Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
ተቀማጭ ገንዘብ ዘካ የሚወጅብበት አመት የሞላው ከሆነ ነው። እንጂ ለምሳሌ አንድ ሰው በውርስ አምስት መቶ ሺ ብር ቢያገኝና ገና 3 ወር ቢሆነው መጠኑ ለዘካ ስለደረሰ ብቻ የማውጣት ግዴታ አለበት አይባልም።
የንግድ ሸቀጦች ዘካ
~~~~~~~~~~~~~
* መነሻ ተመን (ኒሷብ) ከወረቀት የብር ኖት ጋር ተመሳሳይ ነው። (ቀደም ብየ የለጠፍኩት መለስ ብለው ያገናዝቡ።)
* የሚወጣው መጠን 2•5% ነው።
* ከንግድ ስራው በቀጥታ ተያያዥ የሆነው ገንዘብ አብሮ ተደምሮ ይሰላል ።
* በራሳቸው የግብይቱ አካል ያልሆኑ እንደ መኪና፣ ማሽኖች፣ ቤቶች፣ መጋዘኖች፣ … ያሉ ቋሚ ንብረቶች የንግድ ስራውን ለማቀላጠፍ ቢያግዙም እንኳ ዘካ አይመለከታቸውም።
* ታሳቢ የሚደረገው የሸቀጦቹ ዋጋ የተገዙበት ሳይሆን ወቅታዊ ዋጋቸው ነው።
ዘካን ለቤተሰብ መስጠት ይቻላል?
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ለወላጅ፣ ለልጅ፣ ለሚስት፣ ለአያቶች እንዲሁም በሱ ሃላፊነት ስር ላሉ ዘመዶች ወጪያቸውን የመሸፈን ግዴታውን የራሱ ነውና ለነሱ ዘካ መስጠት አይችልም። [ፈታዋ ለጅነተ አድዳኢማ: 15/341–343]
* ሚስት ግን ለባሏ ዘካ የሚገባው ሰው ከሆነ መስጠት እንደምትችል ዑለማዎች ይገልፃሉ።
በወንበር ላይ መስገድ
=============
① ቆሞ መስገድ የሶላት ሩክን (ማእዘን) ነው። ስለሆነም #በግዴታ ሶላት ጊዜ መቆም የሚችል ሰው ተቀምጦ ቢሰግድ ሶላቱ ውድቅ ነው።
② በህመም ወይም በእርጅና ሳቢያ መቆም ያቃተው ሰው ወንበር ላይ ወይም መሬት ላይ ተቀምጦ ይሰግዳል።
* መቆም አቅቶት ተቀምጦ የሰገደ ሰው አጅሩ አይቀንስበትም።
③ ሩኩዕና ሱጁድ ማድረግ የሚችል ከሆነ ከወንበር ላይ ሆኖ መጠቆም ሳይሆን በትክክል መፈፀም አለበት። ለማይችለው ዑዝር ተሰጠው ማለት የሚችለውንም በዚያው ይሸፍናል ማለት አይደለም።
ለምሳሌ ሱጁድ ማድረግ የሚያቅተው ሰው መቆምና ሩኩዕ ማድረግ ከቻለ መቆምም ሩኩዕ ማድረግም ግዴታው ነው። ለሱጁዱ የተሰጠው ፈቃድ ለሩኩዑም ለመቆሙም አይሆንም። ባጭሩ የሚችለውን ማስገኘት አለበት። የኢብኑ ቁዳማን አልሙግኒ ይመልከቱ [ገፅ: 1/444]
ስለዚህ አንድ ሰው እንደ ህመሙ ሁኔታ
– መቆምም፣ ሩኩዕና ሱጁድም ካልቻለ ሙሉ ሶላቱን ወንበር ላይ ይጨርሳል፤
– መቆም ብቻ ከሆነ የሚያቅተው ለሱ ብቻ እየታገዘበት ሌሎቹን በትክክል ይፈፅማል፤
– መቆም ችሎ ያቃተው ሱጁድ ወይም ሱጁድና ረኩዕ ከሆነ ለሚያቅተው ክፍል ብቻ ወንበሩን ይታገዝበታል።
④ ረኩዕና ሱጁድ የሚያቅተው ሰው ሱጁዱን ከሩኩዑ ዝቅ ያደርጋል።

⑤ ወንበር የሚጠቀም ሰው ከኋላው ያሉ ሰዎችን እንዳያስቸግር መጠንቀቅ አለበት። ወንበሩን ወደ ኋላ አድርጎ በእግሩ ሶፍ ሊጠብቅ አይገባም። አቀማመጡን ከአቀማመጣቸው ጋር ማጣጣም አለበት።
⑥ ቆሞ መስገድ የሚችል ከሆነ ሌሎችን የማያስቸግርበት ቦታ ካገኘ ሶፉን በእግሩ ይጠብቃል። ሌሎችን የሚፈትን ከሆነ ግን ቀደም ብሎ በመቆም የወንበሩን የኋላ እግር ከሌሎች ሰጋጆች እግር ጋር ያስተካልላል።
ወሏሁ አዕለም።
መነሻ ተመን (ኒሷብ) ካልደረሰ ገንዘብ ዘካ ማውጣት አይፈቀድም።
[ሙግኒ፣ ኢብኑ ቁዳማ: 2/631]
የህፃንና የአእምሮ በሽተኛ ገንዘብ መነሻ ተመን (ኒሷብ) ከደረሰ ዘካ ሊወጣለት ግድ ይላል። ሰዎቹን ሳይሆን ገንዘቡን የሚመለከት የደካሞች ሐቅ ስለሆነ ነው።
ስለዚህ ሃላፊ ወይም ተወካይ የሆኑ ሰዎች ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል።
ዘካን በራስም፣ በተወካይም መስጠት ይቻላል። ሆኖም ታማኝነታቸውን የማናውቃቸውን አካላት መወከል አይገባም። በአሁኑ ሰዓት የዘካን ገንዘብ ለቡድናዊ አላማ የሚያውሉ አካላትም በዝተዋል። ስለዚህ ጠንቀቅ ልንል ይገባል። ከቻልን በራሳችን ካልሆነ በምናምነው ሰው ብቻ ትክክለኛ ቦታ እንዲደርስ እናድርግ።
ውዝፍ ዘካ ያለበት!
~~~~~~~~~~~
በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የብዙ አመታት ውዝፍ ዘካ ያለበት ሰው ወደ ኋላ ተመልሶ የማውጣት ግዴታ አለበት። እንጂ ያለፈው አልፏል ይቅር አይባልም።
ዘካ ከወጀበበት በኋላ ሳያወጣ የሞተ ሰው!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ልክ እንደ ሰው እዳ ዘካው መከፈል አለበት። ምክንያቱም የገንዘብ ሐቅ ስለሆነ በሰውየው ሞት ግዴታው አይወርድም። ይህ የዐጧእ፣ የሐሰን አልበስሪ፣ የዙህሪ፣ የቀታዳ፣ የሻፊዒይ፣ የአሕመድ፣ የኢስሓቅ፣ የአቡ ሠውር ፣ ወዘተ አቋም ነው።
"የአላህ እዳ ሊከፈል ይበልጥ የተገባ ነው።" [ቡኻሪና ሙስሊም]
ዘካን ለወላጆች፣ ለልጆች፣ ለእህትና ለወንድም!
~~~~~~~~~~~~~~~~
ለወላጆችና ለልጆች ዘካ መስጠት እንደማይቻል ቁርጡቢ፣ ኢብኑ ሐጀርና ሌሎችም ኢጅማዕ ጠቅሰዋል። ምክንያቱ ደግሞ ልጅ ለወላጅ፣ እንዲሁም ወላጅ ለልጅ መሰረታዊ ወጪን የመሸፈን ግዴታ ስላለባቸው ነው።

ወደላይ አያትና ቅድመ አያት፣ ወደታች የልጅ ልጅም ተመሳሳይ ብይን ይይዛሉ።

ማሳሰቢያ!
~~~~~~~
*እዳ ካለባቸው እና ሊረዳቸው የሚችልበት አቅም ከሌለው ግን ሚዛን የሚደፋው ዘካ ሊሰጣቸው ይፈቀዳል የሚለው ነው ይላሉ ሸይኹል ኢስላም አሕመድ ኢብኑ ተይሚያ። [መጅሙዑል ፈታዋ: 25/90፣ 25/92]
ኢብኑ ዑሠይሚንም ተመሳሳይ ነገር ተናግረዋል። [ሸርሑል ሙምቲዕ: 6/250]

* ወንድም እህቶች ከሰጪው ጋር በአንድ ቤት ሳይሆን በውጭ የሚኖሩ ከሆኑ ዘካ ሊሰጣቸው እንደሚቻል ዑለማዎች ይገልፃሉ። በሰጪው ስር ሆነው አብረው የሚኖሩ ከሆነ ግን ሊሰጣቸው አይፈቀድም።
የወርቅና የብር ዘካ
~~~~~~~~~~~
ወርቅ 85 ግራም
ብር 595 ግራም ከሞላ
በየዓመቱ 2•5% ዘካ ማውጣት ግዴታ ነው።
አንተ የአላህ ባሪያ ሆይ! ለቤተሰብህ የምታወጣውን ወጪ ከአላህ አጅር አገኝበታለሁ ብለህ አስብ፡፡
عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِذَا أَنْفَقَ الرَّجُلُ عَلَى أَهْلِهِ يَحْتَسِبُهَا فَهُوَ لَهُ صَدَقَةٌ ‏"‌‏.‏
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ “አንድ ሰው በቤተሰቡ (ወላጆቹ፣ ሚስቱ፣ ልጆቹ እና እሱ እነሱን መመገብ እና መንከባከብ ግዴታ የሆነበት) ላይ ከአላህ ዘንድ ምንዳ አገኛለሁ ብሎ አስቦ ወጪ ያወጣ ምፅዋት (ሰደቃ) ይሆንለታል” ኢማሙ ቢኻሪ (ረሂመሁላህ) ዘግበውታል
ከሀዲሱ የምንወስዳቸው ትምህርቶች
- የንያ ትልቅነት፡፡ በየቀኑ በየወሩ ለቤተሰባችን ስንት የምናደርገውን ነገሮች ከአላህ ሂሳብ አገኝበታለሁ ብሎ ባለማሰብ ይህን የምፅዋት ምንዳ እናጣለን፡፡ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ለቤተሰባችን በምናወጣው ወጪ ላይ አላህ ይከፍለኛል የሚለውን በጣም ትኩረት እንስጠው፣
- የአላህን ቸርነትና ከባሪያዎቹ የምትወጣውን ትንሽ ተግባር እሱ በመልካም መቀበሉ፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በሌላ ሀዲስ እንደነገሩን ሚስቱን መገናኘቱ፣ ማጉረሱ ሰደቃ ነው ብለውናል፡፡
- መልካም የአላህ ባሪያ ቤተሰቦቹን ንያውን አሳምሮ ከረዳቸው የፍጡራኑ ሁሉ ረዳት አላህ ይህን ባሪያ የምፅዋት ለጋሾችን ድርሻ ይለግሰዋል፣
- አንድ የአላህ ባሪያ አላህ ምንዳዬን ይከፍለኛል ብሎ ለቤተሰቡ እስካወጣ ድረስ ቅናሽ ሳይሆን ከአላህ ዘንድ ምንዳ ነው የሚከፈለው፡፡ ይህም ታላቅ ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ የአላህ ምንዳ ጎድሎት እሳት የሚገባ ሰውም አለና፡፡ በዛ በጭንቅ ቀን ሚዛኑ የሞልቶለት ሰው የእድል ባለቤት ነው፡፡
- ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከናንተ ውስጥ ምርጥ ማለት ለቤተሰቡ ጥሩ የሆነ ነው ብለዋል፡፡ አደራ ለቤተሰቦቻችን መልካም በመዋል ላይ፡፡ ይህንንም ስናደርግ አሁንም አደራ አላህ ይከፍለኛል ብሎ ማሰቡን አደራ አደራ አደራ፡፡
አላህ ሆይ! ቤተሰቦቻችንን ያንተን ፊት ፈልገን ከምንንከባከብ ባሪያዎችህ አድርገን፡፡ እውቀትንም ጨምርልን፡፡ ዲንን አስገንዝበን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor (كوني زوجة صالحة تقية)
Muhammedsirage M.Nur
ከገባ 3 ወይም አራት ቀናትን ብቻ ያስቆጠረ የሚመስለው የተከበረው የረመዳን ወር ተጋመሰ!!

በሚገርም ፍጥነት ላይመለስ ገሰገሰ!!ከፊሎቻችን አደንዛዥ ድራማዎችን በማየት፣ ሌሎቻችን ግዜን ብቻ ሳይሆን ልብንም ጭምር የሚገሉ ሌሎች ከንቱ ነገሮችን በመፈፀም እና በመመልከት ሰንፈንና አመፀኞች ሆነን ከረምን።

በርካቶ ወንድሞችና እህቶች ደግሞ የበረከቱ መልካም ስራዎችን በማብዛት በርካታ ነገርን እየሸመቱበት ይገኛሉ!! አላህ ወደነሱ ይቀላቅለን!

ዛሬም የተውበት በር ክፍት ነው! ረመዳንም አላመለጠም! እንደውም ከረመዳንም የለይለቱል ቀድር መገኛ ሌሊቶች ተብለው በሰፊው የሚነገርላቸው ቀናት ፊት ለፊታችን ይገኛሉ!

አልመሸምና አሁንም ወደ አዛኙ አላህ እንመለስ ስል ነፍሴን ፣እንዲሁም ወንድሞቼንና እህቶቼን እመክራለሁ።
አላህ ይምራን! ! በእዝነቱ ይመልሰን! !

t.me/Muhammedsirage
ስለ ዘካ በኢብን ሙነወር የተዘጋጁትን አጫጭር ፖስቶች ከዚህ በታች በአንድ ላይ ታገኙታላችሁ

የብርህ መጠን ለዘካ መድረሱን እንዴት ነው የምታውቀው?
ዝቅተኛው ዘካ የሚወጅብበት የወረቀት ብር መጠን
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
የወረቀት የብር ኖት የዘካ መነሻ መጠን (ኒሷብ)
ከአመት አመት ሊለያይ ይችላል። ምክያቱም ሂሳቡ የሚሰራው ወቅታዊውን የወርቅና የብር (ሲልቨር) ዋጋ በማስላት ነውና።

አወጣጡም

እንደሚታወቀው
የወርቅ ኒሷብ=85 ግራም ሲሆን
የብር ኒሷብ ደግሞ=595 ግራም ነው።

ስለዚህ ወቅታዊውን የ85 ግራም ወርቅ ዋጋ እና የ595 ግራም የብር ዋጋ አስልተን ዝቅ ያለውን እንወስዳለን።
(ዝቅ ያለውን መነሻ ማድረግ የበርካታ ዑለማዎች አቋም ነው።)

ለምሳሌ ወቅታዊ የ1 ግራም ወርቅ ዋጋ 1,000 ብር ቢሆን
የወርቅ ኒሷብ ዋጋ 85×1,000=85,000 ብር ይሆናል።
ወቅታዊ የ 1 ግራም ብር ዋጋ 80 ብር ቢሆን
የብር ኒሷብ ዋጋ 595×80=47,600 ብር ይሆናል።
በዚህም መሰረት ወቅታዊው የወረቀት ብር ኖት የዘካ መነሻ ተመን ከሁለቱ ዝቅ ያለው ማለትም 47,600 ይሆናል ማለት ነው። እናም ይህን ያክል መጠን ብር ያለው ሰው ዘካ ወጅቦበታል ማለት ነው።
ማሳሰቢያ
① ዛሬ ዛሬ ካለው ሁኔታ ስንነሳ የብር ኒሷብ ከወርቅ ኒሷብ ያነሰ ነው። ስለሆነም በቀጥታ የ595 ግራምን ብር ወቅታዊ ዋጋ በማስላት ገንዘባችን ለዘካ ደርሷል ወይስ አልደረሰም የሚለውን በቀላሉ መለየት እንችላለን።
② ያቀረብኩት የወርቅና የብር ዋጋ ለምሳሌ ብቻ የቀረበ ነው። ወቅታዊውን ዋጋ አጣርቶ ማስላት ያስፈልጋል። መረጃ ያለው ካለም ከስር ቢያስቀምጠው መልካም ነው።
والله أعلم

ተቀማጭ ገንዘብ ዘካ የሚወጅብበት አመት የሞላው ከሆነ ነው። እንጂ ለምሳሌ አንድ ሰው በውርስ አምስት መቶ ሺ ብር ቢያገኝና ገና 3 ወር ቢሆነው መጠኑ ለዘካ ስለደረሰ ብቻ የማውጣት ግዴታ አለበት አይባልም።

የንግድ ሸቀጦች ዘካ
~~~~~~~~~~~~~
* መነሻ ተመን (ኒሷብ) ከወረቀት የብር ኖት ጋር ተመሳሳይ ነው። (ቀደም ብየ የለጠፍኩት መለስ ብለው ያገናዝቡ።)
* የሚወጣው መጠን 2•5% ነው።
* ከንግድ ስራው በቀጥታ ተያያዥ የሆነው ገንዘብ አብሮ ተደምሮ ይሰላል ።
* በራሳቸው የግብይቱ አካል ያልሆኑ እንደ መኪና፣ ማሽኖች፣ ቤቶች፣ መጋዘኖች፣ … ያሉ ቋሚ ንብረቶች የንግድ ስራውን ለማቀላጠፍ ቢያግዙም እንኳ ዘካ አይመለከታቸውም።
* ታሳቢ የሚደረገው የሸቀጦቹ ዋጋ የተገዙበት ሳይሆን ወቅታዊ ዋጋቸው ነው።

ዘካን ለቤተሰብ መስጠት ይቻላል?
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ለወላጅ፣ ለልጅ፣ ለሚስት፣ ለአያቶች እንዲሁም በሱ ሃላፊነት ስር ላሉ ዘመዶች ወጪያቸውን የመሸፈን ግዴታውን የራሱ ነውና ለነሱ ዘካ መስጠት አይችልም። [ፈታዋ ለጅነተ አድዳኢማ: 15/341–343]
* ሚስት ግን ለባሏ ዘካ የሚገባው ሰው ከሆነ መስጠት እንደምትችል ዑለማዎች ይገልፃሉ።
* በራሳቸው ቤት የሚኖሩ ከሆነ (ማለትም በሰጪው ቤት ካልሆኑ) ለእህት ለወንድም ዘካ መስጠት ይቻላል።

የዘካን ገንዘብ ለመስጂድና ትምህርት ቤቶች ግንባታ ማዋል አይቻልም ይላሉ በርካታ ዑለማዎች። ሚዛን የሚደፋውም ይሄ ነው ይላሉ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ።
በዒልም ፍለጋ ላይ ለተሰማሩ ደረሶች መስራት የሚችሉበት አቅም ቢኖራቸው እንኳ መስጠት ይቻላል። ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን። [መጅሙዑል ፈታዋ: 18/409]

ዘካን ለአንድ ሰው ብንሰጥ ይሻላል ወይስ ለብዙ ሰዎች መበተን?
ይበልጥ ጠቃሚ ነው የምንለውን መምረጥ እንችላለን። በርካታ ህዝብ ከባድ ችግር ላይ ወድቆ ከሆነ ለአንድ ሰው ከምናደርገው መጥቀም በሚችል መጠን ለተወሰኑ ሰዎች ማከፋፈሉ ነው የሚሻለው።
("መጥቀም በሚችል" ስል 50: 50 ብር ላከፋፍል ቢል በአሁኑ ሰዓት ምንም ትርጉም እንደሌለው ይታወቃል።)
አንፃራዊ በሆነ መልኩ ድሃዎቹ ያለባቸው ችግር ቀለል የሚል ከሆነ ለአንድ ሰው፣ ለሁለት ሰው በመስጠት ራሳቸውን እንዲችሉ ማገዝ ሊሻል ይችላል።
ባጭሩ የተሻለ ይጠቅማል የምንለውን አይተን መወሰኑ ነው የሚሻለው። ወላሁ አዕለም።

መነሻ ተመን (ኒሷብ) ካልደረሰ ገንዘብ ዘካ ማውጣት አይፈቀድም።
[ሙግኒ፣ ኢብኑ ቁዳማ: 2/631]

የህፃንና የአእምሮ በሽተኛ ገንዘብ መነሻ ተመን (ኒሷብ) ከደረሰ ዘካ ሊወጣለት ግድ ይላል። ሰዎቹን ሳይሆን ገንዘቡን የሚመለከት የደካሞች ሐቅ ስለሆነ ነው።
ስለዚህ ሃላፊ ወይም ተወካይ የሆኑ ሰዎች ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል።

ዘካን በራስም፣ በተወካይም መስጠት ይቻላል። ሆኖም ታማኝነታቸውን የማናውቃቸውን አካላት መወከል አይገባም። በአሁኑ ሰዓት የዘካን ገንዘብ ለቡድናዊ አላማ የሚያውሉ አካላትም በዝተዋል። ስለዚህ ጠንቀቅ ልንል ይገባል። ከቻልን በራሳችን ካልሆነ በምናምነው ሰው ብቻ ትክክለኛ ቦታ እንዲደርስ እናድርግ።

ውዝፍ ዘካ ያለበት!
~~~~~~~~~~~
በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የብዙ አመታት ውዝፍ ዘካ ያለበት ሰው ወደ ኋላ ተመልሶ የማውጣት ግዴታ አለበት። እንጂ ያለፈው አልፏል ይቅር አይባልም።

ዘካ ከወጀበበት በኋላ ሳያወጣ የሞተ ሰው!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ልክ እንደ ሰው እዳ ዘካው መከፈል አለበት። ምክንያቱም የገንዘብ ሐቅ ስለሆነ በሰውየው ሞት ግዴታው አይወርድም። ይህ የዐጧእ፣ የሐሰን አልበስሪ፣ የዙህሪ፣ የቀታዳ፣ የሻፊዒይ፣ የአሕመድ፣ የኢስሓቅ፣ የአቡ ሠውር ፣ ወዘተ አቋም ነው።
"የአላህ እዳ ሊከፈል ይበልጥ የተገባ ነው።" [ቡኻሪና ሙስሊም]

ዘካን ለወላጆች፣ ለልጆች፣ ለእህትና ለወንድም!
~~~~~~~~~~~~~~~~
ለወላጆችና ለልጆች ዘካ መስጠት እንደማይቻል ቁርጡቢ፣ ኢብኑ ሐጀርና ሌሎችም ኢጅማዕ ጠቅሰዋል። ምክንያቱ ደግሞ ልጅ ለወላጅ፣ እንዲሁም ወላጅ ለልጅ መሰረታዊ ወጪን የመሸፈን ግዴታ ስላለባቸው ነው።
ወደላይ አያትና ቅድመ አያት፣ ወደታች የልጅ ልጅም ተመሳሳይ ብይን ይይዛሉ።
ማሳሰቢያ!
~~~~~~~
*እዳ ካለባቸው እንዲሁም ሊረዳቸው የሚችልበት አቅም ከሌለው ግን ሚዛን የሚደፋው ዘካ ሊሰጣቸው ይፈቀዳል የሚለው ነው ይላሉ ሸይኹል ኢስላም አሕመድ ኢብኑ ተይሚያ። [መጅሙዑል ፈታዋ: 25/90፣ 25/92]
ኢብኑ ዑሠይሚንም ተመሳሳይ ነገር ተናግረዋል። [ሸርሑል ሙምቲዕ: 6/250]
* ወንድም እህቶች ከሰጪው ጋር በአንድ ቤት ሳይሆን በውጭ የሚኖሩ ከሆኑ ዘካ ሊሰጣቸው እንደሚቻል ዑለማዎች ይገልፃሉ። በሰጪው ስር ሆነው አብረው የሚኖሩ ከሆነ ግን ሊሰጣቸው አይፈቀድም።

የወርቅና የብር ዘካ
~~~~~~~~~~~
ወርቅ 85 ግራም
ብር 595 ግራም ከሞላ
በየዓመቱ 2•5% ዘካ ማውጣት ግዴታ ነው።

ለሽያጭ/ ለንግድ ታስቦ የተዘጋጀ ቤት/ መሬት ከታሰበበት ጊዜ ጀምሮ አመት ከሞላው ቢሸጥም ባይሸጥም ዘካ አለበት።
* ለሽያጭ የተዘጋጀ ሳይሆን ነገር ግን ጉዳዩን ጨርሶ ወይም ሐሳቡን ቀይሮ ሊሸጠው ወሰነ። በዚህ ላይ እያለ ገዢ አጥቶ ሳይሸጥ አመት ቢቆይ እንኳ ዘካ የለበትም። ከተሸጠ በኋላ ገንዘቡ አመት ሲሞላው ዘካ አለበት።
* መኪናም ቢሆን እንዲሁ ነው። ለሽያጭ ከተገዛ ባይሸጥ እንኳ ወቅታዊ ዋጋው ተገምቶ ዘካ ማውጣት ግድ ነው። ለመገልገያ ከተገዛ ግን የለበትም።
።።።
የአክስዮንና የኮንዶሚኒየም ተቀማጭ ብር ዘካ
።።።።።።
★ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ ድርሻ (አክስዮን) ያለው ሰው ገንዘቡ ለአቅመ ዘካ ከደረሰ ዘካውን ማውጣት አለበት። ብዙ ሰዎች ይህን ሊረሱ ወይም ላያውቁ ስለሚችሉ ማስታወስ አለብን።
★ ለኮንዶሚኒየም ቤት ግዢ፣ ወይም በቦንድ ግዢ፣ ወይም በሌላ ሰበብ ድርጅት ላይ ወይ ሌላ ሰው ላይ ተቀማጭ ገንዘብ ያለው ሰው ለዘካ መጠን የደረሰ ከሆነ ዘካ ማውጣት አለበት።
ማሳሰቢያ!
~~~~~~~
* የዘካ ነገር በጣም ትኩረት የተነፈገው ስለሆነ እባካችሁ በቻልነው አቅም ግንዛቤ እንፍጠር። በትክክል የሚመለከተው ሁሉ ቢያወጣ ስንት ችግር በተቀረፈ፣ ስንት ወገን በተደጎመ ነበር።
* ዘካ ግድ ሆኖበት ነገር ግን በአክሲዮን ወይም በመሬት ወይም በሸቀጥ ላይ ካለው ውጭ ለዘካው የሚከፍለው ብር እጁ ላይ የሌለው ሰው ሂሳቡን አስልቶ ያስቀምጥና በሚችል ጊዜ ይከፍላል።

የእንስሳት ዘካ
=========
ግመል
~~~~~~~
ከ5 ግመል ያነሰ ያለው ዘካ የለበትም። 5 እና ከዚያ በላይ ግመሎች ያሉት ሰው በሚከተለው መልኩ ይሰጣሉ:–
ከ5–9 አንድ ፍየል፤
ከ10–14 ሁለት ፍየሎች፤
ከ15–19 ሶስት ፍየሎች፤
ከ20–24 አራት ፍየሎች፤
ከ25–35 ሁለተኛ አመቷን የጀመረች አንድ ሴት ግመል፤
ከ36–45 ሁለት አመት የደፈነች አንድ ሴት ግመል፤
ከ46–60 አራተኛ አመቷን የጀመረች አንድ ሴት ግመል፤
ከ61–75 አምስተኛ አመቷን የጀመረች አንድ ሴት ግመል፤
ከ76–90 ሁለት አመት የደፈኑ ሁለት ሴት ግመሎች፤
ከ91–120 አራተኛ አመታቸውን የጀመሩ ሁለት ሴት ግመሎች።
ከ120 ሲያልፍ በየ 40ው ጭማሬ ሁለት አመት የደፈናት አንድ ሴት ግመል፤ በየ 50ው ጭማሬ ደግሞ ሁለት አመት የደፈናት አንድ ሴት ግመል
[ቡኻሪ: 1454]
የከብት ዘካ
~~~~~~~
① ከ30–39 አንድ አመት የሞላው/የሞላት አንድ ጥጃ፤
② ከ40–59 ሁለት አመት የሞላው/የሞላት አንድ ጥጃ፤
③ 70 ከሆኑ → አንድ አመትና ሁለት አመት የሚላቸው አንዳንድ፤
በጨመረ ቁጥር በዚሁ መልኩ እያገናዘቡ ይሰላል ። [ሙስነድ አሕመድ: 5/230] [አቡ ዳውድ: 1576]
የበግና የፍየል ዘካ
~~~~~~~~~~~
ፍየልና በግ አንድ ላይ ተቆጥረው ዘካቸው ይወጣል። ዘካው ከሚበዛው አይነት ይወጣል። እኩል ከሆኑ ከፈለገው ማድረግ ይችላል።
ከ40–120 አንድ ፍየል
ከ121–200 ሁለት ፍየል
ከ201–399 ሶስት ፍየል
ከዚህ በላይ በያንዳንዱ መቶ አንዳንድ ፍየል።
[ቡኻሪ: 1454]
* ፈረስ፣ በቅሎ፣ አህያ ዘካ የለባቸውም።
https://t.me/IbnuMunewor
የወር ደሞዝተኛ ዘካ
~~~~~~~~~~~~
የወር ደሞዝተኛ ገንዘብ ዘካ ግዴታ የሚሆንበት የሚከተሉትን መስፈርቶች ሲያሟላ ነው።

① ለዘካ መነሻ መጠን (ኒሷብ) ሲደርስ።
ይህም ከኒሷብ በታች የሆነና በየጊዜው ወጭ የሚደረግ ገንዘብ ዘካ አይመለከተውም።

② ኒሷብ ከደረሰ በኋላ አመት ሲቆይ። አመት ያልሞላው ከሆነ ዘካ አይመለከተውም።

ስለዚህ ለዘካ መጠን ደርሶ አመት ሲሞላው ዘካ ያወጣል። ለማውጪያ ጊዜ ይሆነው ዘንድ ከአመቱ ውስጥ አንድ ቀን ይወስናል። ከዚያም እስከ መጨረሻው ወር ከተጠራቀመው አጠቃላይ ገንዘብ ላይ 2•5% ያወጣል።

ውስብስብ አሰራር ውስጥ ከመግባት በዚህ መልኩ መጠቀም የተሻለ ነው። ወላሁ አዕለም።

@ibnumunewor
የዘንድሮው የወረቀት ብር ዘካ መነሻ መጠን ስንት ነው?
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
መግቢያ: –
የወረቀት ብር ኖት ዘካ አለበት ወይስ የለበትም በሚለው ላይ ቀደም ብሎ ሞቅ ያለ ውዝግብ ነበር። ነገር ግን "ዘካ የለበትም" የሚለው ሀሳብ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀዘቀዘ፣ እየደበዘዘ ነው ያለው። ምክንያቱም ዛሬ የሰው ንብረት እንዳለ የወረቀት ብር በመሆኑ በዚህ ላይ ዘካ የለም ማለት እንዳለ ዘካን ወደ ማራቆት ነው የሚወስደው። በዚህና በሌሎችም ምክንያቶች የብዙሃን ዑለማእ አቋም ከወረቀት ብር ኖት ዘካ ሊወጣ ይገባል የሚለው ሆኗል።


መነሻ ተመኑ (ኒሷቡ) ስንት ነው?
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
የወረቀት ብርን የዘካ መነሻ መጠን አስመልክቶ የዘመናችን ዑለማዎች ሶስት የተለያዩ ሐሳቦችን ሰንዝረዋል። (የልዩነታቸው መንስኤ የወረቀት ብር ድሮ ያልነበረ መሆኑ ነው።) እነሱም: –

ሐሳብ 1:– መነሻ ተመኑ የብር (ሲልቨር) መነሻ ተመን መድረስ ነው። ይህም 595 ግራም ብር የሚገዛ ማለት ነው።

ሐሳብ 2:– መነሻ ተመኑ የወርቅ መነሻ ተመን መድረስ ነው። ይህም 85 ግራም ወርቅ የሚገዛ ማለት ነው።

ሐሳብ 3:– ከሁለቱ መለኪያዎች ዝቅ ያለው ተመን ዋጋ ላይ መድረስ ነው።

★ በዚህ ርእስ ላይ ጥቂት ዳሰሳ ብናደርግ ሶስቱንም ሐሳቦች በየፊናቸው ያንፀባረቁ ዑለማዎች ሊገጥሙን ይችላሉ።

የቱ ሚዛን ይደፋል?
~~~~~~~~~~~~
ወርቅና ብር በነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘመን የነበሩ እራሳቸውን የቻሉ መገበያያዎች ናቸው። ሁለቱም የተረጋገጡ መለኪያዎች ናቸው። ስለዚህ ሁለቱም መለኪያ እንደሆኑ ከተማመንን ከሁለቱ መለኪያዎች የኒሷብ መጠኑ ያነሰውን እናስቀድማለን። (ከላይ 3ኛው ምርጫ ማለት ነው።) ዝቅ ያለውን አልፈን ወደ ከፍተኛው ለመዝለል አጥጋቢ ምክንያት ያስፈልገናል።

ይህንን እንደ ቀመር ከወሰድን በኋላ በአሁኑ ጊዜ ስላለው የወርቅና የብር ዋጋ ስንመለከት ሰፊ ልዩነት እናገኛለን። ቀድመን የምናገኘው የብሩን ኒሷብ ነው። ስለዚህ 595 ግራም ብር ለወረቀት ብር ኖት መነሻ የዘካ ተመን ይሆናል ማለት ነው።

ወቅታዊ ዋጋ
~~~~~~~~
ብር በግራም ስንት እንደሆነ ከተለያዩ ቦታዎች ለማጣራት ሞክሬያለሁ። የደረስኩበት ድምዳሜ በግራም 55 ብር ነው የሚል ነው። ይህም ማለት
55 ብር × 595 ግራም=32,725 ብር ይሆናል ማለት ነው።
ስለዚህ በአሁኑ ወቅት 32,725 ብርና ከዚህ በላይ ያለው ሰው ያጠቃላዩን 2•5% ያወጣል ማለት ነው። ለምሳሌ
32,725 ብር ያለው 818.10 ያወጣል።
40 ሺ ብር ያለው 1 ሺ ብር ያወጣል።
50 ሺ ብር ያለው 1,250 ብር ያወጣል።
በዚህ መሰረት ሌሎችንም መጠኖች ማስላት ነው።

* ልብ በሉ! ብሩ ለዘካ መጠን ከደረሰ በኋላ አመት ሲቆይ ነው ዘካ ግዴታ የሚሆንበት። አመት ካልሞላው ዘካ አይመለከተውም።

والله أعلم
ለምርመራ የሚሰጥ ደም ፆም ያበላሻል?
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ለህክምና ምርመራ ደም መስጠት ፆም አያበላሽም። የሸይኽ ኢብኑ ባዝንና የኢብኑ ዑሠይሚንን ፈትዋ ይመልከቱ።

[መጅሙዑ ፈታዋ ኢብን ባዝ: 15/274] [ፈታዋ አርካኒል ኢስላም፣ ኢብኑ ዑሠይሚን : 478]
ብድርና ዘካ
~~~~~~
ገንዘቡን ለሰው ያበደረ ሰው
① ተበዳሪው ቸግሮት መመለስ ካልቻለ ወይም ደግሞ ባይቸግረውም ዛሬ ነገ እያለ የሚያጉላላ ከሆነ ባለ ገንዘቡ የዘካ ግዴታ የለበትም። ኋላ ገንዘቡ እጁ ከገባ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ አመት ሲሞላው ዘካ ግዴታ ይሆንበታል።

② ተበዳሪው ቢጠየቅ በቀላሉ የሚመልሰው አይነት ብድር ግን ከተበዳሪው ተቀበለውም አልተቀበለውም ዘካው ሊወጣ ግድ ይላል።

ይህን የኢብኑ ባዝ ፈትዋ ያመሳክሩ።

https://binbaz.org.sa/fatwas/8946/%D9%84%D8%A7-%D8%B2%D9%83%D8%A7%D8%A9-%D9%81%D9%8A-%D8%A7%D9%84%D8%AF%D9%8A%D9%86-%D8%A7%D9%84%D8%B0%D9%8A-%D8%B9%D9%84%D9%89-%D9%85%D8%B9%D8%B3%D8%B1
በታክሲ ላይ ዘካ አለበት?
~~~~~~~~~~~~~~~
የህዝብ ማመላለሻና የጭነት መኪኖች በገቢያቸው እንጂ በራሳቸው ዘካ የለባቸውም። የሚያስገቡት ገቢ ለዘካ መጠን ከደረሰ በኋላ አመት ከሞላው የአጠቃላዩን 2•5% ዘካ ይወጣል።

[መጅሙዑል ፈታዋ፣ ኢብኑ ባዝ: 14/181]
[መጅሙዑል ፈታዋ፣ አልለጅነት አድዳኢማህ: 9/349]