Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
ጫት የዱኣ መሳሪያም የእስልምና አካል አይደለም፡፡
ያ ምርጡ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የመጡበት ውብ ሃይማኖት እስልምና በሰርጎ ገቦች ብዙ መጥፎ ነገሮችን የኢስላም አካል አስመስለው ሰግስገውበታል፡፡ የኢስላም ምርጥ ሊቃውንትም በየጊዜው እነዚህ ሰርጎ ገብ እምነቶች እና መጥፎ ተግባራት ከኢስላም አካል አለመሆናቸውን የተቃወመ ቢቃወማቸውም አብራርተው አስረድተዋል፡፡
ጫት እንደሚታወቀው ሙስሊሙን አሽመድምዶ ከጌታው ጋር ያለንም ይሁን ከፍጡራን ጋር ያለውን መብት አንድ ቃሚ እንዲያጓድል ሰበብ የሆነ አደገኛ መጥፎ ቅጠል ነው፡፡ አሳዛኙ እውቀት አላቸው ተብለው ሙስሊሙን ኡማ የሚቅመው በርትቶ እንዲቅም፣ የማይቅመው እንዲቅም ጫትን የኢስላም አካል እና የዱኣ መሳሪያ አድርገው የሚሰብኩ ሆድ አደሩዎች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ በመንዙማቸው፣ ሌላኛዎቹ ባገኙት መድረክ ላይ ጫትን እንደጥሩ ነገር ለሙስሊሙ ያስተዋውቃሉ፡፡ ሙስሊሞች ሊረዱ የሚገባቸው ጫት በጣም አደገኛ ነው፡፡ ይህም በተግባር የምናየው የት ይደርሳሉ የተባሉ ትዳሮች ሲበተኑ፣ የት ይደርሳሉ የተባሉ ወንድም እና እህቶች ተበለሻሽታ ማየታችን ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው፡፡
በመንዙማዎች ላይ ስለ ጫት ከተሰበኩ አደገኛ ስንኞች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
- “ጁሉሱ ሰኣቲን ጥቂት ቃቅምና (ጫት ቃምና ትንሽ ተቀመጥ)
ንገረው ለመውላህ እበሩ ቁምና”
- “እነሱ ይበራሉ በመቶ ሃምሳ ጀት፣ እኛ ቀደም ናቸው በአንድ ዘርባ ጫት”
- “ፍየል ቅጠል በልታ ትወልዳለች መንታ፣
መቼም እርባን የለው በጫት የተመታ”
- “ዝናቡ ዘነበ ጫቱ ለመለመ፣ የሚቅመው ቢያገኝ እያጉረመረመ”
- ከ አስር ሺህ መትረየስ አጥምዶ ከቆመ፣
ከሺህ ፈረሰኛ ተባብሮ ለቆመ፣
ይበልጣል ደግበል አጥብቆ የቃመ፣
ጠላቱንም ጎድቶ ወዳጁን ጠቀመ፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አላህ በዚህ ሱስ የተያዙትን በጠቅላላ እንዲያወጣቸው ዱኣ እና ምክር አይለያቸው፡፡ ጫት የምትቅሙ ወንድም እና እህቶች ሆይ! አላህ የውመል ቂያማ ጊዜያችንን በምን እንዳሳለፍነው ይጠይቀናል፡፡ ከዚህ ጊዜን እና ስብእናን ከሚገድል እርኩስ ቅጠል አላህን ለምናችሁ ለእሱ ስትሉ አቁሙ፡፡
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
April the fool?
ማንቂያ ደውል! እስከመቼ ዲንን መቃረን?
የነብዩን (ﷺ) ቃል ከነፍሶት፣ ከጓደኞቾት እና ከማንም በላይ ያስበልጣሉ ወይንስ አያስበልጡም?
ነብዩ (ﷺ) “ለቀልድም ብሎ መዋሸት አይቻልም” ይሉናል፡፡
ዛሬ ዛሬ ፈረንጅ የሰራውን ሁሉ መስራት የሚፈልግ አለ፡፡ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ሰውን ለማስደንገጥ፣ ያልሞተውን ሞተ፣ ያልተገጨውን ተገጨ፣ ያልደረሰውን ደረሰ ብሎ ሰዎችን ማስደንገጥ የኢስላም አካል አይደለም፡፡ ኢስላም አይደለም ለማስደንገጥ ለቀልድ መዋሸትን ከልክሏል፡፡ እባካችሁ እጅ እንስጥ ሙሉ ለሙሉ ከእዚህ እርኩስ ኩረጃ እንራቅ፡፡ ኢስላም ሙሉ ነው፡፡ ከፈረንጅ መኮረጅ አይፈልግም፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብዩ ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሀቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
አምልኮ ለአላህ ብቻ የተገባ ነው።
ነብዩ (ﷺ) የአላህ ባሪያው እና መልክተኛው ናቸው። ከአምልኮ ምንም አይገባቸውም።
ነብዩ (ﷺ) ማለት፡-
ይታመማሉ፡- ነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) ብዙ ጊዜ ታመው የነበሩባቸው ክስተቶች ነበሩ። ሞት አፋፍ ላይ ሆነውም ከባድ ትኩሳት በሽታ አጋጥሟቸው ነበር። አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው ጌታችን ግን የታመመን ሁሉ የሚያድነው እሱ ብቻ ነው።

ይረሳሉ፡-
ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ይላሉ “እናንተ እንደምትረሱት እኔም እረሳለሁ። ስረሳ አስታወሱኝ።” አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው ጌታችን አላህ ግን ምንንም ነገር አይረሳም።

ይራባሉ፡-
ነብዩ (ﷺ) በአንድ አጋጣሚ እሳቸው፣ አቡበክር እና ኡመረ (ረድየላሁ አንሁማ) ተርበው ነበር። አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው ጌታችን አላህ ግን የሚመግብ እና የማይመገብ ነው።

ይተኛሉ፡-
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንቅልፍ ወስዷቸው ፈጅር ሰላት አምልጧቸው ያውቃሉ። አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው ጌታችን አላህ ግን አያንጎላጅም አይተኛም።

ሞተዋል፡-
ነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) በረቢአል አወል 12፣ ሰኞ ቀን ሞተዋል። በብቸኝነት አምልኮ የሚገባው ጌታችን ግን ህያው እና የማይሞት ነው። ከነብያት ቀጥሎ ምርጥ ሰው የሆነው አቡበክር ሲዲቅ (ረድየላሁ አንሁ) የአላህ መልክተኛ (ﷺ) የሞቱ ጊዜ እንዲህ ብሏል “ሙሐመድን የሚያመልክ ከነበረ ሙሐመድ በእርግጥ ሞቷል። አላህን የሚያመልክ አላህ ህያው እና የማይሞት ነው።”

ሰው ናቸው፡-
አንዳንድ አላዋቂዎች እንደሚሉት ብርሃን ወይንም ከብርሀን የተፈጠሩ አይደሉም። ከአባታቸው አብደላህ እና ከእናታቸው አሚና የተወለዱ ሰው ናቸው። አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው ጌታችን አላህ አልተወለደም።

አግብተዋል ወልደዋል፡-
ነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) አግብተው 7 ልጆች ወልደዋል። አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው ጌታችን አላህ ደግሞ ሚስት የለውም። አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው ጌታችን አላህ አልተወለደም።

ፍጡር ናቸው፡-
ፈጣሪ ብቸኛው አንድ አምላክ አላህ ሲሆን ከእርሱ ውጭ ያሉት በጠቅላላ ፍጡር ናቸው። አምልኮም የሚገባው ለብቸኛው ፈጣሪያችን አላህ ብቻ እና ብቻ ነው።

ይህን በግልፅ ማስቀመጥ ያስፈለገበት ምክንያት ብዙ ሰው ለአላህ ብቻ የሚገባውን አምልኮ ለነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) አሳልፎ ሲሰጥ ይታያል።

ለምሳሌ
- ከአላህ ውጭ እሳቸውን “ነብዩ ልጅ ስጡን” በማለት የሚለምኑ አሉ፣
- ከአላህ ውጭ “ነብዩ ያለፈውን እና መጪ ወንጀላችንን ምረውናል” ያለም አለ፣
- “መገን ነቢ የሁሉ ቀላቢ” የሚሉም አሉ፣
- “ኹዝ ቢየዲ ያረሱለላህ። አጊስና ያረሱለላህ (እጄን ያዙኝ ያ አላህ መልክተኛ ሆይ! እርዱን ካለንበት ጭንቅ አውጡን አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ!)” የሚሉም አሉ፣
- “ያቀመረል መካ አሰላሙ አለይካ…. ልቤ ባንቱ በእርሶ ተመካ” የሚልም አለ፣
- “አብሽር ወንድሜ ግባ በቶሎ፣ ምን ነው ያፈረው ያ ነቢ ብሎ።” እና የመሳሰለውን እያሉ የአላህን ብቸኛ መብት ለነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሚሰጡ አሉ።

ይህ በእርግጥ ሺርክ ነው። አምልኮ የሚገባው ለብቸኛው ፈጣሪ አላህ ብቻ እና ብቻ ነው። ነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) እንደ ሌሎች ነብያቶች ሁሉ ይዘውት የመጡት መልእክት “አላህን በብቸኝነት እንድናመልክ። ከእርሱ ውጭ በሚመለኩት በጠቅላላ እንድንክድ ነው።”

ነብየላህ ኢሳን (አለይሂ ሰላም) ነብይ እና ከ5 የቁርጠኝነት ባለቤት መልክተኞች ውስጥ ከመሆኑ ጋር ምንም አምልኮ አይገባውም ብለን አፋችንን ሞልተን እንናገራለን። ምክንያቱም ውዱ የአላህ ባሪያና መልክተኛ ኢሳ (አለይሂ ሰላም) ከአላህ የተላከውን መልእክት ማድረስ እንጂ ከአላህ ከጌትነትም ይሁን ከአምላክነት ምንም ድርሻ የለውም፣ ሸሪካም አይደለም፣ ረዳትም አይደለም፣ አላህ ከፈቀደ በኋላ ቢሆን እንጂ አያማልድም።
ልክ እንደዚሁ ነብዩ (ﷺ) የአላህ መልክተኛ እና ባሪያው ናቸው። ከአላህ የተላኩትን መልእክት ማድረስ እንጂ ከአላህ ከጌትነትም ይሁን ከአምላክነት ምንም ድርሻ የላቸውም፣ ሸሪካም አይደሉም፣ ረዳትም አይደሉም፣ አላህ ከፈቀደ በኋላ ቢሆን እንጂ አያማልዱም።
አላህ ሆይ! በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ላይ ድንበር ከማለፍ ጠብቀን። ሱናቸውን እስከለተሞታችን የምንከተል አድርገን።
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
By Ibnu Munewor
ለአስተዋዮች ብቻ!! [ቁጥር ①]
አቡ ዑሥማን አስሷቡኒ (373 ዓ.ሂ.) ረሒመሁላህ የሰለፎችን መዝሀብ ሲገልፁ እንዲህ ይላሉ፡-
“የቢድዐ ሰዎችን በመጫን፣ በማዋረድ፣ በማራቅ፣ ከነሱም፣ እነሱን ከመጎዳኘትም፣ እነሱ ጋር ከመኗኗር በመራቅም #ተስማምተዋል፡፡ እነሱን በመራቅና በማኩረፍ ወደ አላህ ዐዘ ወጀል በመቃረብም እንዲሁ (ተስማምተዋል)፡፡” [ዐቂደቱ ሰለፍ ወአስሓቢል ሐዲሥ፡ 113]
በሙብተዲዖች ላይ የተንፀባረቁ የሰለፎች ጠንካራ አቋሞችን አልፎ አልፎ የተከሰቱ ነጠላ ክስተቶች ብቻ እያስመሰሉ ለሚያቀርቡ አካላት!
አሁን ይሄ ሷቡኒ ያሰፈሩት መልእክት የአንድና የሁለት ሰው ነጠላ ክስተት ነው ወይስ የሰለፎችን ኢጅማዕ የሚገልፅ ነው?! አላህ ማስተዋሉን ያድለን።
አንዳንዶች ሳይነቁ የነቁ እየመሰላቸው ስለሆነ እንዲህ አይነት ማስረጃዎችን በሰፊው ልናዳርስ ይገባል።
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
ለአስተዋዮች ብቻ!! [ቁጥር ②]
ኢብኑ ቀይም አልጀውዚያ (751 ሂ) ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ቀደምቶችና ታላላቅ ኢማሞች በቢድዐ ላይ ያላቸው ተቃውሞ የከፋ ነበር፡፡ በየአፅናፉ በቢድዐ ሰዎች ላይ ጩኸዋል፡፡ ፈተናቸውንም በከባዱ አስጠንቅቀዋል፡፡ በዚህ ላይ አስቀያሚ ወንጀሎችን፣ በደሎችና ግፎችን ከሚቃወሙት በላይ ጫፍ የደረሰ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት የቢድዐ ጉዳት፣ የዲን አፍራሽነቷ እና ተፃራሪነቷ የከፋ ስለሆነ ነው፡፡” [መዳሪጁ ሳሊኪን፡ 1/378]
በሙብተዲዖች ላይ የተንፀባረቁ የሰለፎች ጠንካራ አቋሞችን አልፎ አልፎ የተከሰቱ ነጠላ ክስተቶች ብቻ እያስመሰሉ ለሚያቀርቡ አካላት:–
አሁን ይሄ ኢብኑል ቀይም ያቀረቡት ሐሳብ የአንድና የሁለት ሰው ነጠላ ክስተት ነው ወይስ ባጠቃላይ የሰለፎችና ቀደምት ምሁራን አቋም ነው?! ከስሜት ነፃ ሆነን እናስተውል።
አንዳንዶች ሳይነቁ የነቁ እየመሰላቸው ስለሆነ እንዲህ አይነት ማስረጃዎችን በሰፊው ልናዳርስ ይገባል።
By Ibnu Munewor
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
ከሰላማዊ ሰልፍ በፊት እና በኋላ!
******************************
አላህ ሆይ! በሐቅ ላይ አጽናን፡፡

አለም ላይ ከ 6 እና 7 አመት በፊት ስንት “ሰላማዊ ሰልፍ ሀራም ነው፤ ሰላማዊ ሰልፍ የሙስሊሞችን ደም ያስፈስሳል፣ ሰላማዊ ሰልፍ የካፊር ሱና ነው፣ ሰላማዊ ሰልፍ የሱና ሰዎች አካሄድ አይደለም፣ ሰላማዊ ሰልፍ ጉዳት እንጂ ምንም ጥቅም የለውም” ሲሉ የነበሩ በጣም ብዙ ናቸው፡፡

ከዛም የፈተናው ጊዜ መጣና ቱኒስያ ላይ (ይህ ስሙ ብቻ) ሰላማዊ ሰልፉ በመባል የሚታወቀው የጥፋት ሰልፍ ሲጀመር በየአለሙ ይህን ፈተና ትናንት ሲቃወሙ እንዳልነበር ዛሬ እጃቸውን ከተው በንግግር በመደገፍ፣ እራሳቸው በመውጣት፣ ሰልፉን የወጡትን ሰዎች በመደገፍ፣ ሰልፉን የሚቃወሙትን ሰዎች በመቃወም እና በመተቸት ተምቦራጨቁበት፡፡

ይህ ሁሉ ሲሆን የሐቅ ሰዎች ድሮ የሚያውቁት ሐቅ ላይ በአላህ ፍቃድ እና እገዛ ጸኑ፡፡

እነዚህ በሐቅ ላይ መጽናት ያቃታቸው ስሜታቸውን ተከታይ የሆኑ የፊትናው ተሳታፊዎች፣ የፊትናው ቀስቃሾች አለም ላይ ሙስሊሞች ላይ የሚከተለው ሁሉ ጉዳት ሲደርስ ምን ይሰማቸው?
- አደለም ችግሩ ሊወገድ ሙስሊሞች ላይ ጭራሽ ነገሮች ከብደው፣
- ሙስሊሙ ክብሩ ተዋርዶ፣
- ሴቶች ሂጃባቸው ተገፎ እና ተደፍረው፣
- ህፃናት እና ንጹሀን ተገድለው፣
- ስንቶች የአካል ጉዳተኛ ሆነው፣
- ልጆች የቲም ሆነው፣
- ሰላም ጠፍቶ፣
- ሙስሊሞች ለስደት ተዳርገው፣
- አገራቸው የጠላት መጫወቻ ሆና፣
- ገንዘባቸው ተዘርፎ…….
እና የመሳሰለው….
ታድያ እነዚህ በሐቅ ላይ ሳይፀኑ እንደ አየሩ ፀባይ የሚቀያየሩ ሰዎች አላህ ፊት እጃቸው ላረፈበት ፈተና እንደማይጠየቁ ምን አሳወቃቸው?
አያፍሩም መቃወም ባለባቸው ቦታ ዝም ብለው፣ ሰውን አፋቸውን ሞልተው ቀስቅሰው፣ የሰላማዊ ሰልፍ ተጣሪዎችን አግዘው፣ በሰላማዊ ሰልፍ ቀስቃሾች ላይ መልስ የሚሰጡትን በመቃወም የሚያደርጉትን የጥፋት ጉዞ “ጥቅም እና ጉዳትን ማመዛዘን” ሲሉ ይጠሩታል፡፡ ጥቅም እና ጉዳት በቁርኣን እና በሀዲስ እንጂ በሌላ አይመዘንም፡፡ እውነታው ግን እስቲ ያመጡትን ጥቅም ያሳዩን? ከላይ የዘረዘርናቸው ሁሉ ጉዳቶች ናቸው፡፡
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን፡፡
አላህ እንዲህ ይላል
قُلْ هَلْ نُنَبِّئُكُم بِٱلْأَخْسَرِينَ أَعْمَٰلًا
“በሥራዎች በጣም ከሳሪዎቹን እንንገራችሁን?” በላቸው፡፡
ٱلَّذِينَ ضَلَّ سَعْيُهُمْ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَهُمْ يَحْسَبُونَ أَنَّهُمْ يُحْسِنُونَ صُنْعًا
እነዚያ እነሱ ሥራን የሚያሳምሩ የሚመስላቸው ሲሆኑ በቅርቢቱ ሕይወት ሥራቸው የጠፋባቸው ናቸው፡፡

እውቀት ማለት ከፈተና በፊት ያወቁትን በፈተና ወቅት የሚተገብሩት እንጂ እንደ አየሩ ፀባይ የሚቀያየሩበት አይደለም፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አብደላህ ኢብን መስኡድ (ረድየላሁ አንሁ) እንዲህ ይላል “መከተል የፈለገ የሞቱትን (የሰሃባዎች) መንገድ ይከተል፡፡ በህይወት ያለ ፈተና አይታመንለትምና”፡፡ እኛ ልንከተል የሚገባው እነዛ በትክክለኛ እምነታቸው ጌታቸውን የተገናኙትን የሰሃባዎች እና የሰለፉነ ሷሊሂንን መንገድ እና እነሱን በበጎ የተከተሏቸውን ብቻ እና ብቻ ነው፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ በመምጣቱ ምንም የምንቀይረው አቋም የለም፡፡ ሠዎች በሃቅ ይለካሉ ሃቅ በሠዎች አይለካም፡፡
አላህ ሆይ! በሐቅ ላይ አፅናን፣ በዛውም መንገድ ላይ ግደለን፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብዩ ሙሐመድ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሀቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
ወፍ ከአምሳያዎቿ ጋር ታርፋለች (ዘመድ ከዘመዱ .....)

ያሲን ኑሩ ከዚህ ጠሞ አጥማሚ ኢኽዋኒ ዩሱፍ አልቀርዳዊ ጋር ምን ፈልጎ ነው አብሮት ፎቶ የሚነሳው?
ዩሱፍ አልቀርዳዊን ለማታውቁት የሚከተሉት ጥመቶችን የተሸከመ ሰው ነው፡፡

• የኩፍር ንግግሩ፡- የጁምዐ ሁለተኛ ኹጥባ ላይ የሚከተለውን ተናግሯል ‹‹ኹጥባዬን ጨርሼ ከመውረዴ በፊት ትንሽ ስለ እስራኤል ምርጫ መናገር እፈልጋለሁ፡፡ አረቡቹ በጠቅላላ ነዳህ ጲሪዝ ያሸንፋል ብለው ተስፋቸውን ጥለው ነበር፤ ነገር ግን ተሸነፈ፡፡ ከእስራኤል የምንወድላትም ይህንን ነው፡፡ የእኛም ሀገር እነደዚህች አገር እንድትሆን እንመኛለን እንፈልጋለን፡፡ በጥቂት ሰዎች አማካኝነት ሲመራ የነበረው ስልጣኑን አጥቷል፡፡ አገራችን ላይ እንደለመድነው 94% ወይንም 95% (ድምፅ) አይደለም ነገር ግን 99% (አዎን 99%፤ ምንድን ነው ይሄ?) አላህ ለሰው ልጆች እራሱን ተመራጭ አድርጎ ቢያቀርብ ይህንን ያህል ድምፅ አያገኝም ፡፡ይሄ (አረብ አገር ላይ የምናየው ምርጫ) ውሸት ማጭበርበር እና የመሳሰሉት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ እስራኤልን እሰየው እንላታለን››፡፡ ምድር በዚህ የኩፍር ንግግር አትሰነጠቅምን? ለሸይኽ ኢሰይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) ይህ ቃል በድምፅ ተከፍቶላቸው ከሰሙ በኋላ የሚከተለውን ተናገሩ ‹‹በአላህ እጠበቃለሁ፡፡ ይህ ሰው መቶበት ግድ ይለዋል፤ እምቢ ካለ እንደ ሙርተድ (ሀይማኖቱን እንደከዳ ሰው) ይገደል፡፡ ፍጡራንን ከፋጣሪ ስላስበለጠ፡፡ ተውበት ካደረገ አላህ የባሪያውን ወንጀል መሀሪ ነው፤ ካልሆነ ውላቱል አምር (የሙስሊም መንግስት) አንገቱን (በሰይፍ) ይቀንጥሰው፡፡››

• ‹‹ከይሁዳዎችን ጋር የእምነት ጦርነት የለንም የመሬት እንጂ፡፡ ካሃዲያንን ካሃዲያን ስለሆኑ አይደለም የምንዋጋቸው መሪታችንና ቤቶቻችንን ያላግባብ ስለቀሙን እንጂ›› (አራያህ መፅሄት ቁጥር 4696፣ 24 ሸዕባን 1995 ኢ.አ)፡፡ አላህ እና መልክተኛው ምን እንደሚሉ እንስማ፡፡ ይሁዳዎች ከሰዎች ሁሉ ከነሳራም ለአማኞች ጠላትነታቸው የበረታ ነው አለህም እንዲህ ይላል ‹‹ለአማኞች ከጠላትነት በኩል ዩሁዳንና ጣዖታዊያንን ታገኛለህ››ሱረቱል ማኢዳ

• ዘፈንና ሙዚቃን መፍቀዱ፤ እንዲያውም ጥሩ ነገር ነው ማለቱን ‹‹አል ሀራም ወል ሀላል›› ‹‹ፈትዋ ሙዐሲራ›› እና በመሳሰሉ መፀሃፎቹ መግለፁ፡፡ እራሱ እንደተናገረው ‹‹የፋይዛ አህመድ፤ ሻዲያ፤ ኡሙ ኩልሱም፤ ፊሩዝ እና የመሳሰሉትን ሴቶች ዘፈን መከታተል ይወድ እንደነበር ጠቅሷለል›› (አራያህ የሚባል የኳታር መፅሄት ቁጥር 5969 ቀን 19/ ጁማዱል ኡላ 1419 ሂጅሪ)፡፡ ዘፈን ሃራም ለመሆኑ የነብያችን አንድ ሀዲስ ሀቅን ለሚፈልግ ትበቃዋከች ‹‹የአላህ መልክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁንና) ከኔ ኡመት ሰዎች ይመጣሉ ለወንድ ልጅ ሀር ልብስን የሚፈቅዱ፤ መጠጥን እና የሙዚቃ መሳሪያን የሚፈቅዱ›› ኢማሙ ቡኻሪ ዘግበውታል፡፡ የአላህ ባሪያዎች እንደው እናንተው ፍረዱት፡፡

ኡለማዐል ኢስላም ከሰሃባዎች ጀምሮ፤ አቡ ሀኒፋ፤ ኢማሙ ማሊክ፤ ኢማሙ ሻፊዕ፤ ኢማሙ አህመድ፤ ሙሀዲስ ቡኻሪ፤ ሙስሊም ሁሉም በአንድነት ዘፈንን ከልክለዋል፡፡
ኢማሙ ማሊክ እንዲህ ይላሉ ‹‹እኛ ጋር ዘፈን የሚያዳምጥ ፋሲቅ ነው›› ታላቁ ሰሃባ አብደላህ ኢብን መስዑድ (አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና) እንዲህ ይላል ‹‹ዘፈን ማዳመጥ በቀልብ ኒፋቅን ያበቅላል ውሃ አዝርትን እንደሚያበቅል ሁሉ›› ፡፡ ቃዲ ኢያድ የተባሉ የማሊክ መዝሃብ ተከታይ ታላቅ አሊም ዘፈን ሀራም ለመሆኑ ኢጅማዕ ጠቅሰዋል፡፡
የሙዚቃ መሳሪያን አስመልክቶ ኢማሙ አህመድና አቡዳውድ የዘገቡት ሰሂህ ሀዲስ እንጨምር፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) ‹‹አላህ መጠጥን፤ ቁማርን፤ ከበሮ መምታትን ሀራም አደረገ›› ብለዋል፡፡

• የካቶሊኩ ፓፓስ በሞተ ጊዜ ‹‹አላህ ይማረው ማለቱ››፡፡ አላህ ግን መልክተኛውንም ሆነ አማኞችን ለነዛ በኩፍር ላይ ለሞቱ ሰዎች ምህረትን እንዳይጠይቁ አዟል፡፡

• አረቡ አለም ላይ የተነሳውን የስንት ሙስሊሞች ህይወት የጠፋበትን፣ አገር ጥለው የተሰደዱበትን፣ የጠላት መጫወቻ የሆኑበትን፣ ንብረታቸው የተዘረፈበትን ፈተና ቢንዚል በማርከፍከፍ ፊትና ሲቀሰቅስ የነበረ ሰው ነው፡፡

ዩሱፍ አልቀርዳዊ ይህንን እና ብዙ መሰል ከባባድ ስህተቶች አሉበት፡፡
የዩሱፍ አልቀርዳዊን አጥማሚነት ያላወቃችሁ ወንድም እና እህቶች ተጠንቀቁት፣ ወደ ተውሂድ ሳይሆን ወደ ፖለቲካ እና ወደ ጥመት የሚጣራ የፊትና ሰው ነው፡፡ አላህ ከጠሞ አጥማሚዎች ይጠብቀን፡፡

ያሲን ኑሩ ከዚህ በፊትም እንደተናገርነው ወደ ትክክለኛው መንገድ የሚጣራ ሰው አይደለም፡፡ ሙስሊሞች ከሱ ሊጠነቀቁ ይገባል፡፡ ‹‹የተውሂድ አድማስ›› በተሰኘው መፀሀፉም ላይ ዩሱፍ አል-ቀርዳዊ፣ ሰይድ ቁጡብና ሌሎችም መንገድ የሳቱ ሰዎችን እንደ ጥሩ አድርጎ ለኢትዬጵያ ሙስሊም ያስተዋወቀ ሰው ነው፡፡ ያሲን ኑሩና ጓደኞቹ ያሉበትን የተሳሳተ መንገድ ትተው ወደ አላህ ተመልሰው የጥንት የጠዋቷን መንገድ መከተል ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ እስኪሆን ድረስ ግን የኢትዬጵያ ሙስሊም ከነሱ እራሱን፣ ቤተሰቦቹን ያስጠነቅቅ ዘንድ እመክራለሁ፡፡ እንደሜታወቀው ሃቅ በሰዎች አይለካም፣ ሰዎች በሃቅ ይለካሉ እንጂ፡፡

እዚህ ጋር አንዳንድ ወንድሞች የዩሱፍ አል-ቀርዳዊን ስሀተት ተረድተናል ግን ለያሲን ኑሩ ለምን በድብቅ አትመክረውም ይሉ ይሆናል፡፡ መልሱም እሱ ይህን ፎቶ እንደትልቅ ነገር ሲነሳ ከዚህ ጠሞ አጥማሚ ጋር ብሎም ለኢትዬጵያ ሙስሊም በገሃድ እያስተዋወቀው ይህን ግለሰብ እኔ ለምንድን ነው በድብቅ የምመክረው?
እንዲህ በአደባባይ የወጣን ጥመት ማጋለጥ ላይ ሰውየውን በድብቅ መምከር የሚባል መስፈርት የለም፡፡
ያሲን ኑሩ የዩሱፍ አል-ቀርዳዊ ስህተቶች ተዘርዝረውለት ሲያበቁ በአደባባይ ሚድያን ተጠቅሞ ዩሱፍ አል-ቀርዳዊ ጥመት ላይ እንደሆነ እና እሱም ቀርዳዊን ለኢትዬጵያ ሙስሊም በማስተዋወቁ ለአላህ ተውበት በማድረግ ለህዝቡ ደግሞ ከስህተቱ በመመለስ ሃቁን ግልፅ ሊያደርግ ግድ ይለዋል፡፡ ይህን ሳያደርግ ለቀርዳዊ ወግኖ ጥፋቱን ሸፍኖለት አስተዋውቀዋለሁ ቢል ከራሱ ጀምሮ ባጠመማቸው ሰዎች ልክ ወንጀሉን ይሸከማል፡፡

እኛ ደግሞ እውነት እራሳችንንና ኡማውን ከጥመት ለመጠበቅ ከሆነ ወደ ጥመት የሚጣሩ ሰዎች መጋለጣቸው ሊያሳስበን አይገባም፡፡ እኛ ዘንድ ከምንምና ከማንም በላይ ተወዳጅ ሊሆን የሚገባው ሃቅ ነው፡፡

አላህ ሆይ ሃቅን በሃቅነቱ አሳየን የምንከተለውም አድርገን፣ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡ የአላህ ሰላትና ሰላም በነብየት ሁሉ መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
ስለ ሰሞኑን ከባድ ብርድ እስልምና ምን ይላል፡፡
የአላህ ባርያዎች ሆይ! አሁንም አረፈደም ንሰሃ እንግባ
ኢስላም የነብያት ሁሉ ሀይማኖት ነው፡፡ እንደሚታወቀው በሀይለኛ ሙቀት እና በሀይለኛ ብርድ ሰው ተቸግሯል፡፡ ይህም ከመሆኑ ጋር ለአላህ ካጠፋነው ጥፋቶች ንሰሀ ከመግባት ይልቅ በየዜና አውታሩ “የአለም በረዶ ስለቀለጠ ነው፣ ዛፎች በመቆረጣቸው ነው፣ ኦዞን በመሳሳቱ ነው…..” እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች ናቸው እየተባለ ይለፈፋል፡፡
እስቲ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ምን እንደሚሉ እንይ
አቡ ሁረይራ (ረድየላሁ አንሁ) ባስተላለፉት፣ ኡማሙ አል-ቡኻሪ በዘገቡት ትክክለኛ ሀዲስ ላይ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ
“ጀሀነም (እሳት) ወደ ጌታዋ ስሞታ አቀረበች፡፡ ከፊሌ ከፊሌን በላው አለች፡፡ አላህ ሁለት ጊዜ እስትንፋስን ፈቀደላት፡፡ አንደኛው በቀዝቃዜ ወራት ሌላኛው ጊዜ በሙቀት ወራት፡፡ በሙቀት ጊዜ የምታገኙት ከባድ ሙቀት እና በቅዝቃዜ ጊዜ የምታገኙት ከባድ ውርጭ (ቅዝቃዜ፣ ቀቅ) (ናቸው)፡፡”
حَدَّثَنَا أَبُو الْيَمَانِ، أَخْبَرَنَا شُعَيْبٌ، عَنِ الزُّهْرِيِّ، قَالَ حَدَّثَنِي أَبُو سَلَمَةَ بْنُ عَبْدِ الرَّحْمَنِ، أَنَّهُ سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ اشْتَكَتِ النَّارُ إِلَى رَبِّهَا، فَقَالَتْ رَبِّ أَكَلَ بَعْضِي بَعْضًا، فَأَذِنَ لَهَا بِنَفَسَيْنِ نَفَسٍ فِي الشِّتَاءِ وَنَفَسٍ فِي الصَّيْفِ، فَأَشَدُّ مَا تَجِدُونَ فِي الْحَرِّ، وَأَشَدُّ مَا تَجِدُونَ مِنَ الزَّمْهَرِيرِ ‏"‌‏.‏
ልብ እንበል ከባዱም ሙቀት እና ከባዱም ብርድ የአዋቂዎች ሁሉ አዋቂ፣ የአላህን ፈሪዎች ሁሉ ፈሪ፣ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ እንደነገሩን የጀሃነም እሳት የምትተነፍሰው ሁለት ትንፋሽ ምክንያት ነው፡፡
ሌላው መገንዘብ ያለብን ነገር እስልምና ሙሉ መሆኑን ለማንኛውም አለም ላይ ላለ ክስተት በል እንዲያውም ለሚቀጥለው አለም ጉዳዩች፣ የሚቀጥለው አለም ላይ ምን እንደሚከሰት በዝርዝር እና በጥቅል የተናገር ዉድ፣ ልዩ፣ የማይበረዝ፣ የማይሰረዝ፣ የማይደለዝ፣ ዘመን የማያልፍበት ሀይማኖት ነውና አጥብቀን እንያዘው፡፡ ይሀው ተመልከቱ አከም “Econmic Crisese” ኢኮኖሚክ ክራይስስ ብለው ሲያወሩ አላህ ጥንትም የወለድ መጨረሻው ይህ መሆኑን ነግሮን ነበር፡፡
ትዳር እንዲመሰረት እና ከዝሙት እንድንታቀብ ከጥንትም የነብያት ሁሉ ሀይማኖት መክሮ ነበር፡፡ ግን ይህን አልሰማ ብለው አሁን አለም ላለችበት ከባባድ በሽታዎች ተዳርገዋል፡፡
በሁሉም የህይወት ዘርፍ ላይ የጥንት የጠዋቱ ኢስላም (ሰለፍያ) በሄደበት መንገድ መሄድ ብቻና ብቻ ነው ዋስትናው፡፡ ሁለት ሃቅ የለም፡፡ ሁሉም ሙስሊም ከጥመት ቡድኖች እርቆ ወደ ብቸኛዋ አማራጭ እና ሁለተኛ ወደሌላት ሃቅ ጎዳና፣ ሰለፉነ ሷሊሂን የተጓዙባት ጎዳና መመለስ ግድ ይለዋል፡፡ አለበለዚያ በሙስሊሙ አለም ላይ እንዳየነው አሁንም ከባድ ኪሳራ ይከሰታል፡፡
ታድያ ምን ይበጀን?
አማኞች ወደ ጌታቸው በንሰሃ ሊመለሱ፣ ያችን “ጭማሪ አለን?” ብላ የምትጠይቀውን ጀሀነም ከሷ ጌታችን እንዲጠብቀን እሱን ዘውትር መለመን ግድ ይለናል፡፡ የአላህ ባርያዎች ሆይ! አሁንም አረፈደም ንሰሃ እንግባ፡፡ አላህ እነዚህን ሁሉ ተዓምራት የሚያሳየን በሰጠን አእምሮ የሱን ጌትነት፣ በቸኛ ተመላኪነት አውቀን ወደሱ እንድንመለስ ነው፡፡
አላህ ሆይ! ሁሌ ወዳንተ በጸጸት ከሚመለሱት አድርገን፡፡
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
ትግሬ፣ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀደሬ፣ ወለኔ፣ … አረብ፣ ነጭ፣ ጥቁር፣ እና የመሳሰለው ሁሉም
የዘር ሀረጋቸውን ወደላይ ሄዶ ሄዶ ከሰው ልጆች አባት ነብዩላህ አደም (አለይሂ ሰላም) ውጭ አይደለም፡፡ አደም ደግሞ የተፈጠረው ከአፈር ነው፡፡ ከአፈር የተፈጠረው የሰው ልጅ ደግሞ ሲሞት ወደ አፈር ይመለሳል፡፡
ታድያ ለምን ይሆን ዘሩን እንዲህ የሚመፃደቅበት እና አንዱ አንዱን የሚያንቋሽሽበት?
የፍጡራን ሁሉ ፈጣሪ፣ ብቸኛው አምላክ አላህ የሰው ልጆች የሚለያዩት ለእርሱ ባላቸው ፍራቻ ብቻና ብቻ እንደሆነ እንዲህ ሲል ይነግረናል፡፡
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَٰكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَٰكُمْ شُعُوبًا وَقَبَآئِلَ لِتَعَارَفُوٓا۟ ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ ٱللَّهِ أَتْقَىٰكُمْ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ
እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡
አንድ አምላክ ዘንድ የሰው ልጆች የሚበላለጡት እሱን በመፍራታቸው ብቻና ብቻ ነው፡፡
ለአእምሮ ባለቤቶች ይህ ትልቅ ትምህርት አለበትና ዘረኝነትን ሁላችንም እንራቀው፡፡
ጠለኣል በድሩ አለይና ትክክለኛ ሀዲስ አይደለም፡፡
ሃይማኖታችን በትክክለኛ ማስረጃ ላይ የተገነባ ነው፡፡
ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን እንዲህ ሲባል ጥያቄ ቀረበላቸው፡፡
ጠያቂ፡- የተከበሩ ሸይኽ አላህ ትክክለኛውን ነገር ይግጠሞትና የመዲና ሰዎች መልክተኛውን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጠለኣል በድሩ አለይና የሚለውን ነሺዳ እያሉ ተቀብለዋቸዋል የሚባለው እውነት ነውን?
(ይህንን ጥያቄ የጠየቅኩት) ይህንን ታሪክ (ቂሳ) ለነሺዳ ማስረጃ (መረጃ) የሚያደርጉ ሰዎች ስላሉ ነው፡፡

ሸይኽ ፈውዛን መልስ፡- ይህች ቂሳ (ታሪክ) ትክክለኛ ሆና አልተገኘችም (አልመጣችም)፡፡ በውስጧ ትክክለኛ አለመሆኗን የሚያመላክት ነገር አለ፡፡ ምክንያቱም (ስንኙ) “ጠለኣል በድሩ አለይና ሚን ሰንየቲል ወዳእ” ይላል፡፡ ሰንየተል ወዳእ (ከመዲና) በመካ አቅጣጫ አይደለም ያለው፡፡ ምክንያቱም መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና የመጡት በደቡብ አቅጣጫ ነው፡፡ መልክተኛው በሰሜን (አቅጣጫ) አልመጡም በሰንየተል ወዳእ ሊያልፉ ዘንድ፡፡ ሰንየተል ወዳእ ለመዲና በሰሜን አቅጣጫ ነው ያለው፡፡ ይሄ የማይገናኝ ነገር ነው፡፡

የሸይኽ ፈውዛን ንግግር እዚህ ላይ አበቃ፡፡
ሀይማኖታችን በማስረጃ ላይ የተገነባ ነው፡፡ በኢስላም ግጥም አለ፡፡ ግጥምን ለነሺዳ ማስረጃ አድርጎ ለማቅረብ መሞከር ወይ አላዋቂነት ወይ አውቆ አጥፊነት ነው፡፡ ኡመተል ኢስላም የተጠማው ኢስላማዊ ብለው የሚጠሩትን ዜማ፣ አዝማች፣ ሙዚቃ መሳሪያ ያለው፣ በኮምፒውተር የተቀናበረ ዘፈን ሳይሆን የጌታችንን ቃል ቁርኣን፣ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሀዲስ፣ የሰሃባዎችና ፈለጋቸውን የተከተሉ አስተምህሮትን ነው፡፡
እባካችሁ ቻናል ከፍታችሁ ኡማውን በነሺዳ ቀልቡን የምታደርቁትና ከቁርኣን የምታዘናጉት ሰዎች አላህን ፍሩ፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
በቁድስ ስም መነገድ ይቁም፡፡
የአላህን ትእዛዛት ብትፈፅሙ አላህ ይረዳችኋል፡፡
አል አቅሷን ማስለቀቅ የሚቻለው በአላህ ዲን ላይ በመፅናት ብቻ ነው፡፡
ዛሬ ዛሬ ወደ ዲናችን እንመለስ የሚሉ ሰዎች የነ አል አቅሷና የሌሎች ሙስሊሞች ጉዳዬች የማያገቧቸው ተደርገው እንዲታዩ የጥፋት ተጣሪዎች ይፅፋሉ፡፡ ሺርክና ቢድኣ ከነባለቤቶቹ ማስጠንቀቂያ በተሰጠባቸው ቁጥር “የቁድስ፣ የቦርማ፣ የሶሪያ ጉዳይ አያሳስባችሁም ወይ?” እየተባለ በነቁድስ ስም ይነገዳል፡፡ እነ ቁድስን የጥፋታቸው አለመታረሚያ ሰበብ አድርገው ያቀርቧቿል፡፡ እውነታው ግን ወደ ትክክለኛው የአላህ ዲን ሳንመለስ አይደለም አላቅሷን ማስለቀቅ ይባስ መከራ ውስጥ ነው የምንገባው፡፡
ብዙ በአል አቅሷ ስም የሚነግዱ ግን አላህ ያዘዘውን ለመፈፀም ዝግጁ ያልሆኑ አሉ፡፡
አላህ እኮ የአላህን ህግጋት ብትከተሉ (ብትፈፅሙ) አላህ ይረዳችኋል ሲል ቃል ገብቶልናል፡፡ ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አስተምህሮት እንደተነገረን ደጃል ሁሉን እያጠፋ መግደል የሚያቅተው የእምነት ባለቤት የሆነውን ግለሰብ ነው፡፡ ስለዚህ ደጃል ከባዱ ፈተና ሆኖ ሳ፣ የሁዳዎች ተከትለውት ሲያበቁ አብዛኛን ድል አድርጎ መጨረሻው ሲደርስ ያንን አንድ አማኛ ግለሰብ መግደል ያቅተዋል፡፡ ድል አላህና መልክተኛውን በመታዘዝ ነው፡፡ ውርደት አላህና መልክተኛውን በማመፅ ነው፡፡ ዛሬ አላህን በማመፅ፣ የመልክተኛውን ትእዛዝ በመራቅ ድል ይገኛል የተባለ ይመስል አላህን እያመፁ ኢስላማዊ ስም ይሰጡታል፡፡
አላህ ካዘነላቸው ጥቂቶች ውጭ
- ሙስሊም ነኝ እያሉ በታላላቅ ሺርክ ተጥለቅልቀዋል፣
- ቢድኣ ሙስሊም አገራት ላይ ሳይቀር ነግሶ፣
- የወላጅ ሀቅ እየተበደለና እየተጣሰ፣
- ሰሃባዎች እየተሰደቡና እየተተቹ፣ ብሎም ሰሃባ ተሰዳቢና ለሰሃባ ተሳዳቢ ጥብቅና የሚቆም እንደ አዋቂ እየተያ፣
- ዝሙት ተስፋፍቶ፣
- ወለድ እየተበላ፣
- ጀመኣ ሰላት በተለይ ፈጅር አንድ ሰፍ ሁለት ሰፍ እየተሰገደ (የሰላማዊ ሰልፍ ጊዜ አደባባይ ላይ ሚሊዬኖች ወጥተው)፣
- ሴቶች አላህ የረገመውን ቅንድብ መቀንደብ ማስቀንደብ፣ ዊግ መቀጠል ማስቀጠል፣ ንቅሳት መንቀስ ማስነቀስ እየፈፀሙ፣
- ከቀቁርኣን ተርቆ፣
- መጠጥ እየተጠጣ፣
- አደንዛዡን ጫት እየተቃመ፣
- ሲጋራ፣ ሺሻ እየተጨሰ፣
- ለኳስ ሲሉ ወንድ ልጆች ጀመኣ ሰላትን እየተዉ፣
- ሴቶች ሙሰልሰል እያሉ ፊልም እያዩ፣
- ከሀይማኖታዊ እውቀት ተርቆ እና ሌሎችም ………. መጥፎ ተግባራት እየተሰሩ ……
ቁድስ ልባችን ውስጥ ናት፣ ቦርማ፣ ዋ ሶሪያ እየተባለ በስማቸው ሶሺያል ሚድያ ላይ ይነገዳል፡፡
አል አቅሷን ትላንት ከየሁዳዎች እጅ አስለቅቋት የነበረው ኡመር ኢብኑ አል-ኸጣብ (ረድየላሁ አንሁ) ነው፡፡ ዛሬም ኡመርን የሚሳደቡ ራፊዳ ሺአዎች ወይንም ለነሱ ጥብቅና የሚቆሙት ኢኽዋኖች አያስለቅቋትም፡፡
እስቲ አላህን እንፍራና አላህ ግዴታ ያደረገብንን ሁላችንም በነፍስ ወከፍ እንፈፅም፡፡ ከከለከለን ሁሉ በቁርጥ እንራቅ፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ሲባል ከሚወጣው ሰው በላይ መስጂዳችንን ከፈጅር ሰላት ጀምሮ እናስውበው…….. እና ሌላም ትእዛዛትን መፈፀም ክልከላዎችን እንከልከል፡፡ ከዛም አላህ ይረዳናል፡፡
አላህን እንፍራ ኡመተል ኢስላም በጠቅላላ ወደ አላህ ስንመለስ ሁለት አገር ለስኬት እንበቃለን፡፡ በመጨረሻም ሙስሊሞች በነዚህ የሁዳዎች ላይ ድልን ይጎናፀፋሉ፡፡ አላህ እውነተኛ ሙስሊም ያድርገን፡፡ አል-ቁድስን፣ በርማን፣ ሶሪያም መላው አለም ላይ ያሉ ሙስሊሞችን መከራችንን ያንሳልን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
አፍሪካ ቲቪ ላይ ማስታወቂያቸው ተለቀቀላቸው ስለተባሉት ሩቃ ቤቶች…..
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩሕሩሕ እጅግ በጣም አዛኝ፡፡
ይህች አጭር ፅሁፍ የምትሆነው ሰሞኑን ፌስቡክ ላይ በደንብ ስለ ተራገበው ቲቪ አፍሪካ ላይ ማስተወቂያቸው ስለ ተለቀቀላቸው ሩቃ ቤቶችና ስለሚሰሩት አፀያፊ ተግባር የሚጠቅስ ነው፡፡

ወንድም ኢድሪስ ኢብን ኢልያስ በፃፈው ፅሁፍ ላይ አፍሪካ ቲቪ ላይ ማስታወቂያ ከለቀቁት ሩቃ ቤቶች ውስጥ አብዛኛዎቹ እዚህ መጥፎ ተግባራት ላይ የተሰማሩ መሆናቸው ማስረጃ እንዳለ ጥናት እንዳለም ነግሮኛል፡፡

ይህ ከሆነ እውነታው አፍሪካ ቲቪ ማስታወቂያ ከለቀቁት አጥፊዎች ውስጥ በማስረጃ የተረጋጋጡትን እዛው ቻናል ላይ እነዚህ ሩቃ ቤቶች በዚህ በዚህ ማስረጃ ሙስሊሞችን የሚጎዳ ይህን ይህን ጥፋት ፈፅመዋል ብሎ በግልፅ ማጋለጥ አለበት፡፡
በዚሁ በሶሺያል ሚድያ ላይም እነዚህ መጥፎ ሩቃ ቤቶች ከትክክለኞቹ ይለዩ ዘንድ በስነስርኣት ሊጋለጡ እና ኡማው ሊጠነቀቃቸው ይገባል፡፡
አፍሪካ ቲቪ መጀመሪያ ላይ የነዚህን ሩቃ ቤቶች መጥፎ ስራ ሳይውቅ ቀርቶ ሊሆን ይችላል፡፡ አሁን ግን ጥናት የሰሩ ወንጀሎቹን የተከታተሉ ወንድሞች ስላሉ ያን ማስረጃ ይዞ ሙስሊሙን ማህበረሰብ ይቅርታ ሊጠይቅ፣ ለወደፊቱ እንዲህ አይነት ማስታወቂያዎችን ከመስራቱ በፊት ያ ማስታወቂያ እንዲለቀቅለት የሚፈልገውን ድርጅት አሰራር ከሸሪኣ አኳያ ማጥናት አለበት፡፡ እዚህ ጋር “እኛ ማስታወቂ እናግኝ እንጂ ስለሌላው ምን አገባን” የሚባል አባባል የለም፡፡ ምክንያቱም አፍሪካ ቲቪ እራሱን የሀይማኖት ተቋም አድርጎ ስለሚንቀሳቀስ፡፡

እነዚህ ሙስሊሙ ላይ በእምነቱ፣ በክብሩ፣ በገንዘቡ በተለይ ሴት እህቶቻችን ላይ የተጫወቱ ሩቃ ቤቶች አፍሪካ ቲቪን ተጠቅመው ማስታወቂያቸውን ረጭተው ህዝብ ዘንድ እንደደረሱ ሁሉ አፍሪካ ቲቪ አሁንም ስርጭቱን ተጠቅሞ፣ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ወግኖ፣ ጥቅም ሳያታለው፣ ሀፍረት ሳይዘው፣ እንዲህ አይነት አውሪዎችን ማስጠንቀቅም ከኢስላም ክፍሎች ስለሆነ ስማቸውን ጠቅሶ ተጠንቀቋቸው ማለት አለበት፡፡

በዚሁ ትክክለኛ የሩቃና የባህል ህክምና ቤቶች የምናውቅ ወንድም እና እህቶች ለሙስሊሙ ማህበረሰብ እነዚህ ትክክለኞቹ ጋር እንዲሄዱ መጠቆም አለብን፡፡

ሙስሊሞች ሆይ! እራሳችንን በቁርኣን፣ በሀዲስና ሸሪኣው ባስቀመጣቸው ማር ጥቁር አዝሙድ….. በመሳሰሉት ማከም እንችላለን፡፡
ኢንሻ አላህ በዚህ በኩል ተከታታይ ፅሁፎች መዘጋጀት ይኖርባቸዋለው፡፡
አላህ የታመሙ ሙስሊም ወንድም እና እህቶቻችንን ከበሽታቸው ይፈውሳቸው፡፡
ፍልስጤም መቼ ነው የምትመለስልን?
በሸይኽ ሙሐመድ ሰኢድ ረስላን (ሀፊዘሁላህ)
አለም ላይ ያለ ማንኛውም ሙስሊም “ፍልስጤም መቼ ነው የምትመለስልን?” ብሎ ከጠየቀ
መልሱም “ወደ አላህ (በትክክለኛው እምነት፣ መልካም ስራ፣ አላህና መልክተኛውን በመታዘዝ ክልከላቸውን በመራቅ) ስትመለስ ፍልስጤም ያኔ ትምለሳለች፡፡”
ይህ መልስ ከአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሀዲስ የተውጣጣ (የተጨመቀ) ነው፡፡ ኢማሙ አሕመድ እና አቡ ዳውድ ከሰውባን (ረድየላሁ አንሁ) ይዘው በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ
“ህዝቦች በናንተ ላይ ይጠራራሉ፡፡ ልክ ሰዎች እርስ በርስ ከቀስ (ሰፊ ትሪ ላይ የቀረበ ምግብ) ለመብላት እንሚጠራሩት፡፡”
እነሱም (ሰሃባዎች) ጠየቁ “የአላህ መልክተኛ ሆይ! ያን ቀን በቁጥር አንሰን ነውን?”
እሳቸውም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ መለሱ “በፍፁም፡፡ ያን ጊዜ በቁጥር በጣም ብዙ ናችሁ፡፡ ነገር ግን ልክ እንደ ጉሳእ (የባህር አረፋ) ናችሁ፡፡ አላህ ከጠላቶቻችሁ ልብ ውስጥ ለናንተ የነበራቸውን ፍራቻ ያነሳና እናንተ ልብ ውስጥ ዋህንን ያደርጋል፡፡”
እነሱም (ሰሃባዎች) አሉ “የአላህ መልክተኛ ሆይ! ዋህን ምንድን ነው?”
እሳቸውም አሉ “ዱንያን መውደድና ሞትን መጥላት”
ኢማሙ አሕመድ 21897 እና አቡ ዳውድ 4297. ኢማም አልባኒ አሰሂሃ ላይ ትክክለኛ ብለውታል 8183
ወደ አላህ (በትክክለኛው እምነት፣ በመልካም ስራ፣ ትእዛዝን በማክበር፣ ክልከላን በመራቅ፣ በተውበት) የተመለስን ጊዜ ከእኛ የተወሰደብንን ይመልስልናል፡፡ ከአላህ መራቁን (እምነታችንን ሳናስተካክል፣ ቢድኣን እያጨማለቅን፣ መልካም ስራን ሳንሰራ፣ ሳንታዘዝ፣ ክልከላን ሳንርቅ) ከቀጠልንበት በእጃችን ያለውንም እናጣዋለን፡፡
በእርግጥ አላሁ (ተባረከ ወተኣላ) ይህንን ፍርድ በተከበረው መፀሀፉ እንዲህ ሲል አስቀምጦታል
[Q 14:7] وَإِذْ تَأَذَّنَ رَبُّكُمْ لَئِن شَكَرْتُمْ لَأَزِيدَنَّكُمْ ۖ وَلَئِن كَفَرْتُمْ إِنَّ عَذَابِى لَشَدِيدٌ
ጌታችሁም «ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ ብትክዱም (እቀጣችኋለሁ) ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነውና» በማለት ባስታወቀ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡
እሱ (የላቀውና ከፍያለው) የተሰጠንን አለማመስገን ያንን ፀጋ እንደሚያጠፋው አብራርቶልናል፡፡ አዋቂዎቻችን እንዲህ ይላሉ “በረካ የሚታደን ነገር ነው፡፡ ለተሰጠን በረከት ማመስገን ደግሞ (በረከቱ) እንዲፀና እንዲቀጥል እንዳይጠፋ ያደርገዋል (መጠበቂያ ነው)፡፡”
[ምንጭ :መታ ተኡዱ ኢለይና ፍልስጢን፡ ገፅ 7-8]
የሸይኽ ሙሐመድ ሰኢድ ረስላን ንግግር እዚህ ጋር ተፈፀመ፡፡
በአላህ ፍቃድ እዚሁ ፊስ ቡክ ላይ፣ በየመንደሩ፣ በየትምህርት ቤት፣ በየመስጊዱና ሁሉ ቦታ ፍልስጤም መቼ ነው ወደኛ የምትመለሰው እያልን ለምናስብ ኢትዬጵያዊ ወንድም እና እህቶች ሁሉ የሚከተለውን ጥያቄዎች ከነፍሴ ጀምሮ እጠይቃለሁ
1) ምን ያህሉ ሰው የተፈጠረለትን አላማ ያውቃል?
2) አገራችን ኢትዬጵያ ላይ ነብያት ከምንም በፊት ያስቀደሙት የተውሒድ ጥሪ በገጠርም በከተማም የሚገባውን ያህል ተሰራጭቷል?
3) ምን ያህሉ ኡለማ፣ ዳኢ ነብያት ሁሉ የተላኩበትን ተውሒድ ለኡማው በየቋንቋው አድርሷል?
4) የኢትዬጵያ ሙስሊም ከ40 ሚሊዬን በላይ ነው ይባላል፡፡ ምን ያህሉ የላኢላሃ ኢለላህን መስፈርቶች፣ የላኢላሃ ኢለላህን ትርጉም፣ የላኢላሃ ኢለላህን መእዘናት፣ ላኢላሃ ኢለላህን የሚያፈርሷትን ማስረጃዎቿን ጠንቅቆ ያውቃል?
5) ምን ያህሉ አርካኑል ኢስላምና አርካኑል ኢማንን በዝርዝር ጠንቅቆ ያውቃል?
6) ምን ያህሉ ስለ ሺርክ አደገኝነት ያውቃል?
7) ምን ያህሉ በሺርክ ተዘፍቋል?
8) ምን ያህሉ ከአላህ አምልኮ ወጥቶ ለቀብር ይሰግዳል፣ ያርዳል፣ ይሳላል……? ኡለማዎችና ዱአቶች እውነት አደራቸውን ተወጥተዋልን?
9) የሩቅ እውቀት በጠቅላላ ለአላህ ብቻ ሆኖ ሳለ አገራችን ላይ የክህደት መፀሀፍ የሆነውን “የሸህ ሁሴን ትንቢት” ምን ያህል ሰው እውነት ነው ብሎ ይቀበለዋል?
10) ምን ያህሉ ጌታችን አላህ ከአርሽ በላይ ከፍጡራኑ ሁሉ በላይ መሆኑን ያምናል?
11) አላህ በሐቅ ላይ አንድ ሁኑ ብሎን ሲያበቃ አገራችን ላይ አንድ የሀቅ መንገድ ብቻ ነው ያለው ወይንስ አንዷን ብቸኛ የሐቅ መንገድ የሚቃረኑ ብዙ የጥመት መንገዶች? ለምሳሌ (አህባሽ፣ ሱፊ፣ አሽአሪ፣ ሺኣ፣ ተብሊግ፣ ኢኽዋን፣ ቲጃኒ፣ የቃጥባሪ ሙሪዶች፣ የአብሬት ሙሪዶች፣ የአልከሶ ሙሪዶች፣ የኑርሁሴን ሙሪዶች…………)
12) አገራችን ላይ አንድነት ሲባል በተግባር ያየነው በሐቅ ላይ መሰባሰብ ነው ወይንስ ሺርክና ቢድኣ የሚሰራውን ሁሉ ደባልቆ “አንድ ነን” ብሎ መዋሸት?
13) ምን ያህሉ ኡማ ሱናን እና የሚፃረራትን ቢድአ ለይቶ ያውቃል?
14) ምን ያህሉ ከቢድኣ ርቆ ጌታችንን አላህ በሱና ይገዛል?
15) ምን ያህል በኢስላም የሌለ መውሊድ ወይንም የልደት በአሎች አገራችን ላይ ይከበራሉ? ለምሳሌ “የአብሬት መውሊድ፣ የቃጥባሪ መውሊድ፣ የጀማ ንጉስ መውሊድ፣ የቦረናው መውሊድ፣ የዳንግላው መውሊድ፣ የአልከሶ መውሊድ፣ የአሊ ጎንደር መውሊድ…..”? ኡለማና ዳኢ የሚባሉ ይህንን ሱናን አፍራሽ ተግባር ላይ በመቃወም ሚናቸውና ትኩረታቸው ምን ያህል ነው?
16) አገራችን ላይ ትክክለኛው የአቂዳ ትምህርት አላህ ካዘነላቸው ጥቂቶች ውጭ በኡለማዎች፣ በዳኢዎች፣ በቻናሎች፣ በሪድዬ ጣቢያዎች ነብያት የሰጡትን ያህል ትኩረት ተሰጥቶታልን?
17) ምን ያህሉ ለዲን ቦታ ሰጥቶ ሸሪኣን ይማራል?
18) ምን ያህሉ ልጅ የቤተሰቡን ሃቅ ያሟላል?
19) ፔንጤ ሙስሊሙን እያከፈረ ነው ተብሎ በሰፊው ይነገራል፡፡ ፔንጤዎቹ ደግሞ ሙስሊሞቹን የሚያከፍሩት በዱንያ እንደሆነ በማስረጃ ሁሉ ይነገራል፡፡ ታድያ በዚህ ጊዜ አላህ መልካም የዋለለት በጣም ብዙ ሙስሊም ሀብታም አለ ምን ያህል እነዚህን በዱንያ ምክንያት ወደ ክህደት እየሄዱ ያሉ ግለሰቦችን ለመታደግ መፅውቷል? አገራችን ላይ በቀን ስንት ሚሊዬን ብር ሙስሊሞች ለጫት ያወጣሉ? እውነት በዱንያ ጉዳይ የሚከፍሩትን ሙስሊሞች ለመታደግ እነዚህ ጫት ቃሚዎች ለጫት የሚያወጡት ገንዘብ ፔንጤ ለሚያከፍራቸው ለምን አልተለገሰም?
20) አገራችን ላይ ባሉ ዳኢዎችና ኡለማዎች የጫትን አስከፊነት በተመለከተ ተገቢው ማስጠንቀቂያና ማንቂያ ደውል ለሙስሊሙ ኡማ ተደርጓልን?
21) ምን ያህሉ ባል የሚስቱን ሀቅ ይጠብቃል?
22) ምን ያህሉ ሚስት የባሉን ሃቅ ይጠብቃል?
23) ምን ያህሉ ሰው ሰላት ይሰግዳል?
24) ከሰጋጆች ውስጥ ለወንድ ልጅ ግዴታ የሆነውን ጀመኣ ሰላት ምን ያህሉ ይሰግዳል?
25) ምን ያህሉ ሴት አላህ የረገመውን ቅንድብ መቀንደብና ማስቀንደብ፣ ዊግ መስራትና ማሰራት፣ ንቅሳት መንቀስና ማስነቀስ ይሰራል?
26) ምን ያህሉ ወንድ ይህንን አደንዛዥ ቅጠል ጫት ይቅማል?
27) ምን ያህሉ ወንድ ሲጋራ ያጨሳል?
28) ምን ያህሉ ሰው ከዝሙት እራሱን ጠብቆ ወደ ትዳር በጊዜ ይገባል?
29) ምን ያህሉ ሙስሊም ወጣት መጠጥ ይጠጣል?
30) ምን ያህሉ ነጋዴ ከወለድ ፀድቷል?
31) ምን ያህሉ ከቁርኣን ከሱና ተዘናግቶ ወደ ፊልም ድራማ ሙዚቃ ተጎትቷል “ኢስላማዊ” የሚሉትን ጭምር?
32) እና የመሳሰሉትን በጣም ብዙ ጥያቄዎች ለነፍሳችን እንመልስ
ያኔ እውነት እኛ አሁን ያለንበት ሁኔታ ፍልስጤም እንድትመለስልን መስፈርቱን አሟልተናል ወይ? የሚለውን ቁልጭ ብሎ ይታየናል፡፡
እግር ኳስ አለ ሲባል ከለሊቱ 6 እና ሰባት ሰኣት ላይ አይኑ ዲሽ ቤት የሚፈጠው አብዛኛውን ወጣት ፈጅር ሰላት ላይ መስጂዶቻችንን ላይ መምጣት ማቃቱ ብቻ አእምሮ ላለው ትልቅ ጥቆማ ነው፡፡
እባካችሁ የፍልስጤምንም ይሁን አለም ላይ ሌሎች ሙስሊሞች ላይ የሚደርሰውን በደል እና ጭቆና ለአላህ ትክክለኛ ባሪያ ሳንሆን እዚሁ ሶሺያል ሚድያ ላይ አካኪ ዘራፍ “ዋ አቅሷ” ምናምን ብሎ መፎከሩ አያዋጣም፡፡ ይሄ በፍፁም ትክክለኛ መፍትሄ አይሆንም፡፡ ሰይጣንን እና ሰራዊቶቹን ማሸነፍ ማለት በአርሰናልና ማንቸስተር መሃል ያለ የእግር ኳስ ፍልሚያ እንዳይመስለን፡፡
አላህ እንዲህ ይላል
[Q 47:7] يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِن تَنصُرُوا۟ ٱللَّهَ يَنصُرْكُمْ وَيُثَبِّتْ أَقْدَامَكُمْ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን (ህግጋቱን ብትፈፅሙ) ብትረዱ፤ ይረዳችኋል፡፡ ጫማዎቻችሁንም ያደላድላል፡፡
መቼም ሰው ያልዘራውን አያጭድም፡፡ ሰሃባዎች በአላህ የሚገባውን ትክክለኛ እምነት አምነው ተገኙ፣ የመልክተኛውን ሱና አጥብቀው ያዙ ለሁለት አገር ድል በቁ፡፡
ስለዚህ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አላህ እንዲረዳን ከፈለግን በትክክለኛው እምነት፣ ብቸኛ አንዷ የሀቅ ጎዳና፣ የነብዩ ሱና፣ የሰሃባዎች አረዳድ፣ እውነተኛ አንድነት ላይ እንሰባሰብ፡፡ ከዛም ቃል ኪዳኑን በመሙላት የሚታወቀው አላህ ሁለት አገር ድል በድል ያደርገናል፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በመልክተኛው፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሀቅን በተከተሉ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡ አሚን፡፡
ሌሎች ፅሁፎችን ለማንበብ የሚከተለውን የቴሌግራም ቻናል ይጫኑ
https://t.me/SadatTextPosts
“ሙስሊም አይዋሽም፡፡”፣ “ለቀልድ አንኳን ውሸት ሃራም ነው፡፡” ይላሉ ታማኙ የአላህ መልክተኛ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
ከስሜት አምላኪዎችና የጥመት አራማጆች ውስጥ አንዱ እንዲህ ሲሉ ይዋሹብኛል
“ሰበር ዜና ሳዳት ከማል ለቢዝነስ ሲል የከፈተው ሩቃ ቤት ገቢያ እንዳያጣ አፍሪካ ቲቪን ማግባባት ጀመረ”
ማስረጃ አምጣ እውነተኛ ከሆንክ ቢሉት ማስረጃ የለውም፡፡ ውዱ ነብይ ለቀልድ እንኳን ውሸት ሀራም ነው ብለው ሲያበቁ፣ ስሜት ተከታዬች ከቻሉ ዲኑን ለሚፈልጉት አላማ ይጠመዝዙታል፣ ካልቻሉ ውሸት ይነዛሉ፡፡ አስገራሚው የአላህ መልክተኛ “ሙስሊም አይዋሽም” ሲሉ እነሱ ደግሞ እራሳቸውን የኢስላም ጠበቃ አድርገው ማቅረባቸውና በተከታዬቻቸው ዘንድ የሙስሊም ጠበቃ ተደርገው መወሰዳቸው ነው፡፡
በጣም የሚያሳዝነው እና እጅግ ገርሞ የሚገርመው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “እውነተኞች ውሸታም፣ ውሸታሞች የሚታመኑበት ዘመን ይመጣል፡፡” ሲሉ ገልፀው ነበር፡፡ ዛሬ እንዲህ አይነት ውሸታሞች ለኡማው እራሳቸውን የሙስሊም ጠበቃ አድርገው መቅረባቸውና በምስኪኑ ዘንድ መታመናቸው ገርሞ የሚገርም ነው፡፡
ምስጋና ለአላህ ይገባው እኛ እነሱ የሚያጠፉትን ጥፋት ስናጋልጥ አንድም ቦታ ላይ አንዋሽባቸውም፡፡ በማስረጃ እውነቱን ብቻ እናስቀምጣለን፡፡ ዛሬ ሰው እየነቃ እና እየተለወጠ ከጥፋት ወጥቶ ወደ ሱና ሲመለስ ሲያዩት የመጨረሻ መሳሪያቸው የሆነውን ውሸት መርጨት ነው፡፡
ግን ውሸታም መጨረሻው ውርደት ነው፡፡ ልክ ሰውየው አሁንም እንደተዋረደው ሁሉ፡፡
አላህ እውነተኛ ባሪያዎቹ ያድርገን፡፡
ማንም ሰው ስሙን ቀይሮ፣ በስሙም፣ ወንዱ በሴት፣ ሴቷ በወንድ ስም ቢፅፉም አላህ በስማችን ነው የሚመዘግበው፡፡ አላህን እንፍራ፡፡
By Muhammedsirage MuhammedNur Gidey
بسم الله الرحمن الرحيم.
ነብዩ صلى الله عليه وسلم በህይወት ዘመናቸው በርካቶችን ለበርካታ ጉዳዮች ሾመዋል። ከነዚህ ተሿሚዎች ውስጥ ግን አንድም ሴት አይገኝበትም ። በግዜው አላህን የሚፈሩ በሸሪዓዊ እውቀታቸውም ከበርካታ ወንዶች ያላነሱ እነ ዐኢሻን የመሰሉ ጠንካራ ሴቶች የነበሩ ቢሆንም ታላቁ ነብይ ግን አንዳቸውንም ሙስሊሙን ይመሩት ዘንድ አልሾሙም ነበር ። ከነብዩም በሇላ በነብዩ አመላካችነት አቡበክር የሙስሊሞች መሪ ሆኖ የተሾመ ሲሆን በዚህ ወቅትም " ሴቶች ሆይ ኑና ምሩን " ያለ አንድም ሶሓባ አይታወቅም!!
ከአቡክር በሇላም ዑመር ፣ ዑስማን ፣ ዐልይ የአማኞች መሪ ሆነው ተመሪዎቻቸውን በፍትህ ያስተዳደሩ ሲሆን ላጠቃላይ መሪነትም ይሁን ላንዲት አነስተኛ አካባቢ መሪነት ወደ ሴቶች አሚርነት የጠቆመ የነብዩ ባልደረባ አልነበረም ። እነዛ ምርጥ ሴቶችም ስልጣን ይገባናል በማለት ዛሬ ዛሬ ወንድነታቸው የጠፋባቸው ወንዶች የሚጮሁትን "ሴቶች ይምሩ " ጩኸት አልጮሁም! !
ይህ ሁሉ የሚጠቁመው ሴት ልጅ በመሪነት ልትቀመጥ እንደማይገባት የሰለፎች የተግባር ስምምነት እንደነበረ ነው ። የሰለፎችን ስምምነቶች የሚነቅፉ ድርጊቶችና አቋሞች ደግሞ ጤና እንደሚጎላቸው አያጠራጥርም ። የሃሳቡ ወይም የአቋሙ ባለቤትም አቅሉና ዲኑ እንደሳሳ አያጠራጥርም!! ስልጣን ይገባናል የሚለው የሴቶች ጥያቄ የተነሳው ከምርጦቹ የሴት ምሳሌዎች ከነ ዐኢሻ፣ ሓፍሳ ፣ ዘይነብ ሳይሆን ከነ ሂላሪ ክሊንተንና መሰል ምናምንቴዎች ነውና ሴቶች ሆይ ምሳሌዎቻችሁን ልብ በሉ ።
ነብዩ صلى الله عليه وسلم እንከን በማይገኝለት ንግግራቸው ሴት ልጅን መሪ ያደረገ ህዝብ ድልን እንደማያገኝ ገልፀዋል ። እንዲህ ብለዋል ፣
لَنْ يُفْلِحَ قَوْمٌ وَلَّوْا أَمْرَهُمْ امْرَأَةً
* ቡኻሪ እና ሌሎችም ዘግበውታል።
ድል የሚገኘው የነብዩን ትእዛዝ በመከተል እንጂ የምእራቡን ከሃዲ ዱካ እየተከተሉ ሴቶችን ወደ ሹመት በመጣራት አይደለም ።
ሺአዎችን እንጠንቀቅ እናስጠንቅቅ፡፡
ጥያቄ፡- አያቶላህ ሁመይኒን አስመልኮ ኢስላማዊ ፍርዱ ምንድን ነው
መልስ፡- ኹመይኒ ኢማሞች ከነብያትና ከመልክተኞች (የአላህ ሰላትና ሰላም በነርሱ ላይ ይሁን) በላይ እንደሆኑ የፃፈበት ኪታብ አለው፡፡ በዚህ ንግግሩ መሰረት ሙስሊም አይደለም፡፡
ምንጭ አል-ሃዊ ሚን ፈትዋ አሽ-ሸይኽ አልባኒ ገፅ 349
ሺአዎች 12 ኢማሞች አሉ ብለው ያምናሉ፡፡ እነዚህ 12 ኢማሞች ምድርን ያስተናብራሉ ብለውም ይህን ኩፍር ያምናሉ፡፡ እነሱ ኢማም ብለው አምልኮን ቢፈፅሙላቸውም ግን ከነሱ ቅጥፈት የፀዱ ናቸው፡፡ ከነሱ ውስጥ የመልክተኛው የአጎት ልጅ የሆነውን አሊይ (ረድየላሁ አንሁ) ይገኝበታል፡፡ እውነታው ግን አሊይ ረድየላሁ አንሁ አይደለም ከነብያት ሊበልጥና ከ አቡበክር፣ ኡመርና ኡስማን እንኳን አይበልጥም፡፡ ይህን ስንል ደግሞ አሊይ እኛ ዘንድ የተወደደ ነው፡፡ ከደረጃው በላይ ከፍ ሊደረግ አይገባውም፣ ከደረጃውም ዝቅ ሊደረግ አይገባውም የሚለውን እያስረገጥን ነው፡፡ ሰሃባዎች ውስጥ አንድኛ አቡበክር፣ ሁለተኛ ኡመር፣ ሶስተኛ ኡስማን፣ አራተኛ አሊይ ናቸው፡፡ ሺአዎች በጣም መጥፎ ሰዎች ናቸው እንጠንቀቃቸው፡፡ የኢትዬጵያ ሙስሊሞች ሆይ! “ከሺአዎች ጋር ላኢላሃ ኢለላህ ሙሐመደ ረሱሉላህ አንድ ያደርገናል” የሚላችሁን አታላይ አትስሙት፡፡ የላኢላሃ ኢለላህ ሙሐመዱ ረሱሉላህን መልክት ከስር ከመሰረቱ የናዱ መጥፎ ፍጡሮች ናቸው፡፡
አላህ አገራችንን የመጀመሪያዎች ምርጥ ትውልዶች ወደ ሀገራችን ሁለት ጊዜ ተሰደውበት ወደ ነበረበት ጥርት ወዳለው ዲን ይመልስን፡፡ ከሁሉም የጥመት ቡድኖች ይጠብቅልን፡፡ የጥንት የጠዋቱን ብቸኛ የሐቅ መንገድ ለግሶን በሱ ላይ የምንሰባሰብ ያድርገን፡፡
አሚን፡፡ https://t.me/SadatTextPosts