Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
መውሊድና ቢዝነስ?
በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ውዴታ ስም የንፁሀን ሙስሊሞችን ብር መበዝበዝ፡፡ ተመልከቱ አገራችን ላይ እነዚህ ሸህ ተብዬ እሾሆች መውሊድ እናክብር በሚል ስም ከሙስሊሙ ኪስ ላይ ገንዘብ በመሰብሰብ ለዋናዎቹ ሁለት ኢዶች የማያርዱትን ግመል ለዚህ አደገኛ ሺርክ የታጨቀበት ቢድኣ ያርዳሉ፡፡
አስገራሚው ለመውሊድ ተብሎ የሚወጣው ገንዘብ ከእነዚህ ሸህ ተብዬዎች ኪስ አይወጣme፡፡ ይልቁንስ ከምስኪኑ ህዝብ ነው፡፡ ሸህ ተብዬዎቹ ይበላሉ፣ ይጠጣሉ፣ ይቅማሉ፣ ይጨፍራሉ፣ ብሎም በዲን ስም የሰው ኪስ ያወልቃሉ፡፡ ይህን ተግባራቸውን “ጀባታ” ብለው ይጠሩታል፡፡ ከተራው ኪስ አውላቂ የባሱ ኪስ አውላቂዎች ናቸው፡፡
እነዛ አላህ የሚወዳቸው እነሱም የሚወዱት ሰሃባዎች አንድም ቀን መውሊድ አላከበሩም፡፡ እነዚህ ሸህ ተብዬዎች ከሰሃባዎች በላይ ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ወደው ነውን? በፍፁም፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! እራሳችንንም ቤተሰቦቻችንንም ከእንዲህ አይነት ኪስ አውላቂዎች፣ እምነት አበላሾች እንጠብቅ፡፡ ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መውደድ የሚገለፀው ሱናቸውን በመከተል ብቻና ብቻ ነው፡፡ መጨፈር፣ አደንዛዥ ቅጠል መብላት፣ ሴትና ወንድ ተቀላቅሎ መጨፈር በፍፁም ነብዩን የመውደድ መገለጫ አይሆንም፡፡ እንዲያውም እሳቸውን የማመፅ ተግባርና ክልከላቸውን መዳፈር ነው፡፡
አላህ በውቡ በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና በሰሃባዎች አረዳድ (ሰለፉነ ሷሊሂን መንሃጅ) ላይ አኑሮ፣ በዛው መንገድ ላይ ይግደለን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
በእስልምና የሰው ስም አንስቶ መናገር ይቻላል ወይ?
========================
ኢማመ ነወዊ (አላህ ይዘንላቸውና) የሚከተሉትን ስድስት ነጥቦች ‹‹ሪያዱ ሷሊሂን››
የተባለው ኪታባቸው ላይ ከቁርዐንና ከሀዲስ ጨምቀው እንዲህ በማለት አስቀምጠዋል፡፡
እወቅ ሀሜት ትክክለኛ ለሆነ አላማ ይቻላል፡፡ ከዚህ መንገድ ውጭ (ስም አንስቶ መናገር)
ሌላ አማራጭ ከሌለ፤ እሱም በስድስት ምክንያት ነው፡፡
1. የተበደለ ሰው፡- የተበደለ ሰው ለሚመለከተው አካል፤ ለዳኛ ወይንም ለባለስልጣን፤
ለመሪ ሰውየው በሌለበት እገሌ በድሎኛል ቢል አይከለከልም፡፡
2. መጥፎን ነገር ለማስቆም (ለማገድ)፡- ለምሳሌ አከሌ መጥፎ ስራ እየወራ ነው፤
መጠጥ እየጠጣ ነው፤ እያጭበረበረ ነው ብለህ ለማስቆም ወይንም ለመምከር አቅም
ላለው ሰው መናገር፡፡ ይህን ሲያደርግ ሰውየውን ለመመለስ ብቻ መሆን አለበት፡፡
3. ፈትዋ ለመጠየቅ፡- ለምሳሌ ለዳኛ አባቴ፤ ወንድሜ፤ ሚስቴ ወይንም እገሌ በድሎኛል፡፡
ለዚህ አካል ይሄ ይገባዋልን? ይበቃለታል ወይ? የሚሻለው ግን አባቴ፤ ወንድሜ ሳይሉ
አንድ ሰው ነበር እንዲህ አደረገ ብሎ መጠየቅ ይሻላል፡፡
4. ሙስሊሞችን ከሸር ለማስጠንቀቅና ለመምከር፡- ለምሳሌ የሀዲስ ዘጋቢዎችና
መስካሪዎችን ችግር ካለባቸው ችግር አለባቸው ማለት (ለምሳሌ የሚረሱ ከሆነ ይረሳሉ
ብሎ መናገር)፤ እንዲያውም ይህ ዋጂብ ግዴታ ነው፡፡
ሌላ ምሳሌ፡- እገሌን ልጄን ልድረው ነበር፤ እገሌን ንግዴ ላይ ሸሪካ ላደርገው ነበር
ምንትላለህ ተብሎ ከተጠየቀ፤ የተጠየቀው ሰው ሀቁን መናገር አለበት፡፡
ሌላው፡- አንድን ጡላበል ኢልም (የዲን ትምህርት የሚቀስም) ሙብተዲዕ (ቢድዐ
የሚያራምድ ሰው) ጋር ወይንም ፋሲቅ ዘንድ ዲን ሊማር ሲመላለስ ካየሀው የሰውየውን
ማንነት መግለፅ ያስፈልጋል፡፡ መስፈርቱም ምክርን አስቦ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ይህ
ሰዎች የሚሳሳቱበት በመሆኑ ነው፤ ምክንያቱም ተናጋሪውን ምቀኝነት ሊያነሳሳው ይችላል፡፡
ሸይጧን ምክር ነው ብሎ ሊያመሳስልበት ይችላል፤ መጠንቀቅ ይገባል፡፡
ሌላው፡- ሰውየው ሀላፍትና ቦታ ይቀመጥና ሀላፍትናውን የማይወጣ ከሆነ ወይ ሀላፍትና
ላይ የተቀመጠው ሰው ለቦታው ብቁ ካልሆነ ወይንም ፋሲቅ ከሆነ ለሚመለከተው አካል፤
አከሌ ተነስቶ አከሌ ቢቀመጥ ብሎ መናገር ይቻላል፡፡
5. ሰውየው ወንጀሉንና ቢድዐውን ግልፅ የሚያደርግ ከሆነ፡- በግልፅ እየሰሩ ያሉትን
በግልፅ ለማህበረሰቡ ስም አንስቶ መጥቀስ
6. ለማስተዋወቅ፡- አንድ ሰው በሚታወቅበት ቅፅል ስም ማንሳት ለምሳሌ ሶስት
ሙሀመዶች ቢኖኑ አንዱን ሙሀመድ የሚያነክሰው ተብሎ ቢጠራ፡፡ ልብ ሊባል የሚገባው
ለመለየት ብቻ እንጂ ለማነወር ከሆነ አይቻልም፡፡ https://t.me/SadatTextPosts
ከኢማሙ ሻፊኢ (ረሂመሁላህ) እና ከድምፃችን ይሰማ ማንን ይቀበላሉ?
……………
እውነትን መናገር ሐቅን ለራስ አውቆ ለሰዎች ማብራራት ግድ ነው፡፡ ከላይ እንዳያችሁት ድምፃችን ይሰማ ብሎ እራሱን የሚጠራው አካል የጥመት ተከታዬች ስለሆኑት ሱፍዬች እያወደሰ የፃፋን ንግግር ከታላቁ የኢስላም ሊቃውንት ኢማሙ ሻፊኢ (ረሂመሁላህ) ስለ ሱፍያ የተናገሩትን እውነታ ለውድድርነት እናይበታለን፡፡
ያለ ማስረጃ ምንም አይነት ኮሜንት እንዳትሰጡ፣ ረጋ ብላችሁ ማስረጃውን እንድታነቡ፣ ከኡለማና ማንነቱ ከማይታወቅ አካል ማናቸው ለሐቅ የቀረቡ እንደሆኑ ረጋ ብላችሁ እንድታዩና ሐቁን እንድትቀበሉ፣ ባጢሉን እንድትርቁ በአላህ ስም ትጠየቃላችሁ፡፡
ሙስሊሞችን ወደ ጥመት ከሚመሩት ቡድኖች ውስጥ ሱፍዬች ይገኙበታል፡፡ ኢማሙ ሻፊዒ (ረሂመሁላህ) ሱፍዬችን አስመልክተው እንደሚከተለው ብለዋል
“አንደ ሰው ንጋት ላይ ሱፊይነት ከጀመረ ለዝሁር ተጃጅሎ እንጂ አይመጣም” ተልቢሱል ኢብሊስ 371
ድምፃችን ይሰማ የሚባለው ማንነቱ የማይታወቀው፣ ሙስሊሞችን የሚያስጨርሰው ደግሞ ሱፍዬችን አስመልክቶ ከአህባሽ ጋር ለማወዳደር ነው በሚል እንዲህ ሲል ያወድሳቸዋል
“ሱፊያዎች ጭንቀታቸው ሙስሊሙ እንዴት አንድ ሆኖ ንጹህ ቀልብ ይዞ አላህ ፊት ይቀርባል” ይህ የድምፃችን ይሰማ ፅሁፍ የቅጥፈቶች ሁሉ ቅጥፈት ነው፡፡
ድምፃችን ይሰማ ቢዋሽም ለሱፍዬች ሽንጡን ገትሮ ጥብቅና ቢቆምም የሱፍዬች እውነታ እንደሚከተለው ነው
- ሱፍዬች ማለት በአገራችን ላይ ኡማውን ወደ ቀብር አምልኮ የተጣሩ ናቸው፣
- ከአህባሽ ጋር ከ90 ፐርሰንት በላይ የሚያመሳስላቸው እምነት እና ተግባር አለባቸው፣
- ዛሬ አህባሾች እየተባሉ የሚጠሩት እንደነ ጠሀ ሀሩን (የአንዋሩ አሰጋጅ) ትላንት የድምፃችን ይሰማ ተከታዬች ሱፊ መሆናቸውን የሚያምኑላቸው አጥፊዎች ወደ ሺርክና ቢድኣ በግልፅ የሚጣሩ ሰዎች ያሉበት ነው፣
- በቢድዓ የተጨማለቁ፣ ሙስሊሙን ኡማ መውሊድ እያሉ ቀብር ለቀብር ሙታንን እንዲያመልክ አለ የሚሉትን ጥሪ ተጠቅመው ኡማውን ያበላሹ ናቸው፣
- ሙስሊሙን ኡማ የበታተኑ እና እራሳቸውም ጠሪቃ እያሉ የተበታተኑ (ለምሳሌ ሻዚሊ፣ ቃዲሪ፣ ቲጃኒ…..)፣ (የአብሬት ሙሪድ፣ የቃጥባሬ ሙሪድ… እያሉ የተበታተኑ) ናቸው፣
- የንፁሀን ሙስሊሞችን እምነት የበረዙ፣ ሀብትና ንብረት የዘረፉና የሚዘርፉ ናቸው፣
- ኡማውን ጫት ቃሚ እንዲሆን፣ ደካማ፣ ዝርክርክ እንዲሆን አድርገዋል፤
- ኡማው በተረተረት እንዲያምን እና ከትክክለኛው ሸሪኣዊ እውቀት እንዲርቅ አድርገውታል፣
እና ሌሎችም መጥፎ ተግባራትን የቃፉ ናቸው፡፡
እንግዲህ እነዚህን ሱፍዬች ነው ድምፃችን ይሰማ “ሱፊያዎች ጭንቀታቸው ሙስሊሙ እንዴት አንድ ሆኖ ንጹህ ቀልብ ይዞ አላህ ፊት ይቀርባል” እንዲህ ሲል ያወደሳቸው፡፡ የውሸት ምስክርነት ትርፉ ኪሳራ ነው፡፡ ሃይማኖታችን ኢስላም ለአንድ ሰው በውሸት መመስከርን እንኳን አይፈቅድም አይደለም ሙስሊሙን ኡማ ለሚያጠመው ሱፍያ ለተባለው የጥመት ቡድን ሊመሰከር ቀርቶ፡፡
ባጢል ላይ ያለ ስብስብ ሁሌም ለውርደት የቀረበ ነውና ለቀላቢው ያልታመነ ለፍጡራን አይታመንም፡፡ ድምፃችን ይሰማ ሙስሊሙን ካሰጨረሰው በላይ ሱፍያና አሻኢራ የተባሉትን የጥመት መንገድ ተከታዬች ለኡመተል ኢስላም እንደ ፃድቅ አድርጎ ማቅረቡ የባሰ በደል ነው፡፡
መቼም ጌታዬን እልፍ አእላፍ የደረሰ ምስጋና አቀርብለታለሁ፡፡ ምክንያቱም በነዚህ ሰዎች ሳንሸነገል፣ ከውሸት ፕሮፖጋንዳቸው ጠብቆን፣ በሐቅ ላይ እንድንፀና ላደረገን፡፡ አህባሽ ይዞ የመጣውን የሺርክና የቢድኣ አጀንዳ ነብያት ሁሉ ቅድሚያ ለተውሂድ እንደሰጡት በአላህ ፍቃድና እገዛ ቅድሚያ ለተውሒድ ሰጥተን ነብያት በሄዱበት መንገድ ሄደን ህዝቡን ከሺርክያት፣ ቢድኣ፣ ፖለቲካ፣ ነሺዳ፣ ድራማ፣ ፊልም፣ ኳስ አህባሽና ሌሎች የጥመት ቡድኖች ይዘውት ከመጡት ጥፋት አቅም በፈቀደ መልኩ ለመታደግ ተችሏል፡፡
ድምፃችን ይሰማን ሲከተሉ የነበሩት ደግሞ ለአቂዳ ሊሰጥ የሚገባውን ትኩረት ሳይሰጡ ወደ ተውሒድ የሚጣሩ ሰዎች ላይ የዋሸውን ቢቢኤን እያዳመጡ፣ ነሺዳቸውን እየዘፈኑ ልባቸውም የደረቀ አሉ፡፡
በሐቅ ላይ መሰባሰብ ስኬት ነው፡፡ በባጢል ላይ መሰባሰብ ውርደት ነው፡፡
አላህ ሆይ! ሐቅን በሀቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፡፡ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡ https://t.me/SadatTextPosts
እውነት የኢትዮጵያ ሙስሊም መውሊድ ማክበር ነበረበትን? በፍፁም።
ምክንያቱም ያኔ የረሱልን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ፊት ያዩት፣ መልክቱን ከምንጩ የጠጡት፣ የመጀመርያዎቹ ትውልዶች፣ ሙሀጂሮች ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው ሲመጡ መውሊድን ይዘውት አልመጡም።
ታድያ አንዳንድ አላዋቂዎች "ሸህ አሊ ጎንደር፣ ሾንኪዎችና ሌሎች" ይፈቀዳል ብለዋል ቢሉ እውነት እንዳይመስልህ። እውነት ማለት የጥንት የጠዋቱ ሰሃባዎች ይዘውት የመጡት ነው።
የአባቶቻችን መንገድ ነው ቢሉህም እንዳትሰማቸው ምክንያቱም የጥንት የጠዋቱ አበዎቻችን ለስደት የመጡት ሰሃባዎች ያላሳዩን ተግባር ነውና እንረቀው። የሚገርመው ግን መውሊድን የሚያከብሩ የጥንት ተደርገውና፣ መውሊድን የሚከለክሉትና የሚያወግዙት እንደ መጤ መቆጠራቸው ነው። ከኀላ የመጣ አይን አወጣ እንደሚባለው ማለት ነው። አላሁል ሙስተአን።
ሰዎች በሀቅ ይለካሉ እንጂ ሀቅ በሰዎች አትለካም።
አገራችን ላይ የሚከበረው መውሊድ ታላቁ ሽርክ ሁሉ የተቀላቀለበት ነው።
ሽርክ ደግሞ ስራን ሁሉ ያበላሻል። አስደናቂው ይህን የታላላቅ ሽርኮች መናሀርያ "አይለያየንም" ብለው የሚሰብኩ ስሜታቸውን አምላኪዎች አሉ።
መውሊድን ሽሸው፣ ተጠንቀቅ አስጠንቅቅ።
https://t.me/SadatTextPosts
‹‹ልዩነት እያለ ልዩነት የለም የሚሉ ሰዎች ለህዝቡ እየጠቀሙት ሳይሆን ህዝቡን እየጎዱት ነው፡፡ እውነት እያስተማሩት ሳይሆን እውነትን እያሳቱት ነው፡፡›› ሸይኽ ሙሐመድ አወል ሰኢድ (ሀፊዘሁላህ)
https://t.me/SadatTextPosts
ይህ ዲን ከአላህ የወረደ ነው፣ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)ና ሰሃባዎቻቸው ሁሉን አሳይተው፣ አስተላልፈውልን ሄደዋል፡፡
ከእኛ የሚጠበቀው መከተል ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ስሜትን እከተላለሁ፣ ቢድዐ አመጣለሁ ማለት ለውርደት፣ ለውድቀት ይዳርጋል፡፡
‹‹መውሊድ አይለያየንም››፣ ‹‹መውሊድ ቅርንጫፍ ነው››፣ ‹‹መውሊድ አቂዳ አይደለም››፣ ‹‹አንድ ነን እኛ›› ሳይሆን መባል ያለበት መውሊድ የሽርክ መናሃርያ ቢድዐ ነው ተብሎ በግልፅ መነገር ያለበት፡፡
2 ሃቅ የለም፡፡ መወሊድ ቢድዐ ነው፡፡ ያውም የሽርክ፣ የፊስቅ መናሃርያ ነው፡፡
የአላህ ባርያዎች ሆይ! ማንም አይሸውዳችሁ አገራችን ላይ ያለው መውሊድ እርኩስ የሆኑ ባዕድ አምልኮዎች ይፈፀሙበታል፡፡
ይሀው ለምሳሌ
- ‹‹አላሁመ ሰሊ አላ ሙሐመዴ፣
መገን ነቢ የሁሉ ቀላቢ››
አላህ ደግሞ የነብዩ ሙሐመድም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሆነ የፍጡራን ሁሉ ቀላቢ አላህ ብቻ ነው፡፡ ታድያ ይህን ታላቁ ሽርክ የተሰራበት ተግባር ምን ሊባል ነው?
ሽርክ ደግሞ አንድ ብቻ ናት የሚባል ነገር የለም፡፡ አንድ ነን ብሎ ሰውን ከማታለል የእውነት አንድ የምንሆንበትን ተውሂድ ዛሬም፣ ነገም፣ ከነገ ወድያም፣ ሞት እስኪመጣን ድረስ ወደ እሱ መንገድ መጣራት በዛው መንገድ ላይ መፅናት፡፡
አላህ በሃቅ ላይ ይሰብስበን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ወዳጅ አያምፅም
‹‹የፍቅረኞች ቀን፤ የእናቶች ቀን›› ብለው ካሃዲያን ህዝቦች የጀመሩትን አንዳንድ ሰዎች መውሊድን ለማክበር እንደማወዳደሪያነት ማስረጃ ሲያቀርቡ ይታያል እንዲህም በማለት ‹‹የማንም ልደት እንኳን ይከበራል፤ አይደለም የነብያችን›› ችግሩ እነዚህ ወንድም እና እህቶች ያልገባቸው፡፡ ካሃዲያን ህዝቦች ለእናት እና አባቶቻቸው፤ ለትዳራቸው ፍትሃዊ እና ሸክም ተቀባይ ስላልሆኑ በአመት አንድ ግዜ ‹‹የእናቶች እና ፍቅረኞች ቀን ይላሉ››፤ የእኛን ነብይ (ሰለላሁአለይሂ ወሰለም) አላህ ሁሌ በማንኛም ጉዳይ እሳቸውን ፈራጅ እንድናደርግ፤ የሳቸውን ሱና ትንሽ ነው ሳንል ሁሉንም እንድንተገብር አላህ አዞናል፡፡ ይህም የሳቸውን ሱና መከተል የእውነተኛ ፍቅር መገለጫ ነው፡፡

ከዚህ ውጭ እየጨፈሩ አንዳንዴም ሽርክ የተቀላቀለበት መንዙማ እያሉ፤ ወንድ እና ሴት ተደባልቆ፤ ወንድ ልጅ እያጨበጨበ እና እያፏጨ እንደ ሙሽሪኮች፤ ይህ እና የመሳሰሉት ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መውደድ ሳይሆን የሳቸውን ሱና በመጣስ ሱናቸውን በማውደም ቢድዓን ለማንገስ የሚደረግ ሩጫ ነው፡፡ እንቆጠብ የአላህ ባሪያዎች ሆይ፡፡ በጣም በትንሹ የአላህ መላክተኛን የሚከተሉት ቦታዎች ላይ ሁሌ እናነሳቸዋለን፡፡

1.አንድ ሰው ወደ እስልምና ሲቀላቀል
2.ዉዱ አድርገን ስንጨርስ
3.መስጊድ ስንገባ
4.ከመስጊድ ስንወጣ
5.አዛን ሲባል
6.ከአዛን በኋላ እሳቸው ላይ ሰለዋት እናወርዳለን
7.ኢቃም ላይ
8.ተሸሁድ (አታህያቱ ላይ)
9.ዱዐ መክፈቻ
10.ዱዐ ሲጠናቀቅ
11.ጁምዐ ቀን በበለጠ ሁኔታ
12.የዳዕዋ መክፈቻ ላይ የሳቸውን ስም እናነሳለን
13.ጁመዐ ኹጥባ ላይ
14.ሞተን ሰላተል ጀናዛ ሲሰገድብን ወይንም የሞተ ሰው ላይ ስንሰግድ
15.አላህን እንዴት ማምለክ እንዳለብን ያሳዩን እሳቸው ናቸው፡፡ አላህ ታዘዙት ‹‹እሳቸውን (ነብያችንን) መታዘዝ አላህን መታዘዝ ነው››
16.እንዚህና መሰሎች ብዙ ቦታዎች ላይ ነብያችን ላይ ሰለዋት እናወርዳለን
ታድያ ለምን ይሆን ቀንን መድበን በዐመት አንዴ፤ ድንበር በማለፍ ሽርክና ጭፈራ የተደባለቀበትን ነገር የምንሰራው?

ወዳጅ አያምፅም፡፡ አደለም ነብያችንን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፤ አላህን መውደድ እንኳን የሚገለፀው ነብያችን በመከተል ነው፡፡ ያል ሰሩትን በመተው ነው፡፡ ከነ አቡበክር፤ ኡመር፤ ኡስማን፤ አልይ (ረድየላሁ አንሁም)፤ ከሙሃጂሮች እና አንሷሮች (ሪድዋኑላሂ አለይሂም)፤ ከሶስቱ ምርጥ ትውልድ የበለጠ ከነሱ በኋላ የመጡት ሸሪዐን ተረዱ?

መውሊድን የጀመሩት ሺዐዎች ናቸው፡፡ ሺዐዎችን ማን እንመሰረተ ደግሞ ግልፅ ነው፤ ኡስማን ኢብን አፋንን (ረድየላሁ አንሁም) ያስገደላቸው፤ አብደላህ ኢብን ሰባዕ አል-የሁዲ ነው፡፡

እውነት ሺዐዎች ለኢስላም አስበው መውሊድን ፈጠሩ ወይንስ ቢድዐን አምጥተው እንዲህ ሊበታትኑን ብቅ አሉ፡፡ መርሳት የሌለብን የአላህ ባርያዎች አንድ የምንሆነው በተውሂድ እና ሱና እንጂ በሽርክ እና ቢድዓ አይደለም፡፡ አንዳንድ አላዋቂዎችን ወይንም አውቆ አጥፊዎችን እንዳትሰሟቸው ቢድዓ ሲወገዝ ‹‹አትለያዩን፤ አትበታትኑን›› የሚል ቃል ይዘው ብቅ ካሉ፤ የሚለያየው ሽርክ እና ቢድዓ ነውና፡፡
ታድያ የአላህ ባሪያዎች ከዚህ ተግባራችን አንቆጠብምን፡፡ አላህ ሆይ! ሃቅን አሳየን የምንከተለውም አድርገን፤ ባጢልንም አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡

የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
መውሊድን አላከብርም፡፡

መጀመሪያ የረሱልን (ﷺ) ሱና ተግብሬም አልጨረስኩም፤ አይደለም ቢድዓን ልፈጥር፡፡ አላህ ደግሞ መልክተኛውን አትቃረኑ በዱንያ ላይ ፈተና፤ በአኸይራ ላይ አሳማሚ ቅጣት አለላችሁ ይላል፡፡ መልክተኛውን በመቃረን የሚመጣውንም ፈተና እያየን ነው

የረሱልን (ﷺ) ሱና ተግብረው ሳይሰሩ
ውሸት ምን ያደርጋል ቢድዓ እየሰሩ፡፡

የአላህ መላክተኛ ሳያስተላልፉ የቀሩት ነገር አለ እያለ ነው መውሊድ የሚያከብር ሰው??? ይቅርብህ ወንድም ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
አላህ 5 ወቅት ሰላትን ብቻ አዞ እና ደንግጎ መልክተኛውም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በተግባር ሰርተው ያሳዩን ይህን 5 ወቅት ብቻ ሆኖ እያለ 6ኛ ብለህ/ሽ ብትሰራ/ሪ አላህ ዘንድ ምን ይሆናል ፍርድህ/ሽ?????
ልክ እንደዚህ ሁሉ አላህ የደነገጋቸው የኢስላም በዓላት ኢደል ፊጥር እና ኢድል አድሃ ብቻ እና ብቻ ናቸው። የአላህ መልክተኛም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የበዓሎቹ ስርዓት እንዴት እንደሚመስል በተግባር አሳይተውናል።
ታድያ አንተ/ቺ መውሊድን የምታከብር/ሪ ሆይ! 3ኛ በዓል ብለህ/ሽ ጨምረህ/ሽ ስታከብር/ሪ ምን ይሆናል ፍርድህ/ሽ?????
ከእኛ በላይ አጉራሽ ማዕድ አበላሽ ይላል ተራቹ። አላህ ይህ ዲን ምን መሆን እንዳለበት ደንግጓል፣ መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከአላህ በተላኩበት ጉዳይ ሁሉ ድካ የደረሰችን መልክት ማድረስ አድርሰዋል። አላህ ዲኑን ሞልቶታል ጭማሪ አይፈልግም።
መውሊድ የጥመት እና የጥፋት ሁሉ መናሃሪያ ነው፣ ሽሸው/ሽሺው የአላህ ባርያ ሆይ።
https://t.me/SadatTextPosts
በልደት ቀናቸው ቢፆሞ ኖሮ ታድያ ለምንድን ነው አመት ጠብቀው ያቺ የተወለዱባትን ቀን ያልፆሙት?????
================================
የተለመደው የሱፍዬች እና የአህባሾች ማምታቻ መውሊድን በተመለከተ ሲጋለጥ
እንዲህም ይላሉ ‹‹ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሰኞን በመፆም የተወለዱበትን ቀን አክብረዋል››
ይሄ በመውሊድ ወቅት ሰው ዘንድ የተሰራጨ ብዥታቸው ነው ‹‹መውሊድ ማክበር ችግር የለውም ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እራሳቸው ሰኞን በመፆም ስላከበሩት፡፡›› ነገር ግን ይሄ ቅጥፈት ነው፡፡ የአላህ መልክተኛ ላይ ውሸትን የሚቀጥፍ ከባድ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡ አላህ ይጠብቀን፡፡
ሀዲሱ እንዲህ ነው የሚለው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሰኞን ስለመፆማቸው ተጠየቁ እሳቸውም ‹‹በዛ (ቀን) ተወለድኩ እናም በዛው ቀን ወህይ (መለኮታዊ ራዕይ) ወረደልኝ›› ሰሂህ ሙስሊም (1162)
እውነታው የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ልደታቸውን አላከበሩም፡፡ የተወለዱበትን ቀን ሰኞ ፆሙ እንጂ በልደት ቀናቸው አልፆሙም፡፡ በሁለቱ መሃል በጣም ሰፊ ልዩነት አለ ድጋሚ አንብቡት ወንድም እና እህቶች፡፡
‹የፆሙት በተወለዱበት (ሰኞ) ቀን እንጂ አመት ተጠብቆ የምትመጣዋን የልደት በዓልዋ ቀን አይደለም›
የተወለዱበት ቀን በሚለው ላይ በኡለማዎች መሃል ልዩነት አለ፡፡ ለምሳሌ ረቢዑል አወል 12, 9 እና የመሳሰሉትን) የሞቱበት ቀን ግን በቁርጥ ረቢዑል አወል 12 ነው፡፡
ጥያቄዎች
=====
የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሰኞን ፆመዋል፡፡ በልደት ቀናቸው ቢፆሞ ኖሮ ታድያ ለምንድን ነው አመት ጠብቀው ያቺ የተወለዱባትን ቀን ያልፆሙት?????
ይልቁንስ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ብዙ ሰኞዎችን ፆመዋል፡፡ በሱፍዬች እና በአህባሾች ሎጂክ መሰረት ‹‹በአመት ውስጥ በተለያየ ግዜ ነው የተወለዱት›› ማለት ነው?????
ማጠቃለያ
======
ሰኞ ቀናቶችን የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና በመከተል እንፆማለን እንጂ ስሜታችንን ለመከተል ሀዲስ አናጣምም፡፡
መውሊድ ውስጡ ሽርክ ያቀፈ ቢድዓ ነው፡፡ የአላህ ባርያዎች ሆይ! እንሽሸው፡፡ ከሃቅ ባኋላ ጥመት እንጂ ምን አለ፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በባልደረባዎቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ስለ መውሊድ ከተዋሸው ውስጥ የሚከተለው ይገኛል፡፡ ክፍል 31
‹‹ረቢዐል አወል የገባ ጊዜና፣
በሀኢሙ (እንስሳው) ሁላ ያቀርባል ምስጋና፣
ለመውሊድ አድርገን እያለ መውላና፡፡››
ምንጭ በሽርክ መንዙማ የሚታወቀው ሙሐመድ አወል፡፡
እስቲ ከቁርዐንና ከሀዲስ ማስረጃ ያምጡ? በአላህ ላይ የማያውቁትን መቀጣጠፍ ከባድ ወንጀል ነው፡፡ እንዲህ ሽርካቸውንና፣ ቢድዐቸውን ከሀይማኖት ለማስመሰል በአላህና በመልክተኛው ላይ ይቀጥፋሉ፡፡ በአላህና በመልክተኛው ላይ መዋሸት ሌላው ላይ እንደመዋሸት አይደለም፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ዶክተር ጀይላን እና ሙሐመድ ፈረጅ እውነት የሀሰን ታጁን ጥመት ሳታውቁ ቀርታችሁ ነበርን? ሀሰን ታጁ የአላህን ስምና መገለጫዎቹን ማጣመም የጀመረው፣ ወደ ቢድኣ በግልፅ የተጣራው፣ ወደ ኢኽዋነል ሙስሊሚን የጥመት ቡድን ኡመተል ኢስላምን በመፀሀፎቹ የሰበከውና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ያጠመመው፣ ወደ ፊልም እና ድራማ “ኢስላማዊ” ብሎ የሚጠራውን ህዝቡ ላይ የቆመረበት ከተቃውሞ ሰልፍ ወጥቶ “መንታ መንገድ” የሚለውን ፅሁፍ ከፃፈ በኋላ አልነበረም፡፡ ይልቁንስ ከዛ በፊት ቢሆን እንጂ፡፡ “ሱኒ ነኝ” የሚል ሰው ጠሞ አጥማሚውን ሀሰን ታጁን መስጂድ ላይ ጠርቶ ለኡማው ጥመቱን እንዲረጭ ይፈቅዳልን? ዶክተር ጀይላን እና ሙሐመድ ፈረጅ የሚገኙበት አየር ጤና አንሷር መስጂድ ላይ ነበር ሀሰን ታጁ የአንድነት እና ሰደቃ ፕሮግራም ተብሎ ጥመቱን የረጨው፡፡ ሙሐመድ ፈረጅ ስለ ኢኽዋን ረድ አደረገ ተብሎ የሆነች ሰሞን ተወርቶ ነበር፡፡ ኢኽዋን ሲል እነ ሀሰን ታጁን ነው የሚፈልግበት? ከሆነ ለምን እስከዚህ ቀን ድረስ ጥመታቸውን እያወቀ ዝም ማለት አስፈለገው? ይህ የዲን አማናን መብላት አይደለምን? ሐቅን መደበቅ አይደለምን? አንድን ሰው ለመቃወም ግዴታ በግል ጉዳይ እስኪጣሉ መጠበቅ ከዲን ነውን? ምክንያቱም የሀሰን ታጁ ጥመት አገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ዛሬ አይደለም፡፡ የአላህን ስም እንደ አህባሾች እንደሚያጣም በፊትም ይታወቅ ነበር፡፡ ይህ ከሆነና እውነት አህባሽን እቃወማለሁ የሚል ሰው ከሀሰን ታጁ አይነት ሰዎች ጋር አንድነትና ሰደቃ ብሎ በየክፍለ ሀገሩ መዞር ነበረበትን? በፍፁም፡፡ በአቂዳ ዶክተር ናቸው የሚባሉት ዶክተር ጀይላን ግን ከአጥማሚው ሀሰን ታጁ ጋር በእድሜ ዘለቅ ያለ ግንኙነት ውስጥ ገብተዋል፡፡ ለዚህም ማስረጃችን ዶክተር ጀይላን፣ ከነ ሀሰን ታጁ፣ ሙሐመድ ዘይን ዘህረዲን፣ ሙሐመድ ሀሚዲንና በድሩ ሁሴን ጋር ቻግኒ ከሚገኙት በገሃድ ወደ ሺርክና ክህደት ከሚጣሩት ቲጃንዬች ጋር የአንድነት ጥሪ ብለው ከአመታት በፊት ከነዚሁ ቲጃኒ ሱፍዬች ጋር አንድ መድረክ ላይ መገኘታቸው ነው፡፡ ዶክተር ጀይላን ቻግኒ ላይ ከቲጃኒ ሱፍዬች ጋር አብረው በነበሩበት መድረክ ላይ “ሀገራችን ላይ አጥፊ ቡድን የለም” ሲል ጠቅሶ ነበር፡፡ ግን በዛ ወቅት አህባሽ የመጅሊሱን ስልጣን አልያዘም ነበር እንጂ እንደ ልቡ ይፈነጭ ነበር፡፡ እነዚሁ በኩፍር የተጨማለቁ ቲጃንዬችም ሀገራችን ላይ አጥፊ ቡድን እንዳለ ታላቅ ማሳያ ናቸው፡፡ ዶክተር ጀይናል ሆይ! ዶክትሬት የሰሩት በአቂዳ ከሆነ እውነተኛ አቂዳ ወላና በራእ የለውምን? ከሀሰን ታጁና ሌሎች አህባሾች ሬድዬ ላይ ሙፍቲ ሆነው ከሚቀርቡ ሰዎች ጋር የተማሩት አቂዳ አብራችሁ አንድ ሁኑ ይላልን? ዶክተር ጀይላን፣ ሙሐመድ ፈረጅና ሌሎችም አላህን ፍሩ፡፡ ሁላችንም አላህን እንፍራ፡፡ ነገ አላህ ፊት ራቁታችንን ቆመን እንጠየቃለን፡፡ ኡመተል ኢስላም ዘርፈ ብዙ ችግሮች አሉት፡፡ በዋናነት ከምንም በፊት አቂዳን ማስተካከል ይቀደማል፡፡ ለሀገራችን ኢትዬጵያም ይሁን አለም አሁን ላለችበት ችግር ከምንም በላይ ነብያት የተጓዙበት የተውሒድ፣ የሱና፣ የሰለፉነ ሷሊሂን መንገድ ብቻና ብቻ ነው የሚያስፈልጋት፡፡ ሀገራችን አህባሽም፣ ኢኽዋንም፣ ተብሊግም፣ አሻኢራም፣ ሙዕተዚላም፣ ማትሩድያም፣ ሙርጂኣም፣ ተክፊርም ሌላም የጥመት ቡድን አያስፈልጋትም፡፡ ብቸኛው የሁለት ሀገር ዋስትና ብቸኛዋ የሐቅ ጎዳና የሰለፉነ ሷሊሂን ጎዳና ብቻ ናት፡፡ ይህ ግልፅ መገሰጫ ይሆን ዘንድ ተመከሩበት፡፡ ጥፋታችሁን እያዩ ዝም የሚሏችሁ ሰዎች ያከበሯችሁ እንዳይመስላችሁ፡፡ በነፍሳችሁ እየተጫወቱባችሁ ነው፡፡ ለናንተም የሚከላከሉላችሁ ሰዎች ወደዋችሁ እንዳይመስላችሁ ወይ እውቀት የላቸውም ወይ አውቆ አጥፊ ናቸው፡፡ እናንተው እራሱ የምትሄዱበት አካሄድ ጥፋት እንደሆነ ተገንዝባችሁታል፡፡ ንቁ ሀቅን ብትከተሉ ለነፍሳችሁ ነው፡፡ በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል ከኢስላም አስተምህሮት ነው፡፡ ለዚህም ሲባል በግል ጉዳይ ምንም የማያገናኘን ነገር ሳይኖር በዲን ጉዳይ የተሳሳታችሁትን ብሎም በአደባባይ ሰዎችን እየጠራችሁበት ያለውን ጥፋት በማስረጃ እርምት ይሰጥበታል፡፡ እናንተም በማስረጃ ጥፋት ካያችሁ አርሙ፡፡ በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል ከኢስላም ትልቅ ክፍል ውስጥ ነው፡፡ የተከታይና አድናቂ ብዛት አያታላችሁ፡፡ ነብያት በሄዱበት መንገድ ያልሄደ ሁሉ ዛቻ አለለት፡፡ በተሰጠው እውቀት ያልሰራ ሁሉ ከባድ አደጋ ውስጥ ነው፡፡ መታወቅ ያለበት በባጢል መንገድ ላይ የተለፋውን ያህል ቢለፋ ክስረት እንጂ ልማት የለም፡፡ ከአመታት በፊት ጀምሮ ስትሰሩ የነበረውን የተበላሸ አካሄድ እራሳችሁ ገምግሙት፡፡ ክስረት እንጂ ምን ጨመረላችሁ፡፡ ጭፍን ተከታዬቻችሁ እንዲህ የምትታረሙበትንም ነገር ሲነገራችሁ “ተሰደባችሁ” ቢሏችሁ እውነት መስሏችሁ የነፍሳችሁ ክብር አይምጣባችሁ፡፡ አልተሰደባችሁም ይልቁንስ በኪሳራ ላይ ኪሳራ ሳያጋጥማችሁ ወደ እውነተኛው የሐቅ ጎዳና ተመለሱ፡፡ እናንተ ከባጢል ሰዎች ጋር ሁሉ አንድ መሆን አይከብዳችሁም፡፡ ይህንንም በተግባራችሁ እያያችሁት ነው፡፡ ድቅድቅ ጥመት ውስጥ ካሉት ቲጃንዬች ጋር ሁሉ አንድነት ትፈጥራላችሁ፡፡ በያገኛችሁት አጋጣሚ ግን የሰለፉነ ሷሊሁንን መንገድ የሚከተሉትን ትወርፋላችሁ፡፡ ሙስሊሙ ዘንድ በመጥፎ ትስሏቸዋላችሁ፡፡ ይሄ ምን አይነት አስፀያፊ ተግባር ነው? አላህን አትፈሩትም፣ አታፍሩትም? አላህ እኛንም እናንተንም ሐቁን መንገድ ይምራን፡፡ አላህ ሆይ! ሐቅን በሐቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፡፡ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡
በአላህ ፍቃድ በድምፅ ፋይል በሰፊው ይብራራል፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
‹‹ሰርጎን በዲጄ???» «ወይንስ በመንዙማ ባንዶች???» ወይንስ ሸሪዐ ባሳየው መልኩ???

አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ነብዩ ((ﷺ)) የላከበት ዲን ተጨማሪም ቅናሽም የማይፈልግ ዘመን የማይሽረው ለማንኛውም ዘምን እስከ ቂያማ (እለተ ትንሳኤ) ድረስ ለሚመጡ ጉዳዬች ነብያችን……. አብራርተው አሳይተዋል፡፡

ሰርግ እንዴት መምሰል እንዳለበት ምርጡ ነብይ ተናግረዋል፤ በተግባርም ሰርተው አሳይተዋል፡፡ ሙስሊሞች ሙስሊም ካሰኛቸው ነገር ውስጥ በዲናቸው ወይንም በረሱል ((ﷺ)) ሱና በማንኛውም ዘመን ሳያፍሩ፤ ሳይቀይሩ፤ ሳይጨምሩ እና ሳይቀንሱ በቻሉት መጠን ለመተግበር እሺ ብለው እጅ መስጠታቸው ነው፡፡

ሰርግ ቤቶች ላይም ይሁን በማንኛውም አይነት መንገድ ከተጠሉ እና ከተከለከሉ ነገሮች ውስጥ ‹‹ኢኽቲላጥ›› ወይንም ‹‹አጅነቢ ወንድ እና ሴት መቀላቀል ነው›› ዛሬ ዛሬ ይህ ወንጀል የተለመደ ነገር ሆኗል፡፡ ሰርግ ላይ ዘመዳማቾች አብረው ሰርግ ላይ ‹‹እስክስታ መባባል›› አለባቸው ‹‹ወገቡ ይታይለት፤ ወገቧ›› ይታይላት ይባላል፡፡ ለዚህም ሲሉ አንዳንድ እራሳቸውን ‹‹ዘመናዊ ሙስሊሞች›› ብለው የሚጠሩ ‹‹ባንድ ወይንም ዲጄ›› የሚባለውን ሰርግ ላይ በመጥራት ወንድ እና ሴትን አስደብልቀው፤ ዳንስ እና እስክስታ ሲጨፍሩ ይታያል፡፡

ስለ ሙዚቃ መሳሪያ
==========
ነብያችን ((ﷺ)) ሙዚቃ መሳሪያን ከልክለዋል ((ﷺ)) እንዲህም ሲሉ ‹‹ከእኔ ኡመቶች ሰዎች ይመጣ (ለወንድ) ሃር መልበስን፤ ዝሙትን እና የሙዚቃ መሳሪያን የሚፈቅዱ ሰዎች›› ብለው ኮንነዋቸዋል፡፡ ሃዲሱን ኢማሙ ቡኻሪ ሰሂሃቸው ላይ ዘግበውታል፡፡

ሌሎች እንዲህ ሲሉ ዲኑ ያስቀመጠውን ትተው የራሳቸውን አስተያየት ሰጡ
‹‹ባንድ እና ዲጄ ከማምጣት፤ መንዙማ እና ሃድራ ባዬች ይሻላሉ›› አሁን አሁን በየሰርጉ የተለመደ ‹‹ድቤ›› የያዙ የተለያዩ ቡድኖች ያን ድቤ እየመቱ ወንዶች ተሰብስበው ‹‹እያጨበጨቡ፤ ዘለል ዘለል›› እያሉ የሚያነሷቸው ስንኞች ላይም ‹‹ሽርክ›› ጭምር የሚደባለቅበት ሁኔታ አለ፡፡
በጣም የሚገርመው ‹‹ሰለዋት›› ኢባዳ ነው፤ ‹‹ሰለዋት›› በማለት ወደ አላህ የምንቃረብበት፡፡ እነዚህ ሰዎች የሚጠሩት ‹‹1500-3000 ብር›› ተከፍሏቸው ነው፡፡ ለምን ይሆን ዲኑን የሚነግዱበት???

እሺ ኢስላም ስለ ሰርግ ምን ይላል???
==================
1) ሰርግ ላይ የሚጨፍሩት ሴቶች ናቸው፤ እሱም ‹‹ደፍ›› የሚባል መሳሪያ አለ፤ እሱን ብቻ ተጠቅመው ድንበር ማለፍ የሌለበትን ግጥም እየገጠሙ፤ ወንድ ሳይሰማቸው መጨፈር ይችላሉ፡፡
2) ወንድ እና ሴት አንድ ላይ በፍፁም ሊደባለቁ አይገባም ያለ መጋረጃ፤ ወይንም የተለያየ ክፍል በማስቀመጥ ቢሆን እንጂ፡፡ አንድ አንድ ቦታ አላህ ይጠብቀን፤ ባል እና ሚስት መድረክ ተሰርቶላቸው ሰው ሁሉ ያያቸዋል፡፡ ነብዩ ((ﷺ)) ‹‹ደዩስ ጀነት አይገባም›› ብለዋል፡፡ ደዩስ ማለት ‹‹በሚስቱ፤ በእህቱ፤ በናቱ፤ በልጁ እንደው በአማኝ ሴቶች የማይቀና›› ጀነት አይገባም፡፡ እንዴት ሰው ሚስቱን እንደምትሸጥ እቃ ለሰው ሁሉ ያሳያታል???
3) ወንድ ልጅ አያጨበጭብም፡፡ ማጨብጨብ የሴት ነው፡፡ ነብያችን((ﷺ)) እንዳሉት
4) ነብዩ ((ﷺ)) እንዲህ ይላሉ ‹‹ከምግብ ሁሉ መጥፎ ምግብ፤ የሰርግ ቤት ምግብ ነው፡፡ (ምግቡን) የሚፈልገው ሰው ይከለከላል፤ የማይፈልገው ሰው ይጠራል››

ሸሪዐው ጭፈራን ለሴቶች ብቻ ነው የፈቀደው፤ ያውም በ ‹‹ደፍ›› ብቻ፤ ድንበር ማለፍ የሌለበት ግጥም እየገጠሙ፤ ወንዶች ሳይሰሟቸው፡፡ ሰለዋት ነው እየተባለ ወንድ እና ሴትን ቀላቅሎ አላህን ማስቆጣት ይቅር፡፡

ዘመናዊነት ለሚሉ ሰዎች ‹‹ከኢስላም የበለጠ ዘመናዊነት አለን???›› አላህ ነብዩ ((ﷺ)) የላከበት ዲን ዘመን የማይሽረው በየትኛውም ወቅት እና ቦታ፤ ለየትኛውም አይነት ማህበረሰብ የበላይነቱ የነብዩን ((ﷺ)) ሱና፤ ፋና፤ መንገድ መከተሉ ነው፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ሁላችንም ከራሳችን ጀምረን፤ ቤተሰቦቻችንን፤ እና ዘመዶቻችንን የሱናን ዉበት ልናሳይ ይገባል፡፡ ስለዚህ ‹‹ዲጄም ይሁን የድቤ ባንድ›› የሚባል ነገር በኢስላም የለም፤ ኢስላም የደነገገውን ከላይ ተጠቅሷል፡፡

አላህ ሆይ! ሃቁን አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፤ ባጢልንም አሳየን የምንርቀው አድርገን፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በአላህ መልክተኞች ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
በውሸት መመስከር ታላቅ በደል ነው፡፡
አላህን መፍራት ለምን ቀረ፡፡ የቢድኣ ሰዎችና የስሜት ተከታዬች መንገድ የሆነውን ተቃውሞ ሰልፍ አቀጣጣይ የሆነን ሰው፣ ለጥመቱ ቡድን ኢኽዋን ከለላ የሚሰጥ ሰው፣ አጥፊዎችን ዝም ሲል የነበረ ሰው፣ የሱና ሰዎችን ባገኘው አጋጣሚ የሚጎሽም በግልፅ ተመልሻለሁ ሳይል የሰለፊያን ካባ ማልበሱ በደል ነው፡፡ ሌላው ሊረሳ የማይገባው ሰዎች ትላንት የነበሩበት አቋም ዛሬ ድረስ ውዳሴ አያሰጣቸውም፡፡ በሐቅ ላይ እስከለተሞት መፅናት ግድ ነው፡፡ ትላንት የሱና ሰው የነበረ ወይንም ወደ ተውሒድ የተጣራ ሰው ዛሬ ኢኸዋኒ፣ ተብሊጊ፣ አህባሽ ቢሆን ወይንም ለነሱ ጥብቅና ቢቆም ይህ ሰው የሱና ሰው አይባልም፡፡ በሱና ላይ መፅናት ያቃተው እንጂ፡፡ እዝነት በሚል ስም ሸይጧን አይጨወትባችሁ፡፡ ለሁሉ ነገር ልክ አለው፡፡ አንዳንድ ወንድሞች ደግሞ “ሰዎችን ከሱና ማስወጣት ከባድ ነው” የሚለውን የኢማሙ አሕመድ ንግግር ይጠቅሳሉ፡፡ ታድያ ግለሰቡ እራሱ ከነበረበት ሱና ወጥቶ አዲስ መንገድን መከተል፣ ወደሱ መጣራት፣ ለዛ መንገድ ጥብቅና መቆም ብሎም የነበረበትን የሐቅ መንገድ መቃረን ሲጀምር “ሰዎችን ከሱና ማስወጣት ከባድ ነው” ብለን ዝም እንላለን ወይ?
በፍፁም፡፡ ለምሳሌ አገራችን ላይ አላህ ይምራው ማሕሙድ ሀሰን የሚባል ግለሰብ ነበር፡፡ ወደ ተውሒድና ሱና በመጣራት፣ ሺርክና ቢድኣን በማስጠንቀቅ፣ የሱና ተግባራትን የበላይ ለማድረግ፣ መጥፎ መንገዶችን በመቃወም የተወሰነ ጊዜ ለፍቶ ነበር፡፡ በወቅቱም ማሕሙድ ሀሰን የሱና ዳኢ በሚባል አብረውት የነበሩ ሰዎች ሰለፊ፣ የሱና ሰው መሆኑን አረጋግጠውለት ነበር፡፡ ከጊዜ በኋላ ተቀየረ ከባባድ አፈንጋጭ አቋሞችን ማንፀባረቅ ጀመረ፡፡ የቢድኣ ካዝና ከሆነው ሀሰን ታጁ ጋርም አፍሪካ ቲቪ ላይ ነቀርሳቸውን አብረው ለመርጨት ሞከሩ፡፡ ከዚህም አልፎ በግልፅ በፊት ስለነበረበት አቋም ሲጠየቅ “ተሳስቼ ነበር” ሲል መለሰ፡፡ ከዛም አልፎ የሱና ሰዎችን መወረፈ ጀመረ፡፡ ይሄ የማሕሙድ ሐሰን ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት ሱና ላይ የነበሩ ከዛም በራሳቸው ፍቃድ ሱናን ተፃረው የኢኽዋንን፣ የአህባሽን፣ የተብሊግን፣ የሱፍያን፣ የሺኣን፣ የተክፊርን እና የመሳሰለውን የጥመት መንገዶች የተቀላቀሉ ግለሰቦች ተጨባጭ ሁኔታ ነው፡፡
ታድያ እንደነ ማሕሙድና መሰሎቻቸውን በትላንት አቋማቸው መፅናት ያልቻሉ ሰዎችን አሁንም ድረስ “ሰለፊ፣ የሱና ሰው” ብለን እንጠራለንን?
በፍፁም፡፡ አላህን እንፍራ ለሁሉም ነገር ልክ አለው፡፡ ከኡለማዎች አንዱ እንዲህ ይላሉ “አንድን ሰው ለአላህ ብዬ እወደዋለሁ ብለህ፣ ከዛም ከአቋሙ ሲለወጥ አሁንም የምትወደው ከሆነ መጀመሪያውንም ለአላህ ብለህ አልነበረም የወደድከው፡፡”
አላህ ሁል ጊዜ በሐቅ መስካሪዎች ያድርገን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
የዩሁዳ ቅጠረኛ?
የኡለማዎችን ስጋ መብላት?
የሰዎችን ስህተት መለቃቀም?
ከመሳደባችሁ በፊት በእርጋታ አንብቡት፡፡

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን፡፡ አሁን ባለንበት ወቅት ነገሮችን ልክ የፖለቲካ ሚድያዎች ውሸትን በመቅጠፍ እንደሚገለባብጧቸው ሁሉ፣ ዛሬ ዛሬ በሃይማኖት ስምም ጥፋታቸውን ለመደባበቅና ጥፋት እንዳይጋለጥ ነገሮችን ገልብጠው የሚያቀርቡ በዝተዋል፡፡
እስቲ የአላህ ባሪያዎች ታዘቡት ሐቅ ስንት ናት?
መልሱም አንድ ናት፡፡ የሚያሳዝነው ሁሉን ጥፋትና ጥመት አቻችሎ ለመሄድ የሚጥሩ ግለሰቦችና ቡድኖች በዝተዋል፡፡ እስቲ የሚከተሉትን ነጥቦች ታዘቧቸው፡፡
1) አንድ የሱና ሰው “አህባሾች” አላህ ከአርሽ በላይ መሆኑን አይቀበሉም፡፡ አህባሹ ኡመር ኮምቦልቻ “የቀብር አፈር እንብላ ብሏል” ብሎ መልስ ቢሰጥበት አህባሽን የሚቃወሙ ኢኽዋኖች ወይንም ሌሎች “ማሻ አላህ፣ በላቸው እነዚህን የዩሁዳ ቅጥረኞች፣ የመንግስት ቅጥረኞች” ይላል፡፡
በተገላቢጦሹ አንድ የሱና ሰው “ሱፍዬች አላህ ሁሉ ቦታ ነው ያለው ይላሉ፡፡ ሱፍዬች ውስጥ የቀብር አፈር ስለመብላት የሚሰብኩ፣ ቀብር ስለመተሻሸት የሚሰብኩ አሉ” ብሎ ስም ጠቅሶ ከተናገረ ከኢኽዋኖች ውስጥ ይህን ግለሰብ “አንተ ኡማውን በታታኝ፣ የኡማው ነቀርሳ፣ የኢሀዲግ ቅጥረኛ፣ የዩሁዳ ቡችላ” እናም ሌላም ሌላም ይላሉ፡፡
ሱብሃነላህ አህባሽን ተቃውመውት የነበረው እውነት የአላህን ከፍጡራኑ ሁሉ በላይ መሆኑን ባለመመስከራቸው ነበርን? ወይንስ ሌላ?
አላህ እውነተኞች ያድርገን፡፡
2) የሱና ሰው “አብደላህ ሀረሬ ሙአዊያ የተባለውን ታላቅ ሰሃባ ይሳደባል” ተጠንቀቁት ቢል፣ ኢኽዋኖች “እነዚህ የሺኣ ቡችሎች በሏቸው” ይላሉ፡፡ ሰይድ ቁጡብ የተባለው የኢኽዋን መሪ “ሙኣዊያን ብቻ ሳይሆን፣ ኡስማንን፣ አምር ኢብነል አስን ይሳደባል፡፡ ብሎም አቡ ሱፍያንን ያከፍረዋል” ብሎ ካስጠነቀቅ የሚከተሉትን ትችቶች ከኢኽዋኖች በኩል ይሰነዘርበታል፡፡ “የኡለማ ስጋ ስትበሉ አይሰለቻችሁም፣ ቅድሚያ ለሀሜት፣ ሰይድ ቁጡብ ሰመኣት (ሸሂድ) ነው፣ እናንተ የዩሁዳ ቅጥረኞች” ይላሉ፡፡ ሱብሃነላህ
3) ሌላው ምሳሌ አንድ ሰው ከአህባሾች ሲያስጠነቅቅ “አህባሾች ወንድና ሴትን ይቀላቅላሉ፡፡” ቢል “የታባታቸው በላቸው እነዚህ የአብደላህ ሀረሪ ቡችሎች፣ የወያኔ ቅጥረኞች፣ የዩሁዳ ምልምሎች” ሲሉ ታያቸውና፡፡ ወንድ እና ሴት በመቀላቀላቸው ተከፍተዋል ብለህ ስትገምት እነሱ ለምሳሌ ግርማ ንዋይ ህንፃ ላይ “የጀዛ ፊልም ምርቃት” ተብሎ ሀሰን ታጁ፣ ያሲን ኑሩ፣ በድሩ ሁሴን ወንድ እና ሴት ያለመጋረጃ ሳይለዩ ፊልም መርቀው ነበር፡፡ ይህንንም በድብቅ ሳይሆን ያደረጉት እስካሁን ድረስ በሚከተለው የዩቲዩብ ሊንክ እንደ ትክክለኛ ነገር በአደባባይ ተለቋል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=BSVhn2dsSbQ
ታድያ ሀሰን ታጁ፣ ያሲን ኑሩ በድሩ ሁሴን የኢስላም ዳኢ ከተባሉ ይህንን አስፀያፊ ኢስላም የማይፈቅደው ተግባር ለምን ፈፀሙ? ያውም አዳራሹ ሌሎች ሙስሊም ተማሪዎች ሲከራዩ ወንድ እና ሴትን በመጋረጃ ይጋርዳሉ፡፡

እነ ያሲን ኑሩ ይህን አህባሾች ወንድና ሴት ይቀላቅላሉ የተባለውን ተግባር እነሱም ፈፅመውታል፡፡ ሙስሊሞች ሆይ! ተጠንቀቁ ከተባለ “እናንተ የመንግስት ቅጥረኞች፣ የዩሁዳ ተልኮ ያላችሁ፣ ሙስሊሙን በታታኞች፣ የሰው ስህተት ለቃቃሚዎች….፣ ቅናተኞች” እና ሌላም ይባላል፡፡
አምባሳደር ቲያትር ቤት አቡበክር አሕመድና ካሚል ሸምሱ ባሉበት ወንድና ሴት በመጋረጃ ሳይለያዩ ተቀምጠው ነበር፡፡
አሁንም ዱባይ ላይ የአረፋ ፕሮግራም ተብሎ ሳዲቅ መሐመድ መድረክ ላይ ባለበት ወንድ እና ሴቶች ያለ መጋረጃ ተቀምጠው ነበር፡፡ ሙአዝ የተባለው ነሺዳ ባይ ወንድ እና ሴቶችን ቀላቅሎ ሰርግ ላይ አስጨፍሯል፡፡ ሙስሊሞች ሆይ! ተጠንቀቁ ይሄ መጥፎ ተግባር ነው ተብሎ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠ ነገሩን ከመንግስት ጋር ያገናኙትና “መንግስት የላካቸው”… ምናንም ብለው ከስህተታቸው ከመታረም ይልቅ በጥፋታቸው ላይ ይቀጥላሉ፡፡
እስልምናችን በአደባባይ የተሰራጨን ስህተት አይታችሁ ዝም በሉ ነው የሚለው? በፍፁም፡፡

እውነታው ይህ ነው፡፡ አህባሽን ስትቃወም ምንም ያላለህ ግለሰብ አህባሽ የሚሰራውን ስራ ሌላ ሰው ሲሰራው ተጠንቀቁት ስትል ሌላ ነገር ካለ ታገስ፡፡ ስምህንም ያጥፉት ኪሳራው በራሳቸው ላይ ነው፡፡

ይሀው የቪድዩ ማስረጃ አቅርቢያለሁ፡፡ ከማስረጃም በኋላ መሳደብን የመረጣችሁ ነፍሳችሁን ፈትሹ፡፡

አላህ እውነተኞች ያድርገን፡፡ አላህ ለእውነት ከሚቆሙ ሰዎች ያድርገን፡፡ አላህ ሆይ! ሐቅን በሐቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፡፡ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
«ቅጥረኞቹ»
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ‹‹ዘመን ይመጣል እውነተኛው ውሸታም፤ ውሸታሙ እውነተኛ የሚባልበት….››፡፡
‹‹የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር›› ይላል ተራቹ
የትኛው መንግስት ይሆን የሚከተለውን የሚሉትን (የውስጥ አዋቂው አላህ ብቻ ነው) ሰዎች ቅጥረኛ አድርጎ የሚይዘው
1) አላህን ብቻ እናምልክ በእርሱም ላይ ማንንም ይሁን ምንንም አናጋራ፤
2) ያአላህ ብቻ እንበል ከአላህ ውጭ ያለን እንራቅ፤
3) እርድን ለአላህ ብቻ እንጂ ለአልከሶ አናድርግ፤
4) ሱጁድን ለአላህ ብቻ እንጂ ለቃጥባሪ ቀብር አይደረግ፤
5) ጠዋፍን ካዕባ ላይ ብቻ እና ለአላህ ብቻ ይደረግ ለኑርሁሴን ቀብር አይደረግ፤
6) ጌታችን አላህ ከፍጡራኑ ሁሉ በላይ ከአርሽ በላይ ነው፤
7) የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱናን አጥብቀን እንያዝ፤ ከቢድዓ ሁሉ በአይነታው እንራቅ፤
8) የሽርክ መናሃሪያ የሆነውን ‹‹መውሊድ›› እንራቀው የእሳት መንገድ ነውና፤
9) ሰሃባዎች ክብራቸው ይከበር አይሰደቡ፤
10) ወለድን እንራቅ፤
11) ሴቶች አላህ እና መልክተኛው የረገሙትን ‹‹ቅንድብ መቀንደብ እና ማስቀንደብ፤ ዊግ መቀጠል እና ማስቀጠል፤ ንቅሳት መንቀስ እና ማስነቀስ›› ትተው ‹‹አላህ የሰውን ልጅ ባማረ ሁኔታ ፈጠርነው›› ብሏል የአላህን ያማረ አፈጣጠር አታበላሹ፤
12) ወንድ እና ሴት ለኢስላም ነው እየተባለ አይደባለቁ፤ ኢስላም አላህን በማመፅ አይረዳም፤
13) ወንዶች ጀመዐ ሰላት ግዴታ ተደርጎብናል፤ ኳስ እያልን የአላህን ቤት ጭር አናድርግ፤
14) በዲን እና ዲንን በተሸከሙ ሰዎች ላይ ማላገጥ ይቅር፤
15) መስጂዶችን የድራማ ሰሪ እየተባለ የአጅነቢ ወንድ እና ሴቶች ፎቶ አይለጠፍባቸው፤
16) ድራማ እና ፊልም የሚባል ነገር በኢስላም የለም፤
17) ጫት የሚባል ነገር የኢስላም አካል አይደለም፤ ሙስሊሞችን የሚያሽመደምድ፤ የሚያደነዝዝ እንጂ፤
እና የመሳሰሉትን የሚሉ መንግስት ቅጥረኛ አድርጎ ይይዛል ተብሎ ሲነገርህ እንዴት ታምናለህ???
ምክንያቱም የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በመልክተኝነት ከመላካቸው በፊት ‹‹ሙሃመዱል አሚን (ታማኙ ሙሃመድ)›› ነበር ስማቸው፡፡ አንድ አላህን ብቻ ተገዙ፤ ከእርሱ ውጭ ያሉትን ሁሉ (ስም ጠቅሰው ላትን፤ ኡዛን፤ ኢሳን፤ መላኢካን፤ ጂንን) ራቁ፤ እኔም የአላህ መላክተኛ ነኝ ሲሉ የሚከተሉትን ተባሉ ስማቸውን ለማጥፋት
‹‹እብድ፤ ገጣሚ፤ ድግምተኛ……. በታታኝ››
ታድያ ነብያት የተላኩበትን መንገድ እነሱ ባሳዩት መንገድ የሄደ፤ ማንኛውንም አይነት መንገድ ተጠቅመው ሰዎች ስሙን ቢያጠፉት እንዳይገርመው እና እንዳይሰማው ይሄ መንገዳቸው ነውና፡፡ ዋናው መገንዘብ ያለበት ነብያት በሄዱበት መንገድ መጓዙን ብቻ እና ብቻ ነው፡፡
እንደየዘመኑ ማስበርገጊያው ይለያያል፡፡
አላህ ብቻ ይመለክ ያለን ‹‹አማልክቶቻችንን የሚሳደብ፤ ነብያችንን የማይወድ፤ ወልዬችን የማይወድ››፤ ወደ እውነተኛው አንድነት የሚጣራውን ‹‹በታታኝ››፤ እና የመሳሰለውን ይሉታል ታድያ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ‹‹ዘመን ይመጣል እውነተኛው ውሸታም፤ ውሸታሙ እውነተኛ የሚባልበት….››፡፡
ሰው መቼም ፍርድ የሚሰጠው ከላይ በሚያየው ነው፤ የውስጥ አዋቂው አላህ ብቻ ነው፡፡ ሰዎች ከሚያወሩት ድፍረት ውስጥ ወደ ተውሂድ እና ሱና የሚጣሩ ሰዎችን ‹‹ሙናፊቆች›› ብለው መጥራታቸው ነው፡፡ የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንኳን ሙናፊቆችን አላህ ያሳወቃቸውን ብቻ ነበር የሚያውቁት፡፡ ዛሬ ውስጥ አዋቂ ይመስል ቢድዐውን ስታጋልጥበት ‹‹ሙናፊቅ›› ብሎ ታፔላውን ይለጥፍብሃል፡፡ ነገ አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ፍርድ በሚጠይቅበት ቀን ምን ይሆን የሁላችንም መልስ?
የአላህ ባርያዎች ሆይ! ሚዛን ይኑረን፡፡ እኛ ፍርድ የምንሰጠው ከላይ በምናየው ነው፤ አላህ ውስጥ አዋቂ ነው፡፡ ከላይ የተዘረዘሩትን ሁሉ በአቅማቸው ልክ የሚሰሩ ወንድም እና እህቶችን ‹‹ቅጥረኛ እና ሙናፊቅ›› ይላሉ፡፡ አላህ ከቅጥረኝነት እና ኒፋቅ ይጠብቀን ሁላችንንም፡፡ እውነት እንዲህ አይነት ቅጥረኛ አለ? የሙናፊቅነትን ጉዳይ አላህ ብቻ አይደለምን የሚያውቀው?
አላህ እንዲህ ይላል
فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُۥ
የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡
وَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ شَرًّا يَرَهُۥ
የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡

የአላህ ባርያዎች ሆይ! ለነፍሳችን እንዘንላት፡፡ ያለ ማስረጃ በደመነፍስ እና በስሜት የተነገረን ሁሉ ሰምቶ ማራገብ ነገ አላህ ፊት ከተጠያቂነት አያድንም፡፡ አላህ ፊት ደግሞ ተጨባጭ ማስረጃ ከሌለ ኪሳራው ከባድ ነው፡፡

አላህ ሃቁን ይምራን፡፡ አላህ ሆይ! ሃቅን በሃቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፤ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በባልደረቦቻቸው፤ ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
እንዳትጠራጠር!!!!

ሃቅ ላይ መሰባሰብ፤ ተውሂድ እና ሱናን ማንገስ፤ ሽርክ እና ቢድዓን ማውገዝ፤ ለህዝቦች የሽርክ እና የቢድዐን ክፋት ዘርዝሮ መናገር ነው ዋናው እንጂ የዚህ ዲን ረዳት አላህ ነው፤ ከእኛ በአቅማችን የሚጠበቀውን እስከሰራን ድረስ፡፡
እንዳትጠራጠር

1) ኑህ (አለይሂ ሰላምን) አላህ ከጥቂት አማኖች ጋር እና ከእንስሳ ጥንድ ጥንድ እዛች መርከብ ላይ ወጥቶ ከአላህ ቅጣት ተጠብቀው ነጃ የወጡት በተውሂድ፤ በሱና፤ በኢማን ነው፡፡

2) ኢብራሂም (አለይሂ ሰላም) እሳት ውስጥ ተወርውሮ፤ መላው ማህበረሰብ እርሱን ለመግደል ያውም በእሳት ለማቃጠል ሲሉ፤ የሁሉ ነገር ባለቤት የሆነው አላህ፤ ኢብራሂምን ነጃ ያወጣው በእምነቱ በተውሂድ ምክንያት ነው

3) ሉጥ (አለይሂ ሰላምን) ከነዛ ሙጅሪም ከሆኑ ማህበረሰብ ተንኮል አቅሙ ያነሰ የነበረ ቢሆንም አሸናፊ የሆነው አላህ በእምነቱ ነጃ አወጣው

4) ሙሳ እና ሃሩን (አለይሂሙ ሰላም) ከበኒ ኢስራኤሎች ጋር፤ ከጨቃኙ የሃይል ባለቤት፤ አምላጋችሁ፤ ጌታችሁ ነኝ ሲል ከነበረው ፊርዓውን ነፃ አውጥቶ፤ ድልን ያጎናፀፋቸው፤ ተውሂድን አንግበው ሽርክ እና ጥንቆላን ያወገዙ ስለነበር ነው፡፡

5) እነ ሹዓይብን፤ እነ ሷሊህን፤ እነ ሁድን (አለይሂ ሰላም) አላህ ነጃ ያወጣቸው የእምነት ባለቤቶች ስለ ነበሩ ነው፡፡

6) ኢሳ (አለይሂ ሰላምን) ህዝቦቹ ተሰብስበው ሊገድሉት ሲሉ፤ አላህ እንዲያርግ ያደረገው በእምነቱ በተውሂድ ምክንያት ነው፡፡

7) ዩኑስ (አለይሂ ሰላም) የአላህን ተውሂድ አረጋግጠው ነው፤ ከአሳነባሪው ሆድ ውስጥ የተተፉት እና ነጃ የወጡት

8) የሰው ልጆች ሁሉ ምርጥ፤ ነብዩ ሙሃመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከ313-317 ያሉ ሰሀባዎቻቸውን (መሳሪያም ስንቅም ጥቂት የነበራቸው) ይዘው ከ1000 በላይ ሙሽሪኮችን (መሳሪያ እና ትጥቃቸው ብዙ የነበሩትን) ድል እንዲጎናፀፉ ያደረጋቸው፤ ተውሂድን ያረጋገጡ ሽርክን ያልደባለቁ፤ የነብዩን ሱናን ያነገቡ ቢድዓን የራቁ ትውልዶች ስለ ነበሩ ነው፡፡

እንዳትጠራጠር!!!!

ታድያ ወደራሳችን እንመለስ
1) የሽርክ እና ቢድዐ መዓት ሙስሊም ነን የሚለው ማህበረሰብ ይፈፅማል፡፡ ሽርክ እና ቢድዐውን እያየ ዝም የሚለውም በዝቷል

2) በወለድ ይሰራል

3) ዝሙት ይፈፀማል

4) ኳስ እና ሙሰልሰል እያለ ጊዜውን የሚጫወትበት ሙስሊም በዝቷል

5) ኢስላማዊ ፊልም እና ድራማ እየተባለ ነብያትን፤ ሰሃባዎችን፤ ኡለማዎችን ክብራቸውን የሚያጎድፍ ፊልሞች ይሰራሉ

6) ሰሃባዎች የሚሰደቡበት ኪታብ እኛው ኢትዬጵያ ውስጥ ነው ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚታደለው

7) ሴት ልጅ ቅንድቧን ተቀንድባ በየካፊቴሪያው ከወንዶች ጋር ኩጭ የሚባለው ኢትዬጵያ ነው

8) ወንዶች በየጫት ቤቱ እየተቀመጡ ገንዘባቸውን እየጨረሱ ትዳራቸውን የሚጎዱ ብሎም የሚበትኑት ይሀው ኢትዬጵያ ነው

9) ለኢስላም ለመስራት እና ለመወያየት ነው እየተባለ ወንድ እና ሴቶች ‹‹የተማሩ›› እየተባሉ ያለ ዲን እውቀት ኢስላምን የሚጋጭ ያለ እውቀት ኡማ ሆቴ፤፤ ምናምን ሆቴል እየተባለ ያለ መጋረጃ የሚያወሩት እዚሁ ኢትዬጵያ ነው

10) እናት እና አባትን አለመታዘዝ እና እነርሱን መጨቃጨቅ ያለው ኢትዬጵያ ውስጥ ነው

እኛ ዘርፈ ብዙ ችግሮች አሉብን፡፡ ዋና እና ዋናው ሽርክ እና ቢድዐ ነው፡፡ እርሱን እንቅረፍ፤ እንማር እናስተምር እንጂ ለተቀረው አላህ ይሰራዋል፡፡
እኛ እራሳችንን እንሳተካክል፤ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቃልን እና ሱናን ለሰው ስንል አንተወው፤ አላህ ያስቀመጠውን ሃቅ ሁላችንም እንተግብር፡፡ አላህ እንደው ሚዛኑን አስቀምጧል፤ የእኛ መብት ሊከበር የሚችለው በዋናነት የአላህ መብት የሆነው ተውሂድን አጥበቀን ስንይዝ ነው፡፡

የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መካ ላይ ተውሂድን ባገኙት አጋጣሚ እና መድረክ ተውሂድን ሲያስተምሩ መስጂድ አልነበራቸውም፡፡ ጥያቂ በሰላሙም ግዜ መስጂዶች በእጃችን በነበሩ ግዜ ስለ ተውሂድ ትምህርት በሰፊው እና በሚጠበቀው መንገድ ትምህርቱ ተሰጥቷል ብሎ ለመናገር አያስደፍርም፡፡ አልተሰጠም ባይባልም፤ የሚገባውን ያህል ተሰጥቷልም አይባልም፡፡ አሁንም አረፈደም ሰዓቱ፤ የተውሂ ትምህርቶችን ዳውን ሎድ በማድረግ ለሰዎች በማሰራጨት፤ አለ የሚባለውን ሚድያ መጠቀም ነው፡፡ አንዳንድ ወንድሞች እና እህቶች ፌስ ቡክን እና ዋትስ አፕን ምን ያህል ሰው ይጠቀመዋል ይባላል፡፡ ልብ ካልን ፊስቡክ እና ዋትስ አፕን ተጠቅሞ አይደል እንዴ የኢንፎርሜሽን መዓት ለህዝቡ እየተሰራጨ ያለው፤ ታድያ ለምን ተውሂድ ሲሆን ይህን ሰበብ መጠቀም አስፈለገ፡፡ ሌላው ፊስቡክ እና ዋትስ አፕ ብቻ አልተባለም፤ አሉ የሚባሉ ኢንፎርሚሽን የሚተላለፍባቸውን ሬድዩ ጣብያዎች፤ ቻናሎች፤ በራሪ ወረቀቶች፤ መቼም በነዚህ እንሞክር እና ከልባችን አዛኙ አላህ እንየዋለን ምን ያህል እንደሚያሰራጨው፡፡

ከዛም በአላህ ፍቃድ የእኛም መብት ይከበራል፡፡

በነብያት መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው፤ ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ የአላህ ሰላት እና ሰላም ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ከተዋሸብኝ ውሸት በጥቂቱ መልስ ልስጥ
‹‹ሳዳት ከማል ከአገር ውስጥ አልፎ፤ የውጭ አገር ኡለማዎችን ይሳደባል››
ኡማውን የሚያከፍር፤ የአላህ ሰም እና ባህሪያትን ውድቅ የሚያደርግ፤ ሰሃባዎችን የሚሳደብ ኡለማ አይታችሁ ታውቃላችሁን?

እስቲ የአላህ ባርያዎች ሆይ! ጥቂት እንበል በአላህ ፈቃድ፡፡ ከጥንት ጀምሮ እንደሚታወቀው የጥመት አራማጆች የያዙትን ጥመት ስሙን ቀይረው ጥሩ አስመስለው ያቀርቡታል፡፡ ሃቅን ደግሞ በመጥፎ ስም ይጠሩታል፡፡
ጥቂት ምሳሌዎች
1) የመካ ሙሽሪኮች ሽርካቸውን ‹‹ወደ አላህ መቃረቢያ፤ አማላጆቻችችን›› ብለው ጠሩት
2) ረሱል (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ‹‹ድግምተኛ፤ አባት እና ልጅን የሚለያይ›› እና የመሳሰሉትን፡፡ ልብ በል ወደ ተውሂድ እና ሱና ሲጠሩ የዚህ ዘመኖቹም ‹‹አንድነት አትበታትኑ ይላሉ›› ጥያቂ ከተውሂድ እና ሱና ውጭ አንድነት አለን?

ወደ ጥያቂው እንምጣ እና ‹‹ኡለማ ይሳደባሉ›› ለተባለው መልስ መስጠት እፈልጋለሁ፡፡
አሊም ማለት ምን ማለት ነው?

አላህን የሚፈራ፤ ቁርዓን እና ሀዲስን አጥብቆ የሚይዝ፤ የሰሃባዎችን መንገድ የሚከተል፤ ሰሃባዎችን የሚያከብር እንጂ የአላህን ስም እና ባህሪያት ውድቅ የሚያደር፤ ኡማውን በጅምላ የሚያከፍር እና ሰሃባዎችን የሚተች አይደለም፡፡

‹‹ሳዳት ከማል ከአገር ውስጥ አልፎ፤ የውጭ አገር ኡለማዎችን ይሳደባል›› ተብሎ በዋናነት ተሳደብኩ ልባል የሚቻለው ‹‹ሰይድ ቁጡብ›› የሚባለውን ጋዜጠኛ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ‹‹ኡለማ፤ ሸሂድ›› ብለው ይጠሩታል፡፡ እስቲ እውነት ይህ ሰው ያሉበትን ችግሮች በግልፅ እናስቀምጥ እና ይህን ሰው ስህተቱን በግልፅ እንየው፤

1) ኡማውን በጅምላ ማክፈሩ፤ የ21 ክፍለ ዘመን የተክፊር መሪ ነው፡፡ ይህንንም ስንል እንደተለመደው በማስረጃ ነው፡፡
• ‹‹በእርግጥ በምድር ላይ ሸሪዐና ፊቅህ መመሪያው የሆነ አገርም ሆነ ማህበረሰብ የለም›› (ዚላል አል-ቁርዐን 4/2122)
• ‹‹በእርግጥ ይህ እየኖርንበት ያለው የጃሂልያ ማህበረሰብ የሙስሊም ማህበረሰብ አይደለም›› (ዚላል አል-ቁርዐን 4/2009)
• ‹‹ዛሬ ጃሂልያ ላይ ነን፡፡ የአላህ መልክተኛ ከመላካቸው በፊት ወደ ነበረው ፤ እንዲያውም ከዚህ በባሰ ዙሪያችን በጠቅላላ ጃሂልያ ነው›› (መዓሊም ፊጠሪቅ ገፅ 21. 17 እትም፣ 1991)
• ከላይ ያነበባችኋቸውን 3 የሰይድ ቁጡብ አባባሎች ኡመተል ኢስላምን ማክፈር አይደሉምን?

የሚከተሉት የነብያችን አባባል፤ የሰይድ ቁጡብን አባባል ውድቅ ያደርገዋል፡፡ ‹‹በኔ መላክ ትልቁ ጃሂልያ ተወግዶላችኋል›› ‹‹ከኔ ኡመት ሀቅ ላይ እና የበላይ የሆነች ቡድን አትጠፋም፤ እነሱን የሚቃወማቸውም አይጎዳቸውም……›› የሚሉት ሀዲሶች ኡመተል ኢስላም ሙሉ በሙሉ ጨርሶ ከሳቸው መላክ በኋላ ሊጠም እና ጃሂልያ ውስጥ ሊገባ እንደማይችል ይጠቁማል፤ ከጀማዓተ አተክፊር የመጣ አመለካከት እንጂ እስልምና ውስጥ ተቀባይነት የሌለው ፍልስፍና ነው፡፡

ድንገት ይህ ከላይ ያያችሁትን ተክፊር አይደለም ይሉ ይሆናል፡፡ እስቲ የገዛ የራሳቸው ፖለቲካ ፓርቲ ተከታይ የሆነው ዩሱፍ አልቀርዳዊ፤ ሰይድ ቁጥብ ወደ ተክፊር እንደሚጣራ እና በጅምላ እንደሚያከፍር እንዲህ ሲል ይመሰክርበታል፡፡

ዩሱፍ አልቀርዳዊ እንደ ዩሮፒያን አቆጣጠር 4 May 2004 ላይ ‹‹ሀል ዩከፊር “ሰይድ ቁጡብ” ሙስሊመል የውም? (ሰይድ ቁጡብ የዛሬ ሙስሊሞችን ያከፍራቸዋል ወይ?)›› በማለት ከታተመ አርቲክል የተወሰደ፡፡ ሰይድ ቁጡብ ስላለበት የተክፊር አስተሳሰብ እንዲህ ሲል ይገልፃል
ዩሱፍ አልቀርዳዊ ከሰይድ ቁጡብ ዚላል (7/269) የሆኑ ያህል መስመሮችን ጠቅሶ የሚከተለውን ተናገረ፡፡

‹‹ፅሁፉ ግልፅ ነው፡፡ ፀሃፊው (ቁጡብ) ማንንም ሙስሊም አይልም የሱን ሀሳብ ከሚከተሉት ውጪ፤ ይህንንም ቡድን የሙስሊም ግንባር በሎ ይጠራዋል፡፡ ይህም ቡድን እራሱን ብቻ የሙስሉሙ ኡማ ነው ብሎ ማሰብ አለበት፤ ይህንን ቡድን ያካበበው ምንም ይሁን ማን እዚህ ጀመዐ ውስጥ ያልገቡ ሁሉ ጃሂልያ ናቸው፤ ሰዎቹም የጃሂልያ ሰዎች ናቸው፡፡ ማለትም ሙሽሪክና ካፊር ናቸው ከእስልምና ምንም ድርሻ የላቸውም ቢሰግዱም፤ ቢፆሙም፤ ዛካ ቢሰጡም ሃጅ ቢያደርጉም፡፡ ይህም ማለት ሁሉም ሙስሊሞች ከመካ ሙሽሪኮች ጋር አንድ ናቸው ነብያችን የተላኩበት ወቅት የነበሩት እንደማለት ነው፤ የሱም ዳዕዋ ከነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዳዕዋ ጋር እኩል ነው እንደማለት ነው፤ በዛ ዳዕዋ ያመነ (ቁጡብ በሚያምንበት) ወደ እስልምና ይገባል፤ ያላመነም ጃሂልያ፤ ካፊር ነው፤ ደሙንም ማፍሰስ ይበቃል››፡፡ ያነበባችሁት የዩሱፍ አልቀርዳዊ ከኢኽዋን አባሎች ዋናዎቹ ውስጥ አንዱን ነው፡፡ ሰይድ ቁጡብ የሚናገራቸው ሁሉ ‹‹የኸዋሪጅ መንገዶች ናቸው (የሙስሊምን ደም ሀላል ማድረግ፤ ልክ ኸዋሪጆች የሰሃባዎችን ደም ሃላል እንዳደረጉት)››

አሁንም ዩሱፍ አልቀርዳዊ ‹‹አውለዊያት አል-ሀረካቲል ኢስላሚያ (የእስልምና እንቅስቃሴዎች ተቀዳሚያቸው)›› በሚባለው መፀሃፉ ገፅ 110 ላይ እንዲህ ይላል

‹‹በዚህም ወቅት ነበር የሸሂድ ሰይድ ቁጡብ መፀሀፎች ብቅ ያሉት የመጨረሻ ሃሳቦቹን የያዙት፡፡ የኡማውን በጠቅላላ መክፈር የሚያረጋግጡ የሆኑት …. የሰው ልጅን በጠቅላላ የተወገዘውን ጂሃድ እነሱ ላይ ማወጅ …፡፡ ይህንን በግልፅ መዐሊም ፊጠሪቅ፤ ፊዚላሊል ቁርዐን እና አል-ኢስላም ወሙሻኪላት አል-ሃዳራሀ በሚባሉ መፀሃፎቹ ላይ አስቀምጧቸዋል››፡፡ ከምስክርነቱ አልፎ የተሰመረበትን ቃል ልብ ብለዋል ሸሂድ፤ የአላህ መልክተኛ በግልፅ ኢማሙ ቡኻሪ በዘገቡት ሀዲስ ላይ ‹‹እገሌ ሸሂድ ነው አትበል›› ብለዋል፡፡

ይህ ነው የሰይድ ቁጡብ ተክፊር፡፡ ኡማውን በጅምላ ሲያከፍር፡፡ የሱን ኪታቦች ኢትዬጵያ ላይ በተለይ በዩኒቨርሲቲ አካባቢ ላሉ ተማሪዎች ሲያሰራጩት ነበር፡፡ ለዛም ሲባል፤ ይህ ሃቅ ሲጋለጥ ያላቸው አማራጭ፤ አሁንም መጥፎውን ጥሩ አድርገው ማቅረብ ነው፡፡ ሰይድ ቁጡብ ‹‹ሸሂድ ኡለማ ነው›› ብለው ይናገራሉ፡፡ ሸሂድ የሆነውን አላህ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡

2) ሰሃባዎችን ማጣጣሉ እናም ብሎ ኡስማን ኢብን አፋን (ረድየላሁ አንሁ) ላይ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት እያደነቀ መፃፉ፤ እነዚህን ሁሉ አዳለቱል ኢጅቲማእያ የሚባለው ኪታቡ ላይ ይገኛሉ፡፡
ጋዜጠኛው ሰይድ ቁጡብ አረብኛን ስለቻለ እና ጋዜጠኛ ስነ ነበረ ብቻ፤ ዲንን ሳይማር ዝም ብሎ ከስሜቱ እና ከቢድዐ ‹‹ሺዐ፤ ረዋፊዳ›› እምነት ተነስቶ ታላቁ ሰሃባ ላይ ኡስማን ኢብን አፋን (ረድየላሁ አንሁም) ላይ የሚከተሉትን አዳለቱል ኢጅቲማኢያ የተባለ መፀሃፉ ላይ አስፍሩዋል፡፡

1)‹‹አልይ ሶስተኛው ኸሊፋ አለመሆኑ ፊትና ነበር›› (ገፅ 191 5ኛው እትም፤ 162 12ኛው እትም)
ይህ እንደሚታወቀው ከሺዐ ክፍል ውስጥ ከሆኑት ውስጥ የአንዳቸው እምነት ነው፡፡ ታላቁ ሰሃባ አብደላህ ኢብን መስኡድ (ረድየላሁ አንሁም) ኢማሙ ቡኻሪ በዘገቡት ሰሂህ ሀዲስ እንዲህ ይላል ‹‹በነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘመን ከነብያችን ቀጥሎ ምርጥ ሰው አቡበክር ነው፤ ከዛም ኡመር ነው፤ ከዛም ኡስማን ነው እንል ነበር››፡፡ ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ልክ ባይሆን ኖሮ ይህ አባባል በዝምታ አያረጋግጡትም ነበር፡፡ ሰይድ ቁጡብ ‹‹አልይ ሶስተኛው ኸሊፋ አለመሆኑ ፈተና ነበር›› ሲል፤ ፈተናው ለማን ነው፡፡ ለሙስሊሞች፤ ለሱኒዬች ወይንስ ለራፊዳዎች???
ኢብን ኡመር (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንዲህ ይላሉ ‹‹የአላህ መልክተኛ (ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) በነበሩበት ወቅት በሰዎች መሃል እናበላልጥ ነበር፤ አቡበክርን ከዛ ኡመርን ከዛ ኡስማንን እንመርጥ ነበር›› ኡማሙ ቡኸሪ

2)ኡስማን የመራው ዘመን በሁለቱ ሸሆች (አቡበክር እና ኡመር) እና በአልይ መሃል የነበረ ክፍት ዘመን ነው (ገፅ 206 5ኛው እትም)

ሰይድ ቁጡብ ምን ለማለት ፈልጎ ነው??? ይህ ጋዜጠኛ ማን ሆኖ ነው ኡስማን የመራው ዘመን ክፍት ዘመን ነው የሚለው??? እውነታው ግን ሰይድ ቁጡብ እንደሚለው ሳይሆን፤ ታላቁ ሰሃባ አብደላህ ኢብን መስዑድ ኡስማን ስልጣን ላይ ሲወጣ እንዲህ አለ ‹‹ከቀሩት ውስጥ ምርጣችንን ነው የመረጥነው፤ ምርጣችንንም በመምረጥ ላይም አልተሳሳትንም›› (አጠበቃት አል ኩብራ 3/63)

ሌላው ኡስማን የሰራውን አደለም ኸሊፋ ሆኖ፤ ከኸሊፋነት በፊት በሰራው ስራ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ

በነብያችን አንደበት ኡስማን ኢብን አፋን የተቡክ ዘመቻን ሲወጡ 100 ግመል በመስጠቱ የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል ‹‹ኡስማን የሰራውን ቢሰራ ከዚህ በኋላ አይጎዳውም››
ታድያ ወገኖቼ የነብያችንን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ወይንስ የራፊዳ፤ ሺዓዎች፤ የቢድዓ አራማጆችን የንፍቅና ንግግር???????????????????????????????????????????????????????????????????????????????

3)የሚያሳዝነው ኡስማን ለኸሊፋነቱ የደረሰው ሽማግሌ እና ወኔው በደከመበት ሰዐት ነው፤ ለእስልምናም የሚፈለገውን ግብ መድረስ አልቻለም (ገፅ 186 5ኛው እትም)
እንደ ሰይድ ቁጡብ እና እንደ ሙናፊቆች አመለካከት የእስልምና ግብ ምን ማለት ይሆን?????????? ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አይደሉ እንዴ ‹‹የኔን እና የቅን ምትኮቼን (ኹለፋኡ ራሺዲን) ፈለግ ተከተሉ ያሉት››??????

ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አይደሉ እንዴ ለኡስማን ኢብን አፋን ልጃቸውን ኡሙ ኩልሱምን ዳሩለት ሞተችበት፤ ሩቅያን ዳሩት ሞተችበት፤ ካዛ ም እንዲህ አሉ ‹‹ሶስተኛ ቢኖረኝ እድርህ ነበር›› ነብያችን ለዚህ ታላቅ ሰው ልጃቸውን እንዲህ የዳሩለት፤ ፍትሃዊነቱን፤ ቅንነቱን እና ታላቅ ሰውነቱን አይተው አይደለምን??????????????????????????????

4)ኡስማን ላይ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስትና የግፍ ግድያ በማድነቅ እንዲህ ይላል ‹‹በእስልምና እይታ ላየው፤ መፈንቅለ መንግስቱ በአጠቃላይ የእስልምና መንፈስ ነበረው›› (ገፅ 160-161)
እንግዲህ ልብ በሉ፤ ኡስማንን የገደሉት ኸዋሪጆች እነዛ የጀሃነም ውሻዎች ናቸው፤ ግድያውን ያቀናበረው ደግሞ አብደላህ ኢብን ሰባዓ አል የሁዲ (ላዕነቱላኢ አለይሂ) ነው፡፡ ሌላ ማብራሪያ አያስፈልግም ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ስለ ኡስማን ፈተና አስመልክተው የተናገሩትን እና የኡስማን ገዳዬች እነማን እንደሆነ ሲተነብዩ እንዲህ ይላሉ

• የአላህ መልክተኛ ከአቡበክርን፤ከኡመርን እና ከኡስማን ጋር እሁድ ተራራ ላይ በወጡበት እሁድ ተንቀጠቀጠች የአላህ መልክተኛው በእግራቸው በታ አደረጓትና እንዲህ አሉ ‹‹የያዝሽው እኮ ነብይ፤ ሲዲቅ እና ሸሂዶች ነው››፡፡ ሲዲቁ አቡበክር ሲሆን ሸሄዶች ኡመርና ኡስማን ናቸው

• ኡስማን ያለ አግባብ እንደሚገደል የአላህ መልክተኛ ተናግረዋል፡፡ አብደላህ ኢብን ኡመር እንዲህ ይላል የአላህ መልክተኛ ‹‹ፊትና እንደሚመጣና እንደሚያልፍ ተናገሩ፡፡ ከዚያም ፊቱን የተሸፈነው ሰው በግፍ ይገደላል አሉ›› ሙስነድ ኢማሙ አህመድ 2/115

• ከዐብ ኢብን ኡጅራ እንዲህ ይሉናል፤ የአላህ መልክተኛ ፊትና እንደሚመጣና ወዲያውም እንደሚያልፍ ተናገሩ፡፡ አንድ ጭንቅላቱን የተሸፈነ ሰው አለፈ የአላህ መልክተኛም ‹‹ያን ቀን ይህ ሰው ሀቅ ላይ ነው›› እየሮጥኩ ሄጄ የኡስማንን እጅ ይዤ ወደ አላህ መልክተኛ አዞርኩና ‹‹ይህ ሰው›› ብዮ ጠየኳቸው አሳቸውም ‹‹አዎን እሱ›› አሉኝ፡፡ (ሰሂህ ሱነን ኢብን ማጃህ 1/24 (111))

• የምእመናን እናት አኢሻ (አላህ ስራዋን ይውደድላትና) እንዲህ ትላለች የአላህ መልክተኛ ኡስማንን አስጠርተው አዋሩት …… የመጨረሻ ንግግራቸው ጀርባውን ይዘው እንዲህ አሉት ‹‹ኡስማን ሆይ አላህ ኩታን ያለብስሃል (ስልጣንን) ሙናፊቆቹ አውልቀው ካሉህ እኔን እስክትገናኘኝ እንዳታወልቀው፡፡ኡስማን ሆይ አላህ ኩታን ያለብስሃል ሙናፊቆቹ አውልቀው ካሉህ እኔን እስክትገናኘኝ እንዳታወልቀው፡፡ኡስማን ሆይ አላህ ኩታን ያለብስሃል ሙናፊቆቹ አውልቀው ካሉህ እኔን እስክትገናኘኝ እንዳታወልቀው፡፡›› ሙስነድ ኢማሙ አህመድ፡፡

ጥያቄ ሰይድ ቁጡብ የት ነው ያለው የአላህ መልክተኛን ቃል በመቃወም ላይ ‹‹በእስልምና እይታ ላየው፤ መፈንቅለ መንግስቱ በአጠቃላይ የእስልምና መንፈስ ነበረው›› የሙናፊቆች ግድያ እንዴት እስላማዊ መንፈስ ይኖረዋል?
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ይህ ነው የሰይድ ቁጡብ እውነታ፡፡ ሰይድ ቁጡብ ፅፏል ብቻ ሳይሆን መባል ያለበት፤ የፃፈው ምንድን ነው መባል አለበት፡፡
ነብያችን እና ሰለፎች ስለ ኡስማን ኢብን አፋን (ረድየላሁ አንሁም) ምን ይላሉ
• ኡስማን የጀነት ነው
• አንድ ቀን ቤት ውስጥ በተቀመጡበት ታፋቸው ተገልፆ ነበር፤ አቡበክር ገባ አልሸፈኑትም፤ ኡመር ገባ አልሸፈኑትም፤ ኡስማን ገባ ሸፈኑት ተጠየቁ ለምን እንዳደረጉ፤ እሳቸውም እንዲህ አሉ ‹‹ኢስማንን አደለም በምድር ያለ በሰማይ ላይ ያለ መላኢካ ያፍረዋል››
• ነብያችን ለኡስማን 2 ሴት ልጃቸውን መዳራቸው ቅፅል ስሙም ‹‹ዙኑረይን›› የሁለቱ ኑሮች ባለቤት፤ አንዷን ድረውት ስትሞት ሌላኛዋን ሰጡት፡፡ አንድ ነብይ ሁለት ሴት ልጁን ሲሰጥ በሰው ልጆች ታሪክ ታይቶ አይታወቅም፡፡ እንዲያውም ሶስተኛ ቢኖረን እንደግምህ ነበር ብለውታል ይባላል
• በነብያችን አንደበት ኡስማን ኢብን አፋን የተቡክ ዘመቻን ሲወጡ 100 ግመል በመስጠቱ የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል ‹‹ኡስማን የሰራውን ቢሰራ ከዚህ በኋላ አይጎዳውም››
• የአላህ መልክተኛ እንዲህ አሉ ‹‹ትናንት ማታ መልካም ሰው ታየ (በህልም) እናም አቡበክር ከአላህ መልክተኛ ጋር፤ኡመር ከአቡበክር ጋር እና ኡስማን ከኡመር ጋር የተያያዙ ናቸው›› ጀሪር ኢብን አብዲላህ (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው) እንዲህ ይላሉ ‹‹የአላህ መልክተኛን ተለይተን ስንሄድ እንዲህ አልንመልካሙ ሰው የአላህ መልክተኛ ናቸው፤ አንዱ ባንዱ መተሳሰራቸው አላህ መልክተኛውን በላከበት ጉዳይ ላይ ሀላፊ ይሆናሉ›› (ሱነን አቢ ዳውድ 2/513)
• ኡስማን ስልጣን ላይ ሲወጣ አብደላህ ኢብን መስዑድ እንዲህ አለ ‹‹ከቀሩት ውስጥ ምርጣችንን ነው የመረጥነው፤ ምርጣችንንም በመምረጥ ላይም አልተሳሳትንም›› (አጠበቃት አል ኩብራ 3/63)
• የአላህ መልክተኛ ከአቡበክርን፤ከኡመርን እና ከኡስማን ጋር እሁድ ተራራ ላይ በወጡበት እሁድ ተንቀጠቀጠች የአላህ መልክተኛው በእግራቸው በታ አደረጓትና እንዲህ አሉ ‹‹የያዝሽው እኮ ነብይ፤ ሲዲቅ እና ሸሂዶች ነው››፡፡ ሲዲቁ አቡበክር ሲሆን ሸሄዶች ኡመርና ኡስማን ናቸው
• ኡስማን ያለ አግባብ እንደሚገደል የአላህ መልክተኛ ተናግረዋል፡፡ አብደላህ ኢብን ኡመር እንዲህ ይላል የአላህ መልክተኛ ‹‹ፊትና እንደሚመጣና እንደሚያልፍ ተናገሩ፡፡ ከዚያም ፊቱን የተሸፈነው ሰው በግፍ ይገደላል አሉ›› ሙስነድ ኢማሙ አህመድ 2/115
• ከዐብ ኢብን ኡጅራ እንዲህ ይሉናል፤ የአላህ መልክተኛ ፊትና እንደሚመጣና ወዲያውም እንደሚያልፍ ተናገሩ፡፡ አንድ ጭንቅላቱን የተሸፈነ ሰው አለፈ የአላህ መልክተኛም ‹‹ያን ቀን ይህ ሰው ሀቅ ላይ ነው›› እየሮጥኩ ሄጄ የኡስማንን እጅ ይዤ ወደ አላህ መልክተኛ አዞርኩና ‹‹ይህ ሰው›› ብዮ ጠየኳቸው አሳቸውም ‹‹አዎን እሱ›› አሉኝ፡፡ (ሰሂህ ሱነን ኢብን ማጃህ 1/24 (111))
• የምእመናን እናት አኢሻ (አላህ ስራዋን ይውደድላትና) እንዲህ ትላለች የአላህ መልክተኛ ኡስማንን አስጠርተው አዋሩት …… የመጨረሻ ንግግራቸው ጀርባውን ይዘው እንዲህ አሉት ‹‹ኡስማን ሆይ አላህ ኩታን ያለብስሃል (ስልጣንን) ሙናፊቆቹ አውልቀው ካሉህ እኔን እስክትገናኘኝ እንዳታወልቀው፡፡ኡስማን ሆይ አላህ ኩታን ያለብስሃል ሙናፊቆቹ አውልቀው ካሉህ እኔን እስክትገናኘኝ እንዳታወልቀው፡፡ኡስማን ሆይ አላህ ኩታን ያለብስሃል ሙናፊቆቹ አውልቀው ካሉህ እኔን እስክትገናኘኝ እንዳታወልቀው፡፡›› ሙስነድ ኢማሙ አህመድ፡፡

ጥያቄ ሰይድ ቁጡብ የት ነው ያለው የአላህ መልክተኛን ቃል በመቃወም ላይ ‹‹በእስልምና እይታ ላየው፤ መፈንቅለ መንግስቱ በአጠቃላይ የእስልምና መንፈስ ነበረው›› የሙናፊቆች ግድያ እንዴት እስላማዊ መንፈስ ይኖረዋል?

• ኢብን ኡመር (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንዲህ ይላሉ ‹‹የአላህ መልክተኛ (ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) በነበሩበት ወቅት በሰዎች መሃል እናበላልጥ ነበር፤ አቡበክርን ከዛ ኡመርን ከዛ ኡስማንን እንመርጥ ነበር›› ኡማሙ ቡኸሪ
ኢብን አባስ ይህንን አንቀፅ ይቀራና هَلْ يَسْتَوِى هُوَ وَمَن يَأْمُرُ بِٱلْعَدْلِ ۙ وَهُوَ عَلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمالنحل: ٧٦‹‹ይህ ነበር ኡስማን›› ይል ነበር (ተፍሲር ኢብን ከሲር 2/579)
እንግዲህ የአላህ ባርያዎች! እኛ ሰሃባን የሚሳደብ ሰው እሱ ሰሃባን እንደተሳደብው ባንሰድበውም፤ በግልፅ ግን ለሰሃባዎች ጥብቅና ቆመን ሃቁን እናወጣለን፡፡ እነዚህ ናቸው እንግዲህ ያለ ማስረጃ የሚያወሩት፡፡ አገር ውስጥ ያሉ ኡለማዎች ስም ላሉት፤ አገር ውስጥ ያሉ የሚከበሩ ኡለማዎች የእውነት አሉ፡፡ እንደዚህ ደግሞ የሰይድ ቁጡብ እና መሰሎቹ ጠበቆች አሉ፡፡ ማንም ይሁን ማን ለሰሃባዎች ተሳዳቢ፤ ሰይድ ቁጡብ ጥብቅና ቆሞ ቢመጣ አንሰማውም፡፡ እንቃወመዋለን፡፡

ተክፊር እና ሰሃባ ተሳዳቢ ለኡማው አሳቢ መስሎ በውሸት ተሞልቶ፤ ሃቅን በባጢል ስም፤ ባጢልን በሃቅ ስም እየጠራ ማንንም ሊያታል አይችልም፡፡ መልስ ይሰጠዋል፡፡ ስለዚህ ሰሃባን የሚሳደብ ሰው እናንተ እንደምትሉት ‹‹ኡለማን ይሳደባሉ›› ብትሉንም፤ እኛ አንሳደብም፤ የናንተን የስድብ መዝገበ ቃላት አየነው፤ ስማችሁን ቀይራችሁ ብትሳደቡ፤ መላኢካዎች በስማችሁ ነው የሚመዘግቡት፡፡
ሰሃባን ለሚሳደብ ሰው ጥብቅና ተቁሞ ድል የለም ውርደት እንጂ፡፡
አላህ ሆይ! ሃቅን በሃቅነቱ አሳየን የምንቀበለው አድርገን፤ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts