Forwarded from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ለበይክ አላሁመ ለበይክ
ሐጅ የኢስላም ልዩ መስህብ የሚሰተዋልበት፣ ድንቅ የአላህ ተዐምር የሚታይበት፣ የተውሒድ ነፀብራቅ ጎልቶ የሚነግስበት፣ ባእድ አምልኮ ከፍ ባለ ድምፅ ባደባባይ የሚወገዝበት ድንቅ ስርአት ነው፡፡ ሴት ወንዱ፣ ነጭ ጥቁሩ፣ መሪው ተመሪው በተመሳሳይ ቦታ እኩል ለአላህ የሚሰለፍበት ትንግርት፡፡ ሐጅ - አምስተኛው የኢስላም ምሰሶ፡፡
በሐጅ (በሰዎችም ውስጥ በሀጅ ትእዛዝ ተጣራ) ለሚለው የአላህ ጥሪ “ለበይክ አላሁመ ለበይክ፣ ለበይከ ላሸሪከ ለከ ለበይክ፣…” /አቤት ጌታችን ሆይ አቤት፣ አቤት ጥሪህን ተቀብለን መጥተናል/” እያሉ መልስ በመስጠት ሚሊዮኖች ይተማሉ፡፡ ከዚያ ጭው ካለ በረሃ “ከአላህ ሀገራት ሁሉ ይበልጥ አላህ ዘንድ የተወደድሽ ነሽ፡፡ ከአላህ ሀገራት ሁሉም እኔ ዘንድ የተወደድሽ ነሽ፡፡ ህዝቦችሽ ካንቺ ባያስወጡኝ ኖሮ አልወጣም ነበር” የሚለውን የነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የቁጭት ንግግር፣ አሜኬላ የበዛበት ህይወታቸውን ልበዎ በሀዘን እየተከፈለ ያስታውሳሉ፡፡ ከዚያ ጭው ካለ በረሃ አስራ አራት ክፍለ-ዘመናት ወደ ኋላ አጠንጥነው የተውሒድ ጮራ ሲፈነጥቅ በአይነ-ህሊናዎ ይመለከታሉ፡፡ ከዚያ ጭው ካለ በረሃ የመካ ሙሽሪኮችን ለከት የለሽ ጭካኔና የነዚያን ፈርጥ የሆኑ ሰሐቦች ከብረት የጠነከረ ፅናት እያሰቡ በትዝታ ይነጉዳሉ፡፡ ከዚያ ጭው ካለ በረሃ የነቢላልን ስቃይ፣ የነሱመያን የጣር ድምፅ አይነዎ እንባ እያቀረረ በሰመመን ያያሉ፡፡ ልበዎ በቁጭት እየደማ ይሰማሉ፡፡ ከዚያ ጭው ካለ በረሃ የአላህ የመጀመሪያ ቤት አለ - የሙስሊሞች ቂብላ፣ ከአለም ሁሉ ምርጡ ቦታ፣ መካ፡፡
ﺇِﻥَّ ﺃَﻭَّﻝَ ﺑَﻴْﺖٍ ﻭُﺿِﻊَ ﻟِﻠﻨَّﺎﺱِ ﻟَﻠَّﺬِﻱ ﺑِﺒَﻜَّﺔَ ﻣُﺒَﺎﺭَﻛًﺎ ﻭَﻫُﺪًﻯ ﻟِﻠْﻌَﺎﻟَﻤِﻴﻦَ ( 96 ) ﻓِﻴﻪِ ﺁﻳَﺎﺕٌ ﺑَﻴِّﻨَﺎﺕٌ ﻣَﻘَﺎﻡُ ﺇِﺑْﺮَﺍﻫِﻴﻢَ ﻭَﻣَﻦْ ﺩَﺧَﻠَﻪُ ﻛَﺎﻥَ ﺁﻣِﻨًﺎ
((በርግጥም ለሰው ዘር (መፀለያ) ሆኖ መጀመሪያ (ምድር ላይ) የተኖረው ቤት ያ በበካህ (በመካ) ያለው የተባረከና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ የሆነው ነው፡፡ በውስጡ (እንደ) የኢብራሒም መቆሚያ (ያሉ) ግልፅ የኾኑ ተዓምራቶች አልሉ፡፡ ወደ ውስጡ የገባም ሰው ደህንነቱ የተጠበቀ ሆኗል፡፡) [ኣሊ ዒምራን፡ 96]
መስጂደልሐራም መጤው ካገሬው እኩል የሚሆንበት ተአምራዊ ቦታ፡፡ የተውሒድ ቦታ፣ የእዝነት ቦታ፡፡ የኢብራሂም፣ የሐጀር፣ የኢስማዒል ትዝታ፡፡ መስጂደል ሐራም በረከት የበዛበት፣ ሰላም የሰፈነበት፣ እዝነት የነገሰበት፣ ተውሒድ የፈነጠቀበት ቅዱስ ቦታ፡፡ መስጂደልሐራም ልቦች ዘወትር የሚናፍቁት፣ አይኖች አይተውት የማይጠግቡት፣ ያላዩት ሊያዩት የሚቋምጡት ድንቅ ቦታ፡፡ መስጂደልሐራም! “የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም” ሀገርኛ ብሂል ፉርሽ የሚሆንበት ልዩ መስህብ፡፡ ለካስ ይናፍቃል! ደካማ አዛውንቶች በሽተኞች ሳይቀሩ ህመም ድካማቸውን ረስተው፣ ስቃይ እንግልቱን ዘንግተው፣ ባላዩት ሀገር ናፍቆት ተብሰክስከው፣ እልፍ አእላፍ ማይሎችን አቋርጠው ይተማሉ፡፡
ﻭَﺇِﺫْ ﺑَﻮَّﺃْﻧَﺎ ﻟِﺈِﺑْﺮَﺍﻫِﻴﻢَ ﻣَﻜَﺎﻥَ ﺍﻟْﺒَﻴْﺖِ ﺃَﻥْ ﻟَﺎ ﺗُﺸْﺮِﻙْ ﺑِﻲ ﺷَﻴْﺌًﺎ ﻭَﻃَﻬِّﺮْ ﺑَﻴْﺘِﻲَ ﻟِﻠﻄَّﺎﺋِﻔِﻴﻦَ ﻭَﺍﻟْﻘَﺎﺋِﻤِﻴﻦَ ﻭَﺍﻟﺮُّﻛَّﻊِ ﺍﻟﺴُّﺠُﻮﺩِ ( 26 )
((ለኢብራሂምም የቤቱን (የካዕባን) ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ “በኔ ምንንም አታጋራ፣ ቤቴንም ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት ሩኩዕ ሱጁድ ለሚያበዙት ንፁህ አድርግላቸው” (ባልነው ጊዜ አስታውስ)፡፡)) [አልሐጅ፡ 26]
ከዕባ፣ ሐጀረል አስወድ፣ መቃም ኢብራሂም፣ ሶፋና መርዋ፣ ሚና፣ ዐረፋ፣ ሙዝደሊፋ፣… የሙስሊሞችን ቀልብ የሚማርኩ ልዩ የዒባዳ አውድማዎች ናቸው፡፡ ተልቢያ፣ ጠዋፍ፣ ሶላት፣ ዱዐ፣ እርድ፣ የጠጠር ውርወራ፣… ለፈፀማቸው ቀርቶ ለተነገረው የሚያጓጉ ሐጅ ላይ የሚመረቱ፤ ተቅዋን የሚያላብሱ የዚያኛው ዓለም ስንቆች ናቸው፡፡ ( ﺫَﻟِﻚَ ﻭَﻣَﻦْ ﻳُﻌَﻈِّﻢْ ﺷَﻌَﺎﺋِﺮَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻓَﺈِﻧَّﻬَﺎ ﻣِﻦْ ﺗَﻘْﻮَﻯ ﺍﻟْﻘُﻠُﻮﺏِ )
ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲሥ አላህ አድሎት የተዋጣለት ሐጅ ያደረገ እናቱ ስትወልደው እንደነበረው እንደህፃንነቱ ከወንጀል ሙሉ በሙሉ እንደሚፀዳ ነው መልእክተኛው አለይሂሰላም ያመላከቱት፡፡ በሐጅ፣ ልቦች በኢማን ይታደሳሉ፣ አማኞች ከወንድሞቻቸው ጋር ይተዋወቃሉ፣ ደካሞች ይታገዛሉ፣ ሙስሊሞች ከቅዱስ ስፋራ፣ ከበረሃው፣ ከሐጁ ስርኣቶች፣ ከተዳሚው ሁኔታ፣ ከዚያ የሚሊዮኖች ስብሰባ ብዙ ተፈኩር ይወስዳሉ፡፡
አላህ አድሎት የሐጅ ስነ-ስርኣት ላይ ለተካፈለ ሰው ልብሳቸው የበሰበሰ፣ ሰውነታቸው የኮሰሰ፣ ኑሮ ያጎሳቆላቸው ስንት አይነት ሰዎችን ከተለያዩ የአለም አፅናፋት ታድመው ይመለከታል፡፡ አንዳንዶቹ ለዘመናት አጠራቅመው ለዚህ ስኬት እንደበቁ ሲቃ እየተናነቃቸው ይናገራሉ፡፡ በተሽከርካሪ ወንበር የሚገፉ፣ በጀርባ የታዘሉ አዛውንቶችን ሲመለከቱ፣ አቅሙም ጤናውም ተሟልቶ ከሐጅ ስለቀረው ወገን በእጅጉ ያዝናሉ፡፡ ሐጅ የወጀበባችሁ ወገኖቼ ሆይ! ጤናን አቅምን ያደላችሁ ጌታ፣ ሐጅን ግዴታ አድርጎባችኋል፡፡ ወንድሞቼ እህቶቼ፣ አባቶቼ እናቶቼ ሆይ! ለአላማ እንደተፈጠራችሁ አትዘንጉ፡፡ የተሰጣችሁ ገንዘብ ያንን አላማ ማሳኪያ እንጂ መጎረሪያም መባከኛም አይደለም፡፡ ሐጁን ብትፈፅሙት ጥቅሙ ለራሳችሁ ነው፡፡ ወንጀላችሁ ይረግፋል፣ ልባችሁ ይፀዳል፤ የዒባዳ ወኔያችሁ ይነሳሳል፡፡ እመኑኝ አንዴ ቆርጣችሁ ከፈፀማችሁት በያመቱ ገና ጊዜው ሲቃረብ ነው ልባችሁ የሚቆመው፡፡ “ወዴት” እንዳትሉኝ፡፡ ወላሂ ስንቶች ናቸው ሐጅ አጠናቀው መካን ሲለቁ፣ በእንባ የሚታጠቡት! ባትፈፅሙትስ ማነው የሚጎዳው? በርግጠኝነት አላህ ምንም አይቀርበትም! መቼስ ከሚታረደው እርድ አይደርሰው ነገር! ያበላል እንጂ አይበላምና፡፡ ከፍጡር ሁሉ የተብቃቃ ጌታ ነውና፡፡
ﻭَﻟِﻠَّﻪِ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟﻨَّﺎﺱِ ﺣِﺞُّ ﺍﻟْﺒَﻴْﺖِ ﻣَﻦِ ﺍﺳْﺘَﻄَﺎﻉَ ﺇِﻟَﻴْﻪِ ﺳَﺒِﻴﻠًﺎ ﻭَﻣَﻦْ ﻛَﻔَﺮَ ﻓَﺈِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻏَﻨِﻲٌّ ﻋَﻦِ ﺍﻟْﻌَﺎﻟَﻤِﻴﻦَ ( 97 )
(ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መሄድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው፡፡ የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡) [ኣሊ ዒምራን: 97]
ዱዓቶች ሆይ ተነሱ! ሰዎችን ቀስቅሱ፡፡ አላህ የጣለባችሁን ሀላፊነት አድርሱ፡፡ ተሳክቶላችሁ በናንተ ሰበብ አንድ ሰው ለሐጅ ቆርጦ ቢነሳ የሚኖራችሁን አጅር አስታውሱ፡፡ ወገን ወደ ግራም ወደ ቀኝም ተመልከት፡፡ ከራሳችን፣ ከቤተሰብ፣ ከጎረቤት ብዙ ሐጅ ያላደረጉትን ፍቀድ፡፡ ዘንድሮ ባይደርስ ለቀጣይ አስታውስ፡፡ (አስታውስ ማስታወሱ አማኞችን ይጠቅማልና፡፡) [አዝዛሪያት፡ 55]
ባይሆን አደራ
ለሐጅ ቆርጠው ከተነሱ፡- በሚገባ ይዘጋጁ፡፡ ስለሐጅ ይጠይቁ፣ ይወቁ፣ ያንብቡ፣ የሚያነቡትም ይያዙ፡፡ ከተቻለም ቀድሞ ሐጅ ያደረገ የዲን ግንዛቤ ያለው ሰው ጓደኛ ማድረገዎን አይርሱ፡፡
(ወደ ኸይር ያመላከተ (ኸይሩን) እንደሚሰራው ሰው ነው (አጅሩ አለው)) ይላሉ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡፡
ለበይክ አላሁመ ለበይክ
ለበይከ ላሸሪከ ለከ ለበይክ
ኢነልሐምደ
ወንኒዕመተ
ለከ ወልሙልክ
ላሸሪከ ለክ!!
ያ ረሕማኑ ቤትህን ለመጎብኘት አንተ ወፍቀን፡፡
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጳጉሜ 3/2006)

ሚካኢል (አለይሂ ሰላም) ለምን አይስቅም?
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መላአኩ ጂብሪልን እንዲህ ሲሉ ጠየቁት
“ለምንድን ነው (መላአኩ) ሚካኢል አንድም ቀን ሲስቅ አይቼው የማላውቀው?”
እሱም (ጂብሪል) “ሚካኢል እሳት (ጀሀነም) ከተፈጠረች ጀምሮ ስቆ አያውቅም” አለ፡፡ ኢማሙ አሕመድ ዘግበውታል፡፡
https://t.me/SadatTextPosts

አባት እና ልጅ ነብያት
ኢብራሂም እና ኢስማኢል፣
ኢብራሂም እና ኢስሃቅ፣
ኢስሃቅ እና ያእቁብ፣
ያእቁብ እና ዩሱፍ፣
ዳውድ እና ሱለይማን፣
ዘከርያ እና የህያ፣
ወንድማማች ነብያት
ሙሳ እና ሀሩን
https://t.me/SadatTextPosts
ኢብራሂም እና ኢስማኢል፣
ኢብራሂም እና ኢስሃቅ፣
ኢስሃቅ እና ያእቁብ፣
ያእቁብ እና ዩሱፍ፣
ዳውድ እና ሱለይማን፣
ዘከርያ እና የህያ፣
ወንድማማች ነብያት
ሙሳ እና ሀሩን
https://t.me/SadatTextPosts
ሱዳኖች የደረሰባቸውን ችግር ሁሉም ሙስሞች እስቲ ይስሙት፡፡
አይ ነፃነት!
አላህ ያሉበትን ይቀይርላቸው፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=yIwUOi5iTTU

አላህን በስሙ ነው የምንጠራው!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
አንድ ገጠሬ መእሙን በሚል ቅፅል ስም የሚታወቀውን ኸሊፋ "ዐብደላህ! ዐብደላህ!" ብሎ ሲጠራው
መእሙን ተቆጣ።
"በስሜ ነው የምትጠራኝ?!" አለው።
•
ገጠሬው: "እኛ አላህንም በስሙ ነው የምንጠራው!" አለው።
•
መእሙን ፀጥ አለ። ልክ ድንጋይ እንዳጎረሰው ነው የሆነው።

"ከሰው ሁሉ አስተዋይ ማለት መልካም ሰሪ ሆኖ (የአላህን ቅጣት) የሚፈራ ነው።
ከሰው ሁሉ ቂል ማለት ክፉ ሰሪ ሆኖ የሚታማመን ነው።"
•
[አትተብሲራ፣ ኢብኑል ጀውዚ: 1/351]
ከሰው ሁሉ ቂል ማለት ክፉ ሰሪ ሆኖ የሚታማመን ነው።"
•
[አትተብሲራ፣ ኢብኑል ጀውዚ: 1/351]
ወለድ አልባ ባንኮች?
ምነው በፈረንካው መደመር አቃተን?
*****************
በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
|
ከሃይማኖት ከዐቂዳ ጋር ግንኙነት ያለውን መጅሊስ፣ በጋራ ሆነን ሙስሊሙን ሁሉ የሚያገለግል አንድ የጋራ ተቋም (መጅሊስ) "እንመስርት፣ እንደመር” ያሉ ሁሉ፣ በባንክ (በገንዘብ) ጉዳይ ሲሆን በጋራ ሙስሊሙን ሁሉ የሚያገለግል አንድ ትልቅ ወለድ አልባ ባንክ እንመስርት አለማለታቸው ታላቅ ትዝብት ውስጥ ይከታቸዋል፡፡ አንድ መንሃጅ የሚከተሉ ሰዎች ጭምር በባንክ (በዱንያ) ተለያይተው ስናይ አሳዛኝ ነው፡፡ ከመጅሊሱ ጋር መለያየት የሚገባው ከእምነት ጋር በተያያዘው ጉዳይ ነበር፡፡ ነገር ግን መጅሊሱን በጋራ ማቋቋሙን የመረጡ ሰዎች እንዴት በዱንያ፣ ያውም በአንድነት መስራት መንቀሳቀስ በጣም አዋጭ በሆነበት ጉዳይ፣ እንደ ሰፈር ውስጥ “ጉሊት” ገና ካሁኑ ተከፋፍለው እና ተቧድነው እራሳቸውንም ኡማውንም ለድክመት ይዳርጉታል?! እንዲህ አይነት ስግብግብ ሩጫ በነገሰበት መልኩ ተገብቶ ነገ ኪሳራ ቢያጋጥም ማነው ተጠያቂው?!
የመጅሊሱን ጉዳይ “ለሙስሊሙ ኡማ አስበን ነው” ከተባለ፣ በዱንያው ጉዳይ በአፋቸው “ሙስሊሙን ለመጥቀም ነው፡፡ ሙስሊሙን ጠንካራ ለማድረግ ነው” ሲሉ እንደሰማነው፣ ታድያ ለምን ይሆን እንደ ችርቻሮ ሱቅ ገና ካአሁኑ፣ አንድም ባንክ ስራ ሳይጀምር የተለያዩ ባንኮችን ስሞች እየሰማን ያለነው?!
በቅድሚያ አንዱ ባንክ ስራ ጀምሮ እንዲጠነክር ይደረጋል፡፡ ከዚያ እየታየ ሌሎችም እዚሁ ቢዝነስ ውስጥ መግባት አለብን ካሉ ቀስ በቀስ አንዱ ሲጠነክር በእግሩ ቆሞ ሲሄድ ሌላኛው ይከፈታል፡፡ ይህ ነበር መሆን የነበረበት።
ነው ወይስ በመልካም ነገር ላይ መተባበር ፈረንካ ያለበትን ዘርፍ አይመለከትም?! አላሁል ሙስተዓን!!
ባንኮቹ ሲበዙ የማርኬቲንግ ጥያቄ ይመጣል፡፡
“የእናንተ ባንክ ከሌሎች በምን ይለያል?” የሚል ይመጣል።
ያኔ “የእኛ ሸሪዐን በጣም ያማከለ ነው፡፡ ግብይቶችን በተመለከተ እኛ አንለሳለስም….” ይባላል። እንዲያውም ካሁኑ ተጀምሯል። ሌላኛው በበኩሉ ይነሳና “እነ እገሌ ዋሽተዋል፡፡ እኛም ከሸሪዐ አልወጣንም። የምን እራስን እያዋደዱ ሌላውን ማሳጣት ነው….” ሊል ነው።
ጭቅጭቅ፣ ውግዘት፣ … አንዱ አንዱን ውስጥ ለውስጥ የማሳጣት አስቀያሚ ስራ ይሰራል፡፡ ከዚያም አለፍ ሲል በዘር የተቧደኑ ወለድ አልባ ባንኮችንም እናይ ይሆናል፡፡ ምናልባት እስካሁን ይሄ ሂደት ካልተጀመረ። አላህ ይጠብቀን፡፡
ያው ነገሩ “በፈረንካ ልቤ ተነካ” ነው፡፡
አላህስ
وَتُحِبُّونَ ٱلْمَالَ حُبًّا جَمًّا
"ገንዘብንም ብዙን መውደድ ትወዳላችሁ" አይደል ያለን?!
ከፊሎች ብዙ ትንንሽ የመንደር ባንኮች መከፈታቸውን እንደ መልካም በመቁጠር “አንዱ ቢዘጋ በሌላው እንጠቀማለን” ይላሉ፡፡ እውነታው ግን መንግስት ከዘጋ ሁሉን ነው የሚዘጋው፡፡ ይሄ NGO አይደለም።
በዚያ ላይ በአቅም ማነስ እንዳይዘጉ በጀመዐ ሸሪዐውን በደንብ በጠበቀ መልኩ ጠንካራ ያልበዙ ባንኮችን መመስረት ነው የሚጠበቀው፡፡ ስለዚህ ወለድ አልባ ባንኮች ዑለማዎች የሚያነሷቸው ነጥቦች በሚገባ ታይተው እነዚህ ሁሉ ነጥቦች ተካተው ጠንካራ የሆኑ በጣም ጥቂት ባንኮች ነው የሚያስፈልጉን፡፡
|
ሌላው ወለድ ከባድ ወንጀል ነው፡፡ ነገር ግን ከወለድ የበለጠው ወንጀል ሺርክ ነው፡፡ እሱም በአላህ ላይ ማጋራት ነው፡፡ ሀገራችን ላይ ባንክ ለመክፈት ተፍተፍ የሚሉትን ኡስታዝ፣ ሸይኾች ስናይ ምን አለ ለአላህ መብት ተውሒድ ይህን ያህል ሞራል ቢኖራቸው ብዬ ተመኘሁ፡፡ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ዳዕዋ ላይ የማናውቃቸው ሰዎች ሁሉ ዱንያዊ ባንኩ ላይ በጣም ብዙ ሰዎች ብቅ ብቅ እያሉ ነው፡፡ የአላህን አማና እንወጣ። አላህ ዱንያ አኺራችንን ያሳምርልናልና፡፡
አላህ ሐቁን ይምራን፡፡ የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው፣ ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡ ኣሚን።

°•°•°• የማስተዋል ግብዣ •°•°•°
~~~~~~~~~~~~
ዶክተር ገርቢያ አልገርቢ ትባላለች። በሙያዋ ዶክተር ናት። እንዲህ ስትል አስተዋዮችን ታናግራለች:–
•
"እጅግ አደገኛና ውስብስብ የሆኑ ቀዶ ጥገናዎች በሰው ልጅ ወሳኝ ክፍሎች ላይ ይካሄዳሉ። በአእምሮውና በልቡ ላይ። ህይወቱ ባጠቃላይ በነዚህ ክፍሎቹ ላይ የተንጠለጠለ ነው።
°
ይህን ቀዶ ጥገና የሚያካሂደው ሰፋፊ አልባሳት የለበሱ፣ እራሳቸውን የሸፈኑ፣ የፊት መሸፈኛ የለበሱ፣ የእጅ ጓንቶችን ያጠለቁ ሰዎች ያሉበት የህክምና ቡድን ነው።
ይህ አለባበሳቸው ግን ለዚህ ውስብስብና አደገኛ ስራ እንቅፋት አልሆናቸውም።
•
ከዚያ ግን ‘ሒጃብና ኒቃብ ስራን፣ እድገትንና ስልጣኔን ከሚያደናቅፉ እንቅፋቶች ውስጥ ናቸው’ የሚል ሰው ታያለህ!!"

ተቀርተው ያለቁ ኪታቦች በከፊል
የሚከተለው የቴሌግራም ቻናል ጆይን በማለት ተቀርተው ያለቁ ሙሉ የኪታብ ኦዲዬዎችን ዳውን ሎድ ያድርጉ
https://t.me/Kitaboch
- አርባኢን (40 ሀዲሶች)
- አቂደቱል ዋሲጥያ (በኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ)
- አል-ሙዕተቀዱ አስ-ሰሒህ
- ኩን ሰለፊያ (በኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ)
- አጀሩምያ (በኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ)
- አል-ዋጂባት
- ኹዝ አቂደተክ
- አል-ኡሱል አስ-ሰላሳ
- አል-ቀዋኢዱል አል-አርበኣ
በተጨማሪ ከ400 በላይ ሙሃደራዎች እና አጫጭር የድምፅ መልእክቶች ለማግኘት የሚከተለውን ቴሌግራም ቻናል ጆይን ይበሉ
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem

ጥቂት ስለ ዐቂቃ /ነሲካ/
~~~~~~~~~~~~~~~
① የዐቂቃ ሌላኛው ስያሜ "ነሲካ" ሲሆን ዐቂቃ ከማለት ይልቅ ይህን ስም ማስቀደሙ የተሻለ እንደሆነ የሚያመላክት ማስረጃ አለ። ይሄ ስያሜ ብዙሃኑ ሙስሊም ዘንድ ስለተዘነጋ ቃሉን ለማስተዋወቅ በማለም ከዚህ በኋላ ዐቂቃ ከማለት ይልቅ "ነሲካ" የሚለውን #በብዛት እጠቀማለሁ።
② ነሲካ ከነብዩ ﷺ ብዙ ትእዛዝ የመጣበት ስለሆነ አቅም ባለው ሰው ላይ ግዴታ ነው። [አልኢርዋእ: 1166] [አሶ፞ሒሐህ: 2760] ያልቻለ ሰው በሚችል ጊዜ ያርዳል።
③ ልጅ እያለ ነሲካ ያልታረደለት ሰው ከቻለ ኋላ ቢያርድ የተወደደ ነው። ነብዩ ﷺ ነብይ ሆነው ከተላኩ በኋላ ዐቂቃ አርደዋል። [አሶ፞ሒሐ: 2726] ኢብኑ ሲሪን "ዐቂቃ እንዳልተደረገልኝ ባውቅ ኖሮ ለራሴ ዐቂቃ አደርግ ነበር" ብለዋል። ሐሰነል በስሪም "ዐቂቃ ካልተደረገልህ ትልቅ ሰው ብትሆን እንኳ ለራስህ ዐቂቃ አድርግ" ብለዋል። [አሶ፞ሒሐ: 506]
④ ነሲካ የሚታረደው በ7ኛው ቀን ነው። ካልተመቸ በ14ኛው፣ ካልተመቸ በ21ኛው ቀን ይታረዳል። [ሶሒሑል ጃሚዕ: 2/4132] ይህም ካልተመቸ በተመቸ ቀን ማድረግ ይቻላል። ማሳሰቢያ:–
* የተወለደበት ቀን እራሱን ችሎ ይቆጠራል።
* በኢስላማዊ አቆጣጠር አንድ ሙሉ ቀን መቁጠር የሚጀመረው ከሌሊቱ ክ/ጊዜ ነው።
⑤ ለነሲካ የሚታረድ እንስሳት ከኡዱሒያ ጋር የሚመሳሰልበት አለው። በሽተኛ፣ ሰባራ፣ አይኑ የጠፋ፣ አንካሳ፣ ጆሮው የተቆረጠ፣ ላቱ የተቆረጠ፣ … መሆን የለበትም። ስጋውም ሆነ ቆዳው አይሸጥም።
⑥ የነሲካ መጠን ለወንድ ልጅ ሁለት በግ፣ ለሴት ደግሞ አንድ በግ ነው።
* የሚታረደው በግ ወንድም ሴትም ቢሆን ችግር የለውም። [ሶሒሑል ጃሚዕ: 4106] [አልሚሽካት: 4152]
* ያልቻለ ሰው ለወንድ ልጅም አንድ በግ ብቻ ማረድ ይችላል። [አቡ ዳውድ: 2841]
* ከብትና ግመል ማረድ እንደሚቻል ብዙሃን ዑለማዎች ቢናገሩም ይህን የሚያሳይ ግልፅ ማስረጃ ግን የለም።
* ልክ እንደ በግ ፍየል ማረድ ይቻላል።
⑦ አጥንቱን አለመሰባበር እንደሚወደድ ከተወሰኑ ሰለፎች ተላልፏል። ግና ግዴታ ስላልሆነ ላጠቃቀም የሚያስቸግር ከሆነ መሰባበሩ ችግር የለበትም።
⑧ የአንድ ልጅን ነሲካ ወላጅ፣ ዘመድ እንዲሁም ባእድ ሰውም ሊያርድለት ይችላል። ነብዩ ﷺ ለልጅ ልጆቻቸው ሐሰንና ሑሰይን አርደዋል።
⑨ ለሞተ ልጅ ነሲካ እንደሚታረድ የሚያሳይ ግልፅ ማስረጃ የለም።
(10) የነሲካ ስጋ እንደ ኡዱሒያ እንደሆነ ሰልፎች ጠቅሰዋል። ስለሆነም ከተቀቀለ በኋላ ለቤተሰብ ይቀርባል፤ ለጎረቤት ወይም ለምስኪን ይሰጣል። የፈለገ ቀቅሎ ለምስኪን ማከፋፈል ይችላል። የፈለገ ጥሬውንም ማከፋፈል እንደሚችል ዑለማዎች ይጠቅሳሉ።
(11) ነሲካ በገንዘብ አይወጣም። በአካባቢው እርድ ማረድ የማይፈቀድ ከሆነ ሌላ ቦታ እንዲታረድ ይደረጋል።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሃምሌ 8/2011)
t.me/IbnuMunewor