Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
በድሩ ሁሴን ሆይ! የአላህ ፍቅር እንኳን በምን እንደሚገለፅ አታውቅምን?
ሰሃባዎች ኡሁድ ዘመቻ ላይ እንደ መውሊድ አይነቱን የሺርክ መነሃሪያ ቢድዓ ሰርተው አይደለም የተሸነፉት፡፡
****************************************
በድሩ ሁሴን አላህ እኛንም እሱንም ይምራን እና አወልያ ላይ “መውሊድ አይለያየንም” እያለ በተናገረበት መፈክር ላይ ሌላን የተሳሳተ ንግግር እንዲህ ሲል ተናግሯል
“የነብዩ (አለይሂ ወሰላቱ ወሰላም) ፍቅር አንድ ያደርገናል፡፡”
በድሩ ሁሴን እና ተከታዬቹ ሆይ! አይደለም ፍጡሩን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ፈጣሪ አላህን እንኳን እወዳለሁ ያለ ሰው ፍቅሩ እውነተኛ ለመሆኑ የሚረጋገጠው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) በመከተል ነው፡፡
እስቲ የአላህን ቃል አብረን እናንብብ
قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ ٱللَّهَ فَٱتَّبِعُونِى يُحْبِبْكُمُ ٱللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
በላቸው፡- «አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡»
ይሀው ከጌታችን አላህ በላይ በተለያየንበት ጉዳይ ማን ፍርድ ይስጥ?
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያላዘዙበትን ተግባር የሚሰሩትን ሰዎች “አንድ ነን”፣ “እዚህ ውስጥ መውሊድ የሚያከብር የማያከብር አለ” ብሎ በድሩ ሁሴን የማይደበለቀውን ሁሉ ደበላለቀው፡፡
ሰሃባዎች ኡሁድ ዘመቻ ላይ እንደ መውሊድ አይነቱን የሺርክ መነሃሪያ ቢድዓ ሰርተው አይደለም የተሸነፉት፡፡ ከተራራ ላይ እንዳትወርዱ ተብለው “የጦር ምርኮ እየተከፋፈለ ነው” ብለው ጦርነት ያለቀ መስሎዋቸው ስለወረዱ ነው፡፡
ታድያ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ (ውድቅ) ነው፡፡” ብለው ሲያበቁ እሳቸው ያላዘዙበትን መውሊድ በድሩ ሁሴን እንዴት ይሆን “የነብዩ (አለይሂ ወሰላቱ ወሰላም) ፍቅር አንድ ያደርገናል፡፡” የሚለው?
ሐቁ ስንት ነው? አንድ ብቻ አይደለምን? ነው እንጂ፡፡ ታድያ ለምን ይሆን በብቸኛው ሐቅ በሱና ላይ አንድ እንሁን ማለት ሲገባቸው የቢድኣውን ቁንጮ፣ የሺርኩን መናሀሪያ መውሊድ “መውሊድ አይለያየንም” የሚሉት?
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ሰዎች በሃቅ ይለካሉ እንጂ፣ ሀቅ በሰዎች አትለካም፡፡
በድሩም ይሁን ማን ከቁርኣን እና ሀዲስ ሲጋጩ መልስ ይሰጥባቸዋል፡፡ ኢማሙ ማሊክ (ረሂመሁላህ) መዲና የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መስጂድ ውስጥ እያስተማሩ ሳለ እንዲህ አሉ “ሁላችንም ከንግግሩ የሚያዝለትና የሚመለስበት አለ፡፡ የዚህ ቀብር ባለቤት ሲቀር” ብለው የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ቀብር ጠቆሙ፡፡
የበድሩ ንግግር በሐቅ ጋር ስለተጋጨ አንቀበለውም፡፡
አላህ ሆይ! ሐቅን በሐቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፡፡ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
“መውሊድ”፣ “ክሪስማርስ”፣ አሹራ….?
***************************************
ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎቻቸው በላይ አውቀው ነው ወይ?
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ነብይ ተደርገው በተላኩ ጊዜ ነሷራዎችም (ክርስትያኖች) ይሁዳዎችም ነበሩ፡፡ ነሷራዎች የኢሳንም ልደት ሲያከብሩ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የወንድማቸውን ኢሳ ልደት አንድም ቀን አክብረው አያውቁም፡፡ ምክንያቱም በአላህ አልታዘዙምና፡፡ የነብይም ይሁን የሌላ ግለሰብ የልደት በዓል ማክበር የነብያቶች እምነት እስልምና በፍፁም የሚያውቀው አይደለም፡፡ ልደት ማክበር የእስልምና አካልም አይደለም፡፡በሌላ በኩል ሌላኛው ወንድማቸው ነብየላህ ሙሳን (አለይሂ ሰላም) አስመልክቶ የሁዳዎች አሹራን ሲፆሙ አዩ፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሁዳዎችን ለምን እንደሚፆሙ ጠየቁ “አላህ ሙሳን እና የእስራኢል ልጆችን ከፊርዐውን ነፃ ያወጣበት ቀን ነው” ሲሉ መለሱላቸው፡፡ ነብዩም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “እኛ በሙሳ ጉዳይ ከናንተ የበለጠ የተገባን ነን” ብለው አሹራን ፆሙ እንዲፆምም አዘዙ፡፡ እንዲያውም ረመዳን ከመደንገጉ በፊት አሹራ በሙስሊሞች ላይ ግዴታ ነበር፡፡ ከረመዳን በኋላ ይሀው እኛም የሳቸውን ፈለግ በመከተል እንፆመዋለን፡፡ ልክ እንደዚሁ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ሰኞ ለምን እንደሚፆሙ” ሲጠየቁ “የተወለድኩበት ቀን ስለሆነ እና ቁርዐን እኔ ላይ የወረደበት ቀን ስለሆነ ነው” ብለዋል፡፡ ታድያ ግዴታ ያልሆነ የሱና ፆም አሹራን በአመት አንዴ እንድንፆመው፣ እሳቸው የተወለዱበትን ቀን እና ቁርዓን የወረደበትን ቀን ሰኞ እንዲሁ በሳምንትን አንዴ ሱና ፆም እንድንፆም ነግረውናል፡፡ የሚያሳዝነው አብዛኛው “መውሊድን” አከብራለሁ የሚል ሰው የታዘዘውን በየሳምንቱ የሚፆመውን ሱና ሲፆም አይታይም፡፡ ይልቁንስ ለምሳሌ “የኢስነይን ሰዎች ነን” እያሉ ሰኞ ሰኞ ጉንጫቸውን በአንደንዛዡ ቅጠል ጫት ወጥረው ሲቅሙ እና ሲጨፍሩ የሚውሉ ሸይጧን የተጫወተባቸው አሉ፡፡ በአመት አንዴ ግን ያልታዘዙትን “መውሊድ” ብለው በማክበር “የኢሳ ልደት” ብለው ከሚያከብሩት ሰዎች ጋር ተመሳስለዋል፡፡ የታዘዙትን ትተው ያልታዘዙትን በመስራት ወደ አላህ እዝነት ሳይሆን ቁጣውን ወደሚያከናንባቸው የሰይጣን መንገድ የሚንደረደሩ ሰዎች ምን አለ ቆም ብለው ቢያስቡ?
አላህ እኮ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) በመከተል እንጂ ውዴታውን እና ምህረቱን ቃል የገባልን ያላዘዙትን በመስራት አይደለም፡፡ ሸይጧን ደግሞ እንዲህ አሳቢ መስሎ ነው ከጥንት እስከዛሬ ሰዎችን ሲያጠም የነበረው፡፡ አላህ ከተንኮሉ ይጠብቀን፡፡
ሌላው ሰሃባዎች አላህ አማኝ፣ እውነተኞች፣ ወድጃቸዋለሁ እያለ ያወደሳቸው….. ከነሱ መንገድ ውጭ ያለን የሚከተል መንገድ የሳተ፣ ጀሀነምም እንደሚገባ አላህ እና መልክተኛው ነግረውን ሲያበቁ፡፡ ለምን ይሆን መውሊድንም ይሁን ሌሎች ተግባራትን በተመለከተ ሰሃባዎች የቆሙበት ቦታ የማንቆመው?
ሰሃባዎች ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በህይወት በነበሩ ግዜም ይሁን ሞተው አንድም ቀን የማንንም ነብይ ይሁን የረሱልን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ልደት አክብረው አያውቁም፡፡
ታድያ እኛ ማን ሆነን ነው ሰሃባዎች ያልሰሩትን የምንሰራው? የአላህን ዲን፣ ንፁሁን የነብዩ ሱና በቢድዐ ለማቆሸሽ፣ የሰይጣንን ተልኮ “ነብዩን መውደድ” በሚል ስም ለማሳካት ደፋ ቀና የሚባለው?
እውነት ሰሃባዎች ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሳይወዱ ቀርተው ነው የነብዩን መውሊድ ያላከበሩት?
ወይንስ እነሱ ለነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያላቸው ውዴታ ሸሪዐ በደነገገው መልኩ በገንዘብ፣ በህይወት መስዋትነት እና በሌላም ስለገለፁ ነው?
እውነታው እነሱ ስለስርዐት አላቸው፡፡ ይህንን ከሰማይ የወረደ ዲን “እኔ እንደሚመስለኝ” እያሉ ሳይዳፈሩ ያንን ንፁህ ምንም ጭማሪ የማይፈልግ ዲን ለእኛ በሰላም አድርሰዋል፡፡ አላህም ወዷቸዋል፡፡ ዛሬ አላህ ዘንድ ገና ፍርድ ያልተሰጠባቸው ሰዎች ይህን ዲን መጥተው በፈለጉ ጊዜ በቀያየሩት ቁጥር እኛ አብረን የምንቀያየረው አላህን ነው የምናመልከው ወይንስ እነዚህ አላህ ያልደነገገውን የሚደነግጉ ዲን አፍራሾች?
መውሊድ የሸሮች ሁሉ መጠራቀሚያ፣ የሙስሊሞችን አንድነት ማፍረሻ፣ የድሆችብ ንብረት መብያ….. እርኩስ ተግባር ነው፡፡ ሙስሊሞች ሆይ! ራቁት፡፡
አይ ሸይጧን በየዘመኑ መጥፎውን ነገር ጥሩ አስመስሎ ስም እየቀያየረ የአደም ልጆችን ያጠማቸዋል፡፡ ወደ እሳትም ይመራቸዋል፡፡ ተመልከቱ አደም እና ሀዋን ያቺን ዛፍ ስሟን አሳምሮ እንዳትበሉ የተባሉትን አስበላቸው ከዛም ስህተት ውስጥ ጣላቸው፡፡ የኑሕን (አለይሂ ሰላም) ህዝቦች በሞቱት 5 ደጋግ ሰዎች ያዘነ መስሎ መቀማመጫቸው ላይ ሀውልት አሰርቶ ገደል ከተታቸው፡፡ የጠፉበትን እርኩስ ተግባር ሽርክ ውስጥ ዘፈቃቸው፡፡ አሁንም ይህን ኡመት “ለነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያላችሁን ውዴት ልደቱን አክብሩለት” የሚመስል የሰይጣን ሹክታ እዚህ ኡማ ላይ ተሰራጭቶ የሽርክ መነሃርያ የሆነውን መውሊድ እያከበሩ ወደ እሳት ሲነዱ ይታያሉ፡፡ መውሊድ ላይ ከባባድ የሽርክ ቃላትን ከእስልምና አስፈንጥረው የሚያስወጡ የሽርክ ተግባራት ይታያሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ አላህን ትቶ ፍጡራንን መለመን፣ እነሱን ድረሱልን ብሎ መጣራት፣ አላህን ትቶ ለፍጡራን ስለት መግባት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
አሳዛኙ ደግሞ ጥመቱን እንደሃቅ፣ ሃቁን እንደ ጥመት ቆጥረው “ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፣ ሰሀባዎቻቸው፣ ታቢኢኖች፣ አትባኡታቢኢን፣ 4 አኢማዎች፣ ሙሐዲሶች፣ 3 ምርጥ ክፍለ ዘመን እና ትውልድ አላከበረውም” ሲባሉ ሃቁን ከመቀበል ይልቅ ያልታዘዝነውን አንሰራም ያሉትን “ነብዩን የማይወዱ፣ የነብዩ ጠላቶች፣ ወሃብዬች እና ሌላም” ሲሉ ይደመጣሉ፡፡
ከድጡ ወደ ማጡ ይሉሃል ይህ ነው፡፡ ሸይጧን ግን ዛሬ ጥፋታቸውን እያሸበረቀላቸው ዲንን በዲን ስም እንዲንዱ እየገፋፋቸው ነው፡፡
ነሷራችን በነብየላህ ኢሳ (አለይሂ ወሰለም) ላይ ድንበር አልፈው “የአላህ ልጅ ነው” እንዲሉ ያደረጋቸው የሰው እና የጂን ሰይጣናት ናቸው፡፡ ነሷራች ኢሳን ድንበር ያለፉበት ጠልተውት ሳይሆን ወደውት ነው፡፡ ግን ድንበር አለፉ፡፡ ከልክ በላይ ከፍ ከፍ አደረጉት፣ ያላታዘዙትን ልደቱን አከበሩለት፡፡ ከዚህም ኡማ ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በመውደድ ስም ሸይጧን መንገድ አስቷቸው ልክ እንደነሷራች ያልታዘዙትን ልደት ማክበር፣ ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “መጣ ያለፈው ወንጀላችንን ማረ”፣ “የሁሉ ቀላቢ”፣ “ልቤ ባንቱ በእርሶ ተመካ” እና የመሳሰሉትን የብቸኛ ፈጣሪና ተመላኪ አላህ መብት አሳልፈው ለነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በመስጠት ታላቁን ማጋራት እና ቢድዐ ሲሰሩ ይታያል፡፡
ሸይጧን መቼም ለሰው ልጎች ከባድ ጠላታቸው ነው፡፡ አላህ ድንበር ከማለፍ፣ ከሽርክ፣ ከቢድዐ እና አላህ ከጠላው ሁሉ ይጠብቀን፡፡ አላህ ወደ ተውሒድ፣ ሱና፣ የሰለፉነ ሷሊሂን አረዳድ፣ እሱ መልካም ወዳለው ሁሉ ይምራን፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሃቅ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
መውሊድ ላይ የሚባሉ የሺርክ፣ ቢድኣና ኹራፋት ስንኞች፡፡ ከሚከተሉት ሊንኮች አውርዳችሁ አንብቡና እውነታው እናንተው ፍረዱ፡፡ 97 አደገኛ ስንኞች
https://goo.gl/x2eDmD
https://goo.gl/4CWQ6a
https://t.me/Menzuma
መውሊድ ብለው የሚያከብሩት የሞቱበትን ወይንስ የተወለዱበትን?
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን፡፡ አዛኙ ነብይ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ቢድኣ (በዲን ላይ ያለ) ፈጠራ ሁሉ ጥመት ነው” ብለው ሲያበቃ፣ ያልታዘዙትን የሚሰሩት የቢድዓ ሰዎች መውሊድ (ነብዩ የተወለዱበትን ቀን) እናከብራለን ብለው ሞገቱ፡፡
ሰይጣን ለሰው ልጆች አደገኛ ጠላታቸው ነው፡፡ ጠላትነቱን በጣም የከፋ የሚያደርገው ደግሞ የሰው ልጆችን አላህ እና መልክተኛው የከለከላከሏቸውን ተግባር ሲያሰራቸው ለነሱ አዛኝ መስሎ ነው፡፡
ጥያቄው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተወለዱበት ቀን ኺላፍ (ውዝግብ) እንዳለበት ይታወቃል፡፡ የሞቱበት ግን ያለ ምንም ውዝግብ ረቢአል አወል 12 መሆኑ ይታወቃል፡፡
ታድያ መውሊድን እናከብራለን የሚሉ ሰዎች የሺርክ ስንኞችን እያቀነቀኑ፣ እየጨፈሩ የሚያሳልፉት በተወለዱበት ወይንስ በሞቱበት ቀን?
ይሉ ይሆናል “የተወለዱበት ቀን ውዝግብ ቢኖረውም፣ የሞቱበት ቀን ረቢዓል አወል 12 መሆኑን ብናውቅም አላህ ንያችንን ይመለከታል፡፡ እኛ ልናከብር የፈለግነው የተወለዱበትን ቀን ነው፡፡” ነገር ግን ንያ ብቻውን ስራ ተቀባይነት እንዲኖረው መስፈርት አይሆንም፡፡ ከንያ በመቀጠል መሟላት ያለበት መስፈርት አለ፡፡ እሱም የሚሰራው ስራ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያዘዙበት፣ የሰሩት፣ ወይንም ሰሃባዎቻቸው ሲሰሩ አይተው ዝም ያሉት መሆን አለበት፡፡ ለዚህም ማስረጃው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “የእኛ ትዕዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ (ውድቅ) ነው” ብለዋል፡፡
እሳቸው የተወለዱበትን ቀን አመት ጠብቆ ማክበር እሳቸው አላዘዙበትም፡፡ ሸይጧን እዚህ ድረስ እሱን የሚከተሉትን ሰዎች አግኝቷል፡፡ እንወዳቸዋለን የሚሉትን ነብይ የሞቱበትን ቀን የደስታ ቀን አድርገው የሚይዙ፡፡ ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን፡፡
አላህ ሆይ! ሐቅን በሐቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፡፡ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
https://www.facebook.com/sadat.kemal
https://www.youtube.com/user/TewhideFirst
👆🏻 37 ጥያቄና መልስ ለልጆች
👆🏻ማን የማን ቅጥረኛ ነው?
ኢኽዋኖች ከኢሀዲግ እስከ ግንቦት 7?
አቡበክር አሕመድ፣ ሀሰን ታጁ …..
የኢትዮጵያ ሙስሊም ሐቁን ለመገንዘብ ማዳመጥ ያለበት እውነታ፡፡
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
አልሐምዱሊላህ ወንድሜ ኢብኑ ሙነወር በአላህ ፈቃድ እና ምህረት ከደረሰበት አደጋጋ በማገገም ላይ ነው፡፡ በአላህ ፍቃድ ወደ አዲስ አበባ መኖሪያ ቤቱ በቀጣይ ቀናቶች ውስጥ ይመለሳል፡፡ አላህ ሆይ! በሁለት አገር አፊያ አድርገን፡፡ ወንድሜን ከከባድ አደጋ ስላተረፍከውም አመሰግንሃለሁ፡፡ ብቸኛው ተለማኝ ህያው ጌታችን ሆይ! መቼም ማናችንም ከሞት አናመልጥምና፣ ስንኖርም ስንሞትም በተውሒድ መንገድ ላይ አኑረህ ግደለን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
አልሐምዱሊላህ አላህ ወንድማችን ኢብኑ ሙነወርን ከልጆቹ ጋር በሰላም አገናኝቶታል፣ ለቤቱም አብቅቶታል፡፡ የሱን ደህንነት ካላችሁበት ሆናችሁ ስትጠይቁና ዱዓ ላደረጋችሁለት ወንድም እና እህቶች በጠቅላላ አላህ አትርፎት ለቤቱ በመብቃቱ አላህ ምንዳችሁን እጥፍ ድርብ አድርጎ ይክፈላችሁ፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
የሐበሻ ሙስሊሞች ሆይ! ማንም ከማንም ዘር አይበልጥም፡፡
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
የሐበሻ ሙስሊሞች ሆይ! አላህን እንፍራ ጥምቡን ዘረኝነት ከላያችን ላይ ጨርሰን አራግፈን እንጣል፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሰሃባዎቻቸው ላይ ከባድ በደል፣ ስቃይ እና እንግልት ሲደርስባቸው “ሂዱ ወደ ሀበሻ” ነበር ያሉት፡፡ እኛ ሙስሊሞች ነን፡፡ የሀበሻ ሙስሊሞች የሚለው ከበቂ በላይ መታወቂያችን ነው፡፡ ዘራችንን ከኢስላም አስቀድመን እርስ በርስ እየተናናቅን መከፋፈሉ ለከባድ አደጋ ነው የሚዳርገን፡፡
አንድ ሰው በእስልምናው እንጂ በዘሩ ጀነት አይገባም፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ስራው ወደ ኋላ ያስቀረውን ሰው ዘሩ (ወደፊት) አያስቀድመውም” ብለዋል፡፡
አንድ ሰው ጀነት ለመግባት ብቸኛው መንገዱ
- ተውሒድን አሳምሮ መያዙ ከሺርክ እና ከባለቤቶቹ ሙሉ ለሙሉ መፅዳቱ፣
- የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን ሱና አጥብቆ መያዙ ቢድኣ የተባለን በጠቅላላ መራቁ፣
- የሰሃባዎችን አረዳድ መከተሉ የጥመት መንገዶችን ሁሉ መራቁ፣
- የአላህንና የመልክተኛውን ትእዛዝ መፈፀሙ እነሱንም አለማመፁ ……
- …..
እንጂ ዘሩ አይደለም፡፡
ዘር ለመተዋወቅ ብቻ እንጅ ለሌላ አይደለም፡፡ እውነቱን ለፈለጉ ሰዎች አላህ እንዲህ ይላል
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَٰكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَٰكُمْ شُعُوبًا وَقَبَآئِلَ لِتَعَارَفُوٓا۟ ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ ٱللَّهِ أَتْقَىٰكُمْ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ
እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡
አላህ በግልፅ እውነታውን ነግሮናል፡፡
ዘረኞች፣ ዘራቸውን ከኢስላም የሚያስቀድሙ ጥምብ አንሳዎች ናቸው፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ዘረኝነት ጥምብ ናት፡፡ ተዋት፡፡” እያሉን የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ትእዛዝ ትተው እሳቸው የከለከሉትን የሚያነሱ ጥምብ አንሳዎች ናቸው፡፡
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “….ተዋት” ብለው ጥንቡን ዘረኝነት እንድንተው ሲነግሩን አይ አልተውም ብሎ ከእስልምና ዘሩን አስቀድሞ ሙስሊም የሆነ ከእሱ ዘር ያልሆነው ላይ አደጋ ሊያደርስ፣ ንብረቱን ሊቀማ የሚያስብ ሰው ምንኛ ከሰረ፡፡
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ሁለት ሙስሊሞች ሰይፍ አይማዘዙም ገዳይም ተገዳይም የእሳት ናቸው” ሲሉ
ሰሃባዎች “ገዳይስ ገድሎ ነው” ተገዳይስ ሲሉ ጠየቁ
የአላህ መልክተኛም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “እሱም ንያ ነበረው” ሲሉ እነዚህ ሰዎች የሚሰሩትን ስራ የእሳት መንገድ እንደሆነ ገለፁ፡፡
ኢስላም ለሁሉም ነገር ዝርዝር የሆነ መተዳደሪያ ያለው፣ ለሁሉም ዘመን፣ ለሁሉም ቦታ፣ ለሁሉም ትውልድ ሙሉና ከበቂ በላይ የሆነ አላህ የሚቀበለው ብቸኛ ሃይማኖት ነው፡፡
ውቡ ኢስላም እርስ በእርስ መጋደላችንን. መበዳደላችንን አጥብቆ ኮንኖታል፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “አንድ ሙስሊም ለአንድ ሙስሊም ወንድሙ ነው፡፡ አይበድለው….” ብለዋል፡፡ ታድያ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “አይበድለው” እያሉ ዘሩ ስላልሆነ ብቻ ሌሎች ሙስሊሞችን ሊገድል የተነሳው ምን ሊባል ነው?
አላህ ይድረስልን፡፡ ከዚህ ቆሻሻ ተግባርም ይጠብቀን፡፡
የሀበሻ ሙስሊሞች ሆይ! ሙስሊም የሆነ ሰው እኛ ዘንድ እንደራሳችን አድርገን ልንወደው ይገባል፡፡ ሙስሊም ደሙም፣ ገንዘቡም፣ ክብሩም የተጠበቀ ነው፡፡ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡
የሀበሻ ሙስሊሞች ሆይ! አላህን እንፍራ ዘረኝነትን ከላያችን ላይ እናራግፍ፡፡ ማንም ማንንም በዘሩ አይበልጥም፡፡ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘሮች የሆኑት አረቦች እንኳን አላህን በመፍራት ቢሆን እንጂ አጀሞችን (ከአረብ ውጭ) ያሉትን አይበልጡም፡፡ ለዚህም የሰው ልጆች ሁሉ ፈርጥ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “አረብ በአጀም (ከአረብ ውጭ ባሉ ሰዎች) ላይ ብልጫ የለውም” ብለዋል፡፡
አላህ እንደነገረን
إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ ٱللَّهِ أَتْقَىٰكُمْ
አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ዘረኝነት ከሺርክና ቢድኣ ቀጥሎ ነቀርሳ ሆኖ እየወጋን ይገኛል፡፡ ይህን መልእክት በየቋንቋችሁ እየተረጎማችሁ ለሁሉም በማድረስ ተባበሩኝ፡፡
አላህ ሆይ! ዘረኝነትን ከመካከላችን አስወግድልም፡፡ ኢስላምን ከዘራቸው የሚያስቀድሙ ምርጥ ትውልዶች አድርገን፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም ዘረኝነትን አጥፍተው እርስ በእርስ ሲጋደሉ የነበሩትን ሰሃባዎች በሱና አንድ ባደረጉት የአላህ ውድ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
በኢስላም ሸይኽም ይሁን ነብይ ሞተ ተብሎ የሙት አመት አይከበርለትም፡፡ ማንም ይስራው ማን፣ ለማንም ይሰራ ለማን
“የሙት አመት”
የሚባል ነገር የለም፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
የኢስላም አስተማሪዎች፣ የመስጂድ ኸጢቦች፣ ሽማግሌዎች ሃላፍትናችሁን ተወጡ፡፡
“የኛሰው”፣ “ነመኬኛ”፣ “የባድ ወልድ” …. ብለን የምንጠራው ማንን ነው?
አንድን ሰው የእኛ ዘርም ባይሆን ሙስሊም እስከሆነ ድረስ አማራው “የኛሰው”፣ ኦሮሞው “ነመኬኛ”፣ ስልጤው “የባድ ወልድ” …… ብለን መጥራት እስካልቻልን ድረስ አደጋ ውስጥ ነን፡፡
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ሙስሊም የሙስሊም ወንድሙ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ ዛሬ ሰይጣን እና ሰራዊቶቹ ባጠመዱላቸው ወጥመድ ውስጥ ገብተው ለዘራቸው ሲሉ ላኢላሃኢለላህ ብለው ሲያበቁ እርስ በእርስ የሚጋደሉ፣ በመጥፎ የሚፈላለጉ፣ ሰው ሲሞት ሁሉ የእድር እቃ አንሰጥም የሚሉ አውሬዎች አሉ፡፡ አላህ ሁላችንንም ልብ ይስጠን፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ሁለት ሙስሊሞች ሰይፍ አይማዘዙም ሁለትሙ የእሳት ናቸው” ብለው ነግረውን ሲያበቁ፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ይህን ጥንብ ዘረኝነት “ተዉቱ” እያሉ፣ እሳቸው የከለከሉት ዘረኝነት አንተውም ብለው ታላቋን የምስክረት ቃል “ከአላህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፡፡ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን እንዲሁ እመሰክራለሁ” ያሉ ሰዎች እርስ በእርስ ሲጋደሉ እንደማየት አስለቃሽና ልብ የሚያደማ ነገር የለም፡፡
ከማንም በላይ ሃላፍትና ያለባቸው የሃይማኖቱ አስተማሪዎች፣ ኢማሞች፣ ዱአቶች፣ ሽማግሌዎች፣ ኢስላማዊ ቻናሎችና ሬድዬኖች ናቸው፡፡ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ኡመተል ኢስላም እርስ በእርስ እንዲህ እየተገዳደለ አላህ ካዘነላቸው በጣም ጥቂቶች ውጭ አብዛኛዎቹ አዋቂ ተብየዎች ዝምታን መርጠዋል፡፡ አላህን ብትፈሩ አይሻልም ወይ? አላህ አያያዙ የበረታ ነው፡፡ ኡለማዎች ሐቅን ማብራራትና አለመደበቅ ነው ያለባቸው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
وَإِذْ أَخَذَ ٱللَّهُ مِيثَٰقَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ لَتُبَيِّنُنَّهُۥ لِلنَّاسِ وَلَا تَكْتُمُونَهُۥ فَنَبَذُوهُ وَرَآءَ ظُهُورِهِمْ وَٱشْتَرَوْا۟ بِهِۦ ثَمَنًا قَلِيلًا ۖ فَبِئْسَ مَا يَشْتَرُونَ
አላህ የነዚያን መጽሐፉን የተሰጡትን ቃል ኪዳን ለሰዎች በእርግጥ ታብራሩታላችሁ አትደብቁትምም በማለት የያዘባቸውን (አስታውሱ)፡፡ በጀርባዎቻቸውም ኋላ ጣሉት፡፡ በርሱም ጥቂትን ዋጋ ገዙ፡፡ የሚገዙትም ነገር ከፋ!
ኡመቱ እርስ በእርስ ሲባላ እያዩ ተው አለማለት ምን የሚሉት ነው?
ዘረኝነት ውስጥ ገብታችሁ የተነሱ እሳቶች ላይ ቢንዚል የምታርከፈክፉ ሰዎች የጥፋታችሁን ልክ ላትገነዘቡት ትችላላችሁ፡፡ ግን ልብ በሉ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “አንድ አማኝ ያለ አግባብ ከሚሞት ካእባ ቢወገድ ይሻላል” ሁሉ ብለዋል፡፡ መቼ ይሆን የምንመከረው? አላህና መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል እየተባልን ልባችን ከድንጋይ በላይ ደርቆ የነሱን ቃል አልቀበልም ብለን ስሜታችንን ጋልበን መጨረሻን ምን ይሆናል ብለን እንገምታለን?
አረ አላህን እንፍራ፡፡ ከባድ የሆነ አዘቅት ውስጥ እንዳንገባ፡፡ ተወደደም ተጠላም ማንኛውም አይነት ችግር ይበልጥ ጎጂነቱ ለሙስሊሙ ነው፡፡ አእምሮ ያለው ልብ ይበል፡፡
አላህ ሆይ! ከሺርክ፣ ቢድኣ፣ ዘረኝነት የፀዳ እውነተኛ አንድነት ስጠን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ስለ ሰሞኑን ከባድ ብርድ እስልምና ምን ይላል፡፡
የአላህ ባርያዎች ሆይ! አሁንም አረፈደም ንሰሃ እንግባ
ኢስላም የነብያት ሁሉ ሀይማኖት ነው፡፡ እንደሚታወቀው በሀይለኛ ሙቀት እና በሀይለኛ ብርድ ሰው ተቸግሯል፡፡ ይህም ከመሆኑ ጋር ለአላህ ካጠፋነው ጥፋቶች ንሰሀ ከመግባት ይልቅ በየዜና አውታሩ “የአለም በረዶ ስለቀለጠ ነው፣ ዛፎች በመቆረጣቸው ነው፣ ኦዞን በመሳሳቱ ነው…..” እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች ናቸው እየተባለ ይለፈፋል፡፡
እስቲ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ምን እንደሚሉ እንይ
አቡ ሁረይራ (ረድየላሁ አንሁ) ባስተላለፉት፣ ኡማሙ አል-ቡኻሪ በዘገቡት ትክክለኛ ሀዲስ ላይ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ
“ጀሀነም (እሳት) ወደ ጌታዋ ስሞታ አቀረበች፡፡ ከፊሌ ከፊሌን በላው አለች፡፡ አላህ ሁለት ጊዜ እስትንፋስን ፈቀደላት፡፡ አንደኛው በቀዝቃዜ ወራት ሌላኛው ጊዜ በሙቀት ወራት፡፡ በሙቀት ጊዜ የምታገኙት ከባድ ሙቀት እና በቅዝቃዜ ጊዜ የምታገኙት ከባድ ውርጭ (ቅዝቃዜ፣ ቀቅ) (ናቸው)፡፡”
حَدَّثَنَا أَبُو الْيَمَانِ، أَخْبَرَنَا شُعَيْبٌ، عَنِ الزُّهْرِيِّ، قَالَ حَدَّثَنِي أَبُو سَلَمَةَ بْنُ عَبْدِ الرَّحْمَنِ، أَنَّهُ سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ اشْتَكَتِ النَّارُ إِلَى رَبِّهَا، فَقَالَتْ رَبِّ أَكَلَ بَعْضِي بَعْضًا، فَأَذِنَ لَهَا بِنَفَسَيْنِ نَفَسٍ فِي الشِّتَاءِ وَنَفَسٍ فِي الصَّيْفِ، فَأَشَدُّ مَا تَجِدُونَ فِي الْحَرِّ، وَأَشَدُّ مَا تَجِدُونَ مِنَ الزَّمْهَرِيرِ ‏"‌‏.‏
ልብ እንበል ከባዱም ሙቀት እና ከባዱም ብርድ የአዋቂዎች ሁሉ አዋቂ፣ የአላህን ፈሪዎች ሁሉ ፈሪ፣ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ እንደነገሩን የጀሃነም እሳት የምትተነፍሰው ሁለት ትንፋሽ ምክንያት ነው፡፡
ሌላው መገንዘብ ያለብን ነገር እስልምና ሙሉ መሆኑን ለማንኛውም አለም ላይ ላለ ክስተት በል እንዲያውም ለሚቀጥለው አለም ጉዳዩች፣ የሚቀጥለው አለም ላይ ምን እንደሚከሰት በዝርዝር እና በጥቅል የተናገር ዉድ፣ ልዩ፣ የማይበረዝ፣ የማይሰረዝ፣ የማይደለዝ፣ ዘመን የማያልፍበት ሀይማኖት ነውና አጥብቀን እንያዘው፡፡ ይሀው ተመልከቱ አከም “Econmic Crisese” ኢኮኖሚክ ክራይስስ ብለው ሲያወሩ አላህ ጥንትም የወለድ መጨረሻው ይህ መሆኑን ነግሮን ነበር፡፡
ትዳር እንዲመሰረት እና ከዝሙት እንድንታቀብ ከጥንትም የነብያት ሁሉ ሀይማኖት መክሮ ነበር፡፡ ግን ይህን አልሰማ ብለው አሁን አለም ላለችበት ከባባድ በሽታዎች ተዳርገዋል፡፡
በሁሉም የህይወት ዘርፍ ላይ የጥንት የጠዋቱ ኢስላም (ሰለፍያ) በሄደበት መንገድ መሄድ ብቻና ብቻ ነው ዋስትናው፡፡ ሁለት ሃቅ የለም፡፡ ሁሉም ሙስሊም ከጥመት ቡድኖች እርቆ ወደ ብቸኛዋ አማራጭ እና ሁለተኛ ወደሌላት ሃቅ ጎዳና፣ ሰለፉነ ሷሊሂን የተጓዙባት ጎዳና መመለስ ግድ ይለዋል፡፡ አለበለዚያ በሙስሊሙ አለም ላይ እንዳየነው አሁንም ከባድ ኪሳራ ይከሰታል፡፡
ታድያ ምን ይበጀን?
አማኞች ወደ ጌታቸው በንሰሃ ሊመለሱ፣ ያችን “ጭማሪ አለን?” ብላ የምትጠይቀውን ጀሀነም ከሷ ጌታችን እንዲጠብቀን እሱን ዘውትር መለመን ግድ ይለናል፡፡ የአላህ ባርያዎች ሆይ! አሁንም አረፈደም ንሰሃ እንግባ፡፡ አላህ እነዚህን ሁሉ ተዓምራት የሚያሳየን በሰጠን አእምሮ የሱን ጌትነት፣ በቸኛ ተመላኪነት አውቀን ወደሱ እንድንመለስ ነው፡፡
አላህ ሆይ! ሁሌ ወዳንተ በጸጸት ከሚመለሱት አድርገን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
የት በደረሱ ነበር?
አላህ ካዘነላቸው ጥቂቶች ውጭ ስለ ግል ጉዳያቸው፣ ስለ ዘራቸው፣ ስለ መብታቸው ደም ስራቸው እስኪገተር ድረስ የሚቆጡ፣ የሚከራከሩ፣ የሚያብራሩ ሰዎችን ታያለህ፡፡ ነገር ግን ሺርክ (በአላህ ላይ ሲጋራ)፣ ቢድኣ (የነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና ላይ ሲጨመር ሲቀነስ) እያ ዝም ሲሉ ትመለከታቸዋለህ፡፡ ለራሳቸው የተቆጡትን ቁጣ ሺርክና ቢድኣን ሲያዩ ያንን ቁጣ አታይባቸውም፡፡ ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን፡፡ ከዚህ የበለጠ ዝቅጠት ምን አለ? የአላህ መብት ሲነካ ሌሎች ጉዳዬች ላይ እንደሚያንዘረዝረን ቢያንዘፈዝፈን፣ ቢዘገንነን፣ ብንቆጣ የት በደረስን ነበር?
አላህ ሆይ! ያንተን መብት ከሚያከብሩና ከሚያስከብሩ ትውልዶች አድርገን፡፡ ውስጥ እላያችንንም አሳምርልን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts