ShegerApps.com - Helpful APPs & Games
473 subscribers
160 photos
9 videos
16 files
178 links
Apps made by Ethiopians, to the world.

Join us, make your life a lot easier using our APPs.

Subscribe on Youtube:
http://bit.ly/SammyYoutube

Like us on Fb:
https://www.facebook.com/HelpfulAPPsAndGames

Website:
http://shegerapps.com

Admin:
@Sammy444
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህ አስተማሪ ቪዲዮ ተመልከቱት!!
እንዲሁም ለወዳጆ አጋሩት።

- እንዴት ማስክ ማድረግ እና ማውለቅ እንዳለብን

- እንዴት ሊፍቶችን መንካት እንዳለብን

- እንዴት በሮችን መክፈት እና መዝጋት እንዳለብን

-ሰላምቶቻችን እንዴት መሆን እንዳለባቸው።

@SammyStudio
#በኮሮና ቫይረስ የተያዙ አራት 4 ተጨማሪ ሰዎች በመገኘታቸው በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር #አስራ_ስድስት 16 መድረሱን የጤና ሚኒስትር አስታወቀ።

Rest in home🏠 or rest in peace⚰️

ምርጫው የራሳችን ነው!!
#መጋቢት 18፣ 2012

መንግስት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሚወሰዱ አዳዲስ እርምጃዎችን ይፋ አደረገ፣

በዚህም መሰረት፦

1. ከዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ የሚደርሱ እና ለለይቶ መከታተያ በተዘጋጁት ሆቴሎች ለመቆየት አቅም የሌላቸው መንገደኞች ወደ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ተዛውረው ከውጪ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ መንገደኞች ለ15 ቀናት ተለይተው እንዲቆዩ የወጣውን መመሪያ ተግባራዊ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

2. ከዛሬ አንስቶ ለተጨማሪ ሁለት ሳምንታት ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማትን ጨምሮ፣ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው የሚቆዩ ይሆናል፡፡

3. በገበያ ስፍራዎች እና በሀይማኖት ተቋማት ውስጥ ማኅበራዊ ርቀትን መጠበቅ በጥብቅ ተፈጻሚ ሊደረጉ ያስፈልጋል፡፡ የፌደራል መንግሥት አስከፊ ብሔራዊ አደጋ በሚከሰት ጊዜ ሀይማኖታዊ ስብሰባዎች እንዲቋረጡ የማድረግ ሕገመንግሥታዊ መብት አለው፡፡ ሆኖም፣ በሕገ መንግሥቱ የተደነገጉትን እርምጃዎች ተግባራዊ ከመደረጋቸው በፊት፣ ዜጎች የማኅበራዊ ርቀት መመሪያን ተግባራዊ እንዲያደርጉ በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

4. ሁኔታው ተጨማሪ ድጋፍን የሚጠይቅ ከሆነ ሁሉም ጡረታ የወጡ እንዲሁም በትምሕርት ላይ ያሉ የሕክምና ባለሙያዎች ለብሔራዊ ግዳጅ እንዲዘጋጁ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡

5. የተለያየ መጠን እና ዓይነት ያላቸው መገልገያዎችን የያዙ ከ134 በላይ ተቋማት ለለይቶ መከታተያ፣ ለይቶ ማቆያ እና ሕክምና እንዲሆኑ ተለይተዋል፡፡ ስለዚህ፣ መንግሥት ሁሉም ዜጎች እንደ አልጋዎች፣ ፍራሾች፣ አንሶላዎች፣ የመተንፈሻ ቬንትሌተሮች እና ሌሎች ከሕክምና ጋር ተያያዥነት ያላቸው እና የሌላቸው መገልገያዎችን ለማሰባሰብ በመሥራት ላይ የሚገኘውን የብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ጥረት እንዲደግፉ ጥሪ ያቀርባል፡፡

6. የማክሮ-ኢኮኖሚ ንዑስ ኮሚቴው የኢኮኖሚ ዘርፉን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ አማራጮችን ለመቀየስ በልዩ ልዩ ዘርፍ ከተሠማሩት ዐበይት የኢንደስትሪ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይትን ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ይህንኑ ተከትሎም፣ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የሚከተሉት እርምጃዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡-

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስፈልጉ የገቢ ዕቃዎች እና ግብአቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ ይደረጋል፡፡

የፋይናንስ ዘርፉን ጤንነት አስጠብቆ የመቀጠል እና ባንኮች በኮቪድ-19 ቫይረስ ለተጎዱ ደንበኞቻቸው ጊዜያዊ የብድር እፎይታ እና ተጨማሪ ብድር ለመስጠት እንዲያስችላቸው፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተጨማሪ 15 ቢሊየን ብር ለግል ባንኮች ይሰጣል፡፡

የውጪ ምንዛሬ የሚያስፈልጋቸው እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስችሉ ዕቃዎችን እና ግብአቶችን ወደ ሀገር ውስጥ ለሚያስገቡ አስመጪዎች ባንኮች ቅድሚያ በመስጠት እንዲያስተናግዱ ይደረጋል፡፡

በፋይናንስ አገልግሎት የተነሳ ገጽ ለገጽ መገናኘት እና የብር ንክኪን ለመቀነስ እንዲቻል፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሞባይል አማካኝነት የሚደረግ ክፍያ እና ገንዘብ የማስተላለፍ ጣሪያውን ከፍ ያደርጋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለውጭ ገበያ በሚቀርብ አበባ ላይ የጣለው ዝቅተኛ የመሸጫ ዋጋ ገደብ በጊዜያዊነት እንዲነሳ ተደርጓል፡፡

ኩባንያዎች የተሻለ የገንዘብ ፍሰት እንዲኖራቸው ለማስቻል፣ የገቢዎች ሚኒስቴር የተጨማሪ እሴት ታክስ አመላለስ ሂደቱን በተለየ መልኩ እንዲያፋጥን ይደረጋል፡፡

የኮቪድ-19ን ወረርሽኝ ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን የሸቀጦች እጥረት እና አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ለመቆጣጠር በንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር የጀመረው ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
━━━━━━━━━━━━━━━
📢: @SammyStudio
━━━━━━━━━━━━━━━
🖍ኢትዮጵያ የባህል መድሀኒት አግኝታለች‼️

ለኮሮና ተዋህሲ ባህላዊ መድሃኒት ኢትዮጵያ አግኝታለች በማለት የሳይንስና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በፌስ ቡክ ገፁ አሳወቋል ።

ምርምሩ የኮሮና ቫይረስ በዓለም ላይ መከሰቱ ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ ከተለያዩ በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጪ ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ተደጋጋሚ የምርመር ሂደት አልፎ ወደ ምርት እና ቀጣይ የእንስሳት ፍተሻ እና ክሊኒካል ፍተሻ ስራዎች እንዲሸጋገር ተደርጓል።

መድሃኒቱ የመከላከል አቅም የሚጨምር፣ መርዛማነት የሌለው እና አዋጭነቱ የተረጋገጠ ነው፡፡ የምርምር ሂደቱ ተጠናቅቆ ወደ ምርት ለመግባት ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን ዝርዝር መረጃዎችን በተመለከተ ዛሬ
መግለጫ ይሰጣል፡፡

VIA ተስፋዬ ጌትነት ፣ MIT-Ethiopia
━━━━━━━━━━━━━━━
📢: @SammyStudio ━━━━
የኮቪድ19 በሽታ የየቀኑ ምልክቶች
*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=
፨ ከ1-3 ቀን
. በነዚህ የመጀመሪያ ቀናት ቀላል ጉንፋን መሰል ሆኖ ቀለል ያለ ትኩሳት እና የጉሮሮ ህመም ብቻ ሲኖር የምግብ እና መጠጥ ፍላጎት ጥሩ ነው ።
. የሰውነት መከላከያ ደከም ያለባቸው ስዎች ቀለል ያለ ተቅማጥ እና ማቅለሽለሽ ሊኖራቸው ይችላል ።

፨ በ 4 ኛው ቀን
. የጉሮው ህመም ይጨምራል እንደዚሁም የድምፅ መወፈር ይኖራል ።
. ብዙ ጊዜ ትኩሳት አይኖርም 36.5 degree ብቻ ይሆናል
. ቀለል ያለ እራስ ምታት እና የምግብ እና መጠጥ ፍላጎት ሊስተገዋጎል ይችላል ።

፨ በ 5 ኛው ቀን
. ስሜቶች የበለጠ ይጨምራሉ ፦ የጉሮሮ ህመም ይጨምራል ፣ ድምፅ የበለጠ ይጎረንናል ።
. በእንቅስቃሴ ወቅት የስውነት ህመምና ቁርጥማት ይኖራል ፤ የሰውነት ድካም ይኖራል ።

፨ በ 6 ኛው ቀን
. ትኩሳት ይጀምራል
. ደረቅ ሳል ከጉሮሮ ህመም ጋር ይበረታል
. ምግብ በመመገብ ፣ የሚጠጣ ነገር ሲወስድ እንደዚሁም በንግግር ጊዜ የጉሮሮ ህመም ይኖራል ።
ተቅማጥና ማቅለሽለሽ የበለጠ ይጨምራል ።

፨ በ 7 ኛው ቀን
. ትኩሳት ከ 38 ድግሪ በላይ ይሆናል
. ደረቅ ሳል ይኖራል ፣ ይጨምራል
. የስውነት ቁርጥማት ፣ ራስ ምታት ፣ ተቅማጥና ማቅለሽለሽ ይጨምራል ።

፨ በ 8 ኛው ቀን
. መተንፈስ መቸገር
. የደረት መክበድና ህመም
. ደረቅ ሳል ይኖራልም ይጨምራልም
. የስውነት ቁርጥማት ፣ ራስ ምታት ይቀጥላልም በጣም ይጨምራል ።
. ትኩሳት ይቀጥላል ፣ ይጨምራል

፨ በ 9 ኛው ቀን እና በሚቀጥሉት ቀናት
. ሁልም ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች በጣም ይጨምራሉ ።

⚠️ማንኛው ስው የሚከተሉት አደገኛ ምልክቶች ካሉ በአፋጣኝ ወደ ህክምና ተቁአም መሄድ ያስፈልጋል ።
፧ የተራዘመ ድረቅ ሳል
፧ የትንፋሽ ማጠር
፧ የደረት ህመም
፧ ከፍተኛ ትኩሳት
━━━━━━━━━━━━━━━
@SammyStudio
━━━━━━━━━━━━━━━
☞ሼር በማድረግ ሃላፊነቶን ይወጡ!!!
🚨ተጠንቀቁ -- ሼር‼️

እንደሚታወቀው በበሽታው ምክንያት ሁላችንም ጭንቀት ውስጥ ነን። ነገ የፈረንጆቹ አፕሪል 1 ወይም April fools day ነው። ስለዚህ ሀላፊነት የሌለው አንዳንድ ድንዙዝ ሰው አይጠፋም እና ነገ ከበድ ያለ ነገር በማህበራዊ ሚዲያም ይሁን ሰዎችም ቢነግሯችሁ ሳታጣሩ ምንም እርምጃ አትውሰዱ። ቅድመ ማስጠንቀቂያ ነውና ብዙዎች እንዳይሸወዱ በጭንቅ ላይ ጭንቅ እንዳይሆንባቸው ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ አጋሩ!!

Share @SammyStudio
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቤትዎ ሆነው በአዲሱ ኢትዮጵያዊ አፕሊኬሽናችን ፈታ ዘና ይበሉ

Check out "ቃል የአማርኛ ፐዝል - Word Amharic Puzzle"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ethiopian.word.puzzle
🇪🇹 ውድ የሆናችሁ የዚህ ቻናል ተከታታዮች የፌስቡክ አካውንቶትን ሌላ ሰው
ሲጠቀም አጭር የፅሁፍ መልዕክት ሞባይሎት ላይ እንዲደርሶት ማድረግ የሚችሉበትን ቀለል ያለ ዘዴ እነሆ ብለናል።

1.የፌስ ቡክ አካውንቶት ውስጥ በተለመደው ሁኔታ ከገቡ በኋላ ሴቲንግ የሚለውን አማራጭ ይጫናሉ ሴቲንግ የሚለው ቦታ እንደ ምትጠቀሙት ብሮዘራችሁ ሰለሚለያይ ፈልጉት
2. በመቀጠልም ከሚመጡት አማራጮች ሴኪዩሪቲ
ሴቲንግ የሚለውን አማራጭ እንመርጣለን ከዚህ በኋላ ሎግ ኢን አለርት የሚለውን አማራጭ እንጫናለን።
3. ከዚህ በኋላም ከተቀመጡት ሶስት አማራጮች ውስጥ ቴክስት ሜሴጅ የሚለው አማራጭን በመጫን የሞባይል ቁጥሮን ያስገባሉ፡፡
4. በመቀጠልም ሴቭ የሚለውን ቁልፍ ሲጫኑ ወደ ሞባይሎ የማረጋገጫ ኮድ ይልክሎታል ይህ ኮድ ሞባይሉ የእርሶ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚላክ ሲሆን ያንን ኮድ ኮምፒተሩ ላይ በተቀመጠው ክፍት ቦታ በማስገባት ሴቭ ማለት በመጨረሻም ቁጥሮ የገባበትን ምርጫ በመጫን ሴቭ ቼንጅስ የሚለውን ስትጫኑ አክቲቭ ይሆናል፡፡ ከዛም በኋላ የትኛውም ኮምፒውተር ወይም ሞባይል ላይ ፌስ ቡኮት ላይ ሲገቡ መግባቶን በአጭር
ጽሁፍ መልእክት ሞባይሎ ላይ ይደርሶታል ማለት ነው፡፡
አስተውሉ⚠️ ይሄን አክቲቬት አድርገው በስልኮ አጭር የጽሁፍ መልእክት ከተላኮለት ያኔ የፌስቡክ አካውንቶን ሌላ ሰው እየተጠቀመ ነው ማለት ነው ያኔ ቶሎ ብለው የአካውንቶን ሚስጥር ቁጥሮን መቀየር አሎበት።

#ሼር

@SammyStudio
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማወስፈፀሚያ ደንብ ይፋ ሆነ።‼️⬇️

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈፀሚያ ደንቡን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ይፋ አደረገ።

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል፣ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በሚኒስተሮች ምክር ቤት የወጣው ረቂቅ አዋጅ ትናንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅጽደቁ ይታወቃል።

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዋጁን ማስፈፀሚያ ደንብ አጠቃላይ ይዘት በሚመለከት ዛሬ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ማስፈፀሚያ ደንቡ አጠቃላይ አራት ዋና ዋና ከፍሎች ያሉት ሲሆን ይሄውም ክልከላን የሚያስቀምጥ፣ ግደታዎችን የሚጥል፣ የአስፈፃሚ አካላትን ክንውን እንዲሁም ልዩ ለዩ ድንጋጌዎችን የያዘ ነው።

ክልከላን በሚመለከት:

 ማንኛውም ሃይማኖታዊ ይሁን ፖለቲካዊ ስብሰባዎች፣ እድር፣ ደቦ፣ እቁብና ሌሎችም ከ4 ሰው በላይ ስብሰባዎች ክልክል ናቸው።

 ከአራት ሰዎችም ቢሆኑ ሁለት የአዋቂ ሰው እርምጃ የጠበቀ መሆን እንዳለበት አቃቤ ህጓ አብራርተዋል።

 ቀብርና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮች ሲኖሩ ግን እየታዩ ሊፈቀዱ የሚችሉበት አሰራር መኖሩን ጠቁመዋል።

 ታራሚዎች ከጠበቆቻቸው ጋር አስፈላጊው ጥንቃቄ ተደርጎ እንዲገናኙ የሚፈቀድ ቢሆንም ጥየቃ ለሚሄዱ ሰዎች የማይፈቀድ መሆኑ ተገልጿል።

 በፖሊስ የተያዙ እስረኞችንም ስንቅ ከማቀበል በስተቀር መገናኘት የተከለከለ መሆኑን አስረድትዋል።

 በድንበር አካባቢ ከካርጎ፣ የደረቅና ፈሳሽ ጭነት አገልግሎቶች በስተቀር ሌሎች እንቅስቃሴዎች ዝግ ተደርገዋል።

 የቤት ተከራዮች በራሳቸው ፍላጎት ካልወጡ በስተቀር ማስውጣትና ኪራይም መጨመር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተከልክሏል።

 ሰራተኞችን መቀነስና የስራ ቅጥር ውል ማቋረጥም መከልከሉን ወይዘሮ አዳነች አብራርትዋል።

 በዚህ ደንብ መሰረት ተማሪዎችና መምህራን በኦን ላይን ካልሆነ በአካል እንዲገናኙ አይፈቀድም።

 ስፖርታዊ ጨዋታዎች፣ የህፃናትም ይሁን የሌሎች መጫወቻ ስፍራዎች እንዲሁም የእጅ መጨባበጥ ሰላምታ የተከለከለ መሆኑን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 በትራንስፖርት ዘርፍም አገር አቋራጭ ካለው ወንበር ከ50 በመቶ በላይ ተሳፋሪ መጫን የተከለከለ ነው፡፡

@SammyStudio
ShegerApps.com - Helpful APPs & Games
Photo
⛪️⛪️⛪️በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን⛪️⛪️

ለመላው #ክርስቲያን #እንኳን_ለሆሳዕና_በዓል_በሰላም_በጤና_አደረሳችሁ_አደረሰን_አሜን!!!

🌾🌿ሆሳዕና ከጌታችን ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ነው ።
🌾🌿ሆሳዕና ማለት:-የዕብራይስጥ ሲሆን #ትርጉሙም እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን ማለት ነው ።

#ዘወረደ
ብለን ጀምረን
#ሆሳዕና
ብለን ለመጨረስ የረዳን እግዚአብሔር ይመሥገን። ከበዓሉ እርድኤት በረከትን ያሳትፈን ፡፡

ከመጣብ ወረርሽኝም ፈጣሪ አምላክ መድሀኒት ይሁነን አሁን ያድነን አሁን ይባርከን፡፡

አሜን አሜን አሜን🙏
#መልካም_የሆሳዕና_በዐዓል_ይሁንልን
🌿🕊🌾🌿🕊🌾🌿🕊🌾🌿🕊🌾
♥️ወስብሐት ለእግዚአብሔር
♥️ወለወላዲቱ ድንግል
♥️ወለመስቀሉ ክቡር
💚አሜን💛አሜን❤️አሜን

https://t.me/joinchat/AAAAAE9_Op24XtjV3ZC4Yw
📲 ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ ሰባት ምልክቶች
▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃

1. #የስልክዎ_ፍጥነት_ከቀነሰ

#ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ከሌላው ጊዜ በተለየ ትዕዛዞችን ለማከናወን ረዘም ያለ ጊዜ የሚፈጅ ከሆነ፤ ባዕድ ሶፍትዌሮች #(ማልዌር) እያስቸገሩት ነው ማለት ነው።

እነዚህ #ማልዌር የተባሉት ቫይረሶች ዋነኛ ሥራቸው የስልክዎን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማዘግየት ሊሆን ስለሚችል፤ በአፋጣኝ #ማስወገድ ተገቢ ነው።

2. #ስልክዎ_በጣም_የሚግል_ከሆነ

#ስልክዎት ከተለመደው ከፍ ባለ ሁኔታ #የሚግል ከሆነ፤ ችግር አለ ማለት ነው። በፍጥነት #እርምጃ ይውሰዱ አልያም #ባለሙያ ያማክሩ።

3. #የስልክዎ_የባትሪ_ኃይል_ቶሎ_የሚያልቅ_ከሆነ

#ስልክዎ ከፍተኛ #ሙቀት አለው ማለት ደግሞ #የባትሪው ኃይል ቶሎ ቶሎ ያልቃል ማለት ነው።

#ምናልባት ስልክዎ አዳዲስ መተግበሪያዎችንና #ሶፍትዌሮችን ለማደስ በሚሞክርበት ወቅት የባትሪውን ኃይል #ሊጨርስ ይችላል። ነገር ግን ምክንያቱ #ይህ ካልሆነ ስልክዎ #ተጠልፎ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ አለብዎ።

4. #ወደ_ማያውቁት_ሰው_መልዕክት_ከተላከ_ወይም_ከማያውቁት_ሰው_መልዕክት_ከደረስዎ

#ብዙ ጊዜ እርስዎ የማያውቋቸው #መልእክቶች የሚላኩት በዋትሳፕና በመሳሰሉ #መተግበሪያዎች በኩል ሲሆን፤ የሚላከው ደግሞ ወደ ጓደኛዎት አልያም ወደ #የማያውቁት ሰው ሊሆን ይችላል።

ወደ እርስዎ የሚላኩ #መልዕክቶች ደግሞ ብዙ ጊዜ #ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ የሚሉ ማሳሰቢያዎች ይበዟቸዋል።

5. #ከበይነ_መረብ_የሚመጡ_ድንገተኛ_መልዕክቶች

ስልክዎን በመጠቀም በይነ መረብን #(ኢንትርኔት) በሚያስሱበት ወቅት #ወደ ሌላ ድረ-ገጽ #የሚያሸጋግሩ መልዕክቶች በተደጋጋሚ የሚመጡ ከሆነ #የስልክዎ መጠለፍ ነገር እውን ሊሆን ይችላል።

#መልዕክቱን ሲጫኑ በአንድ ጊዜ ወደ #ሁለትና ሦስት የድህ-ረገጾች አድራሻዎች የሚመራዎ ከሆነ በፍጥነት ይውጡ።

6. #አጠራጣሪ_መተግበሪያዎችና_ገንዘብ_ነክ_ጥያቄዎች

አንዳንድ ጊዜ እርስዎ #ያልገዙት ወይም ከበይነ መረብ #ያላወረዱት መተግበሪያ ስልክዎት ላይ ሊመለከቱ ይችላሉ። ምናልባትም #የሞባይል ዳታ እና የጽሁፍ መልዕክት ላይ የዋጋ #ጭማሪም ሊያስተውሉ ይችላሉ።

የክሬዲት ካርድና የሞባይል ገንዘብ ማንቀሳቀሻ መንገዶችን የሚጠቀሙ ከሆነ ይህ ሁኔታ #ለጠላፊዎች ምቹ አጋጣሚ ሊፈጥርላቸው ይችላልና ይጠንቀቁ።

#ስለዚህ የይለፍ ቃሎችንና #የግል መረጃዎችን ስልክዎት ላይ ባያስቀምጡ ይመረጣል፤ አልያም #በጠላፊዎች እንዳይገኝ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

7. #ያልተለመዱ_ድምጾች

#የድምጽ ጥሪ በሚያደርጉበት ወቅት ያልተለመዱና ከዚህ በፊት ያልነበሩ ድምጾች #የሚሰማዎት ከሆን ምናልባት ስልክዎ #የጠላፊዎች ሰላባ ሆኖ ሊሆን ይችላል። ይባስ ብሎም የስልክ ጥሪዎችዎ #እየተቀዱም ሊሆን ይችላል።

━━━━━━━━━━━━━━━
📢: @SammyStudio
━━━━━━━━━━━━━━━


👉👉 #መፍትሄዎች
━━━━━━
▫️የስልክ #ማጽጃዎችን ከታማኝ ምንጭ ማግኘት

▫️እርስዎ #የማያውቋቸውን #መተግበሪያዎች ከስልክዎ ማጥፋት

▫️ብዙ ሰው የሚጠቀማቸው #ነጻ የኢንተርኔት #አገልግሎቶችን አለመጠቀም

▫️ስልክዎን #በቀላሉ ሊታወቅ በማይችል #የይለፍ ቃል መዝጋት

▫️ከማይታወቁ #ምንጮች #መተግበሪያዎችን አለመጫን

▫️ስልክዎና በስልክዎ ላይ ያሉ #መተግበሪያዎችን ቶሎ ቶሎ #ማሳደስ (update)

▫️#የስልክ ክፍያዎንና #የዳታ አጠቃቀምዎን #ይቆጣጠሩ

#መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ።

━━━━━━━━━━━━━━━
📢: @SammyStudio
━━━━━━━━━━━━━━━
Download Here: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ethiopian.word.puzzle

እርሶስ ከየትኛው ወገን ይመደባሉ በፍጥነት ቃላቶቸን ማስታወስ ከሚችለው 10 ፐርሰንት ወይስ ቃላቶችን እስኪመጡለት ድረስ ጊዜ የሚወስድባቸውን 90 ፐርሰንት ያህል ህዝብ።
አሁኑኑ አፕሊኬሽኑን ጭነው የማስታወስ ፣ የመመራመር እናም ችግሮችን የመፍታት ብቃቶን ያሳዩ እንዲሁም ያሳድጉ።

Get it on Telegram: https://t.me/joinchat/AAAAAE9_Op24XtjV3ZC4Yw

More Apps on our website: https://shegerapps.com
Channel name was changed to «Helpful APPs & Games - ShegerApps.com»
Forwarded from Sammy
Helpful APPs & Games - ShegerApps.com, [15.04.20 00:15]
Download Here: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ethiopian.word.puzzle

እርሶስ ከየትኛው ወገን ይመደባሉ በፍጥነት ቃላቶቸን ማስታወስ ከሚችለው 10 ፐርሰንት ወይስ ቃላቶችን እስኪመጡለት ድረስ ጊዜ የሚወስድባቸውን 90 ፐርሰንት ያህል ህዝብ።
አሁኑኑ አፕሊኬሽኑን ጭነው የማስታወስ ፣ የመመራመር እናም ችግሮችን የመፍታት ብቃቶን ያሳዩ እንዲሁም ያሳድጉ።

Get it on Telegram: https://t.me/joinchat/AAAAAE9_Op24XtjV3ZC4Yw

More Apps on our website: https://shegerapps.com
Forwarded from Sammy
ይህንን ከላይ ያለውን አዝናኝ የአማርኛ ፐዝል ተጫውቶ ደረጃ 50 ላይ ቀድመው ለደረሱ 3 ሰዎች የመቶ ብር ካርድ እንሸልማለን … ልክ 50ኛው ደረጃ ላይ ሲደርሱ ስክሪንሻት አድርገው ይላኩልን፡፡ ወዲያውኑ ሽልማቶ በእጆ ይገባል፡፡