Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
እንደ ቀልድ ልምድ የሆኑ፣ ነገር ግን መስተካከል ካለባቸው ነገሮች ውስጥ
★ pleaae በእናትህ፣
★ በአባትህ፣
እና የመሳሰለውን እያሉ ሰዎች የሚደጋግሙት ሸሪአን የሚጋጭ አባባል ነው። ይህ አባባል ስህተት ነው።
ትክክለኛው
በአላህ ብቻ ብሎ መጠየቅ እና መለመን ነው ያለበተ።
https://t.me/SadatTextPosts
የዲን አስተማሪዎች ንግግራቸው በጣም ግልፅ ሊሆን ይገባል።
ይህን ማድረግ ከቻሉ ተማሪዎቻቸውን ከጭቅጭቅ ይቆጥባሉ።
ሸሪአም የመጣው ነገሮች ግልፅ በማድረግ ላይ ነው።
አላህ ቁርአንን አስመልክቶ እንዲህ ይላል
بِلِسَانٍ عَرَبِيّٖ مُّبِينٖ
ግልጽ በኾነ ዐረብኛ ቋንቋ (ቁርአን ወረደ)፡፡

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَقُولُواْ قَوۡلٗا سَدِيدٗا
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ፡፡

አላህ ሐቁን ይምራን።
https://t.me/SadatTextPosts
ትብብር የጠየቀንን ሰው በምን አይን ነው የምናየው?!
~~~~~~~~

ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል: –

አራት ሰዎችን ውለታቸውን ልመልስ አልችልም።
1ኛ:– በሰላምታ የጀመረኝን ሰው
2ኛ:– ጉባኤ ላይ መቀመጫ ቦታ ያሰፋልኝ ሰው
3ኛ:– ጉዳዬን ሊፈፅምልኝ እግሮቹ አቧራ የለበሱ
4ኛው:– ግን አላህ – ዐዘ ወጀል – እንጂ ውለታውን የሚመልስልኝ የለም።"

"ማነው እሱ?!" ሲባሉ እንዲህ አሉ:–

"የሆነ ጉዳይ ገጥሞት ችግሩን የሚፈታለት ሰው እያሰበ ሌሊቱን ካነጋ በኋላ ከዚያም ችግሩን እንደምፈታለት አስቦኝ እኔ ላይ የጣለ ሰው ነው።"

[ወፈያቱል አዕያን፣ ኢብኑ ኸሊካን: 3/63]
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor
ሰለፊና ኸለፊ አንድ አይደለም!!
ከነ አቡበክር ጋር የተደባለቀው አንዳንዱ "ተወካያችን" ወይም "መሪያችን" የአሽዐሪዮችን አቂዳ እምነቱ አድርጎ የያዘ ነው።
እነዚህ ሰዎች አላህ ከፍጡራን ፣ ከዐርሹ በላይ መሆኑን በማስተባበል የቁርአንንና የሐዲስን አስተምህሮ እንዲሁም የሰለፎችን ስምምነት ተፃረዋል ፣ ክደውበታል ።
አሽዐሪዮች ዘንድ "አላህ ለአማኞችና ለፍጡራን ያዝናል" ማለት ወይም የእዝነትን ባህሪ ለፈጣሪያችን ማፅደቅ ጥመትና ክህደት ነው— ቁርአንና ሐዲስ ላይ በሰፊው ግልፅ ሆኖ የምናገኘው አቋም ይሄው ሆኖ እያለ።
እነዚሁ ሰዎች ዘንድ አላህ በሙናፊቆችና በከሃዲያን ይቆጣል ብሎ ለሃያሉ ፈጣሪ የመቆጣትን ባህሪ ማስበት የሙስሊሞች እምነት አይደለም — ቅጥፈታቸው እዚህ የደረሰ ነው ። ባጠቃላይ፣ ቁርአንና ሐዲስ ላይ በምናገኛቸው በርካታ የአላህ ባህሪዎች የሚያምኑ አይደሉም ።
ታዲያ ከእንዲህ አይነት የአቂዳ ልዩነት ጋር ምን አይነት አንድነት ፣ ምን የሚሉት ጥምረት ነው የሚታለመው?!! እኛ ዘንድ እንዲህ አይነቱ መደባለቅ የሚሰራ ስሌት አይደለም!!
ከዚህም ሁሉ ጋር " ይህንን አንድነት የሚነካካን ሁሉ ተገቢውን ዋጋ እንሰጠዋለን! በዝምታ አናልፈውም በማለት ይዝታሉ !! አብሽሩ! የሻችሁትን ሁሉ በሉ! ዛቱም! አላህ ፊት የምንቆምበት ቀን የሚቀር አይደለምና ሁላችንም ተገቢያችንን ከአላህ ዘንድ እናገኛለን። የናንተን ዛቻ በመፍራት ሳንተኛና ሳንተነፍስ ማደር አንጀምርም— ኢን ሻ አላህ ። እኛ ትናንትም ዛሬም የጥቃት ዛቻን አናውቅም ። ስራችንን ግን አንፈታም! ልዩነታችንን ዛሬም በሰፊው እንተነፍሰዋለን !! በአላህ ፈቃድ እንቀጥላለን!! ሰለፊና ኸለፊን መደባለቅ ትልቅ ዙልም ነው !!
የሚገርመው ነገር ነጃሳው አህባሽ ከብልሹ የመንግስት አካላት ጋር ሙስሊሞችን ሲያሳስር በነሱም ላይ ሲዝት በወቅቱ "ሙናፊቅ " ብላችሁት ነበር። ዛሬ በተራችሁ መዛትን ያዛችሁ !! አየ እስስቱ ኢኽዋን! ! ብልሹው አሽዐሪ! !
ቀዷ ያለበት ሰው የሸዋልን ስድስት ቀን መፆም ይችላል?
~~~~~`
የረመዳን ፆም ቀዷ ያለበት ሰው ቀዷውን ሳይፆም የሸዋልን ስድስት ቀን መፆም አይቻልም የሚሉ ፈትዋዎች በሰፊው ከመሰራጨታቸው የተነሳ ሌላ የተለየ (መፆም ይቻላል የሚል) ፈትዋ ያለ እስከማይመስል ደርሷል። እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው።
① ለቀዷው ሰፊ ጊዜ ስላለና
② የሸዋል ጊዜ አጭር ስለሆነ
ከቀዷ በፊት ሸዋልን መፆም ይቻላል የሚለው የብዙሃን ዑለማዎች አቋም ነው። (ቀዷው ትንሽ ከሆነ ግን ግዴታውን አስቀድሞ ከዚያ የሸዋልን 6 ቀን ያስከትላል።)
ከስር ያያዝኩት የሸይኽ በድር ኢብኑ ዐልይ አልዑተይቢይ ፈትዋ ይህንኑ ሐሳብ የሚያጠናክር ነው።
youtu.be/P7hg2EzntxA
ለኒካሕ ሃላፊ (ወልይ) የሚሆኑት እነማን ናቸው?
============================
ክፍል አንድ:– ያለ ሃላፊ (ወሊይ) ኒካሕ ዋጋ አለው?
~~~~~~~~~~~~~~~~
በመጀመሪያ ወሊይ ለኒካሕ ወሳኝ ቅድመ ሁኔታ ነው። ያለ ወሊይ እውቅና የተፈፀመ ጥምረት ፈፅሞ ከጋብቻ አይቆጠርም። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:–
(لا نكاح إلا بولي )
"በወሊይ ካልሆነ በስተቀር ኒካሕ የለም!!" [አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል።]

* ስለዚህ ፈትም ሆነች ልጃገረድ አንዲት ሴት ያለ ወሊይ ፈፅሞ ልታገባ አይፈቅድላትም። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:–

أَيُّمَا امْرَأَةٍ نُكِحَتْ بِغَيْرِ إِذْنِ وَلِيِّهَا فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ، فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ، فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ
"ያለ ወሊዩዋ ይሁንታ የተገባች የትኛዋም ሴት ጋብቻዋ ውድቅ ነው! ጋብቻዋ ውድቅ ነው! ጋብቻዋ ውድቅ ነው!" [አቡ ዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።]

ክፍል ሁለት:– ወሊይ የሚሆኑት እነማን ናቸው?
~~~~~~~~~
ወሊይ የሚሆኑት በቅደም ተከተል የሚከተሉት ናቸው:–
1ኛ:– አባት፣
2ኛ:– የአባት አባት፣
3ኛ:– ወንዶች ልጆች፣
4ኛ:– ወንድም፣
5ኛ:– የወንድም ልጆች፣
8ኛ:– አጎቶች …እያለ ይቀጥላል።

* በአባትም በእናትም የሚገናኝ ወሊይ በአባት ብቻ ከሚገናኘው ይቀደማል።
* ተቀዳሚ የሆነው ወሊይ በቀላሉ የማይገኝ ከሆነ ተራውን ጠብቆ ሌሎች ወሊዮች ኃላፊነቱን ይወስዳሉ።

* አንድ ሰው ወሊይ ለመሆን
~~~~~~~~~~~~~~~~~
• ሙስሊም መሆን አለበት። ካፊር ወሊይ ሆኖ ሊድር አይችልም።
• አእምሮው ጤነኛ መሆን አለበት።
• ለአቅመ ኣደም የደረሰ መሆን አለበት።
• ወንድ መሆን አለበት።

* ወሊይ ከነ ጭራሹ ከሌለ ወይም ለአቅመ ኣደም የደረሱ ካልሆኑ ቃዲ ወሊይ ይሆናል።
َ (فالسلطان ولي من لا ولي له )
"አስተዳዳሪ ወሊይ ለሌለው ወሊይ ነው።" [አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል]

* ወሊይ (ሃላፊ) በቅርብ ከሌለ ሌላ ሰው መወከል ይችላል። ውክልናው እንዲሁ "ይበጃል ላልከው ዳርልኝ" አይነት ክፍት ሊሆን ይችላል። ወይም "ለእከሌ ዳርልኝ" የሚል የተገደበ ሊሆን ይችላል።
* የሸሪዐ ቃዲዎች በሌሉበት ሃገር የኢስላማዊ መርከዝ ሃላፊ ወይም የመስጂድ ኢማም ወሊይ ሆኖ መዳር ይችላል።
* ወሊዩ ሺርክ ላይ የተዘፈቀ ወይም ሶላት የማይሰግድ ከሆነ ተራው ተጠብቆ ወደተሻሉት ኃላፊነቱ ይሻገራል።
* ወሊዩ #ያለ_ተጨባጭ_ምክንያት ለመዳር ፈቃደኛ ካልሆነ ተራው ተጠብቆ ወደተሻሉት ኃላፊነቱ ይሻገራል። ሌሎችም ፈቃደኛ ካልሆኑ ወደ ቃዲ ይሻገራል።

ጥንቃቄ ① ተራው ሳይጠበቅ (ሌሎች ወሊዮች እምቢ ሳይሉ) ዘሎ ወደ ቃዲ አይኬድም።
ጥንቃቄ ② ወላጅ ወይም የሚመለከተው ወሊይ በተጨባጭ ምክንያት ከከለከለ ሌሎች አማራጮችን መጠቀም አይፈቀድም። አርፎ መቀመጥ ነው።
ጥንቃቄ ③ የወሊዮች ምክንያት አሳማኝ ባይሆን እንኳ ያለ ወሊይ ይሁንታ የሚገባበት ጋብቻ አደጋዎች ሊኖሩት ስለሚችሉ ሴቶች ከመግባታቸው በፊት የሚችሉትን ያክል ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል። ዛሬ ብዙ ሰው ስነ ምግባሩ ወርዷል። ሴቷ ከቤተሰብ ተቀያይማ የገባችበት ጋብቻ ወይ ተመልካች አጥታ የሰቆቃ ህይወት ስትገፋ ወይ ደግሞ እንደ ዋዛ እየፈረሰ "ከሁለት ያጣች" ስትሆን ማየት እየተለመደ መጥቷል። ስለዚህ ከፍ ያለ ስጋት ካለ የቤተሰብ ተቃውሞ ተጨባጭ ባይሆን እንኳ መግባት አይገባም። ወላሁ አዕለም!!
ሙብተዲዕ ላይ አትማር!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል:–

"አንደበት ርቱእ የሆነ ማራኪ የአነጋገር ክህሎት ያለው ሙብተዲዕ ብናገኝ ከሱ ዘንድ ልንቀመጥ አይገባም። ምክንያቱም ሙብተዲዕ ነውና!! ለምንድን ነው የማይፈቀደው?

1⃣ አንደኛ:– ተንኮሉን ስለምንሰጋ ነው። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ከአገላለፅም ድግምት አለ" ብለዋልና። ቢድዐው ላይ እንስማማው ዘንድ አእምሯችን ላይ ሊደግምብን ይችላል።

2⃣ ሁለተኛ: – ተቀምጠን መከታተላችን ይህን ሙብተዲዕ ያበረታታዋል። በዙሪያው የሚሆኑ ሰዎች እንዲበዙ እናደርጋለን። ታዋቂዎችና ክቡራን ሰዎች ሊቀመጡ ይችላሉ። ይሄ ደግሞ መኮፈስን እና በቢድዐው መጎረርን ይጨምረዋል።

3⃣ ሶስተኛ: – ከሙብተዲዑ ዘንድ የሚቀመጠው ሰው በክፉ ይጠረጠራል። ይህ የሚስተዋለው ግን ዘግይቶ ሊሆን ይችላል። ሰዎች የቢድዐ ባለቤት ዘንድ ስትሄድ ለጊዜው ባይገለጥም በክፉ ይጠረጥሩሀል። ስለዚህ እውቀት ፈላጊ የሆነ ሰው ከቢድዐ ሰዎች ሊርቅ ይገባል። ኧረ እንዲያውም ምራቁ ግዴታው ነው።"

📚 [ሸርሑል ሒልያ: 314]
"ነፃ ትርጉም"
ሪፍቅ (ልስላሴ)
አላህ ለፍጡራኖቹ አዛኝ ነው። ለዚህም ስለሆነ በተውሂድ ያዛቸዋል፣ ሽርክን እንዲርቁ ያስጠነቅቃቸዋል። በተውሂድ ላይ ኖረው፣ ሽርክን ከነባለቤቶቹ ርቀው፣ በተውሂድ ላይ ከሞቱ ጀነት የሚባል ልብ ጠርጥሮት፣ ጆሮ ሰምቶት፣ አይን አይቶት የማያውቅ አገር ተዘጋጅቶላቸዋል።
በተገላቢጦሹ አዛኙ አላህ፣ ፍትሃዊ፣ አያያዙ የበረታ፣ አሸናፊ ፈራጅ ነውና በሱ ላይ የሚያጋሩትን "አጋርያን እርኩሶች (ነጃሳዎች)" ናቸው ሁሉ ብሎ ጠርቷቸዋል። በዱንያ ውርደትን፣ በአኸይራ አሳማሚ ቅጣትን አዘጋጅቶላቸዋል። አላህ ይጠብቀን።
ልክ እንደዚሁ ለአማኞች ከነፍሳቸው በላይ የሆኑት ውዱ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አዛኝ ናቸው። በጣም አዛኝ ከመሆናቸውም የተነሳ ሰዎችን ዘላለም አለም እስታ ውስጥ የሚከታቸውን ሽርክ
1) እያዩ እንዳላዩ ዝም አላሉም፣
2) በሽርክና ቢድአ ጉዳይ ላይ አንድ ነን ብለው አልተስማሙም፣
3) ወደ ሽርክና ቢድአ የሚጣራን አይደለም ወደነዚህ መንገድ የሚወስዱን ነገሮች ዝም አላሉም።
በጣም አዛኙ ነብይ ስለ ቢድአ ሲያስጠነቅቁ ፊታቸው ደም ይለብስ ነበር፣ ይቆጡ ነበር ምክንያቱም ቢድአ ነውና የዚህ ኡማ ትልቁ ፀር።
ስለ ሪፍቅ ሲወራ ባይጠቀስም አብሮት ሺዳ በውስጡ አለ።
እዝነትም (ልስላሲ)፣ ጥንካሪም ቦታ ቦታ አላቸው። መቼም አንድ ዳኢ ሽርክን ስለሚያክል ታላቅ አደጋ እያስተማረ ለምን ይኮሳተራል? ተብሎ ሊጠየቅ አይገባውም። ምክንያቱም የነብያትም፣ በተለይ የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምም አካሄድ ይሄ ነበረና።
ቢድአና ወንጀልንም ለያይተን ማስቀመጥ አለብን። የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ዘንድ ወንጀለኞች (መጠጥ ጠጪዎች፣ ዝሙት የሰሩ) ሲመጡ የነበረውን አቀባበል አንርሳ። ልስላሲ ነበር ከመልክተኛው ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የነበረው። እኚሁ የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ጁምአ ኹጥባቸው ላይ "አዳዲስ በዲን ላይ ያሉ ፈጠራ ጭማሪዎችን ተጠንቀቁ፣ ሁሉም ፈጠራ ጥመት ነው፣ ሁሉም ጥመት የእሳት ነው" ሲሉ ምን ያህል ይቆጡ እንደነበር የሀዲስ መዛግብትን ማየት ይበጃል።
አንድ እናት ልጇን ብትገርፍ፣ አንድ አባት ልጁን ቢቆጣ እንዲስተካከልላቸው እንጂ ጠልተውት አይደለም። ስለሱ የማይጨነቁ ቢሆን ኖሮ ልጃቸውን ከነመጥፎ ባህሪው ይተውት ነበር።
ልክ እንደዚሁ ሁሉ መጥፎ ነገር ሽርክ፣ ቢድአ፣ መሀይምነት፣ ድራማ፣ ፊልምና የመሳሰሉት ተስፋፍተው ሲያዩ የአላህ ባርያዎች ስለሚያዝኑ ነው ለኡማው ያ ሁሉ ውርጅብኝ ከየአቅጣጫው እየወረደባቸው ሀቁን የሚናገሩት። አላህም ለባሮቹ ስለሚያዝን ነው አዛኝ ከመሆኑም ጋር ማስጠንቀቂያዎችንና ዛቻዎችን አብሮ ያስቀመጠው። ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምም እንደዚሁ እዝነት በሚያስፈልገው ቦታ እዝነት፣ ጠንከር ማለት በሚያስፈልገው ቦታ ጠንከር ብለው ያሳዩን።
አሁን ያለንበት ወቅት ላይ በጣም እዝነት ያስፈልገዋል ይህ የማይካድ እውነታ ነው። ይህ ማለት ግን ቢድአና ሙብተዲ ላይ አለመናገር ማለት አይደለም። ቢድአና ሙብተዲ ላይ መናገር ለኡማው በጣም እጅግ በጣም ከማዘን ነው። ምክንያቱም ኢስላምንና ሙስሊሞችን ከውስጥ የሚንደውና የሚያዳክመው አዳዲስ መንገዶችና የቢድአ ሰዎች ናቸውና።
አላህ ሁሉንም በቦታው ላይ ከሚያስቀምጡት ባርያዎች ያድርገን። አላህ ሆይ! እውቀትን ጨምርልን፣ በምናውቀውም የምንሰራ አድርገን፣ በፈተና ወቅትም በሃቅ ላይ ከሚፀኑት አድርገን።
https://t.me/SadatTextPosts
ሐጅ እና ለይለቱል ቀድር
በለይለተል ቀርድ የዘንድሮ ሐጅ አድራጊዎች እንማን እንደሆኑ ይወሰናል፡፡
[Q 44:4] فِيهَا يُفْرَقُ كُلُّ أَمْرٍ حَكِيمٍ
በውስጧ (በለይለተል ቀድር) የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡
አብደላህ ኢብን አባስ (ረድየላሁ አንሁ) ይህንን ሲያብራሩ እንዲህ አሉ
“ከኡሙል ኪታብ (ከለውሀል መህፉዝ) በለይለተል ቀድር በአመት ውስጥ የሚከሰቱት ነገሮች ከሞት፣ ከህይወት፣ ከሲሳይ (ሪዝቅ)፣ ከዝናብ፣ ሐጅ አድራጊዎችም ጭምር እገሌ ሐጅ ያደርጋል፣ እገሌ ሐጅ ያደርጋል ሁሉ ይባላል ተብሎ ውሳኔው ይገለበጣል፡፡”
https://t.me/SadatTextPosts
ሐጅ እና ለይለቱል ቀድር
በለይለተል ቀርድ የዘንድሮ ሐጅ አድራጊዎች እንማን እንደሆኑ ይወሰናል፡፡
[Q 44:4] فِيهَا يُفْرَقُ كُلُّ أَمْرٍ حَكِيمٍ
በውስጧ (በለይለተል ቀድር) የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡
አብደላህ ኢብን አባስ (ረድየላሁ አንሁማ) ይህንን ሲያብራሩ እንዲህ አሉ
“ከኡሙል ኪታብ (ከለውሀል መህፉዝ) በለይለተል ቀድር በአመት ውስጥ የሚከሰቱት ነገሮች ከሞት፣ ከህይወት፣ ከሲሳይ (ሪዝቅ)፣ ከዝናብ፣ ሐጅ አድራጊዎችም ጭምር እገሌ ሐጅ ያደርጋል፣ እገሌ ሐጅ ያደርጋል ሁሉ ይባላል ተብሎ ውሳኔው ይገለበጣል፡፡”
https://t.me/SadatTextPosts
መርከዝ አት-ተውሒድ የቁርዓን ሒፍዝ ማዕከል
የክረምት ኮርስ ለልጆች እና ለወጣቶች አዘጋጅቷል
1) ቁርዓን ላልቀሩ ተማሪዎች ቁርዓንን ከቃኢዳ ኑራንያ ጀምሮ ማስቀራት፣
2) ሙራጅዓ ለመቅራት፣
3) የተለያዩ የኪታብ ቂርዓቶች (አቂዳ፣ ፊቅህ፣ ሀዲስ)…
4) አጠቃላይ ተርቢያ
ኮርሱ ከመጀመሩ በፊት በሚከተሉት ስልኮች መመዝገብ ይችላሉ
0910609894 / 0947052919 / 0972543622
ለበይክ አላሁመ ለበይክ
ሐጅ የኢስላም ልዩ መስህብ የሚሰተዋልበት፣ ድንቅ የአላህ ተዐምር የሚታይበት፣ የተውሒድ ነፀብራቅ ጎልቶ የሚነግስበት፣ ባእድ አምልኮ ከፍ ባለ ድምፅ ባደባባይ የሚወገዝበት ድንቅ ስርአት ነው፡፡ ሴት ወንዱ፣ ነጭ ጥቁሩ፣ መሪው ተመሪው በተመሳሳይ ቦታ እኩል ለአላህ የሚሰለፍበት ትንግርት፡፡ ሐጅ - አምስተኛው የኢስላም ምሰሶ፡፡
በሐጅ (በሰዎችም ውስጥ በሀጅ ትእዛዝ ተጣራ) ለሚለው የአላህ ጥሪ “ለበይክ አላሁመ ለበይክ፣ ለበይከ ላሸሪከ ለከ ለበይክ፣…” /አቤት ጌታችን ሆይ አቤት፣ አቤት ጥሪህን ተቀብለን መጥተናል/” እያሉ መልስ በመስጠት ሚሊዮኖች ይተማሉ፡፡ ከዚያ ጭው ካለ በረሃ “ከአላህ ሀገራት ሁሉ ይበልጥ አላህ ዘንድ የተወደድሽ ነሽ፡፡ ከአላህ ሀገራት ሁሉም እኔ ዘንድ የተወደድሽ ነሽ፡፡ ህዝቦችሽ ካንቺ ባያስወጡኝ ኖሮ አልወጣም ነበር” የሚለውን የነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የቁጭት ንግግር፣ አሜኬላ የበዛበት ህይወታቸውን ልበዎ በሀዘን እየተከፈለ ያስታውሳሉ፡፡ ከዚያ ጭው ካለ በረሃ አስራ አራት ክፍለ-ዘመናት ወደ ኋላ አጠንጥነው የተውሒድ ጮራ ሲፈነጥቅ በአይነ-ህሊናዎ ይመለከታሉ፡፡ ከዚያ ጭው ካለ በረሃ የመካ ሙሽሪኮችን ለከት የለሽ ጭካኔና የነዚያን ፈርጥ የሆኑ ሰሐቦች ከብረት የጠነከረ ፅናት እያሰቡ በትዝታ ይነጉዳሉ፡፡ ከዚያ ጭው ካለ በረሃ የነቢላልን ስቃይ፣ የነሱመያን የጣር ድምፅ አይነዎ እንባ እያቀረረ በሰመመን ያያሉ፡፡ ልበዎ በቁጭት እየደማ ይሰማሉ፡፡ ከዚያ ጭው ካለ በረሃ የአላህ የመጀመሪያ ቤት አለ - የሙስሊሞች ቂብላ፣ ከአለም ሁሉ ምርጡ ቦታ፣ መካ፡፡
ﺇِﻥَّ ﺃَﻭَّﻝَ ﺑَﻴْﺖٍ ﻭُﺿِﻊَ ﻟِﻠﻨَّﺎﺱِ ﻟَﻠَّﺬِﻱ ﺑِﺒَﻜَّﺔَ ﻣُﺒَﺎﺭَﻛًﺎ ﻭَﻫُﺪًﻯ ﻟِﻠْﻌَﺎﻟَﻤِﻴﻦَ ‏( 96 ‏) ﻓِﻴﻪِ ﺁﻳَﺎﺕٌ ﺑَﻴِّﻨَﺎﺕٌ ﻣَﻘَﺎﻡُ ﺇِﺑْﺮَﺍﻫِﻴﻢَ ﻭَﻣَﻦْ ﺩَﺧَﻠَﻪُ ﻛَﺎﻥَ ﺁﻣِﻨًﺎ
((በርግጥም ለሰው ዘር (መፀለያ) ሆኖ መጀመሪያ (ምድር ላይ) የተኖረው ቤት ያ በበካህ (በመካ) ያለው የተባረከና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ የሆነው ነው፡፡ በውስጡ (እንደ) የኢብራሒም መቆሚያ (ያሉ) ግልፅ የኾኑ ተዓምራቶች አልሉ፡፡ ወደ ውስጡ የገባም ሰው ደህንነቱ የተጠበቀ ሆኗል፡፡) [ኣሊ ዒምራን፡ 96]
መስጂደልሐራም መጤው ካገሬው እኩል የሚሆንበት ተአምራዊ ቦታ፡፡ የተውሒድ ቦታ፣ የእዝነት ቦታ፡፡ የኢብራሂም፣ የሐጀር፣ የኢስማዒል ትዝታ፡፡ መስጂደል ሐራም በረከት የበዛበት፣ ሰላም የሰፈነበት፣ እዝነት የነገሰበት፣ ተውሒድ የፈነጠቀበት ቅዱስ ቦታ፡፡ መስጂደልሐራም ልቦች ዘወትር የሚናፍቁት፣ አይኖች አይተውት የማይጠግቡት፣ ያላዩት ሊያዩት የሚቋምጡት ድንቅ ቦታ፡፡ መስጂደልሐራም! “የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም” ሀገርኛ ብሂል ፉርሽ የሚሆንበት ልዩ መስህብ፡፡ ለካስ ይናፍቃል! ደካማ አዛውንቶች በሽተኞች ሳይቀሩ ህመም ድካማቸውን ረስተው፣ ስቃይ እንግልቱን ዘንግተው፣ ባላዩት ሀገር ናፍቆት ተብሰክስከው፣ እልፍ አእላፍ ማይሎችን አቋርጠው ይተማሉ፡፡
ﻭَﺇِﺫْ ﺑَﻮَّﺃْﻧَﺎ ﻟِﺈِﺑْﺮَﺍﻫِﻴﻢَ ﻣَﻜَﺎﻥَ ﺍﻟْﺒَﻴْﺖِ ﺃَﻥْ ﻟَﺎ ﺗُﺸْﺮِﻙْ ﺑِﻲ ﺷَﻴْﺌًﺎ ﻭَﻃَﻬِّﺮْ ﺑَﻴْﺘِﻲَ ﻟِﻠﻄَّﺎﺋِﻔِﻴﻦَ ﻭَﺍﻟْﻘَﺎﺋِﻤِﻴﻦَ ﻭَﺍﻟﺮُّﻛَّﻊِ ﺍﻟﺴُّﺠُﻮﺩِ ‏( 26 )
((ለኢብራሂምም የቤቱን (የካዕባን) ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ “በኔ ምንንም አታጋራ፣ ቤቴንም ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት ሩኩዕ ሱጁድ ለሚያበዙት ንፁህ አድርግላቸው” (ባልነው ጊዜ አስታውስ)፡፡)) [አልሐጅ፡ 26]
ከዕባ፣ ሐጀረል አስወድ፣ መቃም ኢብራሂም፣ ሶፋና መርዋ፣ ሚና፣ ዐረፋ፣ ሙዝደሊፋ፣… የሙስሊሞችን ቀልብ የሚማርኩ ልዩ የዒባዳ አውድማዎች ናቸው፡፡ ተልቢያ፣ ጠዋፍ፣ ሶላት፣ ዱዐ፣ እርድ፣ የጠጠር ውርወራ፣… ለፈፀማቸው ቀርቶ ለተነገረው የሚያጓጉ ሐጅ ላይ የሚመረቱ፤ ተቅዋን የሚያላብሱ የዚያኛው ዓለም ስንቆች ናቸው፡፡ ( ﺫَﻟِﻚَ ﻭَﻣَﻦْ ﻳُﻌَﻈِّﻢْ ﺷَﻌَﺎﺋِﺮَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻓَﺈِﻧَّﻬَﺎ ﻣِﻦْ ﺗَﻘْﻮَﻯ ﺍﻟْﻘُﻠُﻮﺏِ )
ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲሥ አላህ አድሎት የተዋጣለት ሐጅ ያደረገ እናቱ ስትወልደው እንደነበረው እንደህፃንነቱ ከወንጀል ሙሉ በሙሉ እንደሚፀዳ ነው መልእክተኛው አለይሂሰላም ያመላከቱት፡፡ በሐጅ፣ ልቦች በኢማን ይታደሳሉ፣ አማኞች ከወንድሞቻቸው ጋር ይተዋወቃሉ፣ ደካሞች ይታገዛሉ፣ ሙስሊሞች ከቅዱስ ስፋራ፣ ከበረሃው፣ ከሐጁ ስርኣቶች፣ ከተዳሚው ሁኔታ፣ ከዚያ የሚሊዮኖች ስብሰባ ብዙ ተፈኩር ይወስዳሉ፡፡
አላህ አድሎት የሐጅ ስነ-ስርኣት ላይ ለተካፈለ ሰው ልብሳቸው የበሰበሰ፣ ሰውነታቸው የኮሰሰ፣ ኑሮ ያጎሳቆላቸው ስንት አይነት ሰዎችን ከተለያዩ የአለም አፅናፋት ታድመው ይመለከታል፡፡ አንዳንዶቹ ለዘመናት አጠራቅመው ለዚህ ስኬት እንደበቁ ሲቃ እየተናነቃቸው ይናገራሉ፡፡ በተሽከርካሪ ወንበር የሚገፉ፣ በጀርባ የታዘሉ አዛውንቶችን ሲመለከቱ፣ አቅሙም ጤናውም ተሟልቶ ከሐጅ ስለቀረው ወገን በእጅጉ ያዝናሉ፡፡ ሐጅ የወጀበባችሁ ወገኖቼ ሆይ! ጤናን አቅምን ያደላችሁ ጌታ፣ ሐጅን ግዴታ አድርጎባችኋል፡፡ ወንድሞቼ እህቶቼ፣ አባቶቼ እናቶቼ ሆይ! ለአላማ እንደተፈጠራችሁ አትዘንጉ፡፡ የተሰጣችሁ ገንዘብ ያንን አላማ ማሳኪያ እንጂ መጎረሪያም መባከኛም አይደለም፡፡ ሐጁን ብትፈፅሙት ጥቅሙ ለራሳችሁ ነው፡፡ ወንጀላችሁ ይረግፋል፣ ልባችሁ ይፀዳል፤ የዒባዳ ወኔያችሁ ይነሳሳል፡፡ እመኑኝ አንዴ ቆርጣችሁ ከፈፀማችሁት በያመቱ ገና ጊዜው ሲቃረብ ነው ልባችሁ የሚቆመው፡፡ “ወዴት” እንዳትሉኝ፡፡ ወላሂ ስንቶች ናቸው ሐጅ አጠናቀው መካን ሲለቁ፣ በእንባ የሚታጠቡት! ባትፈፅሙትስ ማነው የሚጎዳው? በርግጠኝነት አላህ ምንም አይቀርበትም! መቼስ ከሚታረደው እርድ አይደርሰው ነገር! ያበላል እንጂ አይበላምና፡፡ ከፍጡር ሁሉ የተብቃቃ ጌታ ነውና፡፡
ﻭَﻟِﻠَّﻪِ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟﻨَّﺎﺱِ ﺣِﺞُّ ﺍﻟْﺒَﻴْﺖِ ﻣَﻦِ ﺍﺳْﺘَﻄَﺎﻉَ ﺇِﻟَﻴْﻪِ ﺳَﺒِﻴﻠًﺎ ﻭَﻣَﻦْ ﻛَﻔَﺮَ ﻓَﺈِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻏَﻨِﻲٌّ ﻋَﻦِ ﺍﻟْﻌَﺎﻟَﻤِﻴﻦَ ‏( 97 )
(ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መሄድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው፡፡ የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡) [ኣሊ ዒምራን: 97]
ዱዓቶች ሆይ ተነሱ! ሰዎችን ቀስቅሱ፡፡ አላህ የጣለባችሁን ሀላፊነት አድርሱ፡፡ ተሳክቶላችሁ በናንተ ሰበብ አንድ ሰው ለሐጅ ቆርጦ ቢነሳ የሚኖራችሁን አጅር አስታውሱ፡፡ ወገን ወደ ግራም ወደ ቀኝም ተመልከት፡፡ ከራሳችን፣ ከቤተሰብ፣ ከጎረቤት ብዙ ሐጅ ያላደረጉትን ፍቀድ፡፡ ዘንድሮ ባይደርስ ለቀጣይ አስታውስ፡፡ (አስታውስ ማስታወሱ አማኞችን ይጠቅማልና፡፡) [አዝዛሪያት፡ 55]
ባይሆን አደራ
ለሐጅ ቆርጠው ከተነሱ፡- በሚገባ ይዘጋጁ፡፡ ስለሐጅ ይጠይቁ፣ ይወቁ፣ ያንብቡ፣ የሚያነቡትም ይያዙ፡፡ ከተቻለም ቀድሞ ሐጅ ያደረገ የዲን ግንዛቤ ያለው ሰው ጓደኛ ማድረገዎን አይርሱ፡፡
(ወደ ኸይር ያመላከተ (ኸይሩን) እንደሚሰራው ሰው ነው (አጅሩ አለው)) ይላሉ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡፡
ለበይክ አላሁመ ለበይክ
ለበይከ ላሸሪከ ለከ ለበይክ
ኢነልሐምደ
ወንኒዕመተ
ለከ ወልሙልክ
ላሸሪከ ለክ!!
ያ ረሕማኑ ቤትህን ለመጎብኘት አንተ ወፍቀን፡፡
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጳጉሜ 3/2006)