Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል: –

أيعجز أحدكم أن يقرأ في ليلة ثلث القرآن؟

"አንዳችሁ በአንድ ሌሊት የቁርኣንን ሲሶ መቅራት ያቅተዋልን?"

"እንዴት የቁርኣንን ሲሶ ይቀራል?" ሲሏቸውም

قل هو الله أحد تعدل ثلث القرآن

"ቁል ሁወልላሁ አሐድ የቁርኣንን ሲሶ ትስተካከላለች!!"

[ሙስሊም]
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor (MuhammedSirage M.Nur G)
ድሮና ዘንድሮ
ስንቱ አለፈ! !
ከአመታት በፊት በርካታ አመታትን ባሳለፍንባቸው ሰፈሮች ውስጥ ባይተዋር ሆነን ኖረናል ። "መድኸሊዮች" የሙስሊሙ ጠላቶችና አንድነቱ ላይ የተጋረጡ እንቅፋቶች ናቸው ተብሎ በኢኽዋኖቹ ብዙ ተብሎና ተቀጥፎ ነበርና ብዙ ነገሮች ሲደርሱብን ቆይተዋል ። መስጂዶች ሶስት እና አራት ሆነን መቀመጣችንና ማውራታችን እንኳን ብቻውን እንደ ከባድ ሴራ ይቆጠር ነበር ።
በተልይ ደግሞ እነ " ኮሚቴዎች" እስር ቤት ውስጥ በነበሩ ግዜ የሙስሊሙን አንጀት መብላት ቀላል የሆነላቸው ኢኽዋኖች ጉዳዩን ብዙ አትርፈውበት ነበር ። "ኮሚቴውን የሚያከፍሩ ካድሬዎች" አሉን ። ከዚህም አልፈው " ሙናፊቆች " ብለው ፍርደ ገምድልን ብይን የበየኑብን ነበሩ ።
ለልጅ ለሽማግሌው " እነዚህ ተክፊሮች ናቸው!" በማለት ቀጠፉብን ።
መቼም ውሸት የኒህ ቀጣፊዎች ትልቅ እሴትና የማይነጠላቸው ደዌ ነውና የነሱ መዋሸት አያስደንቅም! !
የዛሬ አምስት አመት አካባቢ ይመስለኛል ። ወቅቱ የግዜው ክፉ ገዢዎች በሙስሊሙ ላይ አሰቃቂ ግፍን ሲፈፅሙበት የነበረ ነው ። ታዲያ አንድ ረመዳን ላይ ግፉ በጅጉ ድንበር እያለፈ ነበር ። በዚህ ወቅት ከወንድሞች ጋር አንድ መስጅድ ላይ ተቀምጠናል ። በእለቱ በበርካታ ወንድሞችና እህቶች ላይ ታጣቂዎች።ከበድ ግፍ መስራታቸው ሰማሁ ። በነገሩ አለቅጥ ተረበሽኩ ። የለመድኩትንና የምፈልገውን ያህል ቁርአን መቅራትም ሆነ ለጥናቴ ያዘጋጀሇቸውን ኪታቦች ማየት ተሳነኝ ። በጣሙን ተረበሽኩ ።
ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ከመስጅዱ በር ወጣ ስል በረንዳ ላይ የተቀመጡ የኢኽዋንን መንሃጅ በማራመድ የሚታወቁ ሰዎች ተቀምጠዋል السلام عيكم
አልኳቸው ። አጉተመተሙ እንጂ አልመለሱለኝም ነበር ። ነገሩ አሰገርሞኝ ወደ ውስጥ ተመልሼ ገባሁ ። ጥቂት ከቆየሁ በሇሏ ሰላምታ መመለስን የነፈጉኝ ሰዎች እኛ ላይ እንዲህ ማለታቸውን ሰማሁ " በሙስሊሙ ላይ በሚደርሰው ድብደባ የሚደሰቱ ናቸውና ከደረሰብን ጉዳት ምንም ነገርን አትንገሯቸው ።
ቅጥፈታቸው፣ ነገራቸው ሁሉ ገረመኝ ።

በዛው ሰሞንም " ኮሚቴውን የሚያከፍሩ ተክፊሮች ብለውን አረፉ ። በእንዲህ አይነት መልኩ ሲወጉን ከረሙ ። ጥቂቶችንም በቅጥፈታቸው በመጥለፍ እኛን ጠላት አድርገው እንዲይዙ ማድረግ ችለው ነበር ። ቆይተው ግን ቅጥፈታቸው ደምቆ ታየ ፣ የቀድሞ ሰሚዎቻቸው እንኳን ጆሮ ነፈጓቸው ።
.......

ይሄ ሁሉ አለፈ! ! ብዙ ነገርን ሲጭኑብን ከነበሩት ውስጥ በርካቶች ሰለፊያን ተቀላቀሉ! አንዳንዶቹ ደግሞ ይህንን የፀዳ መንሃጅ ባይቀላቀሉም እንኳን የቀድሞ ጥላቻቸው ከስሞ ቢያንስ " ሙስሊም ወንድሞቻቸው" መሆናችንን በመቀበል በመልካም ያስተናግዱን ጀመር! ብዙ የተባልንበት መስጅድ ውስጥ ሰለፊያ ሲሰበክ ሰማን! በርካቶች ሰለፊይ ወዳጆቻችን ሆነው አነጉ! !
በርካታ ቤተሰብ የናንተን ዝቅጠት ተገነዘበና ሰለፊያን ተቀላቀለ! !!
ዛሬ ደግሞ የከፋው ውርደታችሁ ይበልጥ እየጎላ ሄደና በብዙ እይከሰራችሁ ትገኛላችሁ ።
وقل جاء الحق وزهق الباطل إن الباطل كان
زهوقا
ኢኽዋኖች ሆይ! ዛሬም አለን! በናንተ ላይ ዝምታን የመረጠ ማየታችሁ ልባችሁን አይሙላው ። እናንተን የሚያቆስል ዛሬም በብዙ ሞልቷል ።የሰበሰባችሁትም ይሁን ሰበሰብንው የምትሉት ሁሉ አያስፈራንም!
በመካከላችን ያለው ውጥረትና ጠላትነት ቀጣይ ነው— ወደሱና እስክትመለሱ ድረስ
t.me/Muhammedsirage
"የተረከብነው ባዶ ካዝና ነው። ድረሱልን" እያሉ ነው አዲሶቹ መጅሊሶች።

① የቀድሞዎቹ የዘረፉትን ቢመልሱ
② ያሁኖቹ ከመመረጣቸው ቀደም ብለው በቅርቡ በየክፍለ ሃገራቱ እየዞሩ የሰበሰቡትን ቢያስገቡ
ተደምሮ የመጅሊሱን ሰፋፊ ሽንቁሮች ይደፍን ነበር። ግን እነዚህ "የዘረፋችሁትን መልሱ" ሲሉ እነዚያ "የሰበሰባችሁትን አስገቡ" ይላሉ። "እባብ ለእባብ ይታያያል ካብ ለካብ!"
እዚህ መሐል የህዝብ ገንዘብ ተበላ። ለምን እንደሚውል አላህ ይወቅ። ተበልቶ ቢቀር እፎይታ ነበር። የባሰ አለኣ!! የሚያስፈራው ህዝብ ለሚያጠም አፍራሽ አላማ መዋሉ ነው።

ብቻ በሁለት አቅጣጫ የተሰበሰበ የህዝብ ንብረት መድረሻው ሳይታወቅ ህዝበ ሙስሊሙ ዳግም "እጅህ ከምን?" እየተባለ ነው። መጪውም ሐጅ አይደል? የመጅሊሱን ለውጥ ተከትሎ ቅናሽ እየጠበቀ ያለው ህዝብ ከወዲሁ ተስፋውን እንዲያሳሳ እየተሰራበት ሊሆን ይችላል። ምን ይታወቃል?!
የሑደይቢያ ውል ለከንቱ አላማ ሲውል
≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈
[ክፍል አንድ]:– በመልካም ነገር ላይ መተባበር በጥፋት ላይ ለመተባበር ሽፋን አይሆንም
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
የቢድዐ አጋፋሪዎችን ጮቤ ላስረገጠው ስምምነት ድጋፍ የሚሰጡ አካላት አካሄዳቸውን በመልካም ነገር ላይ እንደመተባበር አድርገው ሲያቀርቡ በተደጋጋሚ እያየን ነው። ይህን አካሄድ የሚነቅፉ ወንድሞችን ደግሞ "ከቢድዐ ሰዎች ጋር ፈፅሞ በመልካም ነገር ላይ መተባበር አይቻልም" እንደሚሉ አድርገው ይስሏቸዋል። የራስን ጥፋት በጥሩ መሰየም + ሌሎችን ባልዋሉበት መወንጀል= ድርርብ ጥፋት!!

የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል:–
﴿ ﻭَﺗَﻌﺎﻭَﻧﻮﺍ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟﺒِﺮِّ ﻭَﺍﻟﺘَّﻘﻮﻯ ﴾
"በመልካም ነገርና አላህን በመፍራት ላይ ተጋገዙ።" [አልማኢዳህ: 2]

በመልካም ነገር ላይ ማለት በቀጥታ በመልካም ነገር ላይ ነው። አለቀ።
የአሕባሽና የኢኽዋን እርቅ "መልካም ነገር" ለመሆኑ አንዳችም ማረጋገጫ የለውም። እንዲያውም ሰፊ ስጋት ነው ከፊት የተደቀነው። ጅምሩንም በተለያየ መልኩ እያየነው ነው። በዚህ ላይ በአንዳንዶች የሚጠቀሱት "ፋይዳዎች" ቀድመው አቋም ከያዙ በኋላ በባትሪ የሚፈልጓቸው ምናባዊ ስኬቶች ናቸው።

የሚደንቀው ከቢድዐ ጭፍሮች ደጅ መልከስከስን "ሚዛናዊ" ለማድረግ ሲባል ይህን የሚነቅፉ ወንድሞችን በፅንፈኝነት መሳላቸው ነው። ይህ የመጀመሪያ ውንጀላቸው አይደለም። ትላንትም ሰለፍያን ከሚያጠለሸው የነ ያሲን ኑሩ ዘመቻ ማግስት "ጉላት" /ወሰን አላፊዎች/ የሚል እሩምታ የተከፈተው ለኢኽዋኖች አልነበረም።

በነገራችን ላይ ከሙስሊም አንጃዎች ጋር "በመልካም ነገር መተባበርን" እንደምንቃወም በአንዳንዶች የሚስተጋባው ጩኸት ነጭ ውሸት ነው። እንኳን ከሙስሊም ጋር ከካፊርም ጋር በመልካም ነገር ላይ መተባበር እንደሚገባ እናምናለን። እደግመዋለሁ! እንኳን ከሙስሊሞች ጋር ከከሃዲዎች ጋርም በመልካም ነገር ላይ መተባበር እንደሚገባ እናምናለን።
ግና አንዳንዶች የነብያት ክብር በሚጎደፍበት፣ ሸሪዐ በሚጣስበት፣ …መድረክ ላይ መገኘታቸውን፣ ከቢድዐ አጫፋሪዎች ጋር እጅ ለእጅ እየተያያዙ ህብረታቸውን መግለፃቸውን፣… "በመልካም ነገር ላይ መተባበር" ብለው ሸላልመውታል። ይህን አካሄድ የሚነቅፉ ደግሞ ፅንፈኞች እየተባሉ ነው፣ ጉላት!! ይህ ነው አተያያቸው።

ከዚያስ? በኢኽዋን ላይ የዶለደመው ብእር እና የተለጎመው አንደበት ቀለሙን እየቀያየረ እንደተለመደው "ወደ ጎን" ለመውጋት አክቲቭ ሲሆን ይታያል።

* "ከስሜት ተከታዮች ጋር እጅ ለእጅ እየተያያዙ "አንድ ነን" ማለትን እና ከአሕባሽና ኢኽዋን የእርቅ ድግስ ላይ መገኘትን ከ'ወላእ ወልበራእ' ዐቂዳ ጋር ግንኙነት እንደሌለው ሊግቱን ይዳዳቸዋል።
– እጅ ለእጅ እየተያያዙ አንድ ነን ማለት ነው በመልካም ላይ መተባበር?
– የሙብተዲዖችን የእርቅ ድግስ ማድመቅ ነው በበጎ ነገር ላይ መተባበር?
– የነብያት ክብር ሲጎደፍ እርምት መስጠት የማይቻልበት መድረክ ላይ መገኘት ነው በጥሩ ነገር ላይ መተባበር?
– መቋጫው ላልታወቀውና መርዛማ ሐሳቦችን ላጨቀው እርቅ "እንኳን ደስ ያለን" ማለት ነው በመልካም ነገር ላይ መተባበር?

[ክፍል ሁለት]:– "ሀጅር" /ማኩረፍ፣ መራቅ/
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ጭራሽ "በተሳሳቱ ሰዎች ላይ የሚተገበረውን 'ሐጅር' /ማኩረፍ/ ሙሉ በሙሉ ተፈፃሚ ለማድረግ በማሰብ እንዲህ አይነት ስህተት ላይ የሚወድቁም አሉ" ይባልልናል። እንዲህ ነው ሳይረዱ መወረፍ። ለማጠልሸት እንዲመቻቸው ያላልነውን ይለጥፉብናል። ክፉ በሽታ!
ብቻ የሚሳሳት ሰው ብዙ አይነት ነው። ትልልቅ እና ትንንሽ ወንጀሎች፣ ግልፅ ወንጀሎችና ቢድዐዎች፣ ሺርክና ኩፍር የሆኑና ያልሆኑ ወንጀሎች፣ ተሻጋሪና ራስ ላይ የተገደቡ፣… ።
ወንጀለኞችም እንዲሁ ብዙ አይነት ናቸው። ሙብተዲዕና "ፋሲቅ"፣ ወደ ጥፋቱ የሚጣራና የማይጣራ፣ ጧት ማታ ሱንናንና የሱንና ዑለማዎችን የሚያጠለሽና ፊትናው በንፅፅር የቀለለ፣ ቢድዐውን ለማሰራጨት አቅም ያለውና የሌለው፣ ወዘተ።
"በመልካም ነገር ላይ በመተባበር" ስም ከሚቀማመጧቸው ውስጥ ‘ሀጅር’ የማይገባው የትኛው ነው? "ይሻላሉ" የሚባሉት አይደሉ’ንዴ "መዳኺላ" እያሉ ሰፋፊ ዘመቻ የከፈቱት? የሱንና ዑለማዎችን ሌት ከቀን የሚያጠለሹት? በየመሳጂዱ ደርስ የሚከለክሉት? በግድያና በድብደባ የሚያስፈራሩት? በሐሰት እየከሰሱ፣ በሐሰት እየመሰከሩ የሚያሳስሩት? እነዚህን "ሀጅር" ማድረግ /መራቅ/ በምን መመዘኛ ነው እንደ ስህተት የሚቆጠረው?!

* በተረፈ " 'ሀጅር' ሰዎችን ለማረምና ለመገሰፅ ሲባል የሚፈፀም ነው" የሚለው የአንዳንዶች ሙግት ፈፅሞ ስህተት ነው። ‘ሀጅር’ የሚፈፀምባቸው ሌሎችም ምክንያቶች አሉና። በቅጡ ሳይረዱ ሌሎችን ለማሳጣት ከመቻኮል ቀድሞ በስርአት መረዳት ይቀድማል። ለማንኛውም ‘ሀጅር’ ከማረምና መገሰፅ ያለፉ ፋይዳዎች አሉት።
① ‘ሀጅር’ እራስን ለቢድዐና ለስሜቶች ለማጋለጥ ይጠብቃል፣
② ለአላህ ብሎ መውደድና ለአላህ ብሎ መጥላት /‘ወላእ ወልበራእ’/ ከኢማን ቋጠሮዎች ውስጥ ይበልጥ ጠንካራው ነው። ‘ሀጅር’ ይህ ቋጠሮ እንዳይጎዳ ይጠቅማል (ከሙብተዲዕ ጋር መቀማመጥ የለመደ ሰው በነሱ ላይ ጠንካራ አቋም አይኖረውም)፣
③ ‘ሀጅር’ ህዝብ ከሙብተዲዖች አንፃር ጥንቃቄ እንዲኖረው በማድረግ በቢድዐ ተውሳክ የመጠቃቱን እድል ይቀንሳል (በዚህ ላይ አንፀባራቂ የሆኑ በርካታ የሰለፎችን እርምጃዎች መዘርዘር ይቻላል)፣
④ ‘ሀጅር’ የሙብተዲዕን ቅስም በመስበር ቢድዐውን ለማሰራጨት ወኔ እንዳይኖረው ያሸማቅቃል። ለዚህም ፍቱን መድሃኒት እንደሆነ የሰለፎች አካሄድ ያሳያል።

★ ባጭሩ የ ‘ሀጅር’ ፋይዳዎች:–
① የሚራቀውን ወንጀለኛ፣
② ‘ሀጅር’ አድራጊውን አካል እና
③ ህዝበ ሙስሊሙን የሚመለከት ነውና ከአንድ አንግል ብቻ ማየት የራስን የአመለካከት ጥበት ነው የሚያሳየው።
እንደ ጥቅል ‘ሀጅር’ ለፋይዳ ነው የሚደረገው ቢባል ልክ ይሆናል። ዑለማዎች ስለ ‘ሀጅር’ እና ጥንቃቄዎቹ የሚናገሯቸውም በዚህ ዙሪያ የሚሽከረከሩ ናቸው። እንጂ ‘ሀጅር’ ኪታብ ላይ ብቻ የሚገኝ ወደ መሬት የማይወርድ ባዶ ሐሳብ አይደለም።

ምናባዊ ህልሞችን ለማሳካት በትንሽ በትልቁ ከቢድዐ ሰዎች ጋር መቀማመጥ ግን ከሸሪዐዊ ‘ሀጅር’ ጋር የሚጣረስ እንጂ አንዳች ስኬት የሚያመጣ አይደለም። ጭራሽ ደግሞ ስለ ‘ሀጅር’ ከአንድ ዛውያ እየተመለከቱ "የሀጅር ፅንሰ ሐሳብ አልገባችሁም" የሚሉ ሰዎች አስቂኝ ናቸው። ለነገሩ ከራስ መከላከል የወለደው አባዜ እንደሆነ ይገባናል።

[ክፍል ሶስት]:– የሑደይቢያ ውል ለከንቱ አላማ ሲውል
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ከጥፋት ሃይሎች ጋር አላስፈላጊ መተሻሸት የሚፈጥሩ አካላት የሑደይቢያን ውል እንደ ሽፋን ሲጠቀሙ ማየት የጋራ ባህሪ ሆኗል።
በሑደይቢያ ውል ነብያችን -ﷺ- ከሙሽሪኮች ጋር ለ10 አመታት የሚቆይ ስምምነት ተፈራርመዋል። ምን አተረፉ?

① ሃይማኖታቸውን እንዲያስተምሩ፣ እንዲያስፋፉ እድል ሰጥቷል፣ ወደ ተለያዩ ሃገራት ወደ ኢስላም መልእክት ተልኳል፣
② ሌሎች ዘመቻዎችን ለማካሄድ አመቻችቷል (ለምሳሌ የሙእታህ እና የኸይበር ዘመቻዎች! ይህም ከባድ አደጋ የሚፈጥሩ ጠላቶችን ነው ያኮላሸው)፣
③ ለዋናው የመካ መከፈት መንገዱን ጠርጓል፣
④ አዲሱ ኢስላማዊ መንግስት ሌሎች ዘንድ ግርማ ሞገስ እንዲኖረውና እንዲከበር እንዲታፈር ሚና ተጫውቷል፣
⑤ በስምምነቱ መሰረት በቀጣይ አመት ዑምራ አድርገዋል።

ልብ በ
ሉ! በሑደይቢያ ስምምነት ወቅት ነብዩ -ﷺ- እንዲህ ብለው ነበር
" ﻭﺍﻟﺬﻱ ﻧﻔﺴﻲ ﺑﻴﺪﻩ، ﻻ ﻳﺴﺄﻟﻮﻧﻲ ﺧﻄﺔ ﻳﻌﻈﻤﻮﻥ ﻓﻴﻬﺎ ﺣﺮﻣﺎﺕ ﺍﻟﻠﻪ ﺇﻻ ﺃﻋﻄﻴﺘﻬﻢ ﺇﻳﺎﻫﺎ "
"ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ! ማንኛውንም የአላህን ድንጋጌዎች የሚያልቁበትን አንድ ጉዳይ ቢጠይቁኝ ሳላደርግላቸው አልቀርም።"

ይህ የነብዩ -ﷺ- ንግግር የአላህን ህግጋት ለመተግበር እስከሆነ ድረስ ከሙስሊም አንጃዎች ጋር ቀርቶ ከከሃድያን ጋርም መተባበር እንደሚገባ ያስገነዝባል። ኢብኑል ቀዪም እንዲህ ይላሉ:–
"(ከሑደይቢያ ውል ከሚወሰዱት ቁምነገሮች) ውስጥ፦ አጋሪዎች፣ የቢድዐ ሰዎች፣ ጋጠ-ወጦች፣ ወሰን አላፊ አማፅያንና በደለኞች ከተከበሩት የአላህ ድንጋጌዎች አንዱን ለሚያልቁበት ጉዳይ እርዳታ በጠየቁ ግዜ አዎንታዊ ምላሽ ይለገሳሉ። የጠየቁትም ይሰጣቸዋል። በዚህም ላይ እገዛ ይደረግላቸዋል። ምንም እንኳ ሌላውን ነገር ቢከለከሉም። #ክህደታቸውና_ድንበር_ማለፋቸው ላይ ሳይሆን የአላህን ህግጋት በሚያከብሩበት ላይ ይታገዛሉ። ከዚህ ውጪ ያለውን ይነፈጋሉ። አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆነና እርሱን የሚያስደስት ነገር ላይ እገዛን የፈለገ ማንም ይሁን ማን በዚህ ተወዳጅ ተግባር ላይ በሚደረግለት ትብብር ምክንያት ከዚህ #የከፋ_የተጠላ_ውጤት_እስካልተከተለ_ድረስ አዎንታዊ ምላሽ ይሰጠዋል። ይህ እጅግ ረቂቅ የሆነና ለነፍስ (መቀበል የሚያስቸግራት) ከባድና አስጨናቂ ርዕስ ነው።" [ዛዱል መዓድ 3/303]

ይስተዋል!

* በነዚህ ማስረጃዎች መሰረት ለተሻለ ጥቅም ሲባል መስዋዕትነት ሊከፈል እንደሚችል ነው።
* ትብብር ቢጠይቁ የሚታገዙት በመልካም እንጂ በሺርክና በቢድዐ ላይ አይደለም።
* የከፋ ውጤት በማያስከትል መልኩ እንጂ ለሺርኪያት፣ ለቢደዕና ለጥፋቶች እውቅና በሚሰጥ መልኩ አይደለም።
ታዲያ እነዚህን ማስረጃዎች ያለ አግባብ የሚመነዝሩ ሰዎች አሉ። የዛሬ 11 አመት በሱፍያና በኢኽዋን መካከል ውል ሲታሰር "እንዴት ተደርጎ…?" የሚል ተቃውሞ ሲነሳ ኢኽዋኖች ሑደይቢያን ነበር ያጣቀሱት። ትላንት "ሑደይቢያና እናንተ አራምባና ቆቦ ናችሁ" ሲል የነበረው አካል ዛሬ "ሑደይቢያ…" እያለ ነው። "የትላንቱ ውል ከዛሬ የከፋ ስለነበር ነው" እንዳይል ፈፅሞ ከእውነት የራቀ ነው። እንዲያውም የዛሬው የባሰ ነው። አቋራጩ ወይ "ትላንት ተሳስቼ ነበር" ነው። ወይ "ዛሬ ተሳስቻለሁ" ነው። ሁለቱም ግን የለም። "ትላንት ሲቃወሙን የነበሩት ዛሬ ተመልሰዋል" እየተባለ በኢኽዋን ፊታውራሪዎች መዘባበቻ መሆን ያሳቅቃል።
★ ብቻ የዛሬው ውል ከሑደይቢያ ውል በብዙ መልኩ ይለያል።
① የዛሬው ውል (አሽዐርያና ማቱሪዲያን፣ መውሊድን… በማካተት) ዐቂዳን ለድርድር ያቀረበ ነው። ሑደይቢያ ላይ እንዲህ የለም።
② የዛሬው ውል ተዋናዮች በግራም በቀኝም #በዋናነት ሁለት የጥፋት አንጃዎች ናቸው። ሑደይቢያስ ላይ?
③ የዛሬው ውል እጅግ ከባባድ ዐቂዳዊ ልዩነቶች ባልተፈቱበት "አንድነት" እየተዘመረበት ነው። ሑደይቢያ ላይ ፈፅሞ የመርህ መደባለቅ አልነበረም።
④ የዛሬው ውል ከሑደይቢያው በተለየ ሐቅን ለመጠበቅና ለማረጋገጥ ሳይሆን የተቋም ሽሚያ ላይ ያነጣጠረ ነው።
⑤ የዛሬው ውል በአንዳንዶች የሚታለሙ ስጋት ወለድ ምናባዊ ህልሞች እንጂ በቁርጥ የሚታወቁ ፋይዳዎች የሉትም። የሑደይቢያው ላይ በቀጣይ ዑምራ ሊያደርጉ፣ የአስር አመት የሰላም ውል በግልፅ የተቀመጡ ናቸው። እዚህስ ላይ? እንዲያውም አፍራሽ ነገሮች ናቸው በገሃድ የሚታዩት። "ጥሩ" የሚባሉት ነገሮች ውሉም ባይኖር የሚሰሩ ናቸው። ታዲያ የውሉ አስፈላጊነት ምኑ ላይ ነው?
⑥ የዛሬው ውል ‘ሙዳሀና’ እንጂ ‘ሙዳራ’ አይደለም። "የተጣላነው በጥቅም እንጂ ለእስልምና ብለን አልነበረም" ማለት፣ "ሁላችንም አንድ ነን" ማለት፣ የአሽዐርያ–ማቱሪዲያ፣ የመውሊድና መሰል ጉዳዮች፣… ባሉበት መስማማት በምን ስሌት ነው ‘ሙዳራ’ የሚባለው?!

* " 'ሙዳሀና' ለአንዳች ጥቅም ሲባል ሸሪዐዊ ገደቦችን በመጣስ የተከለከሉ ተግባራትን መፈፀም ወይም ከግዴታ ተግባራት መታቀብ" ነው አሉ። መልካም! ታዲያ በዚህ ውልና በሂደአጡ ላይ ስንት ሸሪዐዊ ጥሰቶች ናቸው የተፈፀሙት? ይሄኮ በገሃድ የሚታይ ሐቅ ነው።

* ኢብን ሐጀር -ረሒመሁላህ-
– "ዑለማዎች ‘ሙዳሀናን’ የሚተረጉሙት ፋሲቅ ከሆነ ሰው ጋር ምንም እንዳላጠፋ ሁሉ እርሱን መወዳጀትና የሚሰራው ስራ ትክክል እንደሆነ እውቅና እየሰጡ ከመጥፎ ከመከልከል መቆጠብ ነው" ሲሉት፤
– "ሙዳራት ግን በለስላሳ አገላለፅ የማያውቅን ሰው ማስተማር ፋሲቅን በተለይ ሐቅን አውቆ እንዲመለስ ማላመድ የሚያስፈልግ እስከሆነ በጥሩ ቃል ከጥፋቱ እንዲቆጠብ መምከር ነው" ብለዋል።

ይህን የዛሬውን ውል በዚህ የኢብኑ ሐጀር ንግግር የመዘነ ሰው ‘ሙዳራ’ ሳይሆን ‘ሙዳሀና’ እንደነገሰበት በቀላሉ ያገኘዋል።

* ኢማም ኢብኑል ቀዪምም የሁለቱን ልዩነት እንዲህ ሲሉ ገልፀውታል:–
– " 'ሙዳራ' የሚፈፅም ሰው ምሳሌው ልክ አንድ ህመምተኛን የሚያክም ሐኪም በሽተኛው ሳይሰቃይበት በሽታውን አግኝቶ ከስሩ የሚነቅል ህክምና እንደሚያደርግለት ነው።
– የ'ሙዳሀና' ምሳሌው ግን ሐኪም ሁኖ ለህመምተኛው ህክምና እንደማድረግ 'አይዞህ ቀላል ነው' እያለ በሽታውን አቃልሎ በማዘናጋት በሰውነቱ እንዲሰራጭ የሚያደርግ አይነት ነው።"
[አርሩሕ: 231]

ታዲያ የአሁኑ ውል በየትኛው ምድብ ላይ ነው የሚያርፈው?! ሰው መረጃ የሚሆንበትን ነገር እንዴት ያለ አግባብ ይጠቀማል?! በዚህ ውል እኮ ሁለት በሽተኞች "ጥቅም / መንግስት አጣልቶን እንጂ አንድ ነን" በማለት ዐቂዳዊ ልዩነቶችን ያንሳፈፉበት እርቅ ነው። ሶስተኛው ወገን በዚህ የተደበላለቀ አካሄድ ላይ አጃቢ ከመሆን ያለፈ ሚና የለውም! በፅሁፍም ሆነ በቃል ለመምከርማ ከውጭ ሆኖም ማድረግ ይቻላል። ምናልባት "ቀረብ ካላልን ሐሳባችንን በቀናነት አያዩትም" ከተባለ:–
① ስለቀረባችሁ ምን የተለየ ነገር ተገኘ? የትኛው የሰነዱ አንቀፅ ተለወጠ?
② ደግሞስ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ለውይይትና ለምክክር ከመገናኘት ባለፈ እጅ ለእጅ እያጣመሩ አንድነትን ማሳየቱን፣ ከመጥፎ ነገር ለመከልከል እድል በጠበበበት ጉባኤ ላይ መገኘቱን፣ "እንኳን ደስ ያለን" ማለቱን፣ "በእንኳን ደስ ያላችሁ" ድግሳቸው ላይ መገኘቱን ምን አመጣው? አስገዳጅ ችግር ያልተፈቀደን ነገር ቢያስፈቅድም (ያውም ዶሩራው ከኖረ) የሚፈቀደው በልክ አይደለም እንዴ?!
* ቢያንስ በተገኘንበት ጉባኤ ላይ "ሙሳም ቢመጡ፣ ዒሳም ቢመጡ፣…" ተብሎ የነብያትን ክብር የሚያጎድፍ ዘግናኝ ጥፋት ሲፈፀም ጩኸንም ቢሆን እንደምንም ተሟሙተን በቦታው ማረም አልነበረብንም?
* እሱ ካልሆነ ቢያንስ ጥሎ መውጣት አይገባም? አላህ እንዲህ አላለም እንዴ?!
(وَقَدْ نَزَّلَ عَلَيْكُمْ فِي الْكِتَابِ أَنْ إِذَا سَمِعْتُمْ آيَاتِ اللَّهِ يُكْفَرُ بِهَا وَيُسْتَهْزَأُ بِهَا فَلَا تَقْعُدُوا مَعَهُمْ حَتَّىٰ يَخُوضُوا فِي حَدِيثٍ غَيْرِهِ ۚ إِنَّكُمْ إِذًا مِثْلُهُمْ)

"በእናንተም ላይ በመጽሐፉ ውስጥ የአላህን አንቀጾች በርሷ ሲካድባትና በርሷም ሲላገጥባት በሰማችሁ ጊዜ በሌላ ወሬ ውስጥ እስከሚገቡ ድረስ ከእነሱ ጋር አትቀመጡ ማለትን በእርግጥ አወረደ፡፡ እናንተ ያንጊዜ ብጤያቸው ናችሁና፡፡"
[አንኒሳእ: 140]

* ይህም ይቅር! ከወጡስ በኋላ ለእንዲህ አይነቱ በህዝብ ፊት ለተፈፀመ ዘግናኝ ጥፋት ግልፅ ምላሽ መስጠት አይ
ገባም?! ነብዩ ﷺ እንዲህ አላሉም?
" مَنْ رَأَى مِنْكُمْ مُنْكَرًا فَلْيُغَيِّرْهُ بِيَدِهِ، فَإِنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَبِلِسَانِهِ، فَإِنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَبِقَلْبِهِ، وَذَلِكَ أَضْعَفُ الْإِيمَانِ ".

"ከናንተ መጥፎን ነገር ያየ በእጁ ይቀይረው። ካልቻለ በምላሱ፤ ካልቻለ ደግሞ በልቡ። ይሄኛው የመጨረሻ ደካማው እምነት ነው።" [ሙስሊም]

በተረፈ በየጊዜው የማያባራውን የአህሉል ቢደዕ ዘመቻ እንዳላዩ እያለፉ ቦታና ጊዜ ሳይለዩ ላገኙት ሁሉ ዘወትር ስለ ሪፍቅ፣ ሒክማ፣ ሚዛናዊነት ማቀንቀን ሚዛናዊነት ሳይሆን ከግትር ፅንፈኝነት ማዶ ያለ እንዝህላል ፅንፈኝነት ነው።
ፅሁፌን የምቋጨው በሸይኽ ሱለይማን አርሩሐይሊ ንግግር ነው።

* ጠያቂ:– "የደዕዋው መንገድ ስለተጠበበብን አላህ እስከሚያብቃቃን ድረስ ከአንድ የኢኽዋን ማህበር ለደዕዋ አላማ የሚሆን ቅርንጫፍ ሆነን ፈቃድ ወስደናል…
* ሸይኽ ሱለይማን: – (አላስጨረሱትም) "ወላሂ እየውልህ ወንድሜ! ኢኽዋን ማለት ልክ እንደ እከክ ናቸው። ከነሱ አርቁ ። ወደነሱ አትቅረቡ።
ታያለህ? ወደ ኢኽዋን ህብረት ከምትጠጉ አንድ አንድ ሰው ብትጣሩ ለናንተ የተሻለ ነው። (በመጠጋታችሁ) ደዕዋ ቢኖራችሁ እንኳ!!
ወንድሜ ሆይ! ኢኽዋንዮች ሊደርሱበት የሚያስቡት ጥቅም ኖሯቸው ካልሆነ በስተቀር ሰለፊይ የሆነን ሰው ለደዕዋ አያመቻቹለትም። ከሚያልሙት ጥቅም ሁሉ እጅግ ቅርብ የሆነው የሰለፍዮችን ህብረት መሰንጠቅ ነው፤ በወንድሞች መካከል የቃላት መወራወር እንዲኖር!"
ሱብሓነላህ! አስተዋዮች አስተውሉ!!! ሸይኹ ይቀጥላሉ:–

"ወደ ኢኽዋን አንጃ መጠጋት አይፈቀድም። ከኢኽዋነል ሙስሊሚን ጋርም ወደነሱ በሚጠጋ ነገር ላይ መስራት አይፈቀድም።

እናም ወንድሞቼ ሆይ! አደራዬ: እኛ በማንቆጣጠረው ነገር ላይ እንድንሰማራ የምንገደድ አይደለንም። ወላህ! የደዕዋው መንገድ ከተጠበበብንና መንገድ ካጣን ደዕዋ እንድናደርግ ብለን ሐራም ነገር አንፈፅምም!! በጭራሽ! ‘ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢልላህ’ / ብልሃትም ሃይልም በአላህ እንጂ የለም/ ብለን በምንችለው በዙሪያችን ያሉትን እንጣራለን። ማለፊያ! አላህን – ዐዘ ወጀል – የፈራ ሰው መልካምን እንጂ አያገኝም።"
https://youtu.be/udMx8Af6acQ

*ሰላም!*
(ኢብኑ ሙነወር፣ ግንቦት 23/2011)
ሸይኽ ሱለይማን አርሩሐይሊ "ከኢኽዋን ራቁ" ይሉናል።

* ጠያቂ:– "የደዕዋው መንገድ ስለተጠበበብን አላህ እስከሚያብቃቃን ድረስ ከአንድ የኢኽዋን ማህበር ለደዕዋ አላማ የሚሆን ቅርንጫፍ ሆነን ፈቃድ ወስደናል…

* ሸይኽ ሱለይማን: – (አላስጨረሱትም) "ወላሂ እየውልህ ወንድሜ! ኢኽዋን ማለት ልክ እንደ እከክ ናቸው። ከነሱ አርቁ ። ወደነሱ አትቅረቡ።

ታያለህ? ወደ ኢኽዋን ህብረት ከምትጠጉ አንድ አንድ ሰው ብትጣሩ ለናንተ የተሻለ ነው። (በመጠጋታችሁ) ደዕዋ ቢኖራችሁ እንኳ!!

ወንድሜ ሆይ! ኢኽዋንዮች ሊደርሱበት የሚያስቡት ጥቅም ኖሯቸው ካልሆነ በስተቀር ሰለፊይ የሆነን ሰው ለደዕዋ አያመቻቹለትም። ከሚያልሙት ጥቅም ሁሉ እጅግ ቅርብ የሆነው የሰለፍዮችን ህብረት መሰንጠቅ ነው፤ በወንድሞች መካከል የቃላት መወራወር እንዲኖር

"ወደ ኢኽዋን አንጃ መጠጋት አይፈቀድም። ከኢኽዋነል ሙስሊሚን ጋርም ወደነሱ በሚጠጋ ነገር ላይ መስራት አይፈቀድም።

እናም ወንድሞቼ ሆይ! አደራዬ: እኛ በማንቆጣጠረው ነገር ላይ እንድንሰማራ የምንገደድ አይደለንም (አላህ አንዲትን ነፍስ ከአቅሟ በላይ አላስገደዳትም)። ወላህ! የደዕዋው መንገድ ከተጠበበብንና መንገድ ካጣን ደዕዋ እንድናደርግ ብለን ሐራም ነገር አንፈፅምም!! በጭራሽ! ‘ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢልላህ’ / ብልሃትም ሃይልም በአላህ እንጂ የለም/ ብለን በምንችለው በዙሪያችን ያሉት መልካም! አላህን – ዐዘ ወጀል – የፈራ ሰው መልካምን እንጂ አያገኝም።"
https://youtu.be/udMx8Af6acQ
ኢድ ሙባረክ
ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሀል አእማል።
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
ወንደሞቼ እና እህቶቼ ፣ አላህ መልካም ስራዎቻቸንን ይቀበለን !
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
https://t.me/SadatTextPosts
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor (MuhammedSirage M.Nur G)
አልጀዚራ ቻናል ለግብረ ሰዶማውያን ያለ ምንም ሃፍረት በግላጭ ማስታወቂያ ይሰራል። የሙስሊም ሃገራትን በሚችለው ሁሉ ለማፈራረስ የሚተጋ መርዘኛ ቻናል።
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor (MuhammedSirage M.Nur G)
ከረመዳን በሇላ የሚቀረው ኪታብ የታላቁ ዓሊም ሳሊህ አልፈውዛን
من أصول عقيدة أهل السنة والجماعة
አጠር ያለች ምርጥ ኪታብ / ሪሳላ/
የኪታቧ መጀመሪያ ላይ ሸይኹ መንሃጅን የሚያስጨብጡበት ያማረ መግቢያ አለቸው ከዛም ወደተለያዩ የዓቂዳ ጉዳዮች ይገባሉ ።

t.me/Muhammedsirage
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor (كوني زوجة صالحة تقية)
አሽሙር "የሚፀየፉ" አሽሙረኞች!!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
እኔ እምለው አሽሙር አሽሙር የሚሉ በዙ ልበል?
ደግሞኮ ይህንኑ ሐሳባቸውን በአሽሙር ነው የሚገልፁት። በግልፅ "እነ እከሌን አትንኩብን" ብትሉ አይሻልም? ምነው ፍላጎታችሁን ለመግለፅ ዳር ዳሩን ትዞራላችሁ?!

እንጂ ኢንሷፍ ቢሸታችሁ እነዚህን እዚያ ሰፈር ደጋግመን የምንሰማቸውን ውንጀላዎች ዝም ባላላችሁ ነበር።

* "ጉላት (ወሰን አላፊዎች)"፣
* "ፅንፈኞች"፣
* "ሐዳዲያ"፣
* "ላይክና ሼር መቃረም የሚፈልጉ"፣
* "የደጋፊ ሽሚያ ውስጥ የገቡ"፣ "ደጋፊ ለማብዛት የሚሯሯጡ"
* "የሰለፍያ ጭምብል የለበሱ"፣



ይህ ሁሉ ሲባል ምን ብላችኋል? የትስ ነበራችሁ?!

ደግሞ ምነው ይህን በሰለፍዮች ላይ የሚያሳዩትን ጀግንነት ኢኽዋንም ላይ እያሳዩን ምንም ቢሉን በቻልናቸው!!

* ይሄው ከስር በሐዳዲይነት ሲፈርጁ። ከዚያ ደግሞ ሌላ ገፀ ባህሪ ተላብሰው ሪፍቅ፣ ሪፍቅ ይተውናሉ።

* አንድን ሙስሊም "ጣኦት አምላኪ"፣ "ጴንጤ" እያሉ ከመወረፍ የበለጠ ፀያፍ አለ?! ይሄ ነው እንግዲህ ስለ ፅንፈኝነት የሚያወራውና የሚያሰራጨው!!

ይህ ሁሉ ሲሆን ዝም ያለ ሰው እነሱ ሲነኩ እሪታ ማብዛት ምንድን ነው?! "ጴንጤ" "ጣኦት አምላኪ" እያለ የሚወርፈው ሳዳት ቢሆን ኖሮ ኡስታዞቻችሁም ዝም አይሉም ነበር። በራሳችሁ ጭንቅላት አስቡ። ይሄ በቡድን ማሰብ እራሳችሁን ነው የሚጎዳው።
እነዚህ ናቸውኮ ያለ ምንም ሃፍረት ስለ ሪፍቅ፣ ሊን፣ ሒክማ የሚደሰኩሩት። ሙስሊምን እያከፈረ "አሽሙር ጥሩ አይደለም" የሚል ሰው የተዋጣለት ኮሜዲያን ነው።

* "ሰዎችን ከሱንና ማስወጣት ከባድ ነው" የሚለውን ያራግብና ዞሮ በሐዳዲያነት ይወርፋል። ለመሆኑ እራሳቸውን በምን አይን ነው የሚያዩት?!

ከስር ያያያዝኳቸው የአወል ሸርሞሎ ንግግሮች ናቸው። መካሪ፣ ጓደኛ፣ ቤተሰብ ቢኖረው ይህን ሁሉ እያየ ዝም አይለውም ነበር።

① ቢድዐን የቀሰቀሰ ሳዳት ነው ይለናል።
إذا لم تستحي فاصنع ما شئت!
② "የኢኽዋንን ሬሳ ነፍስ ዘርቶ ለስልጣን ያበቃው ሳዳት ነው ይለናል። መዋሸት እንኳን የማይችል ቀላል ፍጡር። ኢኽዋን ሲሿሿም አብረው የተጣዱት ኡስታዞችህ እንጂ ሳዳት ነው እንዴ?! " እንኳን ደስ ያለን" መግለጫ ያወጣው ሳዳት ነውንዴ?! ኢኽዋን ጋር አይንና ናጫ የሆነውስ ሳዳት ነው ወይስ መርከዛችሁ? ምነው ሃይ የሚላችሁ ጠፋ?!
ቆይ "ኢኽዋን ሙቷል ስትል" ማነው የገደለው? "ገድለነዋል" ልትል ባልሆነ። እና ከሬሳው ጋር ነው ‘ለመስለሐ’ እየተቀማመጣችሁ ያላችሁት? ከሬሳ ጋር ነው ስብሰባ የምትቀማመጡት?!

③ "የተረሳውን መንዙማ በመፅሐፍ ፅፎ ለህዝብ ያስጠና " ይላል።
ሱብሓነላህ! ለወሬ የማይመች ፍጡር!! መንዙማ ተረስቷል? ሳዳት ነው ለህዝብ ያስተዋወቀው?
ሲጀመር በዚህ ጉዳይ ምን የሰራችሁት አለ?! ለካስ ለዚህ ነበር አንዳንዶቹ "መንዙማ" መፅሐፍን ሰ ቃወሙ የነበረው?

ጥላቻ ይህን ያክል ይጋርዳል። ወላሂ የሚናገረውን ባየሁ ቁጥር አእምሮውን በእጅጉ ነው የምጠረጥረው።

④ "የተረሱ የሙታን መቃብር ቦታዎችን ቦታቸውን ሁሌ እየጠቆመ እንዲጎበኙ ያስደረገው ሳዳት ነው ይላል።
ምናለብህ የፈለግከው ብትናገር፣ እንዳሰኘህ ብትዋሽ አንተን ማን ይነካሀል? የሙሪድነት መታወቂያ ይዘሀላ!
ለመሆኑ ጌታ አላህ እነ ላትን፣ እነ ዑዛን፣ እነ መናትን በስም እየጠቀሰ ሲኮንን እንዲመለኩ እያመለካተ ነበር?

⑤ ጠፍተው የነበሩ እርዶች በአልከሶ፣ በቃጥባሬ በአብሬት ከድሮው እንዲባባሱ ያደረገው ሳዳት ነው ከዚህ ወፈፌ ዘንድ።
ሱብሓነላህ!! ወላሂ ኢኽዋኖች እንዲህ ሲሉ ሰምቼ አላውቅም። እነዚህ ናቸው ስለ ሚዛናዊነት የሚደሰኩሩት እንግዲህ።

"አሽሙር ጥሩ አይደለም" ከማለታችሁ በፊት ይህን ተናካሽ ፍጡር አትይዙም?! "መርፉዐል ቀለም" ከሆነም እሰሩት።

* ምናልባት ለምን እስከዛሬ ዝም አላችሁ" የሚል ሊኖር ይችላል። በግምት ከ6 አመት አካባቢ እዚሁ ፌስቡክ ላይ በግልፅ ተናግረናል። ከ2 አመት በፊትም ለሚቀርበው አንድ ኡስታዝ "ለምን ስርአት አታስይዙትም?" ብየ ተናግሬ ነበር። "አናግረነዋል ይስተካከላል" ብሎኝ ነበር። ያናግሩት አያናግሩት የማውቀው ነገር የለም።

(وَإِنْ عُدْتُمْ عُدْنَا)
የሰልሰቢልን ፅሑፍ አየሁት
~~~~~~~~~~~~~~~~
ያየሁት ትላንት ነው። ብዙም ትኩረት ሳልሰጠው አልፌው ነበር። ዛሬ ግን አንድ ትኩረቴን የሳበኝ ነገር በማየቴ ትንሽ ልል ወደድኩኝ። አብዛኛው ረብ የለሽ ስለሆነብኝ ትቼዋለሁ። አንዳንድ ነጥቦችን እየመዘዝኩ ልይ:–

① "በርግጥ በአመለካከት ከሚራራቁ ሰዎች ጋር ግድ ሆኖብህ ስትቀማመጥ ከበባድ ነገሮችን ልትሰማና ልታይ ትችላለህ የሚጠበቅም ነው። ለዛም ነው ፕሮፌሰር አደም ካሚል የነቢያትን ክብር የሚነካ ንግግር ያሰማው" ይላል።

መልስ:–
~~~~~~
እንዲህ አይነት ነገር ሲያጋጥም ሸሪዐዊይ ብይኑ ወይ እርምት መስጠት ወይ ጥሎ መውጣት ነው ሰልሰቢል። አላህ እንዲህ ይላል:–
(وَقَدْ نَزَّلَ عَلَيْكُمْ فِي الْكِتَابِ أَنْ إِذَا سَمِعْتُمْ آيَاتِ اللَّهِ يُكْفَرُ بِهَا وَيُسْتَهْزَأُ بِهَا فَلَا تَقْعُدُوا مَعَهُمْ حَتَّىٰ يَخُوضُوا فِي حَدِيثٍ غَيْرِهِ ۚ إِنَّكُمْ إِذًا مِثْلُهُمْ)

"በእናንተም ላይ በመጽሐፉ ውስጥ የአላህን አንቀጾች በርሷ ሲካድባትና በርሷም ሲላገጥባት በሰማችሁ ጊዜ በሌላ ወሬ ውስጥ እስከሚገቡ ድረስ ከእነሱ ጋር አትቀመጡ ማለትን በእርግጥ አወረደ፡፡ እናንተ ያንጊዜ ብጤያቸው ናችሁና፡፡"
[አንኒሳእ: 140]

ነብዩም ﷺ እንዲህ ብለዋል:–

" مَنْ رَأَى مِنْكُمْ مُنْكَرًا فَلْيُغَيِّرْهُ بِيَدِهِ، فَإِنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَبِلِسَانِهِ، فَإِنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَبِقَلْبِهِ، وَذَلِكَ أَضْعَفُ الْإِيمَانِ "

"ከናንተ መጥፎን ነገር ያየ በእጁ ይቀይረው። ካልቻለ በምላሱ፤ ካልቻለ ደግሞ በልቡ። ይሄኛው የመጨረሻ ደካማው እምነት ነው።" [ሙስሊም]

ተሳታፊዎችህ ግን አንዱንም አላደረጉም። አድርገዋል ካልክ ማስረጃ አቅርብ።

② "ይሁንና ልክ ቦታው ላይ እንደነበሩ ሆነው "ይህ ሲሰማ ዝም አሉ" "ሌላው ቢያቅታቸው ጮኸው መውጣት ነበረባቸው" ወዘተ እያሉ መተቸታቸው ግን ተገቢ አይደለም። ምክንያቱም አንደኛ ተቃውመው ሊሆን ይችላል ወይም ያሉበት ሁኔታ ተቃውሟቸውን በምንም መልኩ ሊገልፁ ማይችሉበት ኡዝር የሚያሰጥ ሁኔታ ሊኖር ይችላል …።" ብለሃል ።

መልስ:–
~~~~
በቦታው ላይ ምላሽ እንዳልሰጡ ባደባባይ ሲመሰክር የነበረ ሰው ይህን ተልቢስ ሼር ሲያደርግ ሳየው ነው ምላሽ ልፅፍ የወሰንኩት።

ወንድሜ በቦታው ላይ ምላሽ አልሰጡም። በሌላም ጉዳይ ቢሆን አሕባሾች ናቸው ተሽለው የጮሁት።
"ተቃውመው ሊሆን ይችላል" ከማለት ጠይቀህ አትፅፍም? ይህን ያክል እሩቅ ናቸው ላንተ? ለማንኛውም አልተቃወሙም። በቦታው ከነበሩ ሰዎች መረጃ አለኝ። ከትግራይና ከአፋር የተካፈሉ ሰዎችን አግኝቼ አነጋግሬያለሁ። አንዱ "ንግግሩ ቢያስደነግጠኝም ሁሉም ፀጥ ሲል ጊዜ እኔ አማርኛየ ደካማ ስለሆነ በተሳሳተ መልኩ ተረድቼው ይሆናል ብየ ነው የገምትኩኝ" ሲለኝ ሌላኛው "ይሄ እጅግ አደገኛ ንግግር ነው። እኔ አማርኛ አልችልም። እንዴት ያ ሁሉ ታዳሚ (እነ እከሌ ብሎ ስም እየጠቀሰ) ዝም አለ?" ብሎኛል።

በተረፈ ከኢብኑ መስዑድ መርከዝ ሰዎች ውስጥ "አንድ ሰው በቦታው ስላልተመቸው ምላሽ ላይሰጥ ይችላል" እያለ የተናገረበት ድምፅ ሰምቻለሁ። ይህ ማለት በቦታው አልተናገርንም ማለቱ ነው። አሁን ያንተን ሾላ በድፍን መከላከያ ሼር ሲያደርግ እያየሁ ነው። እውነት እንዳልሆነ እያወቀ ያንተን ተልቢስ ያጣጥማል።

እሺ በቦታው መናገሩም ይቅር! ሲወጡ እርምት መስጠት አይችሉም ነበር? እንደሚታወቀው ጉባኤው ሰፊ ታዳሚ የተካፈለበት ነው። በዚያ ላይ ተቀርጿል። በዚያ ላይ በአሕባሽ ሲራገብ ነበር። እነዚህ ነገሮች ልክ የግል ውይይት ላይ እንዳለፈ ነገር አንዴ ሆኗል ተብሎ የሚታለፍ አይደለም። ለነገሩ የግልም ዝም ተብሎ አይታለፍም።

ወንድማችን ሰልሰቢል ግን እነዚህ እውነታዎች ባሉበት የተፈፀመውን ስህተት አስረግጦ እንደመነሳት በመከላከል ላይ ሲባክን ይታያል።

③ "ኢብን መስዑድ በዚህ እንቅስቃሴ … በመግባቱም ሳቢያ የተቋማዊ ለውጡ መሰረት በሚፈለገው ምሶሶ ላይ እንዲቆምና በተለይ ከነ ሀሰን ታጁ ጥራዝ ነጠቅ አቋም የፀዳ እንዲሆን የበኩሉን ጥረት አድርጓል ወሊላሂል ሀምድ።"

መልስ
-----
አነጋገሩ አሻሚነት አለው። "ሞክሯል" ሊል ከሆነ እሰየው። የነ ሀሰን ታጁ ተፅእኖ ግን ማንም በማይክደው መልኩ አግጥጦ የሚታይ ነው። ነገሩን ለማጥራት ያክል ነው።

④ "ይህ ሆኖ ሳለ ቀድሞውንም ከረዥም ጊዜ ጀምሮ የኢብን መስዑድ ሰዎች ላይ ሙላሀዛዎች አሉን የሚሉ ወንድሞች ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው በዙልምና በተልቢስ ትችቶችን መሰንዘራቸውን አሟሙቀውታል።"

መልስ:–
~~~~~
ይሄ ንግግርህ በራሱ ዙልምና ተልቢስ ነው። የተናገርነው አንድም አካሄዳችሁ ስህተት ነው ብለን ስላመንን ነው። ችግሩ እራሳችሁን "አይነኬ" ማድረጋችሁ ነው። ቀጥታ አታወጡትም እንጂ "ምን ሲባል ተደፍረን?" ነው ነገራችሁ። እንጂ አመላለሳችን ልክ አይደለም ቢባል እንኳ ከሰፊው የኢኽዋን ዘመቻ ይልቅ የራሳችሁ ጉዳይ አስጨንቋችሁ አትንጨረጨሩም ነበር!!
ሁለተኛ ሀሳባችሁን የሚተችን እንደ ፅንፈኛ እየሳላችሁ ስለሆነ ነው ትችት የምንሰነዝረው።

ይልቅ ማስረጃዎችን ያለ ቦታቸው ማዋል፣ ለምሳሌ የሑደይቢያን ውል ያለ አግባብ መጠቀም ነው ተልቢስ። በሃሳብ ያልተጋራውን በፅንፈኝነት መወረፍ ነው ተልቢስ።

⑤ "በሀቅ መተቸት በትህትና ሀሳብ መስጠት ወይም ስህተቱን በመረጃ አጉልቶ ረድ መስጠት እየቻሉ እንዲህ አይነቱን ማድበስበስ መጠቀም ለምን እንደመረጡ ባይገባንም …"

መልስ
~~~~
ሱብሓነላህ! "ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል!" በሐዳዲያ መወንጀል ነው በሐቅ መተቸት? ጉላት እያሉ መወረፍ ነው በትህትና መሀየስ? "ሺርክና ቢድዐ አሰራጫችሁ፣ ኢኽዋኖችን ለሥልጣን አበቃችሁ" እያሉ መቅጠፍ ነው በአደብ መሞገት? አንዳንዴ እንኳን እራሳችሁን ተመልከቱ እንጂ!

ግራ የሚገባኝ ኢኽዋን ከአመት እስካመት ሲፈነጭ ዝም ብሎ፣ "ተነካን" ብለው ሲያስቡ ነብር የሚሆኑበት ባህሪ ነው። እያድበሰበሱ "አታድበስብሱ!" እየሻከሩ "አትሻክሩ" ብሎ ጩኸት። ከተነኩ እስከ ተብዲዕ እስከ ተክፊር ለመሄድ የማያመነቱ ኡስታዞች ከውስጣቸው እንዳሉ አይተናል። የታል ሪፍቃችሁ? የታል ሒክማችሁ?!

⑥ "ይህን ክስተት ሲተቹ ከገረሙኝ ነገሮች "ስለ መረዳዳት የተናገረው የቁርዓን አንቀፅ ሙብተዲዖችን አይመለከትም። ከሰለፎች አንድም ሰው በዚህ አልፈሰረውም" ብለው ብዙ ሳይቆዩ "በሀቅ ከሆነ አይደለም ከሙብተዲዕ ከካፊር ጋርም መተባበር ይቻላል" እያሉ የሚናጋ መርሆ አንግበው አንድ ላይ መጮኸቸው ነው።"

መልስ:–
~~~~~~
"በሀቅ ከሆነ አይደለም ከሙብተዲዕ ከካፊር ጋርም መተባበር ይቻላል" ብየ የፃፍኩት እኔ ነኝ። የት ቦታ ከሙብተዲዕ ጋር መተባበር አይቻልም እንዳልኩ አቅርበው እስኪ። ያለበለዚያ እየዋሸህ ነው።
ስገምት "አንተ ባትልም ሌላ የሆነ ሰው ብሏል፣ ያው አንድ ናችሁ" ልትል ይመስለኛል። እንዲያ ካልክ የነ አወል ሸርሞሎን የነ ሙሐመድ ዐሊን ንግግር ወደናንተ ስናስጠጋ አይክፋችሁ።

⑦ "ኢብን መስዑድ ተሳትፎ ሲያደርግ ዓላማውም ሆነ ተግባሩ ከላይ የጠቀስኩት ሆኖ ሳለ ስኬት ግን በአላህ እጅ እንደሆነና ከኛ የሚጠበቀው ሰበብን በአግባቡ ማድረስ ብቻ እንደሆነ እናምናለን።"

መልስ:–
~~~~
"ኢብኑ መስዑድ (መርከዝ) የሄደበት መ
ንገድ ውጤት ካመጣ ኋላ ታፍራላችሁ" ያልከው ልጅ ና እስኪ ይህንን እይ! የተሰጠህ ምላሽ ከዚህ የሰልሰቢል ንግግር ጋር አንድ አይደል?
ብቻ ጤነኛ ሰበብ ማድረስ ይጠበቃል። እንጂ "የትም ፍጪው…" እየዘመሩ "ዋናው ሰበብ ማድረስ ነው" አይባልም ።

⑧ የመጅሊሱን ስምምነት አስመልክቶ በራሱ መንገድ ከተበተበ በኋላ "እኔ በእውነቱ በዚ የማይደሰት ትክክለኛ የዓቂዳ ተቆርቋሪ ይኖራል ብዬ አላስብም ነበር" ይላል።

መልስ:–
~~~``
የሚደንቅ ነው። እኔ "ትክክለኛ የዓቂዳ ተቆርቋሪ አይደለህም" ትለኛለህ ብየ ሳልጨነቅ ስምምነቱ አያስደስተኝም እልሀለሁ። ይህን የምለው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው።

አንደኛ:– ለሰለፍያ ደዕዋ ፈተና በመፍጠር በኩል ኢኽዋን የከፋ ነው ብየ ስለማምን ነው። እያወራሁ ያለሁት የሁለቱ ቡድኖች ዐቂዳ ሲነፃፀር አሕባሽ ይሻላል ለማለት አይደለም። ምንም እንኳን ኢኽዋን ውስጥ ከአሕባሽ ፈፅሞ የማይሻሉም እንዲያውም የሚከፉም ሰዎች ከመኖራቸውም ጋር እንደ ጥቅል ግን ኢኽዋን የተሻለ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጂ አሕባሽ የማይመስሉትን ሁሉ ጠላት ሲያደርግ ኢኽዋን ግን አሕባሽንም ሺዐንም በዐቂዳ ልዩነት ሳቢያ ጠላት አያደርግም። ይልቁንም በሙሉ ሃይሉ የሚዘምተው ሰለፍያ ላይ ነው። ይህንን ሐቅ ሌሌች ሊያምኑት ቢከብዳቸው እንኳ ሰለፍዮች ግን በተጨባጭ የሚያውቁት ነው። ይሄው እርቅ በሚዘምርበት ሰዓት እንኳ በአንዳንድ አካባቢዎች አሕባሾችን ማስተማርና መውሊድ መደገስ በፈቀዱበት ቦታ ሰለፍዮችን ሲያግዱ ተስተውለዋል። በአንዳንድ የአማራ፣ ኦሮሚያና አዲስ አበባ አካባቢዎች ላይ ያጋጠሙ ነገሮችን ማስተዋል ነው።
አብረን እየተንቀሳቀስን ነው ብለው አላፈሩም፣ አላረፉም።

ሁለተኛ:– በብዙ መልኩ ኢኽዋን ከአሕባሽ የተሻለ ጉልበት አለው። በአጃቢ ብዛት፣ በሚዲያ አቅም፣ በፋይናንስ… ። ይህም ፈተናቸውን ከአሕባሽ የከፋ ያደርገዋል።
ሶስተኛ:– የራስን አማራጭ መጠቀም ይቻላል። አማራጮች ባልተዘጉበት ዐቂዳን ለድርድር ካቀረበው ህብረት ውስጥ መግባት ማስተዋል ሳይሆን ሌሎች በቀደዱት መፍሰስ ነው።

⑨ "መንግስት አህባሽን ከሀገር ያባርልን የሚል የሚደንቅ ጥያቄ ካነሳን እንጂ አሁን ያለው ተጨባጭ ከመለስ ድፍረት በፊት የነበረው ተጨባጭ ነው።"

"መንግስት አህባሽን ከሀገር ያባርልን" የሚል ቂል የለም። እንዲህ አይነት አነጋገር ነገር ከማንዘላዘል ያለፈ ፋይዳ የለውም። ጥያቄው ከአሕባሽ… ጋር ሳይጋፉ መስራት ይቻላል ነው። የነገሩ ማሰሪያ እዚህ ላይ ነው። እራስህን ችለህ መስራት ከቻልክ ከአፈንጋጮች ጋር ምን አሰለፈህ?

(10) "ሚዛናዊ እንሁን እያልን የተለመደ ዲስኩር እያላችሁ የምታጣጥሏትንም «ሂክማ» የምንደጋግመውም ለዚህ ነው" ይላል።

መልስ:–
~~~~
ሒክማን ሳይሆን በሒክማ ስም መነገድን ነው ያጣጣልነው። በሒክማ ስም መዋሸትን ነው የተቃወምነው። በሒክማ ስም እየሰበኩ ፀያፍ የዱርየ ቃላት የሚተፉ "ኡስታዞቻችሁን" ያዙ ነው ያልነው። የተቀያየሟቸውን ሙስሊሞች ሲፈልጉ ከሱንና ሲፈልጉ ከኢስላም የሚያስወጡ ዋልጌዎቻችሁን ያዙ ነው ያልነው። እናንተ "ሒክማ የላቸውም" ከምትሏቸው ውስጥ ይህን ያደረገ አላውቅም። ኢኽዋኖችን ዝም ብሎ ሰለፍዮችን ማብጠልጠል ሒክማ አይደለም ነው የምንለው። ታላላቅ ዑለማዎች፣ ነብያትን ጨምሮ ባደባባይ ሲጠለሹ የተለጎመ አፍ ሰለፍዮች ላይ ለመዝመት መሞከሩ ሒክማ አይደለም ነው የምንለው። ይህንን የተገለበጠ አካሄድ "ሒክማ" ማለት ተልቢስ ነው።

(11) "ሂክማን ካልተረዳህ ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስኪገባ ዳዒ ልትሆን አትችልም።"

መልስ
~~~~~
ሒክማ ያለው ሰው ይህን ቢል አይገርምም ነበር። ለመሆኑ እነ ሙሐመድ ዐሊ፣ አወል ሸርሞሎ እናንተ ዘንድ ዳዒዎች ኡስታዞች የሆኑት ባለ ሒክማ ሆነው ነው? ሲበዛ ፍርደ ገምድል ነህ?!
ስለ ሒክማ ከመስበካችሁ በፊት የስድብ ናዳ እያወረዱ ያሉ ዋልጌዎቻችሁን አደብ አታስይዙም?

ወንድሜ ያልመሰላቸውን "ሒክማ የለውም" እያሉ ማጣጣል የብዙዎች መታወቂያ ነው። ልዩነቱ አንተ እራስህን የምታይበት አይን ሌላ መሆኑ ነው።

ሲጀመር ሒክማን የምትዘምረው ብዙ ጊዜ ሌሎችን ለማሳጣት ነው። እንጂ በዐቂዳ ሂሳብ ሁሉን በሚያግበሰብሱት፣ ዑለማዎችን በሚያጠለሹት ኢኽዋኖች ላይ "ሒክማ የላችሁም" ብለህ አልዘመትክም። ይህም "ሒክማህ" የከንቱ አላማ ማስፈፀሚያ እንደሆነ ነው የሚያሳየው።

በተረፈ እነ ኢብኑ ተይሚያም፣ እነ አልባኒም፣ እነ ሙቅቢል፣ እነ ረቢዕም… ሙብተዲዖች ዘንድ ሒክማ የላቸውም። የሞጋቾች ሙግት መለኪያ አይሆንም ለማለት ያክል ነው። (ይህን ስል "እራሳችሁን ከነዚህ ዐሊሞች ጋር አመሳሰላችሁ" የሚል የዋህ እንዳይኖር እየሰጋሁ ነው።)
ጥቂት ስለ ኡስታዝ አቡ ሙስሊም
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ወንድማችን ዑመር ሐሰን አቡ ሙስሊም ከ10 አመት በፊት የኡሙል ቁራ ዩኒቨርስቲ የትምህርት እድል (scholarship) በማግኘቱ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሲከታተለው የነበረውን አካዳሚ ትምህርት በመተው ወደ መካ አቀና። ከሄደበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ለአስር አመታት ዒልም በመቅሰም ላይ ነው ያለው።

* የመጀመሪያ ዲግሪውን በመካ ከተማ ከሚገኘው የኡሙል ቁራ ዩኒቨርሲቲ በ
الكتاب والسنة مع الإعداد التربوي
አጠናቋል።
* የሁለተኛ ዲግሪውን በ الحديث وعلومه
(በሐዲሥ ጥናት ዘርፍ) መደበኛ ትምህርቱን እያጠናቀቀ በአሁኑ ሰዓት የሶስተኛ አመት ተማሪ ሲሆን የማሟያ ጥናት (ቴሲስ) በመስራት ላይ ነው።
* ከመደበኛው የኡሙል ቁራ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱ ጎን ለጎን ከሄደበት ጊዜ አንስቶ ለ10 አመታት ታላላቅ ዑለማዎች ዘንድ በመሄድ በትጋት ይከታተላል። የተማረባቸውንና እየተማረባቸው ያሉ ዑለማዎችን ለምሳሌ ያክል ልጥቀስ:–

① ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አልመድኸሊ፣
② ሸይኽ ዐብዱረሕማን አልዐጅላን፣
③ ሸይኽ ሙሐመድ ዐሊ ኣደም አልወሎዊ፣
④ ታዋቂው ሙሐዲሥ ሸይኽ ወሲዩላህ ኢብኑ ሙሐመድ አልዐባስ
⑤ ሸይኽ የሕያ ኢብኑ ዑሥማን (ከሸይኽ ሙቅቢል ሸይኾች ውስጥ ናቸው)፣
⑥ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዑመር ባዝሙል፣
⑦ ሸይኽ አሕመድ ኢብኑ ዑመር ባዝሙል (በአሁኑ ሰዓት ለማስትሬት ጥናቱ አማካሪው (አድቫይዘሩ) ናቸው።)

ከነዚህም በተጨማሪ ወደ መካ በሚመጡበት ጊዜ ባገኛቸው አጋጣሚ የተማረባቸው ዑለማዎች አሉ። ለምሳሌ:–
⑧ ሸይኽ ሷሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አልፈውዛን
⑨ ሸይኽ ሷሊሕ አልሉሐይዳን፣
(10) ሙፍቲ ዐብዱል ዐዚዝ ኣሊ ሸይኽ፣
(11) ሸይኽ ፉኣድ ኢብኑ ሰዑድ አልዐምሪ፣
(12) ሸይኽ ዓዲል ኢብኑ መንሱር አልባሻ
(13) ሸይኽ አቡ ሁማም ሙሐመድ ኢብኑ ዐሊይ አልበይዷኒ እና ሌሎችም።

ከመካም ውጭ በተለያዩ ደውራዎች (አጫጭር ስልጠናዎች) ላይ በመካፈል ዒልም የቀሰመባቸው መሻይኾች ብዙ ናቸው። ለምሳሌ ያክል:–

* ሸይኽ ዘይድ ኢብኑ ሙሐመድ አልመድኸሊ (ረሒመሁላህ)፣
• ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲ አልመድኸሊ፣
• ሸይኽ ሱለይማን አርሩሐይሊ፣
• ሸይኽ ሙሐመድ ረምዛን አልሃጂሪ፣
• ሸይኽ ዐብዱረሕማን ኢብን ሙሕዪዲን፣
• ሸይኽ ዐልይ ኢብኑ የሕያ አልሐዳዲ፣
• ሸይኽ ዐብዱረዛቅ አልበድር፣
• ሸይኽ ሙሐመድ ኢብን ዐብዲል ወሃብ አልዐቂል፣
• ሸይኽ ኡሳማ አልዐምሪ እና ሌሎችም።

* ወንድም አቡ ሙስሊም ተባባሪና ፈጥኖ ሰው ጋር የሚግባባ ነው። ከሚማርባቸው መሻይኾች ዘንድ ያለው ቅርበት እና አመኔታ የሚያስቀና ነው።
* አቡ ሙስሊም የሳዑዲ ኢስላማዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ከሚያሰማራቸው ዱዓት ጋር በመሆን በየዓመቱ ወደ መካ ለሚመጡ ኢትዮጵያውያን ሑጃጆች በማስተማር ይጠመዳል።
* ከሐጅ ውጪም የተለያዩ የማስተማር ስራዎች ላይ ይሳተፋል።
* በአንድ የመንግስት ትምህርት ቤት ውስጥም አስተምሯል።
* ወንድም አቡ ሙስሊም እኔ እስከማውቀው ድረስ ፌስቡክ ላይ የለም። በቴሌግራም ግን በአማርኛም በኦሮምኛም ያስተምራል። ትምህርቱን መከታተል ለሚሹ የቴሌግራም ቻናሉ ይሄውና

🌐 t.me/AbumuslimAlarsi