Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
በቁድስ ስም መነገድ ይቁም፡፡
የአላህን ትእዛዛት ብትፈፅሙ አላህ ይረዳችኋል፡፡
አል አቅሷን ማስለቀቅ የሚቻለው በአላህ ዲን ላይ በመፅናት ብቻ ነው፡፡
ዛሬ ዛሬ ወደ ዲናችን እንመለስ የሚሉ ሰዎች የነ አል አቅሷና የሌሎች ሙስሊሞች ጉዳዬች የማያገቧቸው ተደርገው እንዲታዩ የጥፋት ተጣሪዎች ይፅፋሉ፡፡ ሺርክና ቢድኣ ከነባለቤቶቹ ማስጠንቀቂያ በተሰጠባቸው ቁጥር “የቁድስ፣ የቦርማ፣ የሶሪያ ጉዳይ አያሳስባችሁም ወይ?” እየተባለ በነቁድስ ስም ይነገዳል፡፡ እነ ቁድስን የጥፋታቸው አለመታረሚያ ሰበብ አድርገው ያቀርቧቿል፡፡ እውነታው ግን ወደ ትክክለኛው የአላህ ዲን ሳንመለስ አይደለም አላቅሷን ማስለቀቅ ይባስ መከራ ውስጥ ነው የምንገባው፡፡
ብዙ በአል አቅሷ ስም የሚነግዱ ግን አላህ ያዘዘውን ለመፈፀም ዝግጁ ያልሆኑ አሉ፡፡
አላህ እኮ የአላህን ህግጋት ብትከተሉ (ብትፈፅሙ) አላህ ይረዳችኋል ሲል ቃል ገብቶልናል፡፡ ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አስተምህሮት እንደተነገረን ደጃል ሁሉን እያጠፋ መግደል የሚያቅተው የእምነት ባለቤት የሆነውን ግለሰብ ነው፡፡ ስለዚህ ደጃል ከባዱ ፈተና ሆኖ ሳ፣ የሁዳዎች ተከትለውት ሲያበቁ አብዛኛን ድል አድርጎ መጨረሻው ሲደርስ ያንን አንድ አማኛ ግለሰብ መግደል ያቅተዋል፡፡ ድል አላህና መልክተኛውን በመታዘዝ ነው፡፡ ውርደት አላህና መልክተኛውን በማመፅ ነው፡፡ ዛሬ አላህን በማመፅ፣ የመልክተኛውን ትእዛዝ በመራቅ ድል ይገኛል የተባለ ይመስል አላህን እያመፁ ኢስላማዊ ስም ይሰጡታል፡፡
አላህ ካዘነላቸው ጥቂቶች ውጭ
- ሙስሊም ነኝ እያሉ በታላላቅ ሺርክ ተጥለቅልቀዋል፣
- ቢድኣ ሙስሊም አገራት ላይ ሳይቀር ነግሶ፣
- የወላጅ ሀቅ እየተበደለና እየተጣሰ፣
- ሰሃባዎች እየተሰደቡና እየተተቹ፣ ብሎም ሰሃባ ተሰዳቢና ለሰሃባ ተሳዳቢ ጥብቅና የሚቆም እንደ አዋቂ እየተያ፣
- ዝሙት ተስፋፍቶ፣
- ወለድ እየተበላ፣
- ጀመኣ ሰላት በተለይ ፈጅር አንድ ሰፍ ሁለት ሰፍ እየተሰገደ (የሰላማዊ ሰልፍ ጊዜ አደባባይ ላይ ሚሊዬኖች ወጥተው)፣
- ሴቶች አላህ የረገመውን ቅንድብ መቀንደብ ማስቀንደብ፣ ዊግ መቀጠል ማስቀጠል፣ ንቅሳት መንቀስ ማስነቀስ እየፈፀሙ፣
- ከቀቁርኣን ተርቆ፣
- መጠጥ እየተጠጣ፣
- አደንዛዡን ጫት እየተቃመ፣
- ሲጋራ፣ ሺሻ እየተጨሰ፣
- ለኳስ ሲሉ ወንድ ልጆች ጀመኣ ሰላትን እየተዉ፣
- ሴቶች ሙሰልሰል እያሉ ፊልም እያዩ፣
- ከሀይማኖታዊ እውቀት ተርቆ እና ሌሎችም ………. መጥፎ ተግባራት እየተሰሩ ……
ቁድስ ልባችን ውስጥ ናት፣ ቦርማ፣ ዋ ሶሪያ እየተባለ በስማቸው ሶሺያል ሚድያ ላይ ይነገዳል፡፡
አል አቅሷን ትላንት ከየሁዳዎች እጅ አስለቅቋት የነበረው ኡመር ኢብኑ አል-ኸጣብ (ረድየላሁ አንሁ) ነው፡፡ ዛሬም ኡመርን የሚሳደቡ ራፊዳ ሺአዎች ወይንም ለነሱ ጥብቅና የሚቆሙት ኢኽዋኖች አያስለቅቋትም፡፡
እስቲ አላህን እንፍራና አላህ ግዴታ ያደረገብንን ሁላችንም በነፍስ ወከፍ እንፈፅም፡፡ ከከለከለን ሁሉ በቁርጥ እንራቅ፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ሲባል ከሚወጣው ሰው በላይ መስጂዳችንን ከፈጅር ሰላት ጀምሮ እናስውበው…….. እና ሌላም ትእዛዛትን መፈፀም ክልከላዎችን እንከልከል፡፡ ከዛም አላህ ይረዳናል፡፡
አላህን እንፍራ ኡመተል ኢስላም በጠቅላላ ወደ አላህ ስንመለስ ሁለት አገር ለስኬት እንበቃለን፡፡ በመጨረሻም ሙስሊሞች በነዚህ የሁዳዎች ላይ ድልን ይጎናፀፋሉ፡፡ አላህ እውነተኛ ሙስሊም ያድርገን፡፡ አል-ቁድስን፣ በርማን፣ ሶሪያም መላው አለም ላይ ያሉ ሙስሊሞችን መከራችንን ያንሳልን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
አፍሪካ ቲቪ ላይ ማስታወቂያቸው ተለቀቀላቸው ስለተባሉት ሩቃ ቤቶች…..
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩሕሩሕ እጅግ በጣም አዛኝ፡፡
ይህች አጭር ፅሁፍ የምትሆነው ሰሞኑን ፌስቡክ ላይ በደንብ ስለ ተራገበው ቲቪ አፍሪካ ላይ ማስተወቂያቸው ስለ ተለቀቀላቸው ሩቃ ቤቶችና ስለሚሰሩት አፀያፊ ተግባር የሚጠቅስ ነው፡፡

ወንድም ኢድሪስ ኢብን ኢልያስ በፃፈው ፅሁፍ ላይ አፍሪካ ቲቪ ላይ ማስታወቂያ ከለቀቁት ሩቃ ቤቶች ውስጥ አብዛኛዎቹ እዚህ መጥፎ ተግባራት ላይ የተሰማሩ መሆናቸው ማስረጃ እንዳለ ጥናት እንዳለም ነግሮኛል፡፡

ይህ ከሆነ እውነታው አፍሪካ ቲቪ ማስታወቂያ ከለቀቁት አጥፊዎች ውስጥ በማስረጃ የተረጋጋጡትን እዛው ቻናል ላይ እነዚህ ሩቃ ቤቶች በዚህ በዚህ ማስረጃ ሙስሊሞችን የሚጎዳ ይህን ይህን ጥፋት ፈፅመዋል ብሎ በግልፅ ማጋለጥ አለበት፡፡
በዚሁ በሶሺያል ሚድያ ላይም እነዚህ መጥፎ ሩቃ ቤቶች ከትክክለኞቹ ይለዩ ዘንድ በስነስርኣት ሊጋለጡ እና ኡማው ሊጠነቀቃቸው ይገባል፡፡
አፍሪካ ቲቪ መጀመሪያ ላይ የነዚህን ሩቃ ቤቶች መጥፎ ስራ ሳይውቅ ቀርቶ ሊሆን ይችላል፡፡ አሁን ግን ጥናት የሰሩ ወንጀሎቹን የተከታተሉ ወንድሞች ስላሉ ያን ማስረጃ ይዞ ሙስሊሙን ማህበረሰብ ይቅርታ ሊጠይቅ፣ ለወደፊቱ እንዲህ አይነት ማስታወቂያዎችን ከመስራቱ በፊት ያ ማስታወቂያ እንዲለቀቅለት የሚፈልገውን ድርጅት አሰራር ከሸሪኣ አኳያ ማጥናት አለበት፡፡ እዚህ ጋር “እኛ ማስታወቂ እናግኝ እንጂ ስለሌላው ምን አገባን” የሚባል አባባል የለም፡፡ ምክንያቱም አፍሪካ ቲቪ እራሱን የሀይማኖት ተቋም አድርጎ ስለሚንቀሳቀስ፡፡

እነዚህ ሙስሊሙ ላይ በእምነቱ፣ በክብሩ፣ በገንዘቡ በተለይ ሴት እህቶቻችን ላይ የተጫወቱ ሩቃ ቤቶች አፍሪካ ቲቪን ተጠቅመው ማስታወቂያቸውን ረጭተው ህዝብ ዘንድ እንደደረሱ ሁሉ አፍሪካ ቲቪ አሁንም ስርጭቱን ተጠቅሞ፣ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ወግኖ፣ ጥቅም ሳያታለው፣ ሀፍረት ሳይዘው፣ እንዲህ አይነት አውሪዎችን ማስጠንቀቅም ከኢስላም ክፍሎች ስለሆነ ስማቸውን ጠቅሶ ተጠንቀቋቸው ማለት አለበት፡፡

በዚሁ ትክክለኛ የሩቃና የባህል ህክምና ቤቶች የምናውቅ ወንድም እና እህቶች ለሙስሊሙ ማህበረሰብ እነዚህ ትክክለኞቹ ጋር እንዲሄዱ መጠቆም አለብን፡፡

ሙስሊሞች ሆይ! እራሳችንን በቁርኣን፣ በሀዲስና ሸሪኣው ባስቀመጣቸው ማር ጥቁር አዝሙድ….. በመሳሰሉት ማከም እንችላለን፡፡
ኢንሻ አላህ በዚህ በኩል ተከታታይ ፅሁፎች መዘጋጀት ይኖርባቸዋለው፡፡
አላህ የታመሙ ሙስሊም ወንድም እና እህቶቻችንን ከበሽታቸው ይፈውሳቸው፡፡
ፍልስጤም መቼ ነው የምትመለስልን?
በሸይኽ ሙሐመድ ሰኢድ ረስላን (ሀፊዘሁላህ)
አለም ላይ ያለ ማንኛውም ሙስሊም “ፍልስጤም መቼ ነው የምትመለስልን?” ብሎ ከጠየቀ
መልሱም “ወደ አላህ (በትክክለኛው እምነት፣ መልካም ስራ፣ አላህና መልክተኛውን በመታዘዝ ክልከላቸውን በመራቅ) ስትመለስ ፍልስጤም ያኔ ትምለሳለች፡፡”
ይህ መልስ ከአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሀዲስ የተውጣጣ (የተጨመቀ) ነው፡፡ ኢማሙ አሕመድ እና አቡ ዳውድ ከሰውባን (ረድየላሁ አንሁ) ይዘው በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ
“ህዝቦች በናንተ ላይ ይጠራራሉ፡፡ ልክ ሰዎች እርስ በርስ ከቀስ (ሰፊ ትሪ ላይ የቀረበ ምግብ) ለመብላት እንሚጠራሩት፡፡”
እነሱም (ሰሃባዎች) ጠየቁ “የአላህ መልክተኛ ሆይ! ያን ቀን በቁጥር አንሰን ነውን?”
እሳቸውም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ መለሱ “በፍፁም፡፡ ያን ጊዜ በቁጥር በጣም ብዙ ናችሁ፡፡ ነገር ግን ልክ እንደ ጉሳእ (የባህር አረፋ) ናችሁ፡፡ አላህ ከጠላቶቻችሁ ልብ ውስጥ ለናንተ የነበራቸውን ፍራቻ ያነሳና እናንተ ልብ ውስጥ ዋህንን ያደርጋል፡፡”
እነሱም (ሰሃባዎች) አሉ “የአላህ መልክተኛ ሆይ! ዋህን ምንድን ነው?”
እሳቸውም አሉ “ዱንያን መውደድና ሞትን መጥላት”
ኢማሙ አሕመድ 21897 እና አቡ ዳውድ 4297. ኢማም አልባኒ አሰሂሃ ላይ ትክክለኛ ብለውታል 8183
ወደ አላህ (በትክክለኛው እምነት፣ በመልካም ስራ፣ ትእዛዝን በማክበር፣ ክልከላን በመራቅ፣ በተውበት) የተመለስን ጊዜ ከእኛ የተወሰደብንን ይመልስልናል፡፡ ከአላህ መራቁን (እምነታችንን ሳናስተካክል፣ ቢድኣን እያጨማለቅን፣ መልካም ስራን ሳንሰራ፣ ሳንታዘዝ፣ ክልከላን ሳንርቅ) ከቀጠልንበት በእጃችን ያለውንም እናጣዋለን፡፡
በእርግጥ አላሁ (ተባረከ ወተኣላ) ይህንን ፍርድ በተከበረው መፀሀፉ እንዲህ ሲል አስቀምጦታል
[Q 14:7] وَإِذْ تَأَذَّنَ رَبُّكُمْ لَئِن شَكَرْتُمْ لَأَزِيدَنَّكُمْ ۖ وَلَئِن كَفَرْتُمْ إِنَّ عَذَابِى لَشَدِيدٌ
ጌታችሁም «ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ ብትክዱም (እቀጣችኋለሁ) ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነውና» በማለት ባስታወቀ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡
እሱ (የላቀውና ከፍያለው) የተሰጠንን አለማመስገን ያንን ፀጋ እንደሚያጠፋው አብራርቶልናል፡፡ አዋቂዎቻችን እንዲህ ይላሉ “በረካ የሚታደን ነገር ነው፡፡ ለተሰጠን በረከት ማመስገን ደግሞ (በረከቱ) እንዲፀና እንዲቀጥል እንዳይጠፋ ያደርገዋል (መጠበቂያ ነው)፡፡”
[ምንጭ :መታ ተኡዱ ኢለይና ፍልስጢን፡ ገፅ 7-8]
የሸይኽ ሙሐመድ ሰኢድ ረስላን ንግግር እዚህ ጋር ተፈፀመ፡፡
በአላህ ፍቃድ እዚሁ ፊስ ቡክ ላይ፣ በየመንደሩ፣ በየትምህርት ቤት፣ በየመስጊዱና ሁሉ ቦታ ፍልስጤም መቼ ነው ወደኛ የምትመለሰው እያልን ለምናስብ ኢትዬጵያዊ ወንድም እና እህቶች ሁሉ የሚከተለውን ጥያቄዎች ከነፍሴ ጀምሮ እጠይቃለሁ
1) ምን ያህሉ ሰው የተፈጠረለትን አላማ ያውቃል?
2) አገራችን ኢትዬጵያ ላይ ነብያት ከምንም በፊት ያስቀደሙት የተውሒድ ጥሪ በገጠርም በከተማም የሚገባውን ያህል ተሰራጭቷል?
3) ምን ያህሉ ኡለማ፣ ዳኢ ነብያት ሁሉ የተላኩበትን ተውሒድ ለኡማው በየቋንቋው አድርሷል?
4) የኢትዬጵያ ሙስሊም ከ40 ሚሊዬን በላይ ነው ይባላል፡፡ ምን ያህሉ የላኢላሃ ኢለላህን መስፈርቶች፣ የላኢላሃ ኢለላህን ትርጉም፣ የላኢላሃ ኢለላህን መእዘናት፣ ላኢላሃ ኢለላህን የሚያፈርሷትን ማስረጃዎቿን ጠንቅቆ ያውቃል?
5) ምን ያህሉ አርካኑል ኢስላምና አርካኑል ኢማንን በዝርዝር ጠንቅቆ ያውቃል?
6) ምን ያህሉ ስለ ሺርክ አደገኝነት ያውቃል?
7) ምን ያህሉ በሺርክ ተዘፍቋል?
8) ምን ያህሉ ከአላህ አምልኮ ወጥቶ ለቀብር ይሰግዳል፣ ያርዳል፣ ይሳላል……? ኡለማዎችና ዱአቶች እውነት አደራቸውን ተወጥተዋልን?
9) የሩቅ እውቀት በጠቅላላ ለአላህ ብቻ ሆኖ ሳለ አገራችን ላይ የክህደት መፀሀፍ የሆነውን “የሸህ ሁሴን ትንቢት” ምን ያህል ሰው እውነት ነው ብሎ ይቀበለዋል?
10) ምን ያህሉ ጌታችን አላህ ከአርሽ በላይ ከፍጡራኑ ሁሉ በላይ መሆኑን ያምናል?
11) አላህ በሐቅ ላይ አንድ ሁኑ ብሎን ሲያበቃ አገራችን ላይ አንድ የሀቅ መንገድ ብቻ ነው ያለው ወይንስ አንዷን ብቸኛ የሐቅ መንገድ የሚቃረኑ ብዙ የጥመት መንገዶች? ለምሳሌ (አህባሽ፣ ሱፊ፣ አሽአሪ፣ ሺኣ፣ ተብሊግ፣ ኢኽዋን፣ ቲጃኒ፣ የቃጥባሪ ሙሪዶች፣ የአብሬት ሙሪዶች፣ የአልከሶ ሙሪዶች፣ የኑርሁሴን ሙሪዶች…………)
12) አገራችን ላይ አንድነት ሲባል በተግባር ያየነው በሐቅ ላይ መሰባሰብ ነው ወይንስ ሺርክና ቢድኣ የሚሰራውን ሁሉ ደባልቆ “አንድ ነን” ብሎ መዋሸት?
13) ምን ያህሉ ኡማ ሱናን እና የሚፃረራትን ቢድአ ለይቶ ያውቃል?
14) ምን ያህሉ ከቢድኣ ርቆ ጌታችንን አላህ በሱና ይገዛል?
15) ምን ያህል በኢስላም የሌለ መውሊድ ወይንም የልደት በአሎች አገራችን ላይ ይከበራሉ? ለምሳሌ “የአብሬት መውሊድ፣ የቃጥባሪ መውሊድ፣ የጀማ ንጉስ መውሊድ፣ የቦረናው መውሊድ፣ የዳንግላው መውሊድ፣ የአልከሶ መውሊድ፣ የአሊ ጎንደር መውሊድ…..”? ኡለማና ዳኢ የሚባሉ ይህንን ሱናን አፍራሽ ተግባር ላይ በመቃወም ሚናቸውና ትኩረታቸው ምን ያህል ነው?
16) አገራችን ላይ ትክክለኛው የአቂዳ ትምህርት አላህ ካዘነላቸው ጥቂቶች ውጭ በኡለማዎች፣ በዳኢዎች፣ በቻናሎች፣ በሪድዬ ጣቢያዎች ነብያት የሰጡትን ያህል ትኩረት ተሰጥቶታልን?
17) ምን ያህሉ ለዲን ቦታ ሰጥቶ ሸሪኣን ይማራል?
18) ምን ያህሉ ልጅ የቤተሰቡን ሃቅ ያሟላል?
19) ፔንጤ ሙስሊሙን እያከፈረ ነው ተብሎ በሰፊው ይነገራል፡፡ ፔንጤዎቹ ደግሞ ሙስሊሞቹን የሚያከፍሩት በዱንያ እንደሆነ በማስረጃ ሁሉ ይነገራል፡፡ ታድያ በዚህ ጊዜ አላህ መልካም የዋለለት በጣም ብዙ ሙስሊም ሀብታም አለ ምን ያህል እነዚህን በዱንያ ምክንያት ወደ ክህደት እየሄዱ ያሉ ግለሰቦችን ለመታደግ መፅውቷል? አገራችን ላይ በቀን ስንት ሚሊዬን ብር ሙስሊሞች ለጫት ያወጣሉ? እውነት በዱንያ ጉዳይ የሚከፍሩትን ሙስሊሞች ለመታደግ እነዚህ ጫት ቃሚዎች ለጫት የሚያወጡት ገንዘብ ፔንጤ ለሚያከፍራቸው ለምን አልተለገሰም?
20) አገራችን ላይ ባሉ ዳኢዎችና ኡለማዎች የጫትን አስከፊነት በተመለከተ ተገቢው ማስጠንቀቂያና ማንቂያ ደውል ለሙስሊሙ ኡማ ተደርጓልን?
21) ምን ያህሉ ባል የሚስቱን ሀቅ ይጠብቃል?
22) ምን ያህሉ ሚስት የባሉን ሃቅ ይጠብቃል?
23) ምን ያህሉ ሰው ሰላት ይሰግዳል?
24) ከሰጋጆች ውስጥ ለወንድ ልጅ ግዴታ የሆነውን ጀመኣ ሰላት ምን ያህሉ ይሰግዳል?
25) ምን ያህሉ ሴት አላህ የረገመውን ቅንድብ መቀንደብና ማስቀንደብ፣ ዊግ መስራትና ማሰራት፣ ንቅሳት መንቀስና ማስነቀስ ይሰራል?
26) ምን ያህሉ ወንድ ይህንን አደንዛዥ ቅጠል ጫት ይቅማል?
27) ምን ያህሉ ወንድ ሲጋራ ያጨሳል?
28) ምን ያህሉ ሰው ከዝሙት እራሱን ጠብቆ ወደ ትዳር በጊዜ ይገባል?
29) ምን ያህሉ ሙስሊም ወጣት መጠጥ ይጠጣል?
30) ምን ያህሉ ነጋዴ ከወለድ ፀድቷል?
31) ምን ያህሉ ከቁርኣን ከሱና ተዘናግቶ ወደ ፊልም ድራማ ሙዚቃ ተጎትቷል “ኢስላማዊ” የሚሉትን ጭምር?
32) እና የመሳሰሉትን በጣም ብዙ ጥያቄዎች ለነፍሳችን እንመልስ
ያኔ እውነት እኛ አሁን ያለንበት ሁኔታ ፍልስጤም እንድትመለስልን መስፈርቱን አሟልተናል ወይ? የሚለውን ቁልጭ ብሎ ይታየናል፡፡
እግር ኳስ አለ ሲባል ከለሊቱ 6 እና ሰባት ሰኣት ላይ አይኑ ዲሽ ቤት የሚፈጠው አብዛኛውን ወጣት ፈጅር ሰላት ላይ መስጂዶቻችንን ላይ መምጣት ማቃቱ ብቻ አእምሮ ላለው ትልቅ ጥቆማ ነው፡፡
እባካችሁ የፍልስጤምንም ይሁን አለም ላይ ሌሎች ሙስሊሞች ላይ የሚደርሰውን በደል እና ጭቆና ለአላህ ትክክለኛ ባሪያ ሳንሆን እዚሁ ሶሺያል ሚድያ ላይ አካኪ ዘራፍ “ዋ አቅሷ” ምናምን ብሎ መፎከሩ አያዋጣም፡፡ ይሄ በፍፁም ትክክለኛ መፍትሄ አይሆንም፡፡ ሰይጣንን እና ሰራዊቶቹን ማሸነፍ ማለት በአርሰናልና ማንቸስተር መሃል ያለ የእግር ኳስ ፍልሚያ እንዳይመስለን፡፡
አላህ እንዲህ ይላል
[Q 47:7] يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِن تَنصُرُوا۟ ٱللَّهَ يَنصُرْكُمْ وَيُثَبِّتْ أَقْدَامَكُمْ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን (ህግጋቱን ብትፈፅሙ) ብትረዱ፤ ይረዳችኋል፡፡ ጫማዎቻችሁንም ያደላድላል፡፡
መቼም ሰው ያልዘራውን አያጭድም፡፡ ሰሃባዎች በአላህ የሚገባውን ትክክለኛ እምነት አምነው ተገኙ፣ የመልክተኛውን ሱና አጥብቀው ያዙ ለሁለት አገር ድል በቁ፡፡
ስለዚህ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አላህ እንዲረዳን ከፈለግን በትክክለኛው እምነት፣ ብቸኛ አንዷ የሀቅ ጎዳና፣ የነብዩ ሱና፣ የሰሃባዎች አረዳድ፣ እውነተኛ አንድነት ላይ እንሰባሰብ፡፡ ከዛም ቃል ኪዳኑን በመሙላት የሚታወቀው አላህ ሁለት አገር ድል በድል ያደርገናል፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በመልክተኛው፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሀቅን በተከተሉ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡ አሚን፡፡
ሌሎች ፅሁፎችን ለማንበብ የሚከተለውን የቴሌግራም ቻናል ይጫኑ
https://t.me/SadatTextPosts
“ሙስሊም አይዋሽም፡፡”፣ “ለቀልድ አንኳን ውሸት ሃራም ነው፡፡” ይላሉ ታማኙ የአላህ መልክተኛ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
ከስሜት አምላኪዎችና የጥመት አራማጆች ውስጥ አንዱ እንዲህ ሲሉ ይዋሹብኛል
“ሰበር ዜና ሳዳት ከማል ለቢዝነስ ሲል የከፈተው ሩቃ ቤት ገቢያ እንዳያጣ አፍሪካ ቲቪን ማግባባት ጀመረ”
ማስረጃ አምጣ እውነተኛ ከሆንክ ቢሉት ማስረጃ የለውም፡፡ ውዱ ነብይ ለቀልድ እንኳን ውሸት ሀራም ነው ብለው ሲያበቁ፣ ስሜት ተከታዬች ከቻሉ ዲኑን ለሚፈልጉት አላማ ይጠመዝዙታል፣ ካልቻሉ ውሸት ይነዛሉ፡፡ አስገራሚው የአላህ መልክተኛ “ሙስሊም አይዋሽም” ሲሉ እነሱ ደግሞ እራሳቸውን የኢስላም ጠበቃ አድርገው ማቅረባቸውና በተከታዬቻቸው ዘንድ የሙስሊም ጠበቃ ተደርገው መወሰዳቸው ነው፡፡
በጣም የሚያሳዝነው እና እጅግ ገርሞ የሚገርመው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “እውነተኞች ውሸታም፣ ውሸታሞች የሚታመኑበት ዘመን ይመጣል፡፡” ሲሉ ገልፀው ነበር፡፡ ዛሬ እንዲህ አይነት ውሸታሞች ለኡማው እራሳቸውን የሙስሊም ጠበቃ አድርገው መቅረባቸውና በምስኪኑ ዘንድ መታመናቸው ገርሞ የሚገርም ነው፡፡
ምስጋና ለአላህ ይገባው እኛ እነሱ የሚያጠፉትን ጥፋት ስናጋልጥ አንድም ቦታ ላይ አንዋሽባቸውም፡፡ በማስረጃ እውነቱን ብቻ እናስቀምጣለን፡፡ ዛሬ ሰው እየነቃ እና እየተለወጠ ከጥፋት ወጥቶ ወደ ሱና ሲመለስ ሲያዩት የመጨረሻ መሳሪያቸው የሆነውን ውሸት መርጨት ነው፡፡
ግን ውሸታም መጨረሻው ውርደት ነው፡፡ ልክ ሰውየው አሁንም እንደተዋረደው ሁሉ፡፡
አላህ እውነተኛ ባሪያዎቹ ያድርገን፡፡
ማንም ሰው ስሙን ቀይሮ፣ በስሙም፣ ወንዱ በሴት፣ ሴቷ በወንድ ስም ቢፅፉም አላህ በስማችን ነው የሚመዘግበው፡፡ አላህን እንፍራ፡፡
By Muhammedsirage MuhammedNur Gidey
بسم الله الرحمن الرحيم.
ነብዩ صلى الله عليه وسلم በህይወት ዘመናቸው በርካቶችን ለበርካታ ጉዳዮች ሾመዋል። ከነዚህ ተሿሚዎች ውስጥ ግን አንድም ሴት አይገኝበትም ። በግዜው አላህን የሚፈሩ በሸሪዓዊ እውቀታቸውም ከበርካታ ወንዶች ያላነሱ እነ ዐኢሻን የመሰሉ ጠንካራ ሴቶች የነበሩ ቢሆንም ታላቁ ነብይ ግን አንዳቸውንም ሙስሊሙን ይመሩት ዘንድ አልሾሙም ነበር ። ከነብዩም በሇላ በነብዩ አመላካችነት አቡበክር የሙስሊሞች መሪ ሆኖ የተሾመ ሲሆን በዚህ ወቅትም " ሴቶች ሆይ ኑና ምሩን " ያለ አንድም ሶሓባ አይታወቅም!!
ከአቡክር በሇላም ዑመር ፣ ዑስማን ፣ ዐልይ የአማኞች መሪ ሆነው ተመሪዎቻቸውን በፍትህ ያስተዳደሩ ሲሆን ላጠቃላይ መሪነትም ይሁን ላንዲት አነስተኛ አካባቢ መሪነት ወደ ሴቶች አሚርነት የጠቆመ የነብዩ ባልደረባ አልነበረም ። እነዛ ምርጥ ሴቶችም ስልጣን ይገባናል በማለት ዛሬ ዛሬ ወንድነታቸው የጠፋባቸው ወንዶች የሚጮሁትን "ሴቶች ይምሩ " ጩኸት አልጮሁም! !
ይህ ሁሉ የሚጠቁመው ሴት ልጅ በመሪነት ልትቀመጥ እንደማይገባት የሰለፎች የተግባር ስምምነት እንደነበረ ነው ። የሰለፎችን ስምምነቶች የሚነቅፉ ድርጊቶችና አቋሞች ደግሞ ጤና እንደሚጎላቸው አያጠራጥርም ። የሃሳቡ ወይም የአቋሙ ባለቤትም አቅሉና ዲኑ እንደሳሳ አያጠራጥርም!! ስልጣን ይገባናል የሚለው የሴቶች ጥያቄ የተነሳው ከምርጦቹ የሴት ምሳሌዎች ከነ ዐኢሻ፣ ሓፍሳ ፣ ዘይነብ ሳይሆን ከነ ሂላሪ ክሊንተንና መሰል ምናምንቴዎች ነውና ሴቶች ሆይ ምሳሌዎቻችሁን ልብ በሉ ።
ነብዩ صلى الله عليه وسلم እንከን በማይገኝለት ንግግራቸው ሴት ልጅን መሪ ያደረገ ህዝብ ድልን እንደማያገኝ ገልፀዋል ። እንዲህ ብለዋል ፣
لَنْ يُفْلِحَ قَوْمٌ وَلَّوْا أَمْرَهُمْ امْرَأَةً
* ቡኻሪ እና ሌሎችም ዘግበውታል።
ድል የሚገኘው የነብዩን ትእዛዝ በመከተል እንጂ የምእራቡን ከሃዲ ዱካ እየተከተሉ ሴቶችን ወደ ሹመት በመጣራት አይደለም ።
ሺአዎችን እንጠንቀቅ እናስጠንቅቅ፡፡
ጥያቄ፡- አያቶላህ ሁመይኒን አስመልኮ ኢስላማዊ ፍርዱ ምንድን ነው
መልስ፡- ኹመይኒ ኢማሞች ከነብያትና ከመልክተኞች (የአላህ ሰላትና ሰላም በነርሱ ላይ ይሁን) በላይ እንደሆኑ የፃፈበት ኪታብ አለው፡፡ በዚህ ንግግሩ መሰረት ሙስሊም አይደለም፡፡
ምንጭ አል-ሃዊ ሚን ፈትዋ አሽ-ሸይኽ አልባኒ ገፅ 349
ሺአዎች 12 ኢማሞች አሉ ብለው ያምናሉ፡፡ እነዚህ 12 ኢማሞች ምድርን ያስተናብራሉ ብለውም ይህን ኩፍር ያምናሉ፡፡ እነሱ ኢማም ብለው አምልኮን ቢፈፅሙላቸውም ግን ከነሱ ቅጥፈት የፀዱ ናቸው፡፡ ከነሱ ውስጥ የመልክተኛው የአጎት ልጅ የሆነውን አሊይ (ረድየላሁ አንሁ) ይገኝበታል፡፡ እውነታው ግን አሊይ ረድየላሁ አንሁ አይደለም ከነብያት ሊበልጥና ከ አቡበክር፣ ኡመርና ኡስማን እንኳን አይበልጥም፡፡ ይህን ስንል ደግሞ አሊይ እኛ ዘንድ የተወደደ ነው፡፡ ከደረጃው በላይ ከፍ ሊደረግ አይገባውም፣ ከደረጃውም ዝቅ ሊደረግ አይገባውም የሚለውን እያስረገጥን ነው፡፡ ሰሃባዎች ውስጥ አንድኛ አቡበክር፣ ሁለተኛ ኡመር፣ ሶስተኛ ኡስማን፣ አራተኛ አሊይ ናቸው፡፡ ሺአዎች በጣም መጥፎ ሰዎች ናቸው እንጠንቀቃቸው፡፡ የኢትዬጵያ ሙስሊሞች ሆይ! “ከሺአዎች ጋር ላኢላሃ ኢለላህ ሙሐመደ ረሱሉላህ አንድ ያደርገናል” የሚላችሁን አታላይ አትስሙት፡፡ የላኢላሃ ኢለላህ ሙሐመዱ ረሱሉላህን መልክት ከስር ከመሰረቱ የናዱ መጥፎ ፍጡሮች ናቸው፡፡
አላህ አገራችንን የመጀመሪያዎች ምርጥ ትውልዶች ወደ ሀገራችን ሁለት ጊዜ ተሰደውበት ወደ ነበረበት ጥርት ወዳለው ዲን ይመልስን፡፡ ከሁሉም የጥመት ቡድኖች ይጠብቅልን፡፡ የጥንት የጠዋቱን ብቸኛ የሐቅ መንገድ ለግሶን በሱ ላይ የምንሰባሰብ ያድርገን፡፡
አሚን፡፡ https://t.me/SadatTextPosts
Forwarded from Sunnah Tube /ሱንና ቲዩብ (Seid Mohammed)
በእስልምና ወሮች 12 ናቸው እነሱም
1) ሙሐረም፣
2) ሰፈር፣
3) ረቢእ አል-አወል፣
4) ረቢእ አስ-ሳኒ፣
5) ጀማዳ አል-አወል፣
6) ጀማዳ አስ-ሳኒ፣
7) ረጀብ፣
8) ሻእባን፣
9) ረመዳን፣
10) ሸዋል፣
11) ዙል ቃኢዳ፣
12) ዙል ሂጃህ ናቸው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ተውሂድና ሱና አንድ ያደርጋሉ፣ የውሸተኛው አንድነት ፀር ናቸው፡፡
ሽርክና ቢድዐ ይበታትናሉ፣ የእውነተኛው አንድነት ፀር ናቸው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts/58
አቂደቱል ዋሲጥያ በኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ አቡ ኢምራን ከክፍል 1-25 የሚከተለውን የቴሌ ግራም ቻናል ጆይን በማለት ይጠቀሙ
https://t.me/Aqidetul_Wasiteya
ባሪከላሁ ፊኩም ሼር በማድረግ ለሌሎች ያዳርሱ
By Kal'amin Tsegaye
*መዲናሕ አረበኛ መፅሐፍ ሰዋሰዋዊ ማስታወሻ መፅሐፍ አንድ ሙሉእ*
በዚህ ሊንክ ተስፈንጥረው ዳውንሎድ ያድርጉ፡፡(http://bit.ly/2hBQsgF)
ሼር በማረግ እጅግ መሰረታዊ እውቀትን በነፃ ያሰራጩ!!
.
ማስታወሻ፡- ከዚህ በፊት የተለቀቀው ፒዲኤፍ የመፅሐፍ አንድን ቀዳማይ ክፍል ብቻ ያካተተ ሲሆን ይህ ግን ሌሎችም ርዕሶች ተካተውበት የመዲናህ መፅሐፍ ጥራዝ አንድ ሙሉውን ክፍል የዳሰሰ እጅግ ጠቃሚ ማስታወሻ ነው፡፡ የተዘለለ ክፍል አሊያ የትርጉም ስህተት ካስተዋሉ ይጠቁሙ!
-
በዚህ ክፍል ስር ከተቃኙ ርዕሶች ውስጥ
-
1. የንግግር ክፍሎች
2. አረበኛ ፊደሎች
3 .አናባቢ ቃላት
4. ማዕሪፋህ እና ነኪራህ
5. ይህ(هَذَا) vs. ያ (ذَلِكَ)
6. ፀሐያዊ እና ጨረቃዊ ቃላት
7. የስሞች መጨረሻ
8 .ስማዊ አረፍተነገር
9. هَمزَةُ الوَصَلِ وَهَمزَةُ القَطعِ
10. መስተዋድድ (حَرفُ جَرٍّ) & (مَجرُورٌ)
11. ገለልተኛ ተውላጠ ስም (ضَمِيرٌ مُنفَصِلٌ)
12. مُضَافٌ وَمُضَافٌ إِلَيهِ (ንብረትና ባለ ንብረት)
13. ፆታ
14. ምትክ (بَدَلٌ)
15. ተውሳከ ግስ (ظَرْفٌ)
16. ገላጭ (نَعتٌ)
17. አንፃራዊ ተውላጠ ስም (الاِسْمُ المَوْصُوْلُ)
18. አላፊ ግስ (الفِعْلُ المَاضِي)
19. ተቀጥያ ተውላጠ ስም (ضَمِيْرٌ مُتَّصِلٌ)
20 . خَبَرٌ مُقَدَّمٌ وَمُبتَدَأٌ مُؤَخَّرٌ (ቀዳማይ ዜና እና ዳህራይ ርዕስ )
21. ብዙ ቁጥር (جَمْعٌ)
22. ቁጥር (أَعدَادٌ)
23. ዲፕቶት (المَمنُوعُ مِنَ الصَّرفِ)
24. የኸበር አይነቶች (أَنوَاعُ الخَبرِ)

ዳውንሎድ ያድርጉ —- http://bit.ly/2hBQsgF
👆🏻ተውሂድን ለልጆች ማስተማር
ድል ለአላህ፣ ለመልክተኛውና ለአማኞች ነው፡፡
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለነዛ በሺርክ ጨለማ ውስጥ ተዘፍቀው ለነበሩ አጋሪያን ማህበረሰቦች ተላኩ፡፡ እሳቸውም ከጌታቸው የተላኩበትን የተውሒድ መልክት ይፋ አደረጉ፡፡ አለ የሚባል መከራ ሁሉ ደረሰባቸው፡፡ ስማቸውን ማጥፋት፣ እሳቸውንም ባልደረባዎቻቸውን ማሰቃየት፣ እሳቸውን ለመግደል መሞከር፣ ሲሰደዱ ጋር ሰውራ ድረስ ለመግደል ተከታተሏቸው፡፡ የሚወዷትን ውድ ከተማ መካ “ህዝቦችሽ ነው ያስወጡኝ እወድሻለሁ” እያሉ ዞር እያሉ እያዩት ጥለዋት ተሰደዱ፡፡
መዲና አላህ በሰላም አደረሳቸው፡፡ መካ በነበሩበት ጊዜ አማኞች ሲገደሉ፣ ሲደበቁ እንዳልነበር አላህ መዲና ላይ ባሉበት መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ህልምን አዩ፡፡ አላህ ህልማቸውን አስመልክቶ እንዲህ ይለናል
لَّقَدْ صَدَقَ ٱللَّهُ رَسُولَهُ ٱلرُّءْيَا بِٱلْحَقِّ ۖ لَتَدْخُلُنَّ ٱلْمَسْجِدَ ٱلْحَرَامَ إِن شَآءَ ٱللَّهُ ءَامِنِينَ مُحَلِّقِينَ رُءُوسَكُمْ وَمُقَصِّرِينَ لَا تَخَافُونَ ۖ فَعَلِمَ مَا لَمْ تَعْلَمُوا۟ فَجَعَلَ مِن دُونِ ذَٰلِكَ فَتْحًا قَرِيبًا
አላህ ለመልክተኛው ሕልሙን እውነተኛ ሲኾን አላህ የሻ እንደ ኾነ ጸጥተኞች ኾናችሁ ራሶቻችሁን ላጭታችሁ፣ አሳጥራችሁም የማትፈሩ ስትኾኑ የተከበረውን መስጊድ በእርግጥ ትገባላችሁ፤ ያለውን በእርግጥ እውነት አደረገለት፡፡ (ከእርቁ) ያላወቃችሁትንም ነገር ዐወቀ፡፡ ከዚህም በፊት ቅርብን መክፈት አደረገ፡፡

ከዛም ያችን ውድ የከተሞች እናት መካ መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከአማኞች ጋር ሆነው ከፈቷት፡፡
وَقُلْ جَآءَ ٱلْحَقُّ وَزَهَقَ ٱلْبَٰطِلُ ۚ إِنَّ ٱلْبَٰطِلَ كَانَ زَهُوقًا
በልም «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»

መታገስ ነው እንጂ የአላህ ቃል ሁሌም እውነት ነው፡፡ ሁለት አገር ድል የፈለገ ነብያት ሁሉ የሄዱበትን ብቸኛ የሐቅ ጎዳና ይጓዝበት፡፡ ብቸኛዋን የሐቅ መንገድ ረዳቷ አላህ ነው፡፡ ከሐቅ፣ ከተውሒድ፣ ከሱና፣ ከመንሀጀ ሰለፍ ጎዳና ውጭ ያሉት ሁሉ የሚታገሉትም በሰይጣን መንገድ ላይ ነው፡፡ የሰይጣን መንገድ ደግሞ መቼም ቢሆን ድልን አይጎናፀፍም፡፡ ሁለት አገር ክስረት ነው፡፡ አማኞች እስከታገሱ በሐቅ ላይ እስከፀኑ ድረስ አላህ እንዳለው ሁለት አገር ድል ይቀምሳል፡፡
وَلِلَّهِ ٱلْعِزَّةُ وَلِرَسُولِهِۦ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَلَٰكِنَّ ٱلْمُنَٰفِقِينَ لَا يَعْلَمُونَ
«አሸናፊነትም ለአላህ፣ ለመልክተኛውና ለምእምናን ነው፡፡ ግን መናፍቃን አያውቁም፡፡
አልሐምዱሊላሂ ረቢል አለሚን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
3ቱ ታላላቅ አብዛኛው የካዳቸው እውነታዎች፡፡
በሐቅ ላይ መፅነት ነው፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ሐቅ በሰዎች አይለካም፡፡ ሰዎች በሐቅ ይላከሉ እንጂ፡፡አብዛኛው ሰው ብዙ ታላላቅ እውነታዎችን ይቃረናል፡፡ ይህ ማለት ግን ሐቅ ላይ ያሉ ሰዎች አብዛኛውን አይተው አቋማቸውን መቀየር አለባቸው ማለት አይደለም፡፡ አላህ መልክተኞቹን ሁሉ ከፀሐይ ብርሃን በላይ ፍንትው ያለውን የእሱን ብቸኛ ተመላኪነት እንዲያውጁና ከእርሱ ውጭ ከሚመለኩት እንዲያስጠነቅቁ ለየህዝቡ ልኳል፡፡ ግን ለመልክተኞቹ መልካምን መልስ የሰጠውና የተቀበላቸው በጣም ጥቂት ነው፡፡ መልክተኞቹ ግን ሰው ተቀበለም አልተቀበለም ከጌታቸው የተላኩበትን መልክት እስኪሞቱ ድረስ ይፋ አድርገዋል፡፡ መልክተኞቹን የተከተሉ በየዘመኑ ያሉ አማኞችም በቁጥር ጥቂት ቢሆኑም በሐቅ ላይ ፀንተዋል፡፡ እስቲ የሚከተሉትን ታላላቅ ሶስት እውነታዎች ልብ እንበል፡፡
1) አላህ እኛን የፈጠረን እሱን በብቸኝነት እንድናመልክ ነው፡፡ መፀሀፍትን ያወረደው፣ መልክተኞችን የላከው የሰው ልጆች የተውሒድን መልክት አውቀው፣ ጠንቅቀው ተረድተው፣ ተግብረው ወደ ጀነት እንዲገቡና ከእሳት እንዲጠበቁ ነው፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ አብዛኛው ግን አልተቀበላቸውም፡፡ ካለመቀበልም አልፎ የሚከተሉትን አባባሎች እነዛ ሙሽሪኮች ተናገሩ
- قَالُوا۟ يَٰصَٰلِحُ قَدْ كُنتَ فِينَا مَرْجُوًّا قَبْلَ هَٰذَآ ۖ أَتَنْهَىٰنَآ أَن نَّعْبُدَ مَا يَعْبُدُ ءَابَآؤُنَا وَإِنَّنَا لَفِى شَكٍّ مِّمَّا تَدْعُونَآ إِلَيْهِ مُرِيبٍ
“ሷሊህ ሆይ! ከዚህ በፊት በእኛ ውስጥ (መሪ ልትሆን) በእርግጥ የምትከጅል ነበርክ፡፡ አባቶቻችን የሚገዙትን ከመገዛት ትከለክለናለህን? እኛም ወደርሱ ከምትጠራን ነገር በእርግጥ አወላዋይ በሆነ መጠራጠር ውስጥ ነን” አሉ፡፡
- وَعَجِبُوٓا۟ أَن جَآءَهُم مُّنذِرٌ مِّنْهُمْ ۖ وَقَالَ ٱلْكَٰفِرُونَ هَٰذَا سَٰحِرٌ كَذَّابٌ
ከእነርሱ የሆነ አስፈራሪም ስለ መጣላቸው ተደነቁ፡፡ ከሓዲዎቹም “ይህ ድግምተኛ (ጠንቋይ) ውሸታም ነው” አሉ፡፡
أَجَعَلَ ٱلْءَالِهَةَ إِلَٰهًا وَٰحِدًا ۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَىْءٌ عُجَابٌ
“አማልክቶቹን አንድ አምላክ አደረጋቸውን? ይህ አስደናቂ ነገር ነው” (አሉ)፡፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በአላህ ፍቃድ ከአሳማሚዉ የጀሀነም እሳት ለይተው ወደ ጀነት የሚገባበትን መንገድ ሲመክሯቸው የመካ አጋሪያን እሳቸውን እንዲህ ሲሉ ጠሯቸው
- “ቤተሰብን የሚበታትን፣ እብድ፣ ገጣሚ፣ ድግምተኛ……”
የተውሒድን እውነታ ማንም ቢቃወመው፣ አብዛኛው ባይከተለውም መልክተኞችና ተከታዬቻቸው ሁሌም ይለፉለታል፣ ይፀኑበታል፡፡ ነቃ እንበል የአላህ ባሪያዎች ሆይ! በሐቅ ላይ እንፅና፡፡
2) አላህ ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መታዘዝ አላህን እንደመታዘዝ ነው ብሎ ሲያበቃ፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የእኔን እና ቅኑን ፈለግ የተመሩ ምትኮቼን (አቡበክር፣ ኡመር፣ ኡስማን፣ አልይ) ሱና አደራ ተከተሉ፣ አዳዲስ በሃይማኖት ላይ ከተፈጠሩ መጤ ነገሮች ሁላ ራቁ ብለው ሲያበቁ፡፡ “ይህ የእኔ ኡመት 73 ቦታ ይከፋፈላል ሁሉም የእሳት ነው አንዷ ስትቀር” ብለው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሲናገሩ ሰሃባዎች ጠየቁ “የቷ ናት ያቺ ብቸኛ ነጃ የምትወጣው መንገድ?” ተብለው ተጠየቁ፡፡ እሳቸውም “እኔና ሰሃባዎቼ ዛሬ ያለንባት መንገድ ናት” ሲሉ ተናገሩ፡፡ የሳቸው ሱና ብቸኛው የጀነት መንገድ እሱን የተቃረነ ሁሉ የእሳት መንገድ ሆኖ ሳለ፣ ዛሬ አብዛኛው አላህ ካዘነላቸው ጥቂቶች ውጭ ይህን እውነታ ተቃውመው የቢድኣና የጥመት ቡድኖችን አካሄድ ይሄዳሉ፡፡
ይህ ከመሆኑ ጋር ዛሬ ዛሬ የመልክተኛውን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና መከተል ብሎም መውሊድ የመሳሰሉትን ቢድኣዎች እንራቅ ማለት የሚከተሉትን ያስብላል
- ነብዩን የማይወዱ የነብዩ ጠላቶች፣
- ወሃቢዬች፣
- ቀብር ዚያራ ክልክል ነው የሚሉ ሰዎች መጥተዋል፣
- ዱኣ አይቻልም የሚሉ ሰዎች መጥተዋል፣
- ሰደቃ ክልክል ነው የሚሉ ሰዎች መጥተዋል፣
- ኋላ ቀሮች፣
- ደረቆች፣
- የሙስሊሙ ጉዳይ የማያሳስባቸው፣
- “መውሊድ አይለያየንም፣ መውሊድ ቅርንጫፍ ነው፣ መውሊድ አቂዳ አይደለም” ከዚህም አልፎ “መውሊድ” የሚል መፀሃፍ ፅፎ ቢድኣን ለማንገስ ሱናን ለማርከስ ብቅ ያለም አለ፡፡
- ጉዞ ወደ “አብሬት መውሊድ፣ ነጃሺ፣ ቃጥባሬ መውሊድ፣ አልከሶ መውሊድ፣ አሊ ጎንደር መውሊድ፣ ዳንግላ መውሊድ፣ ኑር ሁሴን…. ” አብዛኛዎቹ ቦታዎች በአላህ ላይ የሚጋራባቸው ናቸው፡፡
ምንም እንኳን አብዛኛው ሰው ይህን አስቀያሚ እርኩስ ቢድኣ ቢፈፅምም፣ ይህንን ተግባር አልፈፅምም የሚሉ ሰዎችን በመጥፎ ስም ቢጠራቸውም አማኞች በነብያችን ሱና ላይ ፀንተው ይሀው ቀጥ ብለዋል፡፡
3) አላህና መልክተኛው ለሙስሊም መሪ በመልካም እስካዘዝ ድረስ፣ ሰላትን እስከሰገዱ ድረስ ስሟቸው ታዘዟቸው ብለዋል፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “መሪውን መምከር የፈለገ በድብቅ ይምከረው” ብለዋል፡፡ ደጋግ ቀደምቶቻች “አንድ ሰው ለሙስሊም መሪ ዱኣ ሲያደርግ ካየሀው እወቅ ይህ ሰው የሱና ሰው ነው፡፡ ሙስሊም መሪውን ሲራገም ካየሀው እወቅ ይህ ሰው የቢድኣ ሰው ነው፡፡” ብለዋል፡፡ የሙስሊም መሪን አለመታዘዝና እሱ ላይ አምፆ መውጣት ይሀው ተጨባጩ አረብ አገራት ላይ እንዳየነው አገርንና ክብርን ያጎድፋል፡፡ እውነታ ይህ ሆኖ ሳለ አብዛኛው ሙስሊም የተጠመደው መሪዎችን በመራገም፣ እነሱን በማዋረድ፡፡ ድንገት ይባል ይሆናል እነዚህ እውቀት ስለሌላቸው ነው፡፡ ነገር ግን አዋቂ የሚባሉት የመስጂድ ኢማሞች የኹጥባ ሚንበሮቻቸውን የሙስሊም መሪዎችን በመራገም ህዝብ እንዳይታዘዛቸው በማሳመፅ ላይ እና ፈተናን በመቀስቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡ እውነተኛ የሱና ተከታዬች ግን አንድ የሙስሊም መሪ መጥፎ ሲሰራ ሲያዩ ይጠላሉ አይወዱትም፣ ካገኙት በድብቅ ይመክሩታል፣ አላህ እንዲያስተካክለው ዱኣ ያደርጉለታል፡፡ በነዚህ ሙስሊም መሪዎች ላይ ፋሲቅ ቢሆኑም አምፀውባቸው አይወጡም፡፡ ፈተናን ከማብረድ አኳያ ይታገሳሉ፡፡ የስሜት ተከታዬች እነዚህን ቁርኣንን፣ ሀዲስን የሰለፎችን አረዳድ አካሄዳቸው ያደረጉ ኡለማዎችንና አማኞችን በሚከተሉት አስፀያፊ ስሞች ይጠሯቸዋል፡፡
- “የቤተ መንግስት ፍርፋሪ ለቃቃሚዎች”፣
- “የዩሁዳ ቅጥረኞች”፣
- “መብታችንን እንዳይከበር የባለስልጣናትን እድሜ ለማራዘም የሚሰሩ”፣
- “ጃምያ፣ መድከሊያ” እና የመሳሰለውን

እውነታ ግን ከላይ ያሉትን ሶስታ ታላላቅ መርሆዎች (አላህን በብቸኝነት ማምለክ በእሱ ላይ ማንንም አለማጋራት፡፡ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ሱና መከተል ከቢድኣ ሁሉ መራቅ፡፡ ለሙስሊም ባለስልጣናት በመልካም እስካዘዙ ድረስ መስማትና መታዘዝ በእነሱም ላይ አምፆ አለመውጣት) አብዛኛው ሰው ቢቃረናቸውም ሐቅ የሚለካው በሰው አይደለምና በሐቅ ላይ መፅናት ግድ ይላል፡፡ ትእዛዙን ያዘዙት አላህና መልክተኛው ናቸውና፡፡

አላህ በሐቅ ላይ ከሚፀኑት ያድርገን፡፡ የአላህ ሰላትና ሰላም በመልክተኛው፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
በቁርኣን እንደማይጨፈረው፣ እንደማይጨበጨበው፣ እንደማይደነሰውና እንደማይፏጨው ሁሉ፣
በሰለዋትም አይጨፈርም፣ አይጨበጨብም፣ አይደነስም አይፏጭም፡፡
ሰለዋት ኢባዳ ነው፡፡ ኢባዳ ተውቂፍያ (አላህና መልክተኛው ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ባዘዙት መንገድ ብቻ የሚተገበር) ነው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
የሳሎን ውስጥ ጭምብል ለባሽ ተቃውሞ ሰልፈኞች፡፡
حاكم غشوم خير من فتنة تدوم
وقال ابن مسعود رضي الله عنه
السعيد من وعظ بغيره
اللهم احفظ المملكة العربية السعودية وأهلها من مضلات الفتن
እንስቲ ተመልከቷቸው ወንድነት አጥተው በኢንተርኔት ላይ የተውሒድ አገር ሳውዲን ሊያምሱ የተዘጋጁ የቤት ውስጥ የሳሎን ውስጥ ኒቃብ ለባሽ ሰላማዊ ሰልፍ ወጪዎች፡፡ አላህ ከሸራቸው ይጠብቀን፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሙስሊሞችን መሳሪያ ከያዙ መሪዎች ጋር እንዲጋፈጥ የሚቀሰቅሱት እንዲህ አይነት በቦታው ላይ የማይገኙ ፈሪዎች ወይንም ጭምብል ለባሾች ናቸው፡፡ መሪዎች እንዲስተካከሉ እኛ መጀመሪያ ስራችንን ከአላህም ከፍጡራን ጋር ያለንን ግንኙነት ማስተካከል ይጠበቅብናል፡፡ የጠላትን አላማ በማስፈፀም በኢስላም የሌለን የተቃውሞ ሰልፍ “መብትን ማስከበር” በሚል ሽፋን ቀረች የተባለችውን የሙስሊሞች ቂብላ የሚገኝባት አገር ሳውዲ ላይም ሰልፍ ካልተወጣ እያሉ የሚቀሰቅሱ አሉ፡፡ የኢስላም ጠላት የሆኑት የሁዳዎች እነዚህ ሙስሊም አገራት ላይ በመብት ስም ተቃውሞ ሰልፍ እንዲወጣና ብጥብጥ እንዲፈጠር ከዛም እነዚህ ሙስሊም አገራት ጉልበታቸው ሲደክም እነሱ የመስፋፋት አላማቸውን ያስፈፅማሉ፡፡
የዚህ ኡለማ ፈርጦች እንዲህ ሲሉ ይመክሩናል፡፡
ከሚቀጥል (ከማይቋረጥ) ፈተና በጣም በዳይ መሪ ይሻላል፡፡
አብደላህ ኢብን መስኡድ (ረድየላሁ አንሁ) “እድለኛ ማለት በሌሎች የተመከረ ነው፡፡” ይላሉ፡፡
አላህ ሆይ! መምለከተል አረቢያ ሰኡድያን መሪዎችን ህዝቿንም የአለም ሙስሊሞችንም ከአጥማሚ ከሆኑ ፈተናዎች ጠብቀን፡፡
አላህ ሆይ! አለም ላይ ያሉ ሙስሊም መሪዎችንና ህዝቦችን አስተካክለን፡፡ አንተ ለምትፈልገውም መልካም ነገር ምራን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts