Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
6. የዘመናዊ የተክፊር አስተሳሰብ መሰረቱ ኢኽዋን ነው፡፡ “እሄ የምንኖርበት ማህበረሰብ እራሱ ሙስሊም ማህበረሰብ አይደለም፡፡” “ጉዳዩ የማመንና የመክፈር ጉዳይ ነው፡፡ ሰዎች እንደሚሞግቱት ሙስሊሞች አይደሉም፣ የሚኖሩት የጃሂሊያ ህይወት ነው፣ ደዐዋችን የተነሳው እነኚህን ጃሂሊዮች ወደ ኢስላም ለመመለስ ነው-እንደ አዲስ ሙስሊም ለማድረግ፡፡” እነዚህ የኢኽዋኒው ሰይድ ቁጥብ ንግግሮች ናቸው፡፡(ፊ ዚላሊል ቁርኣን፡ 3/1816) (መዓሊሙን ፊጦሪቅ፡ 173)
7. ኢኽዋኖች ከዘመናችን ሙስሊሞችም አልፈው ሶሐባ ሳይቀር የሚያከፍሩ ናቸው፡፡ "የአቡ ሱፍያንን እስልምና “የከንፈርና የምላስ እስልምና እንጂ የልብ ኢማንና እውነቱን የማግኘት አይደለም፡፡ ኢስላም ወደዚህ ሰውየ ልብ አልሰረፀም፣ ከሰለመ በኋላም የሙስሊሞችን ሽንፈት ሲመኝ የነበረ ነው!!” የሚለው ሰይድ ቁጥብ አይደለምን? “በኑ ኡመያ በጥቅሉ ኢማን ከልባቸው አልሰረፀም፡፡ ኢስላም ለነሱ እንደ ጥቅማቸው ሲያሻቸው የሚለብሱት ሲፈልጉ የሚያወልቁት ካፖርት ማለት ነው፣ ስነ ምግባር፣ ዲን፣ ልቦና የማይገታቸው ሰዎች ናቸው…” የሚለው ሰይድ ቁጥብ አይደለምን? (አልዐዳላህ፡172)
[መ] ይሄው ሃምሳ ሃምሳ የተሰኘው ዋልጌ “የሳዑዲ ንጉሳዊ ቤተሰቦች የአይሁድ ቤተሰብ ርዝራዦች ናቸው” ይላል፡፡ መልስ፡-
1. የሰዑድ ቤተሰብ ታሪክ በዝርዝር የሚታወቅ ስለሆነ ስለሱ አላወራም፡፡
2. ግን የአይሁድ ቤተሰብ ቢሆኑ ምንድን ነው ችግሩ?! እነ ዐብደላህ ኢብኑ ሰላማ፣ እነ ዐጢያ አልቁረዚ፣ እነ ከዕቡል አሕባር የአይሁድ ዘር አይደሉምን?! ታላላቅ የኢስላም ስብእናዎች ውስጥ የአይሁድ ዘር ያላቸው አላለፉምን?! ነው ወይስ አይሁዳዊ ዘር ቢሰልምም የማይፀዳ ቆሻሻ ነው?
3. ነው ወይስ የሰዑድ ቤተሰቦች የሰለሙ መስለው በኢስላምና በሙስሊሞች ላይ የሚያሴሩ ስውር አይሁዶች ናቸው ለማለት ነው?! እነዚህ ናቸው እንግዲህ ሙስሊሞችን እያከፈሩ ከዚያም ሰዎችን ተክፊሮች እያሉ የሚወነጅሉት የኸዋሪጅ ወራሾች!!
ልመለስ እችላለሁ፡፡ (ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 3/2009)
ወዴት እየሄድን ነው?
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን፡፡
ለሂጅራ ቱብ የተሰጠ ማስተካከያና ማስገንዘቢያ፡፡
እግር ኳስ ስንቱን ሙስሊም ከጌታው ያራቀ፣ ጀመአ ሰላትን የሚያዘናጋ ከባድ ፈተና ሆኖ ሳለ እራሱን “Hijra Tube ኢስላማዊ ድህረ ገፅ” ብሎ የሚጠራው ስለ አንድ ታዳጊ ፓንክ የተቆረጠ ሙስሊም ወጣት በምስሉ ላይ እንደምታዩት እያደናነቀ የለቀቀው ጉድ አስገራሚ ነው፡፡
እንዲህም ይላል “ታዳጊ ኡመር አስገራሚ የኳስ ብቃት የአርሰናል የወደፊት ተስፋ ተብሏል ማሻ አላህ በሉት ሙስሊም በሁሉም ዘርፍ ስኬታማና ዝነኛ ሲሆን ማበረታታት ይገባናል” ይላል፡፡
እንግዲህ እራሱን “ኢስላማዊ ድህረ ገፅ” ብሎ የሚጠራው ይህን ያህል የሀይማኖት እውቀት ክፍተት ካለበት ሌላው ሰው ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ነው፡፡ ማሻ አላህ የሚባለውን እና የማይባለውን እንኳን አለማወቁ ያሳዝናል፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ፀጉራችሁን ስትቆረጡ አንዱን ከአንዱ አታበላልጡ” ብለው አዘው ሲያበቁ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)ን ትእዛዝ ተቃርኖ ፓንክ የተቆረጠው ብሎም ስትራይፕ መስመር ያወጣው ወጣት ምኑ ነው የሚደነቀው?
ምኑስ ነው ማሻ አላህ የሚባለው?
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በወጣትነቱ ጌታውን ያመለከ ወደ ጀመኣ ሰላት የተሯሯጠ ጥላ በሌለበት ቀን “አርሽ ጥላ ስር” እንደሚሆን ነግረውን ሲያበቁ ለምን ይሆን ወጣቶች እንዲህ አይነት ከኢስላማዊ እውቀት እና አምልኮ ከሚያርቃቸው ነገር ላይ ቢዚ እንዲሆኑ የሚበረታቱት?
ሱብሃነላህ ያሳዝናል፡፡
“ሙስሊም በሁሉም ዘርፍ ስኬታማና ዝነኛ ሲሆን ማበረታታት ይገባናል” ሲልም ድህረ ገፁ ፅፏል፡፡
ስኬታማነት እና እድለኝነት በምን እንደሆነ አለማወቅ ከባድ አደጋ ነው፡፡ በኢስላም እና ሱና አላህን ፈርቶ የአላህን እና የመልክተኛውን ትዕዛዝ እየተገበሩ እና እነሱን ከመቃረን በመራቅ ቢሆን እንጂ ስኬት እና እድለኝነት አይገኝም፡፡
ዝነኝነት …….
እባካችሁ ሂጅራዎች ወይንም ሌሎች ኡመተል ኢስላምን በተለይ ወጣቱን ትውልድ እንዲህ ሰንካላ ወደ ሚያደርጉት ተግባሮች አትጥሩት፣ አታበረታቱት፡፡
እኛ ከኢስላም በላይ ፀጋ የለንም፡፡ ኢስላምን ሙሉ በሙሉ ከተከተልን በዱንያም በአኸይራም የተከበርን ነን፡፡ ሌላ ሚዛን አታምጡብን፡፡ እናንተ ከአማኞች መሪ ኡመር (ረድየላሁ አንሁም) በላይ አታውቁም፡፡
ኢስላም የሙስሊም ወጣቶችን በኢስላማዊ እውቀት እና ትክክለኛው አምልኮ ላይ ቢዚ እንዲሆን እንጂ ኳስ፣ ድራማ፣ ፊልም፣ የመናገር ብቃት፣ የስነፅሁፍ ምሽት ምናምን እያሉ በማይረባ ጠፊ አለም ታዋቂነት እና ዝነኝነት ላይ ቢዚ የሚሆኑ ትውልዶች እንዲኖሩ አይፈልግም፡፡
የሚገርም ነው፡፡ ትክክለኛውን የመልክተኞች ጥሪ የሚጣሩ ኡለማዎችና ዱኣቶች ከኳስ ራቁ፣ ጀመኣ ሰላት ኑ ይላሉ፡፡ በዚህ በኩል ደግሞ እግር ኳስ ተጫዋቹ ሙስሊም ስለሆነ ብቻ “ሙስሊም በሁሉም ዘርፍ ስኬታማና ዝነኛ ሲሆን ማበረታታት ይገባናል” የሚሉ አፍራሽ ዳእዋዎችን እንዲህ አይነት በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሰዎች ጋር ሊደርሱ የሚችሉ ፔጆችን ይዘው የሚያሰራጩም አሉ፡፡
አንድ ነገር ብዬ ላቁም ሙስሊሞች ሆይ! አላህን እንፍራ እኛ ሁላችንም አንድ ብቸኛ የሆነችውን የሐቅ መንገድ እንከተል፡፡ ይሄ ለሁለት አገር ስኬት ያበቃል፡፡ አለበለዚያ ጫት የሚቅም ብሎም ጫት እንዲቃም የሚያበረታታ የመስጂድ ኢማም፣ አጅነቢ የሚጨብጥ ታዋቂ ሙስሊም፣ ሰላት የማይሰግድ ወይንም ሰላት የሚያሳልፍ ዶክተር ፓይለት ኢንጂነር፣ ሂጃብ የማትለብስ ታዋቂ ጋዜጠኛ ሴት፣ መስጂድ የማይመጣ የስፖርት ዘጋቢ፣ ያለ ጠባቂ አለምን የምትዞርና የምትጓዝ የዱንያ ትምህርት በጣም የተማረች አንደበተ ርቱእ ሴት፣ ፓንክ የሚቆረጡ ወጣት ሙስሊሞች፣ ጫት መጠጥ ሀሺሽ የሚጠቀሙ ሙስሊም ወጣቶች፣ ፂማቸውን የሚላጩ ኦ የሚቆረጡ ቃሪያ እና ሲኪኒ ሱሪ የሚለብሱ ሙነሺዶች፣ ለአቂዳ ቦታ የማይሰጡ ወይንም የሚገባውን ያህል ትኩረት የማይሰጡ ዱኣቶች፣ ፈጅር ሰላትን ተነስተው በሰኣቱ በአላህ ቤት የማይሰግዱ ወንዶች፣ ለድራማ ነው ብለው አጅነቢ የሆኑ ወንድ እና ሴቶች የሚጨባበጡ ሙስሊሞች እና ሌሎችም ነፍሳቸውን እየጎዱ ነው፡፡ ኢስላምን እና ሙስሊሞችን እንጠቅማለን ከማለታቸው በፊት ነፍሳቸውን ሸሪኣዊ እውቀት ተምረው መለወጥ ነው ያለባቸው፡፡
አንዳንዶች ለምን በግል አትነግራቸውም ለሚሉ የምለው አንድ ነገር ነው፡፡ በአደባባይ ለመቶ ሺዎች የተሰራጨ ስህተት በአደባባይ ይታረማል፡፡
ስለዚህ ሁላችንም እራሳችንን አላህን ፈርተን ኢስላም የሚለንን እንከተል፡፡
በውሸት ማሸነፍ አይቻልም፡፡
ነገሮች ሁሉ የማይሰወሩት አላህ እነ ያሲን ኑሩን ሳውዲ ላይ በምን እንደታሰሩ ማን እጁ እንዳለበት ማን እጁ እንደሌለበት ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ “ሳዳት ከማል አሳስሯቸዋል” ብሎ አንድ የሚያወራ ግለሰብ ተቀድቶ የላከው ኦዲዬ ደረሰኝ፡፡ ምን እላለሁ ሁሉን ቻይ እና አሸናፊ ሀቁን ያውጣው ከማለት ውጭ፡፡ እኔ ሳውዲ መሄዳቸውንም ያው በየቦታው እየተነሱ ሶሺያል ሚድያ ላይ ከሚለቀቀው ፎቶዋቸው ነው ያወቅኩት፡፡
ከእስር ቤት ሲወጡ ቀናችሁ ይላሉ፡፡ እስር ቤት ሲገቡ እገሌ ነው ያሳሰራቸው ይባላል፡፡ አሁን ይህ ግለሰብ ማስረጃ አምጣ ተብሎ ቢጠየቅ ከየት ያመጣል?
እኔ ግር እንዳይላችሁ ግልፅ ማድረግ የምፈልገው ሙስሊም የሆነ ሰው ሲቸገር፣ ሲታሰር የምደሰት አይደለሁም፡፡ እነ ያሲን ኑሩ በአደባባይ በሚረጩት የተበላሸ አስተምህሮት አበሳጫለሁ፡፡ እጄንም አጣጥፊ አልቀመጥም መልስ ከወንድሞች ጋር ተማክሪ እንሰጥባቸዋለን፡፡ ከዛ ውጭ የነሱን ጥፋት ዝም ያላለ ሁሉ የኢስላም ጠላት ነው የሚባል የኸዋሪጅ አካሄድ ነው፡፡
አልሐምዱሊላህ እነሱም መርዛቸውን ይረጫሉ እኛም መልስ እንሰጣለን ጥፋታቸውን እናርማለን ሐቁ ከእለት እለት ግልፅ እየወጣ ነው፡፡ እነሱ ላይ መልስ በመስጠታችን ሐቁ ግልፅ እየሆነ ሰዎች ከተሳሳተው መንገድ እየወጡ ስለሆነ ጌታዬን ከልብ አመሰግነዋለሁ፡፡ በአላህ እርዳታ እና ሀይል ቢሆን እንጂ እኛ ደካማዎች እና አቅመቢሶች ነን፡፡ የስሜት ተከታዬች አለ የሚሉትን ሚድያ፣ ቻናል፣ መስጂዶች፣ የመስጂድ ኮሚቴዎች፣ ባለሃብቶችንና አብዛኛውን ጭፍን ተከታዬቻቸውን ተጠቅመው የረጩትን መርዝ በአላህ ፍቃድ እና እገዛ በመታገዝ እና በመታገስ ይሀው ዛሬ ጥቂቶች የማይባሉ ከተበላሹ መንገዶች ወጥተው ወደ ሀቁ ጎዳና በአላህ ፍቃድ ተቀንተዋል፡፡
አልሐምዱሊላህ አሁንም አልሐምዱሊላህ፡፡
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
ገንዘብ ከፍለው የተቀዳደ ልብስ የሚለብሱት ለምንድን ነው?
አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ “ፋሽን፣ እስታይል” እየተባለ ከተማው ላይ ታፋ፣ ጉልበትና ሌላም ቦታ የተቦጫጨቀ እና የተቀደደ ከዛም አልፎ ሀፍረተ ገላን በጣም ወጥሮ የሚያሳይ ልብስ ወንዶችና ሴትች መልበሳቸው እየተለመደ መጥቷል፡፡ አረ አላህን እንፍራ ሰይጣን አደም እና ሀዋን ከሀፍረተ ገላቸው ሊገልፅባቸው እንደጎተጎታቸው ጌታችን አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል፡፡
فَوَسْوَسَ لَهُمَا ٱلشَّيْطَٰنُ لِيُبْدِىَ لَهُمَا مَا وُۥرِىَ عَنْهُمَا مِن سَوْءَٰتِهِمَا
ሰይጣንም ከሐፍረተ ገላቸው የተሸሸገውን ለእነርሱ ሊገልጽባቸው በድብቅ ንግግር ጎተጎታቸው፡፡
ድሮ ሰው የተቀደደ ልብስ የሚለብሰው ወይ ቸግሮት ወይ አብዶ ነበር፡፡ ዛሬ ስንት እና ስንት ገንዘብ አውጥተው “ባለትራክ….” ምናምን እያሉ የተቀደደ ልብስ ይለብሳሉ፡፡ አላህ የልብ መመልከቻችንን ያብራልን፡፡ ወጣቶች ሆይ! ሰይጣን የአባታችን አደም እና የዝርያዎቹ ጠላት ነው፡፡ ጠላት አድርገን እንያዘው፡፡
ወጣቶች ሆይ! አላህን ፍሩ አለባበሳችሁን አስተካክሉ፡፡ እስልምና ውስጥ ጠቅለል ብሎ መግባት ኋላ ቀርነት ወይንም ፋርነት አይደለም፡፡ ነቃ እንበል ብልጥ ማለት ለማይጠፋው አገሩ የሚሆን ስንቅ የሚሰንቅ ነው፡፡
አላህ ወደሱ በንሰሀ ተመላሾች፣ እሱን አመስጋኞች፣ ለሚቀጥለው አለም ከሚዘጋጁ ባሪያዎቹ ያድርገን፡፡
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ትንሹ ኢድ የሚባል ነገር በሸሪዓ የለም፡፡
*************************************
ምስጋና ለአላህ ነው፤ ሁለት የመደሰቻ በአላትን የደነገገ፡፡ አሁንም ምስጋና ይገባው ይህንን ሸሪዓ ከመበረዝ እጠብቀዋለሁ ብሎ ቃል የገባው አላህ፤ የሃይማኖት ድንጋጊን ሁላ ለራሱ ብቻ ያደረገ፤ በዚህም ላይ ታላቅ ጥበቡን ያሳየ፡፡ እንደሌሎቸ ሀይማኖቶች፤ ቀሳውስት እንደበረዙት (እንደጨመሩበት እና እንደቀነሱበት) እንዳይሆን በግልፅ ሸሪዓዊ ድንጋጌን ለራሱ ብቸኛ አውጪ ያደረገ፡፡
ሱና ፆም ፆመን ዝም ብሎ ማለፍ እንጂ ከአላህ የተደነገገ በዓል የለም፡፡ ትንሹ ኢድ የሚባል ነገር፤ ከነብያችንም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፤ ከሰሃባዎቻቸው (ሪድዋኑላሂ አለይሂም)፤ ከ3 ምርጥ ትውልድ፤ ከ4 አኢማዎች አላገኘንም፡፡ ታድያ ለምንድን ነው እኛ ያልታዘዝነውን የምንሰራው???
ሰኞ እና ሀሙስ ፆመን ምንም በአል ከሌለ፤ 13፣14፣15 ፆመን ምንም በአል ከሌለ፤ የሸዋል 6 ከየት መጣ??? አላህን እንፍራ፡፡
አንዳንድ ቦታ ያውም ከዋናው ኢድ በላይ ይህን ቀን ያከብሩታል፡፡
እወቅ የአላህ ባሪያ ከሽርክ ቀጥሎ ሸይጧን ዘንድ የተወደደው ወንጀል ቢድዓ ነው፡፡ ሁሉም ቢድዓ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ ለእሳት ነው፡፡
አላህ በደነገገልን 2 ኢዶች፤ ከዛ በጁምዓ ብቻ እንብቃቃ፡፡ ሁሉ ነገር የሌለው ይቀላውጣል፡፡ አላህ ግን ይህን ዲን ሞልቶታል፤ ታድያ እንደ አህለል ኪታብ መጨማመሩ ምን አስፈለገ፤ የአላህን ቁጣ ለመውረስ ካልሆነ፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ትንሹ ኢድ የሚባል ነገር በሸሪዓ የለም፡፡ ተጠንቀቁ አስጠንቅቁ፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት እና ሩሱሎች ኢማም ላይ ይሁን፡፡
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
ለኡማው አሳቢዎቹ ብልጦቹ የሳውዲ ኡለማዎች፡፡
==============================
የሳኡዲ ኡለሞዎች አልሐምዱሊላህ ብልጦች ናቸው ማንም አላዋቂ ያለውን ቢላቸው የሰይጣንንም ሆነ የአሜሪካን ህልም አያስፈፅሙም፡፡
አላዋቂዎች እና ስሜት የሚጋልባቸው ሰዎች አንድን ሰው “ኡለማ ደፋርና የማይፈራ” የሚሉት ደም የሚያፋስ፣ ሙስሊሞችን ለችግር የሚዳርግ፣ ሙስሊም አገራትን ለጠላት በር ለመክፈት ሰበብ የሚሆንን ግለሰብ ነው፡፡
ሳውዲ እና ኡለማዎቿ አላዋቂዎች እንደሚሉት የአሜሪካ ወዳጆች አይደሉም፡፡ አላዋቂዎች የአሜሪካ ምኞት ምን እንደሆነ ቢያውቁ ለዚህች ውድ የተውሒድ አገር ጥብቅና ይቆሙ ነበር፡፡ ነገር ግን አለማወቅ ከባድ በሽታ ነው፡፡ አለማወቃቸውን አለማወቅ ሲደረብበት ደግሞ የበሽታም በሽታ ነው፡፡
አሜሪካ ሳውዲን አራት ቦታ እንድትከፋፈል እና ልፍስፍስ አገር እንድትሆን ትመኛለች፡፡ ከመመኘትም አልፎ ሙከራዎችን አድርገዋል፡፡ ሌሎች አገራት ላይ ሰልፍ እንደሚቀሰቀሰው ሳውዲም ላይ ሰልፍ ተብሎ ተቀስቅሶ ይህች የተቀደሰች አገር ወደ ብጥብጥ ገብታ እንድትፈራርስ ይፈልጋሉ፡፡ የነብያት ወራሾች፣ ለዲናቸው ታማኝ የሆኑት እነዚህ ብርቅዬ ኡለማዎች ህዝባቸውን ባለው የሙስሊም መሪ ላይ አምፀው እንዳይወጡ፣ ህዝቡ መሪው ላይ ለሚያየው ስህተት ዱኣ እንዲያደርግ እና እንዲታገስ በማድረግ ይሀው አገሪቷ ከአላህ በታች በነዚህ ብርቅዬ ኡለማዎች ሙስሊሞች ደማቸው ሳይፈስ ጠላትም አይኑ እንዳፈጠጠ ቀረ፡፡ አላህ ሳውዲንም ይሁን ሌሎች የሙስሊም አገራትን ከውስጥም ከውጭም ጠላት ይጠብቃቸው፡፡
አስገራሚው ደፋር ተብዬዎቹ የፈተና ቀስቃሾች በሰላም ካሉበት ተቀምጠው ሙስሊም አገራትን እና ህዝባቸውን አሁን ላሉበት አደጋ ዳርገዋል፡፡ የጠላትንም አላማ አሳክተዋል፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለሙስሊሞች መሪን አስመልክቶ የመከሩት ይህን ነበር፡፡
- “የሀበሻ ባሪያም ቢሾምባችሁ ስሙት ታዘዙት”፣
- “እጅህን ጠምዝዞ አንገትህን ይዞ ገንዘብህን ቢቀማህ ሰላትን እስካቋቋሙ ድረስ ……. ስሙ ታዘዙ”፣
- ሰሃባዎች የአላህ መልክተኛን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ጠየቁ “የእሱን ሀቅ የሚጠይቀን የእኛን ሀቅ የማይሞላልን መሪ ካጋጠመን ምን እናድርግ” የአላህ መልክተኛም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ስሙት ታዘዙት” ሲል ይግባኝ የሌለውን ፍርዳቸውን ሰጡ፡፡ እናም ሌሎች ትምህርቶችንም ሰጥተዋል፡፡
አሳዛኙ ዛሬ የነ አሜሪካ ጠላት ነን እያሉ የነ አሜሪካን ህልም የሚያስፈፅሙ በኢስላም ስም የሚንቀሳቀሱ መኖራቸው ነው፡፡ አገራችንም ላይ ይሁን ከአገራችን ውጭ የሳውዲ ለሙስሊሙ መልካም አሳቢ የሆኑትን ኡለሞች የሚያከፍሩና የሚወርፉትን ተመልከቷቸው በኩፍር እና ሺርክ የተሞሉትን ሺአ ራፊዳዎች ምንም ሲሉ አትሰሟቸውም፡፡ ምክንያቱም እነሱ ዘንድ ለአላህ ብሎ መውደድ እና ለአላህ ብሎ መጥላት የለም፡፡ ስልጣን ፍለጋ ማድረግ ያለባቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡ እንዲያውም የግብፁ ኢኽዋን መሪ ሙሐመድ ሙርሲ ስልጣን ሲይዝ ሰሃባዎችን የሚያከፍሩ፣ በኩፍር የተጨማለቁ፣ ቀን እና ለሊት ሰሃባዎችን የሚራገሙትን የኢራን ሺአዎች ግብፅ ላይ በሩን ከፈተላቸው አላህ እሳት ለቀቀበት፡፡ ሰው የዘራውን ያጭዳል፡፡
አሜሪካን ተመልከቱ ኢራንን ላይ ላዩን አሸባሪ ትላታላች ግን የሱንዬችን አገር ኢራቅ ወራ ስልጣኑን ለኢራን አስረክባ ነው የወጣችው፡፡
አረ የአእምሮ ባለቤቶች እንንቃ፡፡ ሳውዲ እና የሳውዲ መሪዎች ልንከላከልላቸው ይገባል ስንል ከስህተት የፀዱ ናቸው እያልኩ አይደለም፡፡ ነገር ግን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሙስሊም መሪ ሲያጠፋ ለብቻው ዞር ተደርጎ እንደሚመከር ስለነገሩን እኛም የሙስሊም መሪዎችን ስህተት አደባባይ ላይ አይለቀቅም የምንለው፡፡ ተወደደም ተጠላም አለም ላይ ተውሒድ እና ሱና የበላይ የሆነባት ሺርክና ቢድኣ የተዋረደባት አገር እንደ ሳዉዲ የለም፡፡ አላህ ሳውዲንም አሁን ካለችበት የተሻለ ያድርጋት፣ ሌሎች ሙስሊም አገሮችንም አላህ ወደሚፈልገው መልካም ይምራቸው፡፡
የሳውዲ እንቁዎች ግን ሰው ያለውን ቢላቸው ሰይጣንን እና መሰሎቹን እየተቃረኑ ኢስላም የሚለውን በግልፅ ያስተምራሉ፡፡ ኡለማ ያልሆኑ በዲን ስም የሚንቀሳቀሱት ደግሞ ሰይጣን እየጋለባቸው የጠላትን አጀንዳ እያስፈፀሙ ሙስሊሞችን እና ሙስሊም አገራትን ለመከራ ይዳርጋሉ፡፡
በነገራችን ላይ አገራችንም ላይ ይሁን ሌሎች ቦታዎች ላይ ስሜታቸውን አምላኪዎች የሳውዲ ኡለሞችን “የንጉሳዊያን ስልጣን ጠባቂዎች”፣ “የአምባገነኖች ምርኩዞች”፣ “የቤተሰመንግስት ፍርፋሪ ለቃቃሚዎች” እንዳሏቸው ሁሉ ነብዩ ሙሐመድን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ምን ሊሏቸው ነው?
ምክንያቱም የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ከእኔ በኋላ የማያዝኑላችሁ መሪዎች ይመጣሉ… ስሟቸው ታዘዟቸው” ብለዋልና ? ? ? ? ? ?
እኮ መልስ ይስጡና ???
የነዚህ ሰዎች ምሳሌ አላህ ቁርኣን ላይ እንዲህ ሲል እንደገለፃቸው ነው
وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا تُفْسِدُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ قَالُوٓا۟ إِنَّمَا نَحْنُ مُصْلِحُونَ
ለነርሱም «በምድር ላይ አታበላሹ» በተባሉ ጊዜ «እኛ አሳማሪዎች ብቻ ነን» ይላሉ፡፡

እነሱ አሳማሪ ነን የሙስሊሙ መብት ያስጨንቀናል ቢሉም አላህ እንዲህ ሲል መልስ ሰጣቸው
أَلَآ إِنَّهُمْ هُمُ ٱلْمُفْسِدُونَ وَلَٰكِن لَّا يَشْعُرُونَ
ንቁ እነርሱ አጥፊዎቹ እነሱው ናቸው፤ ግን አያውቁም፡፡

አላህ ሆይ! በዲን ስም ዲን ከመናድ በአንተው እንጠበቃለን፡፡ ሀቁን መንገድ ምራን በጠላቶቻችን ላይ ድልን አጎናፅፈን፡፡ የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምረሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
ጥፋታቸውን በዲን ሽፋን ቀብተው ይለቁና ሲጋለጡ እንዲህ ይሉናል
“የሰውን ነውር አትከታተሉ”
እኛም እንዲህ እንላቸዋለን
“ነውር ከሆነ ለምን ለቀቁት?”
ስለዚህ በዲን ስም የሚለቀቅ ጥፋታቸውን ህዝብ ይጠነቀቀው ዘንድ እኛም በአደባባይ እናጋልጠዋለን፡፡ የግል ጉዳይ ከዲን ጋር የማይገናኝ ከሆነ የሙስሊም ነውር ስለሚሸፈን እኛም እንሸፍነዋለን፡፡ የእኛንም አላህ ሸፍኖልናል፡፡ አላህም የሁላችንንም የግል ወንጀል ይሸፍንልን፡፡
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
👆🏻እነሱ ሳይፈልጉ ተከታዬቻቸው ነው ፎቶዋቸውን ፖስት የሚያደርጉት ለሚሉ ወንድም እና እህቶች ማስረጃ ይሆናቸው ዘንድ እና እነሱ እራሳቸው ፎቶዋቸውን ኡምራ ሲያደርጉ፣ ሰደቃ ሲሰጡ እና ሌላም ሲያደርጉ አምነውበት ለመሆኑ ይህችን ማስረጃ እንካችሁ፡፡ አንድ ወንድሜ እንዲህ አለ
አላህ በሀዲሰል ቁድስ እንዲህ አለ፦
«ፆም የእኔ ነው በእርሱም የምመነዳው እኔው ነኝ!»
ይህን ገለፃ ይበልጥ የሚያጠናክረው ነገር ቢኖር ሰዎች ዑምራቸውን እንደሚፖስቱት ሁሉ ፆማቸውን መፖሰት አለመቻላቸው ነው!
ዐጃኢብ!!!!!
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
የኢኽዋኖች ሚዛን?
አሁን ያለው የኳታር መሪ (አላህ ይጠብቀው) አባቱ እና አያቱ?
አሁን ያለው የኳታር መሪ (አላህ ይጠብቀው) አባትየው ከአያትየው በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ሲቀማ ኢኽዋኖች ዝም አሉ፡፡ አሁን ያለው የግብፅ መሪ ሲሲ (አላህ ይጠብቀው) ከሙሐመድ ሙርሲ ስልጣን በመፈንቅለ መንግስት ሲቀማ ኢኽዋኖች ሁሉ ተንጫጩ፡፡
ለምን?
አሁን ያለው የኳታር መሪ (አላህ ይጠብቀው) ከአባቱ ስልጣንን ሲረከብ ኢኽዋኖች ዝም አሉ፣ ጭራሽ አደናነቁት፡፡
ታላቁ ሰሃባ ሙአዊያ ኢብን አቡ ሱፍያን (ረድየላሁ አንሁ) ለልጁ ስልጣን ሲያስተላልፍ የሚከተለውን አሉ “ይሄ በኢስላም መሰረት የለውም” ነው እና የመሳሰለውን አሉ፡፡
ሳውዲዎቹ መሪዎች (አላህ ይጠብቃቸውና) ወንድም ለወንድሙ ወይንም አባት ለልጁ ስልጣን ሲያስረክብ ኢኽዋኖች “ስልጣን በዘር መወራረስ በኢስላም የለም” አሉ፡፡
ለኳታር ሲሆን ዝምታ ለሳውዲ ሲሆን ተቃውሞ የሆነው በምን ምክንያት ነው?
አህሉሱና ወል ጀመኣ ሙስሊም መሪ በሰላምም ይያዝ በሃይል በመልካም እስካዘዘ ድረስ ለሱ መስማት እና መታዘዝ አለ ይላሉ፡፡ ኢኽዋንን የመሰሉ የጥመት ቡድኖች እነሱ የሚፈልጉት ሲነግስ መስማት እና መታዘዝ አለብን እሱን መቃወም ክልክል ነው ይላሉ፡፡ እነሱ የማይፈልጉት ሲሆን ስሙን ያጠፉታል፡፡ በሰይጣናዊዉ አልጀዚራ ጣቢያቸው ህዝብ እንዲያምፅበት ይቀሰቅሳሉ፡፡
አላህ ሙስሊም መሪዎችን በጠቅላላ ባሉበት ይጠብቃቸው፡፡ ህዝባቸውንም መሪዎቹንም አላህ ለመልካሙ ይለግሳቸው፡፡ አላህ በመሪዎቹ መካከልም ይሁን በህዝባቸው መካከል መስማማትን ይለግሳቸው፡፡
ኢኽዋኖች ተንቅቶባችኋል፡፡
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
ነብዩ ﷺ “የወር አበባ ላይ ያለችን ሴት ወይም ደግሞ ሴትን በፊንጢጣዋ በኩል የተገናኘ፣ ወይም ከጠንቋይ ዘንድ ሄዶ በሚናገረው ያመነ ሰው በሙሐመድ ላይ በተወረደው ክዷል” ብለዋል፡፡ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል፡፡ [ሶሒሑ አትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 2433]
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
ጠያቂ፦ ነሺዳን ከየት አመጣችሁት?
እነርሱ፦ ረሱል(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሀሳን ኢብኑ ሳቢት የሚባል ገጣሚ ነበራቸው እኮ
ጠያቂ፦ ሀሳን ኢብኑ ሳቢት እንደናንተ ድምፁን ለማሳመር እንደ ሴት ያምጥ ነበር? ቅላፄስ ነበረው? ክሊፕስ ይሰራ ነበር? ረመዳንን እየጠበቀ በግጥሙ ሶሀቦችን ከቁርአን ያሰናክል ነበር? ሱሪውንስ ጎታች ነበር? ያጨበጭብስ ነበር? ሱና ላይ የሚገኙ ወንድሞቹን በነገር ይወጋ ነበር? ሶሀቦችስ ልጆቻቸውን በሀሳን ግጥም ያንፁ ነበር? በየትያትር ቤቱስ ያስመርቁ ነበር?
እነርሱ፦ ኡመቱ አንድ እንዳይሆን ለምን እንቅፋት ትሆናላቹ?
ጠያቂ፦ የረሱል ሱንና ከእናንተ ጋር ከለያየን አዎ አንድ አንሆንም።
By አብጀር አስሀማ ንጉስ አርማ
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
ጫት የዱኣ መሳሪያም የእስልምና አካል አይደለም፡፡
ያ ምርጡ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የመጡበት ውብ ሃይማኖት እስልምና በሰርጎ ገቦች ብዙ መጥፎ ነገሮችን የኢስላም አካል አስመስለው ሰግስገውበታል፡፡ የኢስላም ምርጥ ሊቃውንትም በየጊዜው እነዚህ ሰርጎ ገብ እምነቶች እና መጥፎ ተግባራት ከኢስላም አካል አለመሆናቸውን የተቃወመ ቢቃወማቸውም አብራርተው አስረድተዋል፡፡
ጫት እንደሚታወቀው ሙስሊሙን አሽመድምዶ ከጌታው ጋር ያለንም ይሁን ከፍጡራን ጋር ያለውን መብት አንድ ቃሚ እንዲያጓድል ሰበብ የሆነ አደገኛ መጥፎ ቅጠል ነው፡፡ አሳዛኙ እውቀት አላቸው ተብለው ሙስሊሙን ኡማ የሚቅመው በርትቶ እንዲቅም፣ የማይቅመው እንዲቅም ጫትን የኢስላም አካል እና የዱኣ መሳሪያ አድርገው የሚሰብኩ ሆድ አደሩዎች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ በመንዙማቸው፣ ሌላኛዎቹ ባገኙት መድረክ ላይ ጫትን እንደጥሩ ነገር ለሙስሊሙ ያስተዋውቃሉ፡፡ ሙስሊሞች ሊረዱ የሚገባቸው ጫት በጣም አደገኛ ነው፡፡ ይህም በተግባር የምናየው የት ይደርሳሉ የተባሉ ትዳሮች ሲበተኑ፣ የት ይደርሳሉ የተባሉ ወንድም እና እህቶች ተበለሻሽታ ማየታችን ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው፡፡
በመንዙማዎች ላይ ስለ ጫት ከተሰበኩ አደገኛ ስንኞች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
- “ጁሉሱ ሰኣቲን ጥቂት ቃቅምና (ጫት ቃምና ትንሽ ተቀመጥ)
ንገረው ለመውላህ እበሩ ቁምና”
- “እነሱ ይበራሉ በመቶ ሃምሳ ጀት፣ እኛ ቀደም ናቸው በአንድ ዘርባ ጫት”
- “ፍየል ቅጠል በልታ ትወልዳለች መንታ፣
መቼም እርባን የለው በጫት የተመታ”
- “ዝናቡ ዘነበ ጫቱ ለመለመ፣ የሚቅመው ቢያገኝ እያጉረመረመ”
- ከ አስር ሺህ መትረየስ አጥምዶ ከቆመ፣
ከሺህ ፈረሰኛ ተባብሮ ለቆመ፣
ይበልጣል ደግበል አጥብቆ የቃመ፣
ጠላቱንም ጎድቶ ወዳጁን ጠቀመ፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አላህ በዚህ ሱስ የተያዙትን በጠቅላላ እንዲያወጣቸው ዱኣ እና ምክር አይለያቸው፡፡ ጫት የምትቅሙ ወንድም እና እህቶች ሆይ! አላህ የውመል ቂያማ ጊዜያችንን በምን እንዳሳለፍነው ይጠይቀናል፡፡ ከዚህ ጊዜን እና ስብእናን ከሚገድል እርኩስ ቅጠል አላህን ለምናችሁ ለእሱ ስትሉ አቁሙ፡፡
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
April the fool?
ማንቂያ ደውል! እስከመቼ ዲንን መቃረን?
የነብዩን (ﷺ) ቃል ከነፍሶት፣ ከጓደኞቾት እና ከማንም በላይ ያስበልጣሉ ወይንስ አያስበልጡም?
ነብዩ (ﷺ) “ለቀልድም ብሎ መዋሸት አይቻልም” ይሉናል፡፡
ዛሬ ዛሬ ፈረንጅ የሰራውን ሁሉ መስራት የሚፈልግ አለ፡፡ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ሰውን ለማስደንገጥ፣ ያልሞተውን ሞተ፣ ያልተገጨውን ተገጨ፣ ያልደረሰውን ደረሰ ብሎ ሰዎችን ማስደንገጥ የኢስላም አካል አይደለም፡፡ ኢስላም አይደለም ለማስደንገጥ ለቀልድ መዋሸትን ከልክሏል፡፡ እባካችሁ እጅ እንስጥ ሙሉ ለሙሉ ከእዚህ እርኩስ ኩረጃ እንራቅ፡፡ ኢስላም ሙሉ ነው፡፡ ከፈረንጅ መኮረጅ አይፈልግም፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብዩ ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሀቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡