Forwarded from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ፆምና ህመም
~~~~~~~~
ህመም ከፆም አንፃር ለ4 ይከፈላል።
① በህመሙ ምክንያት መፆም የማይችል ነው። ህመሙ ይድናል ተብሎ ተስፋ የማይጣልበት ቋሚ ህመም ነው። ይሄ ልክ መፆም እንደማይችል ትልክ ሽማግሌ ሲሆን በኢጅማዕ ማፍጠር ይችላል።
ፆም የሚከለክል ቋሚ ህመም ወይም እርጅና ላይ የደረሰ ሰው ለእያንዳንዱ ቀን አንድ ሚስኪን ማብላት እንዳለበት ከበርካታ ሶሐቦች ተገኝቷል። አቅም ከሌለው ግን ምንም የለበትም። አላህ እንዲህ ብሏል
(لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَاَ)
[البقرة 286]
"አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፡፡" [አልበቀራ: 286]
* የምግቡ አይነት እቤቱ ከሚመገበው መካከለኛ ደረጃ ያለው መሆን አለበት።
_
② መፆም ይችላል። ነገር ግን በመፆሙ ህመሙ የሚባባስበት ከሆነ ማፍጠር ግዴታው ነው። አላህ እንዲህ ብሏል: –
(وَلَا تُلْقُوا بِأَيْدِيكُمْ إِلَى التَّهْلُكَةَِ)
[البقرة 195]
"በእጆቻችሁም (ነፍሶቻችሁን) ወደ ጥፋት አትጣሉ፡፡" [አልበቀራ: 195]
★ ባይሆን ሲሻለው ቀዷእ ያወጣል (በምትኩ ይፆማል።)
③ መፆም ይችላል። ነገር ግን በህመሙ ምክንያት ፆም ይከብደዋል። መፆሙ የሚያስከትልበት ጉዳት ግን የለም። ይሄ ማፍጠር ለሱ በላጭ ነው። ኋላ ግን ቀዷ ያወጣል።
④ ህመሙ በፆም የሚባባስ አይነት ካልሆነ (ለምሳሌ የጥርስ፣ የአይን፣ … ህመም አይነት) ወይም ቀላል የህመም አይነት ከሆነ ሊያፈጥር አይፈቅድለትም። ለማፍጠር አሳማኝ ምክንያት መኖር አለበት።
።።።።
ማሳሰቢያ: –
* ህመምተኛ ሕመሙን ችሎ ቢፆም ፆሙ በኢጅማዕ ይቆጠርለታል።
والله أعلم

ፆምና ነፍሰ ጡር
~~~~~~~~~~
ነፍሰ ጡር ሴት ከፆም አንፃር ሁለት ሁኔታዎች ሊኖሯት ይችላሉ።
① ፆም በሷም ሆነ በፅንሷ ላይ ተፅእኖ የማያሳድርባት ንቁና ጠንካራ ከሆነች መፆም ግዴታዋ ነው።
② በእርግዝናው ክብደት ወይም በሰውነቷ መድከም የተነሳ ፆም የሚከብዳት ከሆነች ማፍጠር ግዴታዋ ነው። በተለይ ፅንሱ እንዳይጎዳ የሚያሰጋ ከሆነ።
ኋላ ቀዷ ማውጣት አለባት። ምስኪን የማብላት ግዴታ የለባትም። ይሄ የበርካታ ሰልፎች አቋም ነው።
* አጥቢ የሆነች እናትም ተመሳሳይ ብይን አላት።

ከ 400 በላይ ሙሐደራዎች እና ደርሶችን ከሚከተለው የቴሌግራም ቻናል ያውርዱ፡፡ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ፡፡
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
Forwarded from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ፆም እያለበት የሞተ ሰው
~~~~~~~~~~~~~~~
① በሕመም ምክንያት ያፈጠረ ሰው እስከሚሞት ድረስ ሕመሙ አብሮት ከዘለቀ ቤተሰቡ እንዲፆሙለት አይገደድም። ምስኪን ማብላትም አይጠበቅባቸውም። ምክንያቱም አላህ እንዲህ ብሏልና
(لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَاَ)
[البقرة 286]
"አላህ ነፍስን የችሎታዋን ያክል እንጂ አያስገድዳትም፡፡" [አልበቀራ: 286]
② ቀዷ ማውጣት ሲችል ተዘናግቶ ሳይፆም የሞተ ከሆነ ቤተሰብ ሊፆምለት ይገባል። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል
من مات وعليه صيام صام عنه وليه
"ፆም እያለበት የሞተ ሰው ቤተሰቡ/ ዘመዱ ይፆምለታል።" አቡ ዳውድ ዘግበውታል።
።
ማሳሰቢያ
።
ቤተሰብ ወይም ዘመድ ያልሆነም ሰው ለሟች መፆም ይችላል። ምክንያቱም ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በእዳ ነው የመሰሉት። [ቡኻሪ: 1953] [ሙስሊም: 1148]
እዳን ደግሞ ሌላም ሰው ለሟች መክፈል ይችላል።

የረመዳን ታላቁ ድል፡፡ አኢድ አል-ቀርኒ በግልፅ ከዚህ በፊት የነበረበትን የኢኽዋን ጥመት መንገድ አጋልጧል፡፡ ሳውዲን ለማፍረስ ደፋ ቀና የሚሉትን ሀገራትን እና እርጉሙን አል-ጀዚራ አጋልጧል፡፡ አላህ ሆይ! የአኢድ አል-ቀርኒን ተውበት ተቀበለው፡፡ ባጢል የቆየውን ያህል ቢቆይ እንዲህ ይወድማል፡፡ ሐቅ መጣ ባጢል ተወገድ፣ ባጢል ተወጋጅ ነውና፡፡ አልሐምዱሊላህ፡፡
https://twitter.com/Khalejiatv/status/1125687261197164544
https://t.me/SadatTextPosts

X (formerly Twitter)
روتانا خليجية (@Khalejiatv) on X
#فيديو
د. #عائض_القرني على الهواء مباشرة:
أعتذر باسم #الصحوة للمجتمع السعودي عن الأخطاء التي خالفت الكتاب والسنة وسماحة الإسلام وضيقت على الناس..
#عائض_القرني_في_ليوان_المديفر
#عيشوا_معنا_رمضان
#رمضان_كريم

አላሁ አክበር ከቢራ፡፡
አኢድ አል-ቀርኒ የነበረበት የኢኽዋኖች መንገድ የሚከተሉት ስህተቶች እንዳሉበት እንዲህ ሲል ይገልፃል
- ኢኽዋኖች ቁርኣን እና ሱናን ይፃረራሉ፣
- 40 ሀገራትን ዞሪያለሁ ወደ ተውሒድ አይጣሩም፣
- … ወደ ትክክለኛው አቂዳ አይጣሩም….፣
- የሚቀደመው አቂዳ (እምነት ነው) እኔ ብዙ ሀገር ዞሪያለሁ፡፡ ቀብሮች ይመለካሉ፣ ጠዋፍ ቀብር ላይ ይደረጋሉ፡፡ እነሱ ፓርላማ ለመግባት ነው ጉጉታቸው (ይህንን ሁሉ ባዕድ አምልኮ እያዩ)፣
- እነሱ ለስልጣን ሲሉ ስንት (ምስኪን) ሰዎች አለቁ ……
- …….
ከአኢድ አል-ቀርኒ ኢኽዋንን እና ጠበቃዎቻቸው ትልቅ ትምህርት ቢወስዱ ጥሩ ነው፡፡ ነብያት ሁሉ ለአቂዳ ነው ትኩረት የሰጡት፡፡ ፖለቲካ ነጃሳ ናት፡፡ ኢኽዋንን እና ጠበቃዎቻቸው እባካችሁ ወደ ቀጥተኛው መንገድ ተመለሱ፡፡ አኢድ አል-ቀርኒን አላህ ፅናት ይስጠው፡፡

በረመዳን ለማስተማር ተገቢውን ትኩረት እንስጥ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
አዎ ይህ ወር የቁርኣን ወር ነው። የሰለፎቹም ፈለግ ለቁርኣን ሰፊ ትኩረት መስጠት ነው። ግን ወንድሞች አንድ ሐቅ አለ። የኛ ህዝብ ሲበዛ የዲን ግንዛቤው የሳሳ ነው። በዚያ ላይ ረመዳን ብቻ የምናገኘው ብዙ ህዝብ መኖሩ የማይታበል ሐቅ ነው። ስለዚህ ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመን ሰዎችን ዐቂዳቸውን፣ አርካነል ኢስላም፣ አርካነል ኢማን ማስተማር፤ እንደ ሪባ ፣ አስከባሪ መጠጥ መጠጣት፣ ወለድ መብላት፣ ዝሙት፣ ያሉ ከባባድ ወንጀሎችን ማስጠንቀቅ ቀዳሚ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው።
ማስተማሩን ከረመዳን በኋላ እደርስበታለሁ የሚባል አይደለም። አብዛኛውን ሰው ከረመዳን በኋላ አናገኘውም። እና እባካችሁ ዱዓትና መሻይኽ ይህን ነገር ተገቢውን ትኩረት ስጡት ።

የብርህ መጠን ለዘካ መድረሱን እንዴት ነው የምታውቀው?
ዝቅተኛው ዘካ የሚወጅብበት የወረቀት ብር መጠን
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
የወረቀት የብር ኖት የዘካ መነሻ መጠን (ኒሷብ)
ከአመት አመት ሊለያይ ይችላል። ምክያቱም ሂሳቡ የሚሰራው ወቅታዊውን የወርቅና የብር (ሲልቨር) ዋጋ በማስላት ነውና።
።
አወጣጡም
።
እንደሚታወቀው
የወርቅ ኒሷብ=85 ግራም ሲሆን
የብር ኒሷብ ደግሞ=595 ግራም ነው።
።
ስለዚህ ወቅታዊውን የ85 ግራም ወርቅ ዋጋ እና የ595 ግራም የብር ዋጋ አስልተን ዝቅ ያለውን እንወስዳለን።
(ዝቅ ያለውን መነሻ ማድረግ የበርካታ ዑለማዎች አቋም ነው።)
።
ለምሳሌ ወቅታዊ የ1 ግራም ወርቅ ዋጋ 1,000 ብር ቢሆን
የወርቅ ኒሷብ ዋጋ 85×1,000=85,000 ብር ይሆናል።
ወቅታዊ የ 1 ግራም ብር ዋጋ 80 ብር ቢሆን
የብር ኒሷብ ዋጋ 595×80=47,600 ብር ይሆናል።
በዚህም መሰረት ወቅታዊው የወረቀት ብር ኖት የዘካ መነሻ ተመን ከሁለቱ ዝቅ ያለው ማለትም 47,600 ይሆናል ማለት ነው። እናም ይህን ያክል መጠን ብር ያለው ሰው ዘካ ወጅቦበታል ማለት ነው።
ማሳሰቢያ
① ዛሬ ዛሬ ካለው ሁኔታ ስንነሳ የብር ኒሷብ ከወርቅ ኒሷብ ያነሰ ነው። ስለሆነም በቀጥታ የ595 ግራምን ብር ወቅታዊ ዋጋ በማስላት ገንዘባችን ለዘካ ደርሷል ወይስ አልደረሰም የሚለውን በቀላሉ መለየት እንችላለን።
② ያቀረብኩት የወርቅና የብር ዋጋ ለምሳሌ ብቻ የቀረበ ነው። ወቅታዊውን ዋጋ አጣርቶ ማስላት ያስፈልጋል። መረጃ ያለው ካለም ከስር ቢያስቀምጠው መልካም ነው።

Forwarded from MuhammedSirage M.Noor (كوني زوجة صالحة تقية)
#ሰለፊያ___ምንድን__ነው?
አንድ ሰው ሰለፊ የሚባለው መቸ ነው ?
የሰለፎች ወይም የአህለል ሱና ዋና ዋና መለያ ነጥቦች ወይም ልዩ ምልክቶቻችው ምን ምን ናቸው በሚል አጠር ያለ ምክር
በሙሀመድ ሲራጅ { ሐፊዘሁሏህ }
Download ለማውረድ ሊኩን ይጫኑት👇
https://www.dropbox.com/s/xq55oj3ft6k4wgj/4
ተጨማሪ ለወዳጅ ዘመዶችዎ #ሸር__ማድረግ አይርሱ!!
⚘ t.me/Muhammedsirage
አንድ ሰው ሰለፊ የሚባለው መቸ ነው ?
የሰለፎች ወይም የአህለል ሱና ዋና ዋና መለያ ነጥቦች ወይም ልዩ ምልክቶቻችው ምን ምን ናቸው በሚል አጠር ያለ ምክር
በሙሀመድ ሲራጅ { ሐፊዘሁሏህ }
Download ለማውረድ ሊኩን ይጫኑት👇
https://www.dropbox.com/s/xq55oj3ft6k4wgj/4
ተጨማሪ ለወዳጅ ዘመዶችዎ #ሸር__ማድረግ አይርሱ!!
⚘ t.me/Muhammedsirage
Forwarded from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ዘካ የሚወጣው የአጠቃላይ ገንዘቡን 2•5% ነው። ለምሳሌ
ከ100 ሺህ=2ሺ አምስት መቶ
ከአንድ ሚሊየን =25ሺ
ከ100 ሺህ=2ሺ አምስት መቶ
ከአንድ ሚሊየን =25ሺ
Forwarded from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ተቀማጭ ገንዘብ ዘካ የሚወጅብበት አመት የሞላው ከሆነ ነው። እንጂ ለምሳሌ አንድ ሰው በውርስ አምስት መቶ ሺ ብር ቢያገኝና ገና 3 ወር ቢሆነው መጠኑ ለዘካ ስለደረሰ ብቻ የማውጣት ግዴታ አለበት አይባልም።
Forwarded from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የንግድ ሸቀጦች ዘካ
~~~~~~~~~~~~~
* መነሻ ተመን (ኒሷብ) ከወረቀት የብር ኖት ጋር ተመሳሳይ ነው። (ቀደም ብየ የለጠፍኩት መለስ ብለው ያገናዝቡ።)
* የሚወጣው መጠን 2•5% ነው።
* ከንግድ ስራው በቀጥታ ተያያዥ የሆነው ገንዘብ አብሮ ተደምሮ ይሰላል ።
* በራሳቸው የግብይቱ አካል ያልሆኑ እንደ መኪና፣ ማሽኖች፣ ቤቶች፣ መጋዘኖች፣ … ያሉ ቋሚ ንብረቶች የንግድ ስራውን ለማቀላጠፍ ቢያግዙም እንኳ ዘካ አይመለከታቸውም።
* ታሳቢ የሚደረገው የሸቀጦቹ ዋጋ የተገዙበት ሳይሆን ወቅታዊ ዋጋቸው ነው።

ዘካን ለቤተሰብ መስጠት ይቻላል?
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ለወላጅ፣ ለልጅ፣ ለሚስት፣ ለአያቶች እንዲሁም በሱ ሃላፊነት ስር ላሉ ዘመዶች ወጪያቸውን የመሸፈን ግዴታውን የራሱ ነውና ለነሱ ዘካ መስጠት አይችልም። [ፈታዋ ለጅነተ አድዳኢማ: 15/341–343]
* ሚስት ግን ለባሏ ዘካ የሚገባው ሰው ከሆነ መስጠት እንደምትችል ዑለማዎች ይገልፃሉ።

በወንበር ላይ መስገድ
=============
① ቆሞ መስገድ የሶላት ሩክን (ማእዘን) ነው። ስለሆነም #በግዴታ ሶላት ጊዜ መቆም የሚችል ሰው ተቀምጦ ቢሰግድ ሶላቱ ውድቅ ነው።
② በህመም ወይም በእርጅና ሳቢያ መቆም ያቃተው ሰው ወንበር ላይ ወይም መሬት ላይ ተቀምጦ ይሰግዳል።
* መቆም አቅቶት ተቀምጦ የሰገደ ሰው አጅሩ አይቀንስበትም።
③ ሩኩዕና ሱጁድ ማድረግ የሚችል ከሆነ ከወንበር ላይ ሆኖ መጠቆም ሳይሆን በትክክል መፈፀም አለበት። ለማይችለው ዑዝር ተሰጠው ማለት የሚችለውንም በዚያው ይሸፍናል ማለት አይደለም።
ለምሳሌ ሱጁድ ማድረግ የሚያቅተው ሰው መቆምና ሩኩዕ ማድረግ ከቻለ መቆምም ሩኩዕ ማድረግም ግዴታው ነው። ለሱጁዱ የተሰጠው ፈቃድ ለሩኩዑም ለመቆሙም አይሆንም። ባጭሩ የሚችለውን ማስገኘት አለበት። የኢብኑ ቁዳማን አልሙግኒ ይመልከቱ [ገፅ: 1/444]
ስለዚህ አንድ ሰው እንደ ህመሙ ሁኔታ
– መቆምም፣ ሩኩዕና ሱጁድም ካልቻለ ሙሉ ሶላቱን ወንበር ላይ ይጨርሳል፤
– መቆም ብቻ ከሆነ የሚያቅተው ለሱ ብቻ እየታገዘበት ሌሎቹን በትክክል ይፈፅማል፤
– መቆም ችሎ ያቃተው ሱጁድ ወይም ሱጁድና ረኩዕ ከሆነ ለሚያቅተው ክፍል ብቻ ወንበሩን ይታገዝበታል።
④ ረኩዕና ሱጁድ የሚያቅተው ሰው ሱጁዱን ከሩኩዑ ዝቅ ያደርጋል።
⑤ ወንበር የሚጠቀም ሰው ከኋላው ያሉ ሰዎችን እንዳያስቸግር መጠንቀቅ አለበት። ወንበሩን ወደ ኋላ አድርጎ በእግሩ ሶፍ ሊጠብቅ አይገባም። አቀማመጡን ከአቀማመጣቸው ጋር ማጣጣም አለበት።
⑥ ቆሞ መስገድ የሚችል ከሆነ ሌሎችን የማያስቸግርበት ቦታ ካገኘ ሶፉን በእግሩ ይጠብቃል። ሌሎችን የሚፈትን ከሆነ ግን ቀደም ብሎ በመቆም የወንበሩን የኋላ እግር ከሌሎች ሰጋጆች እግር ጋር ያስተካልላል።
ወሏሁ አዕለም።

መነሻ ተመን (ኒሷብ) ካልደረሰ ገንዘብ ዘካ ማውጣት አይፈቀድም።
[ሙግኒ፣ ኢብኑ ቁዳማ: 2/631]
[ሙግኒ፣ ኢብኑ ቁዳማ: 2/631]
Forwarded from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የህፃንና የአእምሮ በሽተኛ ገንዘብ መነሻ ተመን (ኒሷብ) ከደረሰ ዘካ ሊወጣለት ግድ ይላል። ሰዎቹን ሳይሆን ገንዘቡን የሚመለከት የደካሞች ሐቅ ስለሆነ ነው።
ስለዚህ ሃላፊ ወይም ተወካይ የሆኑ ሰዎች ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል።
ስለዚህ ሃላፊ ወይም ተወካይ የሆኑ ሰዎች ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል።
Forwarded from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ዘካን በራስም፣ በተወካይም መስጠት ይቻላል። ሆኖም ታማኝነታቸውን የማናውቃቸውን አካላት መወከል አይገባም። በአሁኑ ሰዓት የዘካን ገንዘብ ለቡድናዊ አላማ የሚያውሉ አካላትም በዝተዋል። ስለዚህ ጠንቀቅ ልንል ይገባል። ከቻልን በራሳችን ካልሆነ በምናምነው ሰው ብቻ ትክክለኛ ቦታ እንዲደርስ እናድርግ።
Forwarded from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ውዝፍ ዘካ ያለበት!
~~~~~~~~~~~
በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የብዙ አመታት ውዝፍ ዘካ ያለበት ሰው ወደ ኋላ ተመልሶ የማውጣት ግዴታ አለበት። እንጂ ያለፈው አልፏል ይቅር አይባልም።