Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
ጥቂት ስለ ኡስታዝ አቡ ሙስሊም
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ወንድማችን ዑመር ሐሰን አቡ ሙስሊም ከ10 አመት በፊት የኡሙል ቁራ ዩኒቨርስቲ የትምህርት እድል (scholarship) በማግኘቱ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሲከታተለው የነበረውን አካዳሚ ትምህርት በመተው ወደ መካ አቀና። ከሄደበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ለአስር አመታት ዒልም በመቅሰም ላይ ነው ያለው።

* የመጀመሪያ ዲግሪውን በመካ ከተማ ከሚገኘው የኡሙል ቁራ ዩኒቨርሲቲ በ
الكتاب والسنة مع الإعداد التربوي
አጠናቋል።
* የሁለተኛ ዲግሪውን በ الحديث وعلومه
(በሐዲሥ ጥናት ዘርፍ) መደበኛ ትምህርቱን እያጠናቀቀ በአሁኑ ሰዓት የሶስተኛ አመት ተማሪ ሲሆን የማሟያ ጥናት (ቴሲስ) በመስራት ላይ ነው።
* ከመደበኛው የኡሙል ቁራ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱ ጎን ለጎን ከሄደበት ጊዜ አንስቶ ለ10 አመታት ታላላቅ ዑለማዎች ዘንድ በመሄድ በትጋት ይከታተላል። የተማረባቸውንና እየተማረባቸው ያሉ ዑለማዎችን ለምሳሌ ያክል ልጥቀስ:–

① ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አልመድኸሊ፣
② ሸይኽ ዐብዱረሕማን አልዐጅላን፣
③ ሸይኽ ሙሐመድ ዐሊ ኣደም አልወሎዊ፣
④ ታዋቂው ሙሐዲሥ ሸይኽ ወሲዩላህ ኢብኑ ሙሐመድ አልዐባስ
⑤ ሸይኽ የሕያ ኢብኑ ዑሥማን (ከሸይኽ ሙቅቢል ሸይኾች ውስጥ ናቸው)፣
⑥ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዑመር ባዝሙል፣
⑦ ሸይኽ አሕመድ ኢብኑ ዑመር ባዝሙል (በአሁኑ ሰዓት ለማስትሬት ጥናቱ አማካሪው (አድቫይዘሩ) ናቸው።)

ከነዚህም በተጨማሪ ወደ መካ በሚመጡበት ጊዜ ባገኛቸው አጋጣሚ የተማረባቸው ዑለማዎች አሉ። ለምሳሌ:–
⑧ ሸይኽ ሷሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አልፈውዛን
⑨ ሸይኽ ሷሊሕ አልሉሐይዳን፣
(10) ሙፍቲ ዐብዱል ዐዚዝ ኣሊ ሸይኽ፣
(11) ሸይኽ ፉኣድ ኢብኑ ሰዑድ አልዐምሪ፣
(12) ሸይኽ ዓዲል ኢብኑ መንሱር አልባሻ
(13) ሸይኽ አቡ ሁማም ሙሐመድ ኢብኑ ዐሊይ አልበይዷኒ እና ሌሎችም።

ከመካም ውጭ በተለያዩ ደውራዎች (አጫጭር ስልጠናዎች) ላይ በመካፈል ዒልም የቀሰመባቸው መሻይኾች ብዙ ናቸው። ለምሳሌ ያክል:–

* ሸይኽ ዘይድ ኢብኑ ሙሐመድ አልመድኸሊ (ረሒመሁላህ)፣
• ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲ አልመድኸሊ፣
• ሸይኽ ሱለይማን አርሩሐይሊ፣
• ሸይኽ ሙሐመድ ረምዛን አልሃጂሪ፣
• ሸይኽ ዐብዱረሕማን ኢብን ሙሕዪዲን፣
• ሸይኽ ዐልይ ኢብኑ የሕያ አልሐዳዲ፣
• ሸይኽ ዐብዱረዛቅ አልበድር፣
• ሸይኽ ሙሐመድ ኢብን ዐብዲል ወሃብ አልዐቂል፣
• ሸይኽ ኡሳማ አልዐምሪ እና ሌሎችም።

* ወንድም አቡ ሙስሊም ተባባሪና ፈጥኖ ሰው ጋር የሚግባባ ነው። ከሚማርባቸው መሻይኾች ዘንድ ያለው ቅርበት እና አመኔታ የሚያስቀና ነው።
* አቡ ሙስሊም የሳዑዲ ኢስላማዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ከሚያሰማራቸው ዱዓት ጋር በመሆን በየዓመቱ ወደ መካ ለሚመጡ ኢትዮጵያውያን ሑጃጆች በማስተማር ይጠመዳል።
* ከሐጅ ውጪም የተለያዩ የማስተማር ስራዎች ላይ ይሳተፋል።
* በአንድ የመንግስት ትምህርት ቤት ውስጥም አስተምሯል።
* ወንድም አቡ ሙስሊም እኔ እስከማውቀው ድረስ ፌስቡክ ላይ የለም። በቴሌግራም ግን በአማርኛም በኦሮምኛም ያስተምራል። ትምህርቱን መከታተል ለሚሹ የቴሌግራም ቻናሉ ይሄውና

🌐 t.me/AbumuslimAlarsi
እንደ ቀልድ ልምድ የሆኑ፣ ነገር ግን መስተካከል ካለባቸው ነገሮች ውስጥ
★ pleaae በእናትህ፣
★ በአባትህ፣
እና የመሳሰለውን እያሉ ሰዎች የሚደጋግሙት ሸሪአን የሚጋጭ አባባል ነው። ይህ አባባል ስህተት ነው።
ትክክለኛው
በአላህ ብቻ ብሎ መጠየቅ እና መለመን ነው ያለበተ።
https://t.me/SadatTextPosts
የዲን አስተማሪዎች ንግግራቸው በጣም ግልፅ ሊሆን ይገባል።
ይህን ማድረግ ከቻሉ ተማሪዎቻቸውን ከጭቅጭቅ ይቆጥባሉ።
ሸሪአም የመጣው ነገሮች ግልፅ በማድረግ ላይ ነው።
አላህ ቁርአንን አስመልክቶ እንዲህ ይላል
بِلِسَانٍ عَرَبِيّٖ مُّبِينٖ
ግልጽ በኾነ ዐረብኛ ቋንቋ (ቁርአን ወረደ)፡፡

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَقُولُواْ قَوۡلٗا سَدِيدٗا
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ፡፡

አላህ ሐቁን ይምራን።
https://t.me/SadatTextPosts
ትብብር የጠየቀንን ሰው በምን አይን ነው የምናየው?!
~~~~~~~~

ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል: –

አራት ሰዎችን ውለታቸውን ልመልስ አልችልም።
1ኛ:– በሰላምታ የጀመረኝን ሰው
2ኛ:– ጉባኤ ላይ መቀመጫ ቦታ ያሰፋልኝ ሰው
3ኛ:– ጉዳዬን ሊፈፅምልኝ እግሮቹ አቧራ የለበሱ
4ኛው:– ግን አላህ – ዐዘ ወጀል – እንጂ ውለታውን የሚመልስልኝ የለም።"

"ማነው እሱ?!" ሲባሉ እንዲህ አሉ:–

"የሆነ ጉዳይ ገጥሞት ችግሩን የሚፈታለት ሰው እያሰበ ሌሊቱን ካነጋ በኋላ ከዚያም ችግሩን እንደምፈታለት አስቦኝ እኔ ላይ የጣለ ሰው ነው።"

[ወፈያቱል አዕያን፣ ኢብኑ ኸሊካን: 3/63]
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor
ሰለፊና ኸለፊ አንድ አይደለም!!
ከነ አቡበክር ጋር የተደባለቀው አንዳንዱ "ተወካያችን" ወይም "መሪያችን" የአሽዐሪዮችን አቂዳ እምነቱ አድርጎ የያዘ ነው።
እነዚህ ሰዎች አላህ ከፍጡራን ፣ ከዐርሹ በላይ መሆኑን በማስተባበል የቁርአንንና የሐዲስን አስተምህሮ እንዲሁም የሰለፎችን ስምምነት ተፃረዋል ፣ ክደውበታል ።
አሽዐሪዮች ዘንድ "አላህ ለአማኞችና ለፍጡራን ያዝናል" ማለት ወይም የእዝነትን ባህሪ ለፈጣሪያችን ማፅደቅ ጥመትና ክህደት ነው— ቁርአንና ሐዲስ ላይ በሰፊው ግልፅ ሆኖ የምናገኘው አቋም ይሄው ሆኖ እያለ።
እነዚሁ ሰዎች ዘንድ አላህ በሙናፊቆችና በከሃዲያን ይቆጣል ብሎ ለሃያሉ ፈጣሪ የመቆጣትን ባህሪ ማስበት የሙስሊሞች እምነት አይደለም — ቅጥፈታቸው እዚህ የደረሰ ነው ። ባጠቃላይ፣ ቁርአንና ሐዲስ ላይ በምናገኛቸው በርካታ የአላህ ባህሪዎች የሚያምኑ አይደሉም ።
ታዲያ ከእንዲህ አይነት የአቂዳ ልዩነት ጋር ምን አይነት አንድነት ፣ ምን የሚሉት ጥምረት ነው የሚታለመው?!! እኛ ዘንድ እንዲህ አይነቱ መደባለቅ የሚሰራ ስሌት አይደለም!!
ከዚህም ሁሉ ጋር " ይህንን አንድነት የሚነካካን ሁሉ ተገቢውን ዋጋ እንሰጠዋለን! በዝምታ አናልፈውም በማለት ይዝታሉ !! አብሽሩ! የሻችሁትን ሁሉ በሉ! ዛቱም! አላህ ፊት የምንቆምበት ቀን የሚቀር አይደለምና ሁላችንም ተገቢያችንን ከአላህ ዘንድ እናገኛለን። የናንተን ዛቻ በመፍራት ሳንተኛና ሳንተነፍስ ማደር አንጀምርም— ኢን ሻ አላህ ። እኛ ትናንትም ዛሬም የጥቃት ዛቻን አናውቅም ። ስራችንን ግን አንፈታም! ልዩነታችንን ዛሬም በሰፊው እንተነፍሰዋለን !! በአላህ ፈቃድ እንቀጥላለን!! ሰለፊና ኸለፊን መደባለቅ ትልቅ ዙልም ነው !!
የሚገርመው ነገር ነጃሳው አህባሽ ከብልሹ የመንግስት አካላት ጋር ሙስሊሞችን ሲያሳስር በነሱም ላይ ሲዝት በወቅቱ "ሙናፊቅ " ብላችሁት ነበር። ዛሬ በተራችሁ መዛትን ያዛችሁ !! አየ እስስቱ ኢኽዋን! ! ብልሹው አሽዐሪ! !
ቀዷ ያለበት ሰው የሸዋልን ስድስት ቀን መፆም ይችላል?
~~~~~`
የረመዳን ፆም ቀዷ ያለበት ሰው ቀዷውን ሳይፆም የሸዋልን ስድስት ቀን መፆም አይቻልም የሚሉ ፈትዋዎች በሰፊው ከመሰራጨታቸው የተነሳ ሌላ የተለየ (መፆም ይቻላል የሚል) ፈትዋ ያለ እስከማይመስል ደርሷል። እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው።
① ለቀዷው ሰፊ ጊዜ ስላለና
② የሸዋል ጊዜ አጭር ስለሆነ
ከቀዷ በፊት ሸዋልን መፆም ይቻላል የሚለው የብዙሃን ዑለማዎች አቋም ነው። (ቀዷው ትንሽ ከሆነ ግን ግዴታውን አስቀድሞ ከዚያ የሸዋልን 6 ቀን ያስከትላል።)
ከስር ያያዝኩት የሸይኽ በድር ኢብኑ ዐልይ አልዑተይቢይ ፈትዋ ይህንኑ ሐሳብ የሚያጠናክር ነው።
youtu.be/P7hg2EzntxA
ለኒካሕ ሃላፊ (ወልይ) የሚሆኑት እነማን ናቸው?
============================
ክፍል አንድ:– ያለ ሃላፊ (ወሊይ) ኒካሕ ዋጋ አለው?
~~~~~~~~~~~~~~~~
በመጀመሪያ ወሊይ ለኒካሕ ወሳኝ ቅድመ ሁኔታ ነው። ያለ ወሊይ እውቅና የተፈፀመ ጥምረት ፈፅሞ ከጋብቻ አይቆጠርም። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:–
(لا نكاح إلا بولي )
"በወሊይ ካልሆነ በስተቀር ኒካሕ የለም!!" [አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል።]

* ስለዚህ ፈትም ሆነች ልጃገረድ አንዲት ሴት ያለ ወሊይ ፈፅሞ ልታገባ አይፈቅድላትም። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:–

أَيُّمَا امْرَأَةٍ نُكِحَتْ بِغَيْرِ إِذْنِ وَلِيِّهَا فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ، فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ، فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ
"ያለ ወሊዩዋ ይሁንታ የተገባች የትኛዋም ሴት ጋብቻዋ ውድቅ ነው! ጋብቻዋ ውድቅ ነው! ጋብቻዋ ውድቅ ነው!" [አቡ ዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።]

ክፍል ሁለት:– ወሊይ የሚሆኑት እነማን ናቸው?
~~~~~~~~~
ወሊይ የሚሆኑት በቅደም ተከተል የሚከተሉት ናቸው:–
1ኛ:– አባት፣
2ኛ:– የአባት አባት፣
3ኛ:– ወንዶች ልጆች፣
4ኛ:– ወንድም፣
5ኛ:– የወንድም ልጆች፣
8ኛ:– አጎቶች …እያለ ይቀጥላል።

* በአባትም በእናትም የሚገናኝ ወሊይ በአባት ብቻ ከሚገናኘው ይቀደማል።
* ተቀዳሚ የሆነው ወሊይ በቀላሉ የማይገኝ ከሆነ ተራውን ጠብቆ ሌሎች ወሊዮች ኃላፊነቱን ይወስዳሉ።

* አንድ ሰው ወሊይ ለመሆን
~~~~~~~~~~~~~~~~~
• ሙስሊም መሆን አለበት። ካፊር ወሊይ ሆኖ ሊድር አይችልም።
• አእምሮው ጤነኛ መሆን አለበት።
• ለአቅመ ኣደም የደረሰ መሆን አለበት።
• ወንድ መሆን አለበት።

* ወሊይ ከነ ጭራሹ ከሌለ ወይም ለአቅመ ኣደም የደረሱ ካልሆኑ ቃዲ ወሊይ ይሆናል።
َ (فالسلطان ولي من لا ولي له )
"አስተዳዳሪ ወሊይ ለሌለው ወሊይ ነው።" [አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል]

* ወሊይ (ሃላፊ) በቅርብ ከሌለ ሌላ ሰው መወከል ይችላል። ውክልናው እንዲሁ "ይበጃል ላልከው ዳርልኝ" አይነት ክፍት ሊሆን ይችላል። ወይም "ለእከሌ ዳርልኝ" የሚል የተገደበ ሊሆን ይችላል።
* የሸሪዐ ቃዲዎች በሌሉበት ሃገር የኢስላማዊ መርከዝ ሃላፊ ወይም የመስጂድ ኢማም ወሊይ ሆኖ መዳር ይችላል።
* ወሊዩ ሺርክ ላይ የተዘፈቀ ወይም ሶላት የማይሰግድ ከሆነ ተራው ተጠብቆ ወደተሻሉት ኃላፊነቱ ይሻገራል።
* ወሊዩ #ያለ_ተጨባጭ_ምክንያት ለመዳር ፈቃደኛ ካልሆነ ተራው ተጠብቆ ወደተሻሉት ኃላፊነቱ ይሻገራል። ሌሎችም ፈቃደኛ ካልሆኑ ወደ ቃዲ ይሻገራል።

ጥንቃቄ ① ተራው ሳይጠበቅ (ሌሎች ወሊዮች እምቢ ሳይሉ) ዘሎ ወደ ቃዲ አይኬድም።
ጥንቃቄ ② ወላጅ ወይም የሚመለከተው ወሊይ በተጨባጭ ምክንያት ከከለከለ ሌሎች አማራጮችን መጠቀም አይፈቀድም። አርፎ መቀመጥ ነው።
ጥንቃቄ ③ የወሊዮች ምክንያት አሳማኝ ባይሆን እንኳ ያለ ወሊይ ይሁንታ የሚገባበት ጋብቻ አደጋዎች ሊኖሩት ስለሚችሉ ሴቶች ከመግባታቸው በፊት የሚችሉትን ያክል ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል። ዛሬ ብዙ ሰው ስነ ምግባሩ ወርዷል። ሴቷ ከቤተሰብ ተቀያይማ የገባችበት ጋብቻ ወይ ተመልካች አጥታ የሰቆቃ ህይወት ስትገፋ ወይ ደግሞ እንደ ዋዛ እየፈረሰ "ከሁለት ያጣች" ስትሆን ማየት እየተለመደ መጥቷል። ስለዚህ ከፍ ያለ ስጋት ካለ የቤተሰብ ተቃውሞ ተጨባጭ ባይሆን እንኳ መግባት አይገባም። ወላሁ አዕለም!!
ሙብተዲዕ ላይ አትማር!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል:–

"አንደበት ርቱእ የሆነ ማራኪ የአነጋገር ክህሎት ያለው ሙብተዲዕ ብናገኝ ከሱ ዘንድ ልንቀመጥ አይገባም። ምክንያቱም ሙብተዲዕ ነውና!! ለምንድን ነው የማይፈቀደው?

1⃣ አንደኛ:– ተንኮሉን ስለምንሰጋ ነው። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ከአገላለፅም ድግምት አለ" ብለዋልና። ቢድዐው ላይ እንስማማው ዘንድ አእምሯችን ላይ ሊደግምብን ይችላል።

2⃣ ሁለተኛ: – ተቀምጠን መከታተላችን ይህን ሙብተዲዕ ያበረታታዋል። በዙሪያው የሚሆኑ ሰዎች እንዲበዙ እናደርጋለን። ታዋቂዎችና ክቡራን ሰዎች ሊቀመጡ ይችላሉ። ይሄ ደግሞ መኮፈስን እና በቢድዐው መጎረርን ይጨምረዋል።

3⃣ ሶስተኛ: – ከሙብተዲዑ ዘንድ የሚቀመጠው ሰው በክፉ ይጠረጠራል። ይህ የሚስተዋለው ግን ዘግይቶ ሊሆን ይችላል። ሰዎች የቢድዐ ባለቤት ዘንድ ስትሄድ ለጊዜው ባይገለጥም በክፉ ይጠረጥሩሀል። ስለዚህ እውቀት ፈላጊ የሆነ ሰው ከቢድዐ ሰዎች ሊርቅ ይገባል። ኧረ እንዲያውም ምራቁ ግዴታው ነው።"

📚 [ሸርሑል ሒልያ: 314]
"ነፃ ትርጉም"
ሪፍቅ (ልስላሴ)
አላህ ለፍጡራኖቹ አዛኝ ነው። ለዚህም ስለሆነ በተውሂድ ያዛቸዋል፣ ሽርክን እንዲርቁ ያስጠነቅቃቸዋል። በተውሂድ ላይ ኖረው፣ ሽርክን ከነባለቤቶቹ ርቀው፣ በተውሂድ ላይ ከሞቱ ጀነት የሚባል ልብ ጠርጥሮት፣ ጆሮ ሰምቶት፣ አይን አይቶት የማያውቅ አገር ተዘጋጅቶላቸዋል።
በተገላቢጦሹ አዛኙ አላህ፣ ፍትሃዊ፣ አያያዙ የበረታ፣ አሸናፊ ፈራጅ ነውና በሱ ላይ የሚያጋሩትን "አጋርያን እርኩሶች (ነጃሳዎች)" ናቸው ሁሉ ብሎ ጠርቷቸዋል። በዱንያ ውርደትን፣ በአኸይራ አሳማሚ ቅጣትን አዘጋጅቶላቸዋል። አላህ ይጠብቀን።
ልክ እንደዚሁ ለአማኞች ከነፍሳቸው በላይ የሆኑት ውዱ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አዛኝ ናቸው። በጣም አዛኝ ከመሆናቸውም የተነሳ ሰዎችን ዘላለም አለም እስታ ውስጥ የሚከታቸውን ሽርክ
1) እያዩ እንዳላዩ ዝም አላሉም፣
2) በሽርክና ቢድአ ጉዳይ ላይ አንድ ነን ብለው አልተስማሙም፣
3) ወደ ሽርክና ቢድአ የሚጣራን አይደለም ወደነዚህ መንገድ የሚወስዱን ነገሮች ዝም አላሉም።
በጣም አዛኙ ነብይ ስለ ቢድአ ሲያስጠነቅቁ ፊታቸው ደም ይለብስ ነበር፣ ይቆጡ ነበር ምክንያቱም ቢድአ ነውና የዚህ ኡማ ትልቁ ፀር።
ስለ ሪፍቅ ሲወራ ባይጠቀስም አብሮት ሺዳ በውስጡ አለ።
እዝነትም (ልስላሲ)፣ ጥንካሪም ቦታ ቦታ አላቸው። መቼም አንድ ዳኢ ሽርክን ስለሚያክል ታላቅ አደጋ እያስተማረ ለምን ይኮሳተራል? ተብሎ ሊጠየቅ አይገባውም። ምክንያቱም የነብያትም፣ በተለይ የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምም አካሄድ ይሄ ነበረና።
ቢድአና ወንጀልንም ለያይተን ማስቀመጥ አለብን። የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ዘንድ ወንጀለኞች (መጠጥ ጠጪዎች፣ ዝሙት የሰሩ) ሲመጡ የነበረውን አቀባበል አንርሳ። ልስላሲ ነበር ከመልክተኛው ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የነበረው። እኚሁ የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ጁምአ ኹጥባቸው ላይ "አዳዲስ በዲን ላይ ያሉ ፈጠራ ጭማሪዎችን ተጠንቀቁ፣ ሁሉም ፈጠራ ጥመት ነው፣ ሁሉም ጥመት የእሳት ነው" ሲሉ ምን ያህል ይቆጡ እንደነበር የሀዲስ መዛግብትን ማየት ይበጃል።
አንድ እናት ልጇን ብትገርፍ፣ አንድ አባት ልጁን ቢቆጣ እንዲስተካከልላቸው እንጂ ጠልተውት አይደለም። ስለሱ የማይጨነቁ ቢሆን ኖሮ ልጃቸውን ከነመጥፎ ባህሪው ይተውት ነበር።
ልክ እንደዚሁ ሁሉ መጥፎ ነገር ሽርክ፣ ቢድአ፣ መሀይምነት፣ ድራማ፣ ፊልምና የመሳሰሉት ተስፋፍተው ሲያዩ የአላህ ባርያዎች ስለሚያዝኑ ነው ለኡማው ያ ሁሉ ውርጅብኝ ከየአቅጣጫው እየወረደባቸው ሀቁን የሚናገሩት። አላህም ለባሮቹ ስለሚያዝን ነው አዛኝ ከመሆኑም ጋር ማስጠንቀቂያዎችንና ዛቻዎችን አብሮ ያስቀመጠው። ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምም እንደዚሁ እዝነት በሚያስፈልገው ቦታ እዝነት፣ ጠንከር ማለት በሚያስፈልገው ቦታ ጠንከር ብለው ያሳዩን።
አሁን ያለንበት ወቅት ላይ በጣም እዝነት ያስፈልገዋል ይህ የማይካድ እውነታ ነው። ይህ ማለት ግን ቢድአና ሙብተዲ ላይ አለመናገር ማለት አይደለም። ቢድአና ሙብተዲ ላይ መናገር ለኡማው በጣም እጅግ በጣም ከማዘን ነው። ምክንያቱም ኢስላምንና ሙስሊሞችን ከውስጥ የሚንደውና የሚያዳክመው አዳዲስ መንገዶችና የቢድአ ሰዎች ናቸውና።
አላህ ሁሉንም በቦታው ላይ ከሚያስቀምጡት ባርያዎች ያድርገን። አላህ ሆይ! እውቀትን ጨምርልን፣ በምናውቀውም የምንሰራ አድርገን፣ በፈተና ወቅትም በሃቅ ላይ ከሚፀኑት አድርገን።
https://t.me/SadatTextPosts
ሐጅ እና ለይለቱል ቀድር
በለይለተል ቀርድ የዘንድሮ ሐጅ አድራጊዎች እንማን እንደሆኑ ይወሰናል፡፡
[Q 44:4] فِيهَا يُفْرَقُ كُلُّ أَمْرٍ حَكِيمٍ
በውስጧ (በለይለተል ቀድር) የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡
አብደላህ ኢብን አባስ (ረድየላሁ አንሁ) ይህንን ሲያብራሩ እንዲህ አሉ
“ከኡሙል ኪታብ (ከለውሀል መህፉዝ) በለይለተል ቀድር በአመት ውስጥ የሚከሰቱት ነገሮች ከሞት፣ ከህይወት፣ ከሲሳይ (ሪዝቅ)፣ ከዝናብ፣ ሐጅ አድራጊዎችም ጭምር እገሌ ሐጅ ያደርጋል፣ እገሌ ሐጅ ያደርጋል ሁሉ ይባላል ተብሎ ውሳኔው ይገለበጣል፡፡”
https://t.me/SadatTextPosts
ሐጅ እና ለይለቱል ቀድር
በለይለተል ቀርድ የዘንድሮ ሐጅ አድራጊዎች እንማን እንደሆኑ ይወሰናል፡፡
[Q 44:4] فِيهَا يُفْرَقُ كُلُّ أَمْرٍ حَكِيمٍ
በውስጧ (በለይለተል ቀድር) የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡
አብደላህ ኢብን አባስ (ረድየላሁ አንሁማ) ይህንን ሲያብራሩ እንዲህ አሉ
“ከኡሙል ኪታብ (ከለውሀል መህፉዝ) በለይለተል ቀድር በአመት ውስጥ የሚከሰቱት ነገሮች ከሞት፣ ከህይወት፣ ከሲሳይ (ሪዝቅ)፣ ከዝናብ፣ ሐጅ አድራጊዎችም ጭምር እገሌ ሐጅ ያደርጋል፣ እገሌ ሐጅ ያደርጋል ሁሉ ይባላል ተብሎ ውሳኔው ይገለበጣል፡፡”
https://t.me/SadatTextPosts
መርከዝ አት-ተውሒድ የቁርዓን ሒፍዝ ማዕከል
የክረምት ኮርስ ለልጆች እና ለወጣቶች አዘጋጅቷል
1) ቁርዓን ላልቀሩ ተማሪዎች ቁርዓንን ከቃኢዳ ኑራንያ ጀምሮ ማስቀራት፣
2) ሙራጅዓ ለመቅራት፣
3) የተለያዩ የኪታብ ቂርዓቶች (አቂዳ፣ ፊቅህ፣ ሀዲስ)…
4) አጠቃላይ ተርቢያ
ኮርሱ ከመጀመሩ በፊት በሚከተሉት ስልኮች መመዝገብ ይችላሉ
0910609894 / 0947052919 / 0972543622