉ @khulservice ወይም +251932333382 ላይ ይላኩ

ጤና💚ደስታ😁ልህቀት🧠
ሰብዓዊ ምህንድስና
@SelfEngineering | @KhulWorld
❤1
​ለዛሬው ምሽት ቅኝተ ህይወት መርሃ-ግብር እንደ ሁልጊዜው እድለኛ የሆኑ ሰዎችን በነፃ ለመጋበዝ (Giveaway) ዝግጅታችንን ጨርሰናል።

​ለመሳተፍ የሚከተለውን ጥያቄ ይመልሱ፦

ክሁል ሁለንተናዊነት ማዕከል (Khul Wholeness Center) ቢሮ የት ነው የሚገኘው (Location) ?

​መመሪያዎች፦

​ቀድመው ትክክለኛውን መልስ የሚሰጡ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሰዎች የነፃ መግቢያ ትኬት ያሸንፋሉ።

​ከዚህ በፊት በነፃ መግቢያ (Giveaway) አሸንፈው የሚያውቁ ተሳታፊዎች ለዚህኛው ዙር አይካተቱም።

​መልካም እድል!

ለመመዝገብ በውስጥ መስመር (DM) ስሞ እና #ቅኝተህይወት ብለዉ @khulservice ወይም +251932333382 ላይ ይላኩ

ጤና💚ደስታ😁ልህቀት🧠
ሰብዓዊ ምህንድስና
@SelfEngineering | @KhulWorld
❤2
መስዋዕትነትና ፍቅር በሚታሰብበት በዚህ ቅዱስ ዕለት፣ በቸርነትና በአዲስ ተስፋ አብረን እንድንጓዝ እንመኛለን።

እንኳን ለስቅለት በዓል አደረሰን ! ❤️✨"


ጤና💚ደስታ😁ልህቀት🧠
ሰብዓዊ ምህንድስና
@SelfEngineering | @KhulWorld
🔥2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
When was the last time you were a gift—to yourself and to others? 🎁✨

Happy new day, new breath, new moment & happy Holiday to my global family! It’s that time of year again where service fills my life. I call it my Service Birthday.

Deep Gratitude to all of you who have joined me in service For the past 13 years, from orphanages to prisons, from Soil care to planting, from #Forgiveness Campaigns to even walking 100+kms from Addis to Adama, this journey has been enriching.

Today, for my 14th year, I’m inviting you to a new challenge I designed: #iAppreciate 🌊

Why?
One of our deepest human desires is to be seen, heard, and recognized. While there can be much to complain about, the science shows that both giving and receiving appreciation creates a powerful biochemical shift in our systems. It heals. It connects. It engineers a better state of being.

The #iAppreciate Challenge (3x3x3 game):
1️⃣ Pick 3 People: Friends, family, or someone you haven’t spoken to in a long time.
2️⃣ Send Specific Appreciation: Send them (message/voice note) specific to why you appreciate the person
3️⃣ Create the Ripple: Ask them to pay it forward to 3 more people and share your experience in our Appreciation Library.

How to join the movement:
✅ Comment #iAppreciate below so I DM you the challenge template, link to the Appreciation Library & mini gift for your Participation
✅ Forward this to 3 people, who deserve some appreciation and can play along

As I always say: We all came as a gift to Mother Earth... may your gift shine the path of many. 🕯

Much love & Appreciation,
Happy (Yoftahe)

#iAppreciate #ServiceBirthday #14 #SelfEngineering #AppreciationLibrary #SpreadLight
❤1
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ! መልካም የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ።

ጤና💚ደስታ😁ልህቀት🧠
ሰብዓዊ ምህንድስና
@SelfEngineering | @KhulWorld
❤1
ልዩ የጥያቄና የሀሳብ ሽርሽር ምሽት✨

በየሳምንቱ ረቡዕ እንደምናደርገው፣ በዚህም ሳምንት በሰውኛ ጉዳዮች ዙሪያ ሀሳቦችን ለማንሸራሸር ቀጠሮ ይዘናል።

📅 ቀን፦ ረቡዕ ( Apr 15)
⏰ ሰዓት፦ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ
📍 ቦታ፦ @KhulWorld የቴሌግራም ቻናል

🦋 ልዩ ማሳሰቢያ፦ በውይይቱ ወቅት በቀጥታ ለመሳተፍ ካልተመቻችሁ በ @khulservice በኩል በጽሁፍ መላክ ትችላላችሁ።

የቀጥታ ስርጭቱን ተቀላቅለው የለውጥ አካል ይሁኑ!

ጤና💚 ደስታ😁 ልህቀት🧠
ሰብዓዊ ምህንድስና
@SelfEngineering | @KhulWorld
❤1
GIVEAWAY TIME! ✨

🎟️ Tell us the best thing you did this Easter ?

2 lucky winners 🫶 will get a free ticket 🎟 for Awareness Practice 👐

🔗 Registration ፦ send name and #Awareness to @khulservice or +251932333382

KhulWorld | Human Possibilities
@SelfEngineering @KhulWorld
❤1👍1